Tuesday, October 18, 2011

ዘመድኩን እና ጆኒ ራጋ --- Read PDF

ብርሃን ጸጋዬ ከዚህ በፊት ጠባቡ የማኅበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች በሚል ርእስ በሁለት ክፍል የለቀቃቸውን ጽሑፎች ማስነበባችን ይታወሳል፤ ዛሬ ደግሞ ዘመድኩንና ጆኒ ራጋ የሚል ርእስ በሰጠው ጽሑፉ የሚነግረን አለ፡፡

 አርማጌዶን ቪሲዲ በዋናነት መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝን ከመንግስት፣ ከእስላም፣ ከአርቲስቶች ጋር ለማቀሳሰር ታስቦ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ የዜሮ ድምር ውጤት ነው። ሌላውን ትተን ስለ ዘፈን እስኪ እናውራ፤ በዚች  አላፊ አለም ማድመቂያና የማያልፈውን አለም እንዳንወርስ ለብዙ ሀጢያቶች መነሻ የሆነውን ዘፈን በማድነቅ መንፈሳዊነትህን ነው ወይስ አለማዊነትህን ልትነግረን የፈለከው? ኧረ ከዘፋኝ ሞኝ ያልሆነ ማን አለ? ሁሉም በእንጀራ እና በዝና ሰበብ እረፍት እና እንቅልፍ የሌለውን ኑሮ ይኖሩታል፡፡ የልቡን በር በመዘናጋትና በሀጢያት ለአምላኩ የቆለፈ ሰው ማንንም ማንገስ፣ በማንም መንገስም አይችልም፡፡ የሰው ልጅ የሚያርፈው የሴቶችን ልብ ከፍቶ ሲገባ ሳይሆን፣ አምላኩ ክርስቶስ ኢየሱስን በልቡ ሲሾም ብቻ ነው፡፡ እንዲህ ካለ መጃጃል ሳትወጡ ለያሬዳዊ ዜማ እንጨነቃለን፣ ለቤተ ክርስቲያንም እንቆረቆራለን፣ ስትሉ ታሳፍራላችሁ፡፡
ከአሁን በፊት ሀመር  መጽሄት ላይ በእኔ መዝሙር ቤት የሚታተሙት መዝሙሮች ያሬዳዊ ናቸው፤ ለምሳሌ፡- የዘፋኙን የሀብተ ሚካኤል ደምሴን ስትጠቅስ አሳፍረሀኛል፡፡ ከማን ጋር እቃቃ እንደምትጫወት አላውቅም፡፡ ከሌሎች መዝሙር ቤቶች ጋር ተወዳድረህ መዝሙር ማሳተም ሲያቅትህ፣ ይሄው ወሬ እያወራህ ትሸጣለህ፡፡ ይህቺ አለም ደግሞ የወሬ አድማቂዎችም ጭምር ስለሆነች ጥቂት ወሬ ማናፈስህ አልቀረም፡፡ ጥቂቶች ያልገባቸው ስላጨበጨቡልህ አትደነቅ፡፡ ነገ ጠንቅዋይም ብትሆን የሚከተልህ ብዙ ነው፡፡ አሁንም የምትሰራው ስራ ከጥንቆላ ባይተናነስም፣ ከእግዚአብሄር ሀሳብ ግን ሩቅ ነህ፡፡ ይህንን ወሬ ስታዘጋጅ ካማከሩህ የበላይ አለቆችህ አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ነው፡፡ ጥቂት ጸጋ ብትኖረውም በግል ማንነቱ ደግሞ አንገቱ ሲጎብጥ ብዙ ችግር የተሸከመ ነው፡፡

ዳኒ ፕሮፋይልህ ላይ የጣእም ልኬት የዘፈን ፕሮግራም አድናቂ እንደሆንክ ነግረኸናል፡፡ ለመሆኑ ያሬድ ያሬድ አያለ ዘፈንን የሚሰብከንን ሰርጸን ነው? ወይስ መናፍቁን አብርሀም ተስፋዬን ነው የምታደንቀው? ወይስ ዘፈን ገና በልብህ አለ? ትከሻህስ ገና መስበቅ አላቆመም? እናንተ እንዲህ ካለ ሞኝነት ነፃ ሳትሆኑ ማንንስ ማዳን ትችላላችሁ? ዘፋኞችስ ከነቅራቅንቦአቸው ሲሞቱ እያየን፣ በህይወት እያሉ እያጨበጨብንላቸው፣ ነፍሳቸው ግን አምላካቸውን እየፈለገችና እየተጠማች እውነቱን ግን ደፍሮ እርሱ እራሱ ከዘፈን ወጥቶ አትዝፈኑ የሚል ጠፍቶ ዝም ብለን እየተያየን እየተላለቅን ነው፡፡ ለትልልቅ ሀጢአቶች አሳልፎ የሚሰጠን ዘፈን ነው፡፡ ለዚህም ነው ዘፈን ባለበት ስካር አለ፤ ስካር ባለበት ዝሙት አለ፤ ዝሙት ባለበለት በሽታ አለ፤ ከዛም በላይ አምላካችንን እናሳዝናለን፡፡ የተቀደሰ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ የሆነ ገላችንን በዳንስ እየወዘወዝን፣ በስካር እያጠወለግን ተልፈስፍሰን እንውድቃለን፡፡ ብዙዎች በዚህ መስመር ውስጥ ሞተዋል፡፡ አሁንም በብዙ ስቃይ የሚማቀቁም አሉ፡፡

አዎ ዘፋኝነት መጃጃል ነው፤ የተሰጠንም እድል እሳት እና ውሀ ነውና፣ ውሀውን የመረጠ በልቡ አምላኩን አንግሶ በሀዘኑም በደስታውም በጉድለቱም በሙላቱም በመውደቁም በመነሳቱም ሁልጊዜም እስከ ዘለአለምም ሲዘምር ይኖራል፡፡ በፍጻሜውም ክርስቶስ ሲመጣ ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር ይዘምራል፡፡ የክርስቲያንም የመጨረሻው ራእይ ይህ ነው፤ ነገር ግን በዚህ አለም ሞኝነት እየተታለልን ሰው አናዘናጋ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ነገሮች ቀዝቀዝ ቢሉም፣ 3 እና 4 ዓመታት በፊት ዘፋኙ ሁሉ እንዴት ብሎ ዘማሪ እንደሚሆን ሲመኝ አይተናል፡፡ ይህም የነበረው መንፈሳዊ አገልግሎት የምቀኝነት ንፋስ አልገባውም ነበርና ነው፡፡ አሁን ድረስ ዘፋኞች እስኪገረሙ ድረስ ዘፈን ቀዘቀዘ ብለው የሚያቀርቡት ሰበብ በኮፒራይት ቢሳበብም፣ እውነቱ ግን ክርስቲያኑ ቀደም ሲል ከመዝፈን ውጭ የመዘመር አማራጭ አልነበረውም፡፡ አሁን ግን የመዘመር አማራጩን ተጠቅሞ ልቡ በሀይማኖታዊ ቅናት ስለ ተነካ እጁን አንስቶ አምላኩን  ማመስገን ጀምሯል፡፡ በዚህም የዘፈን የመሸጥ አቅሙ ቀንሷል፡፡ መልካም ጊዜ ህዝቡን ሁሉ ባስደናቂ ሁኔታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሰብስቦ ሁሉም ለእግዚአብሄር ክብር ያጨበጨበበት ጊዜ ነበር፡፡ ወጣቱ የቤተ ክርስቲያን በር ሰፊ መስሎት ብሎ ገብቶም ነበር፡፡ ነገር ግን በር ላይ እንደ እናንተ ያሉ በማህበርና በቡድን በሩን ዘግታችሁ አባረራችሁት፡፡ ብዙዎችም በሀይማኖታቸው አፍረው አቀርቅረው እንዲመለሱ ሆነዋል፡፡

ያቺኑ የጥምቀትን በአል ለእግዚአብሄር ማደሪያ ለታቦቱ ክብር መንገድ መጥረጉና ምንጣፍ ማንጠፉን ግን ማንም አልከለከላቸውም፡፡ አሁን እያደረጋችሁ ያለችሁት ህዝቡን ለዘፈን ማመቻቸት ነው፡፡ በየደብሩ ያሉት ታላላቅ ጉባኤያቶች ጠፍተው ጭር እንዲል ነው የፈለጋችሁት፡፡ የእግዚአብሄር እሳት ግን ቢዳፈን እንጂ አይጠፋም፡፡ እናንተ እኮ ያታለላችሁት ህዝብ ማን ፈጠረህ ቢባል ያባቱን ስም የሚጠራ ነው፡፡ ሚካኤል ፈጠረን የሚሉትን ወጣት መበለቶችንም ነው፡፡ እነዚህም ቢሆኑ በባዶ ሀይማኖታዊ ቅናት ተነስተው ነው እንጂ እውነቱን ያወቁ ቀን ደግሞ ለእናንተም አይመለሱም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ በርግጥም የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሆናችሁ በቤተ ክርስቲያን ጉባኤያትም ከተማራችሁ እግዚአብሄር በነማን ላይ አድሮ ለነፍሳችሁ እውነትን ነገራት?

እናንተ እኮ መምህር ዘላለም ወንድሙ ሌባ ነው፤ ግን ብንናገረው ህዝቡ አያስቀምጠንም መኪናስ የሚቀያይረው ከየት አምጥቶ ነው? ብላችሁ የምትጨነቁ ናችሁ፡፡ ምክንያታችሁ ግን የነበጋሻው ደጋፊና ወዳጅ ነው፤ ከታናሽ ወንድሙ ከመምህር አድነው ወንድሙ ጋር በመሆን፣ እነርሱ የሚሰራውን አሻጥር በቅርበት እያዩ ወሬ እንዲያቦኩልህ ትፈልጋለህ እንዴ አዳሜ እስኪ የምር እነማን አስተማሯቸሁ መምህር ታሪኩ አበራ? መምህር በሪሁን? መምህር ተረፈ? መምህር በጋሻው? መምህር አሰግድ? መምህር ገብረ ሚካኤል የማነህ? ወይስ ሌሎች? የምር ከነማንስ ጋር ዘመራችሁ ከትዝታው? ምርቴ? ዘርፌ? አሸናፊ? እዝራ? ቅድስት? ወይስ ከሌሎች ጋር? እነዚህ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ንፁህ አገልጋዮች ናቸው፡፡

ተሀድሶ አለ? የለም? በሚለው ክርክር ውስጥ እነዚህን አገልጋዮች ከሆነ ተሀድሶ የምንለው አዎ ተሀድሶ የለም፡፡ ሌሎችን ከሆነ ደግሞ ለበላይ አካል ጠቁሙና የተባሉትን ሰዎች እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማስደረግ ነው፡፡ የመነኩሴ ቆብ እና እንደ ቄስ የጠመጠመውን ሁሉ በመናፍቃን አዳራሽ እየዘለለ ምንፍቅናውን ሲያካሂድ የተቀረፀውን እያመጣችሁና በራሳችሁ መንገድ እያቀናበራችሁ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተለየ ታሪክ እንደ ተፈፀመ እያስመሰላችሁ ህዝቡን አታጃጅሉት፡፡

የናንተ አላማ አንድና አንድ ነው፤ አንዳንዶቻችሁ ቢዝነስ፣ ሌሎቻችሁ ደግሞ ቅናት ያሰከራችሁ የቤተ ክርስቲያን ክፉ ጠላቶችዋ ናችሁ፡፡ ርግጥ ነው፤ የኖህ መርከብ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ በዚያች መርከብ ውስጥ ታዲያ ርግብና በግ ብቻ አልነበሩም፤ እባብና ውሻም እንጂ፡፡ ዛሬም በቤተክርስቲያን ውስጥ ቅኖችና የዋሆች ብቻ ሳይሆኑ እንደናንተ እንደ ውሻ የሚልከሰከሱና የሚናከሱ እንደ እባብ የሚናደፉ አሉ፡፡ እንደ እናንተ አይነቶቹን እግዚአብሄር በራሱ መንገድ ይውጋችሁ ብለን ዝም አልናችሁ እንጂ ጠማማነታችሁ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሆይ ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር ያውቃል ብቻ ብለን ዝም  ማለት የለብንም፡፡ ሁላችንም የየራሳችንን ድርሻ እንወጣ፡፡ ያለዚያ እግዚአብሄር ያውቃል ብሎ ያለ በቂ እምነት በአፍ ብቻ መለፍለፍ ከሆነ፣ እግዚአብሄር ያለለት ጫካ ውስጥ የተኛ ጅብ ይበላዋል፡፡

ወደድንም ጠላንም አንድ እውነት ልንገራችሁ፡፡ ይህ የአርማጌዶን ቪሲዲ የመጨረሻው የተወረወረና የከሸፈ ድንጋይ ነው፡፡ 20 ብራችሁን አውጥታችሁ የገዛችሁ ምን ያህል እንደ ተፀፀታችሁ ለራሳችሁ ትቼዋለሁ፡፡ አንድም አዲስ ነገር የሌለበት ሐሳቡና ይዘቱ 4ተኛ ጊዜ ተደግሞ የተሸጠ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም እነዘመድኩን ስታጃጅሉት የከረማችሁትን ህዝብ ምን ብላችሁ እውነቱን እንደምትነግሩት ማየት እፈልጋለሁ፡፡

ወደፊትም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚሰጠው ውሳኔ እግዚአብሄርንም ጭምር ሳትከሱ አትቀሩም፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶሱን የሚመራው የአቡነ ገብርኤል የሰው ሀሳብ ሳይሆን፣ የእግዚአብሄር መንፈስ ነውና፡፡ እባካችሁ ሲነቃ ይቀራል እንጂ ህዝቡን ጌታ አልተነሳም ብለው በአይሁድ እምነት እንዳፀኑት እንደ አይሁድ ያለ ስህተት እና ኪሳራ ውስጥ አታስገቡት፡፡ ያበጠው ይፈንዳ፤ እውነቱን ንገሩት፡፡

ዘመድኩን አሁንም ድረስ በመዝሙር ቤትህ የምትሸጠው የእነ ትዝታው እና ዘርፌን የነ በጋሻውንም ስብከት ነው፡፡ ተሀድሶ ከሆኑና ከተሳሳቱ ለምንስ ትሸጣለህ? ነው ወይስ ይሄም ቢዝነስ ስለሆነ አርምጃ አትወስድበትም? ደግሞ ዘመድኩን አንተና መሰሎችህ ከጆኒ የባሳችሁ ጅላጅሎች ብያችኋለሁ፡፡ እውነተኛ የሆኑት የእግዚአብሄር ልጆች ግን በከፈሉት መስዋትነት በሰገነቱና በየአውደ ምህረቱ በድጋሚ ነግሰው ከፍ ከፍም ብለው ሲያገለግሉ ታያለችሁ፡፡ የዚያን ጊዜ አሁን በወሬ አሉባልታ ስትጃጃሉ የከረማችሁ ሁሉ እፈሩ አንላችሁም፤ በይቅርታ አብረን እንዘምራለን ሀሌ ሉያ እያልን።

by Berhan Tsegaye Saturday, October 8, 2011

ይቆየን

15 comments:

 1. What a blog is this. Bravo Aba Selama

  ReplyDelete
 2. min nekah wondme lemehonu Zemedkun yegleseb sim beawdemihret lay atansu ale enj ante endemtilew zefenin degfual ende? Bekinat yetekatelk timeslalehna wode libh temeles wodaje

  ReplyDelete
 3. Zemedekun doesn't represent the Ethiopian Orthodox Church .

  ReplyDelete
 4. Zemedkune is crazy!

  ReplyDelete
 5. Wow you are brave. You said there isn't Tehadiso. Just MK creat the monk and priests to decive us? Wow you are kidding your self,fool. We know the truth.
  By the way about singers ask 'aba' woldetensay. He'll tell you about it, and I belive you'll listen him b/c he is one of you.
  So long man
  Ben

  ReplyDelete
 6. በሃይማኖት ዝምታ ካለ ከእኛ ከጠባቄዎች በኩል ችግር አለ። ማረያም አታማልድም ሲባል፤ ኢየሱሰና አግዘአብሔር የተለያዩ ናቸው የሚለውን ሠው ዝም ማለት ብቻ ሣይሆን ከተንከባከበነው ሥራ ከሠጠነው አቋሙን እንጋራለን ማለት ነው
  ብፀአ አቡነ ገብርኤል

  ReplyDelete
 7. God Bless you Berhan Tsgaye. I wish we have 1000
  of like you and Tesfa which is telling the truth.

  God Grant you Many many years. Amen.

  ReplyDelete
 8. ezaw harer kebetesebocheh gar yenber chat negd yeshaleh neber new ahunem mateb aserhe bedebek techebchbaleh anten mawek yemechelew wedageh seyetan becha new ebake yebetemekdesun legoch lekek aynehen negdeh lay becha yehun ante mecham rasehen yemetayebet geza yelehem mekenyatum terfu ayetayehemena ene ebakeh ye amlaken lagoch lekek dagmawe feron.

  ReplyDelete
 9. btsu abun gebreal yalkewu rashin ewok

  ReplyDelete
 10. berhanu egizeabeheren yemesele talak amlak yematefera defar selehonk kezibelay betekirsiyanen yemigoda tsehufe betestefm ayegermegnem ere bakeh wede lebonah temelese armagedon aranba yanete asteyayet kobo. meleseh semaw benetsa lebona

  ReplyDelete
 11. ዛሬ ልዩነትን በማጥበብ ይተራራቁ በሚቀራረቡበት ዘመን እኛ ግነ . . .
  ቤተክህነት ያሉ ሰዎች ከላይ ኤሰከታች በሙስና ይሰከሩ ለአገሌጌሎት
  የስራ ቅጥር ከገዳም ይሚመጡ አባቶችን 10000 ብር ድረስ የሚጠይቁ
  ሳንሞት እንብላው ስብስብን ትመስላላችሁ
  አሁን ደግሞ ይሉተራውያን ፍርፋሪ ለማግኘት ከውስጥም ከውጭም
  የምትውተረተሩጉዶች ዋ የእግዚሀብሄር ፍርድ እንደቀረበ አውቃችሁ
  ንሰሀ ግቡ

  ReplyDelete
 12. በእዉነት የሚያሳፍር ትችት ነው፡፡ ይህንን ስትፅፉ አቶ በጋሻዉ በየአዉደምህረቱ ላይ ሲሳደብ ይህ የስድብ ቃል የኦርቶዶክስ በተክርስቲያን ድምፅ ነው ዕያላችሁ መሆኑን አውቃችሁታል ፡፡ እኛ የሚሳደብ የሃይማኖት አስተማሪ የለንም፡፡ የዚህ ድረገፅ አዘገጆች አላመችሁ ከኦርቶዶክስ ስርዓት የወጣችሁ አይመስላችሁም? ስለምትፅፉት ነገር አስቡበት እናናተም አብራችሁ ከትክክለኛዋ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ትለያላችሁ አንባቢም አታገኙ የሚየምናችሁም የለም፡፡

  ReplyDelete
 13. ይቅርታ የተፃፈን አስተያየት በነፃ ማስተናገድ ይኖርበችኃል አለበለዚያ ሌላ ያስመስልባችኃልይቅርታ የተፃፈን አስተያየት በነፃ ማስተናገድ ይኖርበችኃል አለበለዚያ ሌላ ያስመስልባችኃል

  ReplyDelete