Tuesday, November 1, 2011

ለሁለቱ ሲኖዶሶች የእርቅ እንቅፋት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች - ታምረ ማርያም? - - - PDF

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ከተወጋገዙ ዓመታት አልፈዋል። አሁን ለመታረቅ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ስንሰማ እጅግ ደስ ብሎን በጉጉት እየጠበቅነው ነው
ነገር ግን አንዳድ እንቅፋቶች ይኖራሉ ብለን ስለምናምን እነዚህን ጉዳዮች ለውይይት ልንቃርባቸው ወደድን።

እንደሚታወቀው ሁለቱም ሲኖዶሶች በተወጋገዙበት ቃለ ውግዘት ውስጥ የኢትዮጵያው ሲኖዶስ በጻፈው ላይ መልክአ ሥእል እና ታምረ ማርያም አያነቡም የሚል ውግዘት እንዳለበት ተመልክተናል። ነገር ግን በአሜሪካው ሲኖዶስ ሥር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ታምረ ማርያም ከቅዳሴ በፊት እንደሚያነቡ ሰምተናል።
ይሁን እንጂ የታምረ ማርያም ነገር በዚህ እርቅ መፍትሔ ካልተሰጠበት የሰው ስም ማጥፊያ፤ የፖለቲካ መጠቀሚያ እየሆነ ትውልድ ሲያወጋግዝ ሊኖር ይችልላና አብሮ ቢታሰብበት ለትውልድ የሚሆን መፍትሔ ያመጣል ብለን እናምናለን።
መጽሐፉን ለግምገማ ይመች ዘንድ በውስጡ ያለውን ይዘት ጥቂት ለማቅረብ ሞክረናል።
ታምረ ማርያም የሚባለው መጽሐፍ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን[1530 ..] ተጽፎ በየገዳሙ እንደተላከና ደቂቀ እስጢፋኖስ እንደተቃወሙት በዚህም ምክንያት በእሳት ተቃጥለው እንደሞቱ የታወቀ ታሪክ ነው።
ይህ ከጊዜ በሁዋላ ሰርጎ የገባ መጽሐፍ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ልጆች ቀሳውስትን፤ ዲያቆናትን ምእመናንን እየከፋፈለ የሚገኝ አንዳዶችንም ያስደበደበ ከዚያም አልፎ ደም ሲያፋስስ የኖረ መጽሐፍ ነው።
በመቅድሙ መጀመርያ ላይ 1 35 ላይ በእሑድ ሰንበት የማርያምን ታምር ለመስማት የማይሄድ ክርስቲያን ቢኖር አባ ገብርኤል እና አባ ሚካኤል በሚባሉ ጳጳሳት ተወግዟል ይላል ስለዚህ ክርስቲያን ነኝ ያለ ሁሉ ከውግዘቱ ለመዳን እሑድ ተገኝቶ ታምረ ማርያም መስማት ግዴታው ነው።
ምእመኑ ታምረ ማርያም ሲባል እንዲሁ በደፈናው ለመስማት እና ለመሳለም ይጣደፋል እንጂ ደም ሲያፋስስ የኖረ መሆኑን በውስጡም ያለውን ይዘት አስተውሎት አያውቅም። ነገር ግን የማርያምን ስም ስለሚጠራ ብቻ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ የኖረ መጽሐፍ ነው።
ዛሬም ከቅዳሴ በኋላ በቀሳውስቱ የሚነበብ ሲሆን አንዳድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት የተረዱ ካህናት ግን እየተሸማቀቁ ሲያነቡት ይታያሉ። አብዛኛዎቹ ቀሳውስት በታምረ ማርያም ማንበብ ደስተኛ አይደሉም ነገር ግን ሕዝብ የለመደው ስለሆነ ሕዝቡን ላለማስቆጣት ስለሚጠነቀቁ በግእዝ ሸፋፍነውት ያልፋሉ።
ለመሆኑ ታምረ ማርያም ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለው ግጭት ምንድን ነው?
ከዚህ ቀጥለን በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ አንዳድ ሐሳቦችን በማቅረብ ለፍርድ አቅርበነዋል።
በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተገብረ ኩሉ ዓለም በእንተ እግዝእትነ ማርያም ተፈጥሩ አዳም ወሄዋን ትርጉም ፍጥረት ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ፤ አዳም እና ሄዋንም ስለ እመቤታችን ተፈጠሩ የዘወትር መቅድም 1 7
ይህ አባባል መጽሐፍ ቅዱስን ፈጽሞ የሚቃረን ነው። ፍጥረት የተፈጠረው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነው። ሰማይና ምድር በሙሉ እንኳ የእግዚብሔርን ክብር እንደሚገልጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል መዝሙር 18 1 ሰማይና ምድር ለሰው ልጆች ሁሉ የተፈጠሩ የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫ ናቸው እንጂ ለእመቤታችን ተፈጠሩ የሚለው የተጋነነ ውሸት ነው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንም ጥንታውያን አባቶችም ትምህርት አይደለም።
አዳም እና ሄዋን ለማርያም ተፈጠሩ ማለትስ ምን ማለት ነው? ያን ያህል ዘመን በሲኦል ሲማቅቁ የኖሩት ለማርያም ተብሎ ነውን? ነገሩ ግልጽ አይደለም። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጌታችን እናት በመሆኗ ክብር ይገባታል። ከዚህ ውጭ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምንወዳት በድንግል ማርያም ስም ማጣመም ተገቢ አይደለም።
ወቅድመ ሥእላ ስግዱ ዘኢሰገደ ላቲ ይደምሰስ እምቅዋሙ ወኢይት አወቅ ዝክረ ስሙ ትርጉም፥ በሥእሏ ፊት ስገዱ ለሥእሏ ያልሰገደ ከቆመበት ቦታ ይጥፋ ስም አጠራሩም አይታወቅ የዘውትር መቅድም 1 35
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ካመነ ስሙ በሕይወት መጽሐፍ እንደሚጻፍ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ሉቃ 10 20 በዘዳ 4 15-19 ላይ እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት ውስጥ ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክ ከቶ አላያችሁምና እጅግ ተጠንቀቁ፤ እንዳትረክሱ፥ ተቀረጸውን ምስል የማናቸውንም ነገር ምሳሌ፥ በወንድ ወይም በሴት መልክ የተሠራውን፥ በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥ በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥ ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕዛብ ሁሉ የሰጣቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባየህ ጊዜ፥ ሰግደህላቸው አምልከሃቸውም እንዳትስት ተጠንቀቅ ይላል። ታዲያ ለሥእል መስገድን ምን አመጣው?

በተለይም የወንድ ወይም የሴት ምስል የሚለውን ቃል ማስተዋልና መጠንቀቅ ተገቢ ነው ለማርያም ስእል ግን መስገድ የተፈቀደበትን ስፍራ አናገኝም። አጼ ዘርዓ ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል ከመተላለፉም በላይ ከቆመበት ይጥፋ ስም አጠራሩ አይታወቅ የሚሉትን የእርግማን ቃላት ያለቦታቸው አስቀምጧቸዋል ሥእል ትምህርት ሰጪ ታሪክን የሚገልጥ ሊሆን ይገባል እንጂ ስግደት ጸሎት አምልኮ ሊቀርብለት እና ሰውን ለማጥፋት መራገሚያ ሊሆን አይገባም።
መልክአ ስእል የሚባለው ድርሰት ሁልጊዜ በየጠዋቱ የሚጸለይ ሲሆን የሚናገረው ስለ ስእል ቁንጅና ለሥእል ስግደት እንደሚገባ የሚናገር ነው ሁልጊዜ ካህናቱ ከኪዳን በፊት የሚጸልዩት የጸሎት ክፍል ነው። በዚህ መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚል አለ።
ዘኢሰገደ ለስእልኪ አሥሪጾ ምማኤ በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሣኤ ትርጉም፦ እራሱን ዝቅ አደሮጎ ለሥእልሽ ያልሰገደ ቢኖር በነፍሱ እና በሥጋው ትንሣኤ አያገኝም
ይህ ድርሰት አባ ስጢፋኖስን ለመራገም የተደረሰ ሲሆን በሐግሪቱ ላይም ሥጋዊ እና ማሕበራዊ ውድቀት ሊያመጣ የሚችል ስለሆነ ባስቸኳይ ሊቆም ይገባል ጸልዩልን ብሎ የሚማጸንን ሕዝብ ለሥእል ካልስገደ ተብሎ በሥጋው[በኑሮው] እና በነፍሱ ትንሣኤ አያግኝም ተብሎ ለዚያውም ጠዋት ጠዋት ሊረገም አይገባውም።
ወዘኢተክህሎ ነሢአ ቍርባነ ሰሚኦ ይሑር ውስተ ቤቱ ወይከውኖ ከመ ቁርባን ለእመ ሰማዐ በአሚን ትርጉም፦ ሥጋውን ደሙን መቀበል ያልቻለ ታምሯን ሰምቶ ይሂድ ሥጋውና ደሙን እንደተቀበለ ይሆንለታል መቅድም 1 45
ይህ ደግሞ ጌታ ሥጋዬን ያልበላ ደሜንም ያልጠጣ የዘለዓለም ሕይወት የለውም ብሎ ያስተማረውን ትምህርት ፈጽሞ ያላገናዘበ ነው ሥጋውን ደሙንም ምንም ዓይነት ታምር ሊወክለው አይችልም። ብዙ ሰዎች ብዙ ታምር ሰምተዋል አይተዋልም ነገር ግን በክርስቶስ ማመን እንዲሁም ሥጋውን ደሙን መቀበል ስላልቻሉ ወደ ሕይወት አልመጡም። በጣም የሚያሳፍር አባባል ነው። ዛሬ ታምር በመስማት የሚንከራተተው ሕዝባችን ከዚህ እርግማን ጋር ተያይዞ የመጣበት ይሆንን?
ዋናው የጠብ ምንጭ በታምረ ማርያም ውስጥ

ኃጥአን አኃውየ እለ ከማየ እምይእዜሰ ኢንሕሥስ ከዊነ አግብርተ እግዚአብሔር ለፈጽሞ ሕግጋት አሠርቱ ወሰደስቱ እስመ ውእቱ መጠወነ ኪያሃ እግዝእተ ኪዳን ጊዜ ቀትር አመ ሀሎ ዲበ ዕፀ መስቀል እንዘ ይብል ነያ እምክሙ ወእግዝእትክሙ ወበእንተዝ እብለክሙ ንቅድም ወንትባደር ከዊነ አግብርት ለማርያም እምነ ወእግዝእትነ
ትርጉም እንደ እኔ ያላችሁ ኃጥአን ወንድሞቼ ሆይ እንግዲህ አሠርቱ ትእዛዛትን እና ስድስቱ ቃላተ ወንጌልን በመጠበቅ የእግዚአብሔር ባሪያ ለመሆን ማሰብ የለብንም እርሱ በቀትር ጊዜ በመስቀል ላይ ሆኖ እመቤታችንን እናት አድርጎ ሰጥቶናልና፤ ይልቁንስ የእመቤታችን እና የእናታችን የማርያም ባሪያ ለመሆን እንሽቀዳደም ይላል። ታምረ ማርያም ምዕራፍ 1252-53
እንግዲህ ይህ አባባል በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ተጽፎ ወደየገዳማቱ በተላከ ጊዜ ከፍተኛ ውዝግብ አስነሥቶ አባ እስጢፋኖስ እና ደቀ መዛሙርቱ እንዲገደሉ ምክንያት የሆነው እና እስከ ዛሬ ድረስ መፍትሔ ያላገኘ እንቆቅልሽ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብትወዱኝ ትዛዜን ጠብቁ ብሎ አስተምሯል። ስድስቱ ቃላተ ወንጌል የሚባሉት ማቴ 25 35-44 ላይ ይገኛሉ። ታዲያ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ምን አይነት መጻሕፍትን ቢያነብ ነው የእግዚአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ አያስፈልገንም ያለው? ይህን መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያናችን ሰይጣን አስርጎ ያስገባው የጠላት ተንኮል እንጂ ልናነበው እና ልንሳለመው የሚገባ መጽሐፍ አይደለም አሁንም ከቤተ ክርስቲያናችን ተጠርጎ መውጣት ያለበት ቆሻሻ ነው። ጥንታውያን የወንጌል አርበኞች ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ይህንን ጉድ ቢያዩ እንዴት ያዝኑ? ወንጌሉን ከማንበብ ይልቅ ሕዝቡ በዚህ መጽሐፍ ተሸፍኖ ሕይወት ያለበትን የወንጌል ቃል እንዳይሰማ ተደርጓል። ወንድሞቻችንንም እያጣንበት ያለ መጽሐፍ ነው።
የኢትዮጵያው ሲኖዶስ አባላት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ታምረ ማርያምን አይቀበሉም አያምኑበትም፤ ሕዝቡን በመፍራት ብቻ ተሸክመውት ይኖራሉ። ነገር ግን እውነቱን እያወቁ ጠላቴ የሚሉአቸውን ማጥቂያ እና የፖለቲካ መሳሪያ ማድረጋቸው አልቀረም። የማሕበረ ቅዱሳንም የመጀመሪያዎቹ አመራሮች ታምረ ማርያምን እንደማያምኑበት ብዙ ጊዜ ባደረግናቸው ውይይቶች ተገንዝበናል። የማህበሩ ተራ አባላት ግን ይህን አይረዱም። የማህበሩ መሪዎች ይህ መጽሐፍ እናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የገባ የሲይጣን ስራ መሆኑን ልባቸው እያወቀው ጠላቴ የሚሏቸውን የቤተ ልርስቲያኒቱን ውድ ልጆች ለማጥቃት ሲሉ የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ማድረጋቸው እጅግ የሚያሳዝን ነው። ለማንኛውም ሕዝባችንን ማሳወቅ የምንፈልገው ሁለቱ በማያምኑበት ነገር የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆኖ ኃጢአት እንዳይሠራ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና የተቀበለቻቸው መጻሕፍት ሰማኒያ አንድ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ታምረ ማርያም እና መልክአ ሥእል አይገኙበትም። አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ እምነቱ መፈተሽ ያለበት በሰማኒያ አሐዱ መጻሕፍት መሆን ሲኖርበት በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝነው ባልተጣሩ እና እርስ በርሳቸው በማይስማሙ የደብተራ ድርሰቶች የቤተ ክርስቲያን ልጆች ጥቃት ሊፈጸምባቸው አይገባም።
ስለዚህ የኢትዮጵያው ሲኖዶስ እርሱ በማያምንበት እና ከሰማኒያ አሐዱ መጻሕፍት ውጭ በሆኑ መጻሕፍት አማካኝነት ስም አጥፍቷልና ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዚህ መጽሐፍ መፍትሔ በመስጠት ወደ ፊት ሊፈጠር የሚችለውን የመከፋፈል አደጋ ከወዲሁ ማስወገድ አለባት። የእርቅ ኮሚቴው እውነተኛ እርቅ ማምጣት ከፈለገ ይህን ጉዳይም ቢመለከተው መልካም ነው፤ የሁለት ግለሰቦች መስማማት ብቻ የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ችግር ሊፈታው አይችልም የሚል ሥጋት አለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
ከሙሉ ሰው

27 comments:

 1. የተዋህዶ ልጅ ነኝ ከአሜሪካNovember 1, 2011 at 6:16 PM

  እንደዚህ እራሳችሁን ስትገልጡ ጥሩ ነው!!!!!

  ReplyDelete
 2. mariam tamalidalech tamalidalech zimbilachihu atikebatru abatoch litareku silehone tekatilachihu new. yilik wedelibachihu temelesu

  ReplyDelete
 3. zewde ze-arat kiloNovember 1, 2011 at 8:42 PM

  ደጀ ሰላሞች?
  እናንተ ያላነሳችሁት ብዙ ግሳንግስ በተባለው ተአምር የተሰገሰጉ መዓት ሲሆኑ ተለቅመው እንዲወጡ ለብዙ ዓመታት የጮህንባቸው ቢሆንም የናንተ ሐሳብ “ይህን መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያናችን ሰይጣን አስርጎ ያስገባው የጠላት ተንኮል እንጂ ልናነበው እና ልንሳለመው የሚገባ መጽሐፍ አይደለም አሁንም ከቤተ ክርስቲያናችን ተጠርጎ መውጣት ያለበት ቆሻሻ ነው”አልተቀበልኩትም። ለምን ብትሉኝ የገቡ ስሕተቶችን ይውጡ በሚለው ማስተባቢያ ቋንቋ እስማለሁ’ንጂ በመጽሓፉ ያሉትን ቁምነገሮች ሳናይ እንዲሁ እንዳልተማረ ሰው በጅምላ ተጠራርጎ ይውጣ ማለት ተፈጥራዊ አነጋገርም አይደለም።
  ነገሩ እንኳን የናንተ አርቲክል እኔ አሁን ኮሜንት ያደረግሁት ነጥብ ለማንያዘዋል ዕድሜ ልኩ ዘርዓያዕቆብን እያመለከ ለሚኖር ያስቀውሰዋል። ደግሞ “ስሜ በመናፍቃን ማህደር ወጥቷል፤ አውቃችሗለሁ እነማን እንደሆኑ፤ ግድየለም ከቅዱስ ሲኖዶስ ስብስባ በሗላ ጉዘዬ ወደነሱ ነው” እያለ እንደወትሮው ወሬውን ሲቀድ ትናንት ሶስት ሆነን ከሙውታን ጓደኞቹ ጋር እናንተ ያልገለጻችሁት በሲኖዶሱ ስለደረሰባቸው ሽንፈት በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሲለቃቀሱበት አግኝተናቸዋል ።

  ReplyDelete
 4. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk mnafk hulem be Embtachen yeqenal ay aba diybilod

  ReplyDelete
 5. This book is full of mis conceptions and it is hard to be believed by most Priests, Deacons and bishops. I don't know why the church is still using it.

  ReplyDelete
 6. yematawkutn tarik atzebarku. Atse zerea yakob yeneberut be 1530 new???

  ReplyDelete
 7. ግልጽ መልዕክት ለነገረ መለኮት ምሩቃን ማህበር አባላትና
  ለቅ/ስ/መ/ኮሌጅ

  የቲኦሎጂ ምሩቃንንና ተማሪዎችን በበላይነት ለመቆጣጠርና በስሩ ለማድረግ የዐመታት ዐቅዱን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኘዉ ማ/ቅ/፤ ለዚሁ ተግባር የመደባቸዉ አባላቱ በምሩቃኑ ስም ማህበሩን የተቆጣጠሩት በመሆኑ፤ ማህበሩን ከማ/ቅ አመራር ለማላቀቅ ቲኦሎጂያን በመማር ላይ የምትገኙ ሁላችሁም ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንድትጀምሩ እያልን ለኮሌጁ ሰላም ሲባልም ጽ/ቤቱ በአስቸኳይ እንዲዘጋ የኮሌጁን አመራር ልንመክር እንወዳለን፡፡

  ReplyDelete
 8. Very nice topic i like it and i am agree with this wonderful explanation. May god bless you. Abba

  ReplyDelete
 9. pdf adrigulign ebakachihu. no amharic font

  ReplyDelete
 10. Ewnetem mulu sew.

  ReplyDelete
 11. Greetings,

  it is very intersting.. I belive reading the Scriptures is a great safeguard against sin.

  "let us honour only, and everyone will honour us; for if we despise one, that is God, everyone will despise us, and we will be lost" abba

  ReplyDelete
 12. አንድ አስተያየት ሰጪ እንደጠቆመው ዘርዓያዕቆብ በ1434-1468 ዓ/ም እንደገዛ በታሪክ አውቀዋለሁ። አሁን ትዝ ሲለኝ ግን የአርቲክሉ ጸሐፊ የሆንክ “ሙሉ ሰው” በ1530 ተጽፎ ተሰራጭተዋል ስትል ማብራርያ ያስፈልጋል። ምክንያቱ ቀደምት ደቂቀ እስጢፋኖስና እስጢፋኖስ ራሱ ለማለት ከፈለግህ ታሪኩ የተፈጸመው ዘርአያዕቆብ በነበረበት ጊዜ ነው፤ ምናልባት ለሗለኞቹ ከሆነ በመረጃ የተደገፈ መልእክት አስተላልፍ፤ አለበዚያ ዓመተ ምሕረቱ የማታውቀው ከሆነ እንደየግል ፍልስፍና በሪሰርች ሜቶዶሎጂ ምልክት [1530 ]ከምትጠቀም በጥያቄ ምልክት [1530?] ብታስቀምጠው ለመሐይምነትህ ትንሽ መምለጫ ታገኝ ነበር።

  ReplyDelete
 13. my comment is for those commentators who insult the article writer rather than criticizing him by evidence. please act like good Ethiopian and tell us your idea with out using offensive words.

  ReplyDelete
 14. ኢትዮጵያ ቀደም ሲል በኦሪቱ በኋላም በወንጌል የበራላትንና ከእግዚአብሔርም የተሰጣት ከአፍሪካ እስከ በመካከለኛው ምስራቅ ገናና ታሪክ እስከ የመንም ድረስ የነበራትን የግዛት እንዲሁም የጸጋ፤የበረከት፤ መሬቷ ወርቅ፤ ወንዞቿ ወይን፤ ደኖቿ ኤደን፤ ሕዝቦቿ ታታሪ ሆነው የኖሩበትን ዘመን የቀየረውና የገለበጠው ምንኩስና የሚባለው የሰነፎችና «የአጸድቃለሁ፤ እኔም በስራዬ እጸድቃለሁ» የሚለው ማኅበር ከተንሰራፋ በኋላና ወንጌልን አሽቀንጥሮ ቤተመቅደሱን የሞላው ገድል የሚሉት የእግዚአብሔርን ክብር በመጋረድ ቅዱሳን ለተባሉት ክብርና መንቀጥቀጥን እንዲሰጥ የሚያስገድደው መጽሐፍ ቦታውን ከያዘና ተአምር የሚባል የዘርዓ ያዕቆብ የግዝት መጽሐፍ ብዙ ደም አፋስሶ፤ አፍንጫና ጆሮ አስቆርጦ፤ በሕይወት ሳሉ ከጉድጓድ አስቀብሮ የደም መሬት ኢትዮጵያ ላይ ከነገሰ በኋላ ነው። በኦርቶዶክስ ቤ/ክ መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ማንበብ የተጀመረው የፕሮቴስታንት እምነት መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ ስለሚሰብክ እሱን ለመቋቋም ተብሎ እንጂ ከእቃ ግምጃ ቤት ወጥቶ አያውቅም። በትግራይ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ የታየ ጴንጤ ወይም ካቶሊክ ያሰኝ እንደነበር አይዘነጋም። ድርሳነ ሚካኤልን ወይም የሆነ ተአምርን ከተሸከመ እሱ የወንጌል ሰው ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊ እንደሆነ ይቆጠራል።
  ሌላው ቀርቶ« ኦርቶዶክሳዊ ሆኖ «ኢየሱስ ጌታ ነው»ብሎ መናገር እንደጴንጤ ያስቆጥራል። ማር 12፤29...ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው» የሚለውን መመስከር ወንጀል ሆኖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለው 78 ሰው ቅርጥፍ አድርጎ በላ የሚባለውን የተረት ታሪክ መናገር እንደክርስቲያን የሚያስቆጥረው በምን ስሌት ነው?
  እኔ ኦርቶዶክሳዊ እምነት ተከታይ ነኝ። እግዚአብሔር የሰጠኝን ክርስትና ሲኖዶስ አይወስድብኝ፤ ማቅ አይከለክለኝ። ይህንን ተአምር የሚባለውን የዘርዓ ያዕቆብ የተረት መጽሐፍ ገመና በማጋለጥና ከተቀመጠበት የወንጌል ስፍራ በማውረድ ወደመጣበት ለዚያውም ወደማያውቁት ግብጾች እመልሰዋለሁ፤ ከወንድሞች ጋር እንመልሰዋለን። እስኪ ይህንን ልብ በሉት!«ላቲ ይደሉ ክብር ወስብሐት ዘምስለ ወልዳ አምልኰ ወስግደት» መስተብቍዕ ዘማርያም። ትርጉሙ- ለእርሷ ክብርና ምስጋና ከልጇም ጋር አምልኰና ስግደት ይገባታል፤ ማለት ነው። ማርያም በድንግልና በንጽሕና ጌታን ወልዳለች፤ ቅድስትና ብጽዕት እያለ ትውልድ ሁሉ ይጠራላታል፤ ይህ የተጻፈ እውነት ነው። ያ ማለት ግን ማርያም እግዚአብሔር ሆና አምልኰና ስግደት ይደረግላታል ማለት አይደለም። እርሷም የእግዚአብሔር አምልኰና ስግደት ይገባኛል አትልም። የነገረችን እውነት ተጽፎ ተቀምጧል፤ « ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች»ሉቃ 1፤47 ነው ያለችው እንጂ እኔ ጌታና አምላክ ስለሆንኩ አምልኰና ስግደት እፈልጋለሁ አላለችም። ይህንን መቃወም ተሃድሶ ወይም ጴንጤ መሆን አይደለም። የተቀበረውን እውነት መግለጥ እንጂ!! ይህ ተአምር ከእስላሞች ጋር ሊያጋጨን የመሐመድ ሚስት ግመል ናት ይለናል። ብልቱም በወገቡ ላይ እንደገመድ የታሰረ ነው ሲል ሲዋሽ ይገኛል። (ተአምር 19) መሐመድ የታወቁ 9 ሚስቶችና ብዙ እቁባቶች እንዳሉት «ሳሂህ አልቡካሪ ቡክ5፤ ምእራፍ45 ቁጥር 282 በግልጽ ይናገራል። የሚስት ችግር እንኳን መሀመድ ተከታዮቹም ችግር የለባቸውም። ደግሞም ብልቱ በወገቡ ላይ ይጠመጠማል የሚለው «የጭራቅ መጣልህ» ተረት ያለዘርዓ ያእቆብ ተአምር በስተቀር የትም አይገኝም። ለመሀመድ ያለውን ጥላቻ ከማንጸባረቅ ባሻገር የመሀመድ የወንድ ብልት እንደማንኛውም ሰው የሆነና ሚስቶችም አግብቶ ልጆች የወለደ ሰው መሆኑ ይታወቃል። ይህንን የተረት ተአምር እሁድ አሁድ ለመስማት ያልመጣ በማይፈታ ጽኑ እስራት ፈጽመን አወገዝን ይባልለታል። ብልቱ ወገቡ ላይ የተጠመጠመውን የመሀመድ ተረት ያዳመጠ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል ተብሎ ሰው ከቁርባን እንዲዘናጋ ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ሲታወጅ ይገኛል። ወገቡ ላይ እንደገመድ ብልቱ መጠምጠሙም አውቃለሁ ተብሎ የሀሰት ምስክርነት በመስጠት ሰዎች ይሳለሙታል። ምንኛ አሳዛኝ ነው?

  ReplyDelete
 15. Holly bible! Holly bible! Holly bible! our church need that.

  ReplyDelete
 16. Sewe yetefeterew zemenun hulu metefo lesera sayehone melkam neger sereto Kerestosen meselo leyalef new.....ekuye tegebare mechereshaw mote new...yegenezabe eteret kalebachu yabatoch eger sere kuch belachu temaru enji kuche belachu ataweru madamete amezazeno lemefered yeredal..Egziabhier amelak lebonachun yemelese!

  ReplyDelete
 17. Thank you very much for your analysis. Ayachihu bedemb sitasawiqun tiru new? Man min endemiasib maweqim tiru new. Hulun mermiru melkamun yazu ayidel yemilew - man endehonachihu beteley beqirbu eyasaweqachihun new. Yih ye egziabher sira newina egnam bedenb enanebachihualen. Thank God egnas tikikilegnawin yemiastemiren alen. Abatachin Abune Paulosi'n chemiro bizu bizu abatoch, liqawinte betekiristian alulin.
  Eski yichin tiyaqe liteyiqachihu - sile gedl, sile teamire mariam bedenb asaweqachihunal enameseginalen. Wengelis tisalemalachihu, eski lezih degmo mabraria situ? Betekiristianinis tisalemalachihu ( I mean Tabot?) Menafiqan eski lezih mabraria situn.

  ReplyDelete
 18. Mechem bihon diabilos Emebetachen sttera aywodm

  ReplyDelete
 19. for the comment:Mechem bihon diabilos Emebetachen sttera aywodm

  yes, your are right diabilos do not like our mother to be praised. but this book is full of false statement or out of reality and controversial to the bible. I was thinking like, however I was also suspicious when they read it after the Sunday service, particularly for the statement which said " if you listen this mariam miracle it will count as you take the holly commune." if that is true Jesus is blood is useless, therefore by the name of our mother cost her, diabious will enjoying. I believe this book should be out of our church.

  ReplyDelete
 20. ''አሁንም ከቤተ ክርስቲያናችን ተጠርጎ
  መውጣት ያለበት ቆሻሻ ነው።'', ''ብፁዐን ሊቃነ
  ጳጳሳት ታምረ ማርያምን አይቀበሉም
  አያምኑበትም'' , ''የደብተራ ድርሰቶች የቤተ ክርስቲያን ልጆች
  ጥቃት ሊፈጸምባቸው አይገባም።'' 100% menafek thank you for revealing your self.

  ReplyDelete
 21. መንፈስ ሁሉን ይመረምራል፣ ነገር ግን በማንም አይመረመርም። ተአምረ ማርያምን ለመረዳት እንዴት ይቻላችኋል?

  ReplyDelete
 22. are ebakachu ene aba selama weshet eko alekebachu betam dekmoachehual ebakachu weshete kenesu

  ReplyDelete
 23. Emebetachin Weladite Amlak yikir tibelachu ewinetawin meged tasayachu. Esuwan satiyizu yetim mediress yelem. Enatun Eyawaredu ersun eketelalehu malet mogninet new.

  ReplyDelete
 24. መጀመሪያ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ከእስጢፋኖስ ጋር ያጣላቸው ብዙ ነገሮች አሉ:: እስጢፋኖስ ለሥዕል; ለመስቀል : ለንጉሥ አልሰግድም አለ:: ንጉሡም የአምላክ እናት; የመስቀል እና የራሱም ክብር ስለተነካ ቀጥቶታል:: ቅ/ጴጥሮስ “ለገሮች ብቻ ሳይሆን ለጠማማች ገዢዎች በፍርሃት ሁናችሁ ተገዙ”(1 ጴጥ 2:18) የሚለዉን ንጉሡ በደንብ ስለሚያዉቀው ለክፉ ንጉሥ ሳይቀር ተገዙ እያለ ቅ/ጴጥሮስ በመንግሥቴ ይህንን አይነት ትምህርት አታስተምር አለው :: እምቢ! አለ:: እስጢፋኖስ ተቀጣ::ንጉሡ ተቆጥቶ ደቂቀ እስጢፋኖስን በዘመኑ ሲቀጣቸው ኑሯል::

  ተሃድሶዎች መጽሓፍ ቅዱስን አትቀበሉም እንጂ ተአምረ ማርያም ከመጽሓፍ ቅዱስ አይጋጭም እናንተ ካላጋጫችሁት በስተቀር::

  በመጀመሪያ ተአምረ ማርያም የተጻፈው በአጼ ዘራዓ ያዕቆብ ነው የሚል ምንም መረጃ የለም:: እስቲ አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ጻፈ የሚል አምጡ:: ተአምረ ማርያም እንደሚለው በቅ/ደቅስዮስ እንደተጻፈ ይነግረናል:: በንጉሥ ዘመን ከአረብኛ ወደ ግዕዝ ተተረጎመ ይላል እንጂ ንጉሡ ጻፈው አይልም::
  ተአምረ ማርያም የሚለው ፍጥረት ሁሉ ለአዳም ተፈጠረ ይለናል:: ለእመቤታችን ተፈጠረ ማለት ምኑ ያጠራጥራል? እሷ እኮ አዳም የአዳም ልጅ ነች::( በዘፍ1:26-30) እንድምናነበው”እግዚአብሔር ፍጥረቱን ሁሉ ለአዳም ፈጥሮ ግዛቸው ለአንተ ነው የፈጠርኩት:እያለ አይ ፍጥረት ለአዳም; ለእመቤታችን አልተፈጠረም ካላችሁ ከእግዚአብሔር ጋር እየተጣላችሁ ነው:: ከአዳም እና ሔዋን እመቤታችን ትበልጣለች:: ይህ የእግዚአብሔር ምስጢር የገባው ፍጥረት ሁሉ ሰለ እመቤታችን ተፈጠረ (ሰለ አዳም ተፈጠረ አለ) ፍጹም መጽሓፍ ቅዱሳዊ ነው:: ሌላው የዚህ ምስጢር በኋለኛው ዘመን ክርስቶስ የሰውን ሥጋ ተዋህዶ እንደሚያድን የእግዚአብሔር ዕቅድ ነበር ለማለት ነው:: (ሉቃ1:48) እመቤታችን “ትውልድ(ፍጥረት) ሁሉ ያመሰግነኛል” ብላለች::ይህ በወንጌል የተጻፈ ነው መሰረዝ አትችሉም:: ይህንን ለማሳየት ነው ፍጥረት ሁሉ ለእመቤታችን ተፈጠረ ያለ:: ምስጢረ ሥጋዌ ያልገባው ይህንን ለመረዳት ይከብደዋል:: የሚያስተዉል ካለ ከተአምረ ማርያም ከምናገኘው በላይ የሚያስደንቅ የድንግል ማርያም ተአምር እኮ ሉቃስ ወንጌል ላይ ተጽፏል::(ሉቃ1:44)″የሰላምታሽን ድምጽ በሰማሁ ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኔ በደስታ ዘለለ” በማለት የመጥምቁ ዮሓንስ እናት ቅ/ኤልሳቤጥ ለወላዲተ አምላክ በድንግል ምክንያት የተፈጸመዉን ተአምር ነገረቻት:: ይህ እኮ ወንጌል ዉስጥ የተጻፈ ተአምረ ማርያም እኮ ነው::
  ዘፍ25:18″እግዚአብሔር ሁለት ኪሩቤል(መላእክት)ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ አለው ሙሴም ሠራ:: አሁንም ከብዙ መቶ አመታት በኋላ ሰሎሞን “በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል(መላእክት) ሠራ”1ነገስት6:23 እንግዲህ እግዚአብሔር የተቀረጸ ምስል አትቅረጹ ብሎ,ወዲያው ሁለት ኪሩቤል ቅረጽልኝ ብሎ እግዚአብሔር ያዘዘው: መናፍቃን እንደሚሉት ሳይሆን: የጌታችንን; የእመቤታችንን; የመላእክትን; የቅዱሳኑን ሥዕል መከልከሉ ሳይሆን የሌላ ምስል እንዳንቀርጽ ነው የታዘዝነው ብለን ማመን አለብን:: አለበለዚያ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው ።ዘጼ20:4&5 ምስል አትቅረጽ አለ:: ዘጸአት25 የኪሩቤልን ሥዕል ቅረጽ ሲል ሁለቱ ፈጽመው አይገናኙም:: ስለዚህ የቅዱሳንን ሥዕል መቃወም ማለት የኪሩቤልን ሥዕል ሥሩ ብሎ ያዘዘዉን እግዚአብሔርን መቃወም ነው:: አታምታቱት:: ስለዚህ እነሙሴ በኪሩቤል መካከል ይሰግዱ እንደነበር እኛም ለቅዱሳን ሥዕሎች እንሰግዳለን:: እስቲ አስቡ ዲያብሎስ እንኳ የራሱን ምስል እንደሚያሠራ ምስሉም እንደሚተነፍስ; እንደሚናገር ብሎም የማይሰግዱትን እንደሚአስገድል ቅ ዮሐንስ በራዩ ጽፎት ይገኛል:: ራዕ 13:15 &16 እንዴት ሰይጣንን ያሸነፈው ቅዱስ ሚካኤል ሥዕሉ; ከዚህ ርኩስ ፍጥረት በበለጠ ተአምር አይሠራ? ክብርስ የማንሰጥ በምን ምክንያት ነው?ከላይ ለኪሩብ (ለመልአክ) ሥዕል እንዲቀረጽ ፈጣሪ እንዳዘዘ አይተናልና:: የእምቤታችን ሥዕልም ከዚህ እጅግ የበለጠ ተአምር ስለሚፈጽም ለሥዕሏ ክብር እንሰጣለን; እንሰግዳለን:: አሁን የነቅዱስ ሚካኤልን እና የሌሎችን ቅዱሳን ሥዕሎች የሚቃወም ነገ እኮ ቅ/ዮሐንስ እንዳለው የአውሬውን ምስል ለመቀበል ነው:ሩጫው:: ተአምረ ማርያም ላይ ለእመቤታችን ሥዕል እንድንሰግድ; ተአምሯን እንድንሰማ ሲነገረን; ክርስቶስን የሚያምን ክርስቲያን; የእመቤታችንን ተአምር ለመስማት አይከበደውም:: እርግጥ ተጠራጣሪዎች አያደርጉትም:: አሁን ተአምረ ማርያምን የተቃወማችሁ: ነገ መጽሓፍ ቅዱስን ትቃወማላችሁ ምክንያቱም በወንጌል” በኔ የሚያምን እኔ የማደርገዉን ያደርጋል;ከዚህም የሚበልጥ”ዮሐ 14:12 የሚለዉን ቃል የሚቀበል ተአምረ ማርያም ለመቀበል አይከብደዉም:: ነው ቀስ ብላችሁ እመቤታችን አታምንም በሉ እና ሰይጣን እንኳ የማይጠራጠረውን ካዱና ይለይላችሁ:: እኛ እመቤታችን ክርስቶስ ያደረገዉን አድርጋለች: ታደርጋለች: አሁን ተአምረ ማርያም ከአንበባችሁት በላይ እንደምታደርግ ክርስቶስ “ከዚህ የሚበልጥ” እያለ በወንጌሉ ይናገራል ሰሚ ካለ:: ይህንን መሰረዝ አትችሉም:: ክርስቶስን የሚወድ እመቤታችንን ይወዳል ለርስዋ ሥዕልም ይሰግዳል; ተአምሯን ይሰማል:: መቅድሙ ላይ እንደተጻፈው:”የታወቀ ምክንያት ካልከለክለው በስተቀር” ክርስቲያን ነኝ እያለ ወደ ቤተ ክርስቲያን የማይሄድ: እና ተአምሯን የማይሰማ :እሷን ብቻ ሳይሆን ልጇንም እንደናቀ ሰለሚቆጠር; ተወገዘ:: መጽሓፍ ቅዱስ ዕብራዉያን 10:28″የሙሴን ሕግ የናቀ ሁለት ሦስት ምስክሮች ከመሰከሩበት ፈጽሞ ይሙት” ይላል:: የክርስቶስ እናት በልጇ ቸርነት ያደረገችዉን ተአምር የሚንቅማ እንዴት አብዝቶ አይቀጣም? ይቀጣል እንጂ:: ክርስቶስ በስጋ የመጣ አምላክ ብሎ የሚታመን መንፈስ በስጋ የወለደችዉን እመቤታችንን ያከብራል:: ለሥዕሏ በመስገድ; ተአምሯን በመስማት ፍቅሩን ይገልጻል::ያወገዙት በትዕቢት ወደ ቤተ ክርስቲያን አልሄድም ብሎ የቀረዉን: እንደሆነ መቅድመ ተአምረ ማርያም ይነግረናል::ቅ ጳውሎስ “እኛ የክርስቶስ ልብ አለን”1ቆሮ2:16:” እኔ ክርስቶስን እመስላለሁ::እናንተም እኔን ምሰሉ አለን”1ቆሮ 11:1 ቅ ጳውሎስ እንዲህ ካለ የእመቤታችን መልኳ;ሃሳቧ;ልቧ የአምላክን(የልጇን) ይመስላል ቢል ምኑ ላይ ነው ከመጽሓፍ ቅዱስ የሚጋጨው? በድጋሜ ቅ ጳውሎስ የገላትያ ሰዎች ለሱ ያላቸውን ፍቅር ሲገልጽላቸው እንዲህ ብሎ ጽፎላቸዋል”አዎን እንደ ክርስቶስ ተቀበላችሁኝ” ገላ4:14:: እና የክርስቶስን እናት እንደ ክርስቶስ አክብረን ብንቀበላት ምኑ ነው ከመጽሓፍ የሚጋጨው?ራሱ ክርስቶስ “እናንተን የተቀበለ እኔን ተቀበለ” ብሎናል እኮ: ካስተዋልን ማቴ 10:40 ስለዚህ ዘጠኝ ወር በማሕጸኗ የተሸከመች ከሓዋርያት: ከነብያት; ከቅዱሳን ሁሉ ትበልጣልች::

  ReplyDelete
 25. ቅዱስ ቁርባን መቀበል ካልቻለ ተአምረ ማርያም ሰምቶ ይሂድ የሚለው ግልጽ እና ጥሩ ምክር ነው::ይህ የአባቶቻችን ምክር ነው:: እንግዲያስ መቀበል ላልቻለ ምን ይበል?ተስፋ ይቁረጥ?” ካልቻለ” ምን ያድርግ?መልሱን ንገረኝ?በእመቤታችን ተማጽኖ ይሂድ አለ እንጂ ሥጋ ወደሙን ይተካዋል:አትቀበሉ:አላለም::አታጣሙት:: እኔ መቀበል ካልቻልኩ ምን ታደርገኝ? በቀኝ የተሰቀለው ስጋ ወደሙ ተቀበለ አይልም::በሚያስደነቅ ምሕረቱ ማረው:: ከነብዩ ኤልያስ አንበልጥ:: እሱ እንኳ ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን(2ነገስት2:9-12) “ካንተ ሳልወሰድ አደርገልህ ዘንድ የምትሻውን ወደ እኔ ለምን(ጸልይ)”አለው:: የኤልሳዕም ጸሎት ልመና “ያንተ መንፈስ እጽፍ ድርብ ሆኖ በኔ ላይ ይወረድ አለው” ኤልያስም ሳርግ ካየህኝ ይሆንልሃል አለው:: አየው መንፈሱ እጽፍ ድርብ ሆኖ አረፈበት::
  ነብዩ ኤልሳዕ ከሞተ በኋላ በአጽሙ የሞተ ሰው አስነሳ:: 2ነገስት13:20-21 ስለዚህ ነብዩ ኤልሳዕ ወደ ኤልያስ ከጸለየ እና ኤልያስም ወደሱ እንዲለምን ከመከረው:እኛም ኣባታችን ሆይ ብለን: ወደ ወላዲተ አምላክ መጸለያችን ምኑ ነው ተአምረ ማርያም ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጨው? ይህ ተአምረ ማርያም ጋር ቢጻፍ ኖሮ ይሰረዝ ትሉ ነበር:: እግዚአብሔር ለሙሴ እኮ የሰጠዉን ሥልጣን ብናስታዉሰው;ብናስተዉለው እንዲህ የእመቤታችንን ክብር አንቃወምም ነበር:: እየረሳነው እኮ ነው:: ዘጸአት7:1 “ሙሴ እይ እኔ ለፈርዖን(ለግብጽ) አምላክ አድርጌሃለሁ አለው”አሁን ልጇ የዚህ አምላክ(ለዚህ ትውልድ)አምላክ አድረጌሻለሁ ቢላት መችም ተሀድሶዎች ሰላማዊ ሰልፍ መዉጣታችሁ አይቀርም:: እናቱ ሰለሆነች;እናትና አባትህን አክብር ብሎ ያዘዘን እናቱን ሲያከብራት አይተናል; እናያለንም(ያሳየናል):: ዲያብሎስ ቢቆጣም:: የእመቤታችንን ክብር ለሙሴ የሰጠዉን; ለሷማ አብልጦ አይሰጣትምን? ይሰጣታል:: ከዚህ የምረዳው ከፈጣሪ ጋር እየተጣላችሁ ነው::እንኳን ለእናቱ ለእመቤታችን ይቅርና በፍርድ ቀን በ12 ዙፋኖች ተቀምጠው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚገባዉን አና የሚወጣዉን የሚፈርዱ እኮ ሓዋርያት ናቸው ማቴ19:28″የሰው ልጅ ሲመጣ በ12 ዙፋኖች ተቀምጣችሁ ተፈርዳላችሁ”አላቸው ::በዚያን ጊዜ ዳኞች(ሓዋርያት) ይቀየሩ ማለት እንደማትችሉ አሁን እወቁት::ሰማይ ምድር ቢያልፍ ቃሉ አያልፍምና;አንድ ጊዜ በቃሉ ስልጣኑን(የመንግስተ ሰማያትን ቁልፍ) ሰቷቸዋልና(ማቴ 16:19)ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን በላይ በሰማይ በታች በምድር የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚተካ እንደሌለ ታስተምራለች::ሁሉም ወደ ሥጋው ወደሙ እንዲቀርቡ;ከቅዱስ ቁርባን እንዳይርቁ ትመክራለች::ነገር ግን ለዚህ ያልበቁትን ተስፋ እንዳይቆርጡ ለማድረግ; ንስሐቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ በደጅ ጥናት ያሉትን;በትምህርት ላይ ያሉትን ሁሉ መቀበል የማችሉትን እንጂ የሚችል ሥጋዉን ደሙን ተቀበሉ ያልቻላችሁ ተአምረ ማርያም ስሙ እና ሂዱ ብላ ትሰብካለች:: በተጨማሪ እየቆረቡን ያለነዉንም መቀበል የማንችልበት ችግር ሲገጥመን:ተአምረ ማርያም ሰምተን;በርሷ ተማጽነን እንሄዳለን:አንጠራጠርም::ይህ እኮ ወንጌልም ላይ ማርቆስ 11:23-24″እውነት እላችኋለሁ; ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ባይጠራጠር …የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ:ይሆንላችሁማል::” የምናምን ኦርቶዶሳዉያም እንደሚደረግለን እናምናለን:ይደረግልናል::ከዚያም በእመቤታችን ምልጃ ንስሐ ገብተን;ለሥጋው ወደሙ እንበቃለን::
  ውግዘት በተአምረ ማርያም አልተጀመረም ቅ:ጳዉሎስ ሁለት ጊዜ “ከተቀበላችሁት የተለየዉን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ(የተወገዘ) ይሁን” ብሏል::45 ሚሊዮን ኦርቶዶክሳውያን የተቀበልነው የተሰበከልነን የሚቃወመዉን መጀመሪያ ቅ ጳዉሎስ በኋላ ደግሞ እነ አቡነ ገብርኤል እና ኣባ ሚካኤል አዉግዘዉልናል::በሥጋዉም በምድር በሰማይ በነፍሱም የክብር ትንሳኤ የለዉም አለ ለዘላለም ይቃጠላል ሲል ነው::
  አሥሩን ትእዛዛት እና ስድስቱን ቃላተ ወንጌል የፈጸምኩ እኔ ነኝ የሚል ማን ነው?ተአምረ ማርያም የሚለው ትእዛዙን ለመፈጸም ባንችልም(አሁንም አልቻልንም) ተስፋ አለን; በክርስቶስ አምነን በእመቤታችን ተማጸነን እንድናለን ነው ያለን:: ትእዛዙን አትፈጽሙ አላለም:ት እዛዙን አትፈጽሙ እንደሚል አድርገህ አታቅርበው:: ይህንን አነጋገር የወሰደው ከቅ ጳዉሎስ ነው”በሕግ ለመጽደቅ የምትፈልጉ ሁሉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል” ይለናል::ገላ5:4;ገላ 2:16″ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ስራ ስለማይጸድቅ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል::” እኛም በክስቶስ አምነናል;በወላዲተ አምላክ ተማጽነናል:: የሐዋር13:39″…በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን” ሮሜ 3:20 & 28 “ይህም የሕግን ሥራ በመስራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው” ሮሜ8:3″ከሥጋ የተነሳ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለዉን ;እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢያተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢያትም ምክንያት ልኮ አድርጓልና” ስለዚህ በተአምረ ማርያም የምናገኘው ሕጉንና ት እዛዙን ባለመፈጸማችን ተስፋ እንዳንቆርጥ;ልክ ቅ/ጳዉሎስ እንዳስተማረው;በልጇ ቸርነት;በወላዲተ አምላክ አማልጂነት ትድናላችሁ ቢለን;ተስፋ ለማቆረጥ የሚጻፈው ጽሑፍ መቆም አለበት::
  የብላዔ ሰብዕ 78 ነፍስ አጥፍቶ መማሩ በማቴ10:42″በደቀ መዝሙር ስም ቀዝቃዛ ዉሃ ቢጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም” በሚለው አምላካዊ ቃል መሰረት ነው:: ተአምራ ማርያም እንደሚነግረን ስምዖን የተባለው ይህ ሰው ብዙ ነፍስ ካጠፋ በሗላ ንስሓ ገባ:ተጸጸተ ልክ በቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ::በወንጌሉ መሰረት ለድሀ ከደቀመዛሙርት ሁሉ;ከፍጥረት ሁሉ በከበረችው በእመቤታችን ስም ቀዝቃዛ ዉሀ ለድሀ አጠጣ:: እመቤታችም በወንጌሉ መሰረት ማርለኝ አለችው; ማረላት::በቀኝ የተሰቀለ ከብላዔ ሰብዕ(ከዚህ ሰብ በላ) የበለጠ ይሥራ; አይሥራ እኛ አናዉቅም:: ቃል ኪዳን ሲሰጥ ክርስቶስ ገደብ አላስቀመጠም(ይህንን ያህል የገደለ አልምርም:የሚል የለ)::በደቀ መዝሙር ስም ያጠጣ አለ እንጂ::ስለዚህ የወንበዴውን መዳንም እየተጠራጠሩ በወንጌል አምናለሁ ማለት አይቻልም:: በወንጌል ተጽፎ ነው እንጂ በቀኝ የተሰቀለው ታሪክ በተአምረ ማርያም ቢጻፍ ኖሮ አይቀበሉትም ነበር::
  ይቀጥላል!….

  ወስብሃት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር

  ReplyDelete
 26. ውድ ኢትዮጵያውያን እውነተኛ ክርስቲያን ወንድሞቼ እኔም እንደ እናንተው ለምን እውነቱ አይወጣም የምል ፈጣሪንም ዘውትር እባክህ እውነትን ወደ ፊት ለፊት እንድናወጣ መንገድን አሳየን እያሉ ከሚማጸኑ ወገን ነኝ::

  ለማህበረ ቅዱሳን አመራሮች እና ድብን ብሎ ቢሞትም ታማኝ ሚስኪን እስረኞች ላስቀረው ለዘርዓ ያዕቆብ የምለው ነገር እንደሚከተለው ነው::
  መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:- 10
  እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን። ወደ ሮሜ ሰዎች 14፥12

  ReplyDelete