Wednesday, October 19, 2011

“ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት ዕዳ” በሚል ርእስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ፡፡ - - Read PDF

መምህር በቃሉ ታመነ በተባሉ አገልጋይ የተጻፈውና በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ላይ ተመሥርቶ የማኅበረ ቅዱሳንን ድብቅ ማንነት የሚገልጠው መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን የአባ ሰላማ ምንጮች ገለጡ፡፡

የመጽሐፉ የፊት ገጽ ጠንካራ መልእክቶችን በሚያስተላልፍ ሥዕል ያሸበረቀ ሲሆን (የመጽሐፉን ሽፋን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ)፣ የአንድ ሰው ጭንቅላት ተከፍቶ ከውስጡ ገንዘብ፣ ሥልጣነ መንግሥትና ሥልጣነ ፓትርያርክ አመልካች ትእምርቶች ይታያሉ፣ በእጁ ደግሞ መቅረፀ ድምፅ (ዎክማን ቴፕ) እና ካሴት ይዟል፡፡ ተጠፍሮ የታሰረ ወንጌልም ከኋላው ይታያል፡፡ ይህ ሰው በመንበረ ፓትርያርክ ሕንፃ ላይ ተረፍቆና ለሕንፃው ከብዶት የሕንፃው ቅርጽ ተጣሟል፡፡ ጸሓፊው ሥዕሉ ራሱ ይናገር ብለው ነው መሰል ማብራሪያ አልሰጡበትም፡፡ በርግጥም ሥዕሉ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አፍ አውጥቶ ይናገራል!! በመጽሐፉ ውስጥ የተገለጸውን የማኅበሩን ማንነትም በሚገባ ይገልጣል፡፡ “ከሺህ ቃላት አንድ ሥዕል” ይባል የለ!
           
በመጽሐፉ መክፈቻ ላይ እንደ ተገለጸው አዘጋጁ በዚህ መልክ ያቀረቡት መጽሐፍ ከዚህ ቀደም ነጋድራስ በተባለው የግል ጋዜጣ ላይ በተለያዩና ወቅታዊ በሆኑ ርእሰ ጉዳዮች የጻፏቸው ሲሆኑ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይም በተከታታይ መውጣታቸውን ይጠቅሳል፡፡ በመጽሐፍ መልክ ሲቀርቡም በአዳዲስ መረጃዎች በልጽገውና ዳብረው እንደ ወጡ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ከፕሮቴስታንት መጻሕፍት እየወሰዱ ነው የሚሰብኩት፣ የሚጽፉት እያለ ሲከሳቸው የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትም ከፕሮቴስታንት መጻሕፍትና ጋዜጦች እየወሰዱ በሚያሳፍር ሁኔታ የራሳቸው ድርሰት አስመስለው መጽሐፍ እስከ ማውጣት መድረሳቸውን መጽሐፉ ያጋልጣል፡፡ የማኅበሩ አባልና የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ሪፖርተር የሆነው ዲያቆን ኅሩይ ባየ፣ “የተለወጠ ሕይወት” በሚለው “መጽሐፉ” ከዶ/ር መለሰ ወጉ የሕይወት መስታወት ጋዜጣ ላይ ርእስ ሳይቀር ቃል በቃል ገልብጦና አንዳንድ የቃላት ለውጥ አድርጎ እንደ ራሱ መጽሐፍ ማሳተሙ በሥነ ጽሑፍ ላይ የተፈጸመ ስርቆት ነው ሲል መጽሐፉ ያትታል፡፡

“ዳንኤል ሌላ ያረጋገጠልን እውነት ማኅበረ ቅዱሳን የስለላ ክፍል ያለው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ክፍል ለአመራሩ በቂ መረጃ ለመስጠት በሚል “የመረጃ ክፍል” ተብሎ እንደ ተቋቋመ ጠቁሟል፡፡ ነገር ግን “የፕሮቴስታንት ኅትመቶችን ከመግዛት ባለፈ መሥራት አልቻለም፡፡ እንዲያውም ሥራውን ትቶ የገዛ አባላቱን እስከ መሰለል ነው የደረሰው፡፡ ወሬና መረጃ መለየት የተሳነው ክፍል ነው፡፡” ሲልም እየሠራ ያለውን ሥራ ፀሓይ ላይ አስጥቶታል፡፡ ይገርማል! ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንዶቹን የቤተ ክርስቲያን ልጆች የወነጀለበት ክስ የፕሮቴስታንቶችን ኅትመቶች ያነባሉ፤ ከዚያ እየጠቀሱ ይሰብካሉ፤ ይጽፋሉ የሚል ነበር፡፡ ራሱ ግን ለክፉም፣ ለደጉም የፕሮቴስታንት ኅትመቶችን የሚከታተልበት ክፍል አደራጅቷል፡፡ ብዙ ጊዜም የእነርሱን ደካማ ጎን ለመተቸት ሲጠቀምባቸው ኖሯል፡፡

“ዐልፎ ዐልፎ ግን አንዳንድ አባላቱ ከፕሮቴስታንት ጽሑፎች ላይ ቃል በቃል እየገለበጡ ምንጭ ሳይጠቅሱ የራሳቸው ጽሑፍ አስመስለው የሚያሳትሙበት አጋጣሚ አለ፡፡ ለምሳሌ፡- በአሁኑ ጊዜ በስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ሪፖርተር ሆኖ የሚሠራው ዲያቆን ኅሩይ ባየ በ2000 ዓ.ም. ባሳተመውና “የተለወጠ ሕይወት” በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ሳምራዊቷ ሴት ያሰፈረው፣ በአብዛኛው ከመለሰ ወጉ “የሕይወት መስታወት” ጋዜጣ ቁጥር 89 ላይ የተወሰደ ነው፡፡ አንዳንዱ ቃል በቃል፣ ሌላው ደግሞ ጥቂት የቃላት ለውጥ ተደርጎባቸው ርእሱ ጭምር ከዚያ የተወሰደ እንደ ሆነ ሁለቱን በማነጻጸር መለየት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- “ያቺ ሳምራዊት፥ የተጨመላለቀ ታሪክ ያላት ሴት መሆኗን ለመሆኑ ኢየሱስ ያውቅ ነበር እንዴ? የሚያውቅ ከሆነ እንዴት ከእንደዚች ዐይነቷ ሴት ጋር ይነጋገራል? ብለን መጠየቃችን አይቀርም፡፡ ከኀጢአተኞች ጋር መዋሉ፣ ከኀጢአተኞች ጋር መብላቱ፣ ኅብረተሰቡ ካልተቀበላቸው ሰዎች ጋር ኅብረት መፍጠሩ እኛን ብቻ ሳይሆን ጥንትም ቢሆን ብዙዎችን ያስደነቀ ነው፡፡” (የሕይወት መስታወት Sep./Oct. 2001, 2)፡፡

“እንዲህ ዐይነት የተጨማለቀ ታሪክ ከነበራት ሴት ጋር ጌታችን ምን አጋጠመው? ለምን ጊዜ ሰጥቶ ሊያወያያት ፈለገ? እንዴትስ አነጋገራት? ብለን እንጠይቅ ይሆናል፡፡ ከኀጢአተኞች ጋር መዋሉ፣ መብላቱ፣ ኅብረተሰቡ ካገለላቸውና ከናቃቸው ሰዎች ጋር ኅብረት መፍጠሩ ብዙዎችን ያስደነቀ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡” (ኅሩይ 2000፣ 24)፡፡

“መቼም አንድ ጸሓፊ ከሌላው ሰው ጽሑፍ ላይ መጥቀሱ ያለ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ሲጠቅስ በቀጥታ የወሰደውን ጥቅስ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ የማስቀመጥና ምንጩንም በተገቢው መንገድ የመጥቀስ ግዴታ አለበት፡፡ በጭምቅ ሐሳብ /Paraphrase/ ዘዴ ከጠቀሰም ምንጩን ሊጠቅስ ይገባል፡፡ አሊያ በሕገ ሥነጽሑፍ ስርቆት /Plagiarism/ ይሆናል፡፡ በሰው ወርቅ ለመድመቅ መሞከርም ነው፡፡ በኮፒራይት መብትም ሊያስጠይቅ ይችላል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ሪፖርተር ‘ለምጽፈው ጽሑፍ ጥሩ ምንጭ ነው’ ብሎ ካመነና ተገቢ ሆኖ ካገኘው የመለሰ ወጉን ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ መገልበጥ ሳይሆን ለሚጽፈው ጉዳይ አስፈላጊ የሆነውን ብቻ መጥቀሱ ተገቢ ነው፤ ስሕተቱ ምንጩን አለመጥቀሱና ጽሑፉ የራሱ ሆኖ እንዲቆጠርለት መፈለጉ ነው፡፡ ይህም ምናልባት ከፕሮቴስታንት መጻሕፍት ውስጥ ጠቅሶ በጎ ትምህርት ማስተላለፍ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ዘንድ እንደ ምንፍቅና ስለሚቆጠር ከዚያ ለማምለጥ አስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንዳንዶችን በዚህ ጉዳይ ሲከሳቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር ላይ ግን ያለው ነገር ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም፤ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በመናፍቅነትና በተሐድሶነት ይጠርጠርልናማi” (ገጽ 54-55)
  
መጽሐፉ ቀደም ብለው ተሐድሶ የሚለውን ቃል ከማንም በላይ ሲጠቀሙበትና ሲያንቆለጳጵሱት የነበሩትንና አሁን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ወግነው ተሐድሶን አጥፊ አድርገው በቅኔ ያወረፉትን መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒንም “ከቤተ ክርስቲያን እየጎረሱ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን መዋጥ ተጀመረ ወይ?” በማለት ከዚህ ቀደም በሌሎች ላይ በተናገሩት ቃላቸው ያጠምዳቸዋል፡፡

“የዜና ቤተ ክርስቲያን ዋና አዘጋጅ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዘንድሮው የዘመን መለወጫ ዕለት ቅዱስ ፓትርያርኩን እንኳን አደረስዎ ለማለት በተዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ያቀረቡትና በደጀሰላም ድረገጽ ላይ “የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ አደጋ በቅኔም ሲጋለጥ” ተብሎ የተራገበለት ጉባኤ ቃና አተዛዛቢ ሆኗል፡፡ ቅኔው እንዲህ ይላል፤“ዘንስር ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ዕቀባ
           ለኦርቶዶክሳዊት ቅድስት እስመ ተሐድሶ ከበባ፡፡” (በንስር የምትመሰል ዮሐንስ ሆይ! ኢትዮጵያን ጠብቃት፤ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ተሐድሶ ከቧታልና፡፡) (Deje Selam September 27, 2011 at 8:28pm). ከላይ ለማሳየት እንደ ተሞከረው፣ እኒህ ሰው በ1970ዎቹ መጀመሪያ ዋና አዘጋጅ በሆኑበት በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ስለ ተሐድሶ አስፈላጊነት፣ በርእሰ አንቀጽ ደረጃ የተጻፉ መልእክቶችን አንብበናል፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ አንዳንድ የተሐድሶ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸው ባይካድም የሚፈለገውን ያህል ተሐድሶ እንዳልመጣ ግን በግልጽ ተጽፏል፡፡ ዛሬ ታዲያ ምን ተገኝቶ ይሆን ተሐድሶን በአሉታዊ መንገድ መግለጽ ያስፈለገው? ከዚህ ቀደም ጋዜጣው ማኅበረ ቅዱሳንን ተቃውሞ በጻፈው ጽሑፍ ውስጥ እንደ ተገለጸው፣ ከቤተ ክርስቲያን ጎርሶ ወደ ማኅበረ ቅዱሳን መዋጥ ተጀምሮ ይሆን ወይ? (ዜና ቤተክርስቲያን 1996፣ 7)፡፡” (ገጽ 35)

መጽሐፉ 72 ገጾች ያሉት ሲሆን በሦስት ምዕራፎች የተከፈለና ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥፋት በተጨባጭ መረጃና አመክንዮ የሚያጋልጥ ነው፡፡ በመዝጊያው ላይም የመፍትሔ ሐሳቦችን ያቀርባል፡፡

መጽሐፉ እስካሁን አዲስ አበባ 4 ኪሎ በሚገኘው ዩኒቨርሳል መጻሕፍት መደብር እየተሸጠ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡  

የመጽሐፉን የፊት እና የሁዋላ ሽፋን በሚቀጥለው ገጽ ይመልከቱ

35 comments:

 1. ማኅበረ ቅዱሳን በደመነፍስ ተኩስ ጥይት እየጨረሰ ነው


  በአፀደ ነፍስ ያሉ አባቶች ጭምር ይወገዙልኝ ሲል አመለከተ  የውግዘቱ ሃሣብ እነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝንም ያካትታል  ክሱ የቀድሞውን ፕሬዚደንት መንግሥቱ ኃ/ማርያምን አለማካተቱ አስቆጭቷል

  ራሱን የቤተክርስቲያንና የሃይማኖት የበላይ ጠባቂ አድርጎ የሰየመው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የውር ድንብሩን በመወራጨት ላይ መሆኑን ድርጊቱን ያስተዋለ ሰው ይረዳል፡፡ ለዓመታት ሲሳደብ፣ ሲራገምና ወንድሞችን ሲከስና ሲያሳድድ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን "እኔ እኮ ያለመረጃ ሰውን አልከስም" በሚል ስሜት ለጠቅላይ ቤተክህነት የክስ ፋይል ማስገባቱን ከራሱ እና ከሌሎች አካላት ያገኘናቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ይህ በማኅበረ ቅዱሳን እና በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አመራር ተብዬዎች ስም የገባው የክስ መዝገብ በርካታ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን፣ የተከበሩ አባቶችንና ታዋቂ ምሁራንን ያካትታል፡፡  ከውጊያ እንደሚሸሽ የጦር ሠራዊት የኋልዮሽ ጥይቱን በጭፍን በማርከፍከፍ ላይ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን "ያገኘውን ያግኝ" በሚል ስሜት በክሱ ውስጥ አሰስ ገሰሱንም በማካተት የበርካታ ሰዎችን ስም ጠቅሷል፡፡ ስማቸው ከተካተቱት ሰዎች ውስጥ፣ በሕይወት የሌሉና ከሞቱ ብዙ ዓመታት ያስቆጠሩ ምሁራን ይገኙበታል፡፡ ክእነዚህም መካከል፣ ታዋቂው ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ ከንቲባ ገብሩ ደስታ፣ ይጠቀሳሉ፡፡ በሕይወት ካሉት፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምም አልቀረላቸውም፡፡  ከቤተክርስቲያን ሊቃውንት መካከል በሕይወት የሌሉት አለቃ ዐጽመ ጊዮርጊስ፣ አለቃ መሠረት ስብሐት ለአብ፣ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ፣ የሚገኙበት ሲሆን በሕይወት ካሉት መካከል፣ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፣ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፣ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ ተካተዋል፡፡  እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አንድ ካህን፣ አገልጋይ ወይም ምዕመን የአስተምህሮ ወይም የአምልኮ ህጸጽ ሲገኝበት በመጀመሪያ ይመከራል፡፡ በሚሰጠው ምክር አልመለስም ካለ እና በአቋሙ ከጸና በሊቃውንት ጉባዔ አቅራቢነት በቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘት ይለያል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ከሞተ በኋላ የሚመከርበት ወይም ከስህተቱ የሚመለስበት ዕድል ስለሌለ፣ ጥፋቱን ሳያምን በደፈናው አይወገዝም፡፡ ሟች ከሞተ በኋላ አይወቀስም፡፡ ግዝት እንኳን ቢኖርበት ከሞተ በኋላ ከግዝቱ የተፈታ ነው፡፡ አጅሬ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ለዚህ አዲስ ሥርዓት ሠርቶ፣ ከሞቱ በርካታ ዓመታትን ያሳለፉ ሊቃውንት አባቶችን ይወገዙልኝ በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ እያለ መሆኑ ብዙዎቹን አስገርሟል፡፡  ይህንን የማኅበረ ቅዱሳን ጉድ የሰሙ ምዕመናን፣ በዚህ አካሄድ ከማኅበረ ቅዱሳን ውጪ ያለው ወገን ሲወገዝ መንግሥተ ሰማያት ለማቅ አባላት ብቻ ልትሆን ተወስኗል ማለት ነው፤ በማለት የተሳለቁ ሲሆን፣ ከነካካ ላይቀር የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያምንም ማስወገዝ ነበረበት ብለዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያብራሩ፣ ጓድ መንግሥቱ የተዋህዶ ልጅ ሆነው ሳለ የእግዚአብሔርን መኖር በመካድ የነባራዊ ዕውነታ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ የነበሩ በመሆናቸው ነው ብለዋል፡፡ ውግዘቱ በእርሳቸው ብቻ ሳያበቃ ጠቅላላ ወደ ሶሻሊስት አስተሳሰብ የፈረጠጠና ሃይማኖቱን የከዳ ሁሉ የኢትዮጰያ መሬትም ላይበቃው ነው ብለዋል፡፡ ውግዘቱ በዚህ ብቻ ማብቃት የለበትም ያሉ ታዛቢዎች፣ በጣሊያን ጊዜ ሀገራቸውንና ሃይማኖታቸውን ከድተው ለጠላት ያደሩ ባንዳዎችን ጨምሮ፣ ከዓፄ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ትንፍሽ ያሉ የ1700 ዓመታት ትውልዶች ሁሉ አጽማቸው ከተቀበረበት ተነስቶ ወደ ሌላ አካባቢ ዞር ሊሉ ይገባል ሲሉም ለማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን አድናቆት እግረ መንገዳቸውን ጠቁመዋል፡፡

  ReplyDelete
 2. Please upload the book in your blog, for us who live in abroad.
  thanks,

  ReplyDelete
 3. hhahhhahhahha, please give one copy to 'aba' sereke, one copy to 'abune' paulos, still one copy to 'abune' fanuel. by the way read a book entitled to 'hamere tewahido' which says much to know what you are ( faresawi -tehadiso -menafkan), i bought it recently and hugely appreciated MK, LONG LIVE MK FOR ITS EFFORT TO ACKNOWLEDGE US WHO THE TEHADISO ARE, WHAT THEIR TRUE OBJECTIVES ARE. I hope mk has distributed it to all 47 bishops except those 3 which i described above and who needs rather the accusations of MK FROM TEHADISO GROUP.

  ReplyDelete
 4. gezahut. really nice book.

  ReplyDelete
 5. DON'T CHEAT US THIS EVIL MADE BOOK IS PREPARED BY ASEGED SAHILU AND SERKE 'LEBAW', IN WHICH CASE THEY CAN GET THEIR SALARY. MK WILL BRING THEM IN TO COURT.

  ReplyDelete
 6. ጎበዝ ማሕበረ ቅዱሳን እኮ አንድ ተራ የቤተክርስቲያናችን ቴረሪስት ነው።
  ምንም ሥልጣንና እውቀት በቤተክርስቲያን ላይ የለውም። ሁልጊዜ ሽብር
  በክርስቲያኖች ላይ ከመንዛት በቀር ሌላ ነገር የማያውቅ ቢከፍቱት ተልባ ነው።
  ወገኖቼ እግዚአብሔር እውነቱን ቶሎ ይግለፅላችሁና ማን የቤተክርስቲያን ጠላት
  እንደሆነ አይናችሁን ከፍቶ ያሳያችሁ። እንደው በነጠላ ተሸፋፍኖ ሐይማኖተኛ
  መስሎአችሁ እንደሆነ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ከቀደመው
  ጠላታችን ዲያቢሎስ ጋር በመተባበር የእርስ በርስ ፍቀር እንዲጠፋና ክርስቲያኖች
  እንዲከፋፈሉ የሚያደርግና በኦርቶዶክስ ካባ ስውር ደባ የሚያደርግ ነው። ነገር ግን
  ቤተክርስቲያን አምላካችን በደሙ የመሰረታት በመሆኑ ማንም ሊበጣጥሳት አይችልም።

  ውሃ ከላይ ወደ ታች ይወርዳል እንጂ ፤ ከታች ወደ ላይ ይፈሳል||\ እንጭጩ እራሱን
  ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የሽብር ማህበር ብሎ ብሎ ደግሞ ከሊቃውንት የሐይማኖት
  አባቶቻችንና ከእግዚአብሔር በላይ እራሱን አድርጎ በመቁጠር ትንሽ አፉን እንኩአን ሳይከብደው
  መናፍቅ ተሀድሶና ሌላም ሌላም ሥም በመስጠት ለማን ሊከስ እንደሆነ እንዲሁ ሲንጠራራና ከመንደር
  መንደር እየተሽሎከለከ መርዙን ሲረጭ ይውላል። አይ ማቅ\\\ እግዚአብሄር እኮ የኃያላን ኃያል ነው።

  አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተባረክ ወዳጄ!

   Delete
  2. sema anete raseh ye betekeresetiyan ena ye Iyesus telat eshoh enedehonek atawekem ende yabatehen ye diyabelosen tegebar bemafaten lay yaleh yediyabelos lije enedehonek atakem lemin rasehen lemedebek mokerek metsehaf enedalew leba selehonek new mahebere kedusanen yemetesadebew yetehadeso kenedu selehonek new yesedeb afe yetesetew yetenete telatachin lij selehonek new.kkkkkkkkkkkkkkkkkk

   Delete
 7. what did u say you kid? Asseged sahilu? please try ur best i know mk not only want him to be in court but you want to kill him. but his fate is not in your hand it is in lords hand. የጅል ሣቅ ጥርሱ እስኪረግፍ ነው አሉ፡፡ ማፈሪያዎች

  ReplyDelete
 8. መጽሀፉ ዩንቨርሳል ብቻ ሣይሆን ቦሌ ብራስ ፊትለፊት ባለ መጽሀፍ ቤት ውስጥም ይገኛል፡

  ReplyDelete
 9. whatever you had write you are false.you are not a human I think so.we are go with Mk,b/c God is with us.you are going to jail.you will see it later.
  ye mtichebitutin ye mitiyzut atachu aydel.Endabede wusha yanenim yanenim menakes jemerachihu.Enanten billo tehadiso-menafik.koyitachihu ersibersachu tinakesalachihu.
  diros keseyitan tebina kirikir engi min yigegnal.Benant bet Mk mawaredachihu new.lemonu maseb akomachu.yemianbewu sew killi adrgachu koterachihut.

  ReplyDelete
 10. ክንፈ ቅዱሳንOctober 20, 2011 at 2:23 PM

  ኣባቶች ሚስማር ሲመቱት ይጠብቃል ይላሉ። የሃሰት ክምር ኣንዲት ቅንጣት እውነት ልትሆን ኣትችልም። ማህበሩን ከኣባቶች ጋር ለማጋጨት ከሆነ ይህ ሁሉ ድካም አና ቁፋሮ ሁሉም እውነታውን ሲያውቁ ሊተርፋችሁ የሚችለው እርግማን ብቻ ነው። ማህበሩን ከሌላው ለየት የሚያደርገው ምን መሰላችሁ,አናንተ የቤተ-ክርስቲያን ጠላት ብቻ ኣይደላችሁም የባህላችን፣የማንነታችን፣ጭምር ጠላቶቻችን ናችሁ። ኣለቆቻችሁ እዚህ ኣሜሪካና ኬንያ ቁጭ ብልው በሚያፈሱልህ እርጥባን ሃገር የምታፈርስ መስሎህ ከሆነ ተጃጅለሃል።ጅል። ታድያ ይህ ማህበር የመንግስትንም ስራ ጭምር አይሰራ ነው ሃገርን ከመክላከል ኣኩያ ምለቴ ነው።መንግስት ብዙ ስራ ስላለበት ይህ ላይታየው ይችላል። ኣንድ ቀን ግን ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ።ይህች ሃይማኖት ለኢትዮጵያ አና ለኢትዮፕያውያን ምን ማለት እንደሆነች በሚገባ እንደምታውቁት በማመን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ! ይህች አንተ የምትላትማ አገራችንን ለዘመናት ያቆረቆዘችና ያኀኸየች የተረት ቤት አንደሆነች ብቻ ነው!

   Delete
  2. ወዳጄ! ይህች አንተ የምትላትማ አገራችንን ለዘመናት ያቆረቆዘችና ያደኸየች የተረት ቤት አንደሆነች ብቻ ነው!

   Delete
  3. ውድ ወዳጄ! ይህች አንተ የምትላትማ አገራችንን ለዘመናት ያቆረቆዘችና ያደኸየች የተረት ቤት አንደሆነች ነው የገባን! ሥልጣኔን እንደ ሃጢአት እየተሰበክን አደግን፣ሥራ እንዳንሰራ የኛው ሆዳም ሰዎች በግብፃዊያን ጥቂት ገንዘብ ሆዳቸውን ለመሙላት ሲሉ ዓመቱን ሙሉ በዓልን እንድናከብር ሲወስኑብን “የእግ/ር ሰዎች” ናቸው ብለን “አሜን” ብለን ተቀበልን ይኸውም ዘመናችንን ሁሉ ችጋር ሞላው፤ የጽድቅ መጨረሻው መመነን እንደሆነ እየተነገረን ኖርን!ታዲያ የቱ ጋ ነው አንተ የታየህ ባለውለታነቷ?

   Delete
 11. eh? what significance would it have on the famous MK? NOTHING! because the book is
  initiated by aseged sahlu
  produced by tamene
  edited by begashaw
  sponserd by muluwongel/other protestant menafikan organization
  approved by sereke
  aurhorized by poulos
  all of which do not represent the orthodox church, so this is the voice of the wolfs which can't have a single impact on MK.

  ReplyDelete
 12. ወደዳችሁም ጠላችሁም ኢስላማዊው ወሃቢያ ከድርጅታዊ እንቅስቃሴው እንደታገደ ይህ ክርስቲያን መሰሉ ወሃቢያ ማኅበረ ቅዱሳንም በቅርቡ በመንግሥት ይታገዳል። እስከአሁንም እድሜ ሊያገኝ የቻለው በያዛቸው የመንግስት ባለስልጣናት አባሎቹ አማካይነት በአማላጅና መንገዴን አስተካክላለሁ እድል ይሰጠኝ ብሎ እንደሆነ የደረሱን ምንጮች ያረጋግጣሉ። አሁን እኔ የለሁበትም አርፌ ተቀምጫለሁ በማለት ሰንበት ት/ቤት በሚባለው ሌላኛው እጁና ውጭ ሀገር በሚገኙ ሃይማኖታዊ መሰል ፖለቲከኞቹ እንዲሁም ዘመድኩንና አንዳንድ ግለሰቦች በኩል የሲኖዶሱ ጉባዔ አቅጣጫ እንዲሄድ የክስ፤የቪዲዮ፤ የገንዘብ ስጦታና አፉን ለደጋፊ ጳጳሳቹ በማከራየት ተጠምዷል። ይሁን እንጂ መንግሥት የዚህን ማኅበር የብዙ ጊዜ እንቅስቃሴና መሻሻል የሌለውን መሰሪ ስራ መታገስ ባለመቻሉ እንዲሁም የዓረቡን አመጽ በመስጋትና መጪውን ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ ይህንን ማኅበር እንደወሃቢያ ለመዝጋት በእርግጥም ቀኑ ቀርቧል።

  ReplyDelete
 13. why you fear mk and go to blacking his name? i think the association is working the truth.

  ReplyDelete
 14. we are living in U.S.A WE ARE STRUGGLING WITH MK, we almost conquer them in the church . guys be strong mk is alaways complaining and accusing people . Guys we need the NEW Book how can we get ? send to us we will buy it and distribute too .In america most of the people 90% know about mk is out Gospel AND SPRITUAL TERRIORIST , thanks to God SOME OF THEIR FOLLOWERS ARE START TO ADMIT THEIR FAULT AND START PARTICIPATE IN BIBLE STUDY WITH US BUT FEW ARE FOLLOWING AS LIKE FBI, CIA BUT WE ARE LOOKING THEM BROTHERLY ONE DAY IF THEY UNDERSTAND THEY KNOW OUR LORD JESUS CHRIST.
  SO GUYS , PRAY TO THEM , GIVE COMMENT TO THEM AND CRITICIZE TOO. DO NOT AFRAID THEM

  ReplyDelete
 15. @Anonymous said...
  October 20, 2011 11:49 PM
  Do you know what ወሃቢያ is? Its a sect of Muslim want to do the same like you Menafeqan Tehadeso.they even say to reform ancient Muslim faith like you doing in our church. Both of you don't appreciate and tolerate living with other religion.they advocate extremism in the name of Allah. you in other side did the same thing they do.
  MK advocate living with Muslims like we did for years. you accuse them of this to not too long ago. 'they prefer Muslim than you' remember? (when i say you it mean you or your faith followers Tehadeso and Pente)
  so beat it man. you are the one who are extreme like whabi not MK. who lie and advocate extremism in the name of Jesus. we want our old (yarejeche, yaltadesheche) church and our different Muslim brothers (not Wuhabi) rather than lier and deceitful Pente Tehadeso. Got It?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ewur neh wedaje! Girdosh be girdosh yetetebetebebeh!!!!! Anten bilo christian!!!!!!!!!1

   Delete
 16. priest abebaw or paster abebaw? are you telling us your menafican adarash or tewahdo cherch. conquering mk will remain as your dream. do not kid us

  ReplyDelete
 17. what significance would it have on the famous MK? NOTHING! because the book is
  initiated by aseged sahlu
  produced by tamene
  edited by begashaw
  sponserd by protestant menafikan organization
  approved by sereke
  aurhorized by poulos
  all of which do not represent the orthodox church, so this is the voice of the wolfs which can't have a single impact on MK.

  ReplyDelete
 18. Yih web site ye kidit betekirstian lijoch yalihonu tekulawoch amid mehonun ye yazachew melikitat yasiredalu:: Ye kidusan amlak tebilo yitera zenid kidusanun yakebere Amlak libona yiestachihu:: Betekirstian gin bekirstos dem yetemeseretech natina lezelealem tinoralech!!!

  ReplyDelete
 19. You token wolfs, you never ever be a fraction of Mahibere Kidusan! Mahibere Kidusan has done tremendous job to our Holly Church and at least it save from the wolfs of your kind!

  ReplyDelete
 20. It is right time to fight against mk. God is working. why don't we open our eyes and see God's miracles? please be patient! Egziabher lqdusanu yibeqelalna zim belu.

  ReplyDelete
 21. zendro yetecegerenw be Geéz tenagari protestantoch new, be sende wusedu, getan tekebelu yeminawkew yetekawawi derejit(haymanot?)...aye ye kinochu abatochachin erest anesetim, It is historical mistake for the youth of our generation not to be member of MK

  ReplyDelete
 22. abet mahebere kedusan gen men hunew new tekit gyze enem abere sereche neber abet tenkolachwu "geta hoy yemiaderguten ayawukumena yeker belachwu.

  ReplyDelete
 23. WHATEVER YOU WRITE ABOUT MK, IT IS NOT SURPRISING THAT YOU WRITE BAD THINGS. DO YOU THINK THAT WE EXPECT GOOD THINGS FROM YOU? HOW COULD WE EXPECT THAT? MK AND YOU ARE AT THE TWO SIDESDS OF LORD JESUS CHRIST, ONE AT THE RIGHT THE OTHER AT THE LEFT RESPECTIVELY. YOU THINK AS THE WESTERN PROTESTANTS AND BREATH THEIR CARBONDIOXIDE HOWEVER MK THINKS BY THE KNOWLEDGE HIVEN TO HIM BY OUR LORD JESUS CHRIST AND BREATHS THE LIFE GIVING OXYGEN WHICH IS NOT THE WEST PRODUCT AS CARBONDIOXIDE. SO RETURN TO THE TRUTH AND BE MEMBERS OF THE SOULS WHO ARE CALLED TO STAND AT THE RIRHT OF JESUS CHRIST AT THE LAST DAY OF JUDGEMENT.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወየው ላንቺ ያኔ!

   Delete
 24. I wish someone can tell me what is MK

  ReplyDelete
 25. Dear friend Meme,what do you mean breath wester's carbondioxide? do you think you and MK only know Jesus Christ? what even makes you think to generalized all western protestants are breath carbondioxide? All what I know is Jesus Christ is love. And love one another do you beleive that? if you beleive love one another you are the real Christ follower otherwise please do not clame MK and your self Christian. Thank you God bless you.

  ReplyDelete
 26. ከአጋንንት ምንም አይጠበቅም
  ማህረቅዱሳን ለዘልአለም ይኑር።

  ReplyDelete
 27. DON`T TALK THAT MUCH PRAY

  TO YOUR GOD IT IS EASY FOR HIM

  ReplyDelete
 28. እኔ እስኪገባኝ ድረስ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሁሉ ክርስቶስን እናመልካለን ያላሉ፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ትሁትና ፍቅር ነው፡፡ እርሱ ሰዎች እንዲከባበሩም ይሰብካል፡፡ ይገርማል ምድር ላይግን ይክን የሚያደርግ ክርስቲያን ጠፍቷል፡፡ ከሚፃፉ ፅሁፈች እና አስተያየቶች ይህን መገንዘብ ይቻላል፡፡ እንዴዬ እናስተውል የሰዎችን ሀይማኖት በመንቀፍ፣ በመዝለፍ እና በመሰዳደብ ክርስቶስን እያስከፋን እንጂ እያስደሰትነው አይደለም፡፡ ይልቁንም የመጠላላት፣የመነቃቀፍ እና እርስበእርስ ያለመከባበር አባት የሆነውን ሰይጣን እያስደሰትነው ነው፡፡ እኔ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምሮ ስላሳመነኝ እና ወደ ክርስቶስ ስላቀረበኝ ተመችቶኛል፡፡ ሌሎች የእኔን እምነት በማንቋሸሻቸው ክርቶስስን ያስደስቱታልን? እኔ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዳችን ምን ያህል የጽድቅ ስራን እየሰራን እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተን ማየት ያለብን ይመስለኛል፡፡ የሌሌችን ጉድፍ ለማየት ስንጣደፍ የእኛን ማን ያይልናልና፡፡

  ReplyDelete