Friday, October 14, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን “ተሐድሶ መናፍቃን” ያላቸው ግለሰቦችና ማኅበራት እንዲወገዙ ጥሪ አቀረበ፡፡

ዘመድኩን በቀለ ሊቃውንት ጉባኤውንና ፓትርያርኩን አስጠነቀቀ፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችንም ለአመጽ ቀሰቀሰ

እርስ በርሱ መከፋፈልና መሰነጣጠቅ የያዘው፣ ህልውናው አጣብቂኝ ውስጥ የገባው፣ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ማሳካት ያልቻለውና በሃይማኖት ሽፋን እያደባ የሚገኘው፣ ከውጪ ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከራሱ ሰዎች ተቃውሞ እያየለበት የመጣው፣ ለህልውናዬ ዋና እንቅፋት ናቸው ባላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቶ የቆየው፣ ወንድሞችን ከመክሰስና በዚያ ሰበብ ገንዘብ ማግበስበስና በቤተ ክርስቲያን ስም መነገድን እንደ ዋና ሥራው የያዘው ማኅበረ ቅዱሳን ሁሉንም ባስገረመና የእርሱን አላዋቂነት ባጋለጠ መልኩ፣ ተሐድሶ መናፍቃን እያለ ሲሰድባቸው የነበሩትን ግለሰቦችና ማኅበራት ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲያወግዛቸው የሚጠይቅበትን እጅግ ዳጎስ ያለ የክስ መዝገቡን ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማስገባቱ ተገለጸ፡፡ ማኅበሩ እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሰውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በይፋ የከፈተው በነሐሴ 2002 ዓ.ም. ባሳተመው ሐመረ ተዋሕዶ ላይ መሆኑ ሲታወቅ፣ መስከረም 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያስገባው ከመንፈቅ ስንክሳር የማያንስ የክስ ድርሳኑ የዘመቻው ምዕራፍ አንድ መዝጊያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳንን ድርሳነ ክስ ወደ ፓትርያርኩ ይዘው የገቡት ማኅበረ ቅዱሳን በመንግሥት በኩል አለኝ የሚለውና የሚመካበት አባሉ አቶ ካሳሁን ኀይለ ማርያም የመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ዲያሬክተርና የማኅበሩ ሰብሳቢ ዶ/ር “ሊቀ ትጉሃን” “ቀሲስ” አቶ ሙሉጌታ ሥዩም መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ማኅበሩ በነሐሴ 2000 ዓ.ም. በይፋ የጀመረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከትሎና በየአዳራሹ በሕገ ወጥ መንገድ በኅቡእ በጠራቸውነ ግንዛቤ ማስጨበጫ የሚል ስያሜ በሰጣቸው ስብሰባዎች “ተሐድሶ መናፍቃን ቤተ ክርስቲያናችንን ሊወርሱ ነው፤ ተነሡ” እያለ ባዘጋጃቸው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮችና በሌሎችም መንገዶች 12 ሚሊየን ብር ያህል መሰብሰቡን ለማኅበሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን፣ በዚህ የገንዘብ ኀይል ተማምኖ የጥቅምቱን ሲኖዶስ ስብሰባ እርሱ በሚፈልገው አቅጣጫ ለመንዳት የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሚጠቀሱት ውስጥ ከሲኖዶሱ ስብሰባ ቀደም ብሎ በሚደረገው የሰበካ ጉባኤ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ከየሀገረ ስብከቱ ለሚመጡ ሥራ አስኪያጆች ማረፊያ ገስት ሀውስ ያዘጋጀ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ ደጋፊ ጳጳስም ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በመስጠት ድጋፍ የማሰባሰቡን ጥረት ቀጥሏል፡፡ ቀድሞ ማኅበሩን ሲቃወሙ የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳትም ብሩ ከተሰጣቸው በኋላ አቋማቸውን ለውጠው “ማኅበረ ቅዱሳን … ማኅበረ ቅዱሳን” እያሉ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቻችን ለአብነትም የሁመራው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሉቃስ ይጠቅሳሉ፡፡ እኒህ ሊቀ ጳጳስ ቀድሞ የሚቃወሙትን ማኅበር ሲያወድሱ የታዘቡ ወገኖች በበላበት ከሚጮኸው የቤት እንስሳ ጋር አመሳስለዋቸዋል፡፡ማኅበሩ ከገንዘብ በተጨማሪ ዕቅዱን ለማሳካት እየተጠቀመበት ያለው ስልት በቡድን በቡድን ሆነው ፓትርያርኩን ከሥልጣን ለማውረድ በስውር እንቅስቃሴ ከጀመሩት የተለያዩ ጳጳሳት ጋር በመሥራት፣ እንዲሁም የተለያየ ነውር አግኝቼባችኋሁ እያለ የሚያስፈራራቸውን ጳጳሳትም ዋ! በማለት ሁሉንም እንደየሁኔታቸው ይዞ ለአንዱ መንበረ ፓትርያርክ እያታገላቸው እንደሚገኝ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ለፓትርያርክነት እርስ በርስ ከሚታገሉት መካከልም ከዚህ ቀደም የተገኘባቸውን ነውር ማስፈራሪያ አድርጎ በርቱ ሲላቸው የነበሩት አቡነ ሳሙኤል አንዱ ሲሆኑ፣ ካሰቡት ሳይደርሱ መዘባበቻ ሆነው ቀርተዋል፡፡ሌላው ፓትርያርክነት ይገባኛል በሚል በምኞት ፈረስ እየጋለቡ ያሉትና የማኅበረ ቅዱሳንን ድጋፍ ፈልገው ከማኅበሩ ጋር በአዲስ ፍቅር ውስጥ የሚገኙት አቡነ ሉቃስ ሲሆኑ፣ እኒህ ጳጳስ “ማስትሬት ያለኝ ጳጳስ እኔ ነኝና ፕትርክናው ይገባኛል” በሚል እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ አቡነ ሄኖክና ሕዝቅኤልም አብረዋቸው እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡ሌላው የማኅበረ ቅዱሳን ዋና መጋለቢያ የሆነው ቡድን የወሎዎች ቡድን ሲሆን፣ ይህ ቡድን ቤተ ክርስቲያናችን ከተጠናወታትና ውስጥ ውስጡን እንደ ብል ሲበላት ከኖረው የዘረኝነት በሽታ እንዳትፈወስ ሌላ ዘረኝነትን ለመትከል የሚንቀሳቀስ ቡድን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ አትናቴዎስ፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ ገብርኤል፣ አቡነ በርቶሎሜዎስ፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ አቡነ ሕዝቅኤል እና አቡነ ኤልያስ የዚህ ቡድን አባላት መሆናቸው ግልጽ ሆኗል፡፡ ከእነዚህ መካከል ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሆናቸውን እንደ ልዩ አጋጣሚ በመቁጠር፣ “ሥራ አስኪያጁ እኛ፣ ጸሐፊውም እኛ በሆንበት በዚህ ጊዜ ነው ለፓትርያርክነቱ መታገል ያለብን” በሚል በቅርቡ ውስጥ ለውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገው የነበረ ሲሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከሥልጣን ሲወርዱ መንበር የሚጠብቅ በሚል አቡነ ቄርሎስን በመንበር ጠባቂነት እስከ ማጨት ደርሰው የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ሁሉ በስተ ጀርባ ያለው ግን ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ እርግጥ ነው የሚሉት ምንጮቻችን፣ ለዚህም ማስረጃ ብለው የሚጠቅሱት ከዚህ ቀደም ማኅበረ ቅዱሳንን እንዳላይ ይሉ የነበሩት አቡነ ፊልጶስ በማኅበሩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሮች ላይ እየተገኙ ሲባርኩና ተሐድሶ መናፍቃን የተባሉትን ሲያወግዙ የነበሩ መሆናቸውን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በማኅበሩ ላይ ባለው ሥልጣን ማኅበሩን ለማስተካከል በሚያደርገው ጥረት እንቅፋት ሲሆኑና ሽፋን ሲሰጡት የነበረ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም በሰኔ ወር 2003 ዓ.ም. ማኅበሩ በአፋጣኝ ኦዲት መደረግ አለበት ብለው ፓትርያርኩ ጥብቅ ትእዛዝ ሲሰጡ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ቅዱስ አባታችን ጉዳዩን ለእኔ ይስጡኝ፤ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ኦዲት እንዲያደርጉ አደርጋለሁ፡፡ ካልሆነ ለፀረ ሙስና ኮሚሽን እከሳቸዋለሁ” ብለው ጉዳዩን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ተዳፍኖ እንዲቀር አድርገዋል፡፡ ይህም ማኅበሩ ከቅጥረኛ ጳጳሳቱ ጋር እየተመሳጠረ ከልዩ ልዩ ወንጀሎች የሚያመልጥበት ስልቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡   ቀድሞ እንደ ሃይማኖተ አበው፣የልደታ ለማርያም ሰንበት ትምህርት ቤት ካሉ ማኅበራት ጋር አለሁ አለሁ ሲሉ የነበሩትና አሁን ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን ፍቅር ማን ይለየኛል በማለት በእርሱ ልብ የሚያስቡትና በእርሱ ሳንባ የሚተነፍሱት አቡነ ገብርኤልም ወደ አዋሳ ተመድበው ከሄዱ ጊዜ ጀምሮ፣ በአዋሳ በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና በቤተ ክርስቲያን ልጆች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ከማርገብና ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ወግነው በየግል መጽሔቱ እርሱ የሚለውን ደግመው እየተናገሩ፣ ማኅበሩን አማኝ፣ ከማኅበሩ ጋር የተጋጩትን ደግሞ መናፍቃን እያሉ በባዶ ሜዳ በየሚዲያው ከአንድ ጳጳስ በማይጠበቅ ሁኔታ እላፊ ቃላት መሰንዘራቸው ከጀርባቸው ማኅበሩ እንዳለ ያመለክታል ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ያክላሉ፡፡ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ተቧድነው የቀረቡለትን ጳጳሳት እንደየፍላጎታቸው በማስተናገድ ለአንዱ መንበር ሲያታግላቸው ዋና ዐላማው የእርሱን ፈቃድ የሚፈጽም ጳጳስ በፓትርያርክነት መሾምና ቤተ ክርስቲያቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ማዋል ነው፡፡ ከዚያም ጉዞውን ወደቤተ መንግሥት ማቅናት ነው፡፡ ይህ ግን ቅዠት እንጂ የሚፈታ ሕልም አይደለም፡፡ ማኅበሩ ካሰበው ሳይደርስ ስለተነቃበት የስልት ለውጥ ለማድረግ ቢሞክርም፣ ተቃውሞው ከውስጥም ከውጪም ስላየለበት፣ ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ “ተሐድሶ መናፍቃን” የሚል ያረጀ ነጋሪት በመጎሰም ወደ እርሱ ያነጣጠረውን ትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ሰሞኑን ከፓትርያርኩ ጀምሮ ለጳጳሳት ሁሉ ያደለው የክስ ስንክሳርና “ተሐድሶ መናፍቃን” ይወገዙልኝ የሚለው ጥያቄው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡ ማኅበሩ ያቀረበው ክስ የጠቅላላው ምእመናን ነው ለማለት የድጋፍ ፊርማ ያሰባሰበ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውግዘትን በድጋፍ ፊርማ የጠየቀ የመጀመሪያው ማኅበር ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጎታል፡፡ ሐምሌ 25 ቀን 2003 ዓ.ም. ፓትርያርኩ በሰጡት መመሪያዊ መግለጫ ውስጥ ውግዘት የሚተላለፈው ተሳስቷል የተባለው ሰው ትምህርት በሚመለከተው የቤተ ክርስቲያኗ አካል ተመርምሮ የስሕተት ትምህርት መሆኑ ሲረጋገጥና ያ ሰው አልመለስ ብሎ በስሕተቱ ከጸና ለቅዱስ ሲኖዶስ ቀርቦ ውሳኔ ሲያገኝ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን ሥሪቱ ፓለቲካዊ እንጂ ሃይማኖታዊ ባለመሆኑ፣ ችግሮቼ ለሚላቸው ጉዳዮች የሚወስዳቸው መፍትሔዎች በአብዛኛው ፖለቲካዊ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፣ የድጋፍ ፊርማ ማሰባሰብም የዚሁ ፖለቲካዊ ወይም ዓለማዊ አሰራር አካል መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡በክሱ ስንክሳር ውስጥ ማኅበሩ ከዚህ ቀደም ቆርጦ እየቀጠለ ካቀረባቸው፣ እንደ ገደልና ድርሳን ፍጹም ውሸትና የፈጠራ ታሪክ ጽፎ ካቀናበራቸውና ሚዛን ከማይደፉት ማስረጃዎቹ የተለየ ነገር እንዳላቀረበ የታወቀ ሲሆን፣ ማኅበሩ ይወገዙልኝ ብሎ በጳጳሳት ፊት ክስ የመሰረተባቸው ግለሰቦችና ማኅበራት ከዚህ ቀደም በመጻሕፍቶቹ፣ በመጽሔቶቹና በጋዜጦቹ፣ በቪሲዲዎቹና በቃልም ሲያብጠለጥላቸው የነበሩትን ወገኖች ነው፡፡ አንድ ማኅበር እንዲህ የማድረግ መብትም ሆነ ሥልጣን የሌለው መሆኑ ቢታወቅም ማን አለብኝ የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ራሱ ከሳሽ፣ ራሱ ጠበቃ፣ ራሱ ዳኛ እየሆነ ብዙዎችን ከእናት ቤተ ክርስቲያን ሲያፈናቅል የኖረበትን ስልት ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲተገብርለት መከጀሉ ትልቅ ድፍረት መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡በተለይ ማኅበራቱ በሕጋዊ መንገድ በሚመለከተው የመንግሥት አካል ተመዝግበው መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ማኅበራት ከመሆናቸው አንጻር ብዙ ሊያስኬድ እንደማይችል እየተነገረ ነው፡፡ አንዳንድ ጳጳሳት በገንዘብ ቢገዙም እንኳ የአንድ ወገን ጩኸት ብቻ በመስማት ፍርደ ገምድልና ሁከትና ብጥብጥ ሊያስነሣ የሚችል ውሳኔ በቅዱስ ሲኖዶስ ይወስናሉ ብሎ መጠበቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ተሐድሶ በሚል ስማቸው እየጠፋ የሚገኝ ግለሰቦችና ማኅበራትም ጉዳዩን በቸልታ እንደማያዩትና ቅዱስ ሲኖዶስ የእነርሱንም ድምጽ የሚሰማበት እድል እንዲያመቻች ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከአስተባባሪዎቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን እና የእነርሱ ትምህርቶች ቢመረመሩ የሚያስወግዝ ትምህርት ይዞ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን የሚናገሩት እነዚሁ አስተባባሪዎች፣ ማን አውጋዥ ማን ተወጋዥ እንደሚሆን ጊዜው ደርሶ የምናየው ይሆናል ሲሉ ያላቸውን ጠንካራ አቋም እየገለጹ ነው፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የባህታዊ ገብረ መስቀል ምክትል ሆኖ በ1985 ዓ.ም. ላይ ምእመናንን ሲያሳምጽ የነበረውና በአሁኑ ወቅት ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳንን አንጃ የተቀላቀለው ጎጋው ነጋዴ ዘመድኩን በቀለ በደጀ ሰላም ድረ ገጽ ላይ ባወጣው መልእክት፣ የስድብ አፉን ለማኅበረ ቅዱሳን ያከራየ መሆኑን ይበልጥ አረጋግጧል፡፡ የጽሑፉ ሙሉ ቃል የሚከተለው ነው፤በሚቀጥለው የሊቃውንት ጉባኤ ላይ እነ በጋሻው በተለያዩ የተሃድሶ ደጋፊዎች ጥረት ነጻ የሚወጡ ከሆነ በየቦታው ያሉ ሰንበት ተማሪዎችን በማስተባበር ሸቃሾጮችን ከቤተክርስቲያን ጠርገን በሃይል ማስወጣት አለብን፡፡ በጋሻውም ሆነ ግብር አበሮቹ ተጠራርገው ሊወጡ ይገባል፡፡ ሳይሆን ማንኛችንም መተኛት የለብንም፡፡ ተሃድሶዎች የሚጫወቱብን ፓትሪያርኩን ተገን አድርገው ነው፡፡ እሳቸውንም ቢሆን ልንለቃቸው አይገባም፡፡ ሽጉጣቸውን አስጥለን ወደ መጡበት እንመልሳቸዋለን፡፡በዚህ መልእክቱ ከብዙዎቹ የድረ ገጹ አንባብያን ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው መሆኑን በድረ ገጹ ላይ ከተሰጡ የተቃውሞ አስተያየቶች መገንዘብ ይቻላል፡፡ አቶ ዘመድኩን በቀለ የሚታወቀው በተቃውሞና አመጽን በማነሳሳት መሆኑን ከእስከ ዛሬው ታሪኩና ተግባሩ ተረጋግጧል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ መናፍቃን በሚላቸው ወገኖች ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱን ተከትሎ፣ ዘመቻው ዳጎስ ያለ ትርፍ ያስገኝልኛል በሚል አርማጌዶን በተባለ ጦረኛ ርእስ ካቀናበረው ቪሲዲ ጠቀም ያለ ትርፍ ያጋበሰ ከመሆኑም በላይ የእነ በጋሻው አገልግሎት በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ በየግል መጽሔቱ ሁሉ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ እላፊ ንግግር እስከማድረግ በመድረሱም በስም ማጥፋት ወንጀል ተከሶ ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ መሆኑ ሲታወቅ፣ ጉዳዩ ውሳኔ ሳያገኝ እንዲህ ያለ መልእክት ማስተላለፉ፣ ግለሰቡ ጤነኛ መሆኑ አጠራጣሪ ነው ሲሉ አንዳንዶች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡የዘመድኩን መልእክት የእርሱ ብቻ መልእክት ነው ማለት እንደማይቻል የሚገልጹት ታዛቢዎች የማኅበረ ቅዱሳንም አቋም መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ማኅበሩ ተሐድሶ መናፍቃን ያላቸው ሰዎች እንዲወገዙለት ጥያቄ ባቀረበ ማግሥት ዘመድኩን እንዲህ ያለ የቤተ ክርስቲያንን ሰላም ሊያደፈርስ የሚችል መልእክት ማስተላለፉ ሆነ ተብሎና ታቅዶ የተደረገ መሆኑን እንደሚያሳይ ጥርጥር የለውም፡፡ ማኅበሩ ዘመድኩንን እንደ አፍ የተጠቀመበት ከዚህ ቀደም አመጽን በማቀጣጠል የተካነ ወልደ አመጽ መሆኑን ስለሚያውቅ መሆኑን የሚናገሩት ውስጥ አዋቂዎች፣ የሊቃውንት ጉባኤን እስከ ማዘዝ የደረሰው ዘመድኩን ነው ማለት እንደማይቻልና እንዲህ ማድረግ የሚፈልገውና የሚደፍረው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ጠቅሰው በዘመድኩን አፍ የተናገረው ማኅበሩ ነው ሲሉ አስረግጠው ያስረዳሉ፡፡       ጉዳዩን በሕጋዊ መንገድ ሳይሆን እነርሱ በሚፈልጉት መንገድ የሊቃውንት ጉባኤው ርምጃ ካልወሰደና እነበጋሻውን ነጻ ካወጣ ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማነሳሳት ሸቃጮች ያላቸውን ክፍሎች ከቤተ ክርስቲያን ጠራርገን በኀይል እናስወጣለን የሚለውም አነጋገር ፍጹም መንፈሳዊነት የጎደለውና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ፡፡ ይህም ቤተ ክርስቲያንን ወደ ስርአተ አልበኛነት ለማሸጋገር ማኅበሩና ግብረ በላዎቹ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ያመለክታል ሲሉም ያክላሉ፡፡የዘመድኩን መልእክት ማሳረጊያ የሆኑት ፓትርያርኩ ሲሆኑ፣ በመልእክቱ ዘመድኩንና ማኅበሩ የሚፈልጉት ካልተወሰነላቸው የተሐድሶ ሽፋን ሰጪ አድርጎ ያቀረባቸውን ፓትርያርኩንም እንደማይለቋቸው ዝቷል፡፡ በ1985 ዓ.ም. ምክትል ባሕታዊ በነበረ ጊዜ ሕዝብን ለአመጽ ሲቀሰቅስበት የነበረውን የሽጉጥ ጉዳይ ለአሁኑ ቅስቀሳው መጠቀሙ ፍጹም ጎጋነቱን ያስመሰከረበት ሆኗል፡፡ የመልእክቱ የመጨረሻ አረፍተ ነገርም በምርጫ 97 ተቃዋሚዎች በመስቀል አደባባይ ያሰሙትን ንግግር ያስታወሰ ሲሆን፣ የዘመድኩንንና አፉን የተከራየውን የማኅበረ ቅዱሳንን ፖለቲካዊ አቋም ግልጽ አድርጓል፡፡


22 comments:

 1. · 1. If you have upbraided, or passed judgment on, or vexed your brother, your peace is lost.

  · 2. If you have been boastful, or have exalted yourself above your fellow, you have lost grace.

  · 3. If you did not drive away forthwith the wanton (dissolute) thought that came to you, your soul will lose love for God and boldness in prayer.

  · 4. If you are fond of power, or money you will never know the Love of God.

  · 5. If you have followed your own will, then you are vanquished by the enemy and despondency will come upon your soul.

  · 6. If you detest your brother, it means that you have fallen away from God, and an evil spirit has taken possession of you.

  · 7. But if you will do good upon your brother, you will gain quiet for your conscience.

  · 8. If you subdue your own will, your enemies will be driven off and you will receive peace in your soul.

  · 9. If you forgive your brother the affronts he puts upon you, and love your enemies, then you will receive forgiveness for your sins, and the Lord will give to you the love of the Holy Spirit.

  · 10. And when you have entirely humbled yourself, you will find perfect rest in the Lord.

  · 11. But if a soul is puffed up, then her day of rejoicing is over, for grace forsakes her and she can no longer pray with a pure heart, and evil thoughts come to harass her.

  · 12. Why is it that man suffers on earth and is beset by afflictions and adversities?

  · 13. We suffer because we lack humility. The Holy Spirit dwells in the humble soul, bringing freedom, peace, love and blessedness.

  · 14. If misfortune overcomes you, do not lose heart but recollect that the Lord in mercy looketh upon you, and do not allow yourself to think, “Is the Lord going to look upon me when I grieve Him?” For mercy is the nature of the Lord.

  · 15. Instead, turn to God in faith, and like the prodigal son say, “I am no longer worthy to be called thy son,” and you will see how pleasing you will be to the Father, and your soul will be filled with joy indescribable.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማህበረ ቅዱሳን እውነተኛና ሕጋዊ ማህበር ነው
   ማህበረ በቅዱሳን እውነተኛ የኦርቶዶክስ የቁርጥ ቀን አለኝታ ነው ሆዳሞች በበዙበት ሰአት በገጠር የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ያስከፈተ ጥምቀት ያላገኙ ወገኖቻችን ጥምቀት እንዲገኙ ሰፊ ስራ የሰራ አባቶች ካህናት ዳቆናት፣ሰባኪን የሃማኖት ዕውቀታቸው እንዲሰፋ ያስተማረ ቤተክነት መስራት ያለበትን ሥራ እና ኃላፊነት የተወጣ ምዕመኑ በአዳዲስ እና በአጭበርባሪ ትምህርቶች በመናፍቃንና በተረፈ አሪዮሳዊያን ተሀድሶ እንዳይወሰድ ጠንክሮ በጥበብ ዕየተዋጋ ያለ ድንቅ ማህበር ነው በተጨማሪም ከአባላቱ የሚሰበስበውን ገንዘብ ሙሉለሙሉ በስራ ላይ በማዋል ሪፖርት የሚቀርብ ገንዘቡ የዋለበትን ፕሮጀክት በተጨባጭ ማስረጅ እንዲሁም በአካል ማየት ለሚፈልግ በየገጠሩ በሚገኙ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት የሚያሳ ነው ለአብነት ከአባላት በሰበሰበው ገንዘብ የአገልግሎት ማስፋፊያ ድንቅ ሕንፃ በ4ኪሎ ዋና ማዕከል ማስገንባቱ ለእውነጠኞችና ንፁህ ህሊና ላላቸው አካላት ማህበሩ ልማታዊና እየንዳንዱ የአባላት መዋጮ በስራ ላይ እንደሚውል ተጨባጭ ማስረጃ ነው እንደሌሎቹ ሌቦች ማህበራትና አጉራዘለል ሰባኪያን ለግል መኖሪቤት መስሪያና መኪና መግዣ አልዋለም ይህም ማህበሩ ምን ህል እውነተኛ እንደሆነ ያስታውቃል ነገርግን " ደጀ ብርሃንና አባ ሰላማ " የሚባሉት የተሀድሶ ማህበራት ማህበሩን ከመንግስት ጋር ለማጣላት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም ነገርግን አልተሳካላቸውም ነገም አይሳካላቸውም ምክንያቱም የማህበሩ ጠባቂ እውነተኛው የአለም ፈጣሪ እየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ በኢንተርኔት እውነት እንናገራልን ቢሉም የእንረሱ ቡድን የሆነው መኪና እያማረጠ አለሙን የሚቀጨው ለአገልግሎት እስከ 16 ሺ ብርና ምቾት ያለው ማረፊያ በቅድሚያ ይዘጋጅልኝ እያለ የምንፍቅና ትምህርትን በፕሮስታንታዊ ቅኝት የሚነዛውና በሚሊኒየም አዳራሽ የእግዚያቤርን ቃል እንደ ሸቀጥ የቸበቸበውን ገንዘቡንም የት እንደገባ ሪፖርት ቤተክርስቲያን ጠይቃ አስካሁን ድረስ ምላሽ ያልሰጠውን ኪራይ ሰብሳቢ የሆነውን የበጋሻውን ቡድንን ለምን ብሩ የት ገባ ብሎ መጠየቅ ተሳነ የማህበረቅዱሳንማ ሂዳሞችንና መናፍቃንን የሚሸበር ህንፃ ለቀጣይ የተጠናከረ አገልግሎት አስገንበቶ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ማስረጃ አቅርቧል፡፡

   Delete
 2. God bless All bishopes,MK, Zemedkun and others who work hard to clean our beloved church. You Whites dogs are very pity. For you MK is a code word to describe anyone who belive in orthodox tewahedo. Everyone who belive in OT faith is MK tahts why you open your dirty, filthy mouth to every bishops. Im MK b/c i agree 100% with them. there faith is my faith too. you are not OT. your faith is 100% similar to those of Mulu wongel. go there leave us alone.
  anyway good job MK. Because of this i contribute a little money in your paypl account. God bless you andyur job.

  Ben

  ReplyDelete
 3. አቶ መዥገር በቀለ ፣ በቅናት ሠክረህ እንደ ይሁዳ
  ራስህን እንዳታንጠለጥል። ለመሆኑ አንተ ማነህ\\\\
  አንተ ሸቃጭ ፈርሳዊ፣ አንተና የሸቀጥ ወደብህ
  ማህበረ ሰይጣን ከአለቃችሁ ከሠይጣንና ከጭፍሮቻችሁ
  ጋር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሰይፍ ትመታላችሁ።

  እነ መጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው እኮ የክርስቶስ ልጆች
  ናቸው። አንተ ማነህ ፡የመውጊያውን ብረት ብትቃወም
  ላንተ ይብስብሃል፡ ባነደዳችሁት እሳት እናንተው ትቃጠላላችሁ
  እንጂ የተዋህዶን ልጆች እውነተኞቹን የልብሳቸውን ጫፍ እንኩአን
  እሳቱ ነበልባሉ አይነካቸውም። እንዲሁ ትደክማላችሁ፡ እናንተ
  እኮ የቤተክርስቲያናችን ካንሰሮች ናችሁ ቀስ ብላችሁ ጀምራችሁ
  አሁን ካንሰራችሁን እያሰራጫችሁ ትገኛላችሁ፣ ነገር ግን ከርስቶስ
  በደሙ የመሰረታት ቤተክርስቲያን ስለሆነች ካንሰሩአን ነቃቅሎ
  ይጥልላታል። አይ መዥገር በቀለ በኢትዮጵያ ለመሆኑ አቡነ
  ጳውሎስ በአንተ አፍ የሚጠሩ ናቸው\ በጣም ታስቃለህ እንኩእን
  ከርስቲያኖች አለቃህ ሰይጣንም መጨረሻችሁን ሰለሚያውቅ በሆዱ
  እየሳቀባችሁ ይገኛል፣ ተራ ዘባተሎ።

  የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የአሸናፊዎች አሸናፊ
  ነውና እውነተኛ የተዋህዶ ልጆችንና የድንግል ማርያም ውዳጆች
  ልጆችን እነ በጋሻውን ይጠብቅልን። ለእናንተም የንስሃ ልብ ይስጣችሁ።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 4. . guys DO YOU BELIEVE zemedekun HAS COMMUNICATION WITH PROTESTANT LEADRES ? WE HAVE VOICE MESSAGE RECORD FROM HIM THAT HE TALKED AND ASKED BENEFITF FROM ONE PROTESTANT PASTOR SO WHY THIS GUY DEFAME AND AGANIST THE ORTHODOX PREACHERS ,WHY HE LOOK LIKE TRUE BELIVER. BROTHERS AND SISTERS , IF HE GO EXTREMLY I WILL SEND TO YOU EVERY DOCUMENT THAT HE HAS CONNECTION WITH PROTESTANT PASTOR.

  ReplyDelete
 5. erkusoch nachu enante.erkus gar degmo mawratm hone menor ayichalm.gedel gibu.geta wagachun yistachu.

  ReplyDelete
 6. kewedeku behuala menferaget lemelalat. Lemehonu benante zend ewunetegnoch papasat eneman nachew? Maferia tsihuf

  ReplyDelete
 7. le sidib yekena andebet yemanew? Be afu leminor yemenafikan wogen "Abaselam bilog" Abatun yemisadeb ligi is not orthodox.whatever you wrote, all are false.b/c you always lay.you are not orthodox why don't be silent.

  are you sure?እውነተኛ የተዋህዶ ልጆችንና የድንግል ማርያም ውዳጆች
  ልጆችን እነ በጋሻውን !!!!! It is from tehadiso protenstant.Anyway this blog is work entairly for protstant and the blonger is also protestant.

  ReplyDelete
 8. All true orthodox know who is the problem of our church.It is all the blogger of abase lama.
  If you do not feel,post it.

  ReplyDelete
 9. Enamesegnalen yezih blog tsehafiwoch ,u think that are telling us how bad mk is .but whoever is mk ,we are indetifying u while u wrote abt mk." ዶ/ር “ሊቀ ትጉሃን” “ቀሲስ” አቶ ሙሉጌታ ሥዩም" kill nachihu bewnet.

  ReplyDelete
 10. ok, now, the strategies of protestant/tehadiso has not worked and gets paralyzed at least for the time being due to the unreserved effort of real tewahdo followers (bishops, mk and real associations, Sunday school students, and others who are in love with the church). enemies guided by 'dabilos' would never stop attacking the CHIRST CHURCH' , hence, users of these blog ( most of u are protestant/tehadiso menafkans) should know that you have no room to achieve the EVIL mission. try another strategy, we await U MUCH MORE ORGANIZED THAN BEFORE

  ReplyDelete
 11. Dn. Zemekun Bergit Endih Aynet Nigigir Kaderege Beewunt Ene Almirwum edebedibewalhu. Gin Wendi Yihun Ena bgil gazeta yakribat new weyis Endelimdachu eyewashachun new?

  ReplyDelete
 12. gena gen atehadiso yitefal.

  ReplyDelete
 13. one of the funniest issue at recent times is that non-believers ( protestants) disguise themselves as followers/church servants in orthodox church for their own interest, but how can they succeed given the true believers are well aware of it on one hand and, anti- menafkan campaign has so intensely been lunched on the other hand despite the patriarch has received a huge amount bribe . protestant menafkans ( mulu wongel, mekaneyesus, kalehiwot meserte kirstos.....) did not realize that the patriarch alone does not have all the power to carry out every scandal.

  ReplyDelete
 14. you,the bloogers are tehadiso. you are fooling me for long period of time. when you insult the bishops i understood as you are not the enemy of mk rather you are the enemy of orthdox church. thanks for your lies.

  ReplyDelete
 15. እረ አባ ስላማዎች ይሄንን ክፍት አፍ የተማመነውን ባውቅ ደስ ይለኝ ነበረ መካሪ የለውም እንዴ ጎበዝ ቢሆን እኮ በጋሻው ያስተማረውን በዚህ ደቂቃ በዚህ ላይ ሄዳችሁ ስሙ ከሚል እራሱ ጥሩ ትምህርት ያስተምር ነበረ ግን እግዚሃብሄር ሳይፈቅድለት አይሆን አሁን ደግሞ በስሜ ፌስ ቡክ ተከፈተ ብሎ እያላዘነ ነው እግዚሃብሄር ከምቀኝነት ያውጣው ሁላችንም እንጸልይልት ልጁ በጣም ያሳዝናል እኔ ዝም ብዬ አይደለም እንዲህ የምለው የቅናት መንፈሱን ስለማውቅ ነው

  ReplyDelete
 16. I don't think the source of this report is from MK. You just made it up. If you want you can contact MK to verify.The blogger is totally a lier and driven by evil spirit.But I am not surprized for you always have never had a true story.Keep fabricating as politicians and protestants.

  ReplyDelete
 17. አስመሳዩ ባህታዊ ማንያዘዋል አበበ እና
  ሕጻናት ልጃገረዶችን ደም በማፍሰስ ያበጠ በላይ ወርቁ
  በቲኦሎጂ ተመራቂዎች ስም ኮሌጁን በማ/ቅ ፤ ለመዉረስ እያደከማችሁ ነዉ፡፡
  አንድ ቀን በኮሌጁ ተማሪዎች እንደ እባብ ስትቀጠቀጡ እናያለን

  ReplyDelete
 18. አስመሳዩ ባህታዊ ማንያዘዋል አበበ እና
  ሕጻናት ልጃገረዶችን ደም በማፍሰስ ያበጠ በላይ ወርቁ
  በቲኦሎጂ ተመራቂዎች ስም ኮሌጁን በማ/ቅ ፤ ለመዉረስ እያደከማችሁ ነዉ፡፡
  አንድ ቀን በኮሌጁ ተማሪዎች እንደ እባብ ስትቀጠቀጡ እናያለን

  ReplyDelete
 19. Aba selamawoch Gata Kenante Gar yun bertu Amen.Begashaw yetewhedo Lej new Kenze Kemyrebu Gata Yexebken Enrsu Yeswen Enje YEgatan Aysebumna Selzi Birr naw Enersu Ende Yewda YEmiwdute.Aba selamwoch Tebarku,

  ReplyDelete
 20. betam yasazinal,I really hate this blog.Egizabher yemifera andebet yesedeben kalat ayawetam.yemetasebut endesega selehone yesega hayel yemiyashenfi yimeslachual.Egziabher yikir yebelachihu ....
  Egziabher meabelun aregageto beselam lejochun sitebik tayalchihu.
  I am really surprised not even seeing the word " Let us pray" .

  ReplyDelete
 21. ሁላችሁም ስለማህበረ ቅዱሣን አወራችሁ እናንተ ለቅድስት ቤተክርስቲያናችሁ ምን ሰርታችኋል ክርስቶስ ሲመጣ የምታቀርቡት ማህበረ ቅዱሳንን መውቀሳችሁን ነው ወይስ ምንም እንደአልተማራችሁ ልታወሩ ነው ይልቅ እውነት ለቤተክርስቲያን የቆማችሁ ከሆነ ስለቤተክርስቲያን ቆማችሁ ጸልዩ ምነው የጅማ ካህን ሲገረፍ የትሄዳችሁ ነበር የዋልድባ ገዳም አባቶች ስቃያቸውን ሲያዩ ምን ትሰሩ ነበር ዛሬ ሰዎችን ለመውቀስ አፋችሁ ተፈታ ከሁላችሁም የተረፈን ወሬ ነው ማንኛችሁ ጥሩ እንደሰራችሁ የሚያውቅ አምላክ ብቻ ነው አሁን ቤተ ክርስቲያን ችግር ውስጥ ናት ምክንያቱም
  1. ምእመኑ ተኝቷል
  2. ወጣቱ የሚመርጠው ጠፍቶበት የውሃላይ ኩበት ሆኗል
  3. ሌላው እኛ የምንፈልገው ሞቅ ያለ መዝሙር ስብከትም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ብዙዎቻችን ቤተክርስቲያን መጸሐፍ ቅዱስ አትሰብክም ብለን እንላለን ለመሆኑ እኛ እራሳችን መጸሐፍ ቅዱስን አንብበን እናውቃለን እኛ መፀሐፍ ቅዱስ አንብበን ብናውቅ ቤተክርስቲያን ምን እንደምትሰብክ እናውቅ ነበር ስለዚህ ከማውራት መስራትና ማሣየት ይበልጣል፡፡
  3. ቤተክርስቲያን በእሣት ስትቃጠል ገድሎቿ ሲሰረቁ እኛ አለን ብለናል እነእከሌ እንዲ አደረጉ ከማለት ውጭ በመጽሐፍት ያሉ አባቶቻችን ስለቅዱሣን ተናግረው አይጠግቡም የአሁን አባትና አሁን ያለ ሰባኪያን ስለ ቅዱሣን ይሰብካሉ ተብሎ ምስክር መስጠት ይቻላል? ስለዚህ ግድ አንድትጠራጠር የሚጋብዝ ነው እኛ አኮ ማውጣት ያለብንን አስራት እንኳን በስርዓት የማናወጣ ሰዎች ነን ስዎችን ከመውቀስ ሁላችንም ስለቤተክርስቲያ ናችን እንፀልይ

  ReplyDelete