Monday, October 24, 2011

በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ዋዜማ ማኅበረ ቅዱሳን ሥርዓተ ጸሎትን ሲያውክ ውሎ ሲያውክ አመሸ


ደም ሊያፋስስ ይችል የነበረ ሤራ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን ርምጃ መክሸፉ ተረጋገጠ
በዘማሪ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ላይ የተቃጣው ጥቃት ማኅበሩ ምን ያህል የማፊያ አደረጃጀትን ይዞ እንደመጣ ያመላክታል ተብሏል
ሰባት የጥቃቱ አራማጆችና ረባሾች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ
ራሱን በአባቶች መንበር አስቀምጦ "እከሌ ይግባ እከሌ ይውጣ" በማለት "ያዙኝ ልቀቁኝ" በማለት ላይ የሚገኘው "ማኅበረ ቅዱሳን"፣ የራሱን ርካሽ ማንነትና ድብቅ ዓላማ ያጋለጠ ድርጊት መፈጸሙን በዚያው የነበሩ ዘጋቢዎቻችን አረጋግጠዋል፡፡ ከነጠላ አለባበስ ጀምሮ የመቋሚያ አያያዝ፣ የደምፅና የዜማ አወጣጥ፣ የስግደትና የአጿጿም ሥርዓትን እኔ ካልመራሁ የሚለው "ማኅበረ ቅዱሳን" ዛሬ ምን ያህል ለሥርዓት የማይገዛ ሥርዓተ አልበኛ እንደሆነ በጠራራ ፀሐይ አሳይቷል ተብሏል፡፡

ለወትሮው እንደሚደረገው ሁሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መጀመሪያ ዋዜማ ላይ የሥርዓተ ጸሎት መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን፣ ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2004 ዓ.ም አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ማሪያም ገዳም የሚካሄደውን የጸሎት ሥርዓት ለመከታተል እና ያለባቸውን ችግሮች ከሥርዓተ ጸሎቱ በኋላ ለአባቶች ለማቅረብ የተገኙ ምዕመናን ቁጥር እጅግ በርካታ ነበር፡፡
እነዚህ ምዕመናን ከአዲስ አበባ፣ ከሀዋሳ፣ ከመቀሌ፣ ከአለታ ወንዶ፣ ከሻኪሶ፣ ከክብረ መንግሥት፣ ከነጌሌ ቦረና፣ ከሐረር፣ ከሀገረ ማርያም፣ ከዲላ እና ከሌሎች ከተሞችና ሀገረ ስብከቶች የመጡ ሲሆን ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ እንዲሁም "ማኅበረ ቅዱሳን" ከሚያሳድዳቸው ዘማሪያንና ሰባክያን ጭምር የተውጣጡ የአገልጋዮችና የምዕመናን ተወካዮች ጭምር ችግራቸውን ለማመልከት በቅጥር ግቢው ተገኝተው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ፣ ዕለቱ ለእርሱ እንደማይሆን አስቀድሞ የተረዳው "ማኅበረ ቅዱሳን"፣ ያለማንም ፈቃድ ከየአድባራቱ የሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶችን በማሰባሰብና የደንብ ልብስ በማልበስ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ አዝምቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ገዳሙ ቅጥር ግቢ መግባት የተጀመረ ሲሆን እነዚህ ከየአድባራቱ የተሰባሰቡ የማኅበረ ቅዱሳን ሠራዊትም ምዕመናን በመግፋት፣ ዐውደ ምሕረቱን በሰው ኃይል በማጠርና ከጣሪያ በላይ በመዝሙር ስም በመጮህ ውጥረቱን እንዳባባሱት ተገልጿል፡፡
ይህ ከቃለ ዐዋዲው ውጪ ዕድሜያቸው ከ40 በላይ የሆኑ ጎልማሶች በሰንበት ት/ቤቶች ወጣቶች ስም የተሰባሰቡበት ሠራዊት ማንኛውንም ነገር በጡንቻ ለማንበረከክ ተሰልፎ እንደመጣ ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ልብሰ ተክህኖ የለበሰ አንድ የማኅበሩ ደጋፊ ከጓደኛው ጋር ወደ ዘማሪ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ተንደርድሮ በመሄድ በዱላ ግንባሩ አካባቢ የመታው ሲሆን ቀላል ጉዳት አድርሶበታል፡፡ ደብዳቢው ግለሰብ ልበሰ ተክህኖውን አውልቆ ራሱን ለመሰወር የሞከረ ቢሆንም በፀጥታ ኃይሎች ቅርብ ክትትል የዕለቱ መርሐግብር ማብቂያ ላይ እርሱን ጨምሮ ሰባት ሰዎችን ፖሊስ ወስዶ በቁጥጥር ሥራ አውሎ ምርምራ እየተካሄደባቸው ነው፡፡ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላትም ማን ሄዶ ማን ይቀራል በሚል ተራ ቅናት ከሲዳማ ሀገረ ስብከት ለአቤቱ ከሄዱ እንግዶች መካከል በጣት እየጠቆሙ ይኸው ይሄም ተሳድቧል፤ ይኸው ይሄም ረብሿል እያሉ በቡድን ተደራጅተው ንፁሃንን ያሳሰሩ ሲሆን፣ ፖሊስ አስፈላጊውን ምርምራ አድርጎ እውነታውን ሲደርስበት እንደሚለቃቸው ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡
ዘማሪ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤልም ሆነ አጠገቡ የነበሩት ዘማሪያንና ሰባክያን ጓደኞቹ ምንም ዓይነት የአጸፋ ምላሽ ሳይሰጡ በንቀት ማለፋቸው የክርስትናቸውን የብስለት ደረጃና ለመስዋዕትነት ያላቸውን ጥንካሬ ያመላከተ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ ክስተት በኋላም የአዲስ አበባ ፖሊስ በተሽከርካሪዎች ፈጥኖ ወደ ስፍራው በመምጣት የከፋ ጉዳትና ደም መፋሰስ ሳይደርስ ሁከቱን በቁጥጥር ሥር ያዋለው ሲሆን፣ የሁለቱንም የገዳሙ መውጫ መግቢያ በሮች በመዝጋትና ወደ ገዳሙ የሚያመሩትን መንገዶች ከተሽከርካሪ አና ከሰው ንክኪ በማራቅ አስፈላጊውን የፀጥታ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የሰንበት ት/ቤት የደንብ ልብስን እንደ መከለያ ቅርፊት (Shell) የሚጠቀመው "ማኅበረ ቅዱሳን" አባላቶቹ የደንብ ልባሳቸውን አውልቀው ከግቢ ወደ ውጭ በመወርወር ጓደኞቻቸውን አልብሰው በስውር ያስገቡ የነበረ ሲሆን፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ፖሊስ የሚገባውንም የሚወጣውንም በጥብቅ በመቆጣጠሩ ሊባባስ የነበረውን ችግር በአግባቡ ተቆጣጥሮታል፡፡
ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በሆነበት ወቅትም፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ በብፁዓን ሊቃነጳጳሳት እና ሊቃውንት ታጅበው ወደ ሥርዓተ ጸሎቱ የመጡ ሲሆን ከዕለቱና ከሰዓቱ ጋር ያልተገናኙ መዝሙሮችን በማሰማት መደማመጥ እንዳይኖር አድርጓል፡፡
በወቅቱ መርሐ ግብሩን ይመሩ የነበሩ አባት መርሐ ግብሩን ለማስጀመር መዝሙሩ ቆሞ እንደማመጥ ብለው ቢማጸኑም የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት ዐውደ ምሕረቱ ላይ በመውጣት ጭምር እያወከ እሺ ሊል አልቻለም፡፡ አሁንም እኝሁ አባት ቢለምኑ ሠራዊቱ ሊሰማቸው አልወደደም፡፡
ይህ ዓይነት የመዝሙር ዝግጅት ቀደም ባሉት ጊዜያት ያልነበረና ዛሬም በሰንበት ት/ቤት በኩል ፈቃድ ያልተጠየቀበት፣ ያልተፈቀደ መሆኑን አስታውሰው "ስለ እግዚአብሔር እንለምናችኋለን፤ የሰንበት ት/ቤተ የደንብ ልብስ የለበሳችሁ ሁላችሁም ቅጥር ግቢውን ለቃችሁ ውጡልን፤ የጸሎት መርሐግብራችንን እናካሂድበት" ብለው ቢለምኑም የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት አሻፈረኝ በማለቱ የጸሎቱ ሥርዓት በጩኸት እየታጀበ ተካሄደ፡፡
የጸሎት መርሐ ግብሩ እንዳበቃ ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት እና ሊቃውንት የተሰበሰበውን አይተው ችግሩ ምን እንደሆነ ጠየቁ፡፡ ከሁሉም አቅጣጫ መጯጯኽና አለመደማመጥ እየተጠናከረ መጣ፡፡ በወቅቱ በሮቹ ድንገት በመዘጋታቸው ወደ ገዳሙ ቅጥር ግቢ መግባት ያልቻለው በርካታ ሕዝብ በውጭ ሆኖ ከገዳሙ ድምፅ ማጉያ የሚተላለፈውን መልዕክት የተከታተለው ሲሆን ከውስጥ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት መዝሙሮችን ከጣሪያ በላይ በመጮኽና የቤተክርስቲያኗን ደወል በመምታት ፍጹም ሥርዓተ አልበኝነት በተሞላበት ሁኔታ ሲያውክ ወሎ ሲያውክ አምሽቷል፡፡
በመጨረሻም "እስኪ የእያንዳንዳችሁን ችግር ለመስማት አንድ፣ አንድ ተወካይ አቅርቡ" በተባለው መሠረት "ማኅበረ ቅዱሳን" በሰንበት ት/ቤቶች ጉያ ተደብቆ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ሕብረት ጥያቄ ነው በሚል ሽፋን ባለ አንድ ገጽ ተኩል ጽሑፍ በንባብ ያሰማ ሲሆን የጽሑፉ ፍሬ ነገርም የሰንበት ት/ቤቶቸ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት አባ ሠረቀ ብርሃን ይወገዙልን የሚል ነጠላ ዜማ የተላለፈበት ነው ተብሏል፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" ከንዑስ ተጠሪነቱ ወደ ላይ አንጋጦ አባ ሠረቀን ይወገዙልኝ የሚለውን ክስ የሚደጋግመው ለምን መስመርህን ጠብቀህ ተጓዝ ተባልኩ፣ እንዳሻኝ መሆን እችላለሁ ከሚል የሥርዓተ አልበኝነቱ ባህርይ የመነጨ መሆኑን ብዙዎቹ ይስማሙበታል፡፡
የሆነው ሆኖ፣ "ማኅበረ ቅዱሳን" የራሱን ተራ ተጠቅሞ ካበቃ በኋላ በማኅበሩ ተከታታይ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉ ዘማሪያንና ሰባክያን በተወካያቸው በመምህር ተረፈ አማካይነት በንባብ መደመጥ ሲጀምር የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት የሁከት አታሞውን መደለቅ ጀመረ፡፡ በኋላም ማኅበሩ አላስደምጥ እያለ ሲያስቸግር፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ የመነጋገሪያውን ማይክ ከመርሐ ግብር መሪው ተቀብለው ችግር አለብን አላችሁ በተራችሁ ተጠቅማችሁ በጥሞና አነበባችሁ፡ ሌው በተራው ሲያቀርብ ለምን ትጮኻላችሁ፣ እውነተኞች ከሆናችሁ የሌላውን ተራ ለምን ትከለክላላችሁ? ስለዚህ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ የሌሎች ችግር እንዳይሰማ በአቋማችሁ ከጸናችሁ፣ የአቤቱታ አቅራቢዎችን ዕሑፎችና ሠነዶች ተቀብለን በአባቶች እንዲመረመር አድርገን እናስወስናለን፤ ብለው ሁሉም ወደመጣበት በሠላም እንዲመለስ አሳስበውና ባርከው አሰናበቱ፡፡
ይህ ክስተት ለብፁዓን አባቶች ከረፈደ በኋላ የተላለፈ የማንቂያ ደወል ነው ሲሉ ታዛቢዎች አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ይኸው የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሠራዊት ሀዋሳ ላይ መስከረም 9 ቀን 2003 ዓ.ም የመብራትና የድምፅ መስመሮችን እንደ አይጥ በመቆራረጥ፣ ደወል በመደወልና መፈክር በማሰማት ሥርዓተ ቁርባንን ማወኩ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በየሀገረስብከቱ በውጭ ሀገርም፣ በሀገር ውስጥም ባሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት በተመሳሳይ ሁኔታ ሥርዓተ ቅዳሴና ሥርዓተ ቁርባንን የማወክ ዕኩይ ተግባር ሲከተል ቆይቷል፡፡ ቀደም ሲልም በሎስአንጀለስና በዳላስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ ይህንኑ የመሰለ ድርጊት በመፈጸም ወገኖች ተፈንክተው የአሜሪካ ፖሊስ ጣልቃ እስከመግባት የደረሰበት አጋጣሚ እንደነበር ፎር ፎክስ የቴሌቪዥን ጣቢያን የተከታተሉ ወገኖች በደንብ ያስታውሱታል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በአሁኑ ሰዓት የዕውር ድንብሩን ባገኘው አቅጣጫ የተስፋ መቁረጥ ጥይቱን በመተኮስ ላይ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ዛሬም፣ ዱርዬዎች ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አወኩ ብሎ ሲከስ እንዳልኖረ ሁሉ፣ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አጠገብ በብፁዓን አባቶች አፍንጫ ሥር ሲረብሽ መገኘቱ የዋልጌነቱን ዳር ድንበር ያመላከተ ነው ተብሏል፡፡ ከዚሀ በፊት በክልል ከተሞችና በየሀገረስብከቱ ምዕመናን ተመሳሳይ ችግር ደርሶባቸው ሲያመለክቱ፣ "የሠይጣን ወሬ ነው እኔ ቅዱስ ነኝ" እያለ በበሬ- ወለድ የፈጠራ ድርሰቱና በአሉባልታው እየተመረኮዘ፣ በቤተክርስቲያንና በመንግሥት ከፍተኛ መዋቅር በተሰገሰጉ አባላቱ እየተደገፈ ብዙዎቹን ሲያሰለቅስ እና ከቤተመቅደስ ሲያሳድድ ኖሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ "ማኅበረ ቅዱሳን" በቅዱሳን ስም የተለበጠበትን ለምድ አውልቆ እውነተኛ ማንነቱን ያጋለጠበት ድርጊቱን በይፋ በማሳየት ላይ ሲሆን በአመራሩና በአባላቱ አማካይነት በራሱ መረብ ላይ ድንቅ፣ ድንቅ ጎሎችን እያስቆጠረ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" አደረጃጀቱ የማፊያ አደረጃጀትን የሚከተል ሲሆን ግልፀኝነት የሚጎድላቸው እንቅስቃሴዎች ይታዩበታል፡፡ የሀብት ምነጩ፣ የገንዘብ ፍሰቱ እና የአባላት ማንነት በቤተክርስቲያንም ሆነ በመንግሥት የማይታወቅ ሲሆን የአባላት ብዛት እንደ አመራሩ ማንነትና አመለካከት የተዘበራረቀ ቁጥር የሚጠቀስ መሆኑ ይስተዋልበታል፡፡ ለምሳሌ ያህል የማኀበሩ አመራር አባል ዲያቆን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም ዕንቁ ለተባለ መጽሔት በቅርቡ በሰጠው ቃለመጠይቅ የማኅበሩ አባላት ብዛት 40ሺህ ነው ያለ ሲሆን፣ የማኅበሩ አመራር አባል የሆነው ዳንኤል ክብረት ከማኅበሩ ጋር በተኮራረፈበት ወቅት ይህንኑ የማኅበሩን ስውር እንቅስቃሴ ገልጾ፣ የአባላትን ቁጥር ወደ 13 ሺህ አውርዶት አልፏል፡፡ የማኅበሩ ፀሐፊ ዲ/ን ግርማ መታፈሪያ ሴፕቴምበር 2007 ለታተመው ፎከስ መጽሔት በሰጠው ማብራሪያ የማኅበሩ አባላትን ቁጥር ወደ 80 ሺህ አድርሶታል፡፡
ይህ ዓይነት አደረጃጀት፣ ጣምራ ተልዕኮ (Double Mission) ለሚከተሉ ሰዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን፣ ቁጥጥር የማይደረግበት ሀብትና ያልታወቀ አባላትን ይዞ የሚጓዝ ማኅበር ከቤተክርስቲያን አልፎ ለመንግሥትም አደገኛ ሊሆን እንደሚችል በተደጋጋሚ እንደስጋት የሚጠቀስ መሆኑ አይዘነጋም፡፡
ኃያል አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ይቆየን!!!

15 comments:

 1. I read it. please read it as "mehabere sitan."

  ReplyDelete
 2. guys it is very good information ,mk is now distribuing every where here in dallas, texas now aba wolde tensae is teaching but they are distrubing, complaining , opposing. so they are out of gospel

  ReplyDelete
 3. ማቅ ሰላም የማይስማማው በሁከት ቦታ ዛሩ የሚነግስለት አመፅ ማስነሳት ክርስትና የሚመስለው
  ብጥብጥ ማወጅ ስራው የሆነ ማህበር ነው ክንዱ ግን በጌታ ሀይል ይሰበራል

  ReplyDelete
 4. Not even a single evidence that MK was behind any violence. its simply your nightmare that is disturbing you. Beniseha Temelesu. Mahibere Kidusan rikash ayidelem. Matured, spiritual members and leaders yalut new.

  ReplyDelete
 5. in no way, protestants/tehadiso menafkans could achieve their evil mission, we are here more organized before to clean the dusts out of our beloved church. one agenda of the synod meeting is to once and for all curb the protestant exterimists/terrorists out of the church.it is not surprising for the lier tezitaw to fall down to the ground to disguse himself as if he is beaten. we know the drama, the pretext it is the system of the devil, when it is becoming unsuccessful. it is an honor/respect for MK to continuously the target by enemies, MK does not stop back for a single second from exposing the tehadiso terrorists

  ReplyDelete
 6. This all is false report. I was there myself, mahibere kidusan was not a part of it at all. It was senbet tamriwoch of addis ababa, and they were so polite! What kind of destructive report are you posting? Please, please, and once again please in the name of God, don't disseminate such kind of hatred and falsified report of no ground!

  ReplyDelete
 7. yetehadiso mechereshaw bete kirstianin mekfel endehone mk yetenagerew ewunet mehonu teregagete Mk bertu erkanachewn eyekeru new.

  ReplyDelete
 8. I am from Addis Idont forget Aba Woldetensae preachig it was very powerful and called to repetance.I wish to Aba Wolde peace health and grace.

  ReplyDelete
 9. thank you abaselama for the detail. mahibere kidusan is disturbing he church. they are scattered all over the world and disturbing the church. pls MK.

  ReplyDelete
 10. i was also there did you know belay werku a well known member of mk he was in romina and he was ordered the Sunday school students to do this and that. they really disturb a lot they even want to here the patriarchs speech. yes mk is behind it and they even bit dn. tizetaw i saw it in my 2 eyes. don't lie your self. if you know the name of God you cant lie in his name. it is all mk members problem. once in your life speak for the truth.

  ReplyDelete
 11. mahebere kidusanema rekase new asadage yegetan kal yemigafa kirestiyanochene siyaye yemidenegite. kalgedelku belo yemyaschegere nwe.

  ReplyDelete
 12. mahbre kisdusan betam migerm honual. be dibdb ena be dula miyanm honual. betbachoch bcha.

  ReplyDelete
 13. ደጄ ሰላም፦ \ማቅ\ ፦መቼም ስህተታችሁን ሲነግሩአችሁ ይብስባችሁአል። ለአንድ አስተያየት ሰጭ የመለሳችሁለት መልስ በጣም ያሳዝናል፣ ዳሩ እናንተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የምትነግዱና በሽብር ምዕመናኑን የምታሳስቱ አስመሳይ ክርስቲያኖች መሆናችሁን ስለምናውቅ ብዙም አይደንቀንም። አሁን አሁንማ በክርስቶስ ብርሃን እየታያችሁ ስለሆነ አለቃችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ አይዙአችሁ እያለ ንፁሃን፣ ቅዱሳን ካለ እናንተ ማን አለ እያለ እያታለለ በክርስቲያኖች ላይ ድንጋይ እንድታነሱ አያደረገ ነው።

  ደጄ ሰላም ፣ ማቅ ፣ የአዲስ አበባና የአካባቢው ሰ\ትምህርት ቤቶች፣ አሁን ደግሞ የጥምቀት በአል ሰራተኞች ፣ አላችሁ\\\ ምን የማትሉት አለ\ የውሸታችሁ ማለቂያ የለው። በዚህ ሲሉአችሁ በዚያ ትሽሎከለካላችሁ ምነው ልቦናችሁን እንዲህ እንደ ይሁዳ ጌታን በ 30 ብር አሳልፎ ለመስጠት እንደተቅበዘበዘው ተቅበዘበዛችሁ ፡ የአውሬው
  ገንዘብ እንደዚህ በዝቶ የተመረጡትን እንኩአን እስከሚያስት ፤ ማለቴ፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያናችንን አባቶች እንኩአን ጨምራችሁ የትንቢት መፈፀሚያ ትሆኑ\ ይገርማል፡ ነገር ግን ሰልፉ የእግዚአብሔር ስለሆነ ፡ ማሸነፉን ለሰከንድ
  እንኩአን አንጠራጠርም። ሰይጣን ግን በመጨረሻው ዘመን መቃጠሉን ስለሚያውቅ ፣ ብቻውን መቃጠል ስለማይፈልግ
  እስከ መጨረሻው ድረስ መቅበዝበዙን አይተውም። ያልበሰሉትን ከመሰብሰብ አያርፍም። አምላካችን ግን ፍጥረቶቹ
  እንዳይጠፉ ስለሚፈልግ ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ንስሀ እንድትገቡ ጊዜ እየሰጣችሁ መሆኑን አስተውሉ።

  የክስ ደብዳቤያችሁን እኮ አይተነዋል። ለመሆኑ የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት፣ መምህራን፣ ዘማሪያንና አንዳንድ
  የተለየ ስጦታ እግዚአብሔር የሰጣቸው ክርስቲያኖች በሙሉ ምን ቀራችሁ በእናንተ ዘንድ እኮ የናንተን ብሎግናየማቅን
  የውስጥ ማንነት ያወቀ ሁሉ መናፍቅ ነው። እንግዲህ ማን ይሆን ትክክለኛ ኦርቶዶክስ\ -እናንተ\ በእናታችሁ
  በቅድስት ድንግል ማርያም ሥም እለምናችኃለሁ መልሱን ፃፉልኝ። ይህችንም ፅሁፌን ተግሳፅም ብትሆን ሰለ እመቤቴ ብላችሁ አውጡልኝ። ከዚህ ቀደም ለብዙ ጊዜ የምሰጣቸውን አስትያየት አንዱንም አውጥታችሁት አታውቁም፣ እስቲ አትፍሩ ።በራሳችሁ መተማመን የለም እንዴ \ አንባቢ ካነበበው እውነቱን ያውቃል ብላችሁ ከሆነ፣ በጣም ተሞኝታችሁአል። ምክንያቱም የማይገለጥ የተከደነ የለምና።

  ቸር ይግጠመን። አሜን።

  ReplyDelete
 14. MK is on the right way but those who do know z sound of coin like begashaw (I know him very well) and his gangsters make things on the other way round. u all are like "Nistiros" the first

  ReplyDelete