Sunday, October 9, 2011

ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች ( ክፍል ሁለት )


ካሁን በፊት ስለማኅበረ ቅዱሳን ከውጪ ሰዎች እንጂ ከማኅበሩ ሰዎች ብዙም ሲነገር አልሰማንም፡፡ ቢነገርም የማኅበሩ ሚዲያዎች የማኅበሩን ጽድቅ እንጂ ኀጢአት ሲያወሩ አላየንም፡፡ እንደችግር የሚነሡ ቢኖሩም እንኳ መከራ ደረሰብን ከሚል ያለፈ ትክክለኛ ድካምን የሚገልጽ አስተያየት እንኳ ማንበብ ሳይቻል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ማኅበሩ ወደ ውድቀቱ እየተፋጠነ መሆኑን የሚያሳዩ አንዳን ድ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በአስተያየቶቹ ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን የት ላይ እንዳለ መገመት ይቻላል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው የብርሃን ጸጋዬ ጽሑፍ ደጀሰላም ፌስቡክ ላይ የወጣ ሲሆን ከዚህ ቀደም ያስነበብነው ቀጣይ ክፍል ነው::


ጠባቡ የማህበረ ቅዱሳን አስተሳሰቦች ( ክፍል ሁለት )


by Berhan Tsegaye on Wednesday, September 7, 2011 at 7:49am

የመንፈሳዊ አገልግሎት ዋናው አላማ ያመኑትን ማፅናት የራቁትን ማቅረብ ያላመኑትን ማሳመን ወንጌል ለዓለም ህዝብ ሁሉ ይዳረስ ዘንድ ነው፡፡ የምንሰራው ስራ ያመኑትን ለማፅናት ብቻ ከሆነ የጠፉትን የራሰቸው ጉዳይ እንደማለት ነው፡፡ ይህም መክሊትን እንደመቅበር ያህል ይቆጠራል፡፡ ገና ገና ብዙ ነገር መስራት ይጠበቅብናል፤ ማህበረ ቅዱሳን በየግዜው ህዝቡ እየተጋዘ መናፍቃን አዳራሽ እንደተጓዘ ይነግረናል እንጂ በምን አይነት አቀራረብ እንገድበው አይልም፤ ሁል ግዜሄዱ” ነው፡፡ የሚወሰድብን እንጂ የምናመጣው ሰው የለም!

እኛ እኮ ማህበሩን እንደቤተክርስቲያን እና እንደ ሐገርም አስፍተን ስናየው ቆይተናል፤ አሁን ግን በራሱ ግዜ እንደ ሰፈር እንድናየው ተገደናል፤ እኔ መናፍቅ እማውቀው መናፍቃን አዳራሽ የሄደ ብቻ አይደለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ እየኖሩ ለወንጌል አገልግሎት እንቅፋት የሆኑትን በሆነ ባልሆነው ምክንያት በተለያየ የራስ ጥቅም የሚረብሹትን ጭምር ነው፡፡ ማህበሩ አመታዊም ይሁን ወቅታዊ እቅድ ውጭ እግዚአብሔር ህዝቡን በቤቱ ለምን ሰበሰበው ብላችሁ ታውካላችሁ፤ የሚገርመኝ አንድን ነገር ለመከልከል ስትነሱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ማሳየት አለመቻላችሁ ነው፡፡

አትማሩ አትዘምሩ እሺ ምን እንዘምር  ... በቃ ዝም በሉ አይነት ነው፡፡ ሐሳቤን የማካፍላችሁ እናንተ ለአገልግሎቱ እውቅና እንድትሰጡ እና እንድትቀበሉት ሳይሆን ካለባችሁ ጥበት እንድትላቀቁ በማሰብ ነው፡፡ አገልግሎቱማ ይቀጥላል! እግዚአብሔርንስ ማን ሊገዳደረው ይችላል! በየዘመናቱ ታናናሾችን እያስነሳ ዘመኑን ይዋጃል፡፡ በእናንተ እኮ ጥበት መንፈሳዊ ኮሌጆች ባይኖሩ ትመርጣላችሁ፤ በዛ ውስጥም የሚማሩ ተማሪዎችንም በተሐድሶነት ትፈርጃላችሁ፤ መንፈሳዊ ማህበራትንማ ትንሽ ጠንከር ብለው ለመንቀሳቀስ ያሰቡትን በጀት መድባችሁ ስም እያጠፋችሁ አሳዳችሁ ትበትናላችሁ፡፡ ይባስ ብላችሁ በኣረብ ሀገራት የሚኖሩ ምዕመናንን ተረጋግተው በእምነታቸው እንዳይፅናኑ የእግዚአብሄርን ጉባኤ ለመበታተን ትጥራላችሁ!

ቴሌቪዠን ጣብያ ሲከፈት ለምን ተቀደምን እሪ ... ይጥፉልን ትላላችሁ፤ ቁም ነገሩ ምን ተላለፈበት ነው መሆን ያለበት? ወይስበስመ አብይሄስ ከባድ የቅናት ዛር ነው!!

ያልነበረንን ግንዛቤ ስለቤተክርስቲያን ለሁለት መከፈል ትሰብካላችሁ፤ ማን እንዳሰለጠናችሁ ምንስ እንዳቀዳችሁ አልገባኝም፡፡ አንድ ህንፃ ስትሰሩ ህንፃውን ይዛችሁ መገንጠል አምሮአችሁ ይሆን!! እንጃ ቤተክርስቲያን ግን በህንፃ ላይ ሳይሆን በደም ላይ የተመሰረተች ናትና ደሙን እዩት! ክርስቶስ በደሙ ቤተክርስቲያንን እንጂ ማህበራትን አልመሰረተም ማህበርን የተጣመሙ ሰዎች ሊያጣምሙት ይችላሉ፤ ንፁህ የሆነች ቤተክርስቲያናችን ላይ ግን ሐሳብ ለመሰንዘር የሚደፍርም የለም ሁል ግዜም ችግር ያለብን እኛ እንጅ ቤተክርስቲያን አይደለችም፡፡

አዎ ማህበሩ የሰራቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ሐገራዊ ስፋት የላቸውም ቤተክርስቲያን ብዙ ስራዎች ስላገዙኝ ብላ ብታጠፉም እንኳን የምትሰሩትን አንዳንድ መልካም ነገሮች በማሰብ ዝም ብላ ብታዝላችሁ በጣም አዘናግታችኋታል፡፡ ቤተክርስቲያን በራሷ መዋቅር ስር ብዙ ሐላፊነቶችን ይዛ ሰርታ ቢሆን ኖሮ ፅዋ ከመጠጣት ያለፈ ተሳትፎ ባልኖራችሁ ነበር፡፡ ማህበሩን የማይነካ ያስመሰለው የተሸከማችሁት ሸክም አለ ተብሎ ስለታሰበ ነው፡፡  ቤተክርስቲያን የራሷን የሽግግር ግዜ እስክታመቻች መኖራችሁ መልካም ነው፡፡ ሌሎች አገልጋዮች ነጋዴዎች ናቸው ትላላችሁ፤ እናንተ ያልሸጣችሁት ምን አለ!! ማህበሩ ውስጥ ያሉ ትልልቅ መምህራን እኮ መፅሐፍትንና ሲዲን እየሸጡ የሚተዳደሩ ብዙ ናቸው፡፡

ለምን ሸጡልንም አላልንም፤ አኛ የምናስበው የሰጡንን እውነት እንጂ ሃያ እና ሰላሳ ብሩን አይደለም፤ ምዕመኑም መንፈሳዊ ውነቶችን ለመግዛት ደከመኝ አላለም፤ እናንተም ምንም ነገር በነፃ ስታድሉ አላየንም፤ ህዝቡም የተሰጡት ስራዎች በሙሉ ስላፅናኑት ነው የተቀበላቸው፤ እናም ስታስቡ ከማህበሩ ህንፃ ፈቅ ብላችሁ አስቡ፡፡ ፈቅ ብላችሁ ስል ከህንጻው በቅርብ ርቀት ያለውን ምግብ ቤታችሁን ማለቴ አይደለም! በማህበሩ ምግብ ቤትም ገብተን የምንጠቀመው የምታዘጋጁት ምግብ ጣፍጦን ሳይሆን ማህበሩን የደገፍን መስሎን ነው፡፡ አንድም ሙዝ የተለወሰ ቅቤ አታበሉንም በሚል ነው!! ብዙውን ጥፋት ስታጠፉም ተሳስተው ያሳሳቷችሁ አሁን ባለው የአገልግሎት መስመር ውስጥ ካልተሳካላቸው በህዝብም ተቀባይነት ካጡ አገልጋዮች ጋር በመቀናጀት እንዲሁም በውጭ የሚኖሩ አንዳንድ የቅናት ዛር ያደረባቸው አገልጋዮችን ጨምሮ ቤተክርስቲያን ጠፋች ተወረረች እያላችሁ በውጭ የሚኖሩ ህዝበ ክርስቲያን እያደናገራችሁ ብዙዎችን መዘበራችሁ፡፡ እስከ መቼ ልባችሁን እንደ ፈርዖን እንዳደነደናችሁ እንደምትኖሩ አላውቅም ! እኔ ግን እላለሁ ግሩፕ ለፈጠረ ሐሳብ ሳይሆን ለህሊናችሁ ኑሩ፡፡ ከስጋዊ ሐሳብ ወጥታችሁ ለምትሰሩት ስራ እግዚአብሔርን በፀሎት የምትጠይቁበት ግዜ ይኑራችሁ፤ ከምንም ነገር የፀዳ የሕሊና መንፈሳዊ አይን አጥርቶ ያሳያልና በመሰለኝ መኖር አልሰለቻችሁም?  ሁል ግዜ የናንተ ሀሣብ ፍፁም እንደሆነ እያሰባችሁ ስንቱን ስትኮንነኑት ትኖራላችሁ!!!! እግዚአብሔር እናንተ ከምታስቡትም በላይ እውነት አለውና አፋችሁን የምትይዙበት ግዜ ሳይቀርብ አስተውሉ!!

“  አንዳንዶች ባልገባችሁ መጠን ልክ በግል ፌስቡክ ሜሴጅ በመፃፍ የምትሳደቡና የምታስፈራሩ ማህበርተኞች ሁላችሁ እኔ የምፈራው ሐጢያትን ሰርቼ እግዚአብሄርን ሳሳዝን ብቻ ነው፤ ስለዚህ አትድከሙ ያላችሁን ሀሳብ ግን ኮሜንት ማድረግ መብታችሁ ነው !!!! ”

8 comments:

 1. አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው
  በፍቅሩና በእውቀቱ ያፅናችሁ። ወንጌል የገባችሁ
  እውነተኞች በመሆናችሁ ዘወትር የምታስተላልፉትን
  ትክክለኛ መልእክት ሳልጎበኝ አድሬ አላውቅም።

  ነገር ግን አንዳንድ የማቅ አላማ አስፈፃሚዎች
  በሚሰጡት ሰይጣናዊ አስትያየት የተነሳ በፍፁም
  ተስፋ እንዳትቆርጡ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃችሁአለሁ።
  ዘወትር አድናቂያችሁና ስለዚች ቅድስት ክርስትናችን
  ከሚጋደሉት አንዱ ነኝ። ሌላም በጣም የበዙ ተከታዮች
  እንዳሉአችሁም ልገልፅላችሁ እወዳለሁ። ሰላም ሁኑ።

  ReplyDelete
 2. We will always be firm and have good standing about what we believe. Dear Berhan Tsegaye, you better watch your mouth. May GOD be with you, Amen. Allah yikiber.

  ReplyDelete
 3. sile Mahbere Kidusan hatiat abztachihu bechohachihu kutir mahiberun bizu eyastewawekachihut endehone endet aygebachihum. Yesew maninetu afu sikefet yitawokal alu.....

  ReplyDelete
 4. so, MK has been well known TO BE the antivirus of the diseases ( tehadiso/protestant-menafkans). what the protestant extremists/fundamentalist should know is that MK never retreats back and it will continue to be the HEADACHE of the church enemies. ETHIOPIA IS NOT SUITABLE FOR THE WESTERN EVIL ACTS.PERIOD.

  ReplyDelete
 5. the more u are against the church, the more MK is committed to defend the church from both internal and external enemies

  ReplyDelete
 6. Anonymous @October 10, 2011 3:39 AM

  It (MK) will continue to be the HEADACHE of the church. But the God of truth is with us.

  ReplyDelete
 7. አንድ እውነት አለ። እሱም እግዚአብሔር ሲፈቅድ ነፍሰጡር ሴት ጊዚዋን ጠብቃ እንደምትወልድ!! በቤተክርስቲንም አንድ እውነት አለ፤ እሱም ጊዜውን ጠብቆ የሚወለድ እውነት!!! ቤተክርስቲያን እስካሁን እውነትን ለመውለድ ምጥ ላይ ነበረች፤ አሁን የተሰወረባትን እውነት ልትወልድ እግዚአብሔር ጊዜውን ወስኗል። ያንን ምጥ ማኅበረ ቅዱሳን አያስቀረው፤ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ አያቆመው!! ያለምንም ጥርጥር ይወለዳል።
  እውነት የሚወለድ ስለመሆኑ ዛሬ ከዚያው ከቤቱ ሰዎች ምስክርነት እየተሰማ ነው።
  አንዱም እኔ ነኝ። እድሜዬን ሙሉ የተሰወረውን እውነት ለኔም ሆነ ላለነው ሁሉ እግዚአብሔር የገለጸው እውነቱ በእርግጥም እንደሚወለድ ማሳያ ነው። ቤተክርስቲያን ያሳለፈችውን መከራ በደስታ የምታይበት የእውነት ጊዜው በእርግጥም ይሆናል።
  ያንጊዜም እኛ «ኢትዘከሮ ለሕማማ ለእመ ወለደት ብእሴ ውስተ ዓለም» እንላታላን፤ እውነትን የተገላገለች ጊዜ።

  ReplyDelete
 8. betam be migerm huneta most the time ymetawerut sel mhaberu Mk cheger new ensu gen sirachwen yeseru new ""meqgna atstagn "" yekdusan tselot mingew zim belachu sirahun betseru enat eko sel ortodox tewhado yagbachum b/c menafq nachuna EGZBHIR AMELAK LEB YESTACHU degmo eymertachu post ymetdergu yeraschun becha new eski ewnat kalhu hulunm post adergun

  ReplyDelete