Tuesday, October 25, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን ከዐመፅ ተግባሩ ያተረፈው ኪሳራ መሆኑ ተገለጸ - Read PDF

30ኛውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤንና ከዚያ ቀጥሎ የሚካሄደውን የጥቅምት 2004 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባን ለግል አጀንዳው ማስፈጸሚያነት ለመጠቀም ቀደም ብሎ ሲዘጋጅ የነበረውና ልዩ ልዩ ስልቶችን ነድፎ ሲንቀሳቀስ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን ያሰበው ሁሉ ሳይደርስ ትክክለኛ ማንነቱ ፈጥኖ እየተገለጠ ልዩ ልዩ ኪሳራዎችን መከናነቡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡

ጥንተ ተፈጥሮው ከሳሽነት ብቻ የሆነውና ለህልውናው አሥጊ ሆነው ያገኛቸውንናገበያ ዘጊበሚል የፈረጃቸውን ታዋቂ ሰባክያንንና ዘማርያንን በመክሰስ፣ የቅርብ ጊዜ ዲያብሎሳዊ አገልግሎቱን የጀመረው ማኅበረ ቅዱሳን፣ በታሪኩ አጋጥሞት የማያውቀውን ሽንፈት እያስተናገደ እንደሚገኝ ለማኅበሩ የጥፋት ተልእኮናከእኔ በቀር ሁሉም ተሳስቷል፣ መናፍቅ ነውለሚል ቅዠቱ እየተሰጠ ካለው ምላሽ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀደም የጨለማው ክብደት አላሳይ ብሏቸውና የማኅበሩን ጨለማዊ ሥራ እንደ ጽድቅ ቆጥረዉለት ቀኝ እጃቸውን የሰጡት ሁሉ ዛሬ ፊታቸውን አዙረው ጀርባቸውን እየሰጡት እንደሚገኙ የሰሞኑ ሁኔታ በቂ ምስክር ነው፡፡

በሁለት የክስ መዝገቦች አደራጅቶ አንዱን በአዲስ አበባ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ስም ያቀረበውናአገር ይወገዝልኝየሚለው ክስ፣ በኅቡእ ለታማኝ ጳጳሳቱ ከተላለፈና ተከድቶ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ ወደ አደባባይ ከወጣ፣ እንደ ነጋድራስ ያሉት የግል ጋዜጦችም ዜናውን ከናኙት በኋላ፣ እንደ ረከሰ መድኀኒት የማይሠራ ስልት ሆኗል፤ እንኳን አገር ሊወገዝ ይቅርናየተሐድሶ መናፍቃንነጠላ ዜማው፣ ከገበያ ውጪ እየሆነና ሰሚ እያጣ መሆኑ ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክስ መዝገቡ እንዲዘጋጅ ሁኔታውን ያመቻቸው መሸሸጊያውን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ያደረገውና በቃለ ዐዋዲው ውስጥ መዋቅሩ ሳይኖር በሕገ ወጥ መንገድ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር እንደ ሆነ ታውቋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እንዳሻው የሚጋልብበት ይህ ሕገ ወጥ አመራር፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቶቹ አመራር የሚሰጥ ሳይሆን፣ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራር የሚቀበልና የሚተገብር መሆኑ በብዙ ማስረጃዎች ተረጋግጧል፡፡ ሕገ ወጡ አመራር በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ድጋፍ ሰጪነት ማኅበረ ቅዱሳን ያረቀቀውን የክስ ሰነድ፣ በቆረጣ ወደ ሊቃውንት ጉባኤ ለማስገባት ሞክሮ አልተሳካለትም ነበር፤ ነገር ግን የሥራ አስኪያጅነቱንና ጸሐፊነቱን ቦታ የያዙት የወሎዎች ቡድን ዋና አጋፋሪዎች አቡነ ፊልጶስና አቡነ ሕዝቅኤል ግንሀገረ ስብከቱ ከሆነ ይችላል፤ መርምሩና ወደ ሲኖዶስ አሳልፉሲሉ ቀጭን ትእዛዝ ያሳለፉ ቢሆንም እስካሁን ተቀባይነት እንዳላገኘ ለማወቅ ተችሏል፡፡     

ለጥቅምት 11/2004 .. “ተሐድሶ-መናፍቃንየሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ የተከፈተባቸው ወገኖች ድምፃቸውን ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለማሰማትና ማኅበረ ቅዱሳን አደብ እንዲገዛ እንዲያደርጉላቸው በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኞች ተገኝተው በረብሻ ሰላማዊ ሰልፉን በማደናቀፍ ለማኅበሩ ጊዜያዊ ድል ያስገኙለት ቢመስላቸውም፣ ማኅበሩ እንዲህ ያለ ሽፍታ መሆኑን፣ ድብቅ ማንነቱን ላልተረዱና በጭፍን ለሚደግፉት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ለብዙዎች ያስመሰከረበት አጋጣሚ ሆኖ ዐልፏል፡፡

በየስፍራው በማኅበረ ቅዱሳን ከፍተኛ እንግልት የደረሰባቸውና ከተለያዩ ከተሞች፣ ማለትም ከሻኪሶ 15 አውቶቡስ፣ ከአዋሳ 7 አውቶቡስ፣ ከክብረ መንግሥት 3 አውቶቡስ፣ ከዲላ፣ ከቦረና፣ ከሐረር፣ ከጉርሱም የመጡ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ የተሰባሰቡ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርት፣ መምህራን፣ መዘምራንና የሰንበት ተማሪዎች እንዲሁም ምእመናን በራሳቸው ተነሣሥተው ሰልፉን ያደራጁት ቢሆንም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ፈረስ የሆነው የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አመራር ተብዬዎች ቀድመው 5 ኪሎ የሚገኘውን የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅጥር ግቢን ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ አጥለቅልቀዉት ነበር፡፡ ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ከአዲስ አበባ ውጪ የመጡ የማኅበረ ቅዱሳን ተቃዋሚዎች ከቅጥሩ ውጪ መቆም ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

ከስብሰባው ዕለት ቀደም ብሎ የማኅበረ ቅዱሳን የግል ንብረት የሆነውና በቤተ ክርስቲያን ላይ የወሬ ዘመቻ ከፍቶ የሚገኘው ደጀ ሰላም ድረ ገጽ፣ ሰልፉ የሚካሄድ ከሆነ ሰንበት ተማሪዎች ይበጠብጣሉ የሚል የተለመደ የዐመፅ ጥሪ አስተላልፎ ነበር፤ ጥሪውን ሰምቶ የመጣ የሰንበት ተማሪ መኖሩን ማረጋገጥ ባይቻልም፣ ግቢውን ሞልተው የታዩት ብዙዎቹ ግን የሰንበት ትምህርት ቤት ልብሰ መዘምራን የለበሱ፣ ነገር ግን ከየመንደሩ በገንዘብ የተገዙ ወጣቶች ሲሆኑ፣ ፀጉራቸውንራስታ ስታይልየተሠሩ፣ ከንፈራቸው በሲጋራ ጢስ የወየበ፣ ጥርሳቸው በጫት የበለዘ፣ በመዘምራኑ ልብስ ውስጥ እንደ ጩቤና ሰንጢ ያሉ የመውጊያ መሣሪያዎችን የታጠቁ ቦዘኔዎችም እንደተካተቱበት ለመታዘብ ተችሏል፡፡ ከመዘምራኑ መካከል ያነጋገርናቸው አንዳንድ ወጣቶች ለምን እንደ መጡ እንኳ እንደማያውቁ የተናገሩ ሲሆን፣ አንዳንዶቹምለቅዱስ አባታችን ሰላምታ ታቀርባላችሁ ተብለን ነው የመጣነውሲሉ መስክረዋል፡፡
የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው አንዳንድ ዐመፀኛ ግለሰቦችና ቡድኖች ሰውን በቀላል መንገድ ለዐመፅ በማንቀሳቀስ የተካኑ መሆናቸው አዲስ ነገር ባይሆንም፣ በዐላማ የሚያስከትሉት ሰው ስለሌለ ግን በዐመፅ መንገድ የሚያገኙት ድል ጊዜያዊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደ ተጻፈው፣ ብር ሠሪ የነበረው ድሜጥሮስ ከጣዖት ምስሎች ሽያጭ ያገኝ የነበረው ዳጎስ ያለው ትርፍ በጳውሎስ የወንጌል አገልግሎት ስለ ቀረበትና ገበያውም ስለ ተቀዛቀዘበት፣ ከገበያ ውጪ እየሆነ መምጣቱም ስላሳሰበው፣ የኤፌሶንን ሕዝብ አሳምፆ ነበር፤ ነገር ግን የተከተለው ሕዝብ በአብዛኛው ለምን እንደ ተሰበሰበ የማያውቅ ነበር፤ ቃሉም ሲመሰክርወዲያና ወዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በጉባኤው ድብልቅልቅ ሆኖ የሚበልጡት ስንኳ ስለ ምን እንደ ተሰበሰቡ አላወቁም ነበርና።ይላል (የሐዋርያት ሥራ 1932)፡፡ የድሜጥሮስ የግብር ልጅ ማኅበረ ቅዱሳን የጠራውና ለምን እንደ ተሰበሰቡ የማያውቁ ወጣቶችን ያቀፈው አደናቃፊ ሰልፍም ተመሳሳይ ዐላማ ነበረው፡፡ ነገር ግን ምን ጊዜም ድሉ የእግዚአብሔር በመሆኑ በዚህ አደናቃፊ ሰልፉ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ረባሽነቱን ያሳየበትና ራሱን እጅግ ያስገመተበት የሁከት ጉባኤ ነበረ ማለት ይቻላል፡፡

ለመረበሽ ወደ ግቢ የገቡት ወሮበሎች ወደ ግቢ ከገቡ በኋላ ልብሰ መዘምራኑን አውልቀው ሌሎች ወሮበላ ጓደኞቻቸው ከውጪ ወደ ውስጥ እንዲገቡ ያቀብሏቸው እንደ ነበር የታዘብን ሲሆን፣ እነ ዲያቆን ትዝታው የአገልግሎት ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ግቢ ሲገቡ ከወሮበሎቹ አንዱ ዲያቆኑን ለመውጋት የሠነዘረው ስለት የሞነጨረው ቢሆንም አንዳች ጉዳት አላደረሰበትም፡፡ የደጀ ሰላም ታናሽ ወንድም የሆነው አንድ ድረ ገጽ ግን፣ ትዝታውና በጋሻው ሆስፒታል ተኝተዋል በማለት በሬ ወለደ ወሬውን አናፍሶታል፡፡

ሌሎች በጠሩት ሰልፍ ላይ ሳይጠራ የመጣውና በረብሻ ሰልፉን የእርሱ ያስመሰለው የማኅበረ ቅዱሳን ጀሌ፣ ያሰማ በነበረው የምስጋና ወይም የልመና ሳይሆን ፖለቲካ ቀመስ ዝማሬዎች ሊደብቀው ቢሞክር አልደበቅ ያለውን የማኅበሩን ፖለቲካዊ አቋም አንጸባርቆበታል፡፡ ቀድሞ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች በሚጠሯቸው ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ይዘመሩ የነበሩ እኒያ ዝማሬዎች ይህን የብጥብጥ መርሐግብርም አድምቀውታል፡፡

ከቤተ ክርስቲያን በኩል ጸጥታ እንዲከበር ጥሪ ሲተላለፍ አንሰማም በማለት ሲያውኩ ላመሹት ለእኒህ የማኅበሩ ቅጥረኞች፣ መመሪያ ሲሰጥ የነበረው ከሁለት የእዝ ጣቢያዎች መሆኑ ሲታወቅ፣ አንደኛው በወቅቱ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ ከነበረውና ዘወትር ነጭ ለብሶ 4 ኪሎ ሰፈር ያለ ሥራ ሲንቀዋለል ከሚውለው የማኅበረ ቅዱሳኑ ፈሪሳዊ ማንያዘዋል ነበር፤ ሁለተኛ የእዝ ጣቢያ ደግሞ መቀመጫውን እዚያው 4 ኪሎ በሚገኘው ሮሚና ካፌ ውስጥ አድርጎ ነበር፤ የእዚህ እዝ ጣቢያ አመራር ሰጪ የነበረው የፈረንሳይ አቦ ሰባኪ የሆነው በላይ ወርቁና ግብር አበሮቹ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነርሱ ካሉበት ሆነው ውስጥ ካሉት ጋር እየተደዋወሉ ዐመፁ እንዲጧጧፍ አመራር ሲሰጡ የነበረ ሲሆን፣ የሮሚናው እዝ ጣቢያድኅንነቶች መጡላችሁሲባል ሁሉም ባገኘው ቀዳዳ ሁሉ እግሬ አውጪኝ ብሎ መበታተኑን ከዐይን ምስክሮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ላይ ተኮልኩለው የነበሩና በር ተዘግቶባቸው በውጪ ለመቆም በተገደዱት የማኅበረ ቅዱሳን ተቃዋሚዎች ላይ፣ እንደ እስጢፋኖስ ገዳዮች አባቶቻቸው የድንጋይ ናዳ ለማውረድ ተሰናድተው የነበሩትን ማጅራት መቺዎች እንቅስቃሴ በንቃት የተከታተለው ፖሊስ ከዚያ ላይ እንዲወርዱ በማድረግ በታትኗቸዋል፡፡

ረብሻው ቢያይልም ከቤተ ክርስቲያን በድምፅ ማጉያ ጸጥታ እንዲከበር ተደጋጋሚ ጥረት ተደርጎ አንዳንድ መመሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ ሰልፍ እንደሚደረግ በይፋ የታወቀ ነገር ባለመኖሩ በዚህ መልክ ውይይት ለማድረግ አስቸጋሪ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተለይም የሰንበት ትምህርት ቤት የመዘምራን ልብስ የለበሱትን ረባሾች፣ ችግር ካለ በየሰበካ ጉባኤያችሁ ልትፈቱ ይገባል የተባለ ሲሆን፣ በዚያ አልፈታ ካለም ደረጃ በደረጃ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነት አካላት በማቅረብ ውሳኔ ሊገኝ እንደሚችል ተገልጿል፤ ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ መምጣት የሚገባው በየደረጃው ተሞክሮ አልሆን ያለ እንደ ሆነ ብቻ መሆኑም ተነግሯቸዋል፡፡ ይሁንና አሁን ማድረግ የሚቻለው በተወካዮቻቸው አማካይነት የሁለቱንም ወገኖች ሐሳብ መስማት ስለሆነ ተወካዮቻቸውን እንዲመርጡና በእነርሱ አማካይነት ንግግሩ እንዲካሄድ መድረክ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኞች ያዘጋጁትንና አባ ሠረቀ ከሥልጣን ይውረዱልን የሚል ይዘት ያለውን የአቋም መግለጫ ካሰሙ በኋላ፣ (የአቋም መግለጫቸው በመምሪያው ኀላፊ ላይ ማተኮሩ፣ ከጀርባ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ያጋለጠ ተግባር ነው፡፡) ከዚያኛው ወገን ተወካዮች ሊናገሩ ሲቀርቡ በጩኸት ተቃውሞአቸውን በማሰማት እንዳይናገሩ ከልክለዋል፡፡ ይህም በፓትርያርኩና በብዙዎቹ ጳጳሳት ዘንድ አልተወደደም፡፡ እንዲያውም ፓትርያርኩ ተቆጥተውእናንተን አዳምጠው እነርሱ እንዳይናገሩ በጩኸት መከልከል እናንተ ችግር እንዳለባችሁ ያሳያልሲሉ፣ ችግር ያለባቸው እነርሱ መሆናቸውን ነግረዋቸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በማግሥቱ እሑድ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በተደረገው የጸሎተ ፍትሐት መርሐ ግብር ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩትናንት ልጆቻችንን ልብስ አልብሰው ሲረብሹ ያመሹት እነማን እንደ ሆኑ ዐውቀናል፤ የፖለቲካ አጀንዳ ያላችሁ ሰዎች በሕፃናት ልጆች ለመጠቀም እንዳሰባችሁ ደርሰንበታልሲሉ ከብጥብጡ ጀርባ የማኅበረ ቅዱሳን እጅ መኖሩን አመላክተዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እሳትን በሰው እጅ ለመያዝ እንደሚሞክር ብልጣብልጥ እንደሚታይ ከዚህ ንግግር መገንዘብ ይቻላል፡፡

ቅዱስነታቸው ከካቴድራሉ ከወጡ በኋላ ከቅድስት ሥላሴ ደቀ መዛሙርት በቀረበላቸው የቁርስ ግብዣ ላይ መገኘት ቢፈልጉም፣ ከተለያዩ ከተሞች የመጡትንና ትናንት ድምፃቸውን ማሰማት ያልቻሉትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማነጋገር አለብኝ በሚል፣ 4 ጳጳሳትን ወክለው ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ነው ያመሩት፡፡ ከተለያዩ ከተሞች ከመጡ የማኅበረ ቅዱሳን ተቃዋሚዎች ጋር 330 ሰዓት የፈጀ ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ በተለይ ከአዋሳ የመጡት የቤተ  ክርስቲያን ልጆች ለፓትርያርኩ ያላቸውን አክብሮት የገለጹ ሲሆን፣ላለፉት 17 ዓመታት የተቃዋሚዎችዎን ጋዜጦች እያነበብን ጠልተንዎ ኖረናል፡፡ አዋሳ የመጡ ጊዜ ግን እውነተኛ አባትነትዎን አየን፤ እዚህ ድረስ የመጣነውም የአባትነትዎን ፍቅር አይተን ነውና ከሰው በላው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲያስጥሉን እንለምንዎታለንሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አንዳንዶችም አቡነ ገብርኤል ያደረሱባቸውን በደል በመዘርዘርና ከዚህ በፊት በዕንቁ መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን ቃል አቀባይ ሆነው የቀረቡበትን ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ፣ ተገቢ ያልሆነና ከአንድ ጳጳስ የማይጠበቅ በደል እንዳደረሱባቸው በማውሳት፣ በአቡኑ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አንጸባርቀዋል፡፡ በየጊዜው ተለዋዋጭ ገጸ ባሕርይ ተላብሰው የኖሩትና በአንድና ወጥ በሆነ ጠባይ የማይታወቁት አቡነ ገብርኤል፣ የተለያዩ ቅጽል ስሞች ሲወጡላቸው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን፣ እግዚአብሔር የተለያት ካሏት ቤተ ክርስቲያንና ከቅዱስ ሲኖዶስ ነጻ መውጣታቸውን እንዳልገለጹ ሁሉ፣ ከኮበለሉ በኋላ እንደገና ታርቀው በተመለሱ ጊዜ፣አባ ልደቱየሚል ስም ወጥቶላቸው የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሕዝቡ ጠልቷቸው ይልቀቁልን እያላቸው እርሳቸው ግን፣ ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጣቸውን ተልእኮ ሳላስፈጽም ከአዋሳ አልወጣም የሚል ግትር አቋም በመያዛቸውአቡነጋዳፊ የሚል ስም የወጣላቸው መሆኑን ከአዋሳ ወገኖች ለማወቅ ተችሏል፡፡         
 

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወደ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሄዱት አራቱ ጳጳሳትም ከቁርስ በኋላ ባሰሟቸው ንግግሮች በቅዳሜው አሳፋሪ ድርጊቱ ማኅበረ ቅዱሳንን ኮንነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስልጆቻችንን መግፋት የለብንም፤ ያጠፉም ካሉ እንመክራለን፡፡ካሉ በኋላእናንተ ብትበረቱ ኖሮ የትናንቱ ዐመፅ አይኖርም ነበርሲሉ ማኅበረ ቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ ያልተጠቀሙበትን ክፍተት ተጠቅሞ ግዛቱን እንዳሰፋ ጠቁመዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በበኩላቸውተሐድሶ፣ ኦርቶዶክስ የሚባል የለም፤ አትከፋፍሉን፤ እኛ አንድ ነንማለታቸው ተሰምቷል፡፡

በዕለቱ ምሽት ላይ ማኅበረ ቅዱሳን ለብፁዓን ጳጳሳት ባዘጋጀው የራት ግብዣ ላይ ተግሣጽ አዘል ንግግር ያሰሙት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ደግሞሳህን አጥባችሁ ከማቅረብ ልባችሁን አጥባችሁ ቅረቡ፡፡ እግዚአብሔር በአጉሊ መነጽር ሳይሆን በልብ ንጽሕና ነው የሚታየውበማለት በራት ግብዣ ሰበብ እኩይ ግብሩን ለመሸፈን የሚሞክረውን ማኅበረ ቅዱሳንን ገሥጸዋል ተብሏል፡፡

አሜሪካ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድታሊባንእየተባለ የሚጠራውና በኢትዮጵያ ደግሞ ወሃቢያ የሚል የግብር ስም የወጣለት ማኅበረ ቅዱሳን፣ በሁከትና በብጥብጥ ዕድሜውን ለማራዘም ቢጥርም ዕድሜውን ይበልጥ እያሳጠረው እንደሚገኝ ከሰሞኑ አካሄዱና በየጊዜውም እየገጠመው ካለው የሕዝብ ተቃውሞ መገንዘብ ይቻላል፡፡ የሲኖዶሱን ስብሰባ ውጤትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ለወደፊት ዘገባ ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡

11 comments:

 1. NICE AND CLEAR. BERTU WEGENOCHE

  ReplyDelete
 2. እናንተ ሽብርተኞች ምኞታችሁና ሃሳባችሁ ምድራዊ የሆነ ታሊባንነታችሁን ያሳያችሁበት ጽሁፍ በመሆኑ በጽሁፋችሁ ተደስቻለሁ ።

  ReplyDelete
 3. Endih betilacha sitisekayu endemitimotu ergit new. No matter what you say, you wouldn't affect MK in any way. Infact, you will add more grace to it. Since your true picture has already been known, its clear why you are so against MK like a mad dog. Bechirash litashenifut atchilum Mahiberun. Menfesawi, chewa, chirstianawi mahber new. Ende enante tera menafik ena zeregna ayidelem.

  Erir dibin tilalachihu enji MK will continue to work for the church and ear its reward from above. Period.

  ReplyDelete
 4. በእውነት በቦታው ነበርኩ ያሳዝናል፡፡ እንዲህ ያለ ትውልድ እንዲህ ያለ ነፍሰ ገዳይ ስላተረፍን ልናለቅስ ይገባናል፡፡ ዛሬ ለእነዚህ ተሐድሶ ለተባሉት አገልጋዮች ዝም ብንል ነገ በሁላችን ይደርሳል፡፡ አንድ ሊቀ ጳጳስ ‹‹ለካ የሚወነጀሉት እንዲህ ባሉት ዱርዬዎች ነው? እኛ እኮ አምነናቸው ነበር፤ ዛሬ ግን አወቅናቸው›› በማለት ሲናገሩ ስሰማ የማቅ ማንነት የተጋለጠበት መሆኑን በማሰብ ደስ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 5. በእውነት በቦታው ነበርኩ ያሳዝናል፡፡ እንዲህ ያለ ትውልድ እንዲህ ያለ ነፍሰ ገዳይ ስላተረፍን ልናለቅስ ይገባናል፡፡ ዛሬ ለእነዚህ ተሐድሶ ለተባሉት አገልጋዮች ዝም ብንል ነገ በሁላችን ይደርሳል፡፡ አንድ ሊቀ ጳጳስ ‹‹ለካ የሚወነጀሉት እንዲህ ባሉት ዱርዬዎች ነው? እኛ እኮ አምነናቸው ነበር፤ ዛሬ ግን አወቅናቸው›› በማለት ሲናገሩ ስሰማ የማቅ ማንነት የተጋለጠበት መሆኑን በማሰብ ደስ አለኝ፡፡

  ReplyDelete
 6. This article truly reflects who you really are.Thank you for your help.The evil spirit always know how to curse rather than objectively critisize.You have nothing good to say and do.

  ReplyDelete
 7. Hello Aba Selama blogger, thank you for posting my 2 critical comments. Appreciate it. In this regard aba selama is better than Dejeselam and Daniel's blog who selectively post comments.Good job! As to your faith you are free to practice whatever you want. But please don't interfere in other religions like EOTC.Also be professional in your articles. Have facts ready not myths.

  ReplyDelete
 8. wow! mehaber sitan!

  ReplyDelete
 9. I am surprized on how much MK members have been released out of the chain of MK. Before Daniel Kibret published their innermost hub to Dejeselam blog, the members had been participating in giving comments but after so the comment givers become less than ten;even in serious issue. How deteriorating it is!
  Not the dying but the dead orginazation-MK!

  ReplyDelete
 10. MK North America born in Dallas, TX. I think your reader may visit this Blog http://www.dallaseotc.blogspot.com/
  How create shame not only the Ethiopian Origin and friends but for all Christian and particularly for the followers of EOTC. And there is hundreds of thousand dollars checks issued and unaccounted from the Dallas St, Michael Cathedral which was embezzle by MK

  ReplyDelete
 11. you gugs ,you are not absolutely from our MOTHER church. you just showed us where you from. DIABLOS

  ReplyDelete