Monday, October 31, 2011

የ"ሲኖዶስ" የተባለውና ማኅበረ ቅዱሳን በሚፈልገው መንገድ ቀርጾ ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ ያስወሰነው ውሳኔ ተቃውሞ እየገጠመውና ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ መከፋፈል እንዳያመራ እያሰጋ መሆኑ በመገለጽ ላይ ነው፡፡ - - - READ PDF

በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው እየተባለ ሲነገርለት የኖረውና የቀደሙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም የሚሰጥና እግዚአብሔርን የሚያስከብር ውሳኔ ሲወስኑበት የቆዩት የጳጳሳት ጉባኤ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 2004 ዓ.ም. ስብሰባው በታሪክ ተጠያቂ የሚያደርገውንና ቤተ ክርስቲያንን ወደ መከፋፈል ሊመራ የሚችል አሰፋሪ ውሳኔ መወሰኑ ብዙዎችን እያሳዘነና እያስቆጣ መምጣቱን ከየስፍራው የደረሱን ዘገባዎች ያመለክታሉ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ ያለ አድልዎ በትክክለኛው መንገድ የመምራትና የማስተዳደር ኀላፊነት ቢኖርበትም፣ አሁን ያሉት ብዙዎቹ ጳጳሳት ይህን ሁሉን በእኩል አይን ተመልክቶ ትክክለኛ ፍትሕ የመስጠት ግዴታቸውን ባለመወጣትና በገንዘብ ተደልለው እውነትን መሸጣቸው ቤተ ክርስቲያኗን ትልቅ ኪሳራ ላይ የሚጥላትና እነርሱንም በታሪክም ተወቃሽ የሚያደርጋቸው መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ሲኖዶሱ ራሱ ያወጣውን መመሪያና ደንብ ራሱ እየጣሰ ይገኛል፡፡ ራሱ ያቋቋመውን የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያም እምነት አጥቼበታለሁ ብሎ ለጥቅም ባደሩ ጳጳሳት የድምፅ ብልጫ ተጨማሪ ጳጳሳትን አጣሪ አድርጎ መሠየሙ፣ ብቃታቸው ተመዝኖ በሊቃውንት ጉባኤ ውስጥ እንዲሠሩ የተመደቡ ተጠያቂ ሊቃውንትን “የተሐድሶ አባላት ናቸው” በማለት የመፈረጁ ዳር ዳርታም ከማኅበረ ቅዱሳን ውጪ ሁሉም መናፍቅ ነው በሚለው የማኅበረ ቅዱሳን ዶግማ በገንዘብ የተገዙት ጳጳሳት ሁሉ ማመናቸውንና መጠመቃቸውን በግልጽ ያመለከተ ተግባር ነው፡፡ እነዚህ ገንዘብ የደለላቸው "ኪራይ ሰብሳቢ" ጳጳሳት ቤተ ክርስቲያኒቱ በሊቃውንቷ ትምህርት ሳይሆን ሳይማር ሁሉን ዐውቃለሁ በሚለው በማኅበረ ቅዱሳን ፍላጎት ብቻ እንድትመራ ፈርደዉባታል፡፡

ሲኖዶሱ በዚህ ስብሰባ የፈጸማቸው በተለይ ሁለት ስሕተቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው ራሱ የሰየመውና 7 አባላት ያሉበት የጳጳሳትና የሊቃውንት አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበትን ድምዳሜ ጥቅም እንደማይሰጥ ወረቀት አጨማዶ ቅርጫት ውስጥ መጣሉ ነው፡፡ አጣሪው ኮሚቴ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያሉበት እንደ መሆኑ በጭፍን ወይም ቤተ ክርስቲያንን በሚጎዳ መልኩ ከሜዳ ተነሥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይዘጋ ሊል አይችልም፡፡ በማኅበሩ ላይ፡- ከውስጥ ከማኅበሩ ሰዎች እየተነሡ ያሉትን ተቃውሞዎች፣ በአገር ውስጥ፣ በውጭ አገርም ካሉ ኦርቶዶክሳውያን የሚሰሙትን ከፍተኛ ሮሮዎችና ስሞታዎች በሚገባ ተመልክቷል፡፡ ማኅበሩ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑም መንግሥት ጥርስ ውስጥ የመግባቱም ጉዳይ ከፍ ያለ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያም በየጊዜው በበቂ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደቀነውን ትልቅ አደጋ በማያወላዳ መንገድ አስረድቷል፡፡ ይህን መርምሮ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ መወሰን ከሲኖዶስ አባላት ይጠበቅ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ሕጋዊም፣ መንፈሳዊም፣ ሳይንሳዊም፣ ኅሊናዊም፣ ያልሆነና ማኅበረ ቅዱሳን ጥፋተኛ ሆኖ ቢገኝም መቀጠል ነው ያለበት የሚል ለወሬ እንኳ የማይመች ኢፍትሐዊ ውሳኔ ነው የተወሰነው፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ አባ ሕዝቅኤል "ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ ለቤተ ክርስቲያን ማን አላት?" በሚለው "የማሳመኛ" ነጥባቸው መሞገታቸው አስገራሚ ሆኗል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን እኮ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተመሠረተች አይደለችም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይፈጠር የነበረች፤ መሠረቷ ክርስቶስ የሆነ የክርስቶስ አካል ናት፡፡ ለማኅበረ ቅዱሳንም የማይነጥፍ የገቢ ምንጭና ለፖለቲካዊ አጀንዳው መሸሸጊያ ዋሻው ነች፡፡ ስለዚህ ያለ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን ነበረች፤ ትኖራለችም፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያናችን ግን ማኅበረ ቅዱሳን አንድም ቀን ሊያድር አይችልም፡፡ ባይሆን አባ ሕዝቅኤል "ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ ለቤተ ክርስቲያን ማን አላት?" ከሚሉ ይልቅ "ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ እኛ ማን አለን?" ቢሉ ያስኬዳል፡፡ ተሐድሶ እየተባሉ በማኅበረ ቅዱሳን ስማቸው የሚብጠለጠለው የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ለእናንተ ስጦታ፣ እጅ መንሻ፣ መታያ፣ የፍቅር መግለጫ፣ ወዘተ. እያሉ በየጊዜው የሚገብሩት ወርቅና ብር የላቸውም፤ ያላቸው የታመኑበትና ከወርቅና ከብር ይልቅ የሚሻለው መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡

ሁለተኛው የሲኖዶሱ ስሕተት ራሱ ያቋቋመውን የሊቃውንት ጉባኤ "ተሐድሶ ነውና የተሐድሶን ጉዳይ ሊመለከት ስለማይችል ሌሎች ጳጳሳት ይመደቡ" ማለቱ ነው፡፡ ለመሆኑ ተሐድሶ ተብሎ በማኅበረ ቅዱሳን የተሰደበ ክፍል እንጂ፣ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን በሕጋዊ መንገድ መርምራና አጣርታ፣ መክራና ዘክራ ተመለስ ያለችው፣ አልመለስ በማለቱም "መናፍቅ" ብላ ያወገዘችው ሰው አለ ወይ? በፍጹም የለም፡፡ በሕግ አሠራር እንኳ አንድ ሰው ወንጀል ሰርቶ እጅ ከፍንጅ ቢያዝ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ብይን እስኪሰጥበት ድረስ ተጠርጣሪ እንጂ ወንጀለኛ እንደማይባል ይታወቃል፡፡ ለቤተ መንግሥት በብዙ ይተርፍ የነበረው ቤተ ክህነት ግን ዛሬ በዚህ ሕጋዊ መንገድ መመራት ተስኖትና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ያለ ስማቸው ስም እየሰጠ ሰብኣዊ መብታቸውን ሲገፍና ጉዳያቸው ተመረምሮ መናፍቃን ሆነው ያልተገኙትን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ልጆች "እገሌ መናፍቅ ነው፤ እገሌ ተሐድሶ ነው፤" ሲል መስማት እንዴት ያሳፍራል? በእውነቱ ይህ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ውርደትና ሞት ነው፡፡ ይህም እነአባ ሕዝቅኤል ጥብቅና የቆሙለት የማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ ውጤት ነው፡፡

ቀደም ሲል በዚህ መንገድ ማንም ከሜዳ ተነሥቶ ማንንም "መናፍቅ፣ ተሐድሶ" እንዳይል በፓትርያርኩ መመሪያ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ በጊዜው ለካስ ቤተ ክርስቲያናችን ሰዎች አሉባት አሰኝቶና አስደንቆ ነበር፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንን ግን ምን ያህል አስከፍቶት እንደ ነበረ በጊዜው ካሰማው ጩኸት ለመታዘብ ተችሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እነአባ ሕዝቅኤል እውነትን በገንዘብ ሸጠው ከሕግ ውጪ ያልተፈረደበትን ሰው ስም እየጠሩ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ወንጀለኛ ማለታቸው ብዙዎችን አሳዝኗል፡፡ ይህን ውሳኔ የሊቃውንት ጉባኤ እንዴት ያየው ይሆን?

በፓትርያርኩ መመሪያ ላይ እንደ ተገለጸው አንድ መናፍቅ ተብሎ የተጠረጠረን ሰው ጉዳይ መመርመር የሚችለውና ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያሳልፈው የሊቃውንት ጉባኤ ነው፡፡ የሊቃውንት ጉባኤ አንዱ ሥራ ሃይማኖታዊ ጉዳይን መመርመርና ለውሳኔ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ማሳለፍ ነው፡፡ የመጨረሻው ብይን ሰጪ አካል ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ይሆናል፡፡ አሠራሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ፣ አሁን ያለው የሊቃውንት ጉባኤ የተሐድሶን ጉዳይ መመርመር አይችልም የተባለበት ምክንያት ከቶ ምን ይሆን? እርሱ መርምሮ ያቀረበውን ውድቅ የማድረግ ሥልጣኑ የሲኖዶስ ነው እኮ! በአሁኑ ስብሰባ ራሱ የሰየመውን የአጣሪ ኮሚቴውን በጥናት ላይ የተመሠረተ ድምዳሜ ያለ አንዳች ምክንያት ውድቅ አድርጎ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ከመፍረስ እንደ ታደገው ሁሉ፣ በዚህኛውም አቅጣጫ ለማኅበረ ቅዱሳን የጎን ውጋት የሆኑትንና ማኅበሩ "ተሐድሶ" እያለ ስማቸውን የሚያጠፋውን ሰዎችም፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ መናፍቃን አይደሉም ቢል እንኳ፣ የእነ አባ ሕዝቅኤል ሲኖዶስ እንደ ለመደው ባለው የቬቶ ሥልጣን ውድቅ ማድረግና በማኅበረ ቅዱሳን በሁለት የክስ መዝገብ የቀረቡትን "የተሐድሶ አራማጆች" የተባሉትን ታላላቅ ሊቃውንትና ምሁራን ሁሉ በድምፅ ብልጫ ማውገዝ ይችላል፡፡

ሲኖዶሱ እንዲህ የማድረግ ሥልጣን እያለውና የሊቃውንት ጉባኤው ደግሞ ጉዳዮችን አጣርቶ መረጃዎችን ለሲኖዶሱ ከመስጠት ያለፈ ሥልጣን እንደሌለው እየታወቀ ታዲያ የሊቃውንት ጉባኤውን "ተሐድሶ ናቸው" በሚል ማሸማቀቅ ለምን አስፈለገ? ቢባል፣ የሊቃውንቱን ስሜት ሆነ ብሎ ለመጉዳትና በሚያደርጉት የማጣራት ሥራ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ተፈልጎ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡     

በእነዚህ ሁለት ታላላቅ የሲኖዶሱ የተሳሳቱ ውሳኔዎች ምክንያት ከማኅበረ ቅዱሳን በተጻራሪ የቆሙት ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ መምህራን፣ ዘማርያን፣ የሰንበት ተማሪዎችና ምእመናን ሁሉ ቅሬታቸውን በተለያየ መንገድ እየገለጹ ነው፡፡ እስካሁን የነበረው ውዝግብ በሲኖዶሱ ውሳኔ እልባት ያገኘ ሳይሆን ወደ ሌላ የባሰ ችግር መሸጋገሩን ነው እነዚሁ ወገኖች የሚናገሩት፡፡ ሲኖዶሱ ውሳኔውን አሻሽሎ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ በእኩልነት የማያስተናግድ ከሆነ ግን፣ መንግሥት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ ጉዳዩን ወደ መንግሥት አካል እንደሚወስዱት እየተነገረ ነው፡፡

"መንግሥት በሃይማኖት፣ ሃይማኖትም በመንግሥት ጣልቃ አይገባም" የሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ሽፋን እየተደረገ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጥፋቶች ሲደርሱ ኖረዋል፡፡ በተለይም አባ ሳሙኤል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩ ጊዜ በብዙ አገልጋዮች ላይ እጅግ የሚሰቀጥጡ የመብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል፡፡ የመንግሥት አካላትና የሰብኣዊ መብት ኮሚሽንም ከፍተኛ ቅሬታ ያሰማ እንደ ነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ጉዳዩ በፓርላማ ላይ እስከ መነሳት ደርሶም የቤተ ክርስቲያኒቱን መልካም ስም ያጎደፈ ክፉ ሥራ ሆኖ አልፏል፡፡ አሁንም ቢሆን የጠባይ ለውጥ ያላመጡት እነዚያው ሰዎች የብዙ ሊቃውንትንና ምእመናንን መብት በመጣስ ለሕገ ወጡ ማኅበረ ቅዱሳን ሽፋን እየሰጡ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጉዳይ፣ ወይም ሃይማኖታዊ ጉዳይ ከመሆን ያለፈ፣ በአገርና በመንግሥት ላይም የተደቀነ ትልቅ አደጋ መሆኑን ከግንዛቤ ማስገባት ይገባል፡፡ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም ለማኅበረ ቅዱሳን የሸጡት ጳጳሳትም "ኪራይ ሰብሳቢዎች" በመሆናቸው መንግሥት ጣልቃ እንዲገባና በሃይማኖት ሽፋን እየተፈጸመ ያለውን ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ደባና የመብት ጥሰት እንዲዳኝ፣ በአጣሪ ኮሚቴው የተደረሰበት ድምዳሜ ውድቅ የተደረገበት ሕጋዊ መሠረት እንዲፈተሽ እንደሚጠይቁና በዚህ ዙሪያ እንቅስቃሴ እንደሚጀምሩ ከአዲስ አበባ፣ ከሐረር፣ ከአሰበ ተፈሪ፣ ከሀዋሳ፣ ከዲላ፣ ከክብረ መንግሥት፣ ከሻኪሶ፣ ከሀገረ ማርያም፣ ከአለታ ወንዶ፣ ከመቀሌ፣ ከጎንደር፣ ከባሕር ዳርና ከሌሎችም ብዙ ከተሞች በርካታ ኦርቶዶክሳውያን እየተናገሩ ነው፡፡

20 comments:

 1. ምነው ከሀገር ውስጥ ብቻ ጠቀሳችሁሳ! እኛ በውጭ ሀገር የምንኖር እስከዛሬ የማህበሩ ቆሻሻ መዝገብ ተሸክመን የኖርን ዛሬ ዛሬ ይራገፋል ስንል ጳጳሳቱንም ጭምር በማሕበሩ እበት መዋኘት ጀመሩ። ጉዳዩ እንዲህ ከሆነማ ጳጳሳቱ ወደያለንበት ቤተ ክርስቲያናችን መጥተው ከቡራኬ ጀምረው ማነኛው ስራ እንዳይሰሩ መከልከል ነው፤ በሚሰሩት ስህተትም ሕግፊት ማቆም እንጀምራለን ከነውራቸው ካልተመለሱ። ድሮውም’ኮ እነ አንጋፈው ሊቅ አቡነ መርሐክርሰቶስ አሉ እያልን እስከዛሬ ተሸወድን እንጂ አንዱ ይለይልን ነበር።

  ReplyDelete
 2. aye..ene yemiasaznegn yihen ewunet meslot yemianeb sew new, long live MK, it is historical mistake not to be member of MK

  ReplyDelete
 3. You don't worth my comment. You are silly.

  ReplyDelete
 4. I got it collection of irrational views, lies. It is so silly. I understand from what you post that you are protestants.

  ReplyDelete
 5. IDLE MIND IS ALWAYS THE WORK SHOP OF A DEVIL. SATAN IS DOING HIS BEST USING YOU.

  SELAM YISTACHEHU!

  ReplyDelete
 6. bahiwate sitat yasarahubat kan binor zare lamajamariya gize yihen website kafche bamayate mikniyatum zenaw bamulu ka and mahiber gar yataganagna naw. try to be trusted website other wise only the owner of this website read this blog. lanagaru yihen alku inji yihen tsufen indamatawatu 99percent irgitagna nagn

  ReplyDelete
 7. የተዋህዶ ልጅ ነኝ ከአሜሪካOctober 31, 2011 at 8:05 PM

  ማ/ቅሳን ባይፈጠር ኖሮ የንደናንተ አይነቱ ሀይማኖት ሻጭ መጫወቻ ሆነን ነበር
  እግዚአብሔር ይጠብቀን

  ReplyDelete
 8. Few comment givers including you tried to blackmail “Manyazewal”. Would you post his photograph with his biography? Then, we will put our comment.

  ReplyDelete
 9. hahahaha "the holy synod of ORTHODOX CHURCH did not pass a solution in favor of the protestants", said by protestants!!!! keep it up you a bunch of the 21 century jokers.

  ReplyDelete
 10. ማኅበረ ቅዱሳን ቢፈርስ ለቤተ ክርስቲያን ማን አላት?"

  ReplyDelete
 11. ምነው ከ ማ/ቅና ከንፁሃን ብፁሃን ጳጳሳት ላይ እጃችሁን አላነሳ አላችሁ እናንተ የመናፍቃን የግብር ልጆች እና ናፋቂዎች፡፡ የሚገርመው ነገር መራክርስቶስ መራክርስቶስ ትላላችሁ እሳቸዉስ የማን ነበሩና አንዴ አልፈዋል እንጂ፡፡ ሁላችንም ለእዉነት እንኑር አይጎዳንም

  ReplyDelete
 12. ክርስቲያን ወገኔ ኣባቶችህን እና ተዋህዶ ሃይማኖትህን ማህበረ ቅዱሳንና እስላም እንዳይነጥቅህ ነቅተህ ጠብቅ

  ReplyDelete
 13. አባ ሰላማዎች እንደት አላችሁ የቤተ ክ/ያን አምላክ ይተብቃችሁ በርቱ መልእክታችሁ ጥሩ ነው ግን ወደ ዘር አትሂዱ ለምሳሌ የወሎዎች ቡድን የሚለው ቃል ጥሩ አይደለም ወሎ ሆኖ የእናንተ ደጋፊ ኣለና ።

  ReplyDelete
 14. ayyyyyyyyyy tenchachu engedih.lemin sereke papas alhonem new adel?engedih yewtalachihu alhonem.ende enante eko orhodox nen lemalet af yelachehum esti rasachihu yemetesefuten degmachehu anbebut.

  ReplyDelete
 15. ምነው ከ ማ/ቅና ከንፁሃን ብፁሃን ጳጳሳት ላይ እጃችሁን አላነሳ አላችሁ እናንተ የመናፍቃን የግብር ልጆች እና ናፋቂዎች፡፡ የሚገርመው ነገር መራክርስቶስ መራክርስቶስ ትላላችሁ እሳቸዉስ የማን ነበሩና አንዴ አልፈዋል እንጂ፡፡ ሁላችንም ለእዉነት እንኑር አይጎዳንም

  ReplyDelete
 16. silemin ewnet atawerum enante ybetkristiyan lijoch weys yegehanem dejoch.

  ReplyDelete
 17. First you should respect the churh fathers, they are at any cost better than you guys. Your blog realy tell us as you are anti-orthodox church. It tells us as you have some benefits from other religion. As church followers your way of writing is completely wrong because you started by insulting our fathers and critisizing the decision of Synodos. You should know and belive that the decision of Synodos is always as the decision of “Holy Spirt ” ,If you belived yourself as true church supporter. But as I can see you are supporter of W/o Ejegayehu, Begashaw, and others who are following and disturbing our church on the side of Tehadiso and Protestant. Simply, I would say you please please accept whatever decision comes from Synodos... you guys are preparing a lot to fall down the church but the holy Synodos fight your evil ideas off with God. Don’t be tired a lot and don’t be fight with God. God knows what’s in your heart and what you are thinking. And don’t insult also Fathers (you said tererist, ashebary). It is shame on you. You are also trying to make difference and separation between the church and followers on writing this blog. however you haven’t recognized that you are revealing yourself as if “Tehadiso “. I would advise you to pray more and take time to realize what you are doing so far. No one accept you. Easily I can assure you that I am a simple church follower who see what wrong things you are doing.
  Amlak yerdachihu !!!
  LensaHa Yabkachihu !!!
  Amen

  ReplyDelete
 18. demoze zemenz saidNovember 2, 2011 at 4:58 AM

  aba selamwoch . what are you to correct the holy synod?ante man honh new menfekdus yemimerawn sinodos sihitet sera yemtlew?

  ReplyDelete
 19. እናንተ በመጀመሪያ የምዘግቡት ስለ ቤተ ክርስቲያን ነው ወይንስ ስለ ማህበረ ቅዱሳን? ይህንን ለማለት የቻልሁት ትክክለኛ የ% አሀዝ ማስቀመጥ ባልችልም ከምትዘግቡት ከ80% እስከ 90% የሚሆነው የማህበረ ቅዱሳን መጥፎ ስራውን ነው(የሚገርመውና እኔን ከበስተጀርባችሁ የሚንጣችሁ(derive) አካል መኖሩን የሚያሳብቅባችሁ ደግሞ የማህበሩን መጥፎነት ስትገልጹ በማስረጃ ወይም ምክንያት(reason) አታስደግፉትም)፡፡ በእውነት እናንተ እንደምትሉት ማህበረ ቅዱሳን አንድም እዚህ ግባ የሚባል መልካም ስራ የለውም ማለት ነው? ስለዚህ ከዚህ ብቻ በመገንዘብ ድህረ ገጻችሁ የሚሰራው ፍትሀዊ ሆኖ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ሳይሆን ከሆነ አካል ተልዕኮ(Mission) ተሰጥቶት የስም ማጥፋት ፐሮፓጋንዳ ወይም ዘመቻ እንደሆነ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

  ReplyDelete