Sunday, October 30, 2011

ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር ማነው?

ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር ማነው?

by Dagnu Amde on Friday, October 28, 2011 at 1:39am
 • የማህበረ ቅድሳንን የሐሰት ፖሮፖጋንዳ አድምጠው ለሚነዱ የዋሐን
እንደ እውነቱ ከሆነ የላይ የላይ ዓላማውን ተመልክተው "ማኅበረ ቅዱሳን" ከቅዱሳን መላዕክት፣ ከቅዱሳን ሰማዕታትና ፃድቃን ረድኤት ያሳትፈናል ብለው በምኞት የሚከተሉት ወንድሞችና እህቶች እጅግ፣ እጅግ በጣም ሊታዘንላቸው ይገባል፡፡
 የክርስትና "ሀሁ" እውነትን ከመናገር፣ ለእውነት ከመመሥከር፣ ለእውነት መስዋዕት ከመሆን ይጀምራል፡፡ ነፍሳችን ውስጥ ለእውነት ቅንጣት ታህል ቦታ ካልሰጠን፣ ምንድነው ክርስትናችን? የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን መምጣቱ ስለእውነት አይደለምን? እርሱ ብርሃናችን ነው፤ እውነትም ከእርሱ ዘንድ ነው፤ እውነትም ፍቅር ነው፣ በፍቅሩ እኛን አከበረን፣ ክብርና ምሥጋና እስከ ዘለዓለም ድረስ ለእርሱ ይሁን፡፡

 ስለ "ማኅበራቸው" እንቅስቃሴ ከኢንተርኔት አንዳች ነገር እናገኛለን እያሉ ለዜና እየጓጉ በከንቱ ዓይናቸውን በኮምፒውተር ስክሪን የሚያጠፉ "ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በየድረገጹ፣ በየበራሪ ወረቀቱ፣ በአጠቃላይ በሕትመትና በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የሚነግራቸውን እያመኑ፣ እርሱ የተናገራቸው ሁሉ እውነት እየመሰላቸው የሚነዱ አባላት ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡  "በሬ ወለደ" ተረቱን እያመኑ ከቤተክርስቲያን፣ ከንስሐ አባቶቻቸው፣ ከብፁዓን አበው፣ ከሊቃውንት ካህናት፣ ከዲያቆናት፣ ከምስኪን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ምዕመናንና ምዕመናት የሚጣሉ፣ የሚጋጩ አያሌ ናቸው፡፡
ያልተወሰነውን ተወሰነ፣ ያልተባለውን ተባለ እያለ፣ እንዲህ ተወስኖ ተግባራዊ ያልሆነው በእነ እከሌ ሥልጣንና እምቢተኝነት ነው እያለ "ላም ባልዋለበት ኩበት ያስለቅማል"፡፡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ አንድ የቤት ሥራ በጋራ ብንወስድ ደስ ይለናል፡፡ እስኪ ቀደም ካሉት የድረ ገጽ ፋይሎቹ፣ የትኞቹ ናቸው እውነትነት የነበራቸው? አብዛኛዎቹ ዜናዎች በአሉባልታ የተደራረቱ መሆናቸውን ትረዳላችሁ፡፡
 "ማኅበረ ቅዱሳን" ቅዳሜ ጥቅምት 11 ቀን 2004 . (ኦክቶቨር 22 ቀን 20011) ደጀ ሠላም "Deje Selam" በተባለ ትዊተርና ፌስቡክ ገጹ ባሠራጨው ዘገባ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ከመጀመሩ በፊት የሚካሄደው የአባቶች የጸሎት መርሐግብር እሁድ ጥቅምት 12 ቀን 2004 . እንደሚሆን ገልጾ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ቅዳሜ ዕለት ይህንኑ ዜና በፌስ ቡክ ላይ በሚጭንበት በዚያው ተመሳሳይ ሰዓት የጸሎት መርሐ ግብሩ እየተካሄደ ነበር፡፡ ይህን ያደረገው "ማኅበረ ቅዱሳን" የተሰደዱና በደል የደረሰባቸው ወገኖች በመርሐ ግብሩ ላይ የሚገኙትን አባቶች እንዳያገኙ ለማድረግ ለማሳሳት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ከቃለ ዐዋዲው ውጪ "የአዲስ አበባ ሰንበት /ቤቶች አንድነት ማኅበር" የሚል አድመኛ ቡድን  አቋቁሞ ቤተክርስቲያንን በሁከት ለመናጥ በማድረግ ላይ ያለውን ሤራ ለመሸፋፈን የአዲስ አበባ ሰንበት /ቤቶች የጋራ ጥያቄ ያቀርባሉ ካለ በኋላ፣ ይህንን ቡድን "የደንብ ልብሳቸውን በመልበስ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የብፁዓን አበው ጸሎት መርሐ ግብር ላይ ለመገኘት ለመግባት ወስነዋል " ብሎናል፡፡  ዘጋቢው ይህንን ዘገባ ፌስቡክ ላይ ሲጭን ቡድኑ ወደ ቅጥር ግቢ ከገባ ሁለት ሰዓት ከሩብ ደቂቃዎች አልፈዋል፡፡ ዕድሜ ለኮምፒውተር ከዚያ መረዳት ይቻላል፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" የሚሠራው ለእውነትና ስለእውነት ከሆነ መዋሸት ለምን አስፈለገው?
ከሐረር፣ ከአሰበ ተፈሪ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከሀዋሳ፣ ከዲላ፣ ከመቀሌ፣ ከክብረ መንግሥት፣ ከሻኪሶ፣ ከሀገረ ማርያም፣ ከአለታ ወንዶ፣ ከሌሎችም ከተሞች ለአቤቱታ የመጡ  ወገኖችን "የሕገወጦቹን የተቃውሞ ትዕይንት በማድመቅ ያግዛሉ የተባሉ በማወቅም ባለማወቅም በጥቅምና በሐሰተኛ ቅስቀሳ የተደለሉ ግለሰቦች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ተደርገዋል" እያለ ለማጣጣል ሞክሯል፡፡
እንግዲህ፣ "ማኅበረ ቅዱሳን" ከሰሜን፣ ከምሥራቅና ከደቡብ የሀገሪቱ ጫፍ የመጡ ምዕመናንን በምን መመዘኛ ነው ባለማወቅ የመጡ ናቸው፣ ሊል የቻለው? ሐሰተኛ ቅስቀሳውስ የቱ ነው? እውነት ከሀገሪቱ ጫፍ የመጡት ምዕመናንና ምዕመናት  "ማኅበረ ቅዱሳን" በደል ያልደረሰባቸው ናቸው? ደሴ ላይ ሰው አልሞተም? ሐረር ላይ ወንጌል አልታጠፈም? ሀዋሳ ላይ ወንጌል አልታጠፈም? ምስኪኖች ወደ ወህኒ አልተወረወሩም? ሌሎች አልታሠሩም? "ማኅበረ ቅዱሳን" መቋሚያና በፖሊስ ቆመጥ አልተቀጠቀጡም? "ማኅበረ ቅዱሳን" በሕገወጥ መንገድ የሀዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳምንና ሀገረ ስብከቱን ጭምር ከላይ እስከ ታች መዋቅሩን አልተቆጣጠረውም? አለታ ወንዶዎች የወንጌልን ቃል በጉባዔ እንዳይሰሙ ከአንድ ዓመት በላይ አልታገደባቸውም? ክብረ መንግሥቶች አዲስ አበባ ድረስ የመጡት ባለማወቅ ተቃውሞውን ለማድመቅ ብቻ ነው? ለምን ይዋሻል?
"ማኅበረ ቅዱሳን" እነዚህን ወገኖች በጥቅም የተደለሉ ናቸው ካለ፣ ያገኙት ጥቅም ምንድነው? እውነት ጥቅም አግኝተው ከሆነ መጠኑን፣ ቀኑን፣ ሰዓቱን፣ ቦታውን፣ በማን አማካይነት እንደሆነ ለምን ቁልጭ አድርጎ አያሰቀምጥም? እውን ይህንን ሕዝብ ለመደገፍና ለማገጓጓዝ እንኳን ስማቸው በተነሳው ምስኪን አገልጋዮች ይቅርና በናጠጡ ሀብታሞች ይቻላል? በመንግሥት ካልሆነ በስተቀር?
 "ማኅበረ ቅዱሳን" የብፁዕ አባታችንን የአቡነ ፋኑኤልን ስም ለማጠልሸት ፈልጎ "አንድ ቤተክርስቲያን ለመባረክና ለመክፈት እስከ ሦስት ሺህ ዶላር እንደሚቀበሉ ውስጥ ውስጡን ይወራል . . ." ብሎናል፡፡ እንግዲህ "ማኅበረ ቅዱሳን" ዘንድ ክርስትና ማለት ይህ ነው፡፡ የወሬ ሱስ ካለባችሁ፣ ውስጥ ውስጡን ከተወራ፣ ለምን ውስጥ ውስጡን እንዳማችኋቸው አትቀሩም? ወሬ ምን ይረባችኋል? ወሬ! ወሬ! ወሬ! ወሬ! ወሬ! ወሬ! ወሬ! ወሬ! . . . . . . ወሬ ብቻ!! ቤተክርስቲያንን በወሬ የሚገነባ፣ ከንቱ የወሬ ትውልድ!!
ያው ከዚህ በፊት እንደነገርናችሁ "ማኅበረ ቅዱሳን" ያልደገፈ ማንኛውም ሰው፣ መናፍቅ፣ ፕሮቴስታንታዊ ተሀድሶ፣ ሌባ እየተባለ መሰደቡ አይቀሬ ነው "ማኅበረ ቅዱሳን" ዘንድ፡፡
 የፈረደበት መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝም የሰሞኑ "ማቅ" ወሬ ሰለባ መሆኑ አልቀረለትም፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" መጋቤ ሀዲስ በጋሻውን ዑራኤል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠገብ ቆሞ "የት ደረሳችሁ ፍጠኑ ለማታው ስብሰባ ለመድረስ እያለ ተስፋዬ መቆያን ሲያነጋግር ተሰምቷል" በማለት ትኩስ ወሬ ሊያጋራን ሞክሯል፡፡ ለመሆኑ መጋቤ ሀዲስ በጋሻው አነጋግሯል ከተባለ፣ የትኛውን ተስፋዬ ነው ያነጋገረው? መምህር ተስፋዬን በቅርብ የሚያውቀው ስለሆነ የአባቱን ስም መጥራት ለምን ያስፈልገዋል? ደግሞስ "ማቆች" ሁሉ ውርጅብኝ ደርሶበት ሳለ የመምህር ተስፋዬን ስም ጮኾ መናገር ለምን ያስፈልገዋል? ሰው ባለበትስ መናገር ለምን ያስፈልገዋል? "ማኅበረ ቅዱሳን" የሰውን የውስጥ ንግግር የሚጠልፍበት ልዩ ችሎታ አለው? ወይንስ ጭራሹኑ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ቦታ የሚገኝ መንፈስ ሆኗል?
 ሌላው አስገራሚ ወሬ፣ አዲስ አበባ ከሚገኙ ሁለት ሰዎች በአንበሳ ባንክ እና በሌላ ባንክ ሠላሳ አምስት፣ ሠላሳ አምስት ሺህ ብር በዲ/ ያሬደ ዐደመ በኩል ለሀዋሳ ምዕመናን ተልኳል ያለው ነው፡፡ የዚህ ዜና ዘጋቢ ምናልባት "ማኅበረ ቅዱሳን" ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው የሀዋሳ ምዕመናንን መብት ለማስረገጥ ለስራ ማስኬጃ ይህን ያህል ብር በተባለው መልኩ ለአባላቱ ልኮ ከሆነ ቢያጣራ ይሻለዋል፡፡ በተረፈ ወሬውን ቢያንስ ለማስመሰል እንኳን የተላከበትን ቀን፣ የኢንቮይስ ቁጥር፣ የላኩትን ሰዎች ስም፣ የተላከበት ቅርንጫፍ ወዘተ ቢጠቅስ መልካም ነበር፡፡ ከዚያ ውጭ ግን ከንቱ ቱልቱላ መንፋት ብቻ ነው፡፡ የዚህ ወሬ ሌላም ዓላማ አለው፤ የየሀገረስብከቱንና የየከተማውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ጥያቄ የማይረባ እና እርሱ የሚያሳድዳቸውና የሚቃወማቸው አገልጋዮች ቅስቀሳ አስመስሎ ለማሳነስ እና ምዕመናኑ ባላወቁት ነገር እንደገቡ አድርጎ ለማሳየት ነው፡፡ ከንቱ ልፋት!!
 የውሸት አባት፣ የሐሰት አባት፣ የአሉባልታ አባት፣ አባላቱን እሰከመቼ እየዋሸ እንደሚኖር እግዚአብሔር ይወቅ፡፡ አባላቱ ግን "ማኅበረ ቅዱሳን" የሚነገራቸው እውነት እየመሰላቸው ኮምፒውተር ላይ አፍጥጠው ውሸትን እንደግሉኮስ ሲመጥጡ ማየት እጅግ የሚያሳዝን ነው፡፡

ለፖለቲካ ሲባል እንጂ፣ ለሃይማኖት ሲባል እንዴት ይዋሻል?

16 comments:

 1. Weye! mehabere sitan.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተሃድሶ ተጋለጠ
   ቅድስት ማሪያም የመዳን ምክንያት ያደረጋት ጌታ ኢየሱስ ነው፣ ፃድቃንን ሐዋሪያትን መርጦ ያከበራቸው ጌታ ኢየሱስ ነው
   ለሐዋሪው ዮሐንስ እና ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የመሰከረው ጌታ እየሱስ ነው ፣ በመፀሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ፃድቃን ካሉ ለእንርሱ ስል ለሕዝቡ ምህረት እሰጣለሁ ያለው ጌታ እየሱስ ነው፣ በፃድቀን ሥም የሚደረግ በጎነገር ዋጋ እንዳለው የተናገረው ጌታ እየሱስ ነው፣ ቅዱሳን መላዕክት ከፈጣሪ በተሰጣቸው ፀጋ የሰውን ልጅ ከመከራ እንደሚታደጉ በመፀሃፍ ቅዱስ ተመስክሯል
   ታዲያ ይህቺ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዕውቀት የተሞላች ምንጎሎባት ነው መታደስ አለባት የሚባለው ቅዳሤው እረዘመ፣ ፆሙ በዛብን፣ ፃድቃንን ፣ ቅድስት ማሪያምን ማመስገን አያስፈልግም ፣ እንደፈለግን እንብላ እንጠጣ፣ እንጨፍር እንዝናና ፣ ፃድቃንን ማክበር አያስፈልግም፣ ስንቱን ፆርና ተጋድሎ በድል የተወጡትን በምድር ላይ እራሳቸውን የካዱትን ፃድቃን ሰማዕታት ከእራሳቸው ሕይወት ጋር የሚያወዳድሩ ነውረኞች ፋሽን ቲሸርት ቀበቶና መነፅር ለመግዛት በየሱቁ ሲሻሙ የሚውሉ የስጋቸውን ፍላጎት መግታት የተሳናቸው አቅመቢሶች ቢያንስ አስከ 6 ሰአት እንኮን መፆም የማይችሉና አብዝቶ መስገድን የሚፈሩ በየካፍቴሪው በርገር እንደ አሳማ ሲሰለቅጡ የሚውሉ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ተሃድሶ መናፍቃን ከቤተክርስቲያን ይመነጠራሉ በቤተክርስቲናችን እድል ፋንታ የላቸውም በተጨማሪም ከላይ ከሰማይ ተሰጥኦ ሳይታደሉ ለቢዝነስ/ ለሆዳቸው መሙያ ስባሪ ሳንቲም ለማግ ኘት/ በኦርቶዶክስ ስም የሚዘምሩ ሐያሉን እግዚሃቤር አቃለው በማይገባ ቃል የሚጠሩ/ ፍቅሬ፣ውዴ፣…../ መዝሙራቸው ዜማው ከአለማዊ ዘፋኞች የተሰረቀ እና ተራ ምንም መልዕክት የሌለው ሕይወታቸው በምሳሌነት የማይቀርብና የማያስተምር፣ የሰውን ብሶት መሰረት ያደረገ ስብከት አይሉት ፉከራ በመንዛት ሲደ በማሳተም ሆዳቸውን የሚሞሉ ማፈሪያዎች በምድራዊ ሕይወታቸው ሰነፎችና ታካቾች በመሆናቸው ዘለግ ያለ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው ለመኖር ሆዳቸውን ለመሙላት አማራጭ ስለሌላቸው ይህችው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚቃትቱ ሰነፎች በእግዚአብሄር እገዛና በእራሳቸው ጥረት በሁለት ወገን የተሳለ ቢላዋ ሆነው/በምድራዊ ትምህርታቸው የመጠቁና የላቁ ዶክተሮች፣ ዳኞች፣ መምህራን፣ ኢንጂነሮች፣ሳንቲስቶች እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በማይታመን ሁኔታ የላቁ አስከ ቅስና ድረስ የዘለቁ / ወንድሞች የመሰረቱትን ማህበር የመናፍቃንና የተሃዱሶዊያን ጠላት የሆነውን ማህበረ ቅዱሳን መናፍቃን በብሎጋቸው ስሙን ጥላሸት ለመቀባት ሲፍጨረጨሩ ይውላሉ ሆኖም ማህበሩ እውነተኛው ዳኛ እግዚሃብሄር የመሰረተውና በሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ልብ ውስጥ ሰርፆ የገባ በመሆኑ ምንም ማምጣት አይቻላቸውም እኛም/የኦርቶዶክስ ልጆች/ በፀሎት፣ በዕውቀት፣ በገንዘባችን ማህበሩን መርዳት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡መስቀል መሳለም፣ የንስሃ አባት፣ የቃልኪዳኑ ታቦት፣ እጣኑ የቅዱሳንን ስም መጥራትና ማመስገን ኤስፈልግም የምትሉ እንዲሁም ስግደትን፣ ፆምን፣ ቅዳሴን የምትፈሩ ሰነፎች እና ሆዳም ተሃድሶዊያን አርብና እሮብ ሳገለግል ይርበናል ስለዚህ አልፆምም መብላት ያስፈልገኛል የምትሉ አጉራ ዘለል ሰባኪያን ከቤተክርስታኒያችን ውጡ ልቀቁ ምክንያቱም ቤተክርስታኒያችን ለሰነፎችና ለሆዳሞች ቦታ የላትም አትመችም ፣ በመዝሙር ሥም ጭፈራ እና የስጋ ድሎት ወደሚፈቀድለት በአዳራሽ ውስጥ ሴሰኝነት ወደ ነገሰበት የዘመኑ መናፍቃን መሰባሰቢያ ሂዱ እንደወደዳችሁም የሥጋችሁን ፈቃድ ፈፅሙ አታለቃቅሱ የፃድቃንን ተጋድሎ በምን አቅማችሁ ትችላላችሁ ወዝ የሌላችሁ ሀሰተኞች አስመሳዮች ጌታ ያከበራቸውን ከእኛ በምን ይበልጣሉ የምትሉ ማፈሪዎች ቅዱሳን ከመወለዳቸው በፊት በእግዚያብሄር እንደሚመረጡ እንኮን የማታስተውሉ ሰነፎች ሀሳባችሁ ምድራዊ የሆነ "መዝሙርና "ስብከታችሁ" ሰውን የማይለውጥ ባዶ የቆርቆሮ ጩኽት አሁንማ ተነቃባችሁ ሲዲ መቸብቸብ ቀረ በመዝሙር ስም ትዝታ፣ አምባሰል ……… እየዘፈናችሁ፣ ሁሉም ነቃ ትንሽ ትልቁ …. ቡዝነስ ቐረ ቦሌ ካፍቴሪያ እያማረጡ ሆድ መሙላት ቀረ ገና እውነተኛ ጌት እየሱስ ክርስቶስ በስሙ የሚነግዱትን ያዋርዳቸዋል፣

   Delete
  2. ማህበረ ቅዱሳን እውነተኛና ሕጋዊ ማህበር ነው
   ማህበረ በቅዱሳን እውነተኛ የኦርቶዶክስ የቁርጥ ቀን አለኝታ ነው ሆዳሞች በበዙበት ሰአት በገጠር የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ያስከፈተ ጥምቀት ያላገኙ ወገኖቻችን ጥምቀት እንዲገኙ ሰፊ ስራ የሰራ አባቶች ካህናት ዳቆናት፣ሰባኪን የሃማኖት ዕውቀታቸው እንዲሰፋ ያስተማረ ቤተክነት መስራት ያለበትን ሥራ እና ኃላፊነት የተወጣ ምዕመኑ በአዳዲስ እና በአጭበርባሪ ትምህርቶች በመናፍቃንና በተረፈ አሪዮሳዊያን ተሀድሶ እንዳይወሰድ ጠንክሮ በጥበብ ዕየተዋጋ ያለ ድንቅ ማህበር ነው በተጨማሪም ከአባላቱ የሚሰበስበውን ገንዘብ ሙሉለሙሉ በስራ ላይ በማዋል ሪፖርት የሚቀርብ ገንዘቡ የዋለበትን ፕሮጀክት በተጨባጭ ማስረጅ እንዲሁም በአካል ማየት ለሚፈልግ በየገጠሩ በሚገኙ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት የሚያሳ ነው ለአብነት ከአባላት በሰበሰበው ገንዘብ የአገልግሎት ማስፋፊያ ድንቅ ሕንፃ በ4ኪሎ ዋና ማዕከል ማስገንባቱ ለእውነጠኞችና ንፁህ ህሊና ላላቸው አካላት ማህበሩ ልማታዊና እየንዳንዱ የአባላት መዋጮ በስራ ላይ እንደሚውል ተጨባጭ ማስረጃ ነው እንደሌሎቹ ሌቦች ማህበራትና አጉራዘለል ሰባኪያን ለግል መኖሪቤት መስሪያና መኪና መግዣ አልዋለም ይህም ማህበሩ ምን ህል እውነተኛ እንደሆነ ያስታውቃል ነገርግን " ደጀ ብርሃንና አባ ሰላማ " የሚባሉት የተሀድሶ ማህበራት ማህበሩን ከመንግስት ጋር ለማጣላት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም ነገርግን አልተሳካላቸውም ነገም አይሳካላቸውም ምክንያቱም የማህበሩ ጠባቂ እውነተኛው የአለም ፈጣሪ እየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ በኢንተርኔት እውነት እንናገራልን ቢሉም የእንረሱ ቡድን የሆነው መኪና እያማረጠ አለሙን የሚቀጨው ለአገልግሎት እስከ 16 ሺ ብርና ምቾት ያለው ማረፊያ በቅድሚያ ይዘጋጅልኝ እያለ የምንፍቅና ትምህርትን በፕሮስታንታዊ ቅኝት የሚነዛውና በሚሊኒየም አዳራሽ የእግዚያቤርን ቃል እንደ ሸቀጥ የቸበቸበውን ገንዘቡንም የት እንደገባ ሪፖርት ቤተክርስቲያን ጠይቃ አስካሁን ድረስ ምላሽ ያልሰጠውን ኪራይ ሰብሳቢ የሆነውን የበጋሻውን ቡድንን ለምን ብሩ የት ገባ ብሎ መጠየቅ ተሳነ የማህበረቅዱሳንማ ሂዳሞችንና መናፍቃንን የሚሸበር ህንፃ ለቀጣይ የተጠናከረ አገልግሎት አስገንበቶ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ማስረጃ አቅርቧል፡፡

   Delete
 2. ስለ ማኀበረ ቅዱሳን ለመናገርም ለመፃፍም ማኀበረ ቅዱሳን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ከፅሑፍህ እንደተረዳሁት ግን ስሙ ራሱ ከሰው ብቻ የሰማሀው ይመስላል፡፡ሰለዚህ ማኀበሩ እወቀው ምናልባት የቤተክርስቲያን ልጅ ከሆንክ ብየነው፡፡ካልሆንክ ግን ከፃፍከው ነገር ሌላ አይጠበቅም፡፡

  ReplyDelete
 3. እኔ በግሌ በማህበራችን ውስጥ ካሉት ስህተቶች ውስጥ ያየኋቸው የሚከተሉት ናቸው::

  1 የማህበሩ አባል ወይንም ደጋፊ ያለሆነን ሰው ሁሉ ይኮንናን:: በመልካም አይን ለማየት ጊዜው የለም::
  2 ማህበረ ቅዱሳን ወንጌል ጠለቅ ተብሎ ሢነገር ነገር አለ ይላሉ:: የክርስቶስ ነገር የእግዚአብሔር ቸርነት ፍቅሩን ምህረቱን የሚናገር ሰባኪ ብዙም አይበረታታም::

  3 ዶግማና ቀኖናን ትውፊትና ሃይማኖትን ለይቶ ለማወቅ ፍላጎቱ የለም:: የሚያውቁ ሰዎችም ስለዚህ እንዲናገሩ አይፈለግም::

  4 ኢየሱስ ክርስቶስ የፕሮቴስታንንት ይመስል ኢየሱስ ሲሰበክ መደንገጥ ይበዛል:: ያለ ክርስቶስ ክርስትና የለምና::

  5 በቤተ ክርስቲያን ገድላትና አዋልድ መጽሃፍት ውስጥ ያሉ ስህተቶች በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲስተካከሉ ተባበሩ:: ይህንን ዳንኤል ክብረት አዋልድ መጻህፍት በሚለው ጽሁፉ ነካክቶት አልፏል:: የተበላሹ የቤተ ክርስቲያን መጻህፍት እንዳሉና እነርሱንም ማስተካከል እንደሚገባ::

  ማህበረ ቅዱሳን ይህንን ሲያደርግ እናንተ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን ስታከብሩና በትክክል ኦርቶዶክሳዊ ዶግማዋን ስትከተሉ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ስታከብሩ ቤተ ክርስቲያንን አንድ ወደ ሚያደርግ የተቃና የወንጌል ጉዞ መምራት እንችላለን::

  ReplyDelete
 4. tebarek endante lewenete yiminor tewelede yisten

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማ ቃለ ሕይዎት ያሰማችሁ።እኔ ሁል ጊዜ የሚገርመኝ ጳጳሳቱ መነኮሳቱ ከአንድም ሁለት ሦስት ሚስት አስቀምጠዉ ፦ ራሳቸውን አጽድቀው አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ እንደሚባለው ለራሳቸው የሚመች ሕግ አውጥተው ባለ ሕግ የሆነውን ካሕኑን ሲያስቃዩት ማየታችን የአደባባይ ምስጢር ነው። ካሕኑ ለሃያ ዓመታት ከዚያም በላይ በትንሽ ደመዎዝ ተገድቦ የቤተክርስቲያኑ ስራ እስካለቀበት ጊዜ ድረስ በማስተባበር በማናቸውም ስራ ስራ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቶ ቤተ ከርስቲያኑ በተመረቀ ማግስት ተገድሟል ከዚህ በኋላ መነኩሴ ነው የሚቀድሰው ይባልና ያ ለረጅም ዓመታት ሁለገብ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ካህን ይወጣና መነኩሴ ይሰገሰግበታል ለመሆኑ የክህነት ትንሽና ትልቅ አለው ? አልገባኝም።እኔ እስከማቀው ድረስ የክህነቱን ሙያ በሚገባ የተማሩትና የሚገልጹት ካህናቱ ናቸው ። መነኮሳቱ ሁል ጊዜ እንዳፈርንባቸው ነው።ሌላው ካህናቱ በዚህ ቦታ አይቀድሱም የሚባለው በሕግ ተወስነው መኖራቸው? ወይስ እንደ መነኮሳቱ ሁለት ሦስት ሚስት አለማስቀመጣቸው? ነው እባካችሁ አባ ሰላማዎች በዚህ ላይ የውይይት ርዕስ ክፈቱና ታሪክ ስሩ።

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች ስለመነኮሳት የተሰጠው ኮሜንት ወቅታዊና በጊዜው የቆብ ዘረኝነት ኢየተፈጸመ ያለ ሃቅ ነው ለምሳሌ ካህን ጥንተ ኣብሶ እንዳለበት ክህነቱም ኣናሳ እንደሆነ ኣድርጎ በመቁጠር ገዳም ነው ካህን ኣይገባም እየተባለ ሁለትም ከዚያም በላይ ቅምጥ ያላቸው መነኩሴ ነን ባዮች ወሮ በላዎች ቤተ ክርስቲያኗን ከላይ እስከ ታች ርስት ኣድርገዉ ወረራ በማድረግ ቤተ ክርስቲያንዋን ለመጣል በቆብ መሳሪያ እየገዘገዞኣት ይገኛሉ ፡፡ ቤ/ክንን ግን የሲኦል ደጆች መነኮሳት አያጠፎአትም ።እና ከላይ ለተጠቀሰው በኣዋሳ ገብራኤል ቤ/ክ ገዳም ነው በማለት ካህናት እንዳይቀድሱ መደረጉ ለዚህ ኣቢይ ማስረጃ ነው ።ስለዚህ የትውልዱ ጥያቄ ስለሆነ የውይይት መድረክ መከፈቱ አንድ የታሪክ ምእራፍ ነው።

  ReplyDelete
 7. ውሸት ወሸት ወሸት .......

  ReplyDelete
 8. ከእናንተ በላይ ሁለት ምላስ በዉኑ ሊኖር ይችላልን?
  ላይ ላዩን ላያችሁ እዉነተኞች ትመስላላችሁ፡፡ እስኪ ይህችን ብቻ ልጠይቃችሁ፡፡ በዚህ ጽሑፋችሁ ላይ "ማኅበረ ቅዱሳን" እነዚህን ወገኖች በጥቅም የተደለሉ ናቸው ካለ፣ ያገኙት ጥቅም ምንድነው? እውነት ጥቅም አግኝተው ከሆነ መጠኑን፣ ቀኑን፣ ሰዓቱን፣ ቦታውን፣ በማን አማካይነት እንደሆነ ለምን ቁልጭ አድርጎ አያሰቀምጥም? እውን ይህንን ሕዝብ ለመደገፍና ለማገጓጓዝ እንኳን ስማቸው በተነሳው ምስኪን አገልጋዮች ይቅርና በናጠጡ ሀብታሞች ይቻላል? በመንግሥት ካልሆነ በስተቀር? ብላችኋል፡፡
  በቀደም ባወጣችሁት ‹‹የማንያዘዋል ሲኖዶስ….›› ባላችሁት ጽሑፍ ዉስጥ
  ‹‹የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበት ድምዳሜ ማኅበሩ መፍረስ አለበት የሚል ቢሆንም፣ ከ200 ሺህ ብር በላይ የተከፈላቸው የሚመስሉት የወሎዎች ቡድን ዋና አቀንቃኝ የሆኑት አባ ሕዝቅኤል “ማኅበረ ቅዱሳን ከተዘጋ ቤተ ክርስቲያን ማን አላት? ስለዚህ የማኅበሩ ደንብ ተሻሽሎ እንዲሠራ መደረግ አለበት” ሲሉ በበላ አንጀታቸው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል›› የሚለዉን ረሳችሁት ወይስ እንዲህ ያለዉ ስም ማጥፋት የሚመለከተዉ ሌሎቹን ብቻ ነዉ? ታዲያ ከእናንተ በላይ ሐሰተኛና ሁለት ምላስ እንደ ልቦለድ ምናቡን ብቻ የሚጽፍ ማን ሊኖር ይችላል? ነገራችሁ ሁሉ ፈራሽ መሆኑን በራሱ ይመሰክራል፡፡
  በዚህ ጽሑፍ እንኳ ርእሱን ‹‹ ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር ማነው?›› ማለታችሁን ረስታችሁ ወዲያዉ ደግሞ ‹‹ ስለ "ማኅበራቸው" እንቅስቃሴ ከኢንተርኔት አንዳች ነገር እናገኛለን እያሉ ለዜና እየጓጉ በከንቱ ዓይናቸውን በኮምፒውተር ስክሪን የሚያጠፉ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት ስፍር ቁጥር የላቸውም፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በየድረገጹ፣ በየበራሪ ወረቀቱ፣ በአጠቃላይ በሕትመትና በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የሚነግራቸውን እያመኑ፣ እርሱ የተናገራቸው ሁሉ እውነት እየመሰላቸው የሚነዱ አባላት ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ›› በማለት ራሳችሁ ስለ አባላቱ ብዛት በመናገር በቅጽበት ታፈርሱታላችሁ፡፡
  ነገራችሁን ሁሉ በማጤን ስመለከተዉ በአጠቃላይ እንደዚህ ፈራሽ ሆኖ አገኘዋለሁ፡፡ ታዲያ እናንተ ‹‹ የ"በሬ ወለደ" ተረቱን እያመኑ ከቤተክርስቲያን፣ ከንስሐ አባቶቻቸው፣ ከብፁዓን አበው፣ ከሊቃውንት ካህናት፣ ከዲያቆናት፣ ከምስኪን ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ምዕመናንና ምዕመናት የሚጣሉ፣ የሚጋጩ አያሌ ናቸው፡፡
  ያልተወሰነውን ተወሰነ፣ ያልተባለውን ተባለ እያለ፣ እንዲህ ተወስኖ ተግባራዊ ያልሆነው በእነ እከሌ ሥልጣንና እምቢተኝነት ነው እያለ "ላም ባልዋለበት ኩበት ያስለቅማል"፡፡››
  ብላችሁ ለመክሰስ እንዴት ደፈራችሁ? አንድ ሰዉ እኮ ቢያንስ ቢያንስ ሌሎቹን ከሚከስበት ወንጀል ነጻ መኆን ይጠበቅበታል፡፡ እናንተ ግን የምትከሱበትን ወንጀል በመፈጸም ከምትከሱት አካል በብዙ የምትበልጡ ሆኖ ሳለ ምን ያህል አንባቢን ብትንቁ ነዉ እንደዚህ የምትመጻደቁት? ሌላዉ ቀርቶ ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን ማረጋገጥ እንኳ ሳትችሉ ይህን ያህል የምትጮሁት እናንተስ መናፍስት ናችሁ? እዉነት ለመናገር የእናንተን ስህተታችሁን ከመናገር በነገራችሁ ዉስጥ እዉነት የሆነ ነገር ካል እርሱን ለማግኘት መጣር የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ይህን ደግሞ ዋሾ ኅሊናችሁ እንኳ ይመሰክርባችኋልና ተመለሱ፡፡

  ReplyDelete
 9. +++
  Who said we have to lie for politics!?
  There is nothing hiden, a believer should believe there is time for judgement. The almighty God will judge all. The host for this blog knows who is lying. Don't cover the fight as a fight caused by some people you know who we are fightying! May God provide you peace, and faith!

  ReplyDelete
 10. Why are you not posting my genuine comment? Please be impartial and entertain us equally, otherwise I and others will divert to other blogs where our ideas are entertained and we could also post there what we are denied of here.

  ReplyDelete
 11. Wow, I sense MK is a genuine and strong institution working for the church. Otherwise, such acquisitions against it should not emerge at first place had it been weak and weird.
  This might also help us understand more and more about the sabotage against our God, Jesus Christ, in his earthly life among us 2000 years ago.

  ReplyDelete
 12. mahibere kidusan is the back bone for our lovely church.mk protects the the thehadeso so that you always complian all the times.long life to mk,its my hero!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. የማህበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም ቤተክርስቲያን ግን እሄዳለሁ የማህበረ ቅዱሳንን ጋዜጣ ስምዓ ፅድቅን እከታተላለሁ በጣም ጥሩ ነው የኛ ቤተክርስቲያን /ኦርቶዶክስ ተዋህዶም/ ሆነ እውነተኛ አገልጋዮቹዋ ማህበረ ቅዱሳን አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በደንብ ይሰብካሉ ለዛውም እንደ እናንተ ኢየሱስ ክርስቶስን አማላጅ ብለው ሳይሆን አምላክ ብለው ነው የኛ ቤተክርስቲያን እኮ ገና ግቢዋ ስንገባ ነው አምላካችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምትሰብከን ጉልላቱዋ መስቀል ነው መስቀሉን ስናይ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር አምላክን እናያለን እናንተ ከሃዲ ተሃድሶዎች/መናፍቃኖች/ መቼም ቢሆን አይሳካላችሁም ህዝቡ ሁሉ ነቅቶባችኃል ዕድሜ ለአዋሳ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ሲዲ በተረፈ ማህበረ ቅዱሳንን እግዚአብሄር ያብዛልን ይጠብቅልን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነታችንን ከነታሪኳ በእግዚአብሄር እረዳትነት ጠብቀው ለትውልድ አስተላልፈዋል ገና ያስተላልፋሉ እኛም ለመጪው ትውልድ ልናስተላላፍ በእግዚአብሄር ፊት ቃል እንገባለን አሜን እግዚአብሄር አምላክም እስከ መጨረሻው ከኛ ጋር ነው አሜን ፡፡

  ReplyDelete
 14. ግን እናንተ ማን ናችሁ መታረምን የማይወድ ትውልድ ስተቶችን ሲያወራ ይኖራል ሁልጊዜም እራሱ አይታረምም ይህ ደግሞ ለ/ቤተክርስቲያን እሾክ እንደሆነ ይኖራል

  ReplyDelete