Wednesday, October 12, 2011

እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም ይንቀሳቀሳል የተባለው ዋሃቢያ በአክራሪነት ተፈረጀ

መንግሥት እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰ ነው በማለት ዋሃቢያ የተባለውን ድርጅት በአክራሪነት ፈረጀ፡፡ አንዳንዶች ፍረጃውን በተመለከተ ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡ መስከረም 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በፌዴራል ፖሊስ ዋና መሥርያ ቤት የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሃይማኖት የውይይት መድረክ፣ ዋሃቢያ የተባለው እስላማዊ ድርጅት የአገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር ተግባር እየፈጸመ መሆኑን መንግሥት በማረጋገጡ፣ ድርጅቱ በአክራሪነት እንደተፈረጀ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም ይፋ አድርገዋል፡፡


የመገናኛ ብዙኅን በሃይማኖት ግጭቶችና መቻቻል ላይ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በተዘጋጀው በዚሁ ውይይት ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት ዶ/ር ሽፈራው፣ መንግሥት ዋሃቢያ የተባለውን የእስልምና ድርጅት በአክራሪነት የፈረጀበትን ምክንያት አስረድተዋል፡፡ ድርጅቱ በሚያሰራጨው ትምህርትና በሚያደርገው ተጨባጭ እንቅስቃሴ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የሚፃረር አቋም እያራመደ መሆኑን መንግሥት ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡

‹‹ድርጅቱ ከዋሃቢያ ውጪ ያሉ ሃይማኖታዊ ተቋማት መኖር የለባቸውም ብሎ ተነስቷል፤›› ያሉት ዶ/ር ሽፈራው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሸሪዓ ሕግ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት መቋቋም አለበት በማለት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አክለው ገልጸዋል፡፡

ዋሃቢያ ወታደራዊ ክንፍ እንዳለው ያስረዱት ዶ/ር ሽፈራው፣ የድርጅቱ እንቅስቃሴ በሕገ መንግሥት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነፃነት፣ የመንግሥትና የሃይማኖት መለያየትንና የሃይማኖት እኩልነትን መርሆዎች የሚቃረን መሆኑንም በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ በኢሉባቡር፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በባሌ፣ በጅማና በሌሎችም አካባቢዎች በተከሰቱ የሃይማኖት ግጭቶችና ጥቃቶች የድርጅቱ እጅ እንዳለበትም አስታውቀዋል፡፡

በፌዴራል ጉዳዮች የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አቶ መረሳ ረዳ፣ ‹‹ልማት፣ ዲሞክራሲና የሃይማኖት አክራሪነት›› በሚል ያቀረቡትን ጥናታዊ ጽሑፍ ተከትሎ በተደረገው ውይይት፣ ‹‹የሙስሊም ጉዳዮች›› ጋዜጣ አዘጋጅ ዮሴፍ ጌታቸው፣ ‹‹መንግሥት ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እጁን አውጥቶ አያውቅም›› በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ መንግሥትና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ከማይወክሉ የእስልምና ጉዳዮች መሪዎች ጋር አብረው እየሠሩ ይገኛሉ በማለት አስተያየቱን አጠናክሯል፡፡

‹‹መንግሥት በሙስሊም ድርጅቶች ላይ ጠላትና ወዳጅ እየፈጠረ ነው›› ያለው የጋዜጣው አዘጋጅ፣ በአንድ በኩል ዋሃቢያን በአክራሪነት እየፈረጀ በሌላ በኩል የአሕቢሽ አስተምህሮ ሲስፋፋ ዝም ማለቱ አግባብ አይደለም ሲል ተቃውሞውን ገልጿል፡፡

‹‹ዋሃቢያ የተፈረጀው በአመለካከትና በዶክትሪን አይደለም በአክራሪነት ነው፤›› ያሉት ጽሑፍ አቅራቢው አቶ መረሳ፣ ድርጅቱ በተጨባጭ የሚሰጣቸው አስተምህሮዎችና የሚፈጽማቸው ድርጊቶች የሃይማኖት ነፃነትን የሚፃረሩና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን የማያከብሩ መሆኑ ስለተረጋገጠ በአክራሪነት ተፈርጇል ብለዋል፡፡ ‹‹ጉዳዩ ስም ማጥፋት አይደለም፡፡ የሰው ሕይወት እየጠፋ ነው ያለው፡፡ ጭካኔ የተሞላባቸው ተግባሮች ሲፈጸሙ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ያንን ለመሸፈን የሚደረገው ሙከራ ሕገወጥ ነው፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሙስሊም ነፃ ጋዜጠኞች ኅብረት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጀማል መሐመድ፣ ማናቸውንም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ ተግባሮችን የሚፈጽም ድርጅት ሕገወጥ ነው በማለት፣ ‹‹በሙስሊም ጉዳዮች›› ጋዜጣ አዘጋጅ የተሰጡ አስተያየቶችን ተቃውመዋል፡፡

መንግሥት የሕዝብ ደኅንነትንና ሰላምን የሚያደፈርሱ ማናቸውም ዓይነት ድርጊቶች ሲፈጸሙ ጣልቃ የመግባት ግዴታ እንዳለበት ያስረዱት ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጋር በትብብር በተለያዩ አካባቢዎች ሥልጠናዎች መሰጠታቸውን አስመልክቶ የቀረቡት አስተያየቶች መሠረተ ቢስ መሆናቸውን ገልጸው፣ ‹‹ምክር ቤቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማሳነስ የሚደረግ ዘመቻ ነው፤›› ብለውታል፡፡ ‹‹መንግሥት አሕቢሽን እያበረታታ ነው›› በሚል አንድ የሊባኖስ ምሁር በሥልጠናው ተሳትፈዋል ተብሎ የቀረበው አስተያየትም የተዛባና ሀቅን መሠረት ያላደረገ መሆኑን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

‹‹ይኼ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ድርጊት ሕዝበ ሙስሊሙን ያሳዘነ ነው፤›› ለሚባለው፣ ‹‹የሙስሊሙ ኅብረተሰብ የሚፈልገው ሰላምና ነፃነትን ነው፡፡ የሚያጋጨውንና የሚያናቁረውን አይደለም፡፡ ለመሆኑ አንድ የግል ድርጅት እንዴት የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ወክሎ መናገር ይችላል?›› በማለት አስተያየት ሰጪዎች የሚናገሩዋቸው በመረጃ ላይ የተደገፉ እንዲሆኑና ድርጅቶቻቸውን ብቻ ወክለው እንዲናገሩ ዶ/ር ሽፈራው አሳስበዋል፡፡

                                           ethiopian riporter

8 comments:

 1. nice to hear, but we believe that 'tehadiso' should also be charged for the same crime as they are sects/groups of protestant extremists. in fact, they may be born from orthodox church but they are 'bandas' for their act of bargaining their beloved church for western doctrine in search of money. protestant domination/pastors who incite this act should be charged for their crimes on orthodox church. however, we know it that even if it is illegal, the government does not address this issue for the sake of his interest, even we often believe that the government itself is the core part to play the roll, but we await the real justice from our GOD.

  ReplyDelete
 2. @ 1st comment. Tasekalehe.Do you Know who God is ,we tehadeso are seeking Reformation in the church not for the sake of what you think .That is for the glory of Jesus Christ let me tell you one thing if you understand salvation which is the central message of the Bible I am sure you also understand that Only Jesus is worthy of your Praise .The teaching that says Jesus is the only way of Salvation doesn't come from Westerners .It comes from the Bible even our Ethiopian Orthodox forefathers didn't teach what you belive if you truly seek the truth you can get the answer by studing History, when the false teachings inter in to the Ethiopian orthodox Church any way read the bible your own languge translation but not Geez actually if you know geez it's okay I hope you will get the truth very soon.

  ReplyDelete
 3. This will be the fate of Begashaw and Sereke in particula Tehadiso in general SINCE THEY COMIT SIMILAR CRIME IN AWASSA, DILLA, HARRAR,...

  ReplyDelete
 4. የመጀመሪያው አስተያየት ሰጪ፤ በመጀመሪያ አክራሪነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እወቅ!! ከዚያ በኋላ ስለመታደስና መለወጥ የሚናገሩትን አክራሪ ናቸው ወይም አይደሉም ለማለት ትችላለህ። አክራሪነት የራሱን ፍላጎት በሌላው ላይ እሺ ካለ በውድ፤ እምቢ ካለ በግድ የሚጭን ኃይልን በመጨመር የሚጠቀም ነው። ከሌላው ጋር ውይይት፤ ንግግርና በመረጃ ላይ መግባባትን ሳይሆን እሱ ያለው ትክክል ስለሆነ አምነህ በውዴታ ትቀበላለህ፤ አይስማማኝም ካልክ በኃይል ታምናለህ። እምቢ ካልክ ትገደልና ቦታውን ትለቃለህ። የአክራሪነት እውነታው ይሄ ነው። ታዲያ በክርስትና ዓለም በወንጌል ቃል ታምናለህ ወይ ታሳምናለህ እንጂ በኃይል ወይም በሰይፍ ታስገድዳለህ የሚል ትምህርት የት እንዳለ እስካሁን አላውቅም። ካለ ንገረንና ምን ዓይነት ክርስቲያኖች እንደሆኑ እንወቃቸው!! ጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ መሠረታዊ እምነቷን የሚያፋልሱ የፈጠራና የልብወለድ ታሪክና መጻሕፍት አሉ፤ እነሱም እነዚህና እነዚህ ናቸው፤ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በዚህ መልኩ ይጋጫሉ እያሉ የሚያሳዩትን ብትችል በመጽሐፍ ቅዱስ ምላሽ ማሳመን፤ ካልቻልክ ስህተት ያለበትን እንደእግዚአብሔር ቃል አርሞ ማስተካከል የሚቻል መሆኑን ሁሉም የሚያምንበት ሆኖ ሳለ የትኞቹ አክራሪዎች ናቸው በግድና በጉልበት እያስገደዱ የሚገኙት? ይልቁንም አንተንና ማቅን የመሳሰሉ አክራሪዎች እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ ግን እነዚህ ስህተቶች እንደእግዚአሔር ቃል መታረም አለባቸው የሚለውን ወገን በቃሉ ስህተት ከሆነ ስህተት፤ እውነት ከሆነ እውነት በማለት ከማስተማር ይልቅ ስህተትም ቢሆን ማመን አለብህ! ይህንን ያመኑ ሲዖልም ገብተው ከሆነ አምነህ ያንኑ ፍለጋ የግድ መከተል አለብህ! ብላችሁ ስድብ፤ዱላና ዛቻ የሚቀናችሁ እናንተ አይደላችሁም? በዓለማዊ የስለላ ስራችሁ በቴፕና በሰው አጥምዳችሁ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይዞ የሚናገረውን ሰው በመጽሐፉ ማሳመን ስለማትችሉ በዚህ ዓለም ገዢ በከሳሽ አባታችሁ ድጋፍ ስትከሱ የምትኖሩት እናንተ አይደላችሁም? ወሃቢዝም ተከታዮቹ ከማመን በቀር መጠየቅ፤ ወይም ይሄ ስህተት ነው ብለው ቢገኙ ቅጣታቸው መታረድ ነው። እናንተም እንደወሃቢ ይህ ትክክል አይደለም ወይም መስተካከል አለበት የሚል አንድ ኦርቶዶክሳዊ ቢነሳ ታሳድዱታላችሁ፤ ትከሱታላችሁ፤ አጋጣሚውንም ጠብቃችሁ ትደበድባላችሁ፤ ከቻላችሁም ትገድላላችሁ!!እነ ምርትነሽን መርካቶ ተክለሃይማኖት ስትደበድቡ እሰይ ብላችሁ እርስ በእርሳችሁ ተመሰጋግናችሁ የለ!! ተሃድሶ የሚባል የለም እንጂ ቢኖርና አዲስ እንሁን፤ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር መንፈስ እንለወጥ ቢል ችግሩ ምኑ ላይ ነው? መለወጥን የሚጠላው ሰይጣን ብቻ ነው።

  ReplyDelete
 5. ሰውን የገደለ፡ የሰው መብት የተጋረጠ፡ ቤተ ክርስትያናችን የሰው ደም በኣውደ-ምሕረትዋ እንዲፈስ ያደረገ፡ ሌት ተቀን ባለጋራነት እና ጠላትነትን ሲፈለፍል የሚኖር፡ ከቤተ ክርስትያናችን፡ ሰዎችን የሚያባርር፡ ከምሕረት ክርስቶስ ይልቅ፡ የኦሪትን መርገም፡ የሚሰብክ፡ ከክርስቶስ ኣምላክነት ይልቅ፡ የማርያምን ኣምልኮ የሚቀናው፡ ለኣምላኽ የእድሜ ገደብ የሚከልል፡ እንውነት ለተናገረ ኩሉ፡ ኣሳድጅና ጠላት። በውጫዊ ኣቋም በማተብና በነጠላ፡ ብቻ መናፍቅ እያለ የቤተ ክርስቲያን ሰው የሚሰድብ፡ የሚደባደብ፡ የሚገድል፡ ተሓድሶ ነው ወይስ ማሕብረ ቅዱሳን (ማሕበረ-ሰይጣን)?
  እርግጠኛ ነኝ፡ የሆነ ሰው ይህንን ጥያቄ፡ መልስ ቢባል ሞቶ ከሞቶ፡ ራሳቸው የማሕበረ ርኩሳን ኣባላትም ሳይቀሩ፡ እውነተኛ መልሱ ማቅ (ማሕበረ- ርኩሳን) እንደሚሉ።
  ምክንያቱ ተሃድሶ፡ ከፍቅር፡ ከትሕትና፡ ከክርስቶስ ፍቅር፡ በቀር፡ ሌላ ክፋትና፡ በደል የላቸውምና።
  እና የመንግስት ዓይን ከኣልጋ ዓይን ይበዛልና፡ ጊዜው ሲደር እንደ ዋሃቢያን፡ የማሕብረ ርኩሳን ፍረጃም ኣይቀሬ ነው፡ ብቻ፡ ቸሩ ኣምላኽ እድሜ እና ጤና ይስጠን።

  ReplyDelete
 6. this is good thing for Ethiopia to future. Thanks God!

  ReplyDelete
 7. Enbaqom ZedebreTsgeaOctober 19, 2011 at 8:04 AM

  አክራሪ ማለት ሃይማኖቱን በጥንቃቄ የያዘ: ለእምነቱ ታማኝ በመሆን በፆም በጸሎት የተወሰነ ከሆነ እውነታችሁ ነው አስተያየት ሰጪዎች እነ ማሕበረ ቅዱሳንንና ሌሎች በፈሪሃ እግዚአብሔር እናንተ
  በትዕቢት የተዋችሁትን ንስሐን ገንዘብ ያደረጉትን በአክራሪነት መፈረጃችሁ:: ነገር ግን እነርሱስ
  በትሕትና ከእግዚአብሔር እየተማሩ ዋኖቻቸውን ቅዱሳንን እያከበሩ በደመ ክርስቶስ ልብሶቻቸው ንጹሕ በማድረግ ለመነግሥተ ሰማያት ዝግጁ ለመሆን ደፋ ቀና ይላሉ::
  እናንተ ተሃድሶዎች ግን አክራሪዎች ትባላላችሁ በአሁኑ ብያኔ መሰረት:- የመንግሥት ብያኔ....ሃይማኖቱን በሌላው ለመጫን የሚፈልግ አንጃ...
  እናንተ ፕሮቴስታንት ስትሆኑ: ነገር ግን በቤታችን በቤተ ክርስቲያን መጥታችሁ በንጹሕ አእምሮ ጌታን እያመለክን ሳለ "የለም ተሳስታችሁአል: እናንተ አታውቁም: እኛ ነን መምህራኖቻችሁ" ትሉናላችሁ::
  በቤታችሁ በእነ ሙሉ ወንጌል ሁናችሁ ብትሰድቡን የተለመደ ሥራችሁ ነው:: አሁን ግን አለቆቻችን ሳትሆኑ አለቆቻችሁ ነን: መምህራኖቻችን ሳትሆኑ መምሃራኖቻችሁ ነን በማለት በእግዚአብሔር ፊት ምንፍቅና የሆነውን ትምህርታችሁ ለመጫን በገዛ ቤታችን የቤቱ ባለቤት ሳትሆኑ ትረብሻላችሁ:: አሁንም በጊዜው ወደ አባታችሁ ወደ ዲያብሎስ ቤት መሄዳችሁ አይቀርም:: ጌታ ቤቱ የጸሎት ቤት እንጂ የውንብድና ቤት አይደለምና::

  ReplyDelete
 8. Ye'EGZIABIHER menfes ahunim yiseral. Sew hulu zim yibel.

  ReplyDelete