Monday, October 17, 2011

በሁለት ስልት የቀረቡት የማኅበረ ቅዱሳን የክስ መዝገቦች ይፋ ሆኑ - - Read PDF

ሙሉውን የክስ ዝርዝር ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በጥቅምት 2004 .. በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲወገዙ ማኅበረ ቅዱሳን በክስ ስንክሳሩ ስም ዝርዝራቸውን ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብርቅዬ ሊቃውንት፣ በአገር ውስጥ ያሉ በውጪ አገር የሚኖሩ፣ ፖለቲከኞችና ምሁራን ሕያዋኑና የሞቱቱ ሁሉ ጉዳይ አስገራሚ ውዝግብ እያስነሣ ነው፡፡

ጥቂት በጥቂት ወደ እብደት እያመራ የሚገኘውና የሚይዝ የሚጨብጠው የጠፋው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በራሱ ስምና በአርኣያውና በአምሳሉ ጠፍጥፎ የሠራቸው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር ተብዬዎች ስም፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከእኛ በቀር ማንንም አንይ በሚል እብደት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያናችንን በሊቅነታቸው ያስጠሩ፣ ለአገርና ለወገን የሚያኮሩ መልካም ተግባራትን ያከናወኑ፣ ታላላቅ ሰዎችን ጭምር ይወገዙልን የሚል ጥያቄ ማቅረቡ ማኅበሩና ተከታዮቹ በምን ዐይነት ወራዳ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከማሳየቱም በላይ፣ የትክክለኛነት ልኩ እኛ ነን የሚል ግብዝነት የተሞላ አስተሳሰብ እንደ ተጠናወታቸው አመላካች ሆኗል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም የቀረበው የይወገዙልን የክስ መዝገብ ሙሉ በሙሉ ካሁን ቀደም ማኅበረ ቅዱሳን በተለያዩ ጊዜያት ሲያወራው የነበረው የራሱ ሐሳብ መሆኑን በውስጡ ካካተታቸው ሐሳቦች ተረጋግጧል፡፡
የክሶቹ ሁሉ ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ እየታወቀ ለምን ክሱን በሁለት ከሳሾች ስም ማለትም በአዲስ አበባ ሰንበት ተማሪዎች ስም እና በማኅበረ ቅዱሳን ስም ማቅረብ አስፈለገው? ለምን ሁሉንም በራሱ ስም አላቀረባቸውም? የሚሉትን ጥያቄዎች ማስነሣቱ አልቀረም፡፡ በሁለቱ የክስ መዝገቦች የተዘረዘሩትን ግለሰቦችና ማኅበራት ስም፣ ተገኘባቸው ከተባለውኑፋቄ ጋር ማስተያየት ብቻ ሳይሆን የትኞቹ ስሞች በየትኛው የክስ መዝገብ፣ በማን አቅራቢነት ይቅረብ የሚለው ሆነ ተብሎ የተደረገ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ ሰንበት ተማሪዎች ስም የቀረበውን ክስና የተከሰሱትን ሰዎች ማንነት ከተመለከትን በጣም ልንሥቅ፣ ልናዝን፣ ልንበሳጭ፣ ብቻ ሌሎችም ልዩ ልዩ ስሜቶች ሊሰሙን ይችላሉ፡፡ እንዲህ የተደረገው ደግሞ የሰንበት ተማሪዎች ልጆች ናቸው፤ ያሻቸውን ሳያገናዝቡ ይናገራሉ ተብሎ የማኅበረ ቅዱሳን የልብ ሐሳብ በልጅ ደንብ እንዲወሰድ ተፈልጎ ይሆናል፡፡ ከኋላችን ሚሊዮኖችን አሰልፈናልና የምንለውን ሁሉ ፈጽሙ ለማለትም ይመስላል፡፡ እውነታው ግን ማኅበሩ እስከ የት ድረስ እንደሚያስብና በልቡ የያዘውን እኩይ ተግባር በሰንበት ተማሪዎች አስታኮ መናገር እንደ ፈለገ አስረድቷል፡፡     

ማኅበረ ቅዱሳን በስም የጠቀሳቸውን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ታላላቅ ሰዎችን ይወገዙ ለማለት እርሱም ሆነ በስማቸው የሚነግደው የአዲስ አበባ ሰንበት ተማሪዎች እነማን ናቸው? የሚለው እስካሁን ያልተፈታ፣ ነገር ግን አሁን ሊፈታ የቀረበ ጥያቄ ሆኗል፡፡ ሳይማር ሁሉን አውቃለሁ የሚለውና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሥርዐት በዘመናዊ ትምህርት ዲግሪና ዲፕሎማ እመዝናለሁ፣ እኔ ከማምነው ውጪ የሚያምንና የሚያስተምር ሁሉ የተሳሳተ ነው በሚል የብዙዎችን ስም እያጠፋ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሊቃውንት ድኻ ለማድረግና በእርሱ ወገበ ነጮች ሊሞላ ታጥቆ የተነሣው ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያናችንን አይታ ወዳማታውቀው ቀውስ ውስጥ ሊከታት የእውር ድንብሩን እየተወላከፈ ይገኛል፡፡ ዐይኑን በጥቁር ጨርቅ ግጥም አድርጎ አስሮ እኔ እንደማየው ማን ያያል? ስለዚህ ተከተሉኝ ብሎ የሚመጻደቀው፣ ከፍ ብሎ የማይጠየቀው፣ ዝቅ ብሎ የማይጠይቀው፣ ጎጋውና ዕውር ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ተያይዘው …’ በተባለው መሠረት የዕውሮች መሪ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ስማቸውን ጠቅሶ ይወገዙልኝ ያላቸው ሊቃውንት ጉዳይ የእርሱ ማንነት በከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተመዝኖበታል፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ዐይኖች ለመጫወት እንደሚከጅል ጅላጅል ተቆጥሮ በዐይን ቀልድ የለም ሊባል ይገባዋል ሲሉ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡

ከሁሉም ያስገረመው ማኅበሩ ዛሬ በሕይወት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ያንቀላፉትን ሁሉ ሙት ወቃሽ ሆኖ ይወገዙ ማለቱ ነው፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉትንና በሰሜን ኢትዮጵያ የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑትን፣ በሥጋ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ያሉ የሚመስሉትን፣ በመንፈስ ግን ከእርሱ ተለይተው እርሱ ከሚያሳድዳቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ጎን የቆሙትን ሊቀ ጳጳስ ይህን መረጃ በእጃችን ስላስገቡልን ከልብ እያመሰገንን፣ ባላዋቂው ማኅበር የተከሰሱትን የአንዳንዶቹን ስምና የተከሰሱበትን ኑፋቄ ለአብነት ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡


በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት መካከል

·         መሪጌታ ፀሓይ ብርሃኑ (ማሳቹሰትስ)

በኦርጋን መዘመር ክልክል ነው የሚሉ እጅግ ተሳስተዋል በማለት የጻፈ፡፡ (ገጽ 19)

ሊቁ መሪጌታ ፀሐይ በዜማ ሊቅነታቸው ስለ መዝሙርና የዜማ መሣሪያዎች ቢናገሩ ያምርባቸዋል፤ ሙያቸው ነውና፡፡ የኦርጋንን ምንነትና ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ ስትገለገልበት የኖረ የዜማ ዕቃ መሆኑን ከዚህ ቀደም በጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ጎጋው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ከሜዳ ተነሥቶና በጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ ስልት በኦርጋን መዘመር ኑፋቄ ነው አለ፡፡ ተው እንዲህ በማለትህ ተሳስተሃል ያሉትን ሊቁን የተሐደሶ ኑፋቄ አራማጅ ሲል ፈረጃቸው፡፡ ስለዚህ ጎጋው ማኅበረ ቅዱሳን በሳተበት ነገር ተሳስተሃል ያሉት ሁሉ ኑፋቄ እንደተገኘባቸው ተቆጥረው ተሐድሶ ይባላሉ ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ የሚሄድ በሌላው የቤተ ክርስቲያን ልጅ ላይ የቀረበውን ኑፋቄ ደግሞ እንመልከት፡፡


·         ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ የነበረና ከኮሌጁ የተባረረ)፡፡ ማኅበረ ሰይጣን በተባለ መጽሐፉ ኑፋቄን ያሰራጨ (ገጽ 24) ተብሏል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ከእርሱ ትምህርትና ልማድ ውጪ የሚኖረውን ሁሉ አንድ ወጥመድ ሠርቶ ከቤተ ክርስቲያን የሚባረርበትን መንገድ ይፈልግና በኋላ ላይ መናፍቅ ሆኗል ሲል ይፈርጀዋል፡፡ ዲያቆን ሙሉጌታን ከመጀመሪያው ሲያሳድደው የነበረውና ከኮሌጅ እንዲወጣ ምክንያት የሆነው ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ዲያቆኑ ከተባረረ በኋላ የዚህን እኩይ ማኅበር ግብር ለመግለጥ ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን የሚል መጽሐፍ ጽፎ ማኅበሩን ተቸ፡፡ ማኅበሩን በሰይጣናዊ ግብሩ መተቸት ኑፋቄ የሚሆነው ታዲያ እንዴት ነው? ሰንበት ተማሪዎች ሆይ የመጽሐፉን ርእስ ማኅበረ ሰይጣን ብቻ ብላችሁ የጠራችሁትና ማኅበረ ቅዱሳን የሚለውን የገደፋችሁት ለምን ይሆን? እርግጥ ልክ ናችሁ ራሳችሁን መስደብ ይሆናል፡፡ ለዚህ እኮ ነው እኛም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ይህን ክስ የመሰረተው ማኅበረ ቅዱሳን ነው የምንለው፡፡·         ደቂቀ እስጢፋኖስን በመደገፍ የቤተ ክርስቲያኒቱንና የዘረያዕቆብን ታሪክ በማዛባትና በዓላትን በመቃወም የጻፉ ተብለው በአንድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ደግሞ፡-

ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌ

መምህር ገብረ ዮሐንስ ገብረ ማርያም

ካህሣይ ገብረ እግዚአብሔር

ግርማ ኤልያስ (ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ)

ናቸው፡፡ ይገርማል! ኑፋቄን ከታሪክ መለየት የተሳነው የወገበ ነጮች ስብስብ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን እነዚህን ታላላቅ ሊቃውንት የተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች ሲል መፈረጁ ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ከማጋለጡም በላይ የኑፋቄ ትርጉም ከቶ ያልገባውና የዐይናችሁ ቀለም አላማረኝም በሚል ብቻ ከመሬት ተነሥቶ ያገኘውን ሁሉ መናፍቅ ማለት የሚቀናው ግብዝ ማኅበር መሆኑን ያመለክታል፡፡ እስከ ዛሬ ተዛብቶ ይቀርብ የነበረውን እውነተኛ ታሪካችንን ከተቀበረበት ማውጣትና ሐቁ እንዲወጣ ማድረግ የጽድቅ ስራ እንጂ መች መናፍቅነት ነው፡፡ በወጣው ታሪክም ማን መናፍቅ ማን አማኝ መሆኑ ከፍሬው እየተለየ ነው፡፡ እናንተና አባቶቻችሁ ለሰው በላው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጽላት የቀረፃችሁበት፣ መልክእ የደረሳችሁበት፣ የሌለውን የቅድስና ማዕርግ ሰጥታችሁ እንዲመለክ ያደረጋችሁበት የታሪክ ምዕራፍ ሊዘጋ ተቃርቧል፡፡ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋዮችና እስከ ሞት ድረስ ስለ ስሙ መከራን የተቀበሉት ሰማዕታተ ወንጌል ደቀቀ እስጢፋኖስ ግን ገድላቸው እያበራ ታሪካቸው እየጎመራ በመሄድ ላይ ነው፤ እኛንም ወልዷል፡፡  

·         የተሐድሶዎቹን መጻሕፍት በመደገፍ አስተያየት የሰጡ በሚለው የክስ ጭብጥ ከተከሰሱት መካከል፡-

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ይገኙበታል (ገጽ 25)

መቼም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አስተያየት የሰጡበት መጽሐፍ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌ ደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፕሮፌሰሩ መጽሐፉን አንብበው የተሰማቸውን አስተያየት ሰጡ፡፡ አስተያየት የሰጡት ከሃይማኖት አንጻር ላይሆን ይችላል፤  ምናልባት ከፖለቲካ ወይም ከኅሊና ፍርድ አንጻር እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ከሃይማኖት አንጻርም ቢሆን አስወጣው! አውግዘው! በለው! ግደለው! በሚለው በእናንተ አስተምህሮ ካልሆነ በቀር ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ትክክለኛ ነበር የሚል ሰው ይገኛል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ደግሞ ሃይማኖተኛ ሳይሆን ልክ እንደ እናንተው ማኅበር ሃይማኖትን ለፖለቲካው ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ አምባገነን ንጉሥ ነው፡፡ ለሥልጣኑ ሲል ቤተክርስቲያን የማታውቀውን የስሕተት ትምህርት በጉልበት ያስገባውን፣ አምልኮተ ደስክን አጠፋለሁ በሚል ተንቀሳቅሶ የስም ለውጥ በማድረግ አምልኮተ ማርያምና አምልኮተ መስቀልን በማስገባትና በማስፋፋት ቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊ ወደሚመስል ውስጡ ሲፈተሽ ግን አምልኮ ባዕድ  ወደሆነ ሌላ ልምምድ የመራውን፣ የቅዱሳንን ደም በግፍ ያፈሰሰውን ግፈኛ ንጉሥ፣ በሃይማኖት ሽፋን ለፖለቲካው ሲል የልጆቹን ደም ሳይቀር የጠጣውን ሰው በላ ንጉሥ ፕሮፌሰር መስፍን እንዴት አድርገው ጻድቅ እንዲሉላችሁ ነበር የጠበቃችሁት? የማይገለጥ የተሰወረ የለምና ጻድቁን ጻድቅ ኀጥኡን ኀጥእ ማለት እውነተኛ ምስክርነት ነው፡፡ ለእናንተ ግን መናፍቅነት ቢሆን ምንም አይገርምም፡፡ ልካችሁ እስከዚህ ድረስ ነውና፡፡

ምነው ታዲያ በነካ እጃችሁ አቦይ ስብሐትም ይወገዙልን ያላላችሁት? መንግሥት በፖለቲካ ውስጥ ገቡ እንዳይላችሁ ፈራችሁ እንዴ? አቦይ ስብሐትን በዚህኛው የክስ መዝገብ ብቻ ሳይሆን ከላይ በተጠቀሰው በዲያቆን ሙሉጌታ የክስ መዝገብም እኮ ልትከሷቸው ትችሉ ነበር፤ ምክንያቱም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ ነው የሚል ኑፋቄ ጋዜጣ ላይ ጽፈዋል እኮ!

ሙት ወቃሹ ድንጋይ ነካሹ ማኅበረ ቅዱሳን

ሌላው ማኅበረ ቅዱሳን በተሐድሶነት የፈረጃቸው በእርሱ አፍ ሊጠሩ የማይገባቸው ስመ ጥር ቀደምትና ደኀርት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ ነገር ግን ማኅበሩ ካራ ታጣቂ ወላጆቹ ሲያወሩ የሰማውን ብቻ ይዞ አንቱ የተባሉትንና ታላቅ ክብር የተጎናጸፉትን አበው ባልታረመ አንደበቱ አንተ እያለ ከፍ ዝቅ ሊያደርጋቸውና ሊያዋርዳቸው ሞክሯል፤ ሆኖም ያዋረደው ራሱን ነው፡፡

በዚህ የክስ መዝገብ ስማቸውን ከዘረዘራቸው ሊቃውንት መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-

አለቃ ተክለ ጽዮን፣

አለቃ ዓፅመ ጊዮርጊስ፣

አለቃ ክፍለ ጊዮርጊስ፣

አለቃ ኪዳነ ወልድ (ብዙ ጊዜ መዝገበ ቃላታቸውን መጠቀሙ አልቀረም)

ዐቃቤ ሰዓት ከብቴ፣

ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (ከዚህ ቀደም ቤተክርስቲያንህን ዕወቅ በሚለው የማኅበሩ መጽሐፍ ላይ ያተመውን የጳውሎስን ሥዕል የወሰደው ጥሩ ምንጭ ከተሰኘው የብላቴን ጌታ ኅሩይ መጽሐፍ ላይ ነው)

አለቃ ተወልደ መድኅን ገብሩ፣

አለቃ ታየ ገብረ ማርያም፣

ከንቲባ ገብሩ ደስታ፣

ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣

አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ፣

መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ

ዓለማየሁ ሞገስ (ዓለማየሁ ሞገስ ከጻፏቸው መጻሕፍት መካከል ብዙዎቹ ለማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ ላይስማሙ ይችላሉ፤ ነገር ግን ለምን አልሰለምሁም? (ገጽ 4 25) የሚለው መጽሐፍ ምናቸውን ነካና ነው የጠቀሱት? ነው ወይስ ማኅበሩ ሌላም ተልእኮ ይኖረው ይሆን? ከዚህ ቀደም ጅማ ላይ በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል የተደረገውን ግጭት ተከትሎ በጋዜጣው ላይ ባወጣው ርእሰ አንቀጽ ላይ ስለጉዳዩ ብቻ ከመጻፍ ይልቅ ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ በማለት ተሐድሶ መናፍቃን ያላቸውን ወገኖች ያብጠለጥል እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ የእስልምና አክራሪዎችን እንቅስቃሴ የውሻ ያህል ተመልከቶ የጅቡን ድርሻ አለቦታው ተሐድሶ መናፍቃን ላላቸው ወገኖች መስጠቱ አስተዛዝቦ ማለፉ ይታወሳል፡፡

በውጭ አገር የሚኖሩና ይወገዙልኝ ሲል የፈረጃቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ስም ዝርዝር

·         መልአከ ብርሃን ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
·         አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል (ቆሞስ) አሁን የኢ///// የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ
·         ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኀይሌ
·         አባ መዓዛ በየነ (ቆሞስ)
·         ሊቀ ማእምራን / አማረ ካሣዬ
·         መጋቤ አእላፍ መክብብ አጥናው
·         ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
·         ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ
·         አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ
·         ቄስ ልዑለ ቃል አካሉ
·         ቄስ መላኩ ባወቀ
·         አባ ቀፀላ መንግሥቱ
·         አባ ገሪማ ተስፋዬ
·         ቄስ እንግዳ ቸሩ
·         አባ ላእከ ማርያም አስማረ
·         ዲ/ን በእደ ማርያም እጅጉ

በተመሳሳይ ሁኔታ በአገር ውስጥ ያሉና ይወገዙልኝ ሲል የከሰሳቸው 40 በላይ የሚጠጉ ግለሰቦች ናቸው፡፡35 comments:

 1. wey mak? maferiya mahebere!! likun hulu menafeke belo Teter lebese hone liker new? yasazenal?

  ReplyDelete
 2. አረ እንዴት ያለ ነገር ነው እነዚህ ሰዎች ታወሩ እኮ ብለው ብለው ከሙት ጋር ውጊያ ገጠሙ ሙት ወቃሽ ድንጋይ ነካሽ የሚለውን ተረት አልሰሙም ምናልባትም እኮ አይሁድ የክርስቶስን መቃብር ከፍርሀት የተነሳ እንዳሥጠበቁ እነርሱም መቃብራቸው ይጠበቅልን በእነርሱ ስጋት ገብቶናል ብለው ያስወሩ ይሆናል፡፡ ያልታደሉ፡፡

  ReplyDelete
 3. አረ እንዴት ያለ ነገር ነው እነዚህ ሰዎች ታወሩ እኮ ብለው ብለው ከሙት ጋር ውጊያ ገጠሙ ሙት ወቃሽ ድንጋይ ነካሽ የሚለውን ተረት አልሰሙም ምናልባትም እኮ አይሁድ የክርስቶስን መቃብር ከፍርሀት የተነሳ እንዳሥጠበቁ እነርሱም መቃብራቸው ይጠበቅልን በእነርሱ ስጋት ገብቶናል ብለው ያስወሩ ይሆናል፡፡ ያልታደሉ፡፡

  ReplyDelete
 4. የፈጠራ ክሳችሁን አቁሙ። እውነት ማኅበሩ ይህን አድርጎ ቢሆን ኖሮ መረጃውን ስካን አድርጋችሁ ፖስት ባደረጋችሁት ነበር።

  ReplyDelete
 5. Mane:Tekel:Fares:

  ReplyDelete
 6. Awrew!! Orthodox meslo mekreb gn kihdetin mastemar ye Aba Selama blog mefekir.

  If u have the truth teach us in the true way, but not like this way. [memsel yediabilos enji mechem yikrstina aidelem]

  Haimanot sheket aderegachut.

  Long live Mahibere Kidusan!!!!

  Egzihabher Ethiopianina ezbochuan yibark.
  Minfkinan besilela melk yemifetsimutin lib yistilin.
  yihininm blog Egzihabher yastagsilin, letsehafiwm libuna yistilin

  ReplyDelete
 7. yigermal! gin enezih hulu yetehadiso aramaj honew new weys agar lemaggnet yetezerezerut? miknyatum yeleyelachew menafikan sim endalebet meredat echilalehu.lemanegnawim letinkake zirzru lebetekirstian yitekimalina meterteru aykefam. lemanegnawim enameseginalen.

  ReplyDelete
 8. አመሰግናለሁ አባ ሰላማዎች ለዚህ መረጃ:

  አባ ሰላማዎች እንደምን ሰንብታችሁአል መቼም በየጊዜው የምታቀርቡት እውነተኛ መረጃዎች፤
  አንጄቴን ነው የሚያርሰው። ምክንያቱም እኔና እኔን መሰል የተዋህዶ ልጆች የምናየውን፣
  የምንሰማውንና የምንከታተለውን እውነት ስለሆነ የምትገልጡት። አንዳንድ የማህበሩ አባላት
  እንዲሁ በጭፍን የሚከተሉት ሲሆን፤ አንዳንዱ ደግሞ እውነት የሐይማኖት ሥራ የሚሰሩ መስሎአቸው፤
  አንዳንዱ ደግሞ የተረገመውን አላማ ይዞ በሐይማኖት ሽፋን ፖለቲካውንም ሆነ ሌብነቱን ለማካሄድ
  በመሆኑ፤ እናንተንና አንዳንድ ሚስጥራቸውን ያወቁባቸውን እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ሥም በማጥፋትና
  የተለያዩ ኢ- ክርስቲያናዊ ደባ ሲፈፅሙ እያየን ነው። ለማንኛውም እስከ ሞት ድረስ የወደደን አምላካችን
  አሸናፊ ነውና እኛም ለዚህ ፍቅር አምላክ እስከመጨረሻው ድረስ እውነቱን እንመሰክራለን። ከእንግዲህ
  ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ በሐሰተኛ ፈሪሳዊያን የሐሰት ምስክር አይፈረድበትም። የሚመጣው ሊፈረድልንና
  ሊፈርድብን ነው። ለነገሩ ማህበረ ሰይጣን በቤተክህነታችን አካባቢ ምን ያለከሰከሰዋል\ ባህል ሚኒስተር
  ሄዶ ይስራ ከፈለገ። ምንም ያልተፈጠረውን ተፈጠረ እያለ ሽበር በህዘበ ክርስቲያኑ ከሚነዛ ማለቴ ነው።

  አባ ሰላማወች ከማህበረ ሠይጣን አባላት ምንም መልካም ነገር ስለማይጠበቅና የራሱን ድርጊት ለመሸፈን
  በሚሰጡት የሥድብ አስተያየት ምንም ሳይሰማችሁ ዘወትር እውነቱን ከማሳወቅ እንዳትቆጠቡ በማለት
  እውነተኛ ምክሬን እገልፃለሁ።

  የጌታችን ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

  ReplyDelete
 9. Abet abet lsemayu nigus

  ReplyDelete
 10. mk lalkesesachew teteyaki aydelem. mk yale mereja mannm aykesm. lemikesachew mulu mereja alew. shi btaweru yemiyashenfew ewnet slehone bekentu atdkemu.

  ReplyDelete
 11. Gud bel gonder ale Yagere sew Yehe Yesettan mahebere Yelekefewe Yeaganenete menfese kemutan gar yalatemewe jemer aydel?

  ReplyDelete
 12. እረ እንዳውም በጣም ትንሽ ሰው ነው ያሉት እንደነሱ እኮ ማህበረ ቅዱሳን ካልሆነ እግዚሃብሄር የማይስማው ነው የሚመስላቸው በመስረቱ ነገሩ የጠፋው እኮ ከስም አወጣጣቸው ጀምሮ ነው በነሱ ቤት የቤተ ክርስቲያን ተቆርቅሪ እነርሱ በቻ ናቸው በነ ዘመድኩን አጨብጫቢነት ይቀጥሉ ክርስትና ሳትነሳ ልታቕቁም ሄደች ይላል ያገሬ ሰው

  ReplyDelete
 13. i am from Eurpoe brothers and sisters . i am one of the reformer but why not they include my name ? why i need yebatoch wog yedersye..
  mk God bless you . you guys you loose your church fathers , youare efoyet , killing their fathers.

  ReplyDelete
 14. ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ትናንት አኮ ማቅን የመሰረቱ ስትሉ ነበር:: የዛ ጊዜ የፃፋችሁት ወይም ይሄ ውሽት ነው አይደል? አይ የውሽታም ነገር ትናንት ያለውን ዛሬ ይረሳል::

  ReplyDelete
 15. what about the key tehadiso menafkan like aseged, begashaw, tiztaw all of whom have contributed to create this blog(aba selama) sponsored by protestant menafkan organizations like mulu wongel, mekaneyesus, kale hiwot....

  ReplyDelete
 16. don't worry! God is working againt MK. The truth is coming. God's saints are going to be happy. It is time to thank God. We see the glory of God on His saints suffering from false witnesses against them. Thank you God!Thank you God!Thank you God!

  ReplyDelete
 17. እናንተ ግን ያልገባችሁ አንድ ነገር አለ፡፡ ከመዋሸት፤ ከመሳደብ እና ስም ከማጠፋትችሁ በፊት ማወቅ የሚገባችሁ እውነት አለ፤ እስቲ አንድ ጠያቄ ልጠይቃችሁ፤ ለመሆኑ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከሰንበት ት/ቤቶች ቀድሞ የተፈጠረው ማን ነው? በአማካይ 50 እና 60 ዓመት ከዛም በላይ ዕድሜ ያላቸው ብዙ ሰ/ት ቤቶች አሉ እኮ፡፡ እንዴት ነው በአምሳሉ ጠፍጥፎ የሠራቸው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር ተብዬዎች ብላችሁ ለመናገር የደፈራችሁት ደሞ የዚህች ቤ/ክርሰቲያን ተቆርቋሪ እና አባላት ማኀበረ ቅዱሳን ብቻ ናቸው ያላችሁ ማን ነው? ፊለፊት ስላገኛችሁት ማኀበረ ቅዱሳንን አናት አናቱን ለማለት ተመቻችሁ እንጂ የዚህች እውነተኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ተቆርቋሪ ልጆች እነሱ ብቻ ከመሰሉዋችሁ በጣም ተሳስታችኋል፡፡
  ተጨባጭ ያልሆነ የፈጠራ ወሬ ይዛችሁ ብጥብጥ ለመፍጠርና ሰውን ከማሳዘን ብትቆጠቡ ጥሩ ነው፡፡ ደሞ እውነትና ንጋት አይደል እንዴ የሚባለው ማስረጃ ካላችሁ ይዛችሁ ማስነበብ ነው፡፡ ባዶና ገለባ የሆነ ተራ የስድብ ዘገባችሁ ይሰለቻል፡፡

  ReplyDelete
 18. አባ ሰላማወች ጽሁፎቻችሁ በቤተ ክርስቲያን ስላለው ችግር ሳይሆን ማ/ቅን ማጥላላት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው:: ከላይ የዘረዘራችኋቸውን አብዛኛዎቹን እናውቃቸዋለን:: አንዳንዶቹ ከቤተ ክርስቲያን ቀድመው የተለዩ የተወሰኑት ደግሞ መናፍቅነታቸውን ራሳቸው በጻፏቸውና በተገኙባቸው መድረኮች ያረጋገጡ ናቸው እዚህ አሜሪካ ራሳቸውን ኦርቶዶክሳውያን አድርገው በራሳቸው መንገድ እያገለገሉ ነው እናም እናንተ ይህን አገልግሎታቸውን ያለችግር ያለስህተት እዚህ የደረሰ ነው የምትሉን :: ትገርማላችሁ::
  ማ/ቅዱሳንም የሚያምኑበትን እናንተም የምታምኑትን ያለመነቃቀፍ ማድረግ አትችሉምን:: ማ/ቅ ማርያም ንጽህት ቅድስት ናት ከልጇም ታማልደናለች ይላል እናንተ ደግሞ ከኢየሱስ ሌላ አማላጅ የለም ትላላችሁ:: የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ የትኛውን እንደምታራምድ አጣርቶ ከሷ ጋ ያልተስማማው የራሱን መንገድ መከተል ነው:: ነገር ግን የሚያምኑበትን በግልጥ አለማስቀመጥና ተመሳስሎ መኖር ከጌታችን ከመድኃኒታችን ትምህርት ጋራ አይጣጣምም ይህን መንገድ የተከተሉት ደግሞ ከእኛ አገር በስተቀር በቀረው የአፍሪካ ሀገሮች ወንጌልን እየሰበኩ አገሩን ከኋላቸው ላለው የቅኝ አገዛዝ አረመኔና ጨካኝ ወታደር ያስረከቡት ወንጀላውያንን ያስታውሰናል:: እናም እባካችሁ ዓላማችሁን ከጽሁፎቻችሁ ተረድተናቸዋልና ለቀቅ አድርጉን:: አሁን እየተከተላችሁ ያላችሁት ደግሞ ማ/ቅን የሚጠሉላችሁ ሌሎች ወገኖችን ጎትቶ ማግባት ነው:: ማ/ቅን የሚጠሉት አጥብቀው እንደሚጠሉት ሁሉ የሚወዱትም እንደዛው ነው:: ከናንተ ጥረት ግን ብዙ ደጋፊ ያፈራበታል::
  ሙሉ

  ReplyDelete
 19. ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ትናንት አኮ ማቅን የመሰረቱ ስትሉ ነበር:: የዛ ጊዜ የፃፋችሁት ወይም ይሄ ውሽት ነው አይደል? አይ የውሽታም ነገር ትናንት ያለውን ዛሬ ይረሳል:: this is right. God bless mahebere kidusan.

  ReplyDelete
 20. ይገርማል! ለመሆኑ ይህን ሁሉ ሰው ማነው ያወገዘው? ምናልባት እኒያ በኤግዚቢሽን ማእከል ሲያብዱ የነበሩት መነኮሳት ካልሆኑ በቀር በተገቢው መንገድ ተወግዞ የተለየ የለም፡፡ ይህ ሁሉ ግን በማኅበረ ቅዱሳን ስሙ የጠፋ ነው፡፡ ስለዚህ ምናለ ማኅበረ ቅዱሳን የሰደባቸውን ሰዎች ቅዱስ ሲኖዶስ አወገዘ ማለት ብናቆም፡፡ ውግዘት ሌላ ስድብ ሌላ፤ ማቆች ልብ ይስጣችሁ!

  ReplyDelete
 21. Thank you Mulu.
  For this tehadiso menafeqane MK is a code word describe all OT church and it's beliver. That's why every day they open their filthy mouth on everything on our chuch. Be it zeta yaqob, abune teklehaymanot or Mk for that matter. Our difference is clear it start with Jesus. We don't have same teaching about him and st Mary. So they are not OT child rather they are Pente. However, instade of attacking our church they start using a code word MK to attack our church. That's why they mention Mk everytime.

  ReplyDelete
 22. From what I know Dn. Hailegebriel is "Tehadiso" which I can witness. I know also Dn. Solomon of the Egizabher Abe. He has some problem but is knowledgable preacher.

  ReplyDelete
 23. ማኅበረ ቅዱሳን በደመነፍስ ተኩስ ጥይት እየጨረሰ ነው


  በአፀደ ነፍስ ያሉ አባቶች ጭምር ይወገዙልኝ ሲል አመለከተ  የውግዘቱ ሃሣብ እነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝንም ያካትታል  ክሱ የቀድሞውን ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማርያምን አለማካተቱ አስቆጭቷል

  ራሱን የቤተክርስቲያንና የሃይማኖት የበላይ ጠባቂ አድርጎ የሰየመው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የውር ድንብሩን በመወራጨት ላይ መሆኑን ድርጊቱን ያስተዋለ ሰው ይረዳል፡፡ ለዓመታት ሲሳደብ፣ ሲራገምና ወንድሞችን ሲከስና ሲያሳድድ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን "እኔ እኮ ያለመረጃ ሰውን አልከስም" በሚል ስሜት ለጠቅላይ ቤተክህነት የክስ ፋይል ማስገባቱን ከራሱ እና ከሌሎች አካላት ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ በማኅበረ ቅዱሳን እና በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር ተብዬዎች ስም የገባው የክስ መዝገብ በርካታ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን፣ የተከበሩ አባቶችንና ታዋቂ ምሁራንን ያካትታል፡፡  ከውጊያ እንደሚሸሽ የጦር ሠራዊት የኋልዮሽ ጥይቱን በጭፍን በማርከፍከፍ ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን "ያገኘውን ያግኝ" በሚል ስሜት በክሱ ውስጥ አሰስ ገሰሱንም በማካተት የበርካታ ሰዎችን ስም ጠቅሷል፡፡ ስማቸው ከተካተቱት ሰዎች ውስጥ፣ በሕይወት የሌሉና ከሞቱ ብዙ ዓመታት ያስቆጠሩ ምሁራን ይገኙበታል፡፡ ክእነዚህም መካከል፣ ታዋቂው ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ ከንቲባ ገብሩ ደስታ፣ ይጠቀሳሉ፡፡ በሕይወት ካሉት፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምም አልቀረላቸውም፡፡  ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት መካከል በሕይወት የሌሉት አለቃ ዐጽመ ጊዮርጊስ፣ አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ፣ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ፣ የሚገኙበት ሲሆን በሕይወት ካሉት መካከል፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ ተካተዋል፡፡  እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አንድ ካህን፣ አገልጋይ ወይም ምዕመን የአስተምህሮ ወይም የአምልኮ ህጸጽ ሲገኝበት በመጀመሪያ ይመከራል፡፡ በሚሰጠው ምክር አልመለስም ካለ እና በአቋሙ ከጸና በሊቃውንት ጉባዔ አቅራቢነት በቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የሚመከርበት ወይም ከስህተቱ የሚመለስበት ዕድል ስለሌለ፣ ጥፋቱን ሳያምን በደፈናው አይወገዝም፡፡ ሟች ከሞተ በኋላ አይወቀስም፡፡ ግዝት እንኳን ቢኖርበት ከሞተ በኋላ ከግዝቱ የተፈታ ነው፡፡ አጅሬ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ለዚህ አዲስ ሥርዓት ሠርቶ፣ ከሞቱ በርካታ ዓመታትን ያሳለፉ ሊቃውንት አባቶችን ይወገዙልኝ በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ መሆኑ ብዙዎቹን አስገርሟል፡፡  ይህንን የማኅበረ ቅዱሳን ጉድ የሰሙ ምዕመናን፣ በዚህ አካሄድ ከማኅበረ ቅዱሳን ውጪ ያለው ወገን ሲወገዝ መንግሥተ ሰማያት ለማቅ አባላት ብቻ ልትሆን ተወስኗል ማለት ነው፤ በማለት የተሳለቁ ሲሆን፣ ከነካካ ላይቀር የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያምንም ማስወገዝ ነበረበት ብለዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያብራሩ፣ ጓድ መንግሥቱ የተዋህዶ ልጅ ሆነው ሳለ የእግዚአብሔርን መኖር በመካድ የነባራዊ ዕውነታ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ የነበሩ በመሆናቸው ነው ብለዋል፡፡ ውግዘቱ በእርሳቸው ብቻ ሳያበቃ ጠቅላላ ወደ ሶሻሊስት አስተሳሰብ የፈረጠጠና ሃይማኖቱን የከዳ ሁሉ የኢትዮጰያ መሬትም ላይበቃው ነው ብለዋል፡፡ ውግዘቱ በዚህ ብቻ ማብቃት የለበትም ያሉ ታዛቢዎች፣ በጣሊያን ጊዜ ሀገራቸውንና ሃይማኖታቸውን ከድተው ለጠላት ያደሩ ባንዳዎችን ጨምሮ፣ ከዓፄ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ትንፍሽ ያሉ የ1700 ዓመታት ትውልዶች ሁሉ አጽማቸው ከተቀበረበት ተነስቶ ወደ ሌላ አካባቢ ዞር ሊሉ ይገባል ሲሉም ለማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን አድናቆት እግረ መንገዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

  ReplyDelete
 24. እኔን የገረመኝ ማህበረ ቅዱሳን ማነው; በማህበሩ ውስጥ የተሰገሰጉ ምናምንቴዎችን አፍርሰው ሊሰሩ የሚችሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን አውጋዥ ያደረጋቸው ; ይሄ ደሞ ሌላ ቤተክርስቲያንን እና ምዕመናንን ለማወናበድ የሚጠቀሙበት የማምታቻ ስልተ መሆኑ ነው; እባካችሁ ልካችሁን እወቁ የሚላቸው ተፋ ማሌት ነው እንጂ ቤተክርስቲያንን ላይ እንደዚህ አይፈነጩም ነበር ! እድሜ ልካቸውን የንፁሐንን ስም ማጥፋት ልማዳቸው ነው ዛሬም እንደ አባታቸው ዘርያዕቆብ በ14 እና 15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንፁሐን አባቶች በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ የተደረገውን ግፍ ለመድገም የሚፈልጉ ዝርራዦች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ዘርያዕቆብስ የቅዱሱን አባት የእስጢፋኖስን አስከሬን አስወጥቶ አቃጥሎት የለ የዛሬዎቹ ልጆቹም በሰላም ወደ አምላካቸው የሄዱትን የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከሙታን መቃብር አስነስተው ሊያስወግዙ ተነሱ የማን ዘር ጐመንዘር አለ የሀገሬ ሰው የሚገርሙ ናቸው የናፈቀኝ መጨረሻቸው ነው

  ReplyDelete
 25. Hello! Aba selama! are you ortodoxian or orotestant?In my openion,you are too much angry with tehadeso charege of (wegezet).do you belive tehadeso is living in our church or not?most of the mentioned names are who are they? i think you know every thing,but your mission is not protect the EOC from (Tekula-protestant-Tehadeso).My advice is please,help the sunday schools & Mahibere Kedussan effort.God bless our church from protestant-Tehadeso campain.
  Thank you.

  ReplyDelete
 26. ማህበሩ ቤተክርስቲያኗ በገሀድ ከምታምነው ውጭ የሚያምነው የሚታገልለት ድብቅ ትምህርት እንደሌለው ከናንተ በላይ የሚያውቅ የለም።

  ReplyDelete
 27. እናመሰግናለነ 'አባ ሰላማ'።ከዘገባችሁ የናንተን መቃጠል የሰ/ት/ቤቶችን መጋደል አይተንበታል።ሰንበት ት/ቤቶች ከልባቸው ከሰሩትማ ጤና ይስጥልኝ ተሀድሶ።ድሮም መስፈንጠሪያ ሳንቃ ያደረጋችሁት የሰ/ት/ቤት አዳራሾችን ነበር።ሰ/ት/ቤት ደግሞ ስብከተ ወንጌሉን ማገዝ ሲጀምር የት እንደምትደበቁ እናያለን።ቤተመቅደስ ግድየለም ሊቃውንቱንም እሳቱንም ስለማትችሉት አትደፍሩም እናውቃለን።ማኅበረ ቅዱሳን ድካማችሁ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል የሰ/ት/ቤት ወንድሞች በቁጭታና በጥብዓት ለቤተክርስቲያን እየታገሉ ነውና።ነገሩን የማኅበረ ቅዱሳን ማስመሰላችሁ በአንድም በሌላም በኩል ልክ ናችሁ።የማኅበሩ አባላት የሰ/ት/ቤት አባላት መሆናቸውን አትዘንጉ።ሌላው ሰ/ት/ቤት የማኅበሩ ወዳጅ ነው ።ቤተክርስቲያን ዓላማቸው ታገናኛቸዋለችና።ልዩነት ለመፍጠር የምትተጉ እናንተ እነማን ናችሁ ብለን አንጠይቅም።ከፍሬያችሁ አናውቃችኋለን።

  ReplyDelete
 28. i appricate u aba selama god blese u ok

  ReplyDelete
 29. አይ አባ ሰላማዎች በትክክል ከፍሬያችሁ ትታወቃላችሁ መቼ ነው የት ቤተክርስቲያን ነው የማርያም አምልኮ ያለው ይቺ የጠላት ወሬ ነው ከመናፍቃን የተቀዳ ነው

  ReplyDelete
 30. the great shame mk

  ReplyDelete
 31. ክርስቲያን ውሸትን እንደ መከላከያ ማየትና መውስድ ይቻለዋልን?? ማ/ቅዱሳኖችም የተሃድሶ አራማጆችም ትገርማላችሁ:: በዚህ ብሎግ ላይ የምትጽፈው ግን ስለ እግዚአብሂር ብለህ ለቡ አካባቢ የምትገኘው ቅድስት አርሲማ ጸበል ሂድህ ተጠመቅ:: ይለቅሃል:: ዲያቢሎስ እንደሚያሰራህ በትክክል ታስታውቃለህ:: እባክህ ወደ ህይወት ተመለስ?? ይብቃህ የከዚህ በፊቱ:: የሰይጣን ስራ መስራት ለማን ይጠቅማል?? ማ/ቅዱሳንን ከሶ ያጠፋዉን ማስተካከል ወይም እንዲዘጋ ማድረግ ይቻላል:: ሆኖም ግን ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው የመርካቶ ዱርየዎች እንኩዋን የማይጠቀሙበትን የስድብ ቃላት መጠቀም አያሳፍርም??? እረ ተው በሃይማኖታችን እንድናፍር አታድርጉ?? ሃጢያቱ በናንተ ነው?? ልቡናችሁን ይመልስላችሁ!!!

  ReplyDelete
 32. ስለመድረካችሁ በቅድሚያ አባ ሰላማዎችን አመሰግናችኋለሁ፡፡
  የእግዚአብሔር መንግስት የጽድቅና የሰላም እንጂ የሁከትና የጥላቻ አይደለምችም፡፡
  ያለአግባብ ወንድሙን/መምህራኑን/ነቅፎና አውግዞ የጸደቀ ሰው እንዳለ አላውቅምና ለማቅ አባላት የማሳስባቸው ይህንን ነው፡፡ይልቁንም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመመርመርና የእውነተኞቹን አባቶች ትምህርትና አርአያነት በመከተል ወደ እውነት ተመለሱ፡፡እግዚአብሐየር ጊዜ የሰጣችሁ ንስሐ ትገቡ ዘንድ ነውና፡፡አያምልጣችሁ፡፡እኔም እጸልይላችኋለሁ፡፡
  ወልደመድህን

  ReplyDelete
 33. Please pray for peace stop fighting.God solved this problem

  ReplyDelete
 34. All these Information shows our church is being envaded by Menafikans.I decided to stand with MK,most seriously

  ReplyDelete
 35. ባልጌዎች ናችሁ ምናለ የራሳችሁን ሃጢአት ብቻ ብታስቡ

  ReplyDelete