Saturday, October 15, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን" መፈንቅለ መንበረ ፓትርያርክ የማካሄድ ዕቅድ እንዳለው የሚያሳዩ ፍንጮች እየታዩ ነው

ፅንፈኛው "ማኅበረ ቅዱሳን" መፈንቅለ መንበረ ፓትርያርክ የማካሄድ ዕቅድ እንዳለው የሚያሳዩ ፍንጮች እየታዩ ነው
የለውጥ አብዮት ያስፈልጋል በማለት የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ዓላማ እንዳለው ታውቋል
ይህንኑ የለውጥ አጀንዳ በቅርቡ በሚካሄደው የጥቅምት ሲኖዶስ ጉባዔ በአፍቃሬ - "ማኅበረ ቅዱሳን" ሊቃነጳጳሳት በኩል አስርጎ በማስገባት እንወያይበት እንደሚል ይጠበቃል
ለወቅታዊው የቤተክርስቲያን ችግር የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ጣልቃ ገብነት መቆም ዋነኛውና መሠረታዊው መፍትሔ ነው
ቤተክርስቲያን፣ የራሳቸውን ሃይማኖት መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ተቋም በሚወጉ አገልጋዮች ላይ የእርምት ርምጃ ካልወሰደች የከፋ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል
ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ቆላ ደጋ እያማታ የዘለቀው "ማኅበረ ቅዱሳን"፣ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ የቤተክርስቲያን ላይ አብዮት ነጋሪት እየጎሰመ መሆኑ ከራሱ የትዊተር ገጽ እያፈተለኩ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በተለያዩ ስሞች በተከታታይ በወጡት በእነዚህ መረጃዎች "ማኅበረ ቅዱሳን" አሁን ያለውን የቤተክርስቲያን መዋቅር በራሱ አቅጣጫ የመቀየር ጽኑ ፍላጎት እንዳለው አሳይቷል፡፡
መስከረም 12 ቀን 2002 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በታዛቢነት በተገኙበት የሠላም ጉባዔ ላይ ማኅበሩ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያለው አቋም የማያወላውል መሆኑን ገልፆ፣ "በቤተክህነት መሥሪያ ቤት ኋላቀር አሠራር መሻሻል አለበት" ብሎ በድፍረት መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም የጉባዔው አባላት በወቅቱ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዕድገትና ለውጥ የተመዘገበባቸው ወደ አሥራ አምስት ዝርዝር ነጥቦችን በማስረዳት አሳፍረው መልሰውታል  ይሁን እንጂ ከዚህ አስተሳሰቡ የዞረ ድምር (Hangover) ያልተላቀቀው "ማኅበረ ቅዱሳን" ዛሬም ያንኑ የሞኝ ዘፈኑን እየደጋገመ ማሰማቱን ቀጥሎበታል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በለመደው የክህደት ባህርይው "ለቅዱስ ፓትርያርኩ ያለአቋም የማያወላውል ነው" ሲል በገለጸበት አፉ፣ ዛሬ ደግሞ በቀሲስ ወንድምስሻ አማካይነት "የፓትርያርክ ጳውሎስ አሳፋሪው ዘመነ ፕትርክና ሌላው ገጽታ የጵጵስና ክብር ከመጠን በላይ መቃለሉ ነው . . . " በማለት በመሳደብ ላይ ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ የ"ማኅበረ ቅዱሳን"ን አስተሳሰብ የማይደግፍ ወይም ለምን ብሎ የሚጠይቅ ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ተሃድሶ፣ ፕሮቴስታንት፣ መናፍቅ እየተባለ የተፀውዖ ስም ይወጣለታል፡፡ በነገራችን ላይ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በላይ የተናቀ፣ የተገረፈ፣ የተተፋበት፣ እና የተሰቃየ ስለሌለ በእርሱ ስም ክርስቲያኖች የምንባል ተዋህዶ ኦርቶዶክሳውያን፣ ብንሰደብም፣ ብንናቅም፣ ብንሰቃይም በደስታ እንቀበለዋለን፡፡ የክርስትና ወጉ ነው፡፡ ይብላኝለት ወንድሙን ለሚያሰናክል ለዚያ ሰው፡፡ ፈጽሞ ባይወለድ ይሻለው ነበር፡፡
ማኅበሩ በትዊተር ገጹ ከለቀቃቸው መጣጥፎች መካከል ሦስቱ፣
 1. ምን ዓይነት ለውጥ ለቤተ ክርስቲያን? (ለግልጽ ውይይት የቀረበ)
by Deje Selam on Wednesday, September 7, 2011 at 11:59pm
 1. ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ።
by Deje Selam on Tuesday, October 4, 2011 at 1:11pm
(አብርሃም ሰሎሞን)
 1. የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሻሻል- ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ
by Deje Selam on Wednesday, October 5, 2011 at 10:03pm
(ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ)
ሲሆኑ፣ በተለያዩ ስሞች ቢጻፉም በይዘታቸው አንድ ናቸው፡፡ እነዚህን ለምሳሌ ጠቀስን እንጂ በግል ጋዜጦችና መጽሔቶች እንዲሁም በልዩ ልዩ ብሎጎቻቸው ተመሳሳይ አስተሳሰቦችን የሚያራምዱ ጽሑፎች በስፋት ተሠራጭተዋል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" ሴፕቴምበር 7/2011 Deje Selam በተባለው የትዊተር ገጹ "አቡነ ጳውሎስ ከመንበራቸው ቢነሱ . . . ለውጥ ለማምጣት ትልቅ ዕድል ይሰጣል"፤ ሲል፤ ኦክቶበር 5/2011 ደግሞ፣ በቀሲስ ወንድምስሻ አየለ አማካይነት "ልዩ ልዩ ፍላጎት ያላቸው አካላት ወሳኝ ተጽእኖ ሊፈጥሩ የሚፈልጉበትና ዛሬም ሊታይ ይገባዋል የምለው የቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዳይ ሲሆን ለዕርቅ የሚደረገው ጥረት እየቀጠለ በተረጋጋ ሁኔታ ከወዲሁ ውይይት ቢደረግበት እንጂ ቀኑ ሲደርስ መጀመር ለአላስፈላጊ ጫናዎች መጋለጥ ነውና ቢታሰብበት" በማለት በገሃድ አውጇል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" ጉዳዩን በዚህ ሳያበቃ በሴፕቴምበር 7/2011 ጽሑፉ "ቤተ ክርስቲያን የአሥር ዓመት መሠረታዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ወይም አብዮት መጀመር ይገባታል . . . አብዮታዊ ወይም መሠረታዊ እና ፈጣን ለውጥ ይሻላል"፤ ሲል የውስጡን ነግሮናል፡፡
ይኸው አብዮት አሁን ተጀምሮ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ የቤተክርስቲያኗ አመራር ፍጹም ወደ ሆነ "ማኅበረ ቅዱሳናዊ" አስተዳደር እንደሚቀየር ጽሑፎቹ ያመላክታሉ፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በቅርቡ በሚካሄደው የሲኖዶስ ጉባዔ አንድ የለውጥ ኮሚቴ እንደሚሰየም እና ኮሚቴውም ከአራት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የቤተክህነቱ ተቀጣሪ ያልሆኑ ነፃ ባለሙያዎች ብቻ የሚገኙበት ከ10 ያልበለጡ ሰዎች ያሉበት የጥናት ኮሚቴ እንዲያቋቁምና ለኮሚቴውም የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ ያለምንም ስስት ጠቀም ያለ በጀት ይመደብለት በማለት የልቡን ነግሮናል፡፡ እዚህ ውስጥ ማንኛውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ወይም የቤተክርስቲያን ሠራተኛ ለአስረጅነት ካልሆነ በስተቀር በኮሚቴ አባልነት ባይገባ ጥሩ ነው ካለ በኋላ፣ "በመረጃ ስብሰባውና ትንተናው የተማሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ተሳትፎ ብዙ ይጠቅማል"፤ በማለት ውስጥ ውስጡን በተማሩ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ስም ለግቢ ጉባዔያት የማኅበሩ አባላት በር እየከፈተ መሆኑን በይፋ ነግሮናል፡፡
ቤተክርስቲያንን እንደ አንድ የቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ የተመለከተው "ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተክርስቲያን ሊቃውንትንና ሊቃነጳጳሳትን አግልሎ ጥልቅ ዕውቀት የሚጠይቀውን የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ እና ተቋማዊ አስተዳደር ባልበሰሉ ለጋ ወጣቶች ገና ለገና ምናልባት ዲግሪና ዲፕሎም ስላላቸው ብቻ በመረጃ አሰባሰብ እና ትንተና ላይ ይሳተፉ ማለቱ የቱን ያህል ንቀት ያደረበት መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ "የዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር በመዋቅሩም ይሁን በይዘቱ የካህናት ይልቁንም የመነኮሳት ፍጹም የበላይነት የተንሰራፋበት ነው" ካለ በኋላ ይህንኑ ሃሣቡን ሲያጠናክር፣ ". . . የቤተክህነቱ ሰዎች የተማሩ፣ ሌላው ምዕመን ያልተማረ (ጨዋ) የነበረበት ማኅበረሰባዊ ዕውነታ ተቀይሯል፡፡ ዛሬ ዕውቀትን ከነገረ መለኮት መስክ አስፍተን ብንገመግም፣ ብዙ ዕውቀት ያለው በቤተክህነት ሰዎች አካባቢ ሳይሆን በጥንቱ "ጨዋ" ምዕመን ዘንድ መሆኑን እንገነዘባለን" በማለት የራሱን ዓለማዊ ዕውቀት፣ በመንፈሳዊው አመራር ላይ የበላይ የማድረግ ሕልሙን እንደዋዛ አውግቶናል፡፡
"የዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር በመዋቅሩም ይሁን በይዘቱ የካህናት ይልቁንም የመነኮሳት ፍጹም የበላይነት የተንሰራፋበት ነው" ለማለት ያነሳሳው ምክንያት ግልጽ ነው፡፡ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት የሆኑ እና በግቢ ጉባዔያት ስም ሲያሰለጥናቸው የነበሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከምረቃ በኋላ ሥራ በማፈላለግ ላይ ስለሆኑ በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ ሰግስጎ የሥራ ዕድል በመስጠት፣ እናት ቤተክርስቲያንን ከላይ እስከ ታች ጠፍንጎ ለመያዝ ነው፡፡ አንድ ጤነኛ ሰው ወይም ማኅበር ካላበደ በስተቀር የዘመናዊቷ ቤተክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር በመዋቅሩም ይሁን በይዘቱ የካህናት ይልቁንም የመነኮሳት ፍጹም የበላይነት የተንሰራፋበት ቢሆን አይጠላም፡፡ ምክንያቱም በቤተክርስቲያን አስተዳደር መንፈሳዊ ዕውቀት ቀዳሚው ነገር ነውና፡፡ ምናልባት ቀጣዩ ነገር የተቋማዊ አስተዳደር ክህሎት በሥልጠና ማዳበር ነው፡፡

ማንም ሲቪል ተነስቶ በሕዝባዊ ተሳትፎ ስም የመከላከያ ሠራዊትን ቦታ መቀማት እንደማይችለው ሁሉ፣ ክህነት የሌለው ማንም ሰው "ዲግሪ" አለኝና የቤተክርስቲያንን መዋቅር ልምራ ብሎ አያለቅስም፡፡
የሴፕቴምበር 7ቱ ጽሑፍ "የቤተክርስቲያን ሕግ ራሱ ችግር አለበት" ይልና፣ "ችግሩ የአፈጻጸም ነው ማለት ወደ ምን ዓይነት የስህተት አዙሪት እንደሚከት ከኢሕአዴግ መማር ይቻላል" በማለት እግረ መንገዱን የፖለቲካ ቅስቀሳውን አካሂዷል፡፡ ቀጥሎም በቀሲስ ወንድምስሻ አማካይነት "ለፖለቲከኞችና ተሀድሶዎች ራስ ምታት ሆኖ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን . . . " በማለት በሃይማኖት ሽፋን ምን ያህል ፖለቲካ ውስጥ እንደሚዳክር ራሱን በማጋለጥ አሳይቶናል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" ጠቅላይ ቤተክህነትን ባሻው መንገድ ለማተረማመስ እንዲመቸው እና የወጠንኩት የለውጥ አብዮት ይከሽፍብኝ ይሆናል ብሎ በመስጋት፣ "የመንበረ ፓትርያርክ ቅጥር ግቢ ጥበቃ ጉዳይ ለማሻሻያ ሥራው አሳሳቢ መሆኑ ፓትርያርኩን የሚያስወቅስና በመንፈሳዊው ዐውድ መከሠቱ አሳፋሪ ጉዳይ ሲሆን፣ በሲኖዶስ ደረጃ መታየት ባይኖርበትም፣ ለዋናው ጉዳይ እንዲረዳ ውይይቶች በሠላም እንዲከናወኑና ቀጣይ አፈጻጸማቸውም እንዲሠምር የጠቅላይ ቤተክህነቱ ጥበቃ ሙሉ ለውጥ ሊደረግበት ይገባል" በማለት፣ እንደልብ እንዳይጨፍር ጥበቃው ስጋት እንደሆነበት በሚያስገርም ሁኔታ ነግሮናል፡፡ እንደገና ደግሞ ዞር ይልና (አፕሪል 3/ 2011) በደጀሠላም ድረ ገጹ እንዳቅሚቲ መንግሥትን "ምንድነው የምንጠብቀው? ምን እስኪሆን? ለሀገራችንና ለክርስትናችን አንድ የለውጥ አብዬት ማቀጣጠል ያቅተናል? ዝም ብሎ ወሬ ምን ይሰራል? ከአረቦቹ እናንሳለን እንዴ? ሃገራችንንም ቤተክርስቲያናችንንም ነጻ ለማውጣት. . . "? እያለ፣ በፖለቲካ ሲሸነቁጠው የነበረውን ረስቶ "ለጊዜው መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ የግቢውን ጥበቃ ሲረከብ፣ የአስተዳደር ማሻሻያው ከተተገበረ ከዓመታት በኋላ ወደ መደበኛ የጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር ሊመለስ ይገባል" ይለናል፡፡
እዚህ ላይ "ማኅበረ ቅዱሳን" መልስ ሊሰጥበት የሚገባው አንድ ጉዳይ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅጥር ግቢ ጥበቃ ለምንድነው አሳሳቢ የሚሆነው? ጥበቃው አሳፋሪ ከሆነስ፣ ለምንድነው ሌላ ጥበቃ የሚያስፈልገው? ወይም የመንግሥት ተቀጣሪ ጥበቃ፣ እንዴት ነው መንፈሳዊውን ዐውድ ከሐፍረት የሚታደገው?
በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንበረ ፓትርያርክ አንድ ዩኒቨርሲቲን ወይም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትን የሚያህል ተቋም መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ የሀገር ውስጥ እና የልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ እንግዶች በየዕለቱ በሥነ ሥርዓት ይስተናገዱበታል፡፡ ስለዚህ፣ በር ላይ ቆሞ ለሠላምና ለሥራ የመጣውንና ያልመጣውን እየለየ የሚያስተናግድ ጥበቃ መመደብ ግድ ይላል፡፡ ወሮበላ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘው ብሎ የብፁዓን አባቶቻችንን የሌሊትና የቀን ልብሶቻቸውን ይዞባቸው እንዳይሮጥ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም ጥበቃ እንዲኖር ፕሮቶኮሉም ያዛል፡፡ እነ "ማኅበረ ቅዱሳን" ምን ለማድረግ አቅደውና ምን ተሰናክሎባቸው ነው፣ የጥበቃው መኖር አሳሳቢ የሆነባቸው?
አሁን "ማኅበረ ቅዱሳን" ሊታይ የሚገባው የራሱን ካቢኔ ጫካ ውስጥ አቋቁሞ ሕጋዊውን መንግሥት እንደሚዋጋ የጎሪላ ጦር ነው፡፡ ምናልባት ተሳክቶ ጦርነቱን በድል ቢደመድም፣ የሥልጣን ክፍተት (Power Vacuum) ሳይፈጠር ሚኒስትሮቹን ቦታ ቦታቸውን አስይዞ መፈንቅለ መንግሥቱን ባሳካ ማግስት የመንግሥት ሥራውን ለመቀጠል እንደሚመኝ አንድ ባዕድ አካል ነው፡፡
ትላንት ተወልዶ ሃያ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ልቡ ጣራ የደረሰው "ማኅበረ ቅዱሳን"፣ ለአሥራ ሰባት መቶ ዓመታት ያህል ፀንታ የቆየችውን እናት ቤተክርስቲያናችንን ከችግር እታደጋታለሁ በሚል ሰበብ የነበረንን መልካም ዕሴት በማጥፋት ወደ ባሰ ችግር እና ወደ ርስ በርስ መናቆርና አለመከባበር ዝቅተት ውስጥ ከቶናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ "ማኅበረ ቅዱሳን" ድብቅ አጀንዳዎች አሉት ስንል የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚመስላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አባላቱም ቢሆኑ እንደ ግመል ቅፍለት አንዱ አንዱን ከመከተል ውጪ ለምን ይሄ ይሆናል ብለው አይጠይቁም፡፡
ትላንት፣ ዛሬም፣ ነገም ነባሩ የቤተክርስቲያን መዋቅርና አስተዳደር እንዲቀጥል እንሻለን፡፡ ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ያለው መዋቅር ራሱን ከማንም ጣልቃ ገብነት ጠብቆ የቤተክርስቲያንን ሕልውና እንዲያስከብር እንፈልጋለን፡፡ የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የሕግ ማዕቀፍ እና ከፍተኛ ዕምቅ ችሎታ ያለው የሰው ኃይል እንዳለውም እናውቃለን፡፡ ቤተክርስቲያናችን የመንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ ዕውቀት አጣምረው የያዙ አገልጋዮች ባለቤት እንደሆነችም እንገነዘባለን፡፡ ያጋጠሙ እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችል ደረጃ ላይ እንደሆነች እናውቃለን፡፡ ስለዚህ፣ በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለማደንዘዣ ኦፕራሲዮን (Caesarian Surgery) ለማካሄድ ያሰፈሰፈውን የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት አደብ ግዛ እንለዋለን፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" የቤተክርስቲያን ችግር እንዲፈታ እና እንዲወገድ ሙሉ ፍላጎት ካለው፣ እጁን ከቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ያውጣ፡፡ በቤተክርስቲያን ጉያ ውስጥ ተወሽቆ ፖለቲካ ውስጥ መጨማለቁን ያቁም፡፡ የጠቅላይ ቤተክህነት ጥበቃ ትጥቁን ይፍታ ብሎ ከመጠየቅ ይልቅ የራሱን የ"ክተት ሠራዊት" አዋጅ ይግታ፡፡ ጨዋ የቤተክርስቲያን ልጅ መሆኑን ያሳይ፡፡ የ"ሁሉ ዐዋቂነት" እና ጣልቃ ገብነት አባዜውን እርግፍ አድርጎ ይተው፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም የራሱን ድርሻ እየተወጣ ሠላም የሰፈነበት አምልኮአችንን ልንከተል እንችላለን፡፡ ነገር ግን ብፁዓን አባቶችና አገልጋዮች በገለልተኝነት ተቀምጠው የቤተክርስቲያንን ተቋማዊ አስተዳደር "በእኔ አመራር እናስተካክለው" በማለት እና እነእከሌ የፕሮቴስታንታዊ - ተሀድሶ - ኑፋቄ አራማጆች ናቸው እያለ በሚከተለው የትርምስ ስትራቴጂ እስከወዲያኛውም ሠላም ሊሰፍን አይችልም፡፡
ከእናቶች መቀነት ደመወዝ እየተከፈላቸው መልሰው የራሳቸውን ቤተክርስቲያንና ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰድቡ እና የሚወጉ ሊቃነጳጳሳትም ሆኑ፣ ሌሎች ካህናት ከማኅበር ወይም ከቤተክርስቲያን አንዱን መምረጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ፖለቲካን ከሃይማኖት እያጣቀሱ በብልጣ ብልጥነት መሄድ አይቻልም፡፡ ቤተክርስቲያን ምዕመኖቿን "ለባለሥልጣናት ታዘዙ፤ ሥልጣን ከእግዚአብሔር ነውና" እያለች ታስተምራለች፡፡ ነገር ግን ኃላፊነታቸውን የዘነጉ አንዳንድ ሊቃነጳጳሳትና ካህናት፣ ራሳቸውን የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሎሌ በማድረግ አብረው፣ "ምንድነው የምንጠብቀው? ምን እስኪሆን? ለሀገራችንና ለክርስትናችን አንድ የለውጥ አብዬት ማቀጣጠል ያቅተናል? ዝም ብሎ ወሬ ምን ይሰራል? ከአረቦቹ እናንሳለን እንዴ? ሃገራችንንም ቤተክርስቲያናችንንም ነጻ ለማውጣት. . . "? በማለት የሚዘምሩ ከሆነ፣ ቤተክርስቲያናችንን ለቀው እንዲለይላቸው እንመክራቸዋለን፡፡
ቤተክርስቲያንም ኃላፊነታቸውን በዘነጉ እንደ አቡነ ገብርኤል ዓይነቶቹ ሊቃነጳጳሳትና እንደ የጅማው ቀሲስ ወንድምስሻ ዓይነቶቹ ካህናት ላይ ወቅታዊ ዕርምጃ ልትወስድ ይገባል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በቸልታ የሚታለፍ ከሆነ፣ ማንም ማንንም ከቤተክርስቲያን ማስወጣት ስለማይችል ትርፉ ሁለንተናዊ ቀውስና የሀገር ሠላም መታጣት ነው፡፡ ከዚያ የባሰም አደጋ ሊከሰት ይችላል፡፡
ክፉውን ያርቅልን!!!
from tinbitedaniel@religious.com

13 comments:

 1. Really! This is what you got? You are trying to change our faith and blame others who struggle to creat and modernize the system? Like your Protestant faith you are confused.
  Ben

  ReplyDelete
 2. አይ ፅንፈኛው የተሃድሶ ወይፈን የምትሰሩት ግራ ገባችሁ አይደል? በርቱ ካለዛ ደሞዝ አይኖራችሁም::

  ReplyDelete
 3. Abaselama is seems very angry.sorry,you are also going to fall down.it is also my wish to see you removed and fall down from our church.whatever you said about MK, we are so happy.B/c our father (God)is with them since he is always true.
  since you are not from our church(EOTC),so it is not allowed for you to contribute concerning about our church.you have to go to your concern church protestant like muluwongel,and so.That is your better place to seelp nicely for you.,.otherwise our church can not provide whatever you want.

  ReplyDelete
 4. ድሮ ጎንደርና ሸዋ ነበር የሚባለው አሁን ደግሞ ትግሬና ወሎ መሆኑ ነው:: አባ ሰላማዎች በጣም ትገርማላችሁ:: እንድህ የዘቀጠ ሃሳብ ታቀርባላችሁ እንዴ? ለመሆኑ እናንተ በቤተ ክህነት የአስተዳደር ንቅዘት የለም ነው የምትሉት? ማህበረ ቅዱሳንን እንደት እንደምትጠሉት በብዙ ጽሁፋችሁ አይቻለሁ ነገርግን ከናንተ የተሻለ ሃሳብ አላየሁም:: ግለሰቦችን በስም እየጠቀሱ ከመደገፍና ከመሳደብ በስተቀር::

  ReplyDelete
 5. hahahaha, abaselamoch libona amilak yisitachihu kemalet lela min tselot ale.

  May God be with all of us!

  ReplyDelete
 6. እናንተ ልታመጡት ከምትፈልጉት የሀይማኖት ለውጥ የማቅ የአስተዳደር ለውጥ በመጣና እናንተን ድራሻችሁን ባጠፉዋችሁ። ደግሞም አይቀርም። ጴንጤ ሁላ።

  ReplyDelete
 7. ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ይሁን ምን አያመሰግኗችሁም፡፡ እናንተ ግን እውነትን ከመጻፍ አትቦዝኑ፡፡

  ReplyDelete
 8. ማኅበረ ቅዱሳን ምንም ይሁን ምን አያመሰግኗችሁም፡፡ እናንተ ግን እውነትን ከመጻፍ አትቦዝኑ፡፡

  ReplyDelete
 9. please, call it mehabera sitan!

  ReplyDelete
 10. መቆየት ብዙ ያሳያል። አይ አባ ሰላማዎች! የነ ሊቁ ጎርጎርዮስ፣አትናቴዎስ፣ዮሐንስ አፈወርቅ እና የመሰሎቻቸው እናት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ እንደናንተ ያሉ በስሟ ክህደትን የሚነዙ፣ቅዱሳንን የሚያወግዙ፣ ለገንዘብ የሚቅበዘበዙ፣በድንቁርና የነቀዙ የመርገም ልጆች ተፈጥረውባት ማየታችን ምን ያህል በፅኑ መሰረት ላይ መመስረቷንና ጠላቶችዋ የበዙ መሆኗን ያሳዩንል እንጂ ከእምነቷና ከፍቅሯ የሚያናውፁን አይሆኑም።
  ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 11. አባ ሰላማዎች እንደምን ሰንብታችሁአል መቼም በየጊዜው የምታቀርቡት እውነተኛ መረጃዎች፤
  አንጄቴን ነው የሚያርሰው። ምክንያቱም እኔና እኔን መሰል የተዋህዶ ልጆች የምናየውን፣
  የምንሰማውንና የምንከታተለውን እውነት ስለሆነ የምትገልጡት። አንዳንድ የማህበሩ አባላት
  እንዲሁ በጭፍን የሚከተሉት ሲሆን፤ አንዳንዱ ደግሞ እውነት የሐይማኖት ሥራ የሚሰሩ መስሎአቸው፤
  አንዳንዱ ደግሞ የተረገመውን አላማ ይዞ በሐይማኖት ሽፋን ፖለቲካውንም ሆነ ሌብነቱን ለማካሄድ
  በመሆኑ፤ እናንተንና አንዳንድ ሚስጥራቸውን ያወቁባቸውን እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ሥም በማጥፋትና
  የተለያዩ ኢ- ክርስቲያናዊ ደባ ሲፈፅሙ እያየን ነው። ለማንኛውም እስከ ሞት ድረስ የወደደን አምላካችን
  አሸናፊ ነውና እኛም ለዚህ ፍቅር አምላክ እስከመጨረሻው ድረስ እውነቱን እንመሰክራለን። ከእንግዲህ
  ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በሐሰተኛ ፈሪሳዊያን የሐሰት ምስክር አይፈረድበትም። የሚመጣው ሊፈረድልንና
  ሊፈርድብን ነው። ለነገሩ ማህበረ ሰይጣን በቤተክህነታችን አካባቢ ምን ያለከሰከሰዋል\ ባህል ሚኒስተር
  ሄዶ ይስራ ከፈለገ። ምንም ያልተፈጠረውን ተፈጠረ እያለ ሽበር በህዘበ ክርስቲያኑ ከሚነዛ ማለቴ ነው።

  አባ ሰላማወች ከማህበረ ሠይጣን አባላት ምንም መልካም ነገር ስለማይጠበቅና የራሱን ድርጊት ለመሸፈን
  በሚሰጡት የሥድብ አስተያየት ምንም ሳይሰማችሁ ዘወትር እውነቱን ከማሳወቅ እንዳትቆጠቡ በማለት
  እውነተኛ ምክሬን እገልፃለሁ።

  የጌታችን ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

  ReplyDelete
 12. shame to see protestants creating a blog in the names of orthodox church

  ReplyDelete
 13. እኔን የገረመኝ ማህበረ ቅዱሳን ማነው; በማህበሩ ውስጥ የተሰገሰጉ ምናምንቴዎችን አፍርሰው ሊሰሩ የሚችሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን አውጋዥ ያደረጋቸው ; ይሄ ደሞ ሌላ ቤተክርስቲያንን እና ምዕመናንን ለማወናበድ የሚጠቀሙበት የማምታቻ ስልተ መሆኑ ነው; እባካችሁ ልካችሁን እወቁ የሚላቸው ተፋ ማሌት ነው እንጂ ቤተክርስቲያንን ላይ እንደዚህ አይፈነጩም ነበር ! እድሜ ልካቸውን የንፁሐንን ስም ማጥፋት ልማዳቸው ነው ዛሬም እንደ አባታቸው ዘርያዕቆብ በ14 እና 15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንፁሐን አባቶች በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የተደረገውን ግፍ ለመድገም የሚፈልጉ ዝርራዦች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ዘርያዕቆብስ የቅዱሱን አባት የእስጢፋኖስን አስከሬን አስወጥቶ አቃጥሎት የለ የዛሬዎቹ ልጆቹም በሰላም ወደ አምላካቸው የሄዱትን የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከሙታን መቃብር አስነስተው ሊያስወግዙ ተነሱ የማን ዘር ጐመንዘር አለ የሀገሬ ሰው የሚገርሙ ናቸው የናፈቀኝ መጨረሻቸው ነው፡፡
  የእግዚአብሔር ሰላም አይለየን

  ReplyDelete