Friday, October 21, 2011

በሰውና በእግዚአብሔር መካከል መካከለኛ ገድ ተክ ሃይ ም 2፥9 አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ከሚለው ርእስ የቀጠለ። Read PDF

መወገዝ ያለባቸውስ ይህን የጻፉ ያስተማሩ፤ ያሳተሙ የሚሸጡና የሚያሰራጩ ናቸው ሰው ጠፋ እንጂ።
«ዝክሩን ያልዘከረ ቃሉን ያልጠበቀ ከርስቱ ከመንግሥተ ሰማያት የተለየ ይሆናል። ክርስቲያን ጻድቅም ወይም ኃጥእ ቢሆን የሞቱ ሰዎች ነፍስ ሁሉ ከክቡር አባታችን ከተክለ ሃይማኖት ዘንድ ሳይደርሱ አይወስዷቸውምና» ይላል 210
የገድሉ ትልቁና ዋናው ክፋቱ ይህ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ሊመሰክሩትና ሊያስተምሩት የሚገባውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል የሚቀብርና የሚደብቅ በምትኩ የራሱን የክህደትና የጥፋት ትምህርት የሚዘራ እግዚአብሔር ወሰን በሌለው ፍቅሩ ከክፉው ዓለም ያድነን ዘንድ ካህን ንጉሥና ነቢይ አድርጎ በእርሱና በእኛ መካከል መካከለኛ አድርጎ ያቆመውን ጌታችንን በማስካድ ወደ ሞትና ወደ ጥፋት የሚወስድ ይህ ነው። (ባሕታዊ ሰይጣን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ)

ቅዱስ መጽሐፍ መካከለኛው አንድ ብቻ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ይናገራል። ግእዙም «ማዕከለ እግዚአብሔር ወሰብእ» ይላል። 1ጢሞ 25 ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር አብ ልጅነቱ ፍጹም አምላክ ነው፤ በሰው ልጅነቱ ፍጹም ሰው ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል መካከለኛ ሊሆን የሚችል አንድ እርሱ ብቻ ነው።
በአስራ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሱ መናፍቃን ግን ይህን እውነት ወደ ጎን በመተው ተክለ ሃይማኖትን መካከለኛ ነው ብለው ሕዝባችንን ሲያሳስቱ ኖሩ። ጌታ «ሥጋየን ያልበላ ደሜንም ያልጠጣ የዘላለም ሕይወት የለውም» ያለውን ቃል ለመሸፈን «የተክለ ሃይማኖትን ዝክሩን ያልዘከረ ቃሉን ያልጠበቀ ከርስቱ ከመንግሥተ ሰማያት የተለየ ይሆናል» ሲሉ በቋንቋ ሊገለጥ የማይችል ከባድ ክህደት ሲያስተምሩ ኖረዋል። አሁን ግን እንዲህ ዓይነቱ ክህደት ሊገለጥና ሊዋረድ ቦታውንም ለከበረው የጌታ ወንጌል ሊለቅ ጊዜው ደርሷል።
የተክለ ሃይማኖትን ዝክር ያልዘከረ፣ ደብረ ሊባኖስ ያልተቀበረ ወደ መንግሥተ ሰማያት የማይገባ ከሆነ ደብረ ሊባኖስ መቀበር እና ዝክሩን በየወሩ መዝከር የግድ ሊሆን ነው። በዚህ ትምህርት መሰረትም እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ የሰጠበት ዘላለማዊ ፍቅሩ የተክለ ሃይማኖትን ዝክር ባለመዝከር ምክንያት ሊደናቀፍ ነው። ሰዎችም መንግሥተ ሰማያትን ሊያጡ ነው ማለት ነው። እንዴት አይነት ዓይን ያወጣ ክህደት ነው? ዛሬ በየወሩ ንፍሮ በመቀቀልና ዳቦ በመጋገር የገድለ ተክለ ሃይማኖትን ባዕድ ትምህርት ለመፈጸም የሚጋደለውን ወገናችንን ስናይ እጅግ ያሳዝነናል። ደብረ ሊባኖስ እቀበራለሁ በሚል ከንቱ ተስፋ መቃብር አሠርተው ቀናቸውን የሚጠብቁ ብዙዎች ናቸው። ንስሐን ግን ንክች አያደርጓትም። ይህም የስሕተት ትምህርቱ ያመጣው ጠባሳ ነው።
«ጻድቅ ኃጥእም ቢሆን ከተክለ ሃይማኖት ዘንድ ሳያደርሱ አይወስዷቸውም » ይላል። ለምን ከተክለ ሃይማኖት ዘንድ መሄድ አስፈለገ? ዝክሩን ዘክሮ ይሁን አይሁን ወይም ደብረ ሊባኖስ ያልተቀበረ መሆኑን ለማረጋገጥ ሳይሆን አይቀርም። ጌታ ግን «ወአልቦ ዘይመጽእ ኀበ አብ ዘእንበለ እንተ ኀቤየ» ትርጉም፦ በኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ብሏል። ጌታችን በዮሐ 101 ላይ በበሩ የማይገባ ሌባ ወንበዴም ነው ይላል። መናፍቃን ግን ተክለ ሃይማኖትን መካከለኛ አድርገው ስለሰበኩ ብዙ ሌባና ወንበዴ በቤተ ክርስቲያናችን ተትረፍርፏል።
ከጥንት ጀምሮ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ አባቶች ይህን የሀገርና የትውልድ ዕዳ ለማስወገድ ብዙ ሲጥሩ ሲያስተምሩና ሲጽፉ ኖረዋል። ነገር ግን መናፍቃኑ የፖለቲካ የበላይነት ስለነበራቸው ከነገሥታት ጋር በመተባበር ሲያሳድዷቸው ኖረዋል። እነዚህ እውነተኛ ኦርቶዶክሳውያን እየተራቡና እየተጠሙ እየተሰደዱ በዱርና በዋሻ እየተንከራተቱም ቢሆን ለኢትዮጵያ ትውልድ ሐቅን በጽሑፋቸው አስቀምጠው አልፈዋል።
ዛሬም በበሩ መግባት የማይፈልገው ማህበረ ቅዱሳን እነዚህን አባቶች በአካል ቢያገኛቸው እንደኛ ያሳድዳቸው ነበር። ነገር ግን አባቶቻችን ሰማዕትነታቸውን በጽናት ፈጽመው የቀረውን ሩጫ ለኛ ትተውልን አርፈዋል። ሥራውን አፍርሰውበት ያለፉትን አባቶች ዛሬ ሰይጣን የሚበቀላቸው መስሎት በሲኖዶሱ ሊያስወግዛቸው አፉን ከፍቷል።
ማህበረ ቅዱሳን በነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌና በነመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ በእነ አለቃ ኅሩይ ስራዎች ሲጠቀም የኖረ ድርጅት ነው [አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የተረጎሙት ትንቢተ ሕዝቅኤል በማህበረ ቅዱሳን ሱቅ ይሸጣል] አሁን እነዚህን ሊቃውንት ለመክሰስ የተነሳበት ምክንያት ምንድን ነው? የሚል ጥያቄ በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ሊነሳ ይችላል።
1ኛ) ገድልና ድርሳን እየተባለ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ብዙዎቹን መካከለኛ አድርጎ የተቀመጠውን ባዕድ ትምህርት፤ አጥብቀው ይቃወሙ ስለነበረና ዛሬ ያለው ትውልድ የነርሱን ትምህርት ከተደበቀበት እየቆፈረ አውጥቶ በማስተዋል ከሲኦል ባርነት ነጻ እየሆነ ስለመጣ ነው።
2ኛ) ማህበሩ የተመሠረተበት፤ ብዙ ገንዘብና ክብር የሚያገኝበት ባዕድ ትምህርት እየተናደ ስለመጣ ወደ ፊት ሊደርስበት ያለውን ዓላማ ስለሚያደናቅፍበት ነው። እነዚህ ምክንያቶች ናቸው ሊቃውንቱን ለማውገዝ ያነሳሱት። ማህበሩ በአሁኑ ሰዓት የሚንቀሳቀሱ ተሃድሶዎች ታሪክን ለማጥፋት የመጡ ናቸው እያለ ይከሳል የሞቱት ሰዎች ዛሬ የሚከሰሱት ምን ያጠፋሉ ተብሎ ይሆን? ምክንያቱም እነዚህ አባቶች ማህበረ ቅዱሳን ከመወለዱ ከመቶ አመት በፊት የነበሩ ናቸው። ምሥጢሩ ግን ጥንታዊውን የስሕተት ትምህርት በጽሑፋቸው አውገዘውት ስላለፉ ነው።
እንግዲህ መወገዝ ያለበት የኢየሱስ ክርስቶስን መካከለኛነት ሽሮ የተክለ ሃይማኖትን መካከለኛነት የተካው ከሃዲ ነው። ገድለ ተክለ ሃይማኖት በሲኖዶሱ መወገዝ አለበት። ሌሎችም ብዙ የሚወገዙ ክሕደቶች አሉ በእውነት አጥርቶ የሚያይ ሰው ካለ። ነገሩ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጨዋታ ከሆነ ግን ፍርዱን ለእግዚአብሔር እንተወዋለን፤ እውነት መገለጡ! ሐሰት መዋረዱ! ወንጌል መሰበኩ! ሕዝባችንም ነጻ መውጣቱ ግን፣ የማይቀር እውነት ነው።
ክብር! ድል! ጌትነትና ገዥነት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን አሜን!
ተስፋ ነኝ

14 comments:

 1. Good job Tesfa, Bertalen bro.

  ReplyDelete
 2. MY BROTHER TESFA GOD BLESS YOU . GRAT JOB WONDERFUL . YOU GOT IT . MK LOST IT

  ReplyDelete
 3. ጥያቄ ለተስፋ፦ ስለቅዱሷን ገድል የምታስተምረው ገድላቸውን ጽፋ የምታነበው የምታስፋፋው እራሷ ቤተክርስቲያኗ እራሳቸው መጽሀፍትን ጠንቅቀው የሚያውቁት ሊቃውንት አባቶች እያሉ ለምን የሁሉ ነገር ጀማሪ ማህበረ ቅዱሳን ይመስል ጩሀታቸሁ ሁሉ ወደ ማህበሩ ሆነ? ለምን ከአንዳንድ የገድላት አገላለጽ ከሆነ ችግሩ ድርሰቶቹ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲታረሙ ብቻ የጨዋ ጥያቄ አትጠይቁም? እኛ ምእመናን እንደሆነ እድሜ ለእውነተኛ በትርምስ በማያምኑ የቤተክርስቲያኗ መምህራንና ሊቃውንት አባቶች ይሁንና የምናምነውን የምናመልከውን እናውቃለን በድንግል ማርያም በመላእክት በቅዱሳን አማላጅነትም እንጠቀማለን ይሄንን እምነትም ይዛ ቤተክርስቲያኗ የቀረውን በጣም አጭር ዘመን ትሻገራለች። ነገር ግን ተሀድሶዎች በኛና በመናፍቃን መካከል ያለውን ታላቅ ገደል የሌለ አድርጋችሁ የምታደርጉት እሽቅድምድም የትንቢት መፈጸሚያ እያደረጋችሁ ነውና በምታደርጉት የድንበር ማፍረስ ህዝቡን ወደመናፍቃን አዳራሽ ጌታን ፍጡር አማላጅ ወደሚል የተወገዘ የጥፋት መንገድ እየመራችሁት ነውና በቤተክርስቲያኗ የነገረ መለኮት ትምህርት የምታምኑ ከሆነ የአንዳንድ ደራሲዎችን ጽሁፎች ይስተካከሉ ወደማለት ጥያቄያችሁን ብታሻሽሉ ይሻል ይመስለኛል እንጂ ዝምብሎ የምዬን ወደአብዬ ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ብትሉ ምታተርፉት የ60 ዎቹና የ70ዎቹ በፖለቲካ የአንድ ዘመን ትውልድን ደም እንዳቃቡት እናንተም በሃይማኖት ስም የኛን ትውልድ ደም ከማቃባት የተሻለ ነገር አትሰሩም። ማህበሩ ቤተክርስቲያኗ በገሀድ ከምታምነው ውጭ የሚያምነው የሚታገልለት ድብቅ ትምህርት እንደሌለው ከናንተ በላይ የሚያውቅ የለም። ነገር ግን በሊቃውንት አባቶች በሲኖዶስ ህግ መሰረት /በአመጽ ሳይሆን/ ቅዱስ ሲኖዶ የአንዳንድ የአስተዳደር እና የቀኖና ለውጥ ቢያደርግ ማህበሩም ላባቶች ውሳኔ እንደሁሉም የቤተክርስቲያን ልጆች ልጅ ነውና ለውሳኔው ተገዢ ይሆናልና ማህበሩን ለቀቅ እግዚአብሔር የመሰረተውን ማህበር ወጀብ አውሎ አያፈርሰውም። ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን ማፍረስ ህዝቡን ባለቀ ዘመን ወደክህደት ከመግፋት ብትቆጠቡስ?

  ReplyDelete
 4. ayi aba selama bikefitu telba.be talaku abat sim yeminegid blog. aysakalachihum.

  ReplyDelete
 5. Yes Tesfa you are tesfa of Seol!

  ReplyDelete
 6. Thanks to the person who posted this
  ጥያቄ ለተስፋ፦ ስለቅዱሷን ገድል የምታስተምረው ገድላቸውን ጽፋ የምታነበው የምታስፋፋው እራሷ ቤተክርስቲያኗ እራሳቸው መጽሀፍትን ጠንቅቀው የሚያውቁት ሊቃውንት አባቶች እያሉ ለምን የሁሉ ነገር ጀማሪ ማህበረ ቅዱሳን ይመስል ጩሀታቸሁ ሁሉ ወደ ማህበሩ ሆነ? ለምን ከአንዳንድ የገድላት አገላለጽ ከሆነ ችግሩ ድርሰቶቹ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲታረሙ ብቻ የጨዋ ጥያቄ አትጠይቁም? እኛ ምእመናን እንደሆነ እድሜ ለእውነተኛ በትርምስ በማያምኑ የቤተክርስቲያኗ መምህራንና ሊቃውንት አባቶች ይሁንና የምናምነውን የምናመልከውን እናውቃለን በድንግል ማርያም በመላእክት በቅዱሳን አማላጅነትም እንጠቀማለን ይሄንን እምነትም ይዛ ቤተክርስቲያኗ የቀረውን በጣም አጭር ዘመን ትሻገራለች። ነገር ግን ተሀድሶዎች በኛና በመናፍቃን መካከል ያለውን ታላቅ ገደል የሌለ አድርጋችሁ የምታደርጉት እሽቅድምድም የትንቢት መፈጸሚያ እያደረጋችሁ ነውና በምታደርጉት የድንበር ማፍረስ ህዝቡን ወደመናፍቃን አዳራሽ ጌታን ፍጡር አማላጅ ወደሚል የተወገዘ የጥፋት መንገድ እየመራችሁት ነውና በቤተክርስቲያኗ የነገረ መለኮት ትምህርት የምታምኑ ከሆነ የአንዳንድ ደራሲዎችን ጽሁፎች ይስተካከሉ ወደማለት ጥያቄያችሁን ብታሻሽሉ ይሻል ይመስለኛል እንጂ ዝምብሎ የምዬን ወደአብዬ ማህበረ ቅዱሳን ማህበረ ቅዱሳን ብትሉ ምታተርፉት የ60 ዎቹና የ70ዎቹ በፖለቲካ የአንድ ዘመን ትውልድን ደም እንዳቃቡት እናንተም በሃይማኖት ስም የኛን ትውልድ ደም ከማቃባት የተሻለ ነገር አትሰሩም። ማህበሩ ቤተክርስቲያኗ በገሀድ ከምታምነው ውጭ የሚያምነው የሚታገልለት ድብቅ ትምህርት እንደሌለው ከናንተ በላይ የሚያውቅ የለም። ነገር ግን በሊቃውንት አባቶች በሲኖዶስ ህግ መሰረት /በአመጽ ሳይሆን/ ቅዱስ ሲኖዶ የአንዳንድ የአስተዳደር እና የቀኖና ለውጥ ቢያደርግ ማህበሩም ላባቶች ውሳኔ እንደሁሉም የቤተክርስቲያን ልጆች ልጅ ነውና ለውሳኔው ተገዢ ይሆናልና ማህበሩን ለቀቅ እግዚአብሔር የመሰረተውን ማህበር ወጀብ አውሎ አያፈርሰውም። ስለዚህ ቤተክርስቲያኗን ማፍረስ ህዝቡን ባለቀ ዘመን ወደክህደት ከመግፋት ብትቆጠቡስ?

  ReplyDelete
 7. good job aba selama

  ReplyDelete
 8. ለምን ይመስልሀል ማቅን የሚናገሩት? ማህበሩ ጉዳቸዉን ስለሚገልጥ ብቻ ሳይሆን ማቅ ሲሉ የኮድ (ሚስጢራዊ) ቃል ነው:: ማቅ የሚለውን ቤ/ያን እያልክ አንብበው ከዛ ይገባሀል የመናፍቆቹ አላማ:: አሁን አላማቸው ቤታችንን መውረስ ስለሆነ የሚሰድቡትን ማሳነሳቸው ነው ወንድሜ::

  ReplyDelete
 9. In the past we argued on the bible, txs to God everyone knows the bible and has answers, Now the war is on Gedlat and other church books.
  One thing is amazing, there are many pagan, sedom people in the west ( which fund our people who sold their dignity), if it is true religion, please focus on these kinds of people.
  What is happening is a tragic involvement of politics(including western)in religion. Because someone who don't even know a lot about bible tries to give respect, ask and understand before commenting let alone criticizing.

  ReplyDelete
 10. በዚህ ምድር ላይ ካሉት ሃይማኖቶች ሁሉ እራሱን ብቸኛ የእውነት ባለቤት አድርጎ የማይቆጥርና ሌላው ሁሉ የተጃጃለ አድርጎ የማይመለከት ያለ ይመስለን ይሆን? እራሱ ብቻ ከእግዚአብሔር ጋር የተወዳጀና እግዚአብሔር የወደደው ሃይማኖት የርሱ እንደሆነ የማያምን የእምነት ተቋም በዚህ ምድር የለም። ለምን ይመስላችኋል? እራሱ የጻፈውን፤ እራሱ የተረጎመውን፤ እራሱ ያስተማረውንና የተናገረውን በራሱ ጆሮ ሰምቶ በራሱ ጆሮ ትክክል ነህ የሚል ምላሽ ሰጥቶ ራሱን ስለሚያሳምን ብቻ ነው። ግራና ቀኝ እንዳያይ፤ እንዳያነብ፤ እንዳይጠይቅ፤ የሚያምነውን እንዳይመረምር፤ እንዳይለይ በሃይማኖቱ ሰብከት መሰል ማደንዘዣዊ ማስፈራሪያ ተጠፍንጎ ስለተያዘ በምንም መልኩ ከእሱ ውጪ ሌላ ነገር ለመስማት አይፈልግም። ኦርቶዶክስ የብዙ ዘመን መምህር፤ መካሪ አስተማሪና መሪ ሆና ህዝቡ በክርስትና እንዲቆይ ያደረገች ትልቅ ተቋም መሆኗ ባይካድም ብዙ ደካማ ሰዎችና ደካማ ትምህርቶችን ሊተክሉባት እንደሚችሉ በመገመት እንደቀደመው አስተምህሮ ቃሉን መሰረት አድርጋ አገልግሎቷን በጥራት እንዳትቀጥል ጎጋው የጅምላው አማኝ መጠየቅ፤ መመርመር አይገባም እያለ ተሸገርን። ሃይማኖቱን የተወለድኩበትና ያደኩበት ስለሆነ በፍጹም ልተወው አልፈልግም። ያለውን ሁሉ ይዤ እንዳልቀጥል ከቀደመው መሰረቷ ጋር የሚጋጭ፤ እግዚአብሔርን የሚጋርድ ጠላት በውስጧ አስቀምጧል። እንደእግዚአብሔር ቃል ቁጭ ብለን ጠያቂና መላሽ፤ አስተማሪና አራሚ አስቀምጠን እንዳንወያይ «እኔ ብቻ ትክክል፤ አንተ ብቻ ስህተተኛ» እያለ በጩኸት የሚፈርድየሚል በዛ። እስኪ እናንብብ፤ እንመርምር፤ እንጠይቅ፤ እንመልስ፤ እልከኝነቱን እንተው። ቀን ይረዝም እንደሆን እንጂ እውነት እውነቱ ይገለጣል፤ ውሸት ውሸቱ ይነቀሳል። ይሄንን የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው።

  ReplyDelete
 11. መቸም ቢሆን ማቅ ይህንን ቤተክርስቲያንን አንገት የሚያስደፋ የሰው አምላኪነት ባህልና አስተምህሮውን በማናቸውም መልኩ ለመተውና ሌሎችን የዋሀንን ከማሳሳት ለመመለስ መከጀሉ ብቻ እግዚአብሄር ይመስገን የሚያሰኝ ነው። በማቅ የደብተራ ድግምት መሳይ ትምህርት ግራ ለተጋባው ህዝብ ማቅ ታላቅ ይቅርታ መጠየቅ፡ ንስሃም መግባት ይገባዋል። አለዚያ ግን ጌታ ለአምልኮቱ ቀናተኛ ነውና ፍርዱን ያፋጥንበታል

  ReplyDelete
 12. እኔ የሚገርመኝ ነገር የገድላትና የተአምራቶችን አብዛኛው ይዘት አላስፈላጊና ቤተ ክርስቲያናችን ከተቋቋመችለት ዋና ዓላማ ጋር የሚጣረስ፣ ክብር ይግባውና የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሠረታዊ አስተምህሮ የሚጥስ ነው፡፡ ይህም ባይሆን ከስሟ ማለትም ቤተ ክርስቲያን ማለት የክርስቲያኖች ቤት ማለት ሲሆን ትርጉሙም በክርስቶስ ያመኑ ሰዎች ለጸሎት ወይም ለትምህርተ ወንጌል የሚሰባሰቡበት ማለት ነው፡፡ ከስሙ እንኳን ብንነሳ መስበክ ያለባት ክርስቶስ ያስተማረውን ወንጌልን እንጂ ገድላትን ወይም ተአምራትን አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንንም ጉዳይ አብዛኞቹ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያምኑበታል ነገር ግን በግልጽ ለመናገር ተሃድሶ ወይም መናፍቅ መባልን ስለሚፈሩ ብቻ ተሸፋፍኖና ተድበስብሶ እንዲቀር ይጥራሉ፡፡ ሌላው አከራካሪ ጉዳይ የምስኪኖቹና የመንፈሰ ጠንካራዎቹ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ለሥጋቸው ባደሩ የንጉስ አፈ ቀላጤዎች ከየገዳሞቻቸው እየተለቀሙ የተጨፈጨፉት መነኮሳት ጉዳይ ነው፡፡ እውን ደቂቀ እስጢፋኖስ መናፍቃን ነበሩን? ለሚለው ጥያቄ በግልጽ አይናገሩ እንጂ አብዘኞቹ የሚሰጡት መልስ አልነበሩም ነው፡፡ እውነትም አልነበሩም እንደ ምሳሌ ብናይ አንዱ የተከሰሱበት ክስ ፀረ ማርያሞች ናቸው የሚል ነበር እውነታውን ስናይ ግን በትግራይ ውስጥ እነሱ የመሰረቷቸው የእመቤታችን ቤተ ክርስቲያኖች ብዙ ናቸው ዲቦ ማርያም፣ አሲራ መቲራ ማርያም ጉንዳጉንዲ ማርያምን እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ ፀረ ማርያም ቢሆኑ ኖሮ እንዴት የእመቤታችንን ቤተክርስቲያን ሊሰሩ ይችላሉ? ስለዚህ የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ውንጀላ ተራ ውንጀላ ነበር ማለት ነው፡፡
  ለማንኛውም እግዚአብሔር መልካሞቹን ቀኖች ያመጣልን፡፡

  ReplyDelete
 13. besmeab wowld wemenfeskudus.lije betekristan satawkat wede nekefa atrut.eswa hawariawit betekrstian nat. kehonelh tiyake yefeterbih kale abatochen bethtina teyik. alyam metsha manbeb.silkew kehone minew mussie begziabherna be israelawyabn mekakel komo yelem endie?

  ReplyDelete