Monday, November 7, 2011

ማሳሰቢያ ለጸሐፍትና ለአንባብያን - - - Read PDF

አባቶች ብለን የምንጠራቸው የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪዎች እንደ እግዚአብሔር ቃል ሳይሆን እንደ ሰው አእምሮ፣ በፖለቲካዊ አካሄድ፣ ሥጋዊ ውሳኔዎችን እየወሰኑ ሲሄዱ ዝም ለማለት አልቻልንም። ሕዝቡ ምን ያስፈልገዋል? ወደ ፊት ለሚመጣው ትውልድስ ምን እናቆየው በሚለው ላይ በመወያየት ፋንታ በሥጋዊ ጉዳይ ጊዜ ማሳላፋቸው፣ ከዚያም በላይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት እንፈጽም? በማለት መንፈሳዊ እንቅሥቃሴ ከማድረግ ይልቅ የማህብረ ቅዱሳንን ፈቃድ ለመፈጸም በቤተ ክርስቲያናችን አናት ላይ መቆማቸው የተከሰሱትን ሰዎች አስከፍቷል። በዚህም ምክንያት አንዳድ አሳፋሪ [ልንሠውራቸው ያልቻልናቸው]ጽሑፎችን ስናቀርብ ቆይተናል።

የሁለቱን ማለት የማህብረ ቅዱሳንን እና ተሃድሶ የተባሉትን ሰዎች ልዩነት በርጋታ ተመልክቶ ሁለቱንም የሚያስማማ መንፈሳዊና አባታዊ አመራር ከመስጠት ይልቅ እንደ ፓርላማ አሠራር በጅ ብልጫ ያረፉትን እና በሕይወት ያሉትን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንት ለማውገዝ ጣት መጠቆማቸው ብዙዎቹን አስቆጥቷል። ይህ አካሄድ ለማንም የማይበጅ ሩጫ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን። ድሮ መናፍቅ ተብለው በጅ ብልጫና በጫጫታ ስማቸው ጠፍቶ፣ እንዳይናገሩ መድረክ ተከልክለው በግፍ ተባረው ነበር። አሁን ግን እግዚአብሔር የሚጮኹበት መድረክ ሰጣቸውና ማን አውጋዥ ማን ተወጋዥ እንደሆነ ለማሳየት ችለዋል።

ሊቃውንቱን ለማውገዝ የተነሡ ሰዎች ምን ዓይነት እንደሆኑ ለኢትዮጵያውያን ለማሳየት ተችሏል። ለጊዜው የጳጳሳቱን ነውር መግለጡን እናቆየዋለን። ይህ ገደብ ባስቸኳይ ይጠራል እስከተባለው የሲኖዶስ ጉባኤ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። እስከዚያ ስብሰባ ድረስ ባስተምህሮ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የሚካሄዱ አመጾችን በማጋለጥ እንድትጽፉ እናሳስባለን።

   በታቀደው የአባቶች ስብሰባ ጳጳሳቱ የሚይዙትን አቋም አይተን ስለጳጳሳቱ የሚጻፉ ጽሑፎችን ለማውጣት እንወስናለን። ይህን ውሳኔ ልንወስን የቻልነው ምናልባት ወደ እውነት ተመለሰው የእግዚአብሔርን ሥራ ይሠራሉ ብለን ተስፋ ስለምናደርግ ነው። እውነቱን እያወቁ የማህበረ ቅዱሳንን የፖለቲካ ውሳኔ የሚከተሉና እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት፣ የማይሉ ከሆነ ግን እውነተኛ መረጃ የያዙ ጽሆፎችን በዚህ ብሎግ እናስተናግዳለን። እስከዚያ የስብሰባ ቀን ድረስ ግን ጸሐፍት የሆናችሁ ሁሉ በሚከተሉት ርእሶች እንድትጽፉ እናሳስባለን

 . መንፈሳዊና አስተምህሮ ነክ የሆኑ ጉዳዮችን እንጽፋለን፣ የሐስት ድርሳናትን፣ ገድላትን፣ የጸሎት መጻሕፍትን፣ ከመጻሕፍ ቅዱስ አንጻር እናያቸዋለን።

 . ተጀምረው በቀሩ የቤተ ክርስቲያን ሕንጻዎች፣ ሕንጻዎቹ በታቀደላቸው ጊዜ ያላለቁበትን ምክንያት፣ በሕንጻ አሠሪ ኮሚቴና በሰበካ ጉባኤ የሚካሄዱትን ከፍተኛ ሙስናዎች በዚህ ብሎግ ማጋለጥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

. በአምስቱ ማለት በአስተዳዳሪው፣ በጸሐፊው፣ በሒሳብ ሹሙ፣ በቁጥጥሩ፣ በገንዘብ ያዡ፤ በገንዘብ ቆጠራ ወቅት በየአባያተ ክርስቲያናቱ የሚካሄዱ ዝርፊያዎችን በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመርኩዛችሁ እንደትፉ እንጋብዛለን።

. በመናፍስታዊ አሠራር በጥንቆላ፣ አጋንንትን በአጋንንት አለቃ በማጫዎት በሕዝባችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እናጋልጣለን። እናጠምቃለን የሚሉ ጠንቋዮች ሙታን ሳቢዎች ጋኔን የተዋረሱ፣ በሱዳን አስማት በሕዝባችን ላይ የጨከኑ የጠላት ተላላኪዎች በየሥፋራው በማርያም ስም የሚፈጽሙትን ወንጀል ከነአስማቱና ከነ አሠራሩ ለፍርድ እናቀርባለን።

. በአመንዝራ ሕይወታቸው እንዳሉ ወንጌል እንሰብካለን የሚሉ ፌዘኞችን፣ እውነቱን ክደው ለሆዳቸው የሚሠሩትን፣ መጸሐፍ ቅዱስ እናሰራጫለን ብለው ከፕሮቴስንታቱ እርዳታ ካገኙ በኋላ መርካቶ ሸጠው የሚበሉትን፣ ወዘተ ሁሉ እንዳስሳለን፣

. የክህደት መዝሙሮችን ገብያ እያዩ የሚዘምሩ፣ ከኦርቶዶክሳዊ አስተምሮ ውጭ የሆኑ፣ ያለምንም ከልካይ በመዝሙራቸው ክህደትን የሚያሰራጩ፣ ጥሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መዝሙር ቢዘምሩም የዘመሩት ለገንዘብ ማግኛ እንጂ የነርሱ አኗኗር እንደሚዘምሩት አይደለም፣ እነዚህም መዳሰስ አለባቸው።

. በቅዳሴ፣ በዲቁና፣ በመርጌትነት፣ በቤተ ክርስቲያን ተቀጥረው በትርፍ ጊዜያቸው የሚጠነቁሉ፣ የማፍያ ሥራ የሚሠሩ፣ በምታትና በአፍዝ አደንግዝ ደብረ ዘይት በሚገኘው ቢሾፍቱ ሐይቅ የሚፈጸመውን ወንጀልና የቤተ ክርስቲያናችንን ዲቃላዎች እናጋልጣለን።

 ከዚህ በላይ በዘረዘርናቸው ጉዳዮች ላይ ያላችሁን እውነተኛ መረጃ ከስም ማጥፋትና ከጠላትነት ነጻ በሆነ መንፈስ እንድትልኩልን እንጠይቃለን።

የድሬደዋ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ሥራ የተፈጸመበትን የሙስና ተግባር እያጠናነው እንገኛለን ያላችሁን መረጃ ላኩልን። በሚቀጥለው የአየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ይህን ያህል ጊዜ የፈጀበትን ምክንያት በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን።

 ይህን ሁሉ የምናደርገው ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ማስጠቀንቂያ ለመስጠት፣ ለማንቃት፣ ለማስተማር፣ ሐገሪቱን ከሚመጣባት ቁጣ ለማስጠንቀቅ ሲሆን በጠቅላላው በምድሪቱ ንስሐና ለውጥ በአደባባይ እንዲታወጅ፣ በጾምና በጸሎት በጌታ ፊት ወድቀን ማረን እንድንለውና በይቅርታው እንዲያድሰን ነው ከዚህም ጋር ራሳችችንን እና ቤተ ሰባችንን ከወንበዴዎች እንድጠብቅ ነው።

ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ!ድልና ነጻነት ለኢትዮጵያ ይሁን አሜን!  

    አባ ሰላማ

14 comments:

 1. እኔ እኮ ግርም ይለኛል። ምኑ ትሉኝ ይሆናል ፡ እንደው ሁል ጊዜ ግርም ይለኛል። እንደው ምንድነው እሱ እያላችሁ
  ነው አይደል\ የቤተክርስቲያናችንን ነገር ሳስበው ነዋ። እንደው ምን ተፈጥሮ ነው እንደዚህ የሚያባላን\ ይኼ ሁሉ
  -------------- ሽኩቻ፣ ይኼ ሁሉ ሽብር፣ ይኼ ሁሉ ጥላቻ፣ ይኼ ሁሉ ግርግር፣ ይኼ ሁሉ አድማ፣ ይኼ ሁሉ ንዴት፣
  ይኼ ሁሉ ጦርነት፣ እረ ስንቱ፤ እንደው ዝም ብላችሁ ብታስተውሉት እኮ እዚህ ሁሉ የሚያደርስ ከባድ ነገር እኮ
  የለም። እንደው ብቻ ፈርዶብን የትንቢት መፈፀሚያ ሊያደርገን የተመረጥን ህዝቦች ሆነን ይሆን\ ያውም ለአንድ
  ቤተክርስቲያን የምንሠራ፣ በአንድ አምላክ የምናምን፣ አንዲት ሐይማኖት ያለን፣፣ ባንዲት ጥምቀት የምናምን፣
  አንድ እርስት የምንወርስ፤ ሆነን ሳለን እንዲህ ዝብርቅርቃችን የወጣ ለምን ይሆን እያልኩ ዘወትር አስባለሁ።

  በመጨረሻም አንድ ነገር በኃሳቤ መጣ። አገራችን እኔ ነፍስ ካወቅሁበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ
  1982 ድረስ ኢትዮጵያ ነበርኩ፣ በቤተክርስቲያንም የነቃ ተሳትፎ ነበረኝ። በተለይም በደርግ ጊዜ ወጣቱ
  የነበረውን የማርክስና የሌኒን ፍልስፍና መከተል አለበት ተብሎ ጫና ሲደረግብን የነበረው ትዝ አለኝ። ነገር ግን
  ያን ጊዜ እንኩአን የቤተክስቲያን አባቶች ሊጣሉ ቀርቶ በአመለካከት እንኩአን የምንለያይ ወጣቶች አንድም ቀን
  በሐይማኖትም ሆነ በምንም ነገር ተጣልተን አናውቅም። ያውም የሐይማኖት ነፃነት እንዳሁኑ ባለነበረበት ሰዓት።
  ከ16 ዓመት ወዲህ ግን ቀስ በቀስ ሰይጣን በጥቅምና በፖለቲካ የተያያዘ ማህበር በቤተክርስቲያኑ ውስጥ አቁዋቁሞ
  ከሥር ጀምሮ ቅንቅን መልቀቅ ጀመረ። ያም ቅንቅን የሰዎችን አይምሮ እየበላና አየተባዛ ክርስቲያኑን መከፋፈል
  ጀመረ፤ ከዚያም ውስጥ ውስጡን ሳይታወቅ ካንሰር እንደሚሰራጨው ሁሉ አባቶችን ከአባቶች፣ ወንድሞችን ከወድሞች፣
  ሰንበት ት\ቤቶችን ከሰንበት ት\ቤት፣ ካንሰሩ መብላት ጀመረ። ሰይጣንም የሥራውን ውጤት እያየ ሲመጣ ሞቅ
  እያለውና እየታበየ መጣ። ሁሉንም አነካካና ሥልጣን ሁሉ ከእግዚአብሔር መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰይጣን
  አቡነ ጳውሎስን በማህበሩ ላይ አድሮ ጠዋት ማታ ይፈታተናቸው ገባ ፣ እግዚአብሔር ደግሞ አዋቂ ነውና ከፅናትም
  ፅናት ከብርታትም ብርታት እየሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከፍ ከፍ እያሉ መጡ፣ በእርግጥም የማንክደው ነገር
  ቢኖር አቡነ ጳውሎስ በጣም የተማሩ ሊቅ ናቸው። ነገር ግን የኛ ህዝብ የኖረው ና የሚያውቀው ባካባቢው ያለችውን የተወሰነች ነገር እንጂ ሰፋ ያለ አመለካከት ያለነበረው መሆኑን እናውቃለን። በተለይም በቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ
  ሊቃውንት አንድም እንኩአ እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ የተማረ ሰው አልነበረም፤ ከአቡነ ቴዎፍሎስ በቀር።

  ያም ሆነ ይህ ከላይ ለጠየቅሁት ጥያቄና ለሚገርመኝ ነገር መልስ ያገኘሁ ስለሆነ በመንፈሳዊ ህይወቴ ፀንቼ እንድኖር
  እግዚአብሔር አስተምሮኛል። ማህበሩ ግን ያልሆነውን ሆነ፣ ያልተፈጠረውን ተፈጠረ፣ ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ
  እያደረገ፣ ነጠላ ለብሶ መንደር ለመንደር እየተሽሎከለከ አባቶችን ከአባቶች፣ ወጣቶቹን ከአባቶች፣ እያናኮረ እንዲሁ
  ወለም ዘለም እያለ እዚህ የደረሰው ማቅ ነው። በመጨረሻው ዘመን ፍቅር ትቀዘቅዛለች የተባለው ትንቢት በኛ ላይ
  እየተፈፀመ ነው። እባካችሁ ወገኖቼ አሁን ሰማንያ በመቶ ያህል ህዝብ በሽታውን አውቆታል ስለዚህ መድሐኒቱ ፍቅር
  ነውና በፍቅር ሆነን ሁሉን እንችላለን። ደግሞም ክርስቲያን ዘረኛ አይደለም። ከርስቶስ እኮ የሞተው ለአለም ህዝብ
  ሁሉ ነው። አቡነ ጳውሎስን ለቀቅ፣ ፍቅርን ጠበቅ አድርጉ።

  እግዚአብሔር ፍቅር ነውና
  እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ብቻ እንድርግ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. CHIGRACHIN ENDE'EGZIABHER KAL YEMINORNA YEMIYASTEMIR SEW CHURCH WUST MEBARERACHEW NEW.

   Delete
 2. Dont wast your time we can understand from which side you are. who you are! By the name of christyanity ,or by the name orthodox of cherch why you wrigh. try make money not wast your time with out noting. you are not politician you are not religious. i am sorry to you this word but for you i want to use it .you ar ignorant you dont know love what means. try take a time for your self

  ReplyDelete
 3. ርብቃ ከጀርመን ምንድን ነው የምትቀባጥሪው ባንች አፍ ማን ይሙት እንኩአን ሊቃውንት፤ እንደኔ ያለው ምዕመን
  ይጠራል\ ማፈሪያ ነሽ አይን አውጣ ማቅ በሰይጣን መንፈሱ ያጠመቀሽ ወይም የማህበሩ ወሮ በሎች ግርፍ ነሽ።
  ከሁሉ የሚገርመው ደግሞ ፍርድ ስትሰጭ ካ-ካ-ካ-ካ-------------------
  ክርስቲያን ብትሆኝ ኖሮ ይደንቀኝ ነበር፤ ነገር ግን ለካ የዚያ የወንድሞች ከሳሽ ቅብ ነሽ።

  እግዚአብሔር ልቦናሽን ይመልስልሽ

  ReplyDelete
 4. manin new yemitasferarut?

  ReplyDelete
 5. bertu bertu bertu. enanten geta seleseten enamesegenewalen

  ReplyDelete
 6. Whether You post or not I do not care about it because the comment is for you not for readers only. so read it and understand that All the true believers of EOTC knows what to do and what not to do.
  You fulls! Why are you trying to cheat us again? What ever you try to do to day or tomorrow you must know that you are fighting with Our Lord Jesus Christ Who is the winner of very thing. Please don't say because you are not the believers of our faith and you sold your cultures and believes but you are from the loser side that is devil, your leader lucifer who lost every thing he has when our Lord Jesus Christ was on the cross. So please think repeatedly and return to the truth. We, the Ethiopian Orthodox Tewahido Believers choose dying than letting your objectives of taking our churches fulfill. Go to your hall and play with those devilish ceremonies of yours. Leave us alone!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. THEY FINISH BY WRITHING "ክብር ለኢየሱስ ክርስቶስ!ድልና ነጻነት ለኢትዮጵያ ይሁን አሜን!"BUR U SAY"you are fighting with Our Lord Jesus Christ "THIS SHOWS HOW MUCH U DONT UNDERSTAND WHAT U READ AND WHAT U WRITE.TRY TO HAVE POSITIVE MIND(BORN AGAIN CHRISTIAN BY CHRIST)

   Delete
 7. I really like all proposals from Abaselama. I think now you talking the truth and we all Christians has to stand for the truth. All the mess which we see in our church is not the result of yesterday's or last months or last years or last decades rather it is the cumulative effect of all wrong doing in the past may be centuries (two or three or more). From this point I only have a problem with Abaselama, that is why is that always ማህበረ ቅዱሳን???? This is not because I am a member of MK or what, I am just to be logical here. It is 20 years since MK's establishment and furthermore it is just one organization which does not have much power to do whatever he wants.

  Tell us the truth and post all the necessary documents about corruption, miss management in the church, ethnic based job appointment and all others. This time all Christians will be with you including me. There is millions of problem in Orthodox church, so write about that and propose solutions but be logical and with documents.

  Bertu Abaselama not for reformation of church doctrines but for reformation of the whole management.

  GOD bless Ethiopia,
  Yehuligizem anibabiyachihu.

  ReplyDelete
 8. Anonymous said...በመጨረሻም አንድ ነገር በኃሳቤ መጣ። አገራችን እኔ ነፍስ ካወቅሁበትጊዜጀምሮበኢትዮጵያአቆጣጠርእስከ1982ድረስኢትዮጵያነበርኩበቤተክርስቲያንም የነቃ ተሳትፎ ነበረኝ፣
  አቡነ ጳውሎስ በጣም የተማሩ ሊቅ ናቸውበቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉሊቃውንት አንድም እንኩአ እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ የተማረ ሰው አልነበረም፤ ከአቡነ ቴዎፍሎስ በቀር።

  Anonymous

  አሁን ግን የት ትሳተፋለህ? ይህ አባባልህ ብቻ መንፈሳዊ አለመሆንህን ይነግረናል

  በጣም የሚያሳዝንን አባባልህ ደግሞ
  አቡነ ጳውሎስ በጣም የተማሩ ሊቅ ናቸውበቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉሊቃውንት አንድም እንኩአ እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ የተማረ ሰው አልነበረም፤ ከአቡነ ቴዎፍሎስ በቀር።

  መንፈሳዊ እውቀት በመንፈሳዊነት መሆኑ ቀርቶ ድግሪ ወይም ማስትሬት/በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ያልተመረቀ/ በመያዝ የሚለካበት ዘመን ያደረሰንን ተመስገን ነው ወይስ ይቅር በለን ማለት ያለብን ::
  በማንበብ እና በመናገር ብቻ አለሙን የሚዳኝ ምሁር ብልጠትና ዲፕሎማሲ በትሩ፡፡ ትሁት መሳይ ዲፕሎማት ድንቄም ምሁር/

  ReplyDelete
 9. This is the message that I got from your article: That you would make the wrong doings of the "abunas" pulic if they don't support your ideas, and keep it secret if they do. Isn't this blackmailing? The same thing you accuse the "Mahbere Kidusan" group doing? I thought you were better than that. If you are really concerned about the church, you would take the right path and that is " tell it like it is" with no conditions attached. I know this may not be a popular move, but those who tell the truth would not be popular; may even be hated by some. This is the price you pay for keeping your integrity. Thank you.

  ReplyDelete
 10. ቤተ እስጢፋኖስ፣ቤተ ተ/ሃይማኖት፤ቤተ ኤወስጣቴዎስ፤ድሮ ነበሩ.ደግሞ በዘመናችን
  ልጆቻቸው እንዴት ተፈጠሩ?የሚከተሉትን በጽሙና ይመርምሩ ዳሩ ግን ከልብ አይማረሩ.
  ፩ኛ ደቂቀ እስጢፋኖስ፤
  ፪ኛ ደቂቀ ተ/ሃይማኖት፤
  ፫ኛ ደቂቀ ኤወስጣቴዎስ፤ እናም በርኸኞች፣ የመንግሥት ጥገኞችና መንደርተኞች ነበሩ
  ለሁሉም በዓይነ ልቡና ያተኩሩ.

  ReplyDelete
 11. ስሙን ላልገለፀ ጠያቂ መልስ፤ Nov.09/2011 4:18 am.
  አሁንስ የት ይሳተፋሉ ? በለው ለጠየቁት ሰው መልሱ ነቄ ብለናል ነው። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያለበት ሁሉ። ሌላው ደግሞ አባ ጳውሎስን በጣም የተማሩ ያልኩህ የዚህን አለም ትምህርት መሰለህ እንዴ? ድሮም እኮ እንደማታስተውሉ እንውቃለን። ግን ቅዱስነታቸው በቤተክርስቲያን የክርስትና ትምህርት ማለቴ ነው። ገባህ\ሽ?
  መማር እኮ በሁሉም መንገድ መልካም ነው። በጨለማ ውስጥ አያስኬድም። ለዚህ ነበር እኮ ጌታችን በምድር መጥቶ33 አመት ያስተማረን።
  ና ወደ ብርሃኑ ውጣ ሁሉም ይገለጥለሃል። Amen.

  ReplyDelete
 12. የዚህ ድረገጽ አዘጋጆች ወይንም አባ ሰላማዎች የምጠይቃችሁ ጥያቅ እናንተ ለዚህች ቤተክርስቲያን የምታበረክቱት ጥልን ነዉ ወይንስ ሰላምን ይመስለኛል ጥልን ነዉ ሳልጠራጠር የምነግራችሁ ነገር እናንተ ለዚህች ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ መስላችሁ በመታየት ነገር ግን የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች ናችሁ፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የሚሆነዉ እናንተዉ የፃፋችሁት ጽሁፎች ነዉ ህዝቡም ይረዳዋል እናንተ የምትናፍቁት ነገር እንደማይሆን ልታምኑ ይገባ ዛሬ እየሆነ ያለዉ አይነት ክስተት ቤተክርስቲያናችን በየዘመናቱ ያስተናገደችዉ ስለሆነ በዚህ ዘመን ያለን ሀጥአን ልንደነግጥና ልንፈራ እንችላለን ነገር ግን ሁሉን አዋቂ የሆነዉ መድሀኒአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ቤቱን ይጠብቃታል ይመስላችኋል ጌታ እዚህች ቤት የሌለ ይሄንን በዕምነታቸዉ (በጌታቸዉ) የሚጠራጠሩ ሰዎችም ይመስላቸዋል ነገር ግን ትዝ ይላችኋል በአሳ ማጥመጃ ጀልባዉ ላይ የነበረዉ ጌታ ታኝቶ ሳለ ደቀመዛሙርቱንና ጀልባዋን ማእዕበል ሲያናዉጠዉ…… ነገር ግን ሰይጣን ያኔ ይጠብቅ የነበረዉ ጀልባዋ ከጫነችዉ ጌታና ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደምትሰምጥ ነበር ነገር ግን የሞኝ ሀሳብ ሆኖ ብቻ ቀረ ጌታቸዉን የጠሩት ደቀመዛሙርቱ በኢየሱስ ክርስቶስ አንዲት ቃል ከዛ ሁሉ መከራና ፍርሀት ድነዋል ማዕበሉ ሲነሳ ጌታ በጀልባዋ ላይ እንደነበረ አስተዉሉ ሁሉም ነገር ጌታ ሲገስፀዉ እንደሚጠፋ ለምን አታስተዉሉም በዚህች ቤተክርስቲያን ክርስቶስ የለም ብላችሁ ሽብር የምታዉጁ በሙሉ የቻላችሁትን ያክል በጀት በዕርዳታም ሆነ በስርቆት ወይንም ገና እናገኛለን ብላችሁ ጉልበታችሁንና ገንዘባችሁን የምታባክኑ ባትለፉ ብዬ እመክራችኋለሁ ምክንያቱም ኪሳራ ነዉና ህዝቡንም አታወናብዱ አንዴ ቅዱሳን ተሳሳቱ አንዴ መላእክት እንዲህ ናቸዉ እያላችሁ የምትጽፉት እዉነት አልባ የሆነ ነገር አይታመንም እነማን ናችሁ የሚል ጥያቄ ያስጠይቃችኋልና እባካችሁ ከዚህች ንጽህትና ኑፋቄ ከሌለባት ቤተክርስቲያን ጋር በአንድነት ወደ ፈጠረን ይቅር ባይ ወደ ሆነዉ አምላክ እንለምን ይሰማናልና፡፡!

  ReplyDelete