Tuesday, November 29, 2011

የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቷል ዘፍ 18፥20 - - - Read PDF

ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም።ጌቶቼ ሆይ፥ ወደ ባሪያችሁ ቤት አቅኑ፥ ከዚያም እደሩ፥ እግራችሁንም ታጠቡ፤ ነገ ማልዳችሁም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ። እነርሱም። በአደባባዩ እናድራለን እንጂ፥ አይሆንም አሉት። እጅግም ዘበዘባቸው፤ ወደ እርሱም አቀኑ፥ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ማዕድ አቀረበላቸው፥ ቂጣንም ጋገረ እነርሱም በሉ። ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት። በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው። ሎጥም ወደ እነርሱ ወደ ደጅ ወጣ መዝጊያውንም በኋላው ዘጋው፤ እንዲህም አለ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ፤ እነሆ፥ ወንድን ያላወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁ፥ እንደ ወደዳችሁም አድርጓቸው፤ በእነዚህ ሰዎች ብቻ ምንም አታድርጉ፥ እነርሱ በጣራዬ ጥላ ሥር ገብተዋልና። እነርሱም። ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ። ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፤ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ። ሁለቱም ሰዎች እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት ዘፍ 191-10

ብቸኛው የእግዚአብሔር ሰው ሎጥ፤ እራሱን እና ቤተ ሰቡን በጊዜው ከነበረው ርኩሰት በመጠበቅ ከሚመጣው የጥፋት እሳት እራሱን አድኗል። አስቀድሞ ከአብርሃም ጋር በነበረበት ጊዜ ሣርና ውሃን በማየቱ የመረጣት ሰዶም ገሞራ ወደ አመድ እንደምትቀየር አላወቀም ነበር። መንፈሳዊ ዓይኑ አልበራለትምና ለበጎቹና ለከብቶቹ የሚሆነውን ጥቅም እንጂ በሰዶም ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ባዶነት አልተመለከተም። «ሎጥም ዓይኑን አነሣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም አገር ሁሉ ውሃ የሞላበት መሆኑን አየ እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ዞዓር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነት በግብጽ ምድር አምሳል ነበረ» ይላል ቃሉ ዘፍ 1310
የሎጥ አጎት አብርሃም ግን አይኑ የተገለጠለት በመሆኑ እግዚአብሔር ያየለትን ብቻ አየ። ሎጥ ራሱ ወደ አየው አገር ሲሄድ አብርሃም ግን በዚያው ባገሩ በድንኳን መቆየትን መረጠ «እኔ ወደ ማሳይህ ምድር ሂድ» ተብሏልና። እግዚአብሔር ያየልንን ማየት ምንኛ መታደል ነው? እኛ ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር ያየልንን እንድናይ የምዕራባውያንን ሣርና ውሃ ተመልክተን ማንነታችንን እንዳንለቅ እማጸናለሁ።

  ሎጥ እራሱ ለጊዜው ወዳአየው ሣርና ውሃ በራሱ ፈቃድ ከብዙ ሃብት ጋር ሄዶ ባዶ እጁን፣ የልጅነት ሚስቱን እንኳ አጥቶ እንደወጣ የጌታ መንግሥት የታሪክ መጽሐፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ለሳርና ለውሃ ሲባል ባዶ ወደሆነ ሕይወት መሄድ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ሰውን ልዩ ክብር የሚያጎናጽፈው ያለው ሀብትና ንብረት ክብርና ዝና ሳይሆን በመንፈሱ የሞላው ሞራል ወይም ሕሊና የሚባለው ነገር ነው። ቅዱሱ አምላክ የማይስማማበት ሐሳብና ድርጊት ሁሉ እሳትን እንደሚጠራ የዓለምን ታሪክ በማጥናት መገንዝብ ይቻላል።

 እኛ ክርስቲያኖች ከሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ድነናል። ይህን እውነት ልባችንን ሞልተን ለመናገር ያበቃን ደሙ ሕሊናችንን ከኃጢአት ስላነጻው ነው። እግዚአብሔር የሚጸየፈውን ሁሉ እንጸየፋለን። እግዚአብሔርን ስለምንወድ ዓለምን እንጠላለን። ሐስትን ስንሰማ የተበከለ ምግብ እንደበላ ሰው ውስጣችን ይረበሻል፤ በመንግሥታትና በዚህ ዓለም አደጋ ጣዮች ፊት ለእግዚአብሔር ክብር ለመቆም ሙሉ ልብ በክርስቶስ አግኝተናል፤ እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን እንድናመክከው ከሞተ ሣራ ሕሊናችንን አንጽቶታል። «በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?» ይላል ቃሉ ዕብ 914
 ሐዋርያው «ከፉ ከሆነው ካሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን እራሱን ሰጠ» እንዳለ ገላ 14 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያዳነን ክፉ ከሆነው ካሁኑ ዓለም ነው። ከረሃብ፣ ከጦርነት፣ ከስደት፣ ከመከራ፣ ማለት አይደለም፤ እነዚህማ በሕየወታችን ይፈጸሙ ዘንድ ግድ ነው። ከሐሰት ሥራ ከገንዘብ ፍቅር፣ ከስግብግብነት፣ ከሌብነት ከዝሙት ከጣኦት አምልኮ፣ ካድር ባይነት አዳነን ማለት ነው እንጂ። ከነዚህ ክፋቶች ያልዳነ ነገር ግን ክርስቲያን ነኝ እያለ የሚያወራ በየትኛው ሥልጣን ወይም ማዕረግ ላይ ይሁን ከእግዚአብሔር ፍርድ አያመልጥም። ቃሉ የሚለው ድሮ እንዲህ ነበራችሁ አሁን እንዲህ ሆናችኋል ነው
«ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል» 1ቆሮ 69-11

   አዎ በፊት እንዲህ ነበራችሁ አሁን ለዚህ ክፉ ኃጢአት ይገዛ የነበረው ሕሊናችሁ በክርስቶስ ደም ታጥቧል፤ ስለ ታጠበ ተቀድሳችኋል፤ ስለተቀደሳችሁ ጸድቃችኋል ይለናል። ይህ ቃል የሚያስተላልፈው መልዕክት ክፉ ከሆነው ካሁኑ ዓለም ነጻ ለወጡ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንጂ፤ ዛሬም በዚያው ኃጢአት ላይ እያሉ በክርስቶስ ነጻ ወጥተናል እያሉ ራሳቸውን ለሚያታልሉ የስም ክርስቲያኖች አይደለም። አሁንም በዚህ ክፉ ዓለም [ኃጢአት] ተይዛችሁ ለምትሰቃዩ ሁሉ ወደ ክርስቶስ እንድትመጡና ከሸክማችሁ እንድታርፉ እንማጸናለን።

 ዛሬ ይህን ለመጻፍ ያነሣሣኝ ዋና ጉዳይ በአዲስ አበባ የግብረ ሰዶም ጉባኤ እንደሚካሄድ ከሰማሁና የሃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች ምንም ጉዳይ ሳይሰጣቸው እንደቀረ ስለሰማሁ ነው።  የሀገራችን መንግሥት የኢኮኖሚ ችግር ያለበት መሆኑን እረዳለሁ፤ የሚያደርጋቸው የልማት እንቅስቃሴዎችን የገንዘብ አቅም ባይኖረኝም በጸሎቴ አግዛለሁ፤ በሀገሪቱ ዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያውያን ሁሉ እኩልነት የሚረጋገጥበትን መንገድ አፈላልጋለሁ። ሰላምና ጽጥታ እንዲሰፍን የበኩሌን ተሳትፎ ከማድረግ አልቆጠብም። አሁን ግን ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነገር እየሰራ ነው። እስከ አሁን የፈጸማቸውን በደሎች ይቅር እያልሁ ኖሬያለሁ፤ ዳዊት ሳሚ የተባለውን ተሳዳቢ ተውት እግዚአብሔር ልኮት ነውና ይስደበኝ እንዳለ 2ሳሙ 1610 እኔም ኢሀዴግን «እግዚአብሔር ልኮት ነውና ይበለን» እያልሁ ቅጣቱን ተቀብየ እኖር ነበር። አሁን ግን እንደ ሎጥ የምዕራባውያንን ሣርና ውሃ በሥጋ አይኑ ተመልክቶ የርኩሰት ጉባኤ በሀገራችን እንዲካሄድ ፈቅዷልና ከሚመጣው እሳት የሚድን አይመስለኝም። አገሪቱ በጣኦት አምልኮና በጥንቆላ ተጎሳቁላ ባለችበት በዚህ ዘመን፣ ወንጌል እየተሰበከ ወደ ቀደመው የአባቶቻችን ሥነ ምግባራዊ አኗኗር እንድንመለስ ጥረት በምናደርግበት በዚህ ጊዜ፣ የውድቀት ጉባኤ ሀግራችን ላይ እንዲካሄድ መፈቀዱ ልባችንን አድምቷል «ነገር በልቤ እየተቆላ፤ ሣር እስቃለሁ እንደማሽላ» አለ ያገሬ ሰው!

 በኢየሱስ ክርስቶስ መንበር ተቀምጠው ከመንግሥታት ጋር የሚሴስኑ የሃይማኖት መሪዎችም፤ የእግዚአብሔርን እስትንፋስ ሳይሆን የመንግሥትን እየተነፈሱ ነው። አንዳድ የሃይማኖት መሪዎችም ግብረ ሰዶማዊነት መብት ነው የሚሉ፣ ነፋሱ ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ ሆነዋል። እነዚህ መሪዎች ክፉ ከሆነው ካሁኑ ዓለም ድነው ይሆን?
 ጌታ «ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ያመነ የተጠመቀ ይድናል» ያለው ታሪኩን ዓለም እንዲሰማለት ነው ወይስ ከተያዘበት አጸያፊ ኃጢአት ነጻ እንዲወጣ? ግብረ ሰዶማዊነት ለማይረባ አእምሮ ተላልፈው የተሰጡ ሰዎች የሚፈጽሙት ድርጊት ነው «ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው» ተብሎ ተጽፏል ሮሜ 126-28
 ጌታ ለነዚህ ሰዎች ስለሚገደው ነው ወንጌልን እንድንሰብክላቸው የላከን፣ የሃይማኖት መሪዎች ግን ያልተላኩበትን ተልእኮ መብታቸው ነው እያሉ በኃጢአታቸው እንዲቀጥሉ ያበረታቱ ዘንድ እንዴት ደፈሩ? ማን ላካቸው? ጌታ ኢየሱስ ወይስ ገንዘብና ሥልጣን? ማን ላካቸው?
 ኃጢአት ወደ ፍጻሜ ሲደርስና በእግዚአብሔር ዘንድ ሲወሰንበት፤ ከፊት ይልቅ የበለጠ ጉባኤ፣ አድማና ጩኸት እንደሚደረግ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል «የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቷል» ይላል ዘፍ 1820 ሁለቱ መላእክት በእንግድነት በሎጥ ቤት ሲገኙ የሰዶም ሰዎች ከበቧቸው
«ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት» ይላል። «ጠሪ ሲያሞጠሙጥ ይላል ሩጥ ሩጥ» እንዳለው ያገሬ ሰው ፍርዱ ሲደርስ የበለጠ ይጮኹ ነበር።

ሎጥ ሴቶች ልጆቹን እንዲወስዱና የወደዱትን እንዲያደርጉባቸው ቢፈቅድላቸውም ወንዶችን ፈለጉ። ከሎጥ ጋር ስለ ግብረ ሥጋ ይከራከሩ የነበሩት ሰዎች ሽማግሌዎች ወጣቶችና ብላቴናዎች ሁሉ ነበሩ  ሎጥ ግን ቤቱን ዘጋ «ወንድሞች ሆይ ይህን ክፉ ነገር አታድርጉ» እያለ ይሰብክ ነበር 7 ሎጥን ከሳት ያወጣችው ይህች ሃይማኖቱ ናት።  ዛሬም እየሆነ ያለው ይኸው ነው። የሃማኖት መሪዎች የመንግሥት ባለስልጣናት ወጣቶች ልዩ ልዩ ምሁራን ስለ ግብረ ሰዶም መብትነት ለመከራከር ጉባኤ ባሀገራችን ጠርተዋል፤ ጩኸቱ፣ የመብት ተከራካሪው፣ የገንዘብ ድጋፍ እየሰጡ ርኩሰትን የሚያስፋፉ ድርጅቶች በዝተዋል፤ ለተራበውና ለተጠማው ሕዝብ ትንሽ መለገስ የማይወዱ ድርጅቶች ለግብረ ሰዶም ማስፋፊያ ገንዘብ እየበተኑ ሚዛናዊ አመለካከት ያላቸው ዘመናዊ ሰዎች ለመምሰል ይሞክራሉ። በዚህ ጉባኤ ላይ መገኘት በራሱ ከባድ ውድቀት ነው። የእግዚአብሔር ጠላቶች በእግዚአብሔር አገር ላይ በኢትዮጵያ የርኩሰት ጉባኤ ሲያደርጉ ማየት የሞትን ያህል ይሰማናል።
 በክርስቶስ ደም የተዋጃችሁ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ወንድሞቼ ሆይ! ቤታችንን እንዝጋ፤ የርኩሰት ድርጆቶች ሕሊናችንን በገንዘብ ለመግዛት መሞከራቸው በራሱ ዝም ተብሎ የሚታለፍ አይደለም፣ ሞራላችንን ይዘን በድህነት ብንኖር ይሻለናል። በዚህ ብንጸና እግዚአብሔር ከሳቱ ያወጣናል። ይህን ጉባኤ እንደተራ ነገር ብንቆጥረው፤ በሀገራችን ነውር የሚባል ነገር ላይኖር ነው፣ የከበረውና የተዋረደው ተቀላቅሎ በሚመጣው ትውልዳችን ትከሻ ላይ ሊወድቅ ነው፤ እንዲህ ዓይነቱ ጉባኤ መወገዝ አለበት፤ ለሕጻናቱም ሆነ ለወጣቱ ይህ ነገር ነውር መሆኑን ልናስተምራቸው ይገባል።
 መንግሥትም ለሃይማኖት እሴቶችና ለሥነ ምግባር ትልቅ ዋጋ የሚሰጠውን የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቅ ቢያበቃ መልካም መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም።
 የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ስለዚህ ጉባኤ አስተያየታችሁን እንድትሰጡ እጋብዛለሁ

ተስፋ ነኝ  


15 comments:

 1. yihn hulu yameta yenante minfikina ena kihdet mebzat nerw. Sew yezerawun yachidal

  ReplyDelete
  Replies
  1. TRY TO USE UR MIND.THEY R TEACHING US.IF U HAVE POSITIVE MIND U DONT HAVE TO B AGAINST THIS IDEA.LOOK AT UR CHRISTIANITY.

   Delete
 2. it is wrong it shouldnt be allowed

  ReplyDelete
 3. ተስፋ አንተ ግን ማነህ ስለፃፍህልን ቃለህይወት ያሰማልን
  ግን አሁን ከፃፍከው ሐጢት ብትጠበቅም በሌላው ወድቀሐልና ለዚህች ለዛሬይቱ ፁሑፍ ሲል እግዚአብሔር አምላክ ለንሰሐ እንዲያበቃህ ፀሎቴ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. KA....KA...KA....YEMITFERED ANTE MAN NEH?BEFEREDKBET FIRD YIFEREDBHAL.TAKE CARE.(FROM BORN AGAIN CHRISTIAN)

   Delete
 4. ጎበዝ እንዲህ ነው ጠላትን ካወረዱና ከመቱ አይቀር! አናቱን መተርተር እንዲህ ነው እንጅ ሳይሰራ በማይመለሰው ቃለ እግዚአብሔር ብትንትኑን ማውጣት ነው!አሁንም ደጋግማችሁ ጻፉ!ወይ ነዶ አለ የሀገሬ ሰው ወንድና ሴት እንኳን አብሮ እጅ ለእጅ ተያይዞ ለመሄድ በሚያሳፍርበት የጨዋ ሀገር ወንድና ወንድ ሴትና ሴት ይጋቡ የሚል የሰዶምና ገሞራ ወንጀል በይፋ ይታወጅበት>አይ አንቺ ሀገሬእምቢ በሉኝ እምቢ በሉኝ ሆድ ብሶኛል!አቤቱ አምላካችን ሆይ!በዘመናችን ይህንን ታሰማን ታሳየን እባክህን ለእኛ ለድሃዎቹ ፊትህን አዙርልን በአደባባይ ግማታችንን ሽታችንን አታውጣው!!በምትወደውና ከቅድስት ማርያም በተወለደው በልጅ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እነለምንሃለን!
  አሜን!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 5. "በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በአዲስ አበባ በቅርቡ በሚካሄደው 16ኛው የአይካሳ ጉባዔን አስታክኮ በአገሪቱ ጸያፍ፣ ከሥነ ምግባር ውጭና ባህልን የሚያንቋሽሽ አጀንዳ ለማስፈጸም ተነሣሥቷል ያሉትን የአንድ ቡድን እንቅስቃሴን በመቃወም ትናንት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ፡፡...........
  ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መሪዎች በተወካያቸው አማካይነት መግለጫው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ያስታወቁት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አጽሃኖም በተገኙበት የዝግ ስብሰባ አድርገው በጉዳዩ ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ .............
  በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ (1996) ክፍል ሁለት ‹‹ለተፈጥሮ ባሕርይ ተቃራኒ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች›› በሚል ርእስ በአንቀጽ 629፣ ግብረሰዶም እና ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች በሚል ርእስ፣ ‹‹ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ካለው ከሌላ ሰው ጋር ግብረሰዶም ወይም ለንጽህና ክብር ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከቀላል እስራት እስከ ከባድ ወንጀል ቅጣት እንደሚጠብቀው ይደነግጋል፡፡"
  ሪፖርተር - የ ህዳር 20፣ 2004 እትም

  ReplyDelete
 6. ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ Please read this verse as many times as possible till you get it.Afterwards all sin activities conducted by TPLF and tagaye Paulos will vanish forever.

  ReplyDelete
 7. For general knowledge : The Anglican Communion,The Church of England,,German Lutheran, reformed and united churches in EKD, all Swiss reformed churches,the Protestant Church in the Netherlands, the United Protestant Church in Belgium, the Danish National Church, the Church of Sweden, the Church of Iceland and the Church of Norway,The Church of Jesus Christ of Latter-day Saints, ..............
  are some of the churches allowing and supporting gay marriage. from this we can understand that the western protestants are responsible for this mess. .....please it is the perfect time for us to pray to God to save us from the coming curse

  ReplyDelete
  Replies
  1. WE KNOW THAT ALL ETHIOPIAN CHRISTIAN CHURCHES NEVER ALLOWED THIS SIN.

   Delete
 8. ሁሌ ከቤተክርስቲያን ተቃራኒ ስለሆናችሁ ።ግብረ ሰዶም የምትደግፉ ይመስለኛል።እናንተ አምጥታችሁ እናንተ የምትጮኹት ክርስቲያኖች ነን ለማለት ነው? ማኅበረቅዱሳንን ማውገዝ ቤተክርስቲያንን ማጥላላት ብቻ መስሎኝ ስራችሁ።እና እኛ የምናለቅሰው እንዲህ ያለ ነገር እንዳታመጡብን ፈርተን እንጂ።ሃይማኖትማ በቂ አለንኮ።የእናንተ ምክር እንኳን ለበጣ ይመስላል።

  ReplyDelete
 9. በዚህ በመጨረሻው ዘመን የማይታይ፣ የማይሰማ ነገር የለም፡፡
  ልዑል እግዚአብሔር ከምንሰማው መሃት ይሰውረን፡፡ እንጂ

  የወርቅውሃ

  ReplyDelete
 10. በዚህ በመጨረሻው ዘመን የማይታይ፣ የማይሰማ ነገር የለም፡፡
  ልዑል እግዚአብሔር ከምንሰማው መሃት ይሰውረን፡፡ እንጂ

  የወርቅውሃ

  ReplyDelete
 11. ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።

  2 እንደዚህማ ባይሆን፥ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን?

  3 ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤

  4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።

  5 ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ። መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

  6 በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።

  7 በዚያን ጊዜ። እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ

  8 ይላል። በዚህ ላይ። መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥

  9 ቀጥሎ። እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።

  10 በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።

  11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤

  12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥

  13 ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።

  14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።

  15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ

  17 ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።

  18 የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።

  19-20 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥

  21 በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥

  22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤

  23 የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤

  24 ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤

  25 በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

  26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥

  27 የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።

  28 የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤

  29 የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?

  30 በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም። ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።

  31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

  32-33 ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ።

  34 የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ።

  35 እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።

  36 የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።

  37 ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤

  38 ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።

  39 እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

  ReplyDelete
 12. ሕጉ ሊመጣ ያለው የበጎ ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን የነገር ጥላ አለውና፥ ስለዚህም በየዓመቱ ዘወትር በሚያቀርቡት በዚያ መሥዋዕት የሚቀርቡትን ሊፈጽም ከቶ አይችልም።

  2 እንደዚህማ ባይሆን፥ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ነጽተው ከዚያ በኋላ በሕሊናቸው ኃጢአትን ስላላወቁ ማቅረብን በተዉ አልነበረምን?

  3 ነገር ግን በዚያ መሥዋዕት በየዓመቱ የኃጢአት መታሰቢያ አለ፤

  4 የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን እንዲያስወግድ የማይቻል ነውና።

  5 ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ። መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤

  6 በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ሰለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም።

  7 በዚያን ጊዜ። እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ

  8 ይላል። በዚህ ላይ። መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥

  9 ቀጥሎ። እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል።

  10 በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል።

  11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤

  12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥

  13 ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል።

  14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና።

  15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ

  17 ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።

  18 የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም።

  19-20 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥

  21 በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥

  22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ፤

  23 የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና እንዳይነቃነቅ የተስፋችንን ምስክርነት እንጠብቅ፤

  24 ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤

  25 በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።

  26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥

  27 የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።

  28 የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤

  29 የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?

  30 በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም። ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።

  31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

  32-33 ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ።

  34 የሚበልጥና ለዘወትር የሚኖር ገንዘብ በሰማይ ራሳችሁ እንዳላችሁ አውቃችሁ፥ በእስራቴ ራራችሁልኝ የገንዘባችሁንም ንጥቂያ በደስታ ተቀበላችሁ።

  35 እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።

  36 የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።

  37 ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም፤

  38 ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ፥ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም።

  39 እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም።

  ReplyDelete