Tuesday, November 15, 2011

"እንግዲህ በመብል፡ ወይም በመጠጥ፡ ወይም ስለ በዓል፡ ወይም ስለወር መባቻ፡ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ‚ ቈላ 2፥ - - - Read PDF

በብሉይ ኪዳን ዘመን መብልና መጠጥ፣ የተለያዩ በዓላት፣ የወር መባቻና ሰንበት ለእሥራኤል ዘሥጋ የተሰጡ ሥርዓቶች ነበሩ። ሐዋርያው ስለ መብል ማንም አይፍረድባችሁ ሲል ያስተማረው በዚያ ዘመን በመብል ምክንያት መርከስና መቀጣት ስለነበረ ነው። አይሁድ የማይበሏቸው እንስሳት ተለይተው ይታወቁ ነበር። ለምሳሌ በዘሌ 113-8 እንዲህ የሚል ትእዛዝ እናገኛለን፦

   «ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በሉአቸው። ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው። የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ። ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።ጥንቸልም ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። እርያም ሰኮናው ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።  የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው»

 ይህ የሥጋ ሥርዓት በመንፈሳዊው በሐዲስ ኪዳን ሥርዓት እስኪተካ ድረስ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን የሚበላ ማንኛውም አይሁዳዊ ይቀጣ ወይም ይረክስ እንደነበር የታወቀ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ ምድርን በደሙ ከቀደሰ በኋላ ግን ሰውን የሚያረክስ መብል አለመኖሩን ሐዲስ ኪዳን ያረጋግጣል

 ቅዱስ ያሬድ «ምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ» [ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን አደረገች] ያለውም በዚህ ምክንያት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን በደሙ ሲቀድሰን የሚያረክሱ ትዛዝዛትን አስወግዶ ነው፤ እነዚህ ትዛዛት በሕዝብና በአሕዛብ መካከል አንድነት እንዳይኖር የሚከለክሉ ነበሩ። አሕዛብ ሁሉን ይበላሉ፤ አይሁድ ግን ሁሉንም አይበሉም። በዚህ ምክንያት እነዚህ አትብላ፣ አትንካ፣ አትቅመስ፣ የሚሉ ትዛዛት በሁለቱ መካከል እንደ ግድግዳ ሆነው ለያይተው ይኖሩ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በደሙ ምድርን ቀድሶ አይሁድና አሕዛብን ከአዳናቸው በኋላ በመካከላቸው የነበረውን የጥል ግድግዳ [ትዛዛትን] አፍርሶ አስታረቃቸው። በአንድ መንፈስም ወደ አብ እንዲገቡ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቃቸው። ይህን ሐሳብ ከሚከተለው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማስተዋል እንረዳ፦

«አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።  መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤  በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና» ኤፌ 213-18

 «በአዋጅ የተነገሩትን የትዛዛትን ሕግ ሽሮ» የሚለውን ቃል እናስተውል። እነዚህ የተሻሩ ሕግጋት የመብል፣ የመጠጥ የበዓል፣ የወር መባቻ፣ የሰንበት፣ የወር አበባ፣ የአራስ ሴት፣ የቁስል፣ የበሽታ የሬሳ ወዘተ ሕጎችን ነው። በጽላት ላይ ተለይተው የተጻፉ አሥሩን ትእዛዛት ግን አይደለም። አሥሩን ትዛዛት ጌታ ራሱ ሊፈጽማቸው ስለመጣ የተሻሩ አይደሉም። አስሩ ትዛዛት  በመንፈስ በልብ ተጽፈው ስለሚኖሩ የበለጠ መንፈስ ሆነዋል። ሆኖም በእርሱ ሥራ ወደ አብ እንገባለን እንጂ በአሠርቱ ትዛዛት መጽደቅ እንደማይቻል የታወቀ ነው።

 ሐዋርያው ማርቆስ «መብልን ሁሉ እያጠራ [እየቀደሰ] አስተማራቸው» ብሎ ጽፏል ማር 719 ስለዚህ በሕዝብና በአሕዛብ መካከል የነበሩትን የጥል ምክንያቶች [የሥጋ ትዛዛትን] ሽሮ ጥልን በሥጋው አፍርሶ አንድ አድርጓቸዋል።

     ይህን የጌታን ምሥጢር አጥብቆ የተረዳው ጳውሎስም «በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄያለሁ ተረድቻለሁም» ብሎ አስተማረ ሮሜ 1414 በቆሮንቶስ መልዕክቱ ደግሞ የመብልን ጉዳይ ግልጥ አድርጎታል «በሥጋ ገብያ የሚሸጠውን ሁሉ ከሕሊና የተነሳ ሳትመራመሩ ብሉ፤ ምድርና በርስዋ የሞላባት ሁሉ የጌታ ነውና» ብሏል 1ቆሮ 1025 ለቈላስይስ ክርስቲያኖች የጻፈውን ስንመለከት "ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ፣ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት አትያዝ፣ አትቅመስ፣ አትንካ፣ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና» ብሏል ቈላ 221-23

  የመጽሐፍ ቅዱስ መምህራን እነዚህ መልዕክቶች የተጻፉት፦  በአይሁድና በአሕዛብ መካከል በመብል ምክንያት የተነሳውን ጠብ ለመዳኘት ነው በማለት ይስማማሉ። ጳውሎስ በሮሜ 141-3 ላይ «የሚበላ የማይበላውን አይናቀው፤ የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ» በማለት እውነተኛ የሐዋርያነት ፍርድ የሰጠው የወንጌልን ምሥጢር ጠንቅቆ ሰለሚያውቅና በአዋጅ የተነገሩት የትዛዛት ሕጎች በጌታ ደም ስለተሻሩ ነው።

  በአጼ ናኦድ ዘመነ መንግሥት በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ብሉይ ኪዳንን ትመስላለች የሥጋ ሥርዓቶችን እንደ ሃይማኖት አድርጋ ይዛለች ተብላ ቤተ ክርስቲያናችን ተከሳ ነበር። አጼ ናኦድም የኦርቶዶክስን ሊቃውንት ሰብስበው መልስ እንዲሰጡ አድርገው ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የሚከተለው መልስ ተሰጥቷቸዋል። «እኛ በብሉይ ኪዳን የተከለከሉ እንስሳትን የማንበላው ባሕላችን ስለሆነ እንጂ ያረክሱናል ብለን አይደለም» የሚል ነው [የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በአቡነ ጎርጎርዮስ]

  ኢየሱስ ከርስቶስ ከማንኛውም ዕዳ እንዳዳነው የሚያምን ሁሉ በመብል አይረክስም። ሰውን ሊያረክስ የሚችለው የልብ ክፋት፣ የሐስት ሥራ፣ ከልብ የሚወጣ ተንኮል ብቻ ነው። ይልቁንም ከነዚህ ርኩሰቶች ልንነጻ ይገባናል።

 ከሥጋ ሥርዓት ያልተላቀቀው የቤተ ክርስቲያናችን ፈሪሳውያን የነ ዳንኤል ክብረት ማህበር ግን ይህን የጌታ ምሥጢር በመካድ የአጋንንትን ትምህርት እየተከተሉ ሰዎችን ከመብል እንዲርቁ ያዝዛሉ። በአሜሪካ የዘሩት ልዩ ወንጌል ቤተ ክርስቲያንን እስከ አሁን ድረስ ለያይቶ ይገኛል። ክርክሩም ይበላል አይበላም የሚል ነው። የጥንቱ የአይሁድና የአሕዛብ ጠብ ዛሬ በኛ ቤተ ክርስቲያን እንደ አዲስ እያወዛገበ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለነዚህ የአጋንንት ትምህርት ተከታዮች እንዲህ ብሎ ነበር

 «መንፈስ ግን በግልጥ። በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥ እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፥ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ። እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፥ ከምስጋናም ጋር ቢቀበሉት የሚጣል ምንም የለም፤ በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነውና» 1ጢሞ 41-5

 እንግዲህ መናፍቁ ማን ነው? ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ኦርቶዶክሳውያን? ኦርቶዶክሳውያን እንደ አቡነ ጎርጎርዮስና በአጼ ናኦድ ዘመነ መንግሥት እነደነበሩት ሊቃውንት መብል ባሕል ነው ይላሉ። የክርስቶስ ደም የመቀደስ ኃይል አለው፣ ሁሉም ተቀድሷል፣ መብል ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም ይላሉ። 1ቆሮ 88 ማህበረ ቅዱሳን ግን የጌታን ቃል በመተው የአይሁድን ሥርዓት ይከተላሉ። ማን  ነው መናፍቁ?

 የአይሁድን ሥርዓት ወደ ቤተ ክርስቲያን ማን እንዳስገባው ባይታወቅም እንደ ሃይማኖት ሆኖ ስለኖረ አሁን በዚህ ዘመን ለምንኖር ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ ከባድ መከራ እንድንሸከም አድርጎናል። መብልና መጠጥ መናፍቅ ሊያስብል አይችልም፤ እኛ ክርስቲያኖች እንጂ አይሁዶች አይደለንም። ስለዚህ ጌታ በደሙ የሻረው ሕግና ትእዛዝ ሊያስወግዝ አይገባውም። የማህበረ ቅዱሳን አባላትም የሙሴን መጻሕፍት በማንበብ መጋረጃው እንደተዘረጋባችሁ እንረዳለን ከዚህ ክህደት ወጥታችሁ ወደ ጌታ ዘወር እንድትሉ የሚከተለውን ጥቅስ እንጋብዛችኋለን።

 «የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።  ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤  ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል። ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።» 2ቆሮ 313-17

 እግዚአብሔር መጋረጃውን ይውሰድልን።

ስለ በአልና ስለ ሰንበት በሚቀጥለው አቀርባለሁ

ተስፋ ነኝ  

20 comments:

 1. why not the organization, "mulu wongel" change its name and rename as "orthodox", if you call your self as orthodox? hhahhahha because you are the known wolf, you want to use the name which does not belong to you. calm down!! we have known you as what you are! your plan A to convert the orthodox church to "menafkan" organizations could not work. come on with your plan B. CASE CLOSED,MR.EASAW!!!!

  ReplyDelete
 2. it is a good idea if we will have good hearted
  people please contnue to write like that.

  ReplyDelete
 3. Menafequ manewe? Menafequma tehadesou tesfa newe. Ene oritene laferese alemetahume yeleuene menewe eresahewe? Aye yeweldetensay mahebertegna.
  Gene leunetu megebe newe ende? Defar weshetam.
  Lemayaweqehe tatene.

  ReplyDelete
 4. betam turu temehret new bmebel sayhone besera new kale heywote yasemane

  ReplyDelete
 5. መናፈቁ ማነው? መናፍቁማ ተሃድሶው ተስፋ ነው:: እኔ ኦሪትን ላፈርስ አልመጣሁም ያለውን ምነው እረሳሀው? አይ የወልደተንሳይ ማህበርተኛ:: ኢየሱስ ኦሪትን ሙላት ለመስጠት እንጂ እንዲሽረው እንዳልመጣ ማትዎስ ፭: ፩፯ ላይ
  ‘እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ። እንግዲህ ከነዚህ ከሁሉ ካነሱት ትእዛዛት አንዲቱን የሚሽር ለሰውም እንዲሁ የሚያስተምር ማንም ሰው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ታናሽ ይባላል፤ የሚያደርግ ግን የሚያስተምርም ማንም ቢሆን እርሱ በመንግሥተ ሰማያት ታላቅ ይባላል።’
  ግን በእውነቱ ልዩነታችን የምግብ ነው እንዴ? ደፋር ውሸታም ነህ:: ለማያውቅሕ ታጠን:: ይልቁኑ እንደ ጽጌ ስጦታው ደፈር ብለህ እየሱስ ያማልዳል ብትል አይሻልህም? እንደ ወልደተንሳይ ምግብ እና የወር አበባ ላይ ከምትጣበቅ??

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች እንዴት አላችሁ አንዳንድ ጊዜ ቁም ነገር አዘል ነገሮችን ትጽፋላችሁ። በተለይ ይህ አመጋገብን በተመለከተ ዘወትር የሚነሳውን ክርክር ለማስቆም ይረዳ ዘንድ ተስፋ በተባልህ ሰው የጻፍኸው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች የተደገፈ በመሆኑ ለተነሳው ጉዳይ መልስ ሊሰጥ የሚችል ነው ብየ አምናለሁ።
  ነገር ግን በአጼ ናኦድ ጊዜ በኛ ቤተ ክርስቲያን ላይ እንደዚህ አይነት ክስ መቅረቡን እና እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ የምግብ አይነቶች የማንበላው በባህል ምክንያት እንጅ ሃይማኖታችን ስለሚከለክል ላለመሆኑ መልስ መሰጠቱን አቡነ ጎርጎርዮስ የጻፉት የት ላይ ነው? እኔ በአቡነ ጎርጎርዮስ መጽሐፍ እንደዚህ አይነት አረፍተ ነገር ይኖራል ብየ አላምንም። ምክንያቱም እርሳቸው እንደዚህ ቢጽፉ ንሮ የማህበረ ቅዱሳን ሰባክያን ሁሉ በይፋ ይሰብኩት ነበር። በእውነትም አቡነ ጎርጎርዮስ እንደዚህ ጽፈው ከሆነ እስኪ በእናትህ በየትኛው መጽሓፋቸው በየትኛው ምዕራፍ እና በየትኛው ገጽ ላይ እንደሚገኝ ንገረን።

  ReplyDelete
 7. sijemir indezih newu clearly yemenafikan timihirt, belu menafikan mehonachihun ahun awoku menafik mehon mebit newu gin ibakachihu bezich wolda basadegechachewu babelachachewu bastemarechachewu lijochua lik inde Ethiopia balitetkemechiwu tewahido orthodox sim atikelidu Gora leyu.sile medihanyalem sewun atiberizut.

  ReplyDelete
 8. Good! I used to eat pork (mortedela) many years a ago. for the last 12 or 14 years i have not tested it. Two days a ago I ate pizza with pepperoni (pork) a little. My christian brothers and sisters, we are christian not yehoda or Islam however the so call mehaber kidusan (cynical individuals)are blamed for all the mess they brought to our church, we are also responsible to read the bible and know the son of God.

  ReplyDelete
 9. በሕግ ያለ ከሕግ አይውጣ ተብሏል። ፆሙ ተረሳና ስለሆድ ይሰበክ ጀመር? ምንድነው ለሆድ መጨነቅ?

  ReplyDelete
 10. ዶሮ ብታልም ጥሬዋን።

  ReplyDelete
 11. ሁሉ ተፈቅዷል፥ ሁሉም ግን አይጠቅምም::

  ReplyDelete
 12. ብጹዕ አቡነ ጎርጐርዮስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ በተሰኘው መጽሐፋቸው በገጽ 180-181 ላይ እንዲህ ብለዋል። «አሳማን ከመብላት የተከለከልነው እንደ አይሁድ የኦሪትን ሕግ ለመጠበቅ ብለን አይደለም። የሚበላውንም አንጸየፈውም፣ አናረክሰውም። የማይበላውንም ብላ ብለን አናስገድደውም» ይህ አባባል ሐዋርያው ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ 14፣3 «የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና»ያለውን መሠረት ያደረገ ቃል ነው። አንዳንዶች ከላይ የሰጡት አስተያየት መብላት እንደማይቻል ወይም የረከሰ ነው የሚል ክርክራቸውን በማስረጃ ከማቅረብ ይልቅ በተለመደ ሽሙጣቸው ያሰለችናል። መታወቅ ያለበት ነገር አሳማ፤ ከርክሮ፣ ግመል ወይም ሌላ የማያመሰኳ እንስሳ ሳይበላ የኖረውን ሕዝባችንን ብላ ብለን አንሰብከውም፤ መብላት የፈለገውንም ደግሞ አናረክሰውም። ይህንን ያለው የወንጌል ቃል ነው። ቁምነገሩ ያለው ሸኮናው የተከፈተው ቅዱስ ነው፣ ድፍን የሆነው ወይም የማያመሰኳውን የበላ ረክሷል፣ ተኰንኗል የሚሉ ማቃውያን የሚያስተምሩትን የክህደት ትምህርት ነው የምንቃወመው። ቁምነገሩ ብሉ፣አትብሉ ከሚለው ነጥብ ላይ ሳይሆን የሚበሉት እነዚህ ናቸው፣ የሚያረክሱት እነዚህ ናቸው የሚል የሐዲስ ኪዳን ትምህርት ሳይኖር ማቃውያን በሐመር መጽሔታቸው ሲቀድሱና ሲያረክሱ መገኘታቸውን ነው የምንቃወመው። መብላትም አያረክስ፣ አለመብላትም ቅዱስ አያደርግም። እንግዲህ ወንጌሉን አብራርተው የጻፉትን አቡነ ጎርጐርዮስን ተሃድሶ ናቸው ብላችሁ በተለመደው የክስ ወረቀታችሁ ላይ አስፍሩና እንይ! የተነገረውን ከመስማት በስተቀር ስለተነገረው ምንነት እውቀት የሌላቸው «ልሽር አልመጣሁም ብሏል» «ጾም ተረሳና ስለሆድ መስበክ ተጀመረ» መናፍቃን መሆናችሁን ገና አሁን አወቅን» ወዘተ እሮሮዎችን በአስተያየቶች ለመግለጽ የተሞከረው ከቁም ነገር የሚገባ አይደለም። እየተባለ ያለው በልታችሁ የማታውቁትን አሁን ብሉ ወይም ተለማመዱ ወይም ተፈቅዷል ብለን አናደፋፍርም። የሚበሉትን፣ መብላት የፈለጉትን ወይም በጥቅሉ መብላትን አታርክሱ፣ እንደዚህም ብላችሁ አታስተምሩ ነው የምንለው። ጳውሎስም«የሚበላ የማይበላውን አይናቀው የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ፥ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና»

  ReplyDelete
 13. አይ ተስፋ!!!??? ምነው ዝም ብለህ የፈለከውን ብትበላ! ለምን የመብል ተባባሪ ትፈልጋለህ? እንደጠቀስከው "የማይበላውም በሚበላው አይፍረድ" ነውና ብትበላ የሚፈርድብህ ያለ አይመስለኝም። ያለዚያ ግን ቅዱሳት መጻሕፍትን አንተው በመሰለህ "ይኸኛው ተሽሯል ያኛው አልተሻረም" እያልክ የምትተረጕመውን የኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት እያስመሰልክ አትንገረን። ለመኾኑ ጌታ "ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ..." አለ እንጅ ሰፍሮ ቆጥሮ "ይህን አሠርቱ ቃላትን አልሻርኩም ሌላውን ግን ሽሬአለሁ ..." ብሎ አስተምሯል? ጳውሎስስ ከአሕዛብ ወገን ያመኑቱ ክርስቲያኖች በኦሪቱ ሕግ ምክንያት ክርስቶስን ከማመን እንዳይርቁ እንጅ የኦሪት ሕግ እንዲሻር አስተምሯልን? አይደለም። ቢያስተምርማ ኖሮ የአይሁድ ክርስቲያኖችን "ኦሪትን ትታችሁ ክርስቶስን ብቻ ተቀበሉ" ባላቸው ነበር፤ ነገር ግን አላለም። እሱ ያስተማረው ግን አሕዛብ የምግብና ሌሎች ባህሎቻቸውን እንደያዙ (የመጀመሪየው የሐዋርያት ሲኖዶስም ይኽንኑ አጽድቆለታል፡ የሐ ሥራ ፲፭)፣ አይሁድም ኦሪታቸውንና ነቢያቶቻቸውን እንደጠበቁ፣ (እሱም ራሱ ቅሉ ከኦሪትና ከነቢያት እየጠቀሰ በማስተማር)በክርስቶስ እንዲያምኑ ነው።
  እንግዲህ ኢትዮጵያም (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም)ይህን የኦሪቱን ባህል (መቼ ገባ ለሚለው ጥያቄ ኹነኛ መልስ ለጊዜው ባይኖረኝም) ጠብቃ የኖረች ናት ። ከዚሁ ባህሏ ጋርም ክርስትናን ተቀብላለች። (ተስፋ፡ ያንተም ወላጆች በዚሁ ባህል የኖሩ እንደሚኾኑና እምነታቸውንም ከአያት ከቅድመ-አያት እንደወረሱት እገምታለሁ።) እንግዲህ አንተ/ተስፋ/ ከነበርኩበት ባህል ወጥቼ፣ ወደ አሕዛብ ባህል ገብቼ፣ ኹሉንም በልቼ ክርስቶስን እከተላለሁ ብትል የምትጨምረው ጽድቅ ባይኖርም ትኰነናለህ ብዬ አላስፈራራህም። የሚያጸድቅ የሚኰንን ራሱ ባለቤቱ ብቻ ነውና። እኛም በረከትን ያሰጠናል፣ በጐ ሥራ ያሠራናል ብለን ያመንበትን በብሉዩም በሐዲሱም ያለውን ሕግ ይዘን እንሄዳለን። አንተን ም አግዶህ ከዚህ ውጡ ትለናለህ?

  ተስፋ፣ ብዙ የምልህ ነበረኝ፣ ግን ጊዜም የለኝ።
  ሰላም ኹን
  ይነሱልህ

  ReplyDelete
 14. yehe timehert kelikawent yemetebeke newe yebel belenal mk wember zergetachehu bible temaru

  ReplyDelete
 15. those who blame this good teaching u have to convice us by prove .why always thinking blindly do u know this proverb << memar yadergal leke>> pls before blaming first know the bible and what orthodox teache.

  ReplyDelete
 16. derom bihon tenesh ewket lalememarina lalemeteyek tagalitalech. ebakih beewketina bemereja temesreteh lemestaf ha hu bel

  ReplyDelete
 17. rom-14
  15 ወንድምህንም በመብል ምክንያት የምታሳዝን ከሆንህ እንግዲህ በፍቅር አልተመላለስህም። ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለትን እርሱን በመብልህ አታጥፋው።
  ...
  17 የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።
  .....
  1co-07
  18 ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ።

  19 መገረዝ ቢሆን አለመገረዝም ቢሆን ከንቱ ነው፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ።

  20 እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር።
  .....

  1co-08
  8 መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም አይተርፈንም።
  .....
  13 ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም።

  ReplyDelete
 18. all article is tahadeso.you can eat u are hodam people preaching gospel u preaching about food.

  ReplyDelete
 19. For all people commenting on the blog please i beg you on God'd name to come up with biblical evidence , don't blame or insult anyone( የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር። ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም). anyone can say whatever he want to say by giving evidence from bible, dont also forget it is a free blog ,,,,pls pls pls let us grow up. don't say tehadiso , menafik ..or.... if so write them at least one word from the bible zat makes them tehadso/menafik like (ይነሱልህ)

  ReplyDelete