Monday, October 3, 2011

ለደመራ በዓል የተቃጣው የማኅበረ ቅዱሳን የሽብር ጥቃት ከሸፈ!

ተፈጥሮው ሃይማኖት ያልሆነውና የሃይማኖትን ካባ ደርቦ ፖለቲካዊ ሕልሙን እውን ለማድረግ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የሚንቀሳቀሰውና ብዙዎች በአሸባሪ ግብሩ “አልቃኢዳ” እያሉ የሚጠሩት ማኅበረ ቅዱሳን በደመራ በዓል ላይ ለመፈጸም ያሰበው የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተገለጸ፡፡ የሽብር ጥቃቱን ያከሸፉት በቃን ከእንግዲህ ወዲህ አንሰማህም ያሉት የአመዛዛኝ ኅሊና ባቤት የሆኑ በርካታ የማኅበሩ አባላትና ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ማኅበሩ ሃይማኖታዊ ካባውን አውልቆ ጥሎ በፖለቲካዊ የውስጥ ልብሱ መታየት ከጀመረ ወዲህ በሁሉም አቅጣጫ ተቃውሞ የተነሣበት መሆኑንና ብዙ ሊዘልቅ እንማይችል መረዳቱን ከሚያደርጋቸው ቅጣንባራቸው የጠፋ እንቅስቃሴዎቹ መረዳት የሚቻል ሲሆን፣ እርሱም ጥይት መጨረሱንና ባዶ ጠመንጃ ብቻ መሸከሙን ተረድቶ የስልት ለውጥ ማድረጉን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በተለይም መስከረም 12/2002 ዓ.ም. በመንግሥት በኩል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ተከትሎ ጊዜው እየመሸበት መሆኑን የተረዳው  የማኅበሩ አመራር በወቅቱ ስብሰባ አድርጎ፣ “መንግሥት ማኅበሩን ሊዘጋው ይችላል፤ አመራሮቻችንም ሊታሰሩ ይችላሉ፤ ስለዚህ ዐላማችንን ለማሳካት ቁልፍ አባሎቻችንን በየሰንበት ትምህርት ቤቱ በትነን ከታች ወደላይ እንደገና መምጣት አለብን” የሚል አዲስ ስልት ነድፈው መንቀሳቀስ መጀመራቸውን እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡


በዚሁ አዲስ ስልት መሠረት የማኅበረ ቅዱሳንን ተልእኮ እንዲያስፈጽሙ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች መምሪያ ስር የ138ቱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራር የሚል ኮሚቴ እንዲዋቀር ያደርጋሉ፡፡ ኪሚቴው በሀገረ ስብከቱ የተቋቋመ ነው ይባል እንጂ ከጀርባ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ከፍሬው ይታወቃል ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ማሳያዎችን ይጠቅሳሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በዚሁ የአንድነት አመራር ቆስቋሽነት የዮሴፍ ቤተክርስቲያን ሰንበት ተማሪዎች ናቸው የተባሉ ቅጥረኞች የመጋቤ ሐዲስ በጋሻውን የዮሴፍ ቤተክርስቲያን የዕለተ ሠሉስ የሠርክ መርሐግብርን ለማደናቀፍ መንቀሳቀሳቸውንና ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመመሣጠርም ግርግር ለመፍጠር ከጅለው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡

በአንዳንድ አድባራትም ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ የሚል ስመጽርፈት የለጠፈባቸውን ሰዎች እንዲመነጥሩ እነዚህን የአንድነት አመራር ተብዬዎችን ማሰማራቱንና በአንዳንድ ቦታዎችም ስኬታማ ስደት ማሳወጃቸውን መረዳት ተችሏል፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ሳንባ የሚተነፍሰውና “ግልገል ማኅበረ ቅዱሳን” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይኸው ስብስብ በመዝሙር ማጥናት ስም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እየተገኘ የደመራውን በዓል መያዣና ማስፈራሪያ በማድረግ፣ የሚለው እንዲፈጸምለት ካልሆነ ግን በበዓሉ ላይ ብጥብጥ ሊነሣ እንደሚችል ወሬ ሲያናፍስና ሲያስጠነቅቅ መሰንበቱ ይታወቃል፡፡ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው እንደሚባለው፣ ሕዝቡን በወሬ ለመፍታት ሆን ብሎ ከአሁን በፊት ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አንዳንድ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችንና ምእመናንን በስም በመጥቀስ በደመራ በዓል ላይ እንዳይገኙ ካስጠነቀቁ በኋላ የተባሉት ሰዎች ከተገኙ ግን መስቀል አደባባዩን - በእነርሱ አነጋገር “እንቀውጠዋለን” ማለታቸው ግን ብዙዎችን አስገርሟል፤ አስደንቋልም፡፡ ድረገጽ ላይ የሰቀልንለትን ጽሑፍ ሁሉ አሜን ብሎ ይቀበለናል ያሉት ወገን ግን በመቃወምና በዝምታ ከጎናቸው ባለመቆም የሽብር ጥቃታቸውን ማክሸፉ ለቤተክርስቲያናችን ትልቅ ተስፋን የሚፈነጥቅ ክሥተት ሆኖ አልፏል፡፡ይህም አልቃኢዳው ማኅበረ ቅዱሳን እንኳን ሌሎችን አሳምኖ ከጎኑ እንዲቆሙ ሊያደርግ ይቅርና አባላቱም በከፍተኛ ምሬት የተቃወሙት መሆኑን ምንጮቻችን ይጠቅሳሉ፡፡ በዓሉ ብሔራዊ በዓል እንደመሆኑ መገኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሊገኝ የሚችልበት በዓል መሆኑ እየታወቀ፣ የቤተክርስቲያናችንን ሰዎች እንዳይገኙ ማለት ማኅበሩንና ግልገሉን ትልቅ ትዝብት ላይ ጥሎ ያለፈ አሳፋሪ ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ወሬ ያለቀበት የሚመስለው የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ ደጀሰላምም የተለያዩ የፈጠራ ወሬዎችን በማምረትና የወሬ ገበያውን በሐሰት ወሬ እያጥለቀለቀ የመረጃ ግሽበቱ በሁለት እጥፍ እንዲጨምር በማድረግና ከመጠን በላይ በማራገብ ለግልገል ማኅበረ ቅዱሳን ሰፊ የፕሮፓጋንዳ ሽፋን መስጠቱ ተዘግቧል፡፡ ደጀሰላም (ቤተዘኬ) ከሕያዋን እየተበዘበዘ ለሙታን በሚደረግ ተዝካር ካህናትና ዲያቆናት ነፍስ እናስምራለን በሚል ሰበብ እየተንበሸበሹ፣ እየበሉና እየጠጡ፣ እየተሳከሩም የባጥ የቋጡን የሚያወሩበት፣ አንዱን ለመጣል ሤራ የሚሸርቡበት ቤተ ወሬ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ማኅበረ ቅዱሳንም ድረገጹን በዚህ ስም የጠራው ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም መሆኑን ከስራው ፍሬ ማወቅ እንደሚቻል ግልጽ ነው፡፡

ወ/ሮ እጅጋየሁ “ሐውልቱ እስከመቼ” የሚል መጽሐፍ እንዳሳተሙና በደመራ በዓል ላይ ለማሰራጨት እንደተዘጋጁ ያስወራው ደጀሰላም የነዛው ወሬ ሁሉ እንዳልያዘለት የጠቆሙት ምንጮች በበዓሉ ላይ የተባለው መጽሐፍ ፈጽሞ እንዳልታየ ተናግረው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ወሬ ያስወራው ለሽብር ጥቃቱ ትልቅ ግብአት ይሆነኛል ብሎ በማሰብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ የደመራው በዓል እርሱ እንደተመኘው ሳይሆን እጅግ በደመቀ ሁኔታ ያለምንም ችግር ተከብሯል፡፡ እንዳይገኙ የተባሉት አባ ሠረቀ፣ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው፣ መምህር ሣህሉ እና ወ/ሮ እጅጋየሁ በበዓሉ ላይ ለክብር እንግዶች በተዘጋጀው ድንኳን አካባቢ እንደተገኙና ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ የተለያዩ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ያዘጋጁትን ትርኢት በተለመደው አኳኋን እያሳዩ በፊታቸው ማለፋቸው ተዘግቧል፡፡ ይህም ማኅበሩ የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም እንዳልቻለና ያሰበው ሁሉ መክሸፉን አመላክቷል፡፡ ይህ አጋጣሚ የደጀሰላም ገመና የተገለጠበትና ድረገጹ እጅግ የተዋረደበት፣ ቀድሞም አመኔታ የማይጣልበትና የመንደር ወሬ የሚሰለቅበት የአሉባልታ ብሎግ መሆኑን በገዛ አንደበቱ ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡

እነዚሁ ምንጮች የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድት አመራር የተባሉት ግልግል ማኅበረ ቅዱሳን በሌላቸው ሥልጣን እነእገሌ እንዳይገኙ የሚል እገዳ ለመጣል እንዴት ደፈሩ? ሲሉ የሚጠይቁ ሲሆን፣ እንዲህ ያለ ድፍረት ለቤተክርስቲያን ታላቅ ተስፋ ከሆኑት ከሰንበት ትምህርት ተማሪዎች የማይጠብቁት እንደሆነና፣ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ በነደፈው ስልት መሠረት በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስም ያነሳሳው የራሱ የሽብር ጥቃት አካል መሆኑን በሐዘን ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱም ቤተክህነቱን ሽቅብ ለማዘዝ የሚቃጣው ማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የቱንም ያህል የዘንድሮውን የደመራ በዓል ለመረበሽ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ ቅስቀሳው ፈጽሞ እንዳልያዘለትና “አይናቸውን እንዳላይ! በደመራው ላይ ከተገኙ እረብሻለሁ” ባላቸው ሰዎች ፊት ተሰልፎ ለመዘመር መገደዱ ማኅበሩ እንደቀድሞው ደጋፊ እያጣ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ በደጀሰላም ድረገጽ ላይ ለነዛው ሽብር እንደቀድሞው አሜን የሚሉ ብቻ ሳይሆኑ ለምን? የሚሉ በርካታ ሰዎች ሚዛናዊ አስተያየታቸውን መስጠታቸውም ይጠቀሳል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሚከተለውን አስተያየት መጥቀስ ይቻላል፤
"የመስቀል በዓል ላይ እንዳትገኝ" ብሎ መፍረድ ወይም መወሰን አግባብ አይደለም። ክርስትያኑ ቀርቶ ሙሰሊሙም ቢሆን ማንም ሰው በዚህ ብሔራዊ በዓል ለዛውም በአደባባይ በሚከናወን ዝግጅት ላይ የመገኘት መብት አለው። ማንም የማንንም የግል ነፃነትም ሆነ መብት መድፈር አይገባውም። ሠርግ ወይም ድግስ አይደለም፤ እግዚአብሔር ያልከለከለውን ማንም ፍጡር ሊከለክል አይገባም። ከቅርብ ጊዜ... ወዲህ "በሰንበት ትምህርት ቤቶች" አማካኝነት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ከክርስትያናዊ መንገድ በእጅጉ የወጣ ነው። በዕድሜ የሚበልጡንን ወገኖቻችንን ያንቋሽሻል፣ ያጣጥላል፣ ይዝታል፣ ለአመጽ ያነሳሳል። ይህ ሁሉ ሰይጣናዊ አካሄድ እንጂ ክርስትያናዊ አይደለም። ትውልዱ ምን ነካው? "አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሐፍ አውጥታ አጠበች" የተባለው ነገር እየደረሰ ይመስለኛል። "እኛ ብቻ እንስበክ" "አኛ ብቻ እናጥምቅ" "አኛ ብቻ እንናገር" "አኛ ብቻ የምንለውን አድምጡ"... ወዘተ ምነው ጃል! ሁላችንም እኮ ማመዛዘኛ ሕሊና አለን። ሲሆን ቤተ ክርስትያናችን ካጋጠማት ሁለ ገብ ችግር እንድትላቀቅ ጸሎት እና ሱባዔ እንዲያዝ መምከር ሲገባ በማናለብኝነት የሰውን ክብር በሚነካ መልኩ ስም እየጠቀሱ መሳደብንስ ምን አመጣው? ፈራጅ እኮ እግዚአብሔር ብቻ ነው። እንደ ፖለቲካ ድርጅት የጋራ አቋም ማውጣትንስ ምን አመጣው? እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት በቤተ ክርስትያናችን ታሪክ ሰምቼም አላውቅ። ልብ አምላክ ዳዊት "ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፤ ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።" መዝ 13911 በማለት ዘምሯል። እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ!See More

የቤተክርስቲያናችን አባቶች፣ አገልጋዮች፣ ምእመናንና የሚመለከታው ሁሉ የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ የሆነውንና ግልገል ማኅበረ ቅዱሳን የተሰኘውን የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራር የተባለው ስብስብ የማኅበረ ቅዱሳን መደበቂያ ዋሻ ከመሆኑና ሌላ ጥፋት ከማድረሱ በፊት አስፈላጊው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ብዙዎች እየጠየቁ ሲሆን፣ ለስብስቡ ሁኔታዎችን እያመቻቸቹ ያሉት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ማንነትም መፈተሽ እንዳለበትም ያስገነዝባሉ፡፡

በዚህ ሁሉ ቅስቀሳው ያልተሳካለት ድረገጹ በመጨረሻው ሰዓት ላይ “We, Ethiopians Christians, need to bring charcoal from the remains of the Demera fire and mark our foreheads with the shape of a cross + and በቃ. It's is an act of cancellation of our sins and an act of our commitment for the collapse of dictatorship and the wish of our future to be decide by our united hands. የሚል ፖለቲካዊ ጽሑፉን ሰቅሏል፡፡ እጅግ ያስተዛዘበው በደመራው ከሰል በግንባሩ ላይ የመስቀል ምልክት ማስቀመጥ የለመደውን ምእመን ከተለመደው ውጪ “በቃ” የሚል ጽሑፍ አክለህ ተቃውሞህን ግለጽ ሲል አለማፈሩ ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ያልሆነና ከዚህ ቀደም ተሰምቶ የማይታወቅ በከሰሉ የመስቀል ምልክት ማድረግ ኀጢአታችን መደምሰሱ ምልክት ነው ማለቱም፣ ማኅበረ ቅዱሳን እውን ኦርቶዶክሳዊ ማኅበር ነውን? የሚል ጥያቄ አጭሯል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የደጀሰላም ድረገጽ ወደረኛ የሆነው hh://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com" የተባለው ድረገጽ  በአዲስ አባባ መስቀል አደባባይ አንዲት ቅጠል ኮሽ ብትል፣ ማኅበረ ቅዱሳንና የሀገረ ስብከቱ 138 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት /ቤቶች "አንድነት አመራር" ተብዬዎች ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳሉ!!” በሚል ርእስ ባወጣው ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳንን ተቃውሟል፡፡ የጽሑፉ ሙሉ ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡
Sunday, September 25, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ቅዳሜ መስከረም 13 ቀን 2004 ዓ.ም በትዊተር ገጹ ባሠራጨው መረጃ የተወሰኑ አገልጋዮችን ስም በመጥቀስ በመስቀል አደባባይ ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳይኖራቸው አስጠንቅቋል፡፡

ይህ "ማኅበር ነኝ" ባይ ቡድን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት ስም እንዲቋቋም ተፈቅዶለት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሞግዚትነት የተደራጀ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከማደራጃ መምሪያው አልፎ የቤተክርስቲያኗን ህልውና እሰከመፈታተን የደረሰ አካሄድ እያሳየ መምጣቱን ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡

"ማኅበረ ቅዱሳን"፣ በአሁኑ ወቅት እንደ እስልምናው አልቃይዳ ቡድን የፅንፈኝነት፣ የፖለቲካና የቢዝነስ ተግባራትን እያቀላቀለ ሕዝብንና የቤተክርስቲያን አስተዳደርን በነውጥ እያመሰ መሆኑን ምዕመናን አምርረው ይናገራሉ፡፡ ቀደም ባሉ ጊዜያት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በሚገኙ የተለያዩ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ግጭቶች የተከሰቱ ሲሆን፣ በቅርቡም ደሴ ላይ ሁለት ወጣቶች ሞተዋል፡፡ ሀዋሳ ላይም በበርካታ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትና የእሥራት እንግልት መድረሱ ታውቋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ሁሉ፣ እንደ አልቃይዳ ትኩረት ለመሳብ፣ ሕዝብ በብዛት የሚወጣባቸውን የበዓላት ቀናትና ቦታዎችን በመምረጥ ሁከት ለማስነሳት ዝግጅት ላይ መሆኑ ከራሱ አፈትልኮ የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ሲከበር ከሃይማኖታዊ ገጽታው በተጨማሪ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የቱሪስት መዳረሻ በመሆን ለሀገሪቱ መልካም ገጽታ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዓሉ የሁሉም እንደመሆኑ መጠን ከተለያዩ ክልሎችም በዓሉን ለማክበር ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ እንዳሉ በተጨማሪ ይታወቃል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳንና የሀገረ ስብከቱ 138 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች "አንድነት አመራር" ተብዬዎች በዓሉ የጋራ እንደመሆኑ መጠን ተባብረው በዓሉ እንዲሳካ የየግል ድርሻቸውን ከመወጣት በስተቀር በቤተክርስቲያኗ አስተዳደር መዋቅር ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚገኙ አባቶችንና አገልጋዮችን በስም እየጠሩ "እከሌ ይገኝ"፤ "እከሌ አይገኝ"፤ የሚል ሥልጣን የላቸውም፡፡

ባልተሰጠ ሥልጣን፣ "አንዳንድ የሃይማኖት ህጸጽ ያለባቸው ሰዎች ከሃይማኖታችን የተለየ ትምህርት ይሰጣሉ" በማለት ስም በመጥቀስ፣ ልዩ ልዩ ጽሑፎችን የሚበትኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አስመልክቶ ከመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ሐምሌ 25 ቀን 2003 ዓ.ም በቁጥር ል/ጽ/598/1604/03 በወጣው መመሪያም፣ ሕግን ሥርዓትንና የሥልጣን ገደብን ጠብቆ የማይፈጸም ድርጊት፣ የምዕመናንን ኅሊና በማሻከር በቤተክርስቲያኒቱ የአስተዳደር ሥርዓትና በሀገሪቱ ሠላም ላይ እንቅፋት ለመፍጠር ሆን ተብሎ የሚደረግ ሙከራ መሆኑ ታውቆ አስፈላጊው ቁጥጥር እንዲደረግና ድርጊቱም በሕግ እንደሚያስጠይቅ አሳስቧል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ይህንኑ ማስጠንቀቂያና ማሳሰቢያ ወደ ጎን በመተው አንዳንድ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በማሳደምና በ5000 ወጣቶች ስም የዛቻ ወሬ በመበተን ደሴ እና ሀዋሳ ላይ የፈጠረውን ሁከት አዲስ አበባ ላይ በመድገም በንፁሃን ወጣቶች ደም ለመነገድ መቋመጡን ሁኔታው ያሳያል፡፡

ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት መስቀል አደባባይ ላይ ለሚፈጠር ሁከት ማኅበረ ቅዱሳንና የሀገረ ስብከቱ 138 አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች "አንድነት አመራር" ተብዬዎች ሙሉ ኃላፊነቱን የሚወስዱ መሆኑን እየገለጽን፣ በዓሉ ሕዝባዊ እንደመሆኑ መጠን እንደዚህ ዓይነቱን ሁከት በመፍጠር የበዓሉን ገጽታ ለማበላሸት፣ ውስጥ ለውስጥ እየተሹለከለኩ የሚያስተባብሩትን ግለሰቦችና አስተባባሪዎች በአቅራቢያ ለሚገኙ የፖሊስ አካላት በመጠቆም እንድትተባበሩ ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በዓሉ የሠላም፣ የጤና እና የአንድነት ያድርግልን!!!
አሜን!!!

 

   
17 comments:

 1. alamachihu alemesakatun ketsuhfachihu meredat yichalal. Yewshetachihu masaya Begashaw medrek lay neber maletachihu new. BERTU MKalamachihu alemesakatun ketsuhfachihu meredat yichalal. Yewshetachihu masaya Begashaw medrek lay neber maletachihu new. BERTU MK

  ReplyDelete
 2. ማ/ቅዱስ ላይ ያላችሁ አመለካከት በትክክል ስለምናውቀው ሃሳባችሁን በድጋሜ መጠየቅ የለብንም:: ነገር ግን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ በአስተዳደር፣በንብረት አጠባበቅ፣ በአገልጋዮች ምደባ ላይ ያለውን ብልሹ አስተዳደር በተመለከተ እና የተዋህዶ አማኝ ያልሆኑ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ውስት መኖር የለባቸውም ለሚለው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ጥያቄ " ይህ የማኅበረ ቅዱሳን" ነው ከማለት ይልቅ ጥያቄው የተባለው ነገር ሆኖ ከተገኘ ትክክል ነው ወይንስ አይደለም?

  ReplyDelete
 3. Aba Selamawyan,

  Thanks for the News which is so sharp to tell what MK exactly is. By the way I am the member of Mahibere Kidusan even currently working in the office as a staff. This Mahibere really is leaded by the evil spirit which is dividing the church. We here are always crying since we don't have means to survive. We have tried to strike for several times but the hidden leaders tried to cool us down. Believe me the Mahiber is not Alive Spiritually rather is living as a monument of Menillik! Menor ema Ye tiglachinim Hawilit Tikur Anbesa Hospital fitlefit eyenore new - please don't worry about them as they killed themselves.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I AM SO HAPPY TO BE MEMBER OF MAHIBEREKIDUSAN BECAUSE I REALLY UNDERSTAND ABOUT ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH.WE WILL ACCEPT ALL YOUR INSULTS AND YOUR THREATS WITH FULL OF PATIENT . OUR GOD WILL BE WITH US . WE ARE SO STRONG YOU CANNOT SURVIVE US SINCE OUR BASE IS NOT IN YOUR FALSE STATEMENT BUT IT IS BASED ON THE BELIEVE OF JESUS CHRIST AND HIS OTHER OF SAINT MARRY.WE STRUGGLE YOU AND YOUR EVIL ACTIVITIES AND ALL CORRUPTION IN OUR CHURCH BECAUSE OF YOUR MISLEADING BEHAVIOR. IT IS DIFFICULT TO WORSHIP JESUS WITHOUT BEING CLEAN FROM THIS WORLD EVIL ACTIVITIES SO THIS MAHIBE IS WORKING TO MAKE YOU TIDY FROM YOUR SIN AND TO GET JESUS BLOOD AND HIS FESH SO THAT YOU ARE SAVED. PLEASE COOL DOWN AND THINK WHAT THIS MAHIBER IS WORKING IN ETHIOPIA AND OVER ALL THE WORLD. hOPEFULLY YOU WILL AXCEPT ALL OBJECTIVES OF MAHIBEREKIDUSAN POSITIVELY UNLESS IF YOU ARE PROTESTANT OR TEHADISO MENAFIKAN MEMBERSHIP.GOD IS LOVE YOU SO PLEASE LOVE ALL HUMAN BEINGS DON'T POINT YOUR FINGER ON MIHBEREKIDUSAN THERE ARE SO MANY ANGELS AND SAINT AROUND THEM. OTHERWISE YOU WILL BE KILLED AND LOOSE YOUR LIFE. I MEMBER OF MAHIBERE KIDUSAN DO NOT LIKE WHEN YOU KILL YOUR SELF SO PLEASE RESPECT YOUR RELIGION. OUR VOICE IS ALWAYS OUR ORTHODOX TEWAHIDO FAITH.WE RESPECT ALL SAINTS TO BE BLESSED AND TO GET HEAVEN LIFE SO PLEASE BE MEMBER OF ORTHODOX TEWAHIDO FAITH FOLLOWER. GOD BELESS YOU FOR YOUR WONDER FULL INSULTING . PLEASE ALWAYS INSULT US WE ARE SO HAPPY TO GET COMPLAIN FROM EVIL LIKE YOU. MANY THANKS
   BESTS,

   -------------------------------

   Delete
 4. mahebere kidusan yeaganent menfese endemiyaserawe yetaweke new. des yimilewe serawe hulu kentu newe.

  ReplyDelete
 5. 110,000 ትራክት በደመራ ዕለት ተበተነ ይለናል ደጀሰላም። አንዱን ገጽ ትራክት በትንሹ በአንድ ብር ሂሳብ ህትመት ብናሰላው 110,000 ብር ወጪ ሆኗል ማለት ነው። ይህ ብር ደግሞ እነበጋሻውን ከህዝብ ለማራቅ በተሃድሶ ስም የተሰራ ዘመቻ የማህበረ ቅዱሳን እንጂ የሰንበት ት/ቤት ገንዘብ አይደለም። የትራክቱን ቁጥር የሚያውቅ ማን ምን ስለሆነ ነው? ሰንበት ት/ቤት የተባለው የማኅበረ ቅዱሳን ሌላ አዲሱ መሸሸጊያ በደጀሰላም ብሎጉ ጠንካራ ሆኖ እየሰራ መሆኑን በእጅ አዙር ሲነገረን እኛ ደግሞ አወቅነዋ!! ይህ ሰንበት ት/ቤቶች የተባለው አካል ለምን እንዳስፈለገ ታውቃላችሁ? 1/ ቁጥሩ ብዙ ነውና በየደብሩ ስለሚገኝ ለአመጽ አስፈላጊ ኃይል ነው። 2/ በአብዛኛው በማኅበረ ቅዱሳን መንፈስ ቀደም ብሎ የታሰረ ስለሆነ የጊዜው አማራጭ ፈረስ መሆን ስለሚችል ነው። 3/ በቀጥታ ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን አሁን እየተወረወረ ላለበት ዱላ ፊት ፊት ከመላተም የሞተ መስሎ አስቸጋሪውን ወቅት በዝምታ ያሳለፈ በመምሰል በዚያኛው እጅ ለመስራት ጊዜ መግዢያ ነው።
  4/መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን ቢያንስ በጥቁር ሊስቱ ላይ መዝግቦት እንደሚገኝ ስለሚጠረጥር ይህንን ለማስተንፈስ አድራሻና ስም ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ከሚመታ ይልቅ አድራሻና ስፍራ የሌለውን የሰንበት ት/ቤት የሚባለው ጫናውን እንዲሸከምለት፤ አቅጣጫ ለማስቀየርና ለሚባለው ነገር እኔ የለሁበትም ለማለት ሲል ነው።
  አይ ማኅበረ ቅዱሳን!!!

  ReplyDelete
 6. yehawasawn bitbitma man endasnesaw tawko esirbet man endegeba alsemachihum ende. Maferia tsihuf.yehawasawn bitbitma man endasnesaw tawko esirbet man endegeba alsemachihum ende. Maferia tsihuf.

  ReplyDelete
 7. ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ኅጢአት አብዝታችሁ ስትጽፉ ምንድን ናቸው ብየ እንድመረምር አደረገኝ ጎሽ በርቱ!በደንብ ስደቧቸው እረ ዝም እንዳትሉ ልክ ልካቸውን ንገሯቸው :: አሁን ማን ይሙት በዚህ በሰለጠነ ዘመን የቀደመችው ሃይማኖ ትቀጥል ይላል አይ ማኅበረ ቅዱሳን ፋሮች!አባ ሰላማወች ፦ ብዙ ስለሰሩ ለሚፈተኑት ማኅበረ ቅዱሳኖች ዋጋቸውን እያበዛችሁላቸው ነውና እባካችሁ ስድብና ወቀሳውን አታቋርጡት ::

  ReplyDelete
 8. ማኅበረ ቅዱሳን
  የራስ ምታት እንደሆነባችሁ ነው እየተረዳሁ ያለሁት /ገና እንዲህ ለምትጨነቁለት ሆዳችሁም /የሆድ ቁርጠት ይሆንባችሁዋል

  ReplyDelete
 9. AYE ABA SELAMA YET TAKUACHEWALACHIHU ABA SELAMAN YESDIM KAL YETEMOLABET YEKA KA BLOG YEMTLUT KETEFABACHIHU KEMIYAK TEYKU YE ETHIOPIA ORTODOX MIEMENANS MAN EYESERA ENDALE SLEMIYAWUK SM EYETEKESU MESADEB MANNM AYNTIM SLBEDELACHIHU NSHA GIBU ENGBA

  ReplyDelete
 10. እነ የሚለዉ ማንም የፈለገዎን መለጠፍ ይችላል እናንተም ብትሆኑ ግን ብዙም ባትለፉ ጥሩ ነዉ ማህበረ ቅዱሳንን በምግባራቸዉ ስለምናዉቃቸዉ፡፡
  እ/ር አስተዋይ ልቦናይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 11. "ለደመራ በዓል የተቃጣው የማኅበረ ቅዱሳን የሽብር ጥቃትከሸፈ" ????????? ምን ማለት ነው ??????????????ከእስልምናው አልቃኢዳ ጋር መፈረጅ ምን የሚባል ፈሊጥ ነው በጣም በጣም በጣም ሲበዛ ሰራ ፈቶች ናችሁ መጀመሪያ ለመጻፍ ታሪክ ማንበብ ይቀድማል ይህንን የጻፋችሁትን ተረትተረት ለማንበብ ግዜ አላጠፋም ምክንያቱም አርእስቱ ተራ አሉባልታ እንደሆነ ይናገራል እውነት ከእስልምናው አልቃኢዳ ጋር ተፈረጀ ቢሆን ኖሮ እናነተ ሳትሉት በ ፖሊስ ተይዞ ዘብጥያ ይወርድ ነበረ በናታችሁ በናታችሁ በናታችሁ በናታችሁ በናታችሁ በናታችሁ አታወናብዱ

  ReplyDelete
 12. enanta bitilum mahiberu yetawqe new
  le andit hayimanot yeqome

  ReplyDelete
 13. mahiberu yetaweke naw
  le andit hayimanot yeqom naw eshii!!

  ReplyDelete
 14. Who are you? are you devile?

  ReplyDelete
 15. አባ ሠላማዎች ማህበረ ቅዱሳንን ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ የማታደርጉት ጥረት የለም ግን መቼም ቢሆን አይሳካላችሁም ለምን እግዚአብሄር አምላክ ሁሌም ከማህበሩ ጋር አለ ይኖራልም እኛም የማህበሩ አባል ያልሆንነውን ፀረ-ተሃድሶዎች/ፀረ-አባ ሰላማዎች/ ሁሌም በፀሎት ማህበረ ቅዱሳንን እናስባቸዋለን ከእግዚአብሄር ቸርነት ጋር ስለዚህ እባካችሁ ስለሰው ማውራት ትታችሁ ስለራሳችሁ እናንተ መናፍቃኖች ፡፡

  ReplyDelete
 16. "Long live for Mk" midire menafik bitlefelfu minim atametu! betekiristian endehonech yesiol dejoch aychluatm1! mk eske hiwot mesewatnet yagelegilatal!!! errrrrrrrrrrr belu

  ReplyDelete