Saturday, October 29, 2011

የአቶ ማንያዘዋል ሲኖዶስ ታሪካዊ ስሕተት ፈጸመ

ገንዘብ ካለእንደሚባለው፣ ማኅበረ ቅዱሳን በገንዘብ የገዛቸውና ነውራቸውን ማስፈራሪያ አድርጎ ሲጠቀምባቸው የነበሩትን ጳጳሳት ተጠቅሞ ዕድሜውን ማራዘም መቻሉና የፈለገውን ማስወሰኑ ተገለጸ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከትናንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወዛገብበት በነበረው የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና እና የአባ ሠረቀ የማደራጃው መምሪያ ኀላፊነት ጉዳይ ዛሬ በዱላ ቀረሽ ውዝግብ ውሳኔ ያገኘ ይመስላል፡፡ አባ ሠረቀ ከቦታቸው እንዲነሡ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንዳይፈርስና መተዳደሪያ ደንቡ ተሻሽሎ ሥራውን እንዲቀጥል በገንዘብ የገዛቸውና በነፍስ ወከፍ 200 ሺህ ብር የከፈላቸው ሊቃነ ጳጳሳት ማኅበሩ የሰጣቸውን ተልእኮ በሚገባ ተወጥተው ለማኅበረ ቅዱሳን ለወሬ የሚመች ውሳኔ መወሰናቸውን፣ በእውነት ፊት ግን ታሪካዊ ስሕተት መፈጸማቸውንና የቤተ ክርስቲያናችን የመከራ ዘመን እንዲቀጥል መስማማታቸውን ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡

ከዛሬው ውሳኔ ላይ መድረስ የተቻለው በዱላ ቀረሽ ክርክር መሆኑ ሲታወቅ፣ ውሳኔው በማኅበረ ቅዱሳን ገንዘብ የተደለሉ በርካታ ጳጳሳት በሰጡት ድምፅ ብልጫ ከመወሰኑ በፊት፣ ውሳኔውን አራት ኪሎ ላይ ነጭ በነጭ ለብሶ ጧት ማታ ሲንቀዋለል የሚውለው ሥራ ፈቱና የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘር ነኝ እያለ የሚፎክረው የማኅበረ ቅዱሳኑ አቶ ማንያዘዋል ትናንት አርብ ከጠዋት ጀምሮ አባ ሠረቀ ይነሣል፤ የሊቃውንት ጉባኤን ደግሞ በተሐድሶነት እናስጠረጥራለን እያለ ለብዙዎች ሲያወራ ተሰምቷል፡፡ ድረገጻቸው ደጀሰላምም ይህንኑ ሐሳብ አስተጋብቶታል፡፡ ኅሊናቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን አላፊና ጠፊ ብር የሸጡት ጳጳሳትም በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ሳይሆን በገንዘብ ተነድተው ማን ያዘዋል እንዳወራው አባ ሠረቀ ይነሡ ሲል ወስነዋል፡፡

በተጨማሪም የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ራሳቸው ተሐድሶ ስለሆኑ የተሐድሶን ጉዳይ ለማየት ብቁ አይደሉም፤ ስለዚህ ጳጳሳት ለዚህ ሥራ መመደብ አለባቸው በማለት አባ ሕዝቅኤል ያቀረቡት ሐሳብ፣ ማኅበሩ በገንዘብ በገዛቸው ጳጳሳት በአብላጫ ድምፅ ተወስኗል፡፡ በዚሁ መሠረት አራት ጳጳሳት የተመደቡ ሲሆን፣ ከመካከላቸውም አቡነ ቄርሎስና አቡነ ናትናኤል እንደሚገኙበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ እንዲህ ዐይነት ውሳኔ ማስወሰን ለማኅበረ ቅዱሳን አዲስ ባይሆንም፣ ውሳኔው በሥራ ላይ ይውላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በማኅበሩ ላይ የተነሣው ተቃውሞም በገንዘብ በተገዛ ውሳኔ ይቆማል ተብሎ እንደማይጠበቅ የብዙዎች ግምት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ባሰ ችግር እንዳይወስዳትም ያሠጋል፡፡

ቀደም ሲል እንደ ዘገብነው በማኅበሩና በማደራጃ መምሪያው መካከል ያለውን ውዝግብ እንዲያጣራ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው ኮሚቴ የማጣራት ተግባሩን አጠናቆ የደረሰበትን ድምዳሜ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረበ ሲሆን፣ በዚሁ መሠረት ማኅበሩ ከእምነት ተቋምነት ወጥቶ በንግድ ሥራ የተሠማራና በቤተ ክርስቲያን ስም እየነገደ ከፍተኛ ሀብት ያከማቸና ከቤተ ክርስቲያን ቁጥጥር ውጪ የሆነ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደርም ጣልቃ እየገባ አላሠራ ያለ፣ ፖለቲካዊ ንክኪም ያለው ማኅበር በመሆኑና ለራሱ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ያልጠቀመ፣ ይልቁንም ቤተ ክርስቲያንን እያመሰ ያለ ስብስብ ስለሆነ፣ እያደረሰ ካለው ጥፋት አንጻር መዘጋት አለበት ሲሉ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

የተቋቋመው አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበት ድምዳሜ ማኅበሩ መፍረስ አለበት የሚል ቢሆንም፣ 200 ሺህ ብር በላይ የተከፈላቸው የሚመስሉት የወሎዎች ቡድን ዋና አቀንቃኝ የሆኑት አባ ሕዝቅኤል ማኅበረ ቅዱሳን ከተዘጋ ቤተ ክርስቲያን ማን አላት? ስለዚህ የማኅበሩ ደንብ ተሻሽሎ እንዲሠራ መደረግ አለበት ሲሉ በበላ አንጀታቸው ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረዋል፡፡ ይህም ፍርደ ገምድል ውሳኔ በዐፄ ምኒልክ ጊዜ መንዝ ውስጥ ተፈጸመ የተባለውን አጋጣሚ አስታውሷል፡፡

መንዝ ውስጥ ነው፤ አንዱ ወታደር የአንዱን ገበሬ ሚስት ይደፍራል፡፡ የተበደለው ገበሬም ወደ ዳኛ ሄዶ አቤት ይላል፡፡ ዳኛውም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ወቴ ጥፋተኛ መሆኑን ይደርስበታል፤ ነገር ግን ወታደሩን ስለ ፈራው መበደሉን ወታደር በድሏል፤ ነገር ግን ገበሬ ይካስ ሲል በየነ ይባላል፡፡ በዚያው ዘመን አዲስ አበባ ላይም አንዱ ተበድሎ ቢፈረድበት፡-

        እግዚኦ!! ለአራዳ ዳኝነት

        እኔው ተበድዬ እኔው ለካስኩበት

አለ ይባላል፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳን የተወሰነለት ውሳኔም ይህን የመሰለ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ጥፋት እያደረሰ ያለ ጥፋተኛ ማኅበር መሆኑ ሲኖዶሱ በሰየመው አጣሪ ኮሚቴ ተጣርቶ ቀርቧል፡፡ በዚያ ላይ ተመሥርቶ ፍትሐዊ ውሳኔ መስጠት ሲገባ፣ ማኅበረ ቅዱሳን ጥፋተኛ ነው፤ ቢሆንም አባ ሠረቀ ይካሱ የሚል አይነት ውሳኔ መወሰን የሲኖዶሱን ገጽታ የሚያበላሽ እጅግ የወረደ ተግባር ነው፡፡ ምን ይደረጋል! የማኅበሩን እኩይ ተግባር ያጋለጡትና ቤተ ክርስቲያንን ከጥፋት ለመታደግ ማኅበሩን ሥርዐት ይዘህ ተንቀሳቀስ ያሉት አባ ሠረቀ ከማደራጃ መምሪያነታቸው መነሣት አለባቸው ሲል በብር የተገዛውና በበላበት የሚጮኸው የነአባ ሕዝቅኤል ቡድን፣ እንዲሁም ነውርህን እሸፍንልሃለሁ በሚል ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር እከክልኝ፣ ልከክልህ የሚባባለው የነአባ ሳሙኤል ቡድን፣ ለግል ጥቅሙና ነውሩ የተሸፈነለት መስሎት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ታሪካዊ ስሕተትና ከፍተኛ በደል ፈጽመዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የተጀመረውን ንግግር ወደ አባ ሠረቀ በማዞርና አባ ሠረቀ፣ ማርያም ጥንተ አብሶ አለባት ሲሉ ተናግረዋልና ሊወገዙ ይገባል ሲሉ የከሠሧቸው አባ ሳሙኤል መሆናቸው ታውቋል፡፡ አባ ሳሙኤል ለማኅበረ ቅዱሳን ያደሩት የነውር ሥራቸውን የሚያጋልጥ ማስረጃ በማኅበሩ እጅ ገብቷል ተብሎ በስፋት ከተወራ ወዲህ መሆኑ ይነገራል፡፡ ማኅበሩ ከእጄ ገብቷል በሚለው መረጃ እያስፈራራ፣ በመጀመሪያ የአባ ሳሙኤልን ደካማ ጎን በመለየት አቡነ ጳውሎስ እንዲወርዱ ያድርጉልን እንጂ፣ እርስዎ ፓትርያርክነቱን እንዲያገኙ እናደርጋለን፤ በሚል መፈንቅለ ፓትርያርክ የማድረግ ተልእኮን ሰጥቷቸው እርሳቸውም ያለአቅማቸው ፓትርያርክ ለመሆን ቋምጠው ባለ በሌለ ኀይላቸው ተንቀሳቅሰው የነበረ ሲሆን፣ ያሰቡት ሳይሳካ ትልቅ ውርደትና ቅሌት ተከናንበው፣ በሙስና በሰብኣዊ መብት ረገጣና በሌሎችም ጥፋቶች ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተነሥተዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ማስፈራሪያ አድርጎ የያዘውን መረጃ ይፋ ማድረግ ቀላል ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያናችን ክብር ስንል እስከ ዛሬ ከመግለጽ ተቆጥበን ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ አባ ሳሙኤል ያሉት የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪዎች ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየመሯት ስለሆነና ከፍተኛና ታሪካዊ ስሕተት መፈጸማቸው ትዕግሥታችንን ስላሟጠጠው፣ መረጃውን ይፋ ለማድረግ ተገደናል፡፡

ሊወገዝ የሚገባውና ዛሬ አውጋዥ ነኝ ባዩ አባ ሳሙኤል እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት ጳጳስ ነው ይባል እንጂ፣ በአሁኑ ሰዓት / ኤልቤቴል መንገሻ ከምትባል ሴት ጋር በትዳር የሚኖር አቶ ነው፡፡ ይህ ሰው ለዓለም ሞቻለሁ ያለበትን የምንኩስና ቃል ኪዳን አፍርሶ ባለትዳር መሆኑ ሳያንስ፣ በአንድ መወሰን አቅቶት ላፍቶ አካባቢ ያስቀመጣት ቅምጥም እንዳለችው ተረጋግጧል፡፡ እንደርሱ በቆብ አግብተው የሚኖሩ ጳጳሳት መኖራቸው ለቤተ ክርስቲያን ቅርበት ባላቸው በተለይም በካህናትና በዲያቆናት ዘንድ የአደባባይ ምስጢር መሆኑ ይታወቃል፡፡ በቀጣይ የእነዚህን ባለትዳር ጳጳሳት ማንነት ይፋ የምናደርግ መሆናችንን ስንገልጽ ጥልቅ ሐዘን ይሰማናል፤ ቤተ ክርስቲያናችንን አንገት የሚያስደፋ ነውና፡፡ ዓላማችን ቤተ ክርስቲያናችንን እንደ እነዚህ ካሉት ምግባረ ብልሹዎች የምንጠብቅበት ወሳኝ ጊዜ አሁን መሆኑን ለማስገንዘብና ሲኖዶሱ በመንፈስ ቅዱስ መመራቱን ትቶ በገንዘብ በተገዙ ጳጳሳት የድምፅ ብልጫ እውነት ሐሰት፣ ሐሰት ደግሞ እውነት እየተባለ የሚወሰንበት የሙስና መደብር መሆኑን ለማሳየት፣ ለገንዘብ የተገዙና የተሻለ ከተከፈላቸው በጨረታው የማይገደዱ ሰዎች መናኸሪያ እየሆነ መምጣቱን ሁሉም እንዲያውቀው ለማድረግም ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ብፁዕ አቡነ ሚካኤልም ባለትዳር እንደ ነበሩ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል፡፡ በሞት እስከ ተለዩበት ጊዜ ድረስ አብራቸው በትዳር ከቆየችው ከወ/ መሠረት ታደሰ በፊትም ከሌላ ሴት ወንድ ልጅ የወለዱ ሲሆን፣ ይህ ልጅ ስሙ ዮሐንስ እንደሚባልና በሕግ ትምህርት መመረቁ ታውቋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ሚስታቸውና ልጃቸው ወራሾች መሆናቸውን በፍርድ ቤት አስመስክረው ወራሽነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ አቶ አባ ሳሙኤል ግን ለምን ምስጢር አወጣሽ በሚል / መሠረትን ሲያስፈራራ እንደ ነበረና የአቡነ ሚካኤልን ሀብት የሥጋ ዘመዶቻቸው እንዲወርሱ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ እንደ ቆየ ሲታወቅ፣ ሕጋዊ ወራሽዋ / መሠረትም ቅዱስ ሲኖዶስ የአባ ሳሙኤልን ዛቻና ማስፈራሪያ እንዲያስቆምላትና ፍርድ ቤት ያረጋገጠላትን ወራሽነት መሠረት በማድረግ የሚደርሳትን ሀብት የምታገኝበትን መንገድ እንዲያመቻችላት በጻፈችው ማመልከቻ ጠይቃለች፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስና በግልባጭም ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነትና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አሳውቃለች፡፡ ማመልከቻው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት ከገባ በኋላ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሲታመስ እንደ ዋለና ጳጳሳቱ ሁሉ በስብሰባ ተወጥረው እንደ ነበረ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ብዙዎቹ ጳጳሳት ጉዳዩንም ሆነ ወይዘሮዋን በሚገባ የሚያውቁ ቢሆንም ነገሩ ለምን ተገለጠ በሚል ጉዳዩን ሸፋፍነው በማለፍ ሐሰት ነው፤ አንቀበልም ሲሉ ውድቅ አድርገዉታል፡፡ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ወደፊት ተከታትለን የምንዘግብ ይሆናል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ የዚችን ምስኪን ሴት ጉዳይ ተመልክቶ ውሳኔ ሊሰጥ ሲገባ፣ / መሠረት ታደሰ በጻፉት ማመልከቻ ላይ የዘረዘሩት የአባ ሳሙኤል ተግባር ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚጥስ በመሆኑ፣ አባ ሳሙኤል መወገዝ ሲገባው ጉዳዩ ተሸፋፍኖ እንዲያልፍ መደረጉ ሳያንስ፣ ሊወገዝ የሚገባው አባ ሳሙኤል፣ ያለ ሥራቸው አባ ሠረቀን ይወገዙ ማለቱ የሌባ ዐይነ ደረቅ አሰኝቶታል፡፡

ይህች ቤተ ክርስቲያን መዋረድ የጀመረችው እንደነዚህ ያሉትን ከትምህርት ትምህርት፣ ከሥነ ምግባር ሥነ ምግባር የሌላቸውን አባ ሳሙኤልንና መሰሎቹን ጳጳሳት አድርጋ የሾመች ዕለት መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ሲሆን፣ መጀመሪያውኑ የታላቁን አባት የብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስን ምክር ሲኖዶሱ ቢቀበል ኖሮ ይህ ሁሉ አይመጣም ነበር ይላሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ፣ የዛሬው የቀድሞው አባ ተከሥተ የዛሬው አባ ሳሙኤል ገና ለጵጵስና ሲታጭ፣ ምነው ይህንስ ጳጳስ ከምናደርገው ብንድረው አይሻልም ወይ! በእውነቱ ለእርሱ ሥርዐተ ጵጵስና ሳይሆን ሥርዐተ ተክሊል ነው ማድረስ የሚገባው ሲሉ የተናገሩት ትንቢታዊ ቃል ቢሰማ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ አንገቷን አትደፋም ነበር በማለት በሐዘን የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡

25 comments:

 1. አዬ ግብዞች አሁን በእውነት የተፈረደላችሁ ይመስላችሁ ይሆናል። ነገር ግን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
  በገንዘብና በሐሰት ምስክር ነው አምላካችንን የገደሉት። እናም የእግዚአብሔርን ሰው አባ ሰረቀን፡ ለሆዳቸው
  ባደሩ፣ እንደ ይሁዳ በገንዘብ የተገዙ ፣ ቤተክርስቲያናችንን የሚያዋርድና የሚያሳፍር ሥራ እየሰሩ ፣በሐጢያት
  በተጨማለቁ፣ አንዳንድ ጳጳሳት፡ ከዚህ ከወንድሞች ከሳሽ ጋር በመተባበር የሙት ሙታቸውን በበላ አፋቸው
  ለፍልፈውና ውሸቱን እውነት አስመስለው ተናግረው በአባ ሠረቀ ላይ በአድማ ቢያስወስኑም፤ እሳቸውም ሆነ
  እኛ የመድሐኒያለም ልጆች ግን ቀደም ሲል ከመምህራችንና ከጌታችን የተማርነው \በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ\
  ነውና ምንም አይደንቀንም። ነገር ግን አይሁድ ክርስቶስን በሐሰት ከገደሉት በኃላ ትዝ ሲላቸው በሶስተኛው ቀን
  እነሳለሁ ብሎ ተናግሩአልና ንጉስ ጲላጦስ ሆይ የመጀመሪያው ስህተት ከኃለኛው እንዳይብስ እባክዎን የመቃብሩ
  ጠባቂዎች ይታዘዙልን ብለው ጠየቁ፤ ጠባቂም ታዘዘላቸው፡ ነገር ግን ጌታችን በትንሳኤ መነሳቱ አልቀረም።
  የኛ ጌታ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነውና። አሁንም እናንተ በሐሰት የመሰከራችሁ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ጳጳሳት፤
  የመጀመሪያው ጥፋት ከሁዋለኛው እንዳይብስ ለተመረጣችሁለት አገልግሎት በሐቅና በፍቅር ሆናችሁ እራሳችሁን
  መርምሩ። አለዚያ ግን ቤተክርስቲያናችሁንና እራሳችሁን የባሰ ነገር ውስጥ እያስገባችሁት ነው።

  \አትፍረድ ይፈረድብሃል ስለ ሆነ \ የወንድሞች ከሳሽ የሆነው ማህበር ዛሬ በእጄ ስለእናንተ ጉድና የሐጢያት
  ወንጀል ስራ ማስረጃ አለኝ፡ እንደምንም ብላችሁ የኛን ጉዳይ ካላስፈፀማችሁ እኛም ጉዳችሁን እናወጣዋለን፡
  በማለት ሲያስፈራሩአችሁና በገንዘብ ስለገዙአችሁ በሐሰት አስፈፀማችሁላቸው። ለዚህ ነው አይሁድ ፈሪሳዊያን
  እግዚአብሔር ባወቀ ከመጀመሪያው ስህተት የኃለኛው እንዳይብስ ብሎ ያናገራቸውና ፡ እናንተም የማቅን ሥራ
  ስለሰራችሁለት ለጊዜው ጉዳችሁን ባያጋልጠውም፤ የሚቀጥለው የጉዞ ሂደት ግን እራሱ ሰይጣን ብቻውን መቃጠል
  ሰለማይፈልግ ወደ እናንተ ደግሞ ይመጣል። የማይገለጥ የተከደነ የለምና።

  በመጨረሻም አባ ሠረቀና ለእውነት የቆማችሁ ፓትሪያሊክ አቡነ ጳውሎስ፣አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እንዲሁም
  እህቶቻችን አይዙአችሁ በርቱ። \ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ\ አይደል ያለው አምላካችን፡፡ እኔ ለእናንተ
  ይህንን መናገር አይገባኝም ነበር፤ ነገር ግን የተሰማኝን ያህል ለመገለፅ በማለት ነው እንጂ በድፍረት አይደለም።

  እግዚአብሔር እንደ እናንተ ያሉ ሐቀኛና አስተዋይ አባቶች
  አያሳጣን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን።

  ReplyDelete
 2. አዬ ግብዞች አሁን በእውነት የተፈረደላችሁ ይመስላችሁ ይሆናል። ነገር ግን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
  በገንዘብና በሐሰት ምስክር ነው አምላካችንን የገደሉት። እናም የእግዚአብሔርን ሰው አባ ሰረቀን፡ ለሆዳቸው
  ባደሩ፣ እንደ ይሁዳ በገንዘብ የተገዙ ፣ ቤተክርስቲያናችንን የሚያዋርድና የሚያሳፍር ሥራ እየሰሩ ፣በሐጢያት
  በተጨማለቁ፣ አንዳንድ ጳጳሳት፡ ከዚህ ከወንድሞች ከሳሽ ጋር በመተባበር የሙት ሙታቸውን በበላ አፋቸው
  ለፍልፈውና ውሸቱን እውነት አስመስለው ተናግረው በአባ ሠረቀ ላይ በአድማ ቢያስወስኑም፤ እሳቸውም ሆነ
  እኛ የመድሐኒያለም ልጆች ግን ቀደም ሲል ከመምህራችንና ከጌታችን የተማርነው \በኔ ሳላችሁ መከራ አለባችሁ\
  ነውና ምንም አይደንቀንም። ነገር ግን አይሁድ ክርስቶስን በሐሰት ከገደሉት በኃላ ትዝ ሲላቸው በሶስተኛው ቀን
  እነሳለሁ ብሎ ተናግሩአልና ንጉስ ጲላጦስ ሆይ የመጀመሪያው ስህተት ከኃለኛው እንዳይብስ እባክዎን የመቃብሩ
  ጠባቂዎች ይታዘዙልን ብለው ጠየቁ፤ ጠባቂም ታዘዘላቸው፡ ነገር ግን ጌታችን በትንሳኤ መነሳቱ አልቀረም።
  የኛ ጌታ የአሸናፊዎች አሸናፊ ነውና። አሁንም እናንተ በሐሰት የመሰከራችሁ የዘመኑ ፈሪሳዊያን ጳጳሳት፤
  የመጀመሪያው ጥፋት ከሁዋለኛው እንዳይብስ ለተመረጣችሁለት አገልግሎት በሐቅና በፍቅር ሆናችሁ እራሳችሁን
  መርምሩ። አለዚያ ግን ቤተክርስቲያናችሁንና እራሳችሁን የባሰ ነገር ውስጥ እያስገባችሁት ነው።

  \አትፍረድ ይፈረድብሃል ስለ ሆነ \ የወንድሞች ከሳሽ የሆነው ማህበር ዛሬ በእጄ ስለእናንተ ጉድና የሐጢያት
  ወንጀል ስራ ማስረጃ አለኝ፡ እንደምንም ብላችሁ የኛን ጉዳይ ካላስፈፀማችሁ እኛም ጉዳችሁን እናወጣዋለን፡
  በማለት ሲያስፈራሩአችሁና በገንዘብ ስለገዙአችሁ በሐሰት አስፈፀማችሁላቸው። ለዚህ ነው አይሁድ ፈሪሳዊያን
  እግዚአብሔር ባወቀ ከመጀመሪያው ስህተት የኃለኛው እንዳይብስ ብሎ ያናገራቸውና ፡ እናንተም የማቅን ሥራ
  ስለሰራችሁለት ለጊዜው ጉዳችሁን ባያጋልጠውም፤ የሚቀጥለው የጉዞ ሂደት ግን እራሱ ሰይጣን ብቻውን መቃጠል
  ሰለማይፈልግ ወደ እናንተ ደግሞ ይመጣል። የማይገለጥ የተከደነ የለምና።

  በመጨረሻም አባ ሠረቀና ለእውነት የቆማችሁ ፓትሪያሊክ አቡነ ጳውሎስ፣አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እንዲሁም
  እህቶቻችን አይዙአችሁ በርቱ። \ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ\ አይደል ያለው አምላካችን፡፡ እኔ ለእናንተ
  ይህንን መናገር አይገባኝም ነበር፤ ነገር ግን የተሰማኝን ያህል ለመገለፅ በማለት ነው እንጂ በድፍረት አይደለም።

  እግዚአብሔር እንደ እናንተ ያሉ ሐቀኛና አስተዋይ አባቶች
  አያሳጣን። ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን።

  ReplyDelete
 3. የአባ ተከስተን ምነው የቅድስት ማርያሟን የወይዘሮ ምሥራቅን ጉዳይ ተዋችሁት? የአባ ቃለጽድቅንስ(አባ አብርሃምን) የአዲሱ ገበያዋን ያቺ ቆንጆ ወይዘሮ ረሳችኋት? ነገሩ እየገፋ ከመጣ የምስልና የድምጽ ማስረጃውን እናቀብላችኋለን፤ አታስቡ። በእርግጥ መንግሥት ደርሶታል። «ካልደፈረሰ አይጠራም» አለ የሀገሬ ሰው!!

  ReplyDelete
 4. Aba selama?
  I have commented you what you do about the dirty person-Manyazewal.

  ReplyDelete
 5. Good information. tell us more about mehaber sitan too.

  ReplyDelete
 6. ብዙዎቻችን ድጋፋችን እውነት ስለተነገረና ሀቁ ስለወጣ ሳይሆን ምነው እንዲህ ዓይነቱን ጉድና የማዕረግ ጉድፈት ባንሰማና ባናነብ የሚል ነው። እንደቤተክርስቲኗ ሥርዓት መሆን ስላለበት ቅድስና መታገል ሳይሆን እኔ የምዋኝበትን የዝሙት ዓለም እነርሱም ከደገሙት ባይሆን የነርሱን እንዳልሰማ ሰው ዝም ጭጭ ልበል ነው እየታየ ያለው። የውሾን ነገር አታንሱ ዓይነት መሆኑ ነው። ደግሞም ይህ አስተሳሰብ ለሁሉም ቢሆን ባልከፋ በሚጠሏቸው ጳጳሳት ላይ በደጀ ሰላም ብሎግ ጥንብ እርኩሳቸውን ሲወጣ «አይ የቤተክርስቲያን አምላክ አንተ ፍረድ» እያሉ የአዞ እንባ የሚረጩ መሆናቸው ነው የሚያሳዝነው። «evil axis» እያለ በአባ ጳውሎስ፤ በአባ ሠረቀ፤ በአባ ፋኑኤል ላይ ደጀሰላም ሲጽፍ ሁሉም እጁን ሲያጨበጭብ አይተናል። አሁን የጥፋት ምህዋር ስለመሆናቸው በሌሎች ላይ ሲጻፍ ምነው በአባ ሰላማ ብሎግ ስድብ ወረደባት? እንደዚህ ያሉ ሰዎች አማኞች ሳይሆኑ ዘረኞች መሆን አለባቸው። የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳስ ሰይጣንም ቢሆን መነካት የለበትም፤ ማኅበረ ቅዱሳንን ትንሽ የነካ ቅዱስ ቢሆንም መርከስ አለበት ያለማነው? እናንተ ጭፍን የጽድቅ ማቆች!! ዳንኤል ክብረት እውነቱን ነግሮናል። ከደገፈ ማንም ምንም ቢሰራ አይነካም፤ ከተቃወመ ማንም ምንም ባይሰራ እንደሰራ ይቆጠራል ማለቱ አይዘነጋም። አባ ተከስተ፤ አባ ቃለጽድቅና ሌሎቹም አንድ በአንድ የሚታወቅ ለጵጵስና የማያበቃ ነውር ያለባቸው መሆኑ የአደባባይ እውነት ነው። የምስልና የድምጽ ማስረጃ የተገኘባቸው ሰዎች መሆናቸውን አደባባይ ማውጣት በደል የሚሆነውና ዶኒ ለአባ ሠረቀ የጻፈው ደብዳቤ ትክክል ተብሎ የሚታየው በማን ሚዛን ይሆን? ኅሊና ያለው ይፍረድ!! ለማንኛውም እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ማን ምን እንደሆነ በጊዜው ይገለጣል።« መውጊያውን ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል» እንዳለው።

  ReplyDelete
 7. Good job Aba Selama. I like your blogs. Keep blogging. MK are criticizers.

  ReplyDelete
 8. Zewde ze-arat kiloOctober 29, 2011 at 9:28 PM

  Aba selama?
  I have enough concret documents including eye witnesses concerning the evil faces of MK (its leaders), and some carnal bishops. However, still I am waiting untill my patience is ended up for the fact that thinking to the betterment of the church.
  eg. if you want to get additional evidence about Abune Samuael's 'gemena', I lead you to approach the house servant of Abune Michael; she was in Addis Ababa and so as to keep the secrecy for their evil life ,the bishop took her to shire. There, the big drama was also continued.

  If you understand me, my focus is not on the departed bishop as he is already left us but on Abune Samueal whose full darkened history (evidence) is available to the house servant.

  ReplyDelete
 9. Tarikayehu
  Abune merha bicha sayihonu yezare yekuy tegbaru tebabari ABUNE Qerlosm Ato Tekeste "samuel" meshom yelebetm blew neber... zare srqotu lay tebaberut inji.

  ReplyDelete
 10. 1. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  2. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  3. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  4. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  5. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  6. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  7. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  8. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  9. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  10. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  11. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  12. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ

  ReplyDelete
 11. YE DINGIL MARIYAM LIG LIUL AMLAK IGZIABHER IWINETUN YIGLETILACHIHU.....YI HULU YEHONEW LIN BEZA SAYHON LINTERA YE TETERAN SILHONIN CHIMIR NEW! TEMESGEN!!!!

  ReplyDelete
 12. መዋጮ ሰብሳቢ አራጣ አበዳሪ
  ማቅ ለባሽ ቀበሮ ቤተስኪያን ሰርሳሪ
  አሥራትሽ በልቶ ሀብትሽ ቸርቻሪ
  ቢበዛም ቢሰፋም ተዋሕዶ አትፍሪ
  ቋሚዎች አለንሽ ለክብርሽ አዳሪ

  ከተዋሕዶ ውጭ ማኅበር የለንም
  በማኅበራት ጦር ዘውትር ብንወጋም
  ከተዋሕዶ ውጭ ማኅበር የለንም
  ያንችው ነን ሁል ጊዜ ብንኖርም ብንሞትም
  ከተዋሕዶ ውጭ ማኅበር የለንም
  ቅድስት እናታችን ኑሪልን ዘላለም

  አንቺን ለማገልገል ሌላ ደንብ አንሻም
  ካጥቢያሽ ጉባኤ ውጭ መዋጮ አናዋጣም
  በስምሽ ከብረናል ባንች አንነግድም
  ተዋሕዶ ብለን መቼውም አናፍርም

  መደራጀትና የመደብ ትግል የኮሚኒዝም መሆኑን እያወቃችሁ
  ደርጎችን የምትመስሉ ሁላችሁ . . . እባካችሁ
  ቤተ ክርስቲያንን በቡድን/በማኅበር እየከፋፈላችሁ
  አታውኩን ያለፈው ይብቃችሁ

  ReplyDelete
 13. I Like the previous gitim and the following answer against the apology of the MK on Deje selam

  ወዴት ሸሸት ሸተት ነው ከተጋፈጡ ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው፡፡ ማንነታቸሁ ሲጋለጥ የት ልትገቡ ነው፡፡ ይልቁን በሥራችሁ ያሉትን ወጣቶች ማሳት ትታችሁ በእውነተኛ ማንነታችሁ ኑሩ፣ በቃ ሰባ ጉባኤ ይጠናከር፣ ሰንበት ትምህርት ቤት ይስፋፋ እናንተን አንፈልግም፣ ነጋዴዎች ናችሁ፤ ሃያ ሽ ወጣት አሥራት፣ እና ወርሀዊ መዋጮ፣ በሀገር ውስጥ ብቻ ከአርባ በላይ ሱቅ፣ በአብነት ትምህርት ቤትና በገዳማት ስም መጠነ ሰፊ የሆነ ልመና፣ ሲቀርብ የሰማነው ሪፖርት ግን የጧፍና የሻማ እርዳታ፣ አልሰማችሁም እንዴ አንድ ግለሰብ በሦስት ሚሊየን ብር አንድ ትምህርት ቤት በለሚ ሲሠራ ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ማኀበር መሆን አያስፈልግም፣ አትራፊ የሆኑ መጽሔቶችና ጋዜጦች በዓመት ከ600 ሽ በላይ ተሰራጭተዋል፣ከዚህ ሁሉ ገንዘብ አንዲት ቅንጣት ለቤተ ክስቲያን አትገባም፣ የት ይሔዳል ???????????????? …..

  1. የመናፍቃን ዝርዝር ብላችሁ ስትበትኑ የነበራችሁት እናንተ አይደላችሁም እንዴ፣ተሀድሶ የተባሉትንም ሰዎች ከእናንተ በስተቀር ማንም አያውቃቸውም፣ እኔ አ መኖራቸውንም የሰማሁት ከእናንተ ነው፣ ማንም እንደሚያውቀው በመሰረቱ ስም እየጠሩ የሰውን በጎ ስም ማጥፋት ማስተር ያደረጋችሁት እና በዚህ ስራችሁ በኢትዮጵያ ታሪክ አንደኛዎቹ እኮ እናንተ ናቸሁ፡፡ የዱሮዎቹ ሊቃውንትና መምህራን እንዲሁም እንደእናንተ ያሉት ምእመናን ሰው ሲሳሳት ይጸልያሉ፣ ይመክራሉ፣ ተከራክረው በጉባኤ ይታሉ እንጂ ሰው ስም አያጠፉም ሰውም አይደባደቡም፡፡ አሁን ሰዎቹ መልካከም ስማቸውን ለመጠበቅ እንደሚከሱ ስታውቁ ፈራችሁ መሰለኝ
  2. እኛ የምሰጋው አሁን መናፍቅ ቤተ ክርስቲያን ገባ ብላችሁ ኦርቶዶክስ መምህራንንና ሰባክያንን እናንተ ማኀበር አባል ስለአልሆኑብቻ የምታሳድዱና እንደ ትዝታው፣ ባለፈው ደግሞ ተክለሃይማኖት እንደተደባደባችሁት የምተደባደቡ ከሆነ ጵንጤወች ተጸጽተውና ሙስሊሞች አምነው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመጠመቅ ሲመጡ አይገቡም እንዳትሉ ነው፡፡
  3. እስከ አሁን ድረስ የቤተ ክርስቲያን ተቆርቆሪ በመምሰል ሊቃውንትን ስታሳድዱ የነበራችሁት እናንተ ናችሁ፣ አሁን ከሊቃውንት ጋር ለማጋጨት የምትሉት የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህረት ቤት ወጣቶች ብላችሁ ስም የለጠፋችሁባቸውን ልጆች በማሳሰር በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ የተባለው ለመተቀም ወጣቶችን ከፊት እንደፈረሰው የቅንጅት ፓርቲአችሁ ለእሳት እየማገዳችሁ እናንተ በሰው ደም ለመኖር ምታደርጉት ጥረት ማንም አይጠፋውም፡፡
  4. ለማንኛውም እወቁት እነ ባህታዊ ገብረ መስቀልን ምንም ሳትሉ፣ ዘርኣ ያእቆብ የተባለ አንድ የዱሮ ንጉስ ተነካ ብላችሁ ይህን ሁሉ ሰው ይወገዝልን ማለት ምን አመጣው፣ ያከፋፈላችሁት መረጃ እኮ በአባቶች እጅ አለ፣ አሁን እኛ አይደለንም ብላችሁ አባቶችን እርስ በራሳቸው ለማጋጨት ነው፣ ወይስ አባቶች ላይ ያለው መረጃ የእኛ አይደለም በማለት አባቶችን ደግሞ ተሐድሶዎች ለማለት ነው፡፡
  5. ዛሬ በጋሻው መናፍቅ የምትሉት ሰባኪ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች እና የጋግራን እሪታ ተባሉ መጽፎቹን እንዳልቸበቸባችሁ፣ እንዳልገዛችሁ ዛሬ የመስቀሉ ሥር ቁማርተኞች እናንተ መሆናችሁን ሲነግራችሁ መናፍቅ አላችሁት

  ReplyDelete
 14. I like the following view
  about the idea of Mahiber in general what did yuo say,

  ለእኛ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የተደራጀች ናት
  ሌላ አደረጃጀት አንፈልግም
  ሌላ አደረጃጀት እሷን ለማፍረስ የሚደረግ ትግል
  ወይም በእሷ ስም ለመነገድ የሚደረግ ግርግር
  የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የመንደር ጠባብ አስተሳሰብ ዓላማ ለማራመድ የሚፈጠር ነው፡፡
  የቤተ ክርስቲያን አደረጃጀት ምን አለህ ወጣት ከሆንክ በሰንበት ትምሀርት ቤት ታቀፍ፣ ከዚያ ካለፍክ በሰበካ ጉባኤ ታቅፈህ የበኩልህን አበርክት በሰበካ ጉባኤ ውስጥ ልማት አለ፣ ስብከተ ወንጌል አለ፣ ቅዳሴ አለ፣ ክህነት አለ፣ ሰንበት ትምህረት ቤት አለ፣ እና ወንድሜ ልንገርህ አንተም ሆንክ ሌሎች ይህ የሌለ መስሏሁ ግልበታችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ ጊዜያችሁን አታሳልፉ ስትሞት እንኳን የሚቀብርህ አጥቢያህ ነው እንጅ ማኅበር አይደለም፡፡ ጸልይ ሰይጣን አይደለሁም ሰይጣን ማለት እንዳበደ ውሻ ባልተሰጠው ስልጣን ገብቶ የሰው ስም የሚያጠፋ ነው፡፡ ሰይጣን በየዘመኑ በርካታ ሊቃውንትን ስም መናፍቅ እያለ አጥፍቷል፣ ሊቃውንትን አሳዷል፣ መለኰሳትን ወለዱ፣ ካህናትን ወሸሙ አሁን እንደሚደረገው አድርጓል ስለዚህ ሰይጣንን ስር ከኔ ከምስኪን ሳሜ ለይተህ እወቅ፣ ምንም እንኳ በጣም ጥልቅ እውቀት ባይኖረኝም እንዳንተ እንደማስብም፣ እናትህ ቤተ ክርስቲያን ለእኔም እኩል እናቴ መሆንዋን፣ አባትህ እግዚአብሄርም ለእኔም አባት መሆኑን ተረዳ

  የመጨረሻ ምክር የእኛ ጥረት ማህበር ለመቃወም ወይንምስ ለመደገፍ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ ናው መነሳት ያለብን እስኪ መህበር ማህበር ማህበት ከምትሉ ማንንም ሳታጠጋጉ አንዲት ቤተ ክርስያን በሉ፡፡

  ReplyDelete
 15. ማን ያዘዋልን የማውቀው ገና ከደብረ ብርሃን ጀምሮ ነው እንዴት ግን ወደ ኮሌጅ ገብቶ ከኮሌጅ ሊመረቅና ሥራ ሊይዝ እንደቻለ አላውቅም እባካችሁ የምታውቁት ካለ????

  ReplyDelete
 16. ማንያዘዋል መቼ ተማረ ብለህ ለጠየቅህ ወገን:

  ይህ ደንቆሮ ሰውዬ ካደገ በሗላ ራሱ “ማንያዘዋል” ብሎ ስም አውጥቶ “እኔ አባቶችን ሳይቀር አዝዛቸዋለሁ” እያለ በየሜዳው የሚቧርቅ፤ ዓላማው የሸዋ ንግሥና ለመመለስ እንደሆነ ከአንደበቱ ሰምተናል። ለስም ቲኦሎጂ ተመዝግቦ ተማሪዎችን ሲያባላ በቅድሰት ስላሴ መ/ኮልጅ ለተወሰኑ ዓመታት የቆየ፣ ትምህርቱን ሳይዝ በዛም በዛም ብሎ ለማምኖ ልማት ኮሚሽን/ኤይች አይቪ ኤድስ መስራቤት የሚያስገባ ወረቀት አገኘና በስራ ከተመደበበት ጀምሮ እስከዛሬ ቀንና ሌሊት ቤተ ክርስቲያንና ቤተ መንግስትን እያከሰረ ያለ ኩርንችት ነው።
  በጣም ከሚገርማችሁ እሱ የሸውዬዎች ተላላኪ ነው ቋሚ ማደርያም የለው እንደ ውሻ ከቤት ለቤት እየዞረ የሚኖር ልብሱን’ኳ የማያጥብ ሙልጭ ያለ ቆሻሻም ጥንባታም ሰው ነው። ፍላጎታቸው በቤተ ክህነትና ቤተ መንግስት የሸዋ ንግስና ለመመስረት ስለሆነ የአሁኑ ፓትርያርክ ይተካል ተብሎ የተገመተ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል ነበረ። እና በጓዳቸው ውስጥ ሆነው ጳጳሱን ለመጥቀም በማስመሰል “አንተነህ የነገው ፓትርያርክ” ብለው ከአቡነ ጳውሎስ ጋር አላተሙት ፤ መላ አካላቱን በስብእናው እንዲዋረድ አደረጉት። አሁን ዋና ታርጌታቸው ፓትርያርኩ ላይ ሳይሆን “ፓትርያርክነት ይተካሉ ተብለው ግምት ውስጥ ለገቡ ጳጳሳት” ስለሆነ ሳሙኤልን ግፋ በለው ይሉታል ሙሉ በሙሉ እስከሚጠፋ ድረስ ማለት ነው። ይህ ሁሉ ከሆነ ግን በሉ ፕትርክናውን ስጡኝ ብሎ በሚጠይቅበት ጊዜ “አንተማ በሥጋ ንጽሕና ይሁን በሌላ የጎደፈ ታሪክ ስላለህ አትድከም “ይሉታል። ሳሙኤል የከሰረ መሆኑን ከተረዱ በሗላ ደግሞ በሌላ መንገድ ዙሮው “ብጹዕ አቡነ ሉቃስ ናቸው ተጠባባቂ ፓትርያርክ መሆን ያለባቸው” እያሉ ወሬ መርጨት ጀምረዋል።
  ለማንኛውም ጉዱ ተዘርዘሮ አያልቅም።

  ReplyDelete
 17. man yazewal ebdna yeibd aqenqagni

  ReplyDelete
 18. ለZemenu Waju: ሲጀመር አንተ እራስህ ጎጠኛ ነህ:: ማህበረ ቅዱሳኖችን አጋልጣለሁ ብለህ ማንነትህን እንዲሁም ያንተን መሳይ ሰዎች አላማ ግልጥልጥ አረክልን:: ለካ አላማችሁ አባ ጳውሎስ ከሞቱ ወይም ከወረዱ ሊላ የአድዋ ወይም የሽሪ ሰዉ እያጫችሁ ኖሩዋልና??? አቡነ ሳሙኢልን መተካት ነበራ አላማዉ?? ታዲያ መንግስታችሁ ለምን ጥበቃ አላደረገላቸዉም ነበር?? ነዉ አድዋ ስላልሆኑ?? ለማንኛዉም የናንተንም የማ/ቅዱሳንንም አላማ ገና አሁን እየተረዳን ነው:: በርቱ በየዋህነት ስንመራ የነበርነው እየነቃን ነው:: በደንብ ስንነቃ ግን ሁለታችሁም የት እንደምትገቡ ይታያል:: እምነትን እንደ ፓለቲካው ችላ የምንል ከመሰላችሁ ተሳስታችሁዋል::

  ReplyDelete
 19. In the name of The Father and The Son and The Holy Spirit One God Amen!
  Almighty God forgive us all for we are full of hatred. How can we even dare to say that we worship The Almighty God who commanded us to love one another, humble ourself and respect all but live on the contrary by immersing ourselves in the sea of hatred. God forgive us all! Amen!Amlake Kidusan, Orthodox Tewahedo haimanotachinin yitebikilin, yasfalin! Amen!

  ReplyDelete
 20. እብድ ውሻ ያገኘውን ይነክሳል ስለዚህ ቀጥሉ ዲ/ን ማንያዘዋልን በቅርበት የማወቅ እድል አለኝ ግን ለማያውቁት ሰዎች እንዳላችሁት ነው ለሚያውቀው ግን እርሱ እርሱ ነው የሚያኮራ ወንድም ከሃይማኖት በቀር ተልእኮ የሌለው እኔም እስከ ማውቀው እንደናንተ ብዙ ብዬ ነበር ግን አይደለም አምላክ ይግለጥላችሁ ከኑፋቄ እብደት ተመልሳችሁ እንደ ሰው ማሰብ ስትጀምሩ እነደኔ ትጸጸታላችሁ ። ለናንተ አይነቱ መናፍቃን ግን ሰይፍ ነው እነማን እንደ ኾናችሁ ስለማውቅ ይህን ተናገርኩ ስለዚህ ከመነፍቃን ከዚህም በላይ ለመቀበል የተዘጋጀ ወንድም ነው ። እናንተ የምትጠሉትን እጥፍ እጅግ የምንወደውና የምንሳሳለት ብዙ የተዋሕዶ ልጆች በሰሜን በደቡብ በምሥራቅ በምዕራብ በሀገርም ውስጥ ከሀገርም ውጭ አለን ። እንግዲህ ምን ትኾኑ ስለኾነው ሁሉ ደስተኞች ነን አስቀድሞ ስለተነገረን << ያለ ስማችሁ ስም ሲሰጧችሁ ደስ ይበላችሁ >> እንደተባለ ። ደስተኞች ነን ደስ ብሎናን ወንድማችን ሰይፍ ስለኾነ ስላቃጠላችሁ ብዙ ማለት ትችላላችሁ እኛ ግን እንወደዋለን እንኮራበታለን ወንድማችን ነው የማንም የምንም ያይደለ የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ልጅ ። አሁንም ደግሜ እላለሁ ለናንተ ሊመቻችሁ አይችልም የናት ጡት ነካሽ የኑፋቄ እብደት ያለናችሁ ስለኾናችሁ ። ወደ ፊት በሰፊው እንገኛለን በወሬ ሳይኾን በተግባር የመናፍቃን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መከማቸት የአባ ጳውሎስ እና የቢችሎቹ ህልም ከንግዲህ አክትሟል ቁርጣችሁን እወቁ ።

  ReplyDelete
 21. ይህች ቤተ ክርስቲያን መዋረድ የጀመረችው እንደነዚህ ያሉትን ከትምህርት ትምህርት፣ ከሥነ ምግባር ሥነ ምግባር የሌላቸውን አባ ሳሙኤልንና መሰሎቹን ጳጳሳት አድርጋ የሾመች ዕለት

  ReplyDelete
 22. ቀደም ሲል መልስ የመለስከውን አመሰግናለሁ
  በእናተችሁ እኔ ከልቤ ነው የምጠይቀው ማን ያዘዋል እንዴት ከኮሌጅ ተመረቀ እንዴት ተቀጠረ

  ReplyDelete
 23. በእናታችሁ ብለህ ለጠየቅከው እኔ ልመልስልህ የተመረቀው ተምሮ ስለጨረሰ በእግዚአብሔር ስለሚያምን የተዋሕዶ ልጅ ስለሆነ እናንተ ከገነት ጋር ያደረጋችሁት የማባረር ጥረት በእግዚአብሔር ቸርነት ስለከሸፈ እንዳንተና እንደመሰሎችህ መናፍቅ ስላልሆ እግዚአብሔርም መናፍቃን ለሰለጠናችሁበት ለንደዚህ ያለ ቀን ስለሚፈልገውና ለዚህ ስላዘጋጀው ብልህ አይዋጥልህ ይሆን? ካልተዋጠልህ ትፋው እውነታው ግን ይሄ ነው ።

  ReplyDelete
 24. I have got very relevant information for the current condition of our church from this blog or web site just keep it up. The solution is on my views just eradicate all organization of others elements. Sunday school is enough for our chuch.

  ReplyDelete
 25. ይህንን መስማትና ማንበብ የሚያሳዝ ቢሆንም ጽዋ እየሞላ መሆኑን ተረድቻለሁ!እንዲዝህ ለጽዋው መሙላት መቸኮል ተገቢ አልነበረም::የማቆችም ጽዋ ሞላ በጵጵስና ስምም የሚነግዱት ጽዋ እየሞላ ነው::ግን እንዲህ በድብቅ ከሚያደርጉት ምናለ በጉባኤዎች ላይ የሚችል አያግባ የማይችል ያግባ ተብሎ ቢወሰን::መቼም ቤ/ክ ዘመኗን ሁሉ ስትጋደል ነበርና ዛሬ ለእውነት ተጋድለው የለቀቁት ሁሉ ነገ ተመልሰው ይመጣሉ ጥርጥር የለኝም::አባ ሰረቀም ላደረጕት ተጋድሎ ከቅዱስ እግዚአብሔር ዘንድ ሽልማቱ ተዘጋጅቷል::እኛም እንጸልያለን::ይችህን ታሪካዊት ቤ/ክ እንደዚህ ማዋረድ ምን ይሰራላችኋል::ጌታችን ጅራፍ ይዞ መግባቱ አይቀርም::
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete