Sunday, October 9, 2011

በሐረር ምዕመናን ላይ ከፍተኛ የስብከተ ወንጌል ዕቀባ ተደረገ

 


ወንጌልን በጉባዔ ለመስበክና ለመማር አንድ ዓመት የመጠበቅ ግዴታ ተጥሏል


የሐረር ከተማ ምዕመናን ቅሬታቸውን ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና ልዩ ልዩ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያዎች አቀረቡ


ማኅበረ ቅዱሳን ወንጌል እንዳይስፋፋ ባለው ቁርጠኝነት ጉባኤያት እንዳይካሄዱ ለማግባባት ሞክሮ እንደነበር ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ባሠራጨው ደብዳቤ በከተማው አጥቢያ ቤተክርስቲያናትም ሆነ በወረዳዎች በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ ጉባዔ እንዳይካሄድ አዘዘ፡፡ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ በአቡነ ያሬድ ፊርማ ለከተማዋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በመጋቤ ሠናያት ኃይለ ማርያም ፊርማ ለወረዳዎች ቤተክህነት ጽ/ቤቶች ጳጉሜ 2 ቀን 2003 ዓ.ም በቁጥር 905/275/2003 በተሠራጨው በዚህ ደብዳቤ፣ ማንኛውም የስብከተ ወንጌል ጉባዔ ያውም ከንግሥ በዓል ጋር ተያይዞ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዳይካሄድ አስጠንቅቋል፡፡

በጠንካራ ቃላት የታጀበው ይኸው ደብዳቤ አያይዞም፣ የፀሐይን ዑደት ተከትሎ በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄደው ጉባዔ ለአንድ ቀን ብቻ እና ከየትኛውም ገዳምም ሆነ ሀገረስብከት መምህራን ሳይጋበዙ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰባክያነ ወንጌል ብቻ እንዲካሄድ ያስገድዳል፡፡

ይህ በእንዲሀ እንዳለ ሁኔታው ያሳዘናቸውና ያስቆጣቸው ከሦስት ሺህ በላይ የሐረር ከተማ ምዕመናን ይህ የሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ በቃለ ዐዋዲው ስለስብከተ ወንጌል ከተደነገገው መመሪያ ጋር የሚጋጭ እና ሕገወጥ በመሆኑ እንዲሻርላቸው፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና ልዩ ልዩ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያዎች ማቅረባቸውን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አካላት ገልጸውልናል፡፡ የሐረር ምዕመናን ሰኞ መስከረም 22/2004 ዓ.ም እና ረቡዕ መስከረም 24 ቀን 2004 ዓ.ም አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተክህነት መንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት በአድራሻ በጻፉት የቅሬታ ማመልከቻ፣ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች የወንጌል አገልግሎት እንዳይስፋፋ ከፍተኛ ችግር በመፍጠር ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ለወንጌል ጉባዔ በዓመት አንድ ቀንን ጠብቁ መባላቸውን እንደማይቀበሉ እና የተላለፈው የወንጌል ገደብ ደብዳቤ እንዲሻርላቸው በአፅንዖት ጠይቀዋል፡፡

በማመልከቻቸው እንደተጠቀሰው በቃለ ዐዋዲው ማሻሻያ አንቀጽ 21 ንዑስ አንቀጽ 17 ነጥብ 4 (ልሳነ ተዋህዶ ዘ ኦርቶዶክስን ይመልከቱ ) እንደተብራራው፣ ማንኛውም የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ክፍል ጉባዔያትን አዘጋጅቶ ታዋቂ መምህራንን መጋበዝ እንደሚችል የተደነገገ ሲሆን፣ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የቤተክርስቲያንን ደንብ በመሻር ታዋቂ መምህራን እንዳይጋበዙ ያዘዘበት ምክንያትም አሳማኝ አይደለም ብለዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይህንን መመሪያ በፍላጎታቸው የፈረሙት አይደለም የሚሉት እነዚህ ወገኖች፣ ማኅበረ ቅዱሳን በህዳር ወር 2003 ዓ.ም አካባቢ በሐረር ንዑስ ማዕከል ከቤተክርስቲያን የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባደረገው ሚስጥራዊ የፓናል ውይይት ወርሃዊ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮች እንዳይካሄዱ ሲያግባባ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን እኒህን ደግ አባት በሆነው ባልሆነው ጠምዝዞ ሃሳባቸውን አስለውጦ መመሪያውን ፈርመው እንዲያሠራጩ ማድረጉን ይስማሙበታል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የሀገረስብከቱን ጽ/ቤትና የልዩ ልዩ አጥቢያ ሰበካ ጉባዔ ጽ/ቤቶችን በመቆጣጠር መዋቅሩን ከላይ እስከ ታች ሰቅዞ በመያዝና አላፈናፍን በማለት ማስቸገሩን የጠቆሙት እነዚህ ምዕመናን፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኃላፊዎችና ፓትርያርኩም ጭምር ፈር እንዲያስይዙላቸው ተማፅነዋል፡፡

ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተክርስቲያናችን የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል ለዓለም ስትሰብክ የመጀመሪያዋ አይደለም ያሉት እነዚህ ምዕመናን፣ አመቺ ሆኖ ከተገኘ ጉባዔ በየዕለቱስ ቢዘረጋ የሰውን ልጅ ወደ ንስሐ ለመጥራትና ለማፅናናት እንዲሁም አምላካችንን ለማመስገን በዝቷል ሊባል ይችላል ወይ? ብለው በአግራሞት ይጠይቃሉ፡፡ በተለይም ሐረር ከተማ በራስ መኮንን ጊዜ የተቆረቆሩ ጥንታውያን አብያተ ቤተክርስቲያናት ያሏት እንደመሆኑ መጠንና የሃይማኖታችን ተከታዮች ቁጥር በሳሳበት ሁኔታ፣ ወንጌል እንዳይሰበክ በየሰበቡ ደንቃራ መፍጠር በእውነት ለቤተክርስቲያን እንቆረቆራለን ከሚሉ ወገኖች የሚጠበቅ ነው ወይ? በማለት በአንክሮ ጠይቀዋል፡፡

የእኛ ዓላማ ይላሉ እነዚህ ምዕመናን፤ የእኛ ዓላማ በሰባክያነ ወንጌል መካከል ልዩነት ሳይደረግ የወንጌል ጉባዔ ተዘርግቶ በታዋቂ መምህራን የመማር መብታችን በሕገ ወጥ አካሄድ ሊገደብብን እና በጨለማ ዓለም እንድንኖር ሊፈረድብን አይገባም እናም ይህንን በሥነ ሥርዓት ለማሳወቅ ነው ብለዋል፡፡

በሀገረ ስብከቱ የማኅበረ ቅዱሳን አዋኪነት እየጎላ መጥቷል ያሉት እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ባለው አቋም ወንጌል ሲሰበክ እንደሠይጣን እየበረገገ በአገልጋዮች ላይ የፕሮቴስታንታዊ-ተሀድሶ-ኑፋቄ ታፔላ በመለጠፍ በፕሮፓጋንዳ ዘመቻው ቤተክርስቲያንን እያተራመሰ የሚገኝ ጊዜ ወለድ በሽታ እየሆነ መምጣቱን አምርረው ተናግረዋል፡፡ በተለይም ከዕምነት አንፃር ብሉይን ከሀዲስ እያመሳጠረች እግዚአብሔርን የምታመልከው ቤተክርስቲያናችንን ወደ ኦሪትና አይሁድ ትምህርት በመመለስ ቤተክርስቲያንን ከቅዳሴ፣ ከስብከተ ወንጌል፣ ከጸሎት እና ከድኅነት ቤት ይልቅ ከምዕመናን ባዶ በማስቀረት ወደ ሙዚየም ቅርስነት እንዳይለውጠው ተሰግቷል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን በሃይማኖት ተቆርቋሪነት ሽፋን ውስጥ ውስጡን ወደ ሊቃነጳጳሳት በመዝለቅ የቤተክርስቲያንን አስተዳደር በእጅ አዙር የመቆጣጠር ፍላጎቱን ለማስፈጸም ደፋ ቀና በማለት ላይ ሲሆን፣ ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ለሰበካ ጉባዔዎች፣ ሰበካ ጉባዔዎች ለሀገረስብከት ጽ/ቤቶች፣ የሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች ለሊቃነጳጳሳት፣ ሊቃነጳጳሳት ለሲኖዶሱ እና ለቅዱስ ፓትርያርኩ እንዳይታዘዙ እና ርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን በመደበላለቅ እንዲሁም ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አንተባበርህም በሚሉት ሊቃነጳጳሳት ላይ የፕሮቴስታንታዊ-ተሀድሶ-ኑፋቄ ስም በመለጠፍ በሀገሪቱ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ በማስከተል ላይ መሆኑን አባላቱ ሳይቀር ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
from dejeslaam.blogspot.com

11 comments:

 1. ye mahbere kidusanin sim kalanesachihu metsaf atchilum ende? Sitgermu!!

  ReplyDelete
 2. It looks your end is near. Your disepton in our church is numbered. God bless MK and abune Yared, and the rest of guys who work hard enough to tackle MENAFEQANE!

  Habit is a bad thing NOW you are also tring deception in the name of dejeselam too? With doule aa tomorrow I hope I'll see with double ss too. Keep up your lies for money in the name of faith. Good jobi
  Ben

  ReplyDelete
 3. Idle mind the work shop of a devil. Please make up your mind. Don't waste it.One side of your mind judging you more over God is watching you all what you are doing.

  Egziabher yirdachehu

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው
  በፍቅሩና በእውቀቱ ያፅናችሁ። ወንጌል የገባችሁ
  እውነተኞች በመሆናችሁ ዘወትር የምታስተላልፉትን
  ትክክለኛ መልእክት ሳልጎበኝ አድሬ አላውቅም።

  ነገር ግን አንዳንድ የማቅ አላማ አስፈፃሚዎች
  በሚሰጡት ሰይጣናዊ አስትያየት የተነሳ በፍፁም
  ተስፋ እንዳትቆርጡ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃችሁአለሁ።
  ዘወትር አድናቂያችሁና ስለዚች ቅድስት ክርስትናችን
  ከሚጋደሉት አንዱ ነኝ። ሌላም በጣም የበዙ ተከታዮች
  እንዳሉአችሁም ልገልፅላችሁ እወዳለሁ። ሰላም ሁኑ።

  ReplyDelete
 5. ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይህንን አያደርጉም እንዳሳሳቷቸው ግልጽ ነው፡፡ የማኅበረ ቅዱሳንም ግብረ በላ አይደሉም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለጥቅምት ሲኖዶስ አገልጋዮችን ተሐድሶ በሚለው ዘመቻው ማስወገዣ ለጳጳሳት ለእያንዳንዳቸው 200 ሺህ ብር እየሰጠ ይገኛል፡፡ ለአያንዳንዱ የሲኖዶስ አባል ይህን ያህል ገንዘብ መመደብ ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ ሠርተው አላመጡት፡፡ የድሃይቱን ቤት እየዘረፉ ያጠራቀሙት ነው፡፡ ለተሐድሶ ማጥፊያ 12 ሚሊየን ብር ያስፈልገኛል ብሎ ከመርካቶ ነጋዴዎችና ከምእመናን ሲሰበስብ ሰንብቷል፡፡ ታንክ መግዣ ይሁን አይሁን ገና አልታወቀም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን በጭፍን አልጠላም፡፡ ችግራቸውን ግን በዓላማ ስለያዙት አዝናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. hhhahahhahha the antivirus of tehadiso menafik is MK. U LOOK NOW TO BE HOPLESS.

  ReplyDelete
 7. this must be applied to all areas of the country so that tehadiso will be destroyed.

  ReplyDelete
 8. አባ ሰላማዎች! እስከመቸ ነው ኑፋቄን እያራገባችሁ የምተኖሩት! እግዚአብሄር የኢ/ኦ/ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያንን መቸም አይተዋትም እናነተ ቤተክርስቲያንን ለመናድ ያሰባችሁ መናፍቅ መሆናችሁ ይታወቃል:: ሐረር ላይ በአድስ መልክ ያቀዳችሁት ተንኮል ተደርሶበታል ሀገረስብከቱ የወሰደው እርምጃ ትክክል ነው እግዚአብሄር ልባችሁን ይመልስላችሁ:: ለንስሃ ያብቃችሁ::

  ReplyDelete
 9. ስለ ስድብ ከምትጽፍ ህይወትህን ብትፍትሽ ይሻል ነበር:: ማህበረ ቅዱሳን እንደሆነ እግዚአብሄር ያስነሳው እንጅ ከአዳራሽ የተሰበሰበ አይደለም ተንኮላችሁንና ሴራችሁን እየፈለፈለ ስለሚያወጣባችሁ መፈናፈኛ አጣችሁ:: እናንተ ስም ባጠፋችሁ ቁጥር ማንነታችሁን እየገለጻችሁ ነው:: ለማንኛውም እግዚአብሄር ይገስጻችሁ!

  ReplyDelete
 10. ማህበረ ቅዱሳን Eskemechereshaw be Egziabeher hail yewagachihual.Egziabeher Lebetekrestian yesetat ye abune GORGORIOS yebekur lij Eskemechereshaw yegadelelatal. Mesluachihu new ,wedelibachihu temelesu! Menafikan nachihu!Enawkalen!
  Enkuan Enante yegehanem dej yetebale yegibr abatachihum Betekrstianin aychilatim,Yekrestos mushira akalu eko nat,lezelalem Abruat ale.
  Betachihun astekaklu,Temotalachihu!!!

  ReplyDelete
 11. bzmnu Ytnsu bqedusane seme Ymingedu (qedusane hawareYate smatate tsdeqane lqomulte alama ymayeqomu ( ykeresetose wnegeale xlate honwe ,y ayehude sebesebe,Yfrisaweyane ena yksashoche sebesebe)mahebre nachwe eneme der dero yemselnge nbre bngrachene tekelhayemanote, giyoregise,abunegebre mnefse qeduse ena leloche qedusane smatate eko eyesusene sebekwe nwe yalfute. lebe ysexacheu wsebeha legziabeher.

  ReplyDelete