Wednesday, November 30, 2011

የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ፍልስፍና - ክፍል ሁለት - - - Read PDF

ከወልደ አበክረዙን
ባለፈው ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ፖለቲካዊ ዓማውን በሃይማኖት ሽፋን በምን መልኩ ያራምድ እንደነበር እና እንዳለ በመጠኑም ቢሆን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሃይማኖታዊ ዓላማውን /ሃይማኖት ከተባለ/ በፖለቲካ ተጽእኖ ለማሳካት የቀደምት አባቶቹን ስልት እንዴት እንየተጠቀመት እንዳለ ለማየት እንሞክራለን፡፡
በርካታ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሃይማኖታዊ ፍላጎታቸውን በፖለቲካ ጡንቻ ለማሳካት የሞከሩ መሆናቸው ቢታወቅም ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› እንደ ሞዴሉ አድርጎ ከሚወስዳቸው እንደ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና /ድብ-ፀር/ ልጁ በእደማርያም/ አድማስ-ለፀር/ በቅዱሳን ደም የተጨማለቀ የለም፡፡ እነዚህ አባትና ልጅ ነገሥታት  ሥልጣናቸውን  ላለማስነጠቅ ሲሉ አጅግ አረሜናዊ በሆነ ሰይጣናዊ መንገድ የቡዙ ሺሕ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደም አፍስሰዋል፡፡

Tuesday, November 29, 2011

የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቷል ዘፍ 18፥20 - - - Read PDF

ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም።ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ። እነርሱም። በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዘባቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት። በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው፤ እንዲህም አለ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም። ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ። ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት ዘፍ 191-10

Sunday, November 27, 2011

በአዲስ ኪዳን ጽላት እንዴት? - - - Read PDF


ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በዲያቆን ዓባይነህ ካሴ የተሰጠውና ስለጽላት የአዲስ ኪዳን ዘመን አስፈላጊነት ስብከቱ የተነሳ ነው። አባይነህ ካሴ ያልገለጻቸው፣ ያልመለሳቸውና ያላብራራቸው፣ ነገር ግን በምንም መልኩ ሊታለፉ የማይገባቸው ነጥቦች ስላሉ በዚህ ጽሁፍ ይዳሰሳሉ። ምክንያቱም ለክርስቲያኖች ከየትኛውም መረጃ በላይ የእምነታቸው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን እሱም ሳይሸፋፍን ለብሉይ ኪዳኑ ሥርዓትም ይሁን ለአዲስ ኪዳኑ ዘመን እምነት መመሪያን፣ትእዛዛቱንና መንገዶቹን በግልጽ አስቀምጦት ስለሚገኝ ነው።

Saturday, November 26, 2011

ዕንቁ መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ወይስ ነጻ መጽሔት? - - - Read PDF

ማኅበረ ቅዱሳን ሁለት ገጽታ ያለው ማኅበር መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ከፊት ለፊት የሚታየው ሃይማኖታዊ ሽፋኑ ሲሆን፣ ያ ሲገፈፍ የሚቀረው ደግሞ የተደበቀውና ፖለቲካዊ ማንነቱ ነው፡፡ በሁለቱም አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ ሚዲያዎችን ለአላማው ማሳኪያነት እንደየማንነቱ ይገለገልባቸዋል፡፡ ከፊት ለፊት ለሚታየው ሃይማኖታዊ ካባው ሐመርና ስምአ ጽድቅን ሲጠቀምባቸው፣ በማኅበሩ ስም በከፈተው ድረ ገጽም ተመሳሳይ ነገር ያቀርባል፡፡ ለድብቅ አላማው ማራመጃነት ደግሞ በርካታ ብሎጎችን፣ ለምሳሌ፡- ደጀሰላም፣ ገብር ሄር፣ አንዳድርግን፣ አሐቲ ተዋሕዶን፣ ይጠቀማል፡፡ በግለሰቦች ስም የተመዘገቡ የግል ጋዜጦችና መጽሔቶችንም ሁሉ ይጠቀማል፡፡ በተለይም ዕንቁ መጽሔት በግልጽ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ መጽሔቱ እንደ ነጻ መጽሔት አንድን ጉዳይ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ማቅረብ ሲገባው ብዙ ጊዜ ለማኅበረ ቅዱሳን ጥብቅና ቆሞና ሲብስም እርሱን ተክቶ ነው የሚናገረው፡፡ በነጻ ግን አይደለም፤ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ተከፋይ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ መጽሔቱ የማኅበሩን ጉዳይ በጋዜጠኛ ደንብ ሳይሆን እንደማኅበሩ ልሳን ሆኖ የያዘውም ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ያው በበላበት መጮኹ ነው፡፡

Friday, November 25, 2011

ስሕተቶቻችን ይታረሙ - - - Read PDF

ቤተ ክርስቲያናችን ፊልጶስ ባጠመቀው ጃንድረባ አማካኝነት በኢትዮጵያ ከተመሠረተች በኋላ በአባ ሰላማ መሪነት እያደገች እየተስፋፋች መሄዷን፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የሰሜን አፍሪካ መናፍቃን ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መጥተው ልዩ ልዩ ባዕድ ነገሮችን ተክለውባት እንዳለፉ ታሪክ ይናገራል አሁን እያየን ያለነውም ይህንን እውነት ነው።

ለምሳሌ የጥንቆላ ሥራዎች በቤተ ክርስቲያን ሰዎች በስፋት ሲሰራባቸው ይታያል። ጥንቆላው የሰሎሞን ጥበብ እየተባለ ስለሚነገር ብዙ ሊቃውንት ተብለው የሚጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት ነገር ነው። አቃቤ ርእስ፤ ግርማ ሞገስ፤ መስተፋቅር፤ መድፍነ ጸር፤ ወዘተ እየተባሉ የሚጠሩ ድግማቶች በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሚዘወተሩ ናቸው። አሁን አሁን ደግሞ የገብያ፤ የፍቅር ተብለው ተሰይመው በዘመናዊ መሣሪያ እየታተሙ ለምእመናኑ እየተሰራጩ ነው። በተጨማሪም ሕልመ ዮሴፍ፤ ምሕሳበ ቅዱሳን፤ ምህሳበ መላእክት የሚባሉ ድግማቶች አሉ እነዚህ ድግማቶች በስፋት የሚዘወተሩት በባሕታውያኑ ነው።