Tuesday, November 22, 2011

የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዘመን ደብተራዎችና ፈጠራዎቻቸው - - - Read PDF

ሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ [1000 . ገዳማ] ደርግ እስከ መጣበት ድረስ በኢትዮጵያ ሲገዛ የኖረ መንግሥት ነው። መሠረቱ አክሱም ሆኖ እስከ ዛጉዬ ሥርወ መንግሥት [ዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን] ድረስ በአክሱሞች ተይዞ ቆይቷል። የላስታ መንግሥት ዛጉዬ በመባል ይታወቃል "ዘአጕየየ መንግስተ አክሱ" ለማለት ነው። ከዘጠነኛው እስከ አሥራ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገዝቶ አስደናቂ ቅርሶችን አስቀምጦ አልፏል።
 የዛጕየ ዘመነ መንግሥት ማክተም ምክንያቱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መሆናቸው ታውቋል። ገድለ ተክለ ሃይማኖት እንደሚለው ላስታዎች መንግሥት አይገባቸውም ነበር። ምክንያቱን ሲያቀርብ "የሰሎሞን ዘር ስላልሆኑ" ይላል። ስለዚህ መንግሥት ወደ ሰሎሎሞን ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ ሲዛወር ክህነትም የአሮን ዘር ወደ ሆኑት ወደ ተክለ ሃይማኖት ተዛወረ፣ ከተክለ ሃይማኖት ዘር ውጭ ጳጳስ ወይም እጨጌ መሾም እርግማን ነው በማለት ገድላቸው ይደመድማል። ሃይማኖት የፖለቲካ መሳሪያ መሆን የጀመረው ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው። አቡነ ተክለ ሃይማኖት "የሰሎሞን ሥርወ መንግሥት ወደ ትክክለኛው ዘር ወደ ይኩኖ አምላክ መመለስ አለበት" እያሉ ሲሰብኩ ኖረው በመጨረሻ ስብከቱ አላዋጣ ሲል የላስታው ንጉሥ በጦር እንዲገደል ቀጥተኛ ትዛዝ መስጠታቸውን ገድላቸው ይናገራል።[ገድለ ተክለ ሃይማኖት 241-5 እና 26 ያንቡ]

     የላስታው ንጉሥ ይትባረክ በይኩኖ አምላክ ሲገደል ወሎ ውስጥ ከላስታ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው "ድግር መጥረቢያ" ላይ የበርካታ ሰዎች እግር መቆረጡን በአካባቢው ታሪክ ሆኖ ይነገራል። አገሩ "ድግር መጥረቢያ" የተባለበት ምክንያት እግር የተቆረጠበት ቦታ በመሆኑ ነው ይባላል። ይህ ጉዳት ያገኛቸው ሰዎች ግን ያች እግር የተቆረጠው "በጸሎት ብዛት" መሆኑን ይተረካሉ። ነገሩ የፖለቲካ ጨዋታ ስለሆነ ማለባበስ የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው እንዲህ የተባለው የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች አሉ።
 ሃይማኖትን የፖለቲካ መሳሪያ ማድረግ እንደሚቻል ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት የተማሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም በአሜሪካ ቁጭ ብለው ደርግን በኢሕዴግ ሲያስወጉ እንደነበር ይተረክላቸዋል። እርሳቸው ግን አሜሪካ ስለነበሩ እግራቸው በመጥረቢያ ከመቆረጥ ተርፏል። ስለዚህ ስድስት ክንፍ ማውጣት አያስፈልጋቸውም መብረር ከፈለጉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተከራያቸው በራሪ አካላት አሉ።
    ስድት ክንፍ የወጣላቸው ሰው እግር ስለሌላቸው ነው ተብሏል እናም በክንፋቸው በረው ሄደው 24 ካህናተ ሰማይ ላይ ተደረብው 25 ካህን ሆነው እስከ ዛሬ ድረስ የጌታን መንበር እያጠኑ ነው ተብሏል። አንድ ቀን ሰውየው ክንፍ ያወጡት በሥጋቸው ነው ወይስ በነፍሳቸው ብዬ ጠይቄ ነበር። በነፍሳቸው ነው ተባልሁ። ታዲያ ደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ነው ክንፉ የበቀለው ብሎ ገድላቸው ለምን ይናገራል? ስላቸው አይ ይቅርታ በሥጋቸው ነው አሉኝ። በሥጋቸው ከሆነ በደብረ ሊባኖስ ከሚገኘው አጥንታቸው ላይ ክንፋቸውንም አብረን ልናገኘው እንችላለን ስላቸው ክንፋቸው ተሰውሯል ብለውኝ አረፉት። ተሠውሯል? ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀልስ እንዴት ነው ስላቸው አዎ ለክብራቸው ነው አሉኝ ሌላው እውነተኛው አባት ግን ልጄ እንግሊዛዊቷ ንግስት ለአጼ ምኒልክ ባለቤት የሸለሟቸው ስጦታ ነው ብለው እውነቱን ነገሩኝ። አዳዲስ ውሸቶች በጥንቱ ውሸት ላይ እየተጨመሩ አስቸግረውናል ብለውም አከሉልኝ እኔ ግን የፖለቲካ ጉዳይ ነው እላለሁ።
    መለስና ይኩኖ አምላክ፤ አቡነ ጳውሎስና አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ነጉሥ ይትባረክና መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ይመሳሰሉብኛል። ይኩኖ አምላክ ተክለ ሃይማኖት ለዋሉት ውለታ ሲሶ መንግሥት የሰጣቸው ሲሆን፤ መለስም ለአቡነ ጳውሎስ ይኸው ፕትርክናውን ከአቡነ መርቆርዮስ ቀምቶ አጎናጽፏቸው ይገኛል። ክህነት ከአሮን ዘር ወጣ ማለት ነው? ይትባረክ ድግር መጥረቢያ ላይ፤ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዝምባዌ ላይ ወድቀው ቀሩ። ሃይማኖት እስከ አሁን ድረስ የፖለቲካ ጨዋታውን ሞቅ ሞቅ አርጎታል።  ማህበረ ቅዱሳንም ከዚህ ታሪክ በመኮረጅ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፤ ፍጻሜውን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል። እያንዳዱን የጨዋታ ዓይነት ወደ ፊት እመለስበታለሁ። ዛሬ ላሳያችሁ የምፈልገው የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ደብተራዎች የፈጠሩትን እና የቤተ ክርስቲያናችን እምነት ያደረጉትን ጥንታዊ ተረት ነው።

 ተረቱ ባጭር ቃል፦
ትንሽ መነሻ ካገኙ እግራቸውን ወደ ላይ ብለው ውሸታቸውን በመልቀቅ የሚታወቁት የሰሎሞን ሥርወ መንግሥት ደብተራዎች ማፈሪያ የሆነውን ተረት ሲተርቱ እንዲህ ይላሉ።
   የኢትዮጵያ ንግሥት ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ጥበብ ለማየት በሄደችበት ጊዜ[ይህ እውነተኛ ታሪክ ነው 1ነገ 10] ከሰሎሞን ጸንሳ መመለሷንና ቀዳማዊ ምኒልክን እንደወለደች ይተረካል። ምኒልክ በተወለደ በሃያ ዓመቱ አባቱን ለመጎብኘት ሄዶ ነበር። ሲመለስ ልጄን ባዶ እጄን አልሰደውም ብሎ ታቦተ ሚካኤል ከሦስት መቶ በላይ የሆኑ ሌዋውያን ከልዩ ልዩ መጻሕፍት ጋር እንዲሰጠው ታዘዘለት። ሌዋውያኑ ግን በሚካኤል ፈንታ ታቦተ ጽዮንን ሰርቀው ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ታቦተ ጽዮን በኢትዮጵያ እንደምትገኝ ይተርካሉ። የመንግሥታቸው ታሪክ ከዚህ እንደሚጀምርና ንጉሥነትም ከይሁዳ ዘር አይወጣም የተባለውን የጌታ ቃል በመጥቀስ "ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ" ብለው ሰይመው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲገዙበት እንደኖሩ ሁላችን የምናውቀው ጉዳይ ነው። ይህ ያለፈ ታሪክ ዛሬ አይቆጨንም ነገር ግን ዛሬ ላይ ለምንገኝ ኢትዮጵያውያንን መናፍቅ እያሰኘ እያስወገረን ስለሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀውና ፍርዱን እንዲሰጥ እንፈልጋለን።
አትስረቅ የሚለው ሕግ የተጻፈበት ጽላት የተቀመጠበት ታቦት ተሰርቆ መጣ የሚለው ታሪክ የተጋነነ ነው። እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ታቦት አንድ ብቻ ነው ዘጸ 2510-28 የሚካኤል ታቦት አብሮ እንደተሰጠው የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የለም። በታሪክም በአዋልድ መጻሕፍትም ስለሚካኤል ታቦት የሚናገር አይገኝም ከድርሳነ ኡራኤልና ከገድለ ተክለሃይማኖት በቀር።
 በእርግጥ ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ መጣለችን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለታቦተ ጽዮን ምን ይላል?
                                                        መጽሐፍ ቅዱሳዊው ታቦት

                                                   የኢትዮጵያው ታቦት
መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ታቦትና የኢትዮጵያውን ታቦት ተመልከቱ

 
ምኒልክና የሰሎሞን ዘመን መራራቅ

1 ሰሎሞን በነገሰ በአራተኛው ዓመት ከሁለት ወር ቤተ መቅደሱን ለመስራት መሠረት አኖረ። 1 ነገ 61 2ዜና 31-2
2. የቤተ መቅደሱ ሥራ ሶሎሞን በነገሰ 11ኛው ዓመት 8 ወር ተጠናቀቀ። 1ነገ 636-37 ሥራው የፈጀው ጊዜ 7 ዓመት ከስድስት ወር ነው።
3. በጥቅሉ የራሱን ቤት እና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት የፈጀበት ጊዜ 20 ዓመት ነው 1ነገ 910 2ዜና 81-8
 ከዚህ በኋላ ነበር ንግሥተ ሳባ የሶሎሞንን ዝና ሰምታ ለመጎብኘት የሄደችው መጽሐፍ ቅዱስ የቤተ መቅደሱን እና የቤቱን ሥራ እንደጎበኘች ይናገራልና ሥራው ከተጠናቀቀ በኋላ መሄዷን ለመረዳት አንቸገረም 1ነገ 101-13 2ዜና 91-12
4. ንግሥቲቱ ወደ ሶሎሞን ለመድረስ የፈጀባት ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ ባናውቅም በደረሰች ጊዜ ጸነሰች ብለን እንኳ ብናስብ የጽንሱ ጊዜ 9 ወር ነው።
5. እንደ ክብረ ነገሥቱ እንደ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ትረካ ቀዳማዊ ምኒልክ 20 ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ 3 ዓመት ቆይቶ ተመልሷል ስለሚል በድምሩ 23 ይሆናል።
 ጠቅላላ ድምር
 ቤተ መቅደሱ ከመጀመሩ በፊት የነበረው ይሰሎሞን የንግሥና ዘመን 4 ዓመት 2 ወር  
 የቤተ መቅደሱና የራሱ ቤት ሥራ የፈጀው ጊዜ 20 ዓመት  20+4= 24
 ምኒልክ የተጸነሰበት ጊዜ 9 ወር 9+2 = 11 ወር ይሆናል
ምኒልክ ኢትዮጵያ የቆየበት ጊዜ 20 ዓመት እና አባቱ የቆየበት 3 ዓመት 20+3= 23
ጠቅላላ ድምሩ 47 ዓመት 11 ወር ይሆናል።  48 አመት ብንለው ይሻላል።
   መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስረዳን ግን ሰሎሞን የነገሰው 40 ዓመት ብቻ እንደሆነና እንደሞተ ነው። በመጽሐፍ ቅዱሱ መሠረት ምኒልክ የሄደው ሰሎሞን በሞተ 5ኛው ዓመት ነው። ታዲያ ሰሎሞን እና ምኒልክ አራባ ቆቦ ሆነው ሳለ እንዴት በሰሎሞን ትዕዛዝ ሌዋውያንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ ሊመጣ ቻለ? ነገሩ ተረት መሆኑን እንረዳለን።
 ክብረ ነገሥት በቤተ መቅደሱ ከነበሩት ታቦታት ውስጥ አንዱ የማርያም አንዱ የሚካኤል ነበር ይልና የሚካኤልን ውሰድ ቢባል የሚካኤልን በማርያም ሥፍራ ተክተው የማርያምን ይዘው መጡ ይላል። ማርያም በሰሎሞን ጊዜ ነበረችን? ገና መች ተወለደችና ነው ታቦት የሚቀረጽላት? በሬው ወለደዎች!
 በመሠረቱ ታቦተ ጽዮን ከሰሎሞን በኋላ 16 ሆኖ በነገሰው በኢዮስያስ ዘመን እዚያው ኢየሩሳሌም እንደነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ታሪኩን እንደዚህ እናስተውለው
በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው የታቦተ ጽዮን ታሪክ በማያሻማ መልኩ ወደ ባቢሎን ተማረከ የሚል ነው

 ታቦቱ ከመማረኩ በፊት በኢየሩሳሌም እንደነበረ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል "ቅዱሱን ታቦት የእሥራኤል ንጉሥ  የዳዊት ልጅ ሰሎሞን  ባሠራው  ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም" 2ዜና 353 ንጉሥ ኢዮስያስ የተናገረው   ( ኢዮስያስ ለሰሎሞን አሥራ ስድስተኛ ንጉስ ነበር) ከኢዮስያስ በፊት ነግሶ የነበረው ምናሴ  የቤተ መቅደሱን ዕቃ አውጥቶ  በውስጡ  ጣኦት አስቀምጦበት እንደነበር  2ዜና 338 ላይ ይናገራል። በዚህ ምክንያት ካህናቱ ታቦቱን ተሸክመው በየቤታቸው  ይዞሩ ነበር ኢዮስያስ "ከንግዲህ ወዲህ በትክሻችሁ ሸክም አይሁንባችሁ" ያለው በዚህ ምክንያት ነው።

    የባቢሎን ምርኮ ከኢዮስያስ ዘመን በኋላ [600 .]ተጀምሮ በሴዴቅያስ ዘመን ተፈጽሞአል። በባቢሎን የምርኮ ዘመን የነበረው ነቢይ ኤርምያስ ነበር።2ዜና 3611-23
   ነቢዩ ኤርምያስ ስለታቦቱ በራሱ መጽሐፍም እንዲህ ብሎአል"የግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም አያስቡትምም አይሹትምም፤ከንግዲህወዲህም አይደረግምም" ኤር 316። ኤርምያስ ከኢዮስያስ ጀምሮ እስከ ባቢቢሎን ምርኮ እስከ ሴዴቅያስ የነበረ ነቢይ ነው  ኤር11-3 ያንቡ። ኤርምያስ "ከእንግዲህ ወዲህ አይደረግም" ያለው ታቦቱ በባቢሎናውያን እንደሚወሰድ በመንፈስ ቅዱስ ስለተረዳ ነው። ወደ ኢትዮጵያ ከተወሰደ 330 ዓመት በኋላ እንዲህ ሊናገር አይችልም። ኢዮስያስ ያልነበረን ታቦት በቤተ መቅደስ አኑሩት በትክሻችሁ አትሸከሙት ሊል እንደማይችል ሁሉ ኤርምያስም በዘመኑ የነበረውን ታቦት ትንቢት ተናግሮበታል።     ታቦቱ በሴዲቅያስ ዘመን ወደ ባቢሎን እንደተወሰደ የሚናገረው  የመጽሐፍ   ቅዱስ ክፍል የሚከተለው ነው። "እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱን ጥቃቅኑን እና ታላቁን ዕቃ ሁሉ የግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት እቃ ቤትም  ያለውን ሳጥኑንም ሁሉ  ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ" እዝራ ካልእ 154

"ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይምን ግናይቱ እንደጠፋ ምስጋናችን እንደቀረ ዘመራ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፋ የሕጋችን ማደሪያ ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች አታይምን?" እዝራ ሱቱ 9 23

"ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮን እንደ ጠፋች ቀረች ከሷ ጋርም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎናውያን እጅ ወደቅን" እዝራ ሱቱ 9 23
 
    ከዚህ ትምህርት  እንደምንረዳው  መጽሐፍ ቅዱሱና ክብረ ነገስቱ፤ ገ/ተክለ ሃይማኖት፤ድርሳነ ኡራኤል አለመስማማታቸውን ነው።  ምክንያቱም  ሦስቱ መጻህፍት ማለት ክብረ ነገሥት፣ ገድለ ተክለ ሃይማኖት፣ ድርሳነ ኡራኤል፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በማደም በሰሎሞን ጊዜ ታቦቱ ተሰርቆ መጧል ሲሉ  የእግዚአብሔር ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ወደባቢሎን ተማርኳል ይላል። በትውፊት የሚያላክኩ ደብተራዎችን እንቀባላቸው ብንል እንኳ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚቀድም መጽሐፍ የለምና ዘወር በሉ ለማለት እንገደዳለን። ከላይ የጠቀስሗቸውን ጥቅሶች ለማግኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖናዋ የተቀበለችውን ሰማኒያ አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ይመልከቱ።

ማህበረ ቅዱሳን ያሳተመው "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" የሚለው መጽሐፍ ግን ታቦቱ በሰሎሞን ጊዜ ሳይሆን  በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ወደ ግብጽ በተሰደዱ ካህናተ ኦሪት  ለዘመናት ግብጽ ቆይቷል ከዚያም ስደት ሲበዛባቸው ወደ ሱዳን ይዘውት እንደ መጡ ከሱዳን ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይዘውት እንደገቡ ይተርካል ።በጣና ቂርቆስ 800 መቶ አመት ያህል ቆይቶ  የአክሱም ነገሥታት  ከአይሁድ ነጥቀው  እንደወሰዱትና በአክሱም እንዳስቀመጡት፤ እንዲሁም  በዮዲት ጦርነት ጊዜ ወደ ዝዋይ ተወስዶ ቆይቶ  ዮዲት ከተሸነፈች በኃላ ወደ አክሱም ተመልሶ  አሁንም በዚያ እንደሚገኝ መጽሐፉ ይተርካል።ይህ ትረካ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይመሳሰላል፤ ፍርዱን ግን ለአንባቢ እንተወዋለን።

 ማጠቃለያ
ነገሩ የፖለቲካ ጭዋታ መሆኑን ደርሰንበታል፣ እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሕዝባችንን ለመግዛት ታቅዶ የተፈለሰፈ ታሪክ መሆኑን ለማንም ግልጥ ነው። መንግሥት ከይሁዳ ዘር አይወጣም የሚለውን ቃል የሚያከብረው ሕዝባችን የሁዳ መንግሥት በኢየሱስ ክርስቶስ መወረሱን እርሱም የዘላለም ንጉሳችን መሆኑን ሳይነግሩት ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንዲሉ የይሁዳ ዘር እኛ ነን ከሰሎሞን ተወልደናል እናም መንግሥታችንን ማንም እንዳይነካ የአሮን ዘር ስለሆንን ክህነትም የኛ ነው ቃሉን መጠበቅ አለባችሁ በማለት የጌታን ክብር ሠውረው የራሳቸውን ንግሥና ሲያመቻቹ ኖረዋል። በዚህ ምክንያት ነው ይህ ተረት እንዲፈጠር የተደረገው።
   ዛሬ ግን የጽድቅ ጸሐይ ወጥታለች። ይህ እንደሃይማኖት ሆኖ የቆየው ታሪክ ተረት መሆኑን የደረሱበት ከዘር፣ ከፖለቲካ ነጻ የሆኑ፣ ወንጌልን ከእውነት ጋር እንደ ዝናር የታጠቁ የለውጥ ሐዋርያት ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን አፍርታለች። ለውሸት ለጣኦት ለማንኛውም የሥጋ ሥራ ርኅራኄ የላቸውም፣ ለማፍረስና ለመሥራት፤ ለመንቀልና ለመትከል እግዚአብሔር ልኳቸዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ማሳመን ያቃታቸው፣ ለዘመናት ሲሰብኩት የኖሩት ተረት እየተናደ ከላያቸው ላይ የወደቀባቸው ቢጽ ሀሳውያን ግን በጩቤ መዋጋት ጀምረዋል። ሰይፋቸውን ወደ ሰገባቸው ከተው ወንጌልን እንዲቀበሉ፤ ኋላ ቀር የሆነውንና ሃይማኖትን የፖለቲካ መሣሪያ አድርጎ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ሲጎትት የኖረውን ተረት ተረት እንዲጥሉት ጥሪ እናቀርባለን። ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካን ማራመድ ብጥብጥን እንጂ ሰላምን አያመጣም።
 ተስፋ ነኝ     

24 comments:

 1. u are absolutly right,we Ethiopian will have to drop this stupid tales and turn our face to truth.
  God bless u the outher!

  ReplyDelete
 2. ተስፋ እውነትም ተስፋ እውነትን ለመመሥረት ተስፋፋ ማኅበር ተብዮውን ለመበተን ግፋ
  እውነት ትንሰራፋ ውሸት ትጥፋ የውሸቱ ማኅበር ወደ ከሊፋ

  ReplyDelete
 3. በመጀመሪያ መሥረቅን ምን አመጣው፡፡ ስለ ስርቆት መጥፎነት ማውራት ትታችሁ የተሰረቀው መቼ ነው ማን ሰረቀው ወዘተ ላይ ማተኮራችሁ አያሳዝንም፡፡ እንዲህ ከሆነማ አክሱም ጽዮን የተሰረቀ ዕቃ ማስቀመጫ ናት ማለት ነው. ከዚህስ መጽዳት አለባት፡፡

  ReplyDelete
 4. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ:ባትለጥፈዉም ላንተ ትምህርት ይሆንህ ዘንድ እጽፋለሁ።እንደት ያለ ዉሸት ነው የምትጽፈው ተስፋ!በመጀመሪያ ዕዝራ ካልዕ 15 ምእራፍ የለዉም እስከ 9 ምዕራፍ ነው ያለው የሌለ ምዕራፍ ቀጠልክ::ዕዝራ ሱትኤልም ሆነ ዕዝራ ካልዕ ታቦተ ጽዮን የሚል አልጻፉም።አንዳንዶች እየቀጣጠሉ እንደሚዋሹት የለለ ነገር እየጨማመርክ ዋሸህ።ጽዮን ጠፋች ነው የሚለው እዚህ ጽዮን ጠፋች ሲል ሀገሪቱን ጽዮንን እንጂ የለለ ነገር ጨምረህ ነገር ለማጣፈጥ ታቦት የሚል ጨምረህ ለምን ታምታታዋለህ።ጻድቁ ተክለ ሀይማኖት ጵጵስና እና ክህነት ከእነ ወገን እንዳይወጣ ብለዋል አልክ፤እኒያ የመረጧቸው 12 ተማሪዎቻቸው ዘራቸው ዉስጥ ነው ያሉት?ታሪክ የሚነግረን የግብጽ ጳጳስ ሲመጡ አስረክበው ወደ አገልግሎታቸው ሂዱ ነው የሚለው።አንተ ባታከብራቸውም የግብጽ ክርስቲያኖች በተ ክርስቲያን ሰረተዉላቸው የልደት መታሰቢአቸው በደንብ ያከብሩላቸዋል።በተጨማሪ ሥልጣንን ከአንዱ ወደ እግዚአብሐር ወደ ፈቀደው ማሸጋገር እኮ የነብዩ ሳሙእልም ሥራ ነበር።ከሳኦል ወደ ዳዊት ሥልጣን ሲተላለፍ እግዚአብሐር ለነብዩ ያለው ሳኦል ከሰማ እንዳይተናኮልህ በምሥጢር በጥበብ ሂደህ የእሲይን ልጅ ዳዊትን ቅባልኝ ነው ያለው።ተስፋ በአንተ አተረጓጎም ነብዩ ሳሙእልም ፖለቲከኛ ፖለቲካ ዉስጥ የገባ ሳኦልን አዉርዶ ዳዊትን የሾመ የመጀመሪያው ተክለ ሃይማኖት እሱ ነው በለዋ በነካ አፍህ።ሳሙእል የሰራዉን ሳኦል ቢያውቅ ኖሮ ምን እንደሚያደርገው ገምት።ይገለው ነበር፡ስለዚህ እግዚአብሐር በዘደ እንዲሀድ ነገረው።እንዳልከው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የይትባረክ ጦር ወይም ዘመድ ቢያገኛቸው ኖሮ፤እግራቸዉን ብቻ ቆርጦ እንደማይተዋቸው አንተም አይጠፋህም!ምክንያቱም አንተ እንዳልከው ለመንግሥቱ መወሰድ ዋነኛ ሰው ናቸውና።አየህ እንደት ያለ ትልቅ ዉሸትና ክህደት ዉስጥ እንዳለህ?ለላው ታቦተ ጽዮን ጋር ታቦተ ሚካእል አለመኖሩን በምን አረጋገጥክ?ታቦተ ጽዮንን የቀረጸ እኮ ሙሰ ነው፤ለላ ጽላት በተጨማሪ ቀርጾ እንደሆነስ ማን ያዉቃል?በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፈ ነገር ግን እነ ሙሰ ለሎች ነብያት የተናገሩት የሠሩት ስንት ነገር አለ መሰለህ?መጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ስላልተጻፈ ብለህ አፍህን ሞልተህ የለም ማለት አትችልም።ላለመኖሩ መረጃ የለህም።ንጉሱ ኢዮስያስ አባቱ ምናሰ በእግዚአብሐር በተ መቅደስ ጣኦት ሲያቆም ታቦት አለመኖሩን ግልጽ ነው።አንተ እንደፈጠርከው ተረት ካህናቱ ታቦቱን በበታቸው አስቀመጡት የሚል የትም ቦታ አልተጻፈም።ኢዮስያስ በተ መቅድሱን ካጸዳ በኋላ ታቦቱን አስቀምጡት አለ።እሱ ያልገባው ነገር ታቦቱ ያለ መስሎት ነው።ከሰሎሞን ዘመን በኋላ ሰለ ታቦተ ጽዮን መኖርና ሰለተደረገ በዓል የትም ቦታ አልተጻፈም፡ አሁን አንተ አምታተህ ከተረጎምካቸው ጥቅሶች ውጭ።እነዚም መልሰው የአንተን መሳሳት ነው የሚናገሩት፡እንጂ በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦቱ በበተ መቅደስ ተቀመጠ የሚል መረጃ እስቲ አምጣ ከቻልክ?የለህም እንጂ፤ነብዩ ኢርምያስም እስራእል ልብ ስለለላቸው ታቦቱን ረስተዉት እንደሚቀሩ፤እንደማያሳታዉሱት ተናገረ እንጂ።ታቦቱ ወደ ባቢሎን ተወሰደ አላለም።ይገርማል ለ10 ዓመት የተመራመረው እዉቁ ተመራማሪና ጋዘጠኛ ታቦቱ ያለው ኢትዮጵያ ዉስጥ ነው ብሎ ሲደመድም(ምንም እንኳ የዓመት አቆጣተር ከእኛ ጋር አንድ ባይሆንም) አንት ግን ፈጽሞ የለም አልክ።እጅግ ገረመኝ።ይህ ተልኮ የኢትዮጵያን በተክርስቲያን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን አገሪቱንም ለማዉደም ነው የተነሳችሁ ማለት ነው።ስለዚህ የጠቀስካቸው ጥቅሶች አራቦና ቆቦ ናቸው።አሁን አለተሳካልህም፤የማያነቡ መስሎህ ነው እንዲህ የዋሸህው አይደል።

  ReplyDelete
 5. Mk elements have planed to erradicate our true church fathers from earth surface by using of differnt tools such like kiling and abusing. But,through the power of God our true father and famous preacher like Megabe Hadis Begashaw will be winner.

  ReplyDelete
 6. yeah , we have to get rid off "the books of tales" and turn our face to the holly Bible which is the word of God. may God bless you all. Beretu

  ReplyDelete
 7. ሁላችንም ህጻን ልጅ ሆነን አድገን አሁን ካለንበት መድረሳችን እርግጥ ነው። ህጻናትን በተመለከተም ህጻናት ወንድሞችና እህቶችም ይኖሩን ይሆናል። ምናልባትም ህጻናት ልጆች ይኖረንም ይሆናል። ባይኖረን እንኳን ስለህጻናት ያለን እውቀት ትንሽ
  ጥያቄ ላቅርብላችሁ? ህጻናት ጡት የሚተዉት እንዴት ነው? ጡት የሚጠባ ህጻን ጡት ሲያጣ ወይም ጡት ሲከለክሉት እንዴት ያደርገዋል? መቼም እንደማይስቅና እንደማይፍለቀለቅ አናጣውም። ይነጫነጫል፣ያለቅሳል፤ በአቅሚቲ እናቱን ይቧጥጣል፣ጡት አምጪ ብሎ ይማታል ብንል እውነት ነው። ሲያገኝና ሲጠግብ ደግሞ ጤነኛ እስከሆነ ድረስ ይስቃል፣ይጫወታል። እንዲህ እንዲህ እያለ ሁለትና ሶስት ዓመት ሲሞላው ደግሞ ደግሞ ጡቱን ያስጥሉታል።አራትና አምስት ድረስ የሚጠባ ልጅ እንዳለ ሳይዘነጋ መሆኑን ልብ ይሏል? ጡት የምታስጥል የገጠር እናት ያንን የለመደውን ነገር ለማስጣል ከባድ ይሆንባታል። እንዲጠላው ለማድረግ እሬት ይቀቡታል። ይቆነጥጡታል። ሌላም ነገር እያደረጉ ይከለክሉታል። ይሁን እንጂ የህጻኑ ለቅሶ ሲበረታ ልምድ አደገኛ ነውና እንደገና ያጠቡታል። እንደዚያ እንደዚያ እያደረጉ ምግብ እያቀረቡ፣ጡት እየነፈጉ ከህጻንነት የጡት መጥባት ዓለም ያወጡታል።
  ጡትን ጥሎ እህልን የተካ ህጻን መቼም ጡትን ለተረኛው ይለቅ ይሆን እንጂ እርሱ ደግሞ አያገኘውም። ትልቅ ከሆነ በኋላ እንኳን ያንን የጠባሁትና የተውኩት የእናቴ ጡት ምስክር ይሁንብኝ ሲል መሃላውን «የእናቴን ጡት» ብሎ ይምልበት የለ!!
  ይህን ሁሉ ከላይ ያመጣሁት ያለምክንያት አይደለም። ነገሩ እንዲህ ነው።
  ትልቅ ሰው ማለትም ጎልማሳ ሰው ጡት ወይም የህጻናት ወተት ያስፈልገኛል! እኔ ህጻን ነኝ ቢል ምን ትሉታላችሁ?
  ይህ ማደግ የማይፈልግና ከህጻንነት የማይወጣ፣ ባለበት የሚረግጥ፤ የማይሻሻል ብንለው ይስማማዋል። የእግዚአብሔር ቃልን በለውጥና በእድገት የሚያሳይን ሰው ጳውሎስ እንዲህ ይለዋል።

  «ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም። ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና» ዕብ5፣12-13

  ለዚህም ማሳያ እንደህጻን ያንን የልምድ ጡት በመተው ወደ ወጣትነት ብስለት ከመሄድ ይልቅ እሬት የተቀባውን ጡት ላለመተው እንደህጻን እናስቸግራለን። አጥንት መጋጥና የአዋቂዎችን ምግብ መመገብ በሚገባን ወቅት የጽድቅን ቃል እንደማያውቅ ህጻን እናለቅሳለን። ጳውሎስ የተናገረው ለዛፍ ወይም ለተራራ ሳይሆን ትልልቆች ሆነው ዛሬም በጥንቱ ልምድና ባህል በመኖር ጽድቅን ለማወቅ ላልቻሉ ሰዎች ሁሉ ነውና ከሰዎቹ አንዱ ነን።
  ምሳሌ እናንሳ- ዙሐል ወር በገባ በ12 ቀን ይከበር ስለነበረና ህዝቡ ይህንን አደገኛ የቀን አከባበር ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ የሚካኤልን ታቦት አስገብቶ ለዙሐል ሲመጡ ሚካኤልን እንዲያከብሩበት ተደረገ ሲባል ለአዋቂና የጽድቅ ቃል የገባው የበሰለ ሰው፣አዎ ይላል እንጂ 12ኛው ቀን የዙሐል ነበር ግን አሁን ይህንን መናገር ልምዳችንን መሸርሸር ነውና ዝም በሉ! ቢል ምን ይባላል? እሬት የተቀባውን ጡት እየጠባ መኖር እንደሚፈልግ ህጻን መሆን ነው።

  ከሁሉም የሚያሳዝነው በእድሜ ትልቆች፤ በእውቀት ዛሬም እንደልጅነታችን ያልበሰልን መሆናችን የሚያሳዝነው ለህጻን አእምሮአችን የተነገረውን ሁሉ ይዘን ሌላ እውነት ቢነገረን ጆሮአችንን በእምቢታ መጠቅጠቃችን ነው።
  ወላዲተ ቃል ማርያም ታላላቅ ብርሃናትን ብቻዋን ፈጥራለች የሚል ድርሰትን ስህተት ነው ማለት ሲገባ ይህንን ከጽድቅ ቃል ጋር የሚጋጭ ነገር እንዲቆይ በመሟገት እሬት የተቀባውን ጡት እየጠባሁ በእውቀት ሳላድግ ልኑር ማለትን ምን ይሉታል?
  ማርያም የሚባል ጽላተሙሴ አልነበረም ቢባሉ አዎ አልነበረም፤ እግዚአብሔር የጻፈበት ጽላት 10ቱን ትእዛዛት ነው ማለት ሲገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ከተናገረው ይልቅ ጠላት በውስጣቸው ያስቀመጠውን ውሸት የሚያምኑ እነዚህ ምን ይባላሉ?
  እሬት የተቀባውን ጡት እየጠባ ለመኖር እንደሚፈልግ የማያድግ ልጅ መሆን ነው።
  አሁን ያለው የጽላት አሰራር መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፣ ቢባሉ ሙሴ አስመስለህ ቅረጽ ተብሏል ብለው ጠላት ያቀበላቸውን እሬት የተቀባውን ጡት ሊያጠቡን ይሻሉ። ሙሴ ቅረጽ ሲባል ወርዱ፤ቁመቱ፣ስፋቱ፣ብዛቱ ምን ነበር ሲባሉ የኦሪቱን ህግ ትተው የራሳቸውን ህግ ይነግሩናል። ይህንን ህግ እንዲያሻሽሉ የተነገራቸው ሳይኖርና በአንድ በኩል ህግንና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ብሏል እያሉ እያስተማሩ፣ እሬት የተቀባውን መልስ በማምጣት ስርዓት ሊሻሻል ይችላል ብለው የጠላትን ምክር ያቀርባሉ። እነዚህን የጽድቅ ቃል እውቀት የማያውቁ ሁልጊዜ ብስለት የሌለባቸውን ጳውሎስ ምን ይላቸዋል?«ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና» ዕብ5፣12-13
  ብዙው ትምህርታቸው ልምድ፤ ባህልና ትውፊት እንጂ የወንጌል መሰረትነት የለውም ተብሎ ማስረጃ ሲቀርብበት ለመደበቅና ለመሸፋፈን ሲታገሉ ስድብ፤ ጢቅ ማለት፣ መነጫነጭና ማልቀስ ብሎም ተሃድሶ በማለት ስም ማውጣት ይቀናቸዋል።

  «መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው»ዮሐ1፣18
  «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፥ እንደ ሥራህም ያለ የለም»መዝ 86፣8
  ይህንን ቃል ተቃውሞ ሥላሴን ለርስእክሙ፤ለዝክረ፤ስምክሙ፣....ለአፍንጫችሁ፣ለጥርሳችሁ፤ለጆሮአችሁ፤ ለሽንጣችሁ፤ለወገባችሁ፣ለጣታችሁ፣ለክርናችሁ ለምናችሁ፣ ለምናችሁ ወዘተ በማለት ሥላሴን ያዩ ይመስል ወይም ሰው እንደሚያስበው የአካል ክፍልና መጠን አበጅተው ለሥላሴ የአካል ብልት ማውጣት ምን ይሉታል? ከየት የተገኘ ትምህርት ነው? ማን ጻፈው? ማንስ አጸደቀው? በምን ተመዘነ? ምንስ ለማምጣት?

  «መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው»ዮሐ1፣18 ይህ እንግዲህ የጽድቅ ቃልን ለሚያውቁ አዋቂዎች የተነገረ ነው። እሬት የተቀባ የጡት ወተትን አንተውም የሚሉ የቃል ህጻናት ዛሬም በእምቢታቸው እንደጸኑ የሥላሴን ጆሮና አፍንጫ ሳያዩ አይተናል በማለት ጽፈው ለአፍንጫችሁ፣ ለጥርሳችሁ እያሉ ይደግማሉ፣ ያስደግማሉ። ስህተቱ ሲነገራቸው አይሰሙም። ለመስማትም በፍጹም አይሹም። ሲነገራቸው ከኖሩበት ውጪ ግራና ቀኝ ማየት አይፈልጉም።
  «ሐዋርያትም ጌታን። እምነት ጨምርልን አሉት»ሉቃ17፣5
  እባካችሁ የትኛውንም ከመጥላትና ከሸሽ በፊት እንደእግዚአብሔር ቃል መርምሩ! ግራና ቀኝ እዩ!! አዋቂዎች ሆናችሁ አጥንት ለመጋጥ በሚያበቃችሁ እድሜ ላይ እሬት የተቀባውን ጡት በመጥባት አትኑሩ!!!!!

  ReplyDelete
 8. All we have to trust is the Holy Bible and read please Hebrews 9 for now. God bless you. Bravo Aba Selama.

  ReplyDelete
 9. እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ ላልከው anonymous ---------

  በእውነትም እግዚአብሔር ምህረቱን ቸርነቱን ያውርድልህ!!
  ስህተት ያገኘህና ያልተጻፈውን በሀሰት ያስነበበህ መስሎህ «ተስፋ»የተባለውን ጸሐፊ ለመሟገትና እንደው አንድ ነገር ጠብ ያለልህ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሃል!!
  በዚህ እኔ በማቀርብልህ የተስተካከለ ማስረጃ እንደማታምን አውቃለሁ። የማያልቀውን ምክንያት ታመጣ ይሆናል። እውነቱ ግን ተጽፏል። እንዲህ ሲል --
  መጽሐፈ እዝራ ካልዕ ምዕራፍ 1 ቁጥር 54 ላይ «እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱን፣ ጥቃቅኑንና ታላላቁን ዕቃ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርንም ማደሪያ ታቦትንም፣ ከቤተ መንግሥት ዕቃ ቤት ያለውን ሳጥኑንም ሁሉ ማርከው ወደባቢሎን ወሰዱ» በማለት ጽፎት ይገኛል።
  «ከሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ጽዮንም እንደጠፋች ቀረች፣ ወደባቢሎንም ተወሰደች» የሚለው የእዝራ ሱቱኤል 9፣23 አንተ ጽዮን የምትባለው ሀገር ናት ብለህ የሌለ ነገር በውሸት ለመኖር ትሞክራለህ። ባቢሎን የወረደችው ጽዮን የምትባለዋ ሀገር ናት? የማይሰማ የለም። ንጉሥ ዳዊት በኬብሮን 7 ዓመት ነግሶ ሳለ ኢያቡሳውያን ከኢያቡስ ከተማ እየተነሱ በመውጋት ስላስቸገሩት ሊያጠፋቸው ጦር አስከተተ።(ኢያቡስ የኢየሩሳሌም የቀድሞ ስሟ ነው) በውጊያውም አሸንፎ አምባውን ያዘ። ያችም አምባ ጽዮን ናት። «ነገር ግን ዳዊት አምባይቱን ጽዮንን ያዘ፥ እርስዋም የዳዊት ከተማ ናት» 2ኛ ሳሙ 5፣7 ጽዮን ማለት እንግዲህ ይህች ናት። ይህች አምባ (ኮረብታ) ናት ወደ ባቢሎን የተማረከችና የሄደችው?
  ይህንን የሚል የሀሰት አባት ልጅ ብቻ ነው። ጽዮን ማለት ዳዊት በጦር የያዛት ከተማ ናት። በምእራብ የሄኖን ሸለቆ፣ በሰሜን የኢየሩሳሌም ከተማ፣በደቡብ የግዮን ምንጭ፣ በምስራቅ የቄድሮን ሸለቆ የሚያዋስናት ጽዮን ተራራ ዛሬም አለች። ባቢሎን አልሄደችም፣አልተመለሰችምም። ዳዊት የጽዮንን ተራራ ከያዘ በኋላ «የእግዚአብሔርንም ታቦት አገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ በስፍራው አኖሩት ዳዊትም የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ» 2ኛ ሳሙ 6፣17 የእግዚአብሔር ታቦት በጽዮን የዳዊት ከተማ ከአቢዳራ ቤት ወጥታ ከገባች በኋላ በጽዮን ተራራ፣ ታቦቲቱም ታቦተ ጽዮን ተባለች። ዳዊት ጽዮንን ከያዘ ተረጋጋ፣ ጠላቶቹን ሁሉ አሸነፈ፣ ገዢ መሬት ላይ ሆኖ ሁሉን ተቆጣጠረ። በመዝሙሩም እንዲህ ሲል አመሰገነ። «በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው»መዝ 125፣1 ልጁ ሰሎሞን ቤተመቅደሱን ካሰራ በኋላ ወደኢየሩሳሌም ቤተመቅደስ ወስዶ ታቦተ ጽዮንን አስገብቷል። ቤተመቅደሱ ከጽዮን ኮረብታ ግማሽ ኪሎሜትር ቢርቅ ነው። ኢየሩሳሌምንም ዳዊት ከገበሬው ከኦርና ላይ «ዳዊትም ስለ ስፍራው ስድስት መቶ ሰቅል ወርቅ በሚዛን ለኦርና ሰጠው» 1ኛ ዜና 21፣25 የታቦተ ጽዮን ትንሹ ታሪክ ይህ ነው። ቤተመቅደሱን ናቡከደነጾር ሲደመሰስ ሁሉንም ንዋየ ቅድሳት ዘርፏል። እዝራ ሱቱኤልም መስክሯል። 2ኛ እዝራ1፣54
  በሌላ መልኩም ውሸትና ፈጠራዊ ድርሰት ልምዱ የሆነው ሰይጣን ሙሴ ተጨማሪ ጽላቶችንስ ቀርጾ ቢሆንስ ሊለን ይፈልጋል። እንደገናም ኢዮስያስን ታቦቱን አኑሩት- በ2ኛ ዜና 35፣3«እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ አኑሩት ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ» ያለውን ቃል በትክክል ያለ መስሎት ነው ይህንን የተናገረው የሚሉ የዘመናችን ሰዎች እብደት ነው ከሁሉም የሚገርመው። መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረው ውሸትና እነዚህ ሰዎች ፈጥረው የሚናገሩት እውነት የሚሆነው በምን ስሌት ነው? ይህ ሊሆን የሚችለው በሀሰት አባት ሚዛን ብቻ ነው። እኛ ግን ከተጻፈው ውጪ ለመናገር ቀርቶ ለማሰብ(ሎቱ ስብሐት)እንላለን።
  ስለሸዋው ተክልዬ ብዙ መዘርዘር አልፈልግም፤ ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እውነቱን ዘርዝረው ስለጻፉ ያንን ማንበብ ይጠቅማል። ግብጾች አከበሩ፤ በማለትም ማስረጃ ለማጠናከር መሞከር ከንቱ ድካም ነው። በቁጥር ከሆነ እስልምና ከ1 ቢሊዮን በላይ ይሆናል። ስለበዙ ግን እውነት እዚያ ነው ያለው ማለት አይደለም።
  እውነቱን የሚቀበሉ ስላነሱና ውሸቱን የሚያምኑ ስለበዙ ውሸቱ እውነት አይሆንም።
  ይልቁንም በጠባቡ መንገድ የሚገቡት ጥቂቶች ናቸው።
  «በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው»ማቴ 7፣13

  ReplyDelete
 10. ለዐዕወውረሩ ጸሀፈፊ ለተሰስፈፋ፡-
  ጨለማ ሆንክ እንጂ ምኑን ተስፋ ሆንከው
  የተሳካ መስሎህ ብዙ የደከምከው
  በሆድህ ተታለህ የዲያብሎስ ባራያ የሆንከው
  አንተን የገለጠህ ስም ሳይሆን ስራህ ነው

  ReplyDelete
 11. This piece is full of hate against EOTC. Even if I believe that there are mistakes that need to be corrected at EOTC, I cannot follow guys who are filled with nothing but hate.

  Whether we have the original ark of the covenant or not, it does not matter. Why duel so much on an issue that is irrelevant for our lives?

  Tesfa is a non-believer in the power of God. We know God does miracles all the time. What is the surprise for Him to grow angle wings for St. TekleHaimanot? In the Bible, it is written that God took Elias to heaven on the chariots of angles. It is believed that he is still alive in body and soul in heaven. Do you believe that? If so, what makes you doubt the miracles done to St. TekleHaimanot?

  ReplyDelete
 12. pls this is YEPENTA [PROTESTANT WEB NEW....
  LALSEMA ASEMU!

  ReplyDelete
 13. እነሆ የዘንዶው የስድብ አፍ በዚህ አለ።

  ReplyDelete
 14. Nathan, let me tell you something,our generation is not reading Bible, we all need a short cut to be blessed. we forgot our lord Jesus, the dispels did not telling us to read other books, only the holly Bible. I am gonna ask any one of you who got mad about this writer (Tesfa), the question is if this writer (Tesfa) said Eyasuse amalagenew are going to mad? , you would not say any thing , in short you have little knowledge about bible. Brother and sister be Orthodox not protestant, a true orthodox christian read bible and based his or her spiritual life on that not by tert tert book. please Abatachen Abone tekelehamanot does not like all this false statement about him.
  JESUS IS LORD!

  ReplyDelete
 15. አሁንም ተስፋ አልጨምርም (ሎቱ ስብሐት) ካልክ በኋላ ጨምርሀል።"ታቦት እና ወደ ባቢሎን ተወሰደች" የሚሉ ሳይኖሩ አንተ ሀሰትህን ለማብራራት ከጽዮን ስም ጎን ታቦት የሚል ጨመርክ።ክብሯ ወጣ የሚለውን አንተ በተለመደው የማጣመም ስልትህ ወደ ባቢሎን ተወሰደች አልክ።ይህ ነው ክህደት።በክብረ ነገስት ጽላት አመጡ አለ እንጂ በአራት ለዋውያን የሚሸከሙትን ታቦት አመጡ አላለም።2ኛ ዕዝራ ያለው በባስለእል የተሠራው 3 ክንድ ከስንዝር የሚሆነው ታቦት ተወሰደ።በሙሰ የተቀረጸው ጽላት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መጣ።ችግሩ የታቦቱንና የጽላትን ልዩነት አለማወቅህ ነው።ይህ ጽሑፍህ ብርሀን መሆንህን ሳይሆን ጨላማ አሰተሳሰብህን ያሳያል።

  ReplyDelete
 16. ትዕግስት ያቀረብሽውን ሃሳብ እኔም እጋራለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ሃሳብ እኛን በልጁ በኢየሱስ በኩል ማዳን ነው፡፡ የቅዱሳንና የጻድቃን አባቶቻችን ጸሎት ደግሞ እነርሱ በክርስቶስ አምነው መልካም ፍሬ አፍርተው ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንደተሰበሰቡ እኛም የእነሱን መንገድ እንድንከተል ወደ ክርስቶስ ያመለክቱናል፡፡ ምክንያቱም እነርሱም የጸደቁት የክርስቶስን ጽድቅ ተሸፍነው እንጂ ማንም በራሱ የጸደቀ የለም፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እየታገዝን ብናነብ በቂ ነው፡፡ በተረፈ የቀደሙት አባቶቻችን ክርስቶስን የተከተሉት እኛ አሁን የጭቅጭቅ ርዕስ እንድናደርጋቸው አይደለም፡፡ የእነሱም ሃሳብ እኛ ክብር እንድንሰጣቸው ሳይሆን በሰማይ የተዘጋጀላቸውን የክብር አክሊል ለመቀዳጀት ነው፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የእግዚአብሔር ያልሆነውን ትተን እንደ ሃሳቡና ፈቃዱ ወደ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ እንቅረብ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳን!!

  ReplyDelete
 17. Missssssssssss Tigist NO SHORT CUT to join the heaven.

  ReplyDelete
 18. As I understand Pente or protestant undermine Jesus Christ power, I have not seen any problem with web site, the are not protestant, they are telling the truth how our church is messed up by debetera and tert tert books. our church is in the wrong direction believe it or not. I don't have any personal relation with the owner or group of this web site, I see some weakness on this web site, I believe they will improve it.
  we need a God dispels, a true orthodox teaching us the holly bible. I proudly ask the any one who based his life knows a bible to teach us the holly bible on this web site, specifically the the "Heberw message." Thank you guys, I am a true orthodox christian based my life by bible not by tert tert. JESUS IS LORD!!!

  ReplyDelete
 19. Thank you, the about comment. That is what the bible telling be the same as the saint , did not telling us to worship those saint. that is absolutely unacceptable, we have a father, a brother , a creator Jesus Christ to worship. please let us take out our church from the dark! i have a great testimony how Jesus Christ is working in my life. Jesus is living in our church , if you want to find , you will get him. you know how hide him, DEBETRA! yes, Debetera hide our lord Jesus, our eye is blind to see our Jesus Christ, at the same time if you do not have him, our mother Dengel Mariam will not be your mother.
  God bless our church! do not insult each other!

  ReplyDelete
 20. ታቦት የጽላቱ ማደሪያ ነው። ታቦት በሌለበት ጽላት የለም። ቅድስተ ቅዱሳን የሚባል የለም። ታቦት ከሌለ የሥርየት መክደኛው፣ ሁለቱ ኪሩብ የሉም። ይህ ሁሉ በሌለበት እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚያስተላልፈው መልእክት የለም። ዘጸ 25፣22«በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ» ያለታቦት የተቀመጠ ጽላት በእስራኤል ምድር አልነበረም። በታቦቱ ጽላቱ፣ በጽላቱ ታቦቱን መጥራት የነበረ ነው። ዛሬስ የሚካኤል ታቦት ከበረ ይባል የለ?፣ የገብርኤል ታቦት ይነግሳል እየተባለ መነገሩ ጽላቱን መናገሩ ነው። በአጭሩ የኦሪቱ ጽሌ ያለታቦት አልነበረም። አለ ወይም ነበረ የምትል ከሆነ አንተ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዓለም ውጪ ነህ ማለት ይቻላል።
  ባቢሎን በምርኮ የሄደው ታቦቱ እንጂ ጽላቶቹ አይደሉም እያልክ ነው? ወይስ ታቦቱም ጽላቱም አልሄዱም ነው የምትለው? የምትለውን እንኳን እኔ አንተም ራስህ የምታውቀው አይመስለኝም።
  አክሱም የሙሴ ጽላት አለች ተብሎ እንደሚታመን ይታወቃል። ደብተራ ገለፈቶች ጽላቱ አክሱም ስለመኖሩ ከሚናገሩት የተረት ታሪኮች ይልቅ ግራሃም ሀንኩክ ያደረገው ጥናት ስለመኖሯ ሚዛን የሚደፋ መሆኑን ለመጠቆም እውዳለሁ።
  ይህን ጽላትና ታቦትን አለያይቶ የሚያኖረውን ሰው ጥቂት ልጠይቀው? አክሱም ጽዮን ሲባል ሰምተህ ታውቃለህ? አክሱም ጽዮን የተባለችው በዳዊት ከተማ በጽዮን ተራራ ተቀምጣ የነበረችው የሙሴ ጽላት አክሱም ስላለች ያንን የጥንት ስሟን እያነሱ መሆኑን አታውቅም? አክሱም አለ የምትለው ጽላት ያለማደሪያው ታቦት ነው መጣ የምትለው? ምኑ ግራ የገባህ ሰው ነህ?
  የኔን ጽሁፍ ተወት አድርግና ሂድና መምህራኖችህን ጠይቅ! ከዚያ መጥተህ የበሰለ መልስ መስጠት የሚችል እውቀት ይኖርሃል? እዝራ ሱቱኤል ከ9 ምእራፍ በላይ የለውም፤ታቦቱ ወደባቢሎን አልተማረከችም አልክ፣ ጸሐፊውን ተስፋን ውሸታም አልክ። እኔ ብርሃን ደግሞ ዓይንህ እንዲበራ እዝራ ሱቱኤል ካልዕ 1፣54 እና እዝራ ሱቱኤል 9፣23 --2ኛ ዜና35፣3 በደንብ አንብበህ መጽሐፉ ምን እያለና ስለምን እየተናገረ ብትፈልግ መጽሐፉን ተቃውመህ፣ ካሻህም የመሰለህን ማብራሪያ ሰጥተህ እኔ እየጠቀስኩና የሚያስረዳልኝን መረጃ እንዳቀረብኩት ማቅረብ ሲያቅትህ የደብተራ ገለፈትን መጽሐፍ ክብረ ነገሥትን ጠቀስክ። መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነው ትክክል ወይስ የደብተራ ገለፈት ክብረ ነገሥት?
  የመጽሐፍ ቅዱሱን ቃል ጣል ጣል፣ ሸረፍ ሸረፍ፣ አንድም፣ አንድም እያሉ አዳክሞ የደብተራ ገለፈትን መጽሐፎችን ግን አጥብቆ በመያዝ ለማስረጃነት መጠቀም እብደት ነው። ያለእውቀት የሚነገረው ሁሉ ልፋት ነው። ኢዮ 38፣2 ያለ እውቀት በሚነገር ቃል ምክርን የሚያጨልም ይህ ማነው?

  ReplyDelete
 21. ቤተ ክርስቲያን መልስ አላት
  READ IN PDF
  በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለያዩ ዘመናት አያሌ መናፍቃን ተነስተው ነበረ:: ከአርዮስ ጀምሮ ብዙ መናፍቃን በክህደታቸው ምክንያት ሊቃውንቱ ከቤተ ክርስቲያን አውግዘው ለይተዋቸዋል:: አውግዞ መለየትም ብቻ ሳይሆን መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥቶባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ለመናፍቃን መልስ የሚሰጡ ሊቃውንትን አፍርታለች:: ቤተ ክርስቲያን ምልዑ ናት የሚባለው ለዚህም ነው::

  አሁን በእኛ ዘመን ተረፈ አርዮሳውያን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ሳይረዱ፤ ነገር ግን ግዕዝ ስለተናገሩ ብቻ ሁሉንም ነገር እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ተነስተዋል:: ለምሳሌ “አባ ሰላማ” የተባለው ብሎግ ማየት በቂ ምስክር ነው:: ይህ ብሎግ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረው ነገረ እግዚአብሔርን ይቃወማል:: የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት አይቀበልም፤ ነገር ግን የተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነ እያስመሰለ ሲያጭበረብር ይታያል:: የቅዱሳን ገድል እና የቅዱሳን መላእክት ድርሳን የሚተቸው የዘመናችን ተረፈ አርዮሳዊው ለ“አባ ሰላማ” ብሎግ መልስ የሚሆን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተመርጉዘው መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው እንደ ሊቃውንቱ አባቶቻቸው ጦምረዋል:: ይህንን በመጫን ያንብቡ CLICK HERE TO READ
  መልካም ንባብ::

  ReplyDelete
 22. huwey gud!Sewoch min nekachihu! PenTe mender gebtachihu kirikir gize lemabaken kalhone waga yelewum. PenTe meche zemisema joro alew? ''Geta geta ...' kemalet lela minim yemireba neger yelachewum.

  Egziabher tewahedoawyanin yiTebiqilin!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክርስትናን ተገን አድርገው ህዝቡን ለዘመናት እያሳሳቱ የኖሩትን የደብተራዎቻችን ተረቶችን በደንብ ስለሰማኮ ነው ይህንን በመጽሐፍ ቅዱስ የተደገፈ በቂ መልስ እየሰጠ ያለው ::ዴሞክራሲን ያልተረዱ አምባገነናዊ መንግስታት ተቃዋሚዎቻቸውን በሙሉ በአሸባሪነት እንደሚፈርጇቸው መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው የማያውቁ ምዕመኖቻችን ትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል ሲነገራቸው ይህማ መናፍቅ ነው ብለው በፔንጤነት ይፈርጁታል:: ፔንጤ ይሁን ሌላ ስለማንነቱ ሳትጨነቅ ለተነገረህ ነገር በማስረጃ አስደግፈህ ትክክለኛውን መልስ ለመስጠት ሞክር

   Delete
 23. አንዲት ተዋህዶJanuary 31, 2012 at 10:31 PM

  እባካችሁ ንጹሃን የተዋህዶ ልጆች ይህ እኮ እነ ማርቲን ሉተር በ16ኛው ክ_ዘመን ኑፋቄያቸውን ሲያስፋፉ አንድ በአንድ የተጠቀሙበት ዘዴ ነው(except this one is applied online) "ቅዱሳንን መሳደብ (መላዕክትንና እመቤታችንን ጨምሮ) ፣የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናና ትውፊቶችን ማዋረድ፣ የህብረተሰብን ባህል ፡ወግና ስርዓት ማንቋሸሽ(እንደ እነሱ አስተሳሰብና ምኞት ቢሆን ኖሮማ በጠንካራና ድንቅ ባህሏ ከራሷ አልፋ ለጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነችው ሃገራችን ኢትዮጵያም ከካርታ ላይ ትጠፋ ነበር፡ አትድከሙ ይህን ብዙዎች ሞክረውት በእግዚአብሄር አምላክ ቸርነትና ጥበቃ እንዲሁም በማይበገሩት አባቶቻችን ብልህነትና አይበገሬነት በድል ተወጥተነዋል፥ ትልቁ ድክመታችን ድህነታችን ነው እርሱንም ጠንክረን በመስራት ከሃገራችን እንደምናስወግድ ተስፋ አለኝ ፣ መጽሃፍ ቅዱስን አዋቂ በመምሰልና ስለእያንዳንዱ ሃይማኖታዊ ወግና ስርዓት በቂ ዕውቀት የሌለውን ምዕመን የቤተ ክርስቲያኒቷን አካሄድ ከግለሰቦች ፍላጎትና የፖለቲካ ጥያቄ ጋር በማገናኘትና በማደናበር ሌላ የተሻለመንገድ በመከተል እንደሚድን መጎትጎት ... ወዘተ :: ደግሞ ይህ ሁሉ ሲፈጸም የሌላ እምነትና ኑፋቄ አቀንቃኝ መሆናቸውን በመሸፈን የቀጥተኛዋ መንገድ(ኦርቶዶክስ ተዋህዶ) ተከታይ እንደሆኑ በተቆርቋሪነት መንፈስ በመስበክ የሃሰት ደቀመዘሙራትን ማብዛት፥ በነገራችን ላይ ማርቲን ሉተር ለ10 አመታት ያህል ፕሮቴስታንትነቱን protestantism ሳያውጅ ነበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ስር ስርዓት ተዛብቷል እኔ መፍትሄ አለኝ ሲል የቆየው እርሱ እንኳን ግን የዘመናችንን መናፍቃንን ያህል ጻድቃንን በድፍረት አላንቋሸሸም:: ወገኖቼ እነዚህ ሰዎችም እያንዳንዱን የማርቲን ሉተር ታክቲክና አካሄድ ቤተ ክርስቲያናችንን ለማፈራረስ እየተጠቀሙ ስለመሆኑ በፍጹም አትጠራጠሩ ቀኑ ሲደርስም ማንነታቸውን በይፋ እንደሚያውጁ አልጠራጠርም ማርቲን ሉተርም ሆነ እንደነ ዳርዊን ያሉ አሳሳቾች ግን በመጨረሻ የእድሜ ዘመናቸው ተፀፅተው በንስሃ የፃፏቸው መፃህፍት አሉና እውነትን የሚሻ የተዋህዶ ልጅ አስገራሚውን "በየዘመኑ የሚነሳ ጥራዝ ነጠቅ ክህደት" አንብቦ ይረዳው:: በዚህም ዙሪያ ፍላጎቱ ያላችሁ ወገኖች ያሉኝን መፃህፍትና የንባብ ጥቆማዎች ለማካፈል ዝግጁ እንደሆንኩ ለመጥቀስ እወዳለሁ::
  ስለ እነዚህ ሰዎች (አባ ሰላማ እና መሰሎቻቸው)ማንነት በቀላሉ ለማወቅ በቅድሚያ የማርቲን ሉተርን አነሳስና የተጠቀመባቸውን ዘዴዎች ማንበቡ ብቻ በቂ ነው ይንንም እንድታደርጉ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆችን በአክብሮት እጠይቃለሁ:: በተረፈ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለእያንዳንዱ የፕሮቴስታንታዊም ሆነ ሌሎች መናፍቃዊ ጥያቄዎቻችሁ መልስ አላት፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከነዚህ ውገኖች ውስጥ ራሳችሁን በማይሆን ጥርጣሬ ውስጥ ያገኛችሁ ሰዎች ክህደትን ተሸክማችሁና ጠፍታችሁ ሌሎችንም ከማሳሳታችሁ በፊት ብትወዱ ይህን ወንድማዊ ምክሬን ስሙኝ:_
  1) በሃገር ውስጥ በከተሞች አካባቢ የምትገኙ ምዕመናን፣ በተለይም ይህ የኑፋቄ ትምህርት በተለያየ መንገድ ያወካችሁ ወጣቶች ወንድሞቼና እህቶቼ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በመደበኛነት የሚሰጠውን የኮርስ ትምህርት በመከታተል ለእያንዳንዱ ለተፈጠረባችሁ የጥርጣሬ ጥያቄ ልክ እንደእኔ ያለምንም መሸማቀቅ በመጠየቅ መልስ ማግኘት ትችላላችሁ ያኔ እውነተኛ የሆነው ጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምን ያህል በተዋህዶ እምነታችን እንደሚሰበክ፣
  እርሱም የማይናወጥ የእምነታችን መሰረት እንደሆነና እያንዳንዱ አባቶቻችን በትውፊት ያወረሱን ክርስቲያናዊ ስርዓታችንም መጽሃፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ትረዳላችሁ እናንተም በኩራት ለልጆቻችሁ ታስተምራላችሁ ::
  2) ከሃገር ውጭ በተለያየ የዓለማችን ክፍል የምትገኙ ወገኖችም በቅርቡ እውነተኛውንና ጌታ በደሙ የዋጃት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት በቅርቡ በኢንተርኔት online program ለመጀመር ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ በመሆኑ ደረታችሁን ነፍታችሁ ለእያንዳንዱ የመናፍቃን ጥያቄ ከበቂ በላይ መልስ እንደምትሰጡ ከራሴ የህይወት ተሞክሮ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ (በነገራችን ላይ እኔም የማያባሩ ጥያቄዎችና ጥርጣሬዎች ከዩኒቨርስቲ ህይወቴ ጀምሮ በአምሮዬ ይመላለሱ ነበር) እስከዚያው ግን እውነተኛ የተዋህዶ መምህራን የሚያስተምሩትን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ከተለያዩ ብሎጎችና ዌብሳይቶች በጥንቃቄ መርምራችሁ እንድትከታተሉ አደራ እላለሁ::
  በመጨረሻም ረቂቅ የሆነውን ሚስጥረ ስላሴ ሳይገነዘቡ መፅሃፍቅዱስ ጥቅስ ስለመዘዙ ብቻ እውነተኛውን እየሱስ ክርስቶስ ለማወቅ ይቻላል ብሎ ማሰብ ትርፉ መጨረሻ
  በሌለው የክህደት ቀለበት ውስጥ ሲሽከረከሩ መኖር ነው :: ለዚህም ማስረጃ በአለማችን በሺዎች የሚቆጠሩ መናፍቃዊ ሃይማኖቶችበየቀኑ መፈልፈላቸው ነው ፡ መፅሃፍቅዱስ ስለገለፁና የክርስቶስን ስም ስለጠሩ ብቻ እውነትና ድህነትን አገኘን በማለት የቀደሙት ታላላቅ አባቶችን ማንቋሸሽ (መችም ባዶ አፍን መክፈት እንደሌሎች የአህዛብ እምነቶች ስርዓት አይከለከልምና) የራሳቸውን ፅድቅ የሚያበዙ የሚመስላቸው ሁሉ የክህደትና የአላዋቂ ድፍረት ምላሳቸውን በፃድቃን ላይ ይመዛሉ ዳሩ ግን "እርሱ ያከበረውን ማን ይቃወመዋል ?" ተብሎ እንደተፃፈ እወቁ

  መዝ 31፥18
  በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።

  ReplyDelete