Saturday, October 29, 2011

ሃይማኖቶች ስለፍርድ፦


የትኛውም ሃይማኖት በንድፈ ሃሳብ ደረጃ (theorically) ከሚያመልከው አምላክ ሕግና
ትእዛዝ ከወጣ ቁጣና ቅጣት እንደሚጠብቀው የወል የእምነት ስምምነት አለ። ይህንኑ ቅጣት
አስቀድሞ ለመከላከል በሕይወታቸው ሳሉ ያደርጉ ዘንድ የሰጣቸውን መመሪያ በሚችሉት አቅም
ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ተግባራዊ ለማድረግ ደፋ ቀና ማለታቸውም አይቀሬ ይሆናል።
እንደዚያም ሆኖ ከሞተ በኋላ መልካሙ ሥራው መልካም ዋጋው ሆኖ ስለመከፈሉ ወይም ቁጣን
ስለመቀበሉ ማረጋገጥ አይችሉምና ከአጠገባቸው ለተለየው ሟች በመሪር ልቅሶና በልዩ ልዩ ዓይነት
የሥርዓት አቀባበር ሰውዬውን በመንከባከብ እንዲሁም በማሰማመር የልባቸውን ስሜት በጥሩ
መንፈስ ለመሙላት ይጥራሉ። ምግብና መጠጥ፤ ማብሰያ ቁሳቁስና አልባሳትን ጭምር እዚያ
በጉድጓዱ ከተማ እንዳይቸገር አብረው በመቅበር የችግሩ ልባዊ ተካፋዮች ለመሆን ሁሉን
ያደርጉለታል።
ጉድጓዱን ጥልቅ በማድረግ፤ ወደ ጎን ልዩ የኪስ ጉድጓድ በማዘጋጀት፤ የሬሳውን
የማረፊያ አቅጣጫ ወደምሥራቅ፣ ወደምዕራብ ወይም በቁመት በመቅበርም ዘላለማዊ እረፍት ያገኝ
ዘንድም ይደክሙለታል። አንዳንዶችም ሬሳውን ዛፍ ላይ በመስቀል ወይም በእሳት በማቃጠል
ከአምላኩ እንዲታረቅ ይጥሩለታል። ይህንና ይህንን የመሳሰለውን ሁሉ ማድረጋቸው ሰውየው
ዘላለማዊ እረፍትን እንዲያገኝ ከሚያመለከው አምላክ እንዲታረቅና ማድረግ ያለባቸውን
ባለማድረጋቸው የሟች ነፍስ እንዳትከሳቸው ከመፍራት የተነሳ ነው።
ይህ እንግዲህ ፍጹም ላልሆነው ሃይማኖታቸው የሃይማኖት ጉድለት ማሟያ ሥራዎችን በማቅረብ
የሚያምኑትን የሚመለከት ሲሆን እኛ ምሉዓን የክርስቶስ ወገኖች ነን የሚሉትን ሳይጨምር መሆኑ
ነው።
የክርስትናው ሃይማኖት ተከታዮችም ቢሆኑ ዘላለማዊ ፍርድ ስለመኖሩ ከጥቂቶቹ በስተቀር ብዙኃኑ
ይስማማሉ። ጸድቀን ጨርሰናል የሚሉቱ፤ ገነት ይህችው ምድር ናት ሌላ አንጠብቅም የሚሉ፤
ለመጽደቅ ብዙ የጽድቅ ሥራ ይጠበቅብናል ባዮች፤ የጸደቅነው በክርስቶስ ደም ነው የሚሉ
በመኖራቸው ከሞት በኋላ ስላለው የፍርድ ሁኔታ የተለያየ ግንዛቤ እንዲኖር አድርጓል። ከሞት በኋላ
የነፍስ እጣ ፈንታ በምድር በነበረው የእምነት ደረጃ ይታወቃል የሚሉ፤ በዚህ ምድር ምን መልካም
እምነት ቢኖረው ማወቅ ስለማይቻል ለሞተ ነፍስ ጥቂት የነፍስ ማስማሪያና ማስተካከያ ከምድር
ሊደረግለት ይገባል የሚሉ ወገኖች መኖራቸው አይካድም። በዚህም ይሁን በዚያ የእምነት ሕግ
ባለው ሥርዓት የሚደረገው እንደተጠበቀ ሆኖ ቅዱሱ መጽሐፋችን ግን ከሰዎች አባባልና ወግ በተለየ
ምን ይላል? የሚለውን መመልከቱ ጠቃሚ ሳይሆን አይቀርምና በዚያ ላይ ቆይታ እናድርግ!

ሃይማኖቶች ስለጽድቅ፦
«ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይመጣም» ኢዮ 7፤9
ይህ እውነት ሰዎች ሟችን ዛፍ ላይ ይስቀሉት፤ ከባሕር ይወርውሩት፤ ያቃጥሉት፤ ጥልቅ ጉድጓድ
ይዱሉት ለሲኦል የሚያበቃ በደልና ፍርድን አግኝቶ ከሆነ ከሲኦል አያወጣውም፤ አያድነውም፤
መፍትሄንም አይሰጠውም። እንዲህ የሚለውን የፍርድ ቃል ሰዎች ሰምተው አይወቁት ወይም
ሰምተውትም ቢሆን የሚሆን ቃል ነው ብለው አምነው አይቀበሉት በእርግጥና በትክክል የሚሆንና
የሚደረግ የእግዚአብሔር ቃል ነው። አዎ ሲኦል የወረደ አይወጣም!
ሰዎች ከሞት በኋላ የሚሆነውን ፍርድ ባለማወቃቸው ምንጊዜም በፍርሃትና በጭንቀት የሚኖ
ፍጥረቶች ሆነው ይታያሉ። ምንም ጥሩ ሥራ ቢሰሩ፤ የቱንም ያህል ቢያመልኩት ለእግዚአብሔር
እንደተገዙ ስለማይሰማቸው ጭንቀታቸው ከሲኦል ለመዳን በመሆኑ ከፍርሃት መንፈስ መቼም
ወጥተው አያውቁም። በእርግጥ እግዚአብሔር ለሚገዙለት ዘላለማዊ ሕይወትን ላልታዘዙለት
ዘላለማዊ እሳትን ማዘጋጀቱ አይካድም። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አማኞች በፍርሃትና በጭንቀት
እንዲገዙለት የሚሻ ሆኖ የሚኖር አምላክ ባለመሆኑ ይህ እግዚአብሔርን ጨካኝ ፈራጅ አድርጎ
በሰው አእምሮ የሚስል አመለካከት ከሰይጣን የመነጨ ካልሆነ በስተቀር ከእግዚአብሔር የሚመጣ
መንፈስ አይደለም።
ለሰዎች ኃጢአት የተገባው ዘላለማዊ እሳት ሆኖ ሳለ አንድያ ልጁን ለእሳት የሚያበቃውን የሰው
ሁሉ ኃጢአት እንዲሸከም ወደዚህ ዓለም ባልላከውም ነበር። «በእርሱ የሚያምን የዘለዓለም
ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ፤ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን
እንዲሁ ወዶአልና»ዮሐ 3፤16 የሚለው የእግዚአብሔር ቃል የታመነ ስለሆነ አምላካችን የፍቅር
አምላክ እንጂ በጭንቀትና በፍርሃት የሚገዛ ሳይሆን የሚሻው በፍቅር የሚያመልኩ ልጆቹ
እንድንሆንለት ብቻ ነው።
የሚገርመው ግን የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ እየተናገሩ በአባታቸው ቤት ስላለው ዘላለማዊ
ኑሮ እርግጠኞች ያልሆኑ ብዙዎች ናቸው። የሰው ልጅ ሥራ መቼም ለጽድቅ የሚያበቃ ባለመሆኑ
በሚሰሩት መልካም ሥራቸው እረፍት ማግኘት እንደማይችሉ ከሚነግራቸው መንፈስ የተነሳ ምን
ጊዜም እግዚአብሔር ለልጆቹ ባዘጋጀው ዘላለማዊ ኑሮ ቤተኞች ስለመሆናቸው የመናገር ድፍረቱ
የላቸውም። «በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» ሮሜ
3፤21፣31 በማለት የሚናገረው መጽደቅ ያቃተን የሰው ልጆች በጻድቁ በእግዚአብሔር ልጅ
በኢየሱስ በኩል እንድንጸድቅ እንጂ ማጽደቅ የማይችለውን ስራችንን ለእግዚአብሔር የጻድቅነት
ዋጋችን አድርገን እንድናቀርብ አይደለም። ከዚህም የተነሳ ነው በቤቱ ውስጥ መኖር ስለመቻላችን
ውስጣችን አምኖ ለመቀበል የሚቸገረው። እኔ በክርስቶስ ጻድቅ ሆኛለሁ፤ የተሰጠኝ ጸጋ ጠብቄ
በሰማያት የተዘጋጀልኝ አክሊል እቀበላለሁ ብለው በእምነት የሚናገሩትን ሰዎች እነዚህ ድፍረት
የለሾች የሚሰጡት ምላሽ ይህ አጉል ትምክህተኝነትና እራስን በራስ የማጽደቅ ትእቢት ነው እንጂ
በምንም መልኩ ሰው ራሱን ጻድቅ ስለመሆኑ ሊያውቅ አይችልም ብለው ያወራሉ። ይህ አባባላቸው
የመነጨው ወንጌል የሚናገረውን ትተው እነሱ እንደሚፈልጉት አስበው ለልባቸው ተናግረው
ስለደመደሙ ነው። ይሁን እንጂ
ሐዋርያው ለቲቶ በጻፈው መልእክቱ ይህንን ቃል በደንብ አስረግጦ ሲናገር ቲቶ 3፤5-6
«እንደምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ አዳነን እንጂ
እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ሥራ ስለነበረው ሥራ አልነበረም» ይለናል። ስለዚህ እኛ የጸደቅነው
እግዚአብሔር በልጁ በኩል ባደረገልን ነጻ ስጦታ የተነሳ ብቻ ነው። በሰማያዊው ልጁ ደም ከሞት
ወደ ሕይወት መሻገራቸውን አምነው የተቀበሉ ጻድቅ ስለመሆናቸው የተናገረው እግዚአብሔር
በመሆኑ ያንን አምነን ልንቀበል ይገባል። በክርስቶስ ደም የጸደቁ ማለት የክርስቶስን ትእዛዛት
የማይጠብቁ፤ የጽድቅ ዋጋ ተግባራትን የማይፈጽሙ ማለት አይደለም። «ብትወዱኝ ትእዛዜን
ጠብቁ» በማለቱ በክርስቶስ የጸደቁ ሁሉ የጽድቁን ትእዛዛት ይጠብቃሉ። ጻድቅ ከኃጢአት ጋር
መቼም ቢሆን ኅብረት የለውምና ነው። «እግዚአብሔርንም የሚያምኑ በመልካም ሥራ በጥንቃቄ
እንዲጸኑ፤ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ፤ ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው»
ቲቶ 3፤8 በማለቱ የሚያሳየን ነገር ያመኑቱ ሁሉ በመልካም ሥራ መጽናት እንደሚገባቸው ነው።
ከላይ እየተመለከትን እንደመጣነው ሰዎች ትእዛዛቱን የሚጠብቁት በክርስቶስ ደም የቀደመ
ኃጢአታቸው ተደምስሶ ጻድቅ የመሆንን ብቃት እንዲያው ስለተሰጣቸው እንጂ ያልተሰጣቸው
ጽድቅ ገና ለማግኘት ለጻድቅነት የሚያበቃ ሥራ መሥራት የግድ ስለሆነባቸው አይደለም። ያማ
ከሆነ የክርስቶስ ሞት ባላስፈለገም ነበር። የተሰጠንን የጽድቅ ስጦታም መካድ ይሆናል። ሁላችን
በኃጢአት የሞትና ለጽድቅም የሚያበቃ ምንም ነገር ስላልነበረን ይህንኑ ባዶነት ሊሞላ አምላክ
የሰው ልጅ ሆኖ ተገለጠ። «ሁሉም ኃጢአት ሰርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል፤
በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ» ሮሜ3፤23-24
«አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንደሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታ አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ
ሰው ለኲነኔ መጥቷልና፤ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ» ሮሜ 5፤16-17
ክርስቶስ የመጣው በአዳም በኩል የጠፋውን ጽድቅ መልሶ እኛን ሊያጸድቅ እንጂ በእኛ ሥራ
የጽድቅን ዋጋ እንዲሰጠን እንዳይደለ ቃሉ የሚናገረውን መቀበል የግድ ነው። ይህን አለመቀበል
መብት ቢሆንም የእግዚአብሔርን ቃል እውነተኛነት ያስቀረዋል ማለት ባለመሆኑ ላመኑበት የሚሰራ
ኃይል ያለው እውነት ነው። በክርስቶስ ስጦታ የጸደቁና የጽድቁን ትእዛዛት የሚጠብቁቱ
የእግዚአብሔር ልጆች ስለመሆናቸው የሚገባቸውን የብቃትነት ምስክር ለመናገር አንዳች ስጋት
የለባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መተማመን በግልጽ ቃል
ሰጥቶናል። «በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።
የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል» ሮሜ8፤14-
16 ማለቱ ለንባብ ሳይሆን ለእውነት የተነገረ ነውና።
የጽድቅ ዋጋ ከሞት በኋላ፦
እግዚአብሔርን ባምንም ከሞት በኋላ እጣ ፈንታዬ ከክርስቶስ ጋር ይሁን ሲኦል ምንም የማውቀው
ነገር የለም፤ እንዲያው በቸርነቱ ካልማረኝ በቀር የኔ ነገርስ እንጃ! የል ሰው ቁጥሩ ጥቂት
አይደለም። ከዚህ የባለሙሉ ተስፋነት ጉድለት ለመዳን የሆነ መተማመኛ ነገር ሊፈልግ ይገደዳል።
አብዝቶ በመጾም፤ በመስገድ፤ በመጸለይ፤ የመቁረብ ብቃቱን እድሜ ልኩን እንደማያሟላ
ቢያውቅም እንኳን ቆሞ በማስቀደስ፤ ከገዳም ገዳምና ከደብር ደብር በመዞር፤ ከ 7 የበለጠም
ሲያገኝ ባለ 12 እና ባለ 30 ትውልድ የቃልኪዳን ቤዛ በመፈለግ ተጠምዶ ለራሱና ለወገኖቹ
ለመትረፍረፍ እንደሚባክን የሚታወቅ እውነት ነው። እሁድ ቀን እባብ ቢገድል፤ ስሙን በአንዱ
ኃያል ጻድቅ ስም ቢያወጣ፤ ዳቤውን ቢበላ፤ የንፍሮውን ውሃ ቢጠጣ፤ አፈር ትቢያ ቢልስ፤ ይህንን
ሁሉ አድርጎ እኔ ጻድቅ ነኝ ብሎ የመናገር ድፍረት የሌለው ሰው ከመሆን አያመልጥም። ዛሬም
እንደቸርነቱ ካልሆነ እኔ መዳኔን አላውቅም ብሎ ይናገራል። ይህንን ማለቱ እግዚአብሔር ታላቅ
ስለሆነ እንደቸርነቱ ስል እኔ በፊቱ ትሁት መሆኔን ያንጸባርቅልኛል ብሎ ራሱን ይሸነግላል። በዚህ
ምድር ጻድቅ የመሆንን ብቃት የተሰጠው ለተወሰኑት ብቻ ነው ብሎ ያምናል። ይህ ግን
እግዚአብሔር ከተናገረው ቃል ጋር የማይስማማ ነው። «ልጆች ሆይ ማንም አያስታችሁ፤ እርሱ
ጻድቅ እንደሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው» 1 ኛዮሐ 3፤7 የተነገረው ለሁላችን እንጂ
ለተወሰኑት ብቻ እንዳልሆነ ያረጋግጥልናል። ይህንን አምኖ ለመቀበል የሚቸገረው ምንጊዜም
የልፋቱና የድካሙ መነሻ ነገር እኔ በክርስቶስ ደም በነጻ ጻድቅ ሆኛለሁ፤ ይህንን ጻድቅነት ጠብቄ
ለመኖር ነው ትእዛዛቱን የምጠብቀው ብሎ ስለማያምንና ከክርስቶስ ዘንድ ገና የሚሰጠኝን ጻድቅነት
ዋጋ ለማግኘት የግድ መታገል አለብኝ ብሎ ስለሚያምን ብቻ ነው።
አባታችን ኖኅ በእምነቱ ጻድቅ የተባለው ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ቃል እውነት ነው ብሎ
በተቀበለበት ሰዓት እንጂ የዝናሙ ውሃ ከጎደለና የብስ ላይ ካረፈ በኋላ አይደለም። ኖኅ ከውሃው
ቁጣ የዳነው ገና መርከብ ሳይሰራና ከእግዚአብሔር ቃል በደረሰው ሰዓት ባመነ ጊዜ እንጂ አራራት
ተራራ ላይ ባረፈበት ሰዓት አይደለም። በደረቁ የብስ፤ መርከብ ሊያንሳፍፍ የሚችል የውሃ ዘር
በሌለበት ወቅት አንተና ቤተሰቦችህ ትድናላችሁ ባለው ጊዜ ከእግዚአብሔር የወጣ ቃል እውነትና
የሚደረግ መሆኑን በማመኑ ያን ጊዜ ጻድቅ ተባለ እንጂ ለጻድቅነት የሚያበቃውን መርከብ
የመሥራት፤ በቅጥራን የመቀባት፤ እንስሳቱን በየወገናቸው የማስገባትና በማየ አይኅ ላይ መንሳፈፍ
ከጀመረ በኋላ አይደለም። መጀመሪያ የተነገረውን አምኖ ሲቀበል ጻድቅ ተባለ፤ ከዚያም የጻድቅነት
ሥራን የተሰጠውን መመሪያ በመፈጸም አሳየ። አራራት የእምነቱ ምእራፍ እንጂ የእምነቱ መነሻ
አይደለችምና የጥፋት ውሃን በእምነት አውቆ መርከብ ሰራ፤ ጻድቅም ተባለ። ዕብ 11፤7 ሌሎቹ
እንደኖኅ ሰምተው ለመሥራት ባልፈለጉ ጊዜ ተፈረደባቸው እንጂ ውሃ ካሰጠማቸው በኋላ
የተፈረደባቸው አይደሉም። የተነገረውን አምኖ ባለመቀበል አስቀድሞ የተሰጠውን የጥፋት ፍርድ
በሲኦል በተመሰለው በውሃ መስጠም አረጋገጡ።
ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታው እንደፈለገው ሆኖ አገልግሎቱን በመፈጸሙ በሕይወት ሳለ የጽድቅ
አክሊል ተዘጋጅቶልኛል አለ እንጂ የጽድቅ አክሊል እንደሚሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ ብሎ
አላስተማረንም። ይልቁንም «መገለጡን ለሚጠብቁ ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም» ይለናል። 2 ኛ
ጢሞ4፤8
ታዲያ የኔ እጣ ፈንታ ሲኦል ይሁን ገነት ካለቸርነቱ እኔ አላውቅም የሚሉ መምህራን ያለንን
የእምነት ድፍረት በመፈታተን ሊያስክዱን ይሻሉ። በፈተና የሚጸናስ የክብርን አክሊል ይቀበላል
ተብለን የለ እንዴ? ያዕ 1፤12
ስለሆነም የጻድቅነትን ክብር ያገኘነው ከኛ ሥራ ሳይሆን ነጻ ከሆነው ከእግዚአብሔር ስጦታ የተነሳ
ነው።ትእዛዛቱንም የጠበቅነውና የምንጠብቀው ጻድቅ ስለሆንና የተዘጋጀልንን የጽድቅ አክሊል
ለመቀበል እንጂ በመውጣት በመውረድ ድካማችን የጻድቅነት ክብር እንዲሰጠንና በሰማይ ደግሞ
እጣ ፈንታችን የት እንደሆነ ባለማወቅ ግምት እንድንኖር አይደለም።
«ጻድቅ በእምነት ይኖራል»ሮሜ1፤17 በማለት እንተናገረው በደረቂቱ የብስ ጻድቅ ስለመሆናችን
ባገኘነው እምነት ባገኘነው የኖኅ መርከብ ጽድቃችንን እስከመጨረሻው ጠብቀን፤ በአራራት የጽዮን
ተራራ በተዘጋጀልን እረፍት በጽድቅ አክሊል እንከብራለን እንጂ ከተራራው ምእራፍ ሳይደርስና
የተነገረውን ሳይሰማ ውጭ እንደቀረው ቁራ መጀመሪያችንንና መጨረሻችንን የማናውቅ
አይደለንም።
ከሲኦልስ?
ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ምንም የተጨበጠ እምነት የሌላቸው እነዚህ ሰዎች የመጨረሻ እጣ
ፈንታዬን ስለማላውቅ እያሉ ሲኦል ከወረዱም በኋላ ቢሆን የሚታደጋቸውን ብልሃት ከወዲሁ
ለማዘጋጀት ተገደዋል። የሚያሳዝነው ነገር ቢኖር ሲኦል የገባች ነፍስ ከዚያ መውጣት አለመቻሏን
አለማወቃቸው ነው።
«ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ ሲኦል የሚወርድም ዳግመኛ አይወጣም»ኢዮ 7፤9
ያለእግዚአብሔር የታመነ ነው።ይህንን የማይቀበል የዋህ ግን፤ እጣ ፈንታው ሲኦል ከሆነ
ሊታደጉትና ከሲኦል ፍርድ ሊያድኑት የሚችሉ ሰዎችን በዚህ ዓለም ሳለ ለማዘጋጀት ብዙ ለመጣር
ይገደዳል። «ዘተሰርዓ በምድር ተሰርዓ በሰማይ» በምድር የተሰራው በሰማይም ተሰርቷል የሚል
ማደንዘዢያ በመጠቀም «እኔ ከዓለም ስላልሆንኩ እናንተም ከዓለም አይደላችሁምና ስለዚህ ዓለም
ይጠላችኋል» ዮሐ 15፤19 የተባለውን ቃል ክደው የዚህ ዓለም አሰራር ሁሉ ከዚህ ዓለም ገዢ
እንደሚመነጭ ባለማመን በዚህ ዓለም ያለውን አሰራር ወደሰማይ ገልብጠው በሰማይም ያለው
የፍርድ ሂደት ከዚህ ዓለም ተመሳሳይ ነው በማለት ሰው ሁሉ እንደዚህ ዓለሙ አሰራር የሰማይ ቤት
አማላጅ እንዲፈልግ ያታልሉታል። የሰራውን ሰርቶ ከሞቱ በኋላ ሲኦል የሚያስገባ ፍርድም
ቢያጋጥመው በጠንካራ ባለቃልኪዳንና «ፊት የማያስመልስ አንገት የማያስቀልስ» ሰው በአማላጅነት
ከያዘ የሲኦሉ ፍርድ ወደተረትነት እንደሚቀየር ውስጡን አሳምኖ በዚህ ምድር ሳለ እንዲህ ዓይነት
ጠንካራ ሰው በማደን ተጠምዶ ይኖራል። ይሁን እንጂ በሰማያዊ ፍርድ እንዲህ ዓይነት የእቃ እቃ
ጫወታ የለም። «ሰው አንዴ ከሞተ የሚጠብቀው በዚህ ምድር ለሰራው ሥራ ፍርድ ብቻ ነው»
ዕብ 9፤27 በሌላ ቦታም እንዲህ ተጽፏል። «ለሚያፌዙ ሰዎች ፍርድ፤ ለሰነፎችም ጀርባ በትር»ምሳ
19፤29 የተዘጋጀ የእግዚአብሔርን ፍርድ ሊመልስ የሚችል ከሰው ልጅ መካከል አንድም የለም።
«...ከእግዚአብሔርስ ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃል?»ሮሜ 2፤3 በፍጹም አታመልጥም፤
የሚያስመልጥህም የለም። ዳዊትም በመዝሙሩ « ኃጢአተኞች ሁሉ ወደሲኦል ይመለሳሉ፤
እግዚአብሔርን የሚረሱ አሕዛብ ሁሉ» መዝ 9፤17 ኃጢአተኞች እጣ ፈንታቸው ሲኦል እንጂ
ከአፉ የወጣውን የእግዚአብሔር ቃል አስቀይሮ ከሲኦል ሊያስወጣ የሚችል ማንም የለም። የኖኅ
ዘመን ሰዎች የተነገረውን ባልተቀበሉና ለመስራት ባልፈለጉበት ወቅት የተዘጋጀው ፍርድ
የደረሰባቸው መሆኑ እንደታወቀ ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የማይፈጽሙ የዚህ ዘመን ሰዎችም
እንዲሁ መሆናቸውን እናረጋግጣለን።
በሉቃስ ወንጌል 16፤20-25 ላይ በዚያ ሀብታምና በደሃው አልዓዛር መካከል የነበረው የዚህ ዓለም
የደሃና የሀብታም የጭካኔ አሰራር የተነሳ ከሞት በኋላ አልዓዛር በአብርሃም አበ ብዙኃን እቅፍ
ሲያርፍ፤ ሀብታሙ ደግሞ የመጨረሻ እድሉ ሲኦልን ማግኘቱን እናነባለን። የእሳቱ ቃጠሎ እረፍት
ቢነሳው «የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ» ባለው ጊዜ
የሰጠው መልስ «ከዚህ ወደእናንተ ማለፍ እንዳይችሉ፤ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደእኛ እንዳይሻገሩ
በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጓል አለ» እና ገደሉን ተሻግሮ መውጣትና ማውጣት
እንዳይቻል ያደረገን የአምላክን ፍርድ ማን ያሻሽለዋል? የኔስ ፍርድ አንዴ ተፈጽሟል «ከመሬት
ላሉ 5 ወንድሞቼ ወደዚህ እሳት እንዳይመጡ ይነግርልኝ ዘንድ ስደድልኝ» ሲለው ከአብርሃም
የተሰጠው መልስ «ሙሴና ነብያት የነገሩአቸውን ይስሙ» ነው ያለው እንጂ «አብርሃም አባት ሆይ
ማረኝ...»ቁ,24 ብሎ ስለለመነ ምህረት አላሰጠውም። ከመሬት ላሉ ወንድሞቹም ተስፋ የሚሰጥ
አማላጅ እንዲላክላቸው አላደረገም። ይልቁንም የመዳን ተስፋቸው በሙሴና በነብያት መጻሕፍት
መሰረት በሚኖሩበት ሕይወት እንደሚወሰን በግልጽ ተነግሯል። አብርሃም አባት...እያለ ሲጣራም
«መቼ እኔን በአማላጅነት ያዝከኝና ነው» አላለውም። «አቤቱ እንደእጃቸው ሥራ ዋጋቸውን
ትከፍላቸዋለህ» ሰቆ ኤር 3፤64 እንዳለው «በምድር ለነበረህ ሥራ የተከፈለህ ዋጋ ነው አሁን አንተ
ያለህበት ቦታ» በማለት በግልጽ ነግሮታል።
«ወንድም ወንድሙን አያድንም፤ ሰውም አያድንም፤ ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም...ነገር
ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴንም ከሲኦል ይቤዣልና» መዝ 48(49)6-20 ነፍስን ከሲኦል
የሚቤዥ ያለእግዚአብሔር ማንም የለም!! ከሞት በኋላ ተስፋ ሊሆን የሚችል እሱ ማነው?
ለእያንዳንዱ እንደሥራው ይከፍል ዘንድ ዋጋው ከእርሱ ጋር ካለው አምላክ የሚደራደር እሱ
ማነው?ራእ 22፤12 «ነፍሱንስ ከሲኦል እጅ የሚያድን ማነው?» መዝ 88(89)፤48
ያለእግዚአብሔር ማንም የለም። «እርሱ ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀና ይችላል?»መክ 7፤13
ማንም አይችልም። «የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቧል የሚያስጥለውስ ማነው? እጁም
ተዘርግታለች የሚመልሳት ማነው?»ኢሳ 14፤27 ከቶ ማንም ሊኖር አይችልም።
ከሲኦል ፍርድ ሊታደግ የሚችል ፍጡር ማንም የለም!!
ከሲኦል የሚታደግ ያለእግዚአብሔር ማንም እንደሌለ ቅዱስ ቃሉ ከነገረን ሲኦል የወረደ ሊወጣ
ይችላልን?
በፍጹም አይችልም። ኢዮብ እንደተናገረው«ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም» ኢዮ 7፤9
የሟች ወገኖች ጸሎተ ፍትሐት፤ ዝክር፤ ድግስ፤ ለተራበ ማብላት፤ አሥራት መስጠት የሞተውን ሰው
ነፍስ አስምሮ ከሲኦል አያወጣም? አዎ በፍጹም አያወጣም። ሲኦል የሚያወርድም የሚያወጣም
የሥልጣን ሁሉ ባለቤት እግዚአብሔር ብቻ እንጂ የሰዎች የድግስ ብዛት ወይም የአማላጅ ጋጋታ
አይደለም።
በሳሙኤል ቀዳማዊ እንዲህ የሚል ተነግሮን የለም እንዴ ጎበዝ?! « እግዚአብሔር ይገድላል፤
ያድናልም፤ ወደሲኦል ያወርዳል ያወጣል» 1 ኛ ሳሙ2፤6 በቃ እውነታው ይሄ ነው። ማዳንም
መግደልም የእግዚአብሔር ኃይል እንጂ የሰዎች መብትና ጥያቄ የሚገለጽበት ጉዳይ አይደለም።
ኃጢአተኞችም ወደሲኦል ይመለሳሉ(መዝ 9፤17) እንጂ ከዚያ የሚያስቀር «አንገት አያስቀልስ፤
ፊት አያስመልስ» ተረት ሥፍራ የለውም።
በጸሎተ ፍትሃትም እኮ ሟችን ከመራገምና ወደሲኦል እየወረደ ስለመሆኑ ከመመስከር የተለየ
ጸሎት የለውም። እስኪ ይህንን ተመልክተው ልብ ይበሉ።
በተለምዶ የጉዞ ፍትሃት በሚባለው የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ለአስከሬኑ ከሚደርሱት ጸሎተ
ፍትሃት አንዱን ዲያቆኑ እያስተዛዘለ የሚያዘመው ይህንን ነው።
«አኀዘኒ ፃዕረ ሞት፤ ወውኂዘ ዐመፃ ሆከኒ፤ ወአገተኒ ፃዕረ ሲኦል» መዝ 25፤5-6 ትርጉም-
«የሞት ጣር ያዘኝ፤ የዐመጽም ፈሳሽ አስፈራኝ፤ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድ ደረሰብኝ»
ማለት ነው። እንግዲህ ዲያቆኑና ካህናቱ ይህንን የሚሉት እነሱ ሞተው ሳይሆን በሞተችው ነፍስ
ምትክ እንደመሆኑ መጠን ያቺ ነፍስ የሲኦል ጣር እንደያዛትና እየተጨነቀች እንደምትገኝ
እየተናገሩላት መሆኑ ነው። ለፍርድ የተዘጋጀች መሆኗን በደንብ አውቀው እየተናገሩላት ነው።
የሟች ቤተሰቦች ግን ያቺ ነፍስ ከሲኦል ጣር የዳነችና በካህናቱ እየተረጋገጠላት የምትገኝ አድርገ
ይገምቱ እንደሆን እንጂ ከዳዊት መዝሙር ጥቅስ ተመርጦላት ፍርድ እየተናገሩባት መሆኑን መቼም
ይገምታሉ ተብሎ አይታሰብም።
እንዲያ እንዲያ እየተባለ ፭ኛ ምዕራፍ ላይ ሲደረስ ዲያቆኑ ካስተዛዘለ በኋላ ቄሱ ሉቃስ 16 ላይ
ያለውን የሃብታሙንና የአልዓዛር የደሃውን ታሪክ ካነበበ በኋላ «ወይፈድዩ ለኲሉ በከመ ምግባሩ»
ብሎ ሲያበቃ ሟች በቀደመ ስራዋ ወይ ይፈረድላታል ወይም ይፈረድባታል እንጂ በጸሎተ ፍትሐት
የሚሻሻልላት ነገር የለም ብሎ መቋጫ ያበጅለታል። «ለሁሉ እንደሥራው ትሰጣለህ» ካሉ ይህች
ነፍስም የስራዋን ታገኛለች ማለት ነው። ታዲያ ምኑን ፈቱት?
የሚያሳዝነው ነገር ሰውዬው ፍርዱን እንደስራው እንደሚያገኝ ተናግረውና የሚያስፈራ የጭለማ
ቃልን ተናግረውበት ሲያበቁ በሐዘን የተቆራመዱ ቤተሰቦቹ ለፍትሃት የሚሆን እርድ ጥለው፤ ድግስ
ደግሰው ያላቸውን ማሟጠጣቸው ሳያንስ የሚወርድባቸውን እርግማን አለማወቃቸው ነው።
ልጆቹም ሚስቱም ሥረ መሠረታቸው እንዲጠፋ ይህ ርግማን ይወርድባቸዋል።
ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ ሹመቱንም ሌላ ይውሰዳት፤ ልጆቹም ደሃ አደግ ይሁኑ፤ ሚስቱም መበለት
ትሁን፤ ልጆቹም ይናወጡ ይቅበዝበዙ፤ ይለምኑ ከሥፍራቸውም ይባረሩ....ለደሃ አደግ ልጆቹ
የሚራራ አይኑር » መዝ 108 በጥሩ ሁኔታ ይደገምላቸዋል። ይህ እንግዲህ ለሟች የሚደርሰ
የመዝሙር ጸሎት ነው። ለይሁዳ የተተነበየው የትንቢት ቃል ለሟች የሚደገምለት ለምን ይሆን?
ይህ ሁሉ እርግማን እንደሥራሽ የተባለችውን ነፍስ ከሲኦል ለማዳን ነው ወይስ ቀሪ ቤተሰቦቹም
ከምድረ ገጽ እንዲጠፉ? ይህን የዳዊት ቃል ሳያደርሱ የፍትሃት ድግስ መብላት ነውር ነውም
ይባላል። አሳዛኝ ነገር!!
«ኦ ነፍስ ህርትምት ወይ ለኪ፤ አሌ ለኪ» አንቺ የከፋሽ ነፍስ ሆይ ወዮልሽ ወዮታ አለብሽ»
በሚባልላት ሁኔታ ከሲኦል እንዴትና ማን ይታደጋት ይሆን? ማንም የለም። እግዚአብሔር ቸር
መሆኑ ባይካድም ቸር ነው እያሉ በሚያዘናጋ የዚህ ዓለም ብልሃት በሆነና ራስን ነጻ ለማውጣት
በሚደረግ ጥረት እየታገዙ ቸርነቱን ለልብ እየነገሩ፤ እግዚአብሔርን ለማባባት መሞከር ሰውኛ
ጥበብ ከመሆን የዘለለ አይደለም። ጽሑፋችንን ስናጠቃልል ሲኦል የወረደን የሚያወጣ የሰው
ችሎት የለም። «ሲኦል የወረደ ዳግመኛ አይወጣም» እንዳለው ኢዮብ 7፤
ይልቁንስ በሞት ከመጋረዳችን በፊት አሁኑኑ እንወቅበት። እግዚአብሔርን ረዳቴና ታዳጊዬ አንተ
ብቻ ነህ እንበለው።መዝ 70፤5
ለዚሁም እግዚአብሔር ይርዳን፤ አሜን።
ብርሃን

6 comments:

 1. I said you are not Orthodox Christians since I know your false teaching on some part of your dogmas. For example the above teaching even though it seems biblical it is not correct. According to bible the following are important in order to get saved:

  1. እምነት፡ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም
  እምነትነታችን መታተም አለበት ይህን ማለት እምታችንን የምናረጋግጥባቸውና ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርገንን ነገር መፈጸም አለብን፡ እነዚህም
   ጥመቀትና መንፈስ ቅዱስን መቀበል ናቸው ፤ከውሃና ከመንፈስ መወለድ ማለት ነው ።
  ከክርስቶስ ጋር አንድ መሆን አለብን፡ ሰው ለመዳን ከክርስቶስ ጋር ህብረት እንዲኖረው ያስፈልጋል። በዮሐ 6፤56 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ 6፡54 ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥
  እምነትን በስራ መግለጥ፡
   ስራ ብቻውን ያድናል አይባልም። ስራ ምን አልባት ወደ እምነት ሊያደርስ ይችል ይሆናል /ሐዋ 10 ቆርነሊዎስ/
   ሰውም በስራው ፍጹም ሊሆን አይችልም ሆኖም በተቻለው መጠን መልካም ነገር ማድረግ አለበት
   እግዚአብሔር ሐጢያተኞችን ይቀጣል።  ሰው ለመዳን እምነት ብቻ እንጂ መልካም ስራ አያስፈልግም የሚሉ አካለት አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እምነት ያለ ስራ የሞተ ነው ይላል።
  ያዕ 2፡14 ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? 17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።26 ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።
  ሐጢያት የሚያደርጉ ሰዎች እንደማይድኑ
  ሮሜ 1፡32 እንደነዚህ (የተዘረዘሩ ሃጢያቶችን) ለሚያደርጉት ሞት ይገባቸዋል የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ እነዚህን ከሚያደርጉ ጋር ይስማማሉ እንጂ አድራጊዎች ብቻ አይደሉም።
  ሮሜ 6፤ 23 ስለዚህ ሐጢያትን የሚያደርጉ ሁሉ ከሞት አያመልጡም።ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው
  ሮሜ 8፤ 6 እንግዲህ ስለ ስጋ ማሰብ ሞት ከሆነ በዚህ ዓለም የስጋ ስራ ወንድምን በመግደልና በልዩ ልዩ ሐጢያቶች ያሉ ሁሉ ሊድኑ ይችሉ ይሆንን?
  1ዮሐ 3፤ 5 ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ

  የእግዚአብሔርን ስም የሚጠሩ ሳይሆን ፈቃዱን የሚያደርጉ ይድናሉ።
  ማቴ 7፡ 21-23 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
  ማቴ 25፡ 32-42
  ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።

  ReplyDelete
 2. Continued ........

  አንዳንድ ተጨማሪ ጥያቄዎች/controversials:

  2. ድህነት በቅጽበት የሚካሄድ ወይስ እስከ ህይወት ፍጻሜ የሚሄዱት
  ድህነት በቅጽበት የሚፈጸም ነው ብለው የሚያስተምሩ አሉ። ይህንን ሲሉ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመነ አንድ ሰው ለመንግስተ ሰማያት ቪዛ ይኖረዋል። ካመነ በሗላ በማነኛውም ሰዓት ቢሞት መንግስተ ሰማያት ይገባል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ድህነት በአንዲት ሰዓት የምናረጋግጠው ሳይሆን እስከ ህይወት ፍጻሜችን በመሄድ የምናገኘው እንደሆነ ያስተምረናል።

  የሚጠቀሰው ጥቅስ፡
  ሮሜ 10፡9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
  የመቶ አለቃው
  ሐዋ 16፡30 ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
  እዚህ ላይ ትድናለህ የሚለው ክርስቲያን ትሆናለህ ማለት እንጂ መንግስተ ሰማያትን ታገኛለህ ማለቱ አይደለም። ምክነያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት ታድለው ያልዳኑ ሰዎች አሉና። የነዚህ ጥቅሶች ሐሳብ ለመዳን እድሉ ይኖርሃል ማለቱ ነው ክርስቲያን ካልሆኑ የእግዚአብሔርን ፊት ማየት አይቻልምና። የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል እንዲል።
  ነገር ግን ለመዳን ታድለው በህይወታቸው ሙሉ እግዚአብሔርን ባለመከተላቸው ከክርስቶስ መንግስቱ የወጡ አሉ። ለምሳሌ፡

  6. ይሁዳ፡ በክርስቶስ አጠገብ የነበረው ሆኖም
  7. ኒቆላወስ ሐዋ 6፤3 ፡ መንፈስ ቅዱስ የሞ
  ራዕ 2፤6፡ በክደት የነጎደና በክርስቶስ የተጠላ
  8. ዴማስ፡ ፊሊሞና ፤ ቆላ 4፡1 የጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረ ነገር ግን ዓለም ስለሳበችው የክርስቶስን መንገድ 2ጢሞ 4፡10 የካደበት ቦታ
  9. ሐዋ 8፡ ሲሞን
  10. ሐዋ 5፡30 ፡ ሐናንያና ሰጲራ


  3. በጸጋው ድናችሗል

  ሮሜ3፡22-25 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
  ኤፌ 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
  2ጢሞ 1፤9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
   እነዚህ ሐሳቦች የሚናገሩት ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው እኛም ክርስቲያን የሆነነውና ለመዳን እድሉን ያገኘነው እኛ ባደረግነው መልካም ስራ ሳይሆን በእርሱ ቸርነት መሆኑን የሚገልጡ እንጂ ስለመንግስተ ሰማያት መግባት አይደለም።
   ክርስቲያን ለመሆን መንግስቱንም ለመግባት የሚያስችል ሙሉ ስራ የለንም ይህንን ነው ጸጋ የሚለው
   ሰዎች እንደሚሉት በጸጋ ስለሚዳን ስራ አያስፈልግም ወይም ሐጢያት እያደረግህ ትድናለህ የሚል ሐሳብ የለውም
  እኔ ገና እንዳልዳንሁ እቆጥራለሁ /ያንን ለማግኘት እንደክማለን/ - ቅዱስ ጳውሎስ
  ፊሊ 3፡11-14 አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።


  4. ቃል ኪዳንና ድህነት
  እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ኪዳንም ሆነ ለቅዱሳን የተሰጠው ቃል ኪዳን (እስከዚህን ያክል ትውልድ ምሬልሃለሁ ፤ምሬልሻለሁ/ የሚለው በእርግጥ ሰዎች እርሱን ሳይከተሉ ምህረት እንደሚያገኙ የሚያሳይ ነውን?
  ዘጸ 20፡5-6 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
  እግዚአብሔር እስከ ሺ ትውልድ እምራለሁ ሲል መንግስተ ሰማያት ይገባል ማለት አይደለም። እዚህ ላይ ማስተላለፍ የፈለገው ነገር ምህረትን አስቀ

  ReplyDelete
 3. Min yemilut blog new! It is not motivating to read the way the fonts and each paragraph is written. I stopped after 10 lines.

  ReplyDelete
 4. Hi Aba Selams' thank you for posting my comments. Dejeselams usually don't post my comments. It may not supporting their mission

  አንዳንድ ተጨማሪ ጥያቄዎች/controversials:

  2. ድህነት በቅጽበት የሚካሄድ ወይስ እስከ ህይወት ፍጻሜ የሚሄዱት
  ድህነት በቅጽበት የሚፈጸም ነው ብለው የሚያስተምሩ አሉ። ይህንን ሲሉ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመነ አንድ ሰው ለመንግስተ ሰማያት ቪዛ ይኖረዋል። ካመነ በሗላ በማነኛውም ሰዓት ቢሞት መንግስተ ሰማያት ይገባል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ድህነት በአንዲት ሰዓት የምናረጋግጠው ሳይሆን እስከ ህይወት ፍጻሜችን በመሄድ የምናገኘው እንደሆነ ያስተምረናል።

  የሚጠቀሰው ጥቅስ፡
  ሮሜ 10፡9 ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤
  የመቶ አለቃው
  ሐዋ 16፡30 ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው። እነርሱም። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።
  እዚህ ላይ ትድናለህ የሚለው ክርስቲያን ትሆናለህ ማለት እንጂ መንግስተ ሰማያትን ታገኛለህ ማለቱ አይደለም። ምክነያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት ታድለው ያልዳኑ ሰዎች አሉና። የነዚህ ጥቅሶች ሐሳብ ለመዳን እድሉ ይኖርሃል ማለቱ ነው ክርስቲያን ካልሆኑ የእግዚአብሔርን ፊት ማየት አይቻልምና። የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል እንዲል።
  ነገር ግን ለመዳን ታድለው በህይወታቸው ሙሉ እግዚአብሔርን ባለመከተላቸው ከክርስቶስ መንግስቱ የወጡ አሉ። ለምሳሌ፡

  6. ይሁዳ፡ በክርስቶስ አጠገብ የነበረው ሆኖም
  7. ኒቆላወስ ሐዋ 6፤3 ፡ መንፈስ ቅዱስ የሞ
  ራዕ 2፤6፡ በክደት የነጎደና በክርስቶስ የተጠላ
  8. ዴማስ፡ ፊሊሞና ፤ ቆላ 4፡1 የጳውሎስ ደቀ መዝሙር የነበረ ነገር ግን ዓለም ስለሳበችው የክርስቶስን መንገድ 2ጢሞ 4፡10 የካደበት ቦታ
  9. ሐዋ 8፡ ሲሞን
  10. ሐዋ 5፡30 ፡ ሐናንያና ሰጲራ

  3. በጸጋው ድናችሗል
  ሮሜ3፡22-25 እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤ ይህም በፊት የተደረገውን ኃጢአት በእግዚአብሔር ችሎታ ስለ መተው ጽድቁን ያሳይ ዘንድ ነው፥
  ኤፌ 2፡8 ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤
  2ጢሞ 1፤9 ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
   እነዚህ ሐሳቦች የሚናገሩት ክርስቶስ ዓለምን ያዳነው እኛም ክርስቲያን የሆነነውና ለመዳን እድሉን ያገኘነው እኛ ባደረግነው መልካም ስራ ሳይሆን በእርሱ ቸርነት መሆኑን የሚገልጡ እንጂ ስለመንግስተ ሰማያት መግባት አይደለም።
   ክርስቲያን ለመሆን መንግስቱንም ለመግባት የሚያስችል ሙሉ ስራ የለንም ይህንን ነው ጸጋ የሚለው
   ሰዎች እንደሚሉት በጸጋ ስለሚዳን ስራ አያስፈልግም ወይም ሐጢያት እያደረግህ ትድናለህ የሚል ሐሳብ የለውም
  እኔ ገና እንዳልዳንሁ እቆጥራለሁ /ያንን ለማግኘት እንደክማለን/ - ቅዱስ ጳውሎስ
  ፊሊ 3፡11-14 አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።


  4. ቃል ኪዳንና ድህነት
  እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ኪዳንም ሆነ ለቅዱሳን የተሰጠው ቃል ኪዳን (እስከዚህን ያክል ትውልድ ምሬልሃለሁ ፤ምሬልሻለሁ/ የሚለው በእርግጥ ሰዎች እርሱን ሳይከተሉ ምህረት እንደሚያገኙ የሚያሳይ ነውን?
  ዘጸ 20፡5-6 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
  እግዚአብሔር እስከ ሺ ትውልድ እምራለሁ ሲል መንግስተ ሰማያት ይገባል ማለት አይደለም። እዚህ ላይ ማስተላለፍ የፈለገው ነገር ምህረትን አስቀ

  ReplyDelete
 5. demo atafrum aba selama bilachuh blog sitkefitu ? and neger litykachihu lemen rasachuhn geltsachuh lemenager tiferalachuh ? yimelegnal enanite kehulum satihonu mekiretachuh new "" yemilachuh neger gin lamenachuhebet atiferu atfru "" gin orthodox nen atbelu ;;lemin besew sim tatalilalachuh wushet eko hatiyat new ''kefireyachuh aweknachuh orthodox tewahedo aydelachuhm dogmachuhm yeteleye new ye enaniten begilts bitnageru yishalal

  ReplyDelete
 6. If you fill discomfort by this blog u can go www.betepawlos.com. you will get what u want.

  ReplyDelete