Tuesday, November 1, 2011

እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል 1ጢሞ 3፥2

የማይነቀፍ የአንዲት ሚስት ባል።

አባቶቻችን ሐዋርያት በነበሩበት ዘመን ሳይፈቱት የቀረ ችግር፣ ረስተው የተውት ነገር የለም። በመልእክታቸው ተጽፎ የምናገኘው እምነታቸውን ደግሞም የእመነታችውን ሥርዓት ነው። በያንዳዱ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሰጥተዋል። ከነዚህ ውሳኔዎች አንዱ የጵጵስና ጉዳይ ነው። ጳጳስ መሆን ያለበት ምን ዓይነት ሰው ነው? እኛ የሐዋርያትን ውሳኔ ላለመቀበል ቃላትን በመሰንጠቅ ትርጉምን ማጣመም ውስጥ ካልገባን በስተቀር እውነቱን በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኘዋለን።


"ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሠራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፥ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል ?‚  1ጢሞ 3፥1-5

  የአባቶቻችን የሐዋርያት ትምህርት ግልጥ ያለ አንድምታ የማያስፈልገው ትምህርት ነው። ጳጳስ መሆን ያለበት ባለትዳርና ልጆች ያሉት ሰው ነው። እግዚአብሔር በቤተ ሰቡእ ውስጥ ማስተዳደርን ካስተማረው በኋላ ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት ያውቃል።  እንደ ሐዋርያት ትምህርት ጳጳስ መሆን ያለበት ለማስተማር የሚበቃ ነው። ገንዘብ የማይወድ የሚለውም የማይለወጥ እውነት ነው። ራሳቸው ሐዋርያት ከቅዱስ ጳዎሎስ በቀር ባለትዳር ነበሩ በወንጌል አገልግሎት ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቅሱም ሚስታቸውን አስከትለው ይሄዱ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል 1ቆሮ 9፥5 ጋብቻ ርኩሰት አይደለም ምንኩስናም ቅድስና አይደለም ለሥራ ያመች እንደሆነ እንጂ። ምንኩስና ለወንጌል ከሆነ የተሻለ አድርጓል እንደ ጳውሎስ ትምህርት 1ቆሮ 7

 ከሐዋርያት ቀጥለው የተነሡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጳጳሳትም እስከ አራተኛው መቶ ክፍለ ዝመን ድረስ ባለትዳርና ራሳቸውን የገዙ ቅዱሳን ነበሩ። ታሪካቸውን ማጥናት ይገባናል።

  ከጥቂት ጊዜ በኋላ በግብጽ በርሃ እየተስፋፋ የመጣው ተነጥሎ የመኖር ፍልስፍና [መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም በወንጌል ምክንያት በመሰደድ ካለሆነ በቀር ተነጥሎ መኖር ለምን?] እንደፍልስፍናው አልዘለቀም። ተነጥሎ መኖር የሚለው ትምህርት ከአቅም በላይ በሆነ የተፍጥሮ አሸናፊነት እየተዳከመ መጣ። እናም የፍልስፍናው ተማሪዎች ከበርሃ የመጡ ቅዱሳን በመምሰል ወደ ከተማ እየገቡ ተፈጥሮአዊውን እውነታ መለማመድ ጀምሩ። መጽሐፈ መነኮሳት እንደሚናገረው መነኮሳትን ለመቆጣጠር ተብሎ ጥብቅ ሕግ ቢወጣም ሕጉን በመፈጸም ፍልስፍናውን በትንቃቄ የሚከተል ሰው አልተገኘም። ስለዚህ ተነጥሎ መኖር የሚለው ፍልስፍና ቀረና የቤተ ክርስቲያንን አመራር ለመያዝ ልዩ ልዩ ትምህርቶች ተፈልስፈው ሥራ ላይ መዋል ጀመሩ። የፍልስፍናው ሕግ አልሰራም የሐዋርያት ቃልም ተሻረና መነኮሳት የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ሆኑ። የአንዲት ሚስት ባል የሚለው ቃል ተተወ። በስውር ከዚያችም ከዚያችም መቀላወጡ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ቀጥሎ እናየዋለን

 ምንኩስናን ወደ ሐገራችን ያስገቡት ዘጠኙ ቅዱሳን ናቸው ይባላል፤ ምን አላባት እነርሱ በዘመናቸው ወንጌልን ቢሰብኩም ተነጥሎ የመኖር ፍልስፍናንንም ሰብከዋል። ምንኩስና  እስከ አስራ ሦተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሀገራችን ከፍ ያለ ሥፍራ ይሰጠው ነበር።

  በአስራ ሦተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሱት አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሕግ ያገቧትን ሚስታቸውን ያለሕግ አባረው ወደ ምንኩስናው ዓለም ከገቡና ከዚያም አልፎ የዛጉየዎችን መንግሥት ለመገልበጥ ባደረጉት የ12 ዓመት ትግል ሥጋዊ ነገር ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው ተነጥሎ የመኖር ፍልስፍናው እጅግ እየቀለለ መጣ። ጵጵስናም በአንስብሮተ ዕድ በቅባተ መንፈስ ቅዱስ ሲሰጥ ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣ ትውፊት በኒህ በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀለበሰ። እርሳቸው ሚካኤል የኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ሾሞኛል፣ በማለት ባልታወቀና በተድበሰበሰ ነገር ጳጳስ ሆኑ። የጵጵስና ቀኖና በመላኩ እንደተሻረ አድርገው የቡልጋ ሰባኪዎች ሰበኩት፣ በመጽሐፍም ጽፈውት እስከ ዛሬ ድረስ ይገኛል። እነዚህ ሰባኪዎች በጻፉት ጽሑፍ ላይ ከተክለ ሃይማኖት ወገን በቀር የሚሾም አይኑር በማለት የቤተ ክርስቲያንን ሹመት በዘር አደረጉት። ጵጵስና በጣም እየወረደ መጣ፣ ጠብና መለያየ አብሮ መጣ እስከ ዛሬ ድረስ አልበረደም።

 ፍልስፍናው በዚህኛው አስተሳሰብ ከተወረሰ በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ ቤተ ክርስቲያናችን እየታመሰች ትገኛለች። ዛሬም ቤተ ክርስቲያንን አልፎ አገሪቱን የሚያምሳት ይሄው ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ እስከ አሁን ድረስ ምሥጢር ነበር። ከዚህ በኋላ ግን የተሠወረ ነገር ይኖራል ብለን አናምንም።

 እምነታችን ሐዋርያዊት ናት ሲሉ ምንም አያፍሩም፣ የሐዋርያትን ቃል አሽቀንጥረው ጥለው ሐዋርያዊ ነን እያሉ በስማቸው ይነግዳሉ። እኛ እንደ ሐዋርያት ትምህርት እንኑር ስንላቸው ተሐድሶዎች ናችሁ ብለው በአድማ ያሳድዱናል። ጳጳስ መሆን ያለበት እንደ ሐዋርያት ትውፊት ባለትዳር ነበር።

  የዚህ ዘመን መነኮሳት ባለትዳር ቄስ ጳጳስ አይሆንም፣ ይህን ጥያቄ የሚያነሳ ተሐድሶ ነው ይላሉ። ነገር ግን እነርሱ ከሁለቱም አይደሉም። በምንኩስናው ሕግ አይመሩም አሊያም ትዳር መሥርተው ሥራት ይዘው አይጓዙም። በስውር እየወለዱ እንዲህ ቤተ ክርስቲያናችንን ያዋርዳሉ እንጂ። እኛ መውለዳቸውን ወይም ማግባታቸውን አንቃወምም፣ ለምን ሕዝባችንን ቅዱሳን በመምሰል ያታልላሉ? ለምን በሕጋዊ መንገድ አያገቡም? ነው ጥያቄያችን። እስካሁን ድረስ ሐሜት ነው እየተባለ ይወራ ነበር አሁን ሐሜት መሆኑ ቀርቷል።  የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት በታሪኩ ለጳጳሳት ሚስቶች የወራሽነት መብት በማጎናጸፍ አኩሪ ታሪክ አስመዝግቧል። በዚህ ዘመን ተሠውሮ የሚቀር ምንም የለም። ገና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምናስተምረው አለን፣ ገና የምንገልጠው ሥውር አመጽ አለ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የነቃ የበቃ ሆኖ ወደ ነጻነትና ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚደርስበትን መንገድ ሁሉ ለማሳየት ደከመን፣ ፈራን፣ ራበን፣ አንልም።

እውነት ነጻ ያወጣናል

ማሳሰቢያ

በኮረብታ ሆቴል ፒያሳ እና በሌሎች የመዝናኛ ቦታዎች በፎቶና በቢዲዮ የተገኙ የምንኩስና ቅሌቶችን በዚህ ብሎግ ለማሳየት ታስቧል

አንባቢ አስተያየቱን ይስጥበት፣ እንግለጠው ወይስ እንሠውረው? አንድም ድምጽ ዋጋ አላትና ድምጻችሁን ስጡ ምን ይሻላል?

ከፒያሳ

35 comments:

 1. የቤተ/ያንን አንድነት የምትፈልጉ ከሆነ ግን ቆም ብላችሁ አስቡ ትክክለኛ የሆነውን መንገድ ፈልጉ:: ሲኖዶስ ሁለት ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎችን ካሳለፈ ወዲህ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያለበትና ጥላቻ የሰፈነበት ጽሑፎችን አስነብባችሁናል:: ለምንድነው ከንቱ ጽሑፍ የምትጽፉት አባሰላሞች:: ቤተ/ያን እኮ ትልቅ ችግር ውስጥ እንደሆነች ማንም ያውቃል ይረዳል:: ሙስና: ዘረኝነት ተንሰራፍታል:: ምዕመኑን ዝም ብላችሁ አታደናግሩት:: ስለአስተዳደር መበላሸት ጻፉ እኔ አንዱ የዓላማችሁ ደጋፊ እሆናለሁ:: ነገርግን እናንተ ያላችሁት ወይም ያሰባችሁት ሲኖዶስ ላይ እስካልተወሰነ ድረስ አመጽ እናስነሳለን የአባቶችን ግብር እናጋልጣለን የምትሉት ለቤተ/ያን ከማሰብ የተነሳ አይመስለኝም:: ስለዚህ ይህ እቅዳችሁ ተገቢ አይመስለኝም::

  አሁን አለን የምትሉት ምስልና ቢዲዮ እውነት ቢሆን አይደንቀኝም:: ሰው ሆኖ የማይፈተን የለምና ሊከሰት ይችላል:: አባቶቻችንም ቢሆኑ ሰው እኮ ናቸው:: መጽሐፍ ቅዱስም ብዙ ታሪኮችን አስተምሮናል (ሶምሶን ታሪክ; ዮሴፍ የተፈተነበት: ዳዊት (በኦርዮን ሚስት) ልጁ ሰሎሞን): አንብበናል:: እግዚአብሔር ሁሌም መልካም ስለሆነ በንስሐ መለሳቸው:: ዮሴፍን ደግሞ ከሃሰት ቅሌት ታድጎታል:: " መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።" ዮሐ 8:7 እንዲል ለምን ከዚህ አንማርም:: ይህ ማለቴ ግን ከቅድስና ሕይወት የወጡ አባቶችን ዝም እንበላቸው ማለቴ አይደለም ግን በፍቅርና በትህትና ቢሆን ምን ክፋት አለው??????????? እኔና እናንተስ ብንሆን ምን ያክል ንጽሖች ሆነን ነው???? እነሱ ሰውናቸውና ሁኔታውን እንረዳ:: እኔን ጨምሮ ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን በእናንተ ወሬ የምንረበሽ አይደለንም:: መልካም አባቶች ደግሞ ሁሌም አሉና መጽናናችን ናቸው::

  እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣችሁ:: አሁን ያቁነጠነጣችሁ መያዣ ያሳጣችሁ ትመስላላችሁ::

  "መርከቧን የሚያውክ ነፋስ መጥቷል" የሚለውን የዲ.ን. ቴዎድሮስ ዮሴፍን መዝሙር እየዘመርን ሁላችንም ስለቤ/ያን እናልቅስ::

  ReplyDelete
 2. Aye qeld!Lemehone beteteqesut botawoch 'Menekuse'nen bayochine yasemarana yeqeretsachewe mane honena.Manem yemayaweqe mesluachu atedekemu.Yenante bite ande "menekuse"negne baye kezare arat amet befit be Nazerthe/Adama/ ategebe alga yazine.Quche beye eyanebebku set yizo meta.Ene ategeb metew teqemetu.Enkuan lemonekese beseme Ab male enkuan ayechelem.Kesuke Yegezawen lebse lebso lemadenager mehone gebagne.Ergete yemayawequ bizu yewahan mesenakelachew ayeqerem.Ebakachu atedekemu!

  ReplyDelete
 3. መጽሐፈ መክብብ
  12፥14
  «እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና»
  እንዳለው ወንድምዬ በሽፍንፍን ቅዱስ መስሎና ኃጢአቱን ሰውሮ ያለንስሐ ከሚሞትና ዐውደ ምኵናን ቆሞ ፍርድን ከሚቀበል አሁኑኑ ተገልጦ በኃጢአቱ አፍሮ አንድም ንስሐ እንዲገባ፤ አንድም ባልተሻረ ኃጢአቱና መሻር በማይችል ብቃቱ ፈታሁሽ፤ አሰርኩሽ እያለ በማታለል የመበለታትን መቀነትና ቤት እንዳይበዘብዝ፤ እንዲሁም «እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል» እንዲሉ እንዳይሆን እባክህን ያልታወቀ ማንነቱን አሳውቀን፤ የማያውቀው እሱነቱን ገልጠህ ንገረው። ይሄ ማግኔት ከሆነው ጥቁር ቀሚስና ቆብ ሥር ያለውን ዘወትር ዝግጁ የሆነ ምስጢር የቀመሱ ሴቶች መመለሻ የሌላቸው መሆኑ ይገርመኛል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጠበቃ የሆነ ሰው የሴት ጓደኛውን ለንስሃ አባቱ መነኩሴ ባስተዋወቀ በወሩ አይንህን ላፈር ያለችውን የ4 ኪሎዋን ኮረዳ መቼም አልረሳውም። ምን ዓይነት ጠበል ቢያቀምሷት ይሆን? የተቀማው ሰውዬ እስካሁን ድረስ ቄስ፤ መነኵሴን እግዚአብሔር ይፍጀው እያለ ይኼው እስከዛሬ ይራገማል። እናም ይህንን ዓይነቱን አድራጎት ለሌላው ማሳወቁ ከቀበኛ ሽፍንፍን ለመከላከል ይቻላልና አታቅማማ!!እኔም አንድ አስቂኝ እውነተኛ ገጠመኝ እነግርሃለሁ።

  ReplyDelete
 4. Pls sihitet be sihitet aytaremim tewew.Abatachin kebate abesa new ende sew limad animelalesim.

  ReplyDelete
 5. zewde ze-arat kiloNovember 1, 2011 at 4:07 AM

  ምንኩስናን አጥብቆ ከሚቃወሙ አንዱ እኔ ነኝ ግን ራሱ “ግሎባላይዜሽን” በሒደት እያስቀረው ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ጊዜ ባይጠፋበት መልካም ነው እላለሁ።
  መረጃ አግንተናል ስላላችሁት ጉዳይ ደግሞ ከኔ ጀምሮ በየቤቱ ያለው ቢቆጠር ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለዓለም በሙሉ አሳዛኝ ታሪክ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ስለዚህ “እንደራበህ አይበላም እንደተናደድክም አይነገርም” እንደተባለው ሁሉ መቸኮሉ ብዙሐንን ይዞ ሊሄድ ስለሚችል መታገሱ ይመረጣል። እኔም’ኮ ስለ ማሕበረ ቅዱሳንና ስለ አንዳንድ ጳጳሳት ገመናችውን የሚገልጹ ሕጋዊ መረጃዎች አሉኝ ነገርግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ብዬ ስለማምን እስካሁን ድረሰ ለመልቀቅ በፈራ ተባ እኖራለሁ።

  ReplyDelete
 6. min medebeqi yasifeligal giletut enji,egna yehayimanotachin meri geta eyesus enji sew aydelem

  ReplyDelete
 7. ቅዱስ ሲኖዶሱ በማሕበረ ቅዱሳን ላይ የወሰነው ውሳኔ ለምን ፖስት አታደርጉትም? እነሱ በራሳቸው ላይ የወረደ መዓት አይጽፉትም በደጀ ሰላም እንዳነበብነው ከሆነ።

  ReplyDelete
 8. ቅሌታቸውን የሚያሳየው ዶኩመንት ይፋ ይውጣ፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ይኸውም ፍጹም እውነትና እንደ ማኅበረ ቅዱሳን በውሸት የተለበጠ እንዳይሆን፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያናችን ከሀሳዊ መሲሆች መጥራት ስላለባት ነው፡፡ ሕዝብን በማስመሰል ያሰቃዩ አስኬማ የጫኑ እና እንደ ንፁሕ ሌላውን የከሰሱ ካህናት ይህ ቅጣታቸው ነው፡፡ አስኬማና ቆባቸውን ለቤተክርስቲያነ መልሰው እነርሱ ዞር ይበሉ፡፡ ትውልድም ከዚሀ ሊማር ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 9. qele rase rasehene berasehe tadenqalehe ende? weshetame

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማዎች በፊት በፊት የናንተን ብሎግ ሳነብ የሚሰማኝ ስሜት ጥሩ አልነበረም። ከዕለት ወደዕለት ግን በዕውነተኝነታችሁ ተማርኬ አድናቂያችሁ ሆኛለሁ። የእውነት አምላክ እግዚኣብሔር ይጠብቃችሁ። በቆብ መሣሪያ ቤተክርስቲያኒቷን ኢየፈተኗት ስላሉት በዘመኑ ስለበቀሉት መራራ ሥሮች የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎት ብሎት የሚያደርገው ጠፍቶት ፍርድ ከእግዚኣብሔር እየጠበቀ ነው ያለው። ምን አለበት አግብተው ቢኖሩ? መጽሐፍ ቅዱስም ያዛል፨ ባለ ሕጉን ካህን እዚህ ቦታ መቀደስ አትችልም!! ገዳም ሆኗል ብለው ያሳድዱታል እነርሱ ግን ሁለትም ሦስትም በየቦታው ኣስቅምጠው እንደልባቸው ይንፈላሰሱበታል ኧረ የክህነት ትንሽና ትልቅ አለው? ክርስቶስ በሞተላቸው ምዕመናን ላይስ በማስመሰል እስከ መቼ ነው ነግሰው የሚኖሩት? ስለዚህ አብዛኛው ሰው ግብራቸውን አውቆ አንቅሮ የተፋቸው ቢሆንም አንዳንድ የዋሀን ሰዎች እኩይ ግብራቸውን እንዲያውቁት ፤ እንዲሁም ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ስለሚፈተፍት ማንነታቸውን የሚገልጠው ቅሌታቸው ቢገለጥ ጥሩ ነው ይበል የሚያሰኝ ነው ለሌሎችም ትምህርት ይሰጣል።

  ReplyDelete
 11. ከወደቁ በኃላ መንፈራገጥ ለመላላጥ አሉ:: እናንተ ሃይማኖት ላይ የምታደርጉትን ቅሌት መች አመናችሁና ነው ሰለሌላው የምታወሩት? ምንም ነገር የላችሁም(ማስረጃ):: ካላችሁት ምን ያስጠበቃችሃል? አውጡት:: ከዛ ለሌላውም መንገድ ትከፍታላችሁ::
  የዛ ጊዜ ደሞ ምን እንደምትሉ አናያለን:: መቸም አታፈሩ:: አይ አባ ዲ**ሎሶች

  ReplyDelete
 12. post it with out any fear,if it is true.

  ReplyDelete
 13. i don't think you dont have any evidence except talk (were). let us see the evidence. please don't post which is not true.

  ReplyDelete
 14. I strongly rcommend you to pay attention on the verse below:

  "...ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።" ዮሐ 8:7

  ReplyDelete
 15. Choose the best answer whom you would like to be:
  A) Small minds discuss people

  B) Great minds discuss issues

  If your answer is "A" post it,If your answer is "B" please read John 8:7 " መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው።"

  ReplyDelete
 16. ማስረጃዎቹ ቢታዩ ለእርማት በጣም ይጠቅማል፡፡ ወደ31 ያህል ሥነ-መለኮታዊ ሥራዎችን ያበረከተ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አባት ተርቱልያን ባለትዳር ነበረ፡፡ እንዲሁም ለሥነ መለኮት ታላላቅ አስተዋጸዖችን ያበረከተው ታላቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ባለትዳር ነበረ፡ ሌሎችም ያገቡ ብዙ ኦርቶዶክሳውያን ቅዱሳን አበው አሉ፡ ማግባት ዓለማዊ ያለማግባት መንፈሳዊ አያደርግም፡ ያለማግባት ስጦታ የሌላቸው አባቶች እንዲያገቡ መደፋፈር አለባቸው፡፡

  ReplyDelete
 17. ግድ የለም እንሰውረው። ሰዎች ራሳቸውን እንዲያጠፉ ይጋብዛቸው ይሆናል እንጂ እነሱንም አይጠቅምም ሌላውንም አይጠቅምም። ምናልባትም ንስሀ ገብተውበት ይሆናል። ስለዚህ አባሰላማዎች ተውት ግድ የለም።

  ReplyDelete
 18. በመሰረቱ ምንኩስና ሰው ሰራሽና ከክርስቶስ ደም ውጪ በራስ ጥረት ለመጽደቅ የሚደረግ የከንቱዎች ትግል ነው። ጳውሎስ በድንግልና ኖሯል፤ ግን ድንግልናው እንዳይፈርስበት ወደ ጫካ አልፈረጠጠም። በንጽሕና ለመኖር የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ሴትን ከማየት እየሸሸ፤ ጭኑ መካከል እሳት ደብቆ እድሜ ልኩን እንደሽኮኮ ዋሻ ይኑር ያለው የትኛው መጽሐፍ ነው? ሰው ስደትና መከራ፤ የአላውያን ስቃይ ሲበዛባቸው፤ ወንጌል እንዳያስተምሩ አዋጅ ሲወጣባቸው ካልሆነ በስተቀር ሀገር ሰላም እያለ፤ እጅ እግሩን እያማታ ዱር የሚኖረው ምን ለማውረድ ነው? ለዓለሙ ምህረት ሊለምን ይሆን? ወይስ ለራሱ የፍትወትን መከራ በስቃይ ሊሸከም? ክርስቶስ እንደሆነ ከሰማያት ወርዶ በደሙ ምህረትና ይቅርታ አውርዷል። በዚያ ምህረት ጸንቶ መኖር፤ ለበደለም ንስሐ ገብቶ መንጻት ተሰጥቶናል። ታዲያ የዱሮቹ ምድረ አባ ምን ቤት ናቸው? እነሱ ጸልየው እንኳን በረከት ለሕዝብ ሊያተርፉ ይቅርና ራሳቸውም ከልመና አልወጡም። ያለ ልመናና ምጽዋት የሚተዳደር የነአባዎች ገዳም የትም የለም። ኢትዮጵያም ድርቅና ረሃብ ሳይለያት ጊዜ እየቆጠረ በመከሰት እነሆ መቶ ዓመት ሞላት። እግዚአብሔር ለወገኖቹ እንኳን ከየብስ ከዓለት ውሃ የሚያጠጣ ቅርብ አምላክ እንጂ ለረሃብ አሳልፎ የሚሰጥ ጨካኝ አይደለም።
  ሮሜ10፥3
  «የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ለማቆም ሲፈልጉ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም» እንዳለው የእግዚአብሔርን ጽድቅ ትተው የራሳቸውን የጽድቅ ዓለም ለማቆም ሲታገሉ የእግዚአብሔር በረከት ከሀገራችን ጠፋ። ከሓዋርያት ሴት ጠልቶ ጫካ የገባ አንድም የለም። ከሊቃውንትም ወንጌል በማስተማርና መናፍቃንን በመርታት፤ ህዝቡን በማረጋጋት ኖሩ እንጂ ሕዝቡን ሜዳ ጥለው፤ ለባዕድ አምልኮ ትተው ጫካ አልገቡም። ሆራ ላይ በመስቀል ወቅት የሚከበረው ባህላዊ አምልኮ ለእግዚአብሔር ህዝብ ያልተገባ ነገር ግን በስም ክርስቲያን እየተባለ ለሚኖረው ማን ማስተማር ነበረበት? አቴቴ፤ ጨሌ፤ ቦረንትቻ፤ ፎሌ፤ ቦቃ፤ ቦሃ፤ ዳለቻ፤ ገብስማ፤ ወሰራ ወዘተ እያለ እስካሁን የሚኖረውን ማን ያስተምር? እንደዝና ከ1 ሺህ በላይ ገዳም አለን እያሉ ማውራት ጀብድ ሳይሆን፤ ወንጌል ሰባኪ መሆን የሚገባቸውን በ100ሺህ ሰዎች ወደዝንጀሮነት ለውጠናቸዋል ማለት ይቀላል። «ኢትርዓይ ገጻ፤ ወኢትስማዕ ድምጻ ለአንስት» የሴቶችን ድምጽ እንዳትሰማ፤ ዓይኗንም እንዳታይ» በሚለው መርህ ከሴት ተለይቶ መኖር ጅልነት ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው። ሴትን እግዚአብሔር የፈጠረው ለኃጢአት ነው? ተሳስቷልም ማለት ነው? ዓይኗንም እንዳታይ፤ ድምጿንም እንዳትሰማ ማለት ሃጢአት ናት ማለት ነውና። የሚገርመው ደግሞ ያልተሰጣቸውን ጸጋ በትግል ለማግኘት ሲሞክሩ ተፈጥሮ ስለሚያስገድዳቸው፤ ወደከተማ ወጥተው፤ ንጹህ ናቸው በሚል የምእመናን የዋህነት እየታገዙ፤የንስሃ ልጁን፤ ስልጣኑን፤ ቦታውን ሁሉ ተቆጣጥረውከደብር ቀዳሽነት እስከጵጵስናው ይዘውት፤ ገንዘቡን ሴቱን አመድ ያወጡታል። ሐዋርያው «ለእመ ፈቀደ ይሠየም ጳጳሰ ይኩን ዘአውሰበ አሐቲ ብእሲት» ጳጳስ መሆን የፈለገ የአንድ ሴት ባል ይሁን» ያለውን ይሄ ስለቄስ ነው የሚናገረው እያሉ ቄሱን በአንድ ሴት ጠፍንገው እነሱ የ80 ፊርማ በሌለው ውስጠዘ ከሁለት በላይ አመድ እያወጡ ይኖራሉ።
  የሚገርመው ብዙዎች በድንግልና መኖርን ከጳውሎስ ተምረናል ይላሉ። ጳውሎስ ሰይፍ በአንገቱ እስኪያርፍ የክርስቶስን ወንጌል ሲሰብክ ኖረ እንጂ እንደነ ድንቄም አባ ዱር ተወትፎ ኖረ እንዴ? ወንጌል የሚሰብክ ጠፍቶ የገጠር እናቶቻችን ኢየሱስንና እግዚአብሔርን እንኳን መለየት የማይችሉ ሆነው ቀርተዋል። እስልምናው ከዜሮ ተነስቶ ዛሬ የሸሪዓ መንግሥት ለማቋቋም እስከመመኘት ተደርሷል። በአጠቃላይ ምንኩስና የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በቡድሃ ሲሆን፤ ከዚያም ወደክርስትናው ዘመን ብቅ ብሎ አባቱ ሞቶበት ሀዘን ላይ በወደቀውና ተስፋ በቆረጠው የግብጽ ሰው አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ከመስፋፋቱ በስተቀር አንድም ክርስቲያናዊነት ያለው አይደለም። ለመነኮሳት ጫካ መኖር ግዴታ ከሆነ ይሄ ሁሉ አሸን የፈላብን ለምንድነው?

  ReplyDelete
 19. mejemriya Ymhabrkidusan amrarochin qilet ensqadimna kziya qandgna qiletamoch papasat ysrutin masaytu tiru new. kazhi ytshale gize ylem. pls do that

  ReplyDelete
 20. እውነት ከሆነ ትለጥፉ ነበር:: ነገር ግን አሁን እንዲህም አይነት ነገር አለ እንዴ ብሎ ሕዝብ ብዢታ ውስጥ እንዲገባ እንጂ መረጃ ኖሯችሁ ወይም እውነት ሆኖ አይመስለኝም:: ደግሞም አይደለም::

  ReplyDelete
 21. ወንጌል የሚሰብክ ጠፍቶ የገጠር እናቶቻችን ኢየሱስንና እግዚአብሔርን እንኳን መለየት የማይችሉ ሆነው ቀርተዋል።

  so, are you saying jesus and God have a difference? wow what a knowladge you got there? and you think you are better than rular mams? who teach you this? Begashaw?

  ReplyDelete
 22. ABA SELAMAWOCH
  YE SELOMON FERED TEZ YEBELACHU BE HULETU EHETEMAMAHCHOCH MEHAL YEFEREDEW FIREDE ENE GIN YEQERE ATASAYUN ELALEHU TEWAHEDO BETAM TASAZENEGNALECH WOGENUA ENA TELATUA TEMETATUAL EBAKACHU SELE MESKINU HEZEB SETELU YE BETACHENEN GEBENA ATAWETU GEDELEM LEHULU YESEMAY GETA FIREDUN YESETAL MAHBERE QEDUSAN SELE BALEGE MEBALEG YELEBACHEHUM YE LIJENETE MENFESE YELELEW YE ENATUN MEWARED YESHAL ENE GIN BEDEKAMAW WOYEM BECHEWAW ANDEBETE TEWUTE ELALEHU.

  GETA YEFEREDEN

  ReplyDelete
 23. አባ ሰላማዎች እንደምን ሰንብታችሁአል የናንተን ብሎግ መልዕክት ሳነብ በጣም የመንፈስ ደስታና እርካታ አገኛለሁ።
  ምክንያቱም ሁልጊዜ እውነተኛ የእግዚአብሔርን ቃልና የክርስትናን ትርጉም በትክክል ስልምትገልፁት። የሆነው ሆኖ
  አሁን ባለው ወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ችግር በአንደኛ ደረጃ የሚጠየቀው፤ እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው አላማው የሐይማኖት ያልሆነ ድርጅት ነው። አሁን በተለይም የዚህ ድርጅት ደጋፊ ወይም የጥቅም ተካፋይ የሆኑ
  አንዳንድ ሐይማኖታቸውንና አደራቸውን ለስጋዊ ጥቅም የሸጡ አባቶች ቢኖሩም፤ በአሁኑ ሰአት ግን መጀመሪያ አንድ
  እስተያየት ሰጭ እንዳለው በቅድሚያ የዚህን ድርጅት ገመና፣ ለቤተክርስቲያናችንና ለአባቶች መከፋፈል፣ ለምዕመናን
  መከፋፈልና ፍቅር ማጣት የካንሰሩ መነሻ የሆነውን ማህበር በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከቀረበው የጥፋታቸው ሥራ
  ተጨማሪና ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ።

  አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎችን ብንመለከት በጣም በብዛት የዚያ\የማቅ\ አባላት ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም። ስለዚህ
  በተለያየ ዘዴ የእነሱም ሆነ የደጋፊዎቻቸው ጳጳሳትና ካህናት የርኩሰት ጥፋት እንዳይወጣ ሰለሚፈልጉ በአነጋገር ማሳመር ማለሳለስና ነገሩን ማዘናጋት ስለሚፈልጉ መንቃት ያስፈልጋል። ባጠቃላይ እኔ የሚመስለኝ፤

  በመጀመሪያ የማቅ አባሎች፤ ከዚያ ደግሞ የዘረኞቹና የሆዳሞቹ አባቶችን ጥፋት በማስረጃ ማቅረብ በጣም
  ያስፈልጋል። እነሱ እንኩአን የሐሰቱን ቅጥልጥል ቀጣጥለው የሙት ሙታቸውን ንፁሃን እባቶቻችንና ወንድሞቻችን
  ሲከሱ ኖረዋል። የሐሰት አባታቸው ዲያቢሎስም በክርስቶስ ኃይል እንደሚሸነፍ እምነታችን ፅኑ ነው። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታልና ።

  እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለመልካምና ለአንድነት ያድርግልን።
  የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
  የተጠሩ ብዙዎች ፣ የተመረጡ ጥቂቶች ናቸውና አይዙአችሁ ከተመረጡት ያድርገን እግዚአብሔር።

  ሜሊ

  ReplyDelete
 24. mahebere kidusan(mahebere cancer) benewerachw eyseferara silehone hasabun eyasfeseme yalew newrun megelete tiru new. bertu

  ReplyDelete
 25. aye aba selama demo ena nte blo selama ebakachihu betecrstiyanachnn lekek argachihu tarat tera tera were yemtawerubetn felgu yemtawetut thuhuf mnm ayrebam yhn tihuf blo gizewun lemiyatefawu sew azenku nsha giba

  ReplyDelete
 26. this is tehdso blog live alone betkrstiyanen i am 100% sure no one give you comment this comment is yours i am so sure you are so full kkkkkkkkkkkkkkkk

  ReplyDelete
 27. Anonymous said...

  ወንጌል የሚሰብክ ጠፍቶ የገጠር እናቶቻችን ኢየሱስንና እግዚአብሔርን እንኳን መለየት የማይችሉ ሆነው ቀርተዋል።

  so, are you saying jesus and God have a difference? wow what a knowladge you got there? and you think you are better than rular mams? who teach you this? Begashaw

  ላልከው አስተያየት ሰጪ፤- ጭፍን የዘርዓ ያዕቆብ ደጋፊ አቀንቃኝ መሆንህ የሚታወቀው እኔ ከሰጠሁት ስለምንኩስና የውሸትና የአጭበርባሪነት ብሎም የክርስትና ተግባር አለመሆን ጥቅል ሃሳቤ ተነስተህ በመረጃ አስደግፈህ በመቃወም ወይም ትክክል ነህ ብለህ በመደገፍ ማሳየት ወይም እዚህ ጋር ጉድለት አለ የምትልም ከሆነ ያንን ነቅሰህ በማውጣት የማስተካከያ ሃሳብህን በተጨባጭ ቃል ማስረዳት ሲገባህ አንዲት ሀረግ መዘህና ስህተት ያገኘህ መስሎህ በሌለህ እውቀት ወዲያና ወዲህ መዝለልህ አስገራሚ ነው። ጽሑፍህ ምናልባት የሚነግረን ነገር ቢኖር እንደማኅበረ ቅዱሳን ነጠላ ከመልበስ የተሻገረ እውቀት የሌለው ጎጋ መሆንህን ነው።
  ወደአነሳኸውና የነበጋሻው እውቀት ነው ወዳልከው ሃሳብህ ስመለስ «ወንጌል የሚሰብክ ጠፍቶ የገጠር እናቶቻችን ኢየሱስንና እግዚአብሔርን እንኳን መለየት የማይችሉ ሆነው ቀርተዋል» ያልኩትን ስለጠቀስከው ጉዳይ ጥቂት ልበል። በመሰረቱ ኢየሱስ ክርስቶስን « እግዚአብሔር» አይደለም የሚል ቃል አልወጣኝም። አንተ በግድ ብለሃል ካላልከኝ በስተቀር። በዮሐ 10፤30 «እኔና አብ አንድ ነን» ብሎ የነገረን ቃል የታመነ ነውና የኢየሱስ እግዚአብሔርነት ከግምት ውስጥ የማይገባ ነውና የጭንቁር ቃላት ጦስህን እዚያው አንተው ተሸከም እንጂ እኔ ላይ አትወርውር!
  ወንጌል እግዚአብሔር አብን፤ እግዚአብሔር በማለትና ወልድን ደግሞ ኢየሱስ እያለ ይጠራል። ያ ማለት ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለቱ ሳይሆን ሰማያዊ ልጅና ሰማያዊ አባትን ለማመልከት መሆኑ ብቻ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ራሱ «ዮሐ10፥36
  የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን» ሲል አብን እግዚአብሔር ሲል እናያለን። በሌላ ቦታም-
  ዮሐ13፥3
  «ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ...» በሌላ ቦታም-

  ዮሐ14፥33
  በታንኳይቱም የነበሩት በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት» የሚለውንና ሌላም ብዙ ብዙ ማስረጃ መጽሐፍ ቅዱሳችን ያሳየናል። የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት...፤ ከእግዚአብሔር እንደወጣሁ...፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልኩ...ወዘተ በሚሉት ቃላት ውስጥ «እግዚአብሔር» የሚለው አብን ለማመልከት የተቀመጡ ናቸው እንጂ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት አይደለም።
  ታዲያ «ኢየሱስንና እግዚአብሔርን» መለየት ላቃታቸው የገጠር እናቶቻችን የሚያስተምር ጠፍቶ...ያልኩት ሀረግ «ስለአብና ወልድ» የተነገረውን የምስራቹን ቃል የሚሰብ አላገኙም ከማለት የሚያጎድለው ምኑ ነው? ኢየሱስ እግዚአብሔርን አከበረ ማለቱ አባቱን ማለቱ እንጂ እሱ እግዚአብሔር እንዳይደለ ተናገረ ማለት ባለመሆኑ ያቀረብከው ትችት ሙሉነት የጎደለውና ከገጠር እናቶቻችን ያልተሻለ እውቀት ስላለህ ገና ማወቅ ይጠበቅብሃል ማለት ነው። እንግሊዝኛውን ከአማርኛው እያቀላቀልክ ከመጻፍ ይልቅ አማርኛውን ጠበቅ አድርገህ ለማንበብ ሞክር ምክሬ ነው። እነበጋሻው እኔ እንደጻፍኩት የሚያምኑ ከሆነ በእውነትም የወንጌልን ቃል ካንተ በመቶ እጥፍ ጨብጠዋል ማለት ነውና ምስጋናችን ይድረሳቸው። አንተም በማኅበረ ቅዱሳን ነጠላ በመሸፋፈን የእውቀት «ሃመልማል» chlorophyll አጥተህ ቢጫ ከምትመስል ፍሬ ለመያዝ እንደተዘጋጀ ተክል ሽፍንፍኑን ትተህ አረጓዴ ሁን!!
  እናቶቻችን ስለእግዚአብሔር አብና ስለ ኢየሱስ እውቀታቸው የደከመ መሆኑን ስናገር እየፈረድኩባቸው ሳይሆን የሚያስተምራቸው አለመኖሩን ለማመልከት ነው። አንድ ምሳሌ ላንሳ። እኔ እናቴም፤ አያቴም በህይወት አሉ። ከጥቂት ዓመታ በፊት በሞት የተለዩ ቅድመ አያቴንም በደንብ አውቃቸዋሉ።የገጠር ክርስቲያን ኦርቶዶክሶች ናቸው። ይሁን እንጂ ስለአብና ስለልጁ ምንም እውቀት የላቸውም። አያቴን ጠየቅኋት፤ ከኢየሱስና ከእግዚአብሔር አብ ማን ይበልጣል? ላልኳት የሰጠችን መልስ እግዚአብሔር ይበልጠዋል ነው። ይህ እንግዲህ የምናገረው እውነት የሆነ ነገር ነው።
  ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን፤ የሞተው እኛን ከኃጢአት ለማዳን መሆኑን፤ ዳግመና መጥቶም የሚፈርድ መሆኑን፤ ዘወትርም የሰጠንን ቃል መረዳት እንደሚገባ የሚያስተምራቸው ባለመኖሩ ተአምረ ማርያምን ምንም ሳትረዳው በግእዝ ተነብንቦ ያንን ተሳልማ ወደቤቷ ስትመለስ ኖራለች።« ወነበረ አሀዱ ብእሲ በሀገረ እገሌ»፤ «በላዔ ሰብእሰ ድኅነ በህፍነ ማይ» «ውሉደ ከልብ እስጢፋኖስ ተቀትለ በመቲረ አእናፊሁ» ወዘተ የዘርዓያዕቆብ ዝንግትል ስንቶች ከወንጌል እንደተለዩ ቤቱ ይቁጠረው! እናም የኛ ተቺ ይህች ላንተ እንኳን ማሳየት ያልቻለች ጽሁፍህን ማሳየት ወደምትችል እውቀት ጠጋ ብለህ ጠይቅ፤ ተማር ምክሬ ነው!!!!

  ReplyDelete
 28. አባ ሰላማዎች እንደምን ሰንብታችሁአል የናንተን ብሎግ መልዕክት ሳነብ በጣም የመንፈስ ደስታና እርካታ አገኛለሁ።
  ምክንያቱም ሁልጊዜ እውነተኛ የእግዚአብሔርን ቃልና የክርስትናን ትርጉም በትክክል ስልምትገልፁት። የሆነው ሆኖ
  አሁን ባለው ወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ችግር በአንደኛ ደረጃ የሚጠየቀው፤ እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው አላማው የሐይማኖት ያልሆነ ድርጅት ነው። አሁን በተለይም የዚህ ድርጅት ደጋፊ ወይም የጥቅም ተካፋይ የሆኑ
  አንዳንድ ሐይማኖታቸውንና አደራቸውን ለስጋዊ ጥቅም የሸጡ አባቶች ቢኖሩም፤ በአሁኑ ሰአት ግን መጀመሪያ አንድ
  እስተያየት ሰጭ እንዳለው በቅድሚያ የዚህን ድርጅት ገመና፣ ለቤተክርስቲያናችንና ለአባቶች መከፋፈል፣ ለምዕመናን
  መከፋፈልና ፍቅር ማጣት የካንሰሩ መነሻ የሆነውን ማህበር በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከቀረበው የጥፋታቸው ሥራ
  ተጨማሪና ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ።

  አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎችን ብንመለከት በጣም በብዛት የዚያ\የማቅ\ አባላት ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም። ስለዚህ
  በተለያየ ዘዴ የእነሱም ሆነ የደጋፊዎቻቸው ጳጳሳትና ካህናት የርኩሰት ጥፋት እንዳይወጣ ሰለሚፈልጉ በአነጋገር ማሳመር ማለሳለስና ነገሩን ማዘናጋት ስለሚፈልጉ መንቃት ያስፈልጋል። ባጠቃላይ እኔ የሚመስለኝ፤

  በመጀመሪያ የማቅ አባሎች፤ ከዚያ ደግሞ የዘረኞቹና የሆዳሞቹ አባቶችን ጥፋት በማስረጃ ማቅረብ በጣም
  ያስፈልጋል። እነሱ እንኩአን የሐሰቱን ቅጥልጥል ቀጣጥለው የሙት ሙታቸውን ንፁሃን እባቶቻችንና ወንድሞቻችን
  ሲከሱ ኖረዋል። የሐሰት አባታቸው ዲያቢሎስም በክርስቶስ ኃይል እንደሚሸነፍ እምነታችን ፅኑ ነው። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታልና ።

  እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለመልካምና ለአንድነት ያድርግልን።
  የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
  የተጠሩ ብዙዎች ፣ የተመረጡ ጥቂቶች ናቸውና አይዙአችሁ ከተመረጡት ያድርገን እግዚአብሔር Amen.
  Miliyon

  ReplyDelete
 29. ኣባ ኣሰላማዎች አሁን አዎቃችሁት ችግሩን ቤ/ተ ክርስቲያናን ለዚህ ፈተና የዳረጋት የመነኮስት አስተዳደር ነዉ። የምን መሸፈን ግለጡት እንጅ የስካሁኑ አይበቃም እስካሁን ተጭበረበርን እንግዲህስ ይብቃን ።ማ/ቅዱሳንን ተውት በራሱ ጊዜ ይወድቃል ምክኒያቱም 1ኛ ሃይማኖት የሌላቸው ሰዎች ስብስብ በመሆኑ 2ኛ የ4 ኪሎ ዱርየ ስብስብ በሆኑና በሌላም እኩይ ተግባሩ ይጠፋል ለዚህም ያደረሰው የመነኮሳት አስተዳደር ነው እሱ ከተስተካከለ ሁሉ ይስተካከላል። የተከፈለው መስዋእትለት ተከፍሎ ቤ/ክንን ከመነኮሳት አስተዳደር ማውጣት አለብን ።ለመሆኑ ውጭ ሃገር የሚላከው መነኩሴ መሆኑ ምን ማለት ነው ።አረብ ሃገር ያለችው ምስኪን ኢትዮጵያዊት እኮ ሃይማኖትዋንም ኣጣች።

  ReplyDelete
 30. my dear beloved. this may help us. sorry for delay.
  "If a man desire the office of a Bishop, he desires a good work. A Bishop then must be blameless, the husband of one wife, ...ruling well his own house, having his children in subjection with all gravity.
  [1 Timothy 3:1-4]

  For this reason I left you in Crete, that you should set in order the things that are wanting, and ordain elders in every city as I had appointed you; If any be blameless, the husband of one wife, having faithful children, not accused of riot, or unruly.
  [Titus 1:5,6]

  Now when Jesus had come into Peter's house, He saw his wife's mother lying sick with a fever.
  [Matthew 8:14]

  But Simon's wife's mother lay sick with a fever, and they told Him about her at once.
  [Mark 1:30]

  Now He arose from the Synagogue and entered Simon's house. But Simon's wife's mother was sick with a high fever, and they made request of Him concerning her.
  [Luke 4:38]


  Councils of the Church

  Canon V of the Canons of the Twelve Apostles (Apostolic Canons):Let not a bishop, presbyter, or deacon, put away his wife under pretence of religion; but if he put her away, let him be excommunicated; and if he persists, let him be deposed.

  Canon LI of the Apostolic Canons:If any bishop, presbyter, or deacon, or any one of the sacerdotal list, abstains from marriage, or flesh, or wine, not by way of religious restraint, but as abhorring them, forgetting that God made all things very good, and that he made man male and female, and blaspheming the work of creation, let him be corrected, or else be deposed, and cast out of the Church. In like manner a layman.
  In conclusion, the Apostolic Canons represent the very early Canon Law of the Church, that the Canons which make up the collection are of various dates, but that most of them are earlier than the year 300, and that while it is not possible to say exactly when the collection, as we now have it, was made, there is good reason for assigning it a date not later than the middle of the fourth century.... There can be no question that in the East the Apostolic Canons were very generally looked upon as a genuine work prepared by the Holy Apostles. [p. 592, Vol.XIV, The Seven Ecumenical Councils of the Undivided Church.

  Let us pray for our church Fathers.

  ReplyDelete
 31. Aba selamawoch,

  I have been following up on this blog since I was recommended by a friend. I have sent an e mal to the e mailed you guys posted here,

  What I said was, continue on this revealing (though some of the material was to be taken with a grain of salt) but please dont go down the path of MK with he said she said and character assasination path which all this kind of blogs take.

  What I see is you guys are going that rout. So, if you guys posted a video of a monk or a bishop, what does that prove except the character of that individual ? How does that prove that "minkusina" or the church Kenona of restricting "bishop" being a monk ? Dont we have many many great personalities of God, with so many unethical, illigal and worest yet Sinful behaviour in the BIBLE?

  The topic of challenging the Kenona is a leget topic of discussion. Any sane individual would agree with it but to say we will post a video of individuals to 'prove our point' is so short sighted and honestly rediculous.

  For me personally, I dont have any problem with the church "Kenona" as Paul said, he who he can should live in sylebacy but if one cant he should have his own wife. There is a leget reason behind the church restricting Bishiphood to monks. Again, the argument against it is leget but if you guys are using character of individuals to make this argument, its FOOLISH,

  Who is to say married man wont be cheating on his wife, or failed to raise his kids in a proper way as Paul suggested, one is going to argue we should bring Angels for "Bishophood"

  Its rediculous adn please retract this MK like witch haunt and continue with the great informative, factual, productive path you guys started. Otherwise, you will fall from grace. It didnt work for MK, and sure IT WONT WORK FOR YOU GUYS,

  TAZABI,

  ReplyDelete
 32. It is better to stop this. That is not good. It makes open for enemy .

  ReplyDelete
 33. Anonymous said...

  አባ ሰላማዎች እንደምን ሰንብታችሁአል የናንተን ብሎግ መልዕክት ሳነብ በጣም የመንፈስ ደስታና እርካታ አገኛለሁ።
  ምክንያቱም ሁልጊዜ እውነተኛ የእግዚአብሔርን ቃልና የክርስትናን ትርጉም በትክክል ስልምትገልፁት። የሆነው ሆኖ
  አሁን ባለው ወቅታዊ የቤተክርስቲያናችን ችግር በአንደኛ ደረጃ የሚጠየቀው፤ እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው አላማው የሐይማኖት ያልሆነ ድርጅት ነው። አሁን በተለይም የዚህ ድርጅት ደጋፊ ወይም የጥቅም ተካፋይ የሆኑ
  አንዳንድ ሐይማኖታቸውንና አደራቸውን ለስጋዊ ጥቅም የሸጡ አባቶች ቢኖሩም፤ በአሁኑ ሰአት ግን መጀመሪያ አንድ
  እስተያየት ሰጭ እንዳለው በቅድሚያ የዚህን ድርጅት ገመና፣ ለቤተክርስቲያናችንና ለአባቶች መከፋፈል፣ ለምዕመናን
  መከፋፈልና ፍቅር ማጣት የካንሰሩ መነሻ የሆነውን ማህበር በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ከቀረበው የጥፋታቸው ሥራ
  ተጨማሪና ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ።

  አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎችን ብንመለከት በጣም በብዛት የዚያ\የማቅ\ አባላት ለመሆናቸው ጥርጥር የለንም። ስለዚህ
  በተለያየ ዘዴ የእነሱም ሆነ የደጋፊዎቻቸው ጳጳሳትና ካህናት የርኩሰት ጥፋት እንዳይወጣ ሰለሚፈልጉ በአነጋገር ማሳመር ማለሳለስና ነገሩን ማዘናጋት ስለሚፈልጉ መንቃት ያስፈልጋል። ባጠቃላይ እኔ የሚመስለኝ፤

  በመጀመሪያ የማቅ አባሎች፤ ከዚያ ደግሞ የዘረኞቹና የሆዳሞቹ አባቶችን ጥፋት በማስረጃ ማቅረብ በጣም
  ያስፈልጋል። እነሱ እንኩአን የሐሰቱን ቅጥልጥል ቀጣጥለው የሙት ሙታቸውን ንፁሃን እባቶቻችንና ወንድሞቻችን
  ሲከሱ ኖረዋል። የሐሰት አባታቸው ዲያቢሎስም በክርስቶስ ኃይል እንደሚሸነፍ እምነታችን ፅኑ ነው። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታልና ።

  እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለመልካምና ለአንድነት ያድርግልን።
  የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
  የተጠሩ ብዙዎች ፣ የተመረጡ ጥቂቶች ናቸውና አይዙአችሁ ከተመረጡት ያድርገን እግዚአብሔር Amen.
  Miliyon

  ReplyDelete
 34. Hulum kentu bicha new yemiyawerawu. Everyone in the world is really selfish. This world sucks as it is full of selfish people. Me, our fathers, you and others are all selfish. Specially in Ethiopia we have selfish people all over the place, in politics, universities. The only surprising and shame event is to see in church, mosque.

  You Abaselam blog also selfish and selfish like me and others.

  So Can everyone stop being selfish for one minutes at least one. I want to live in a world without selfishness for at least one minute and die.

  I don't care if you don't post it anyways.

  ReplyDelete
 35. THanks to OUR LOARD, please donot be affraid of ,it is mandatory to lease or open the document what u have in ur hand.

  ReplyDelete