Friday, November 11, 2011

የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› የአንኮበር ፖለቲካዊ ፍልስፍና (ክፍል አንድ) በአባ አበከረዙን - - - Read PDF

1996ቱዓ. የመጋቢትና ሚያዝያ ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ስለማኅበረ ቅዱሳን ጽንሰት፣ ውለደትና ስያሜ አስመልክቶ እንዲህ ብሎ ነበር፡-

‹‹ማኅበረ ቅዱሳን አሁን የሚጠራበትን የከርስትና ስም ወደ ዝዋይ ወርዶ ሳያገኝ ምን ዓይነት ስመ ተጸውኦ እንደነበረው አሁን ያሉት የማኅበሩ አባላት እንኳን ሊያውቁት አይችሉም ዜና ቤተከርስቲያን ጋዜጣ ግን የቀድሞ ስሙን ገና ከጅምሩ ያውቃል፤ በአንድ ወንዝ ላይ ተመስርቶ /ሠረዝ የራሴ/ የሁለተኛውን ፓትርያርክ አባትነት ላለመቀበል፣ ዓላማቸውን ለማደናቀፍና ለመኮነን አጠቃላይ ጉባኤ በሚል ስያሜ የተቋቋመ ማኅበር ነበር፡፡››

ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልሳን ነውና በነገሩ እውነተኛነት ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም፡፡ ዜና ቤተክርስቲያን በስም ባይጠቅሰውም እኔ ግን ወንዝ ‹‹አንኮበር›› መሆኑን በድፍረት እመሰክራለሁ፡፡ ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› በይፋ የተቋቋመው መንግሥቱ ኃይለማርያም ወያኔ ሰሜን ሸዋን ለመቆጣጠር በተቃረበበትና ወቅት ‹‹አንኮበርን›› ለማዳን ክተት ባወጀበት፣ ብላቴን ጦር ማሠልጣኛ ካምፕ ውስጥ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ይሁንና ወያኔን በጦር መመከት እንደማይችሉና እንዳልቻሉ ሲያውቁ በሂደት ‹‹ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የፖለቲካ ሥልጣን መያዝ ይቻላል›› የሚለውን የአባቶቻቸው ፖለቲካዊ ርእዮት /ፍልስፍና/ በምስጢር በመንደፍ አሁን ድረስ እየተጠሩበት ያለውን ማኅበር መሠረቱ፡፡ አነዚህ በቁጥር ጥቂት ነገር ግን ደግሞ የማኅበሩን አመራርና መዋቅር ከላይ እስከታች በስውር የስለላ መዋቅር ጭምር የሚቆጣጠሩት አካላት ፖለቲካዊ ዓላማቸውን በሃይማኖት ሽፋን ለማስፈጸም የተጠቀሙበት ስልት አጅግ የረቀቀና አስገራሚ ነው፡፡

ማኅበሩ እንደተመሠረተ እንደ ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተዳክሞ የነበረው የወንጌል ትምህረት ይበልጥ አጉልቶ በማስተማር፣ ምእመናንን ከዘመን አመጣሾቹ ወንጌላዊያን ለመከላከል የሚል ነበር፡፡ ከዚህ ዓላማ በመነሳትም ማኅበሩ እጅግ ውጤታማ የሆኑ ሥራዎችን አከናውኗል፡፡ አባላቱም በወቅቱ ያጋጥሙዋቸው የነበሩ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎችን በጽናት በመቋቋም ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የሚጠበቅ መሥዋዕት ሁሉ በመክፈል በርካታ በጐች በተኩላዎች ከመበላት አድነዋል፤ የቤተክርስቲያንዋ አጥር እንዳይጣስ የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡ ዛሬም ይህንን ዓላማ ይዘው በቅንነት መንፈስ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለመታደግ ደፋ ቀና የሚሉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ የማኅበሩ አባላት አሉ፡፡

በወቅቱ ማኅበሩ ለአባላቱ የሚሰጠው አንድ መመሪያ ነበር፣ ይኸውም የማኅበሩ አባት የማኅበሩን መንፈሳዊ ዓላማዎች ከመፈጸምና ከማስፈጸም ባለፈ በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ መሳተፍ እንደሌለባቸው የሚከለክል ነበር፡፡ ይሁን እነጂ አመራሩ የአባላቱ ቁጥር መበራከቱና ተቀባይነቱ እየሰፋ መምጣቱን ከገመገመ በኋላ በድብቅ ይዞት የቆየው ፖለቲካዊ ዓላማውን ሃይማኖታዊ ቀለም በመቀባት ይፋ ማድረግ ጀመረ፡፡ የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› አመራር ፖለቲካዊና ሃይማኖት እሳትና ጭድ ናቸው ብለው ባወሩበት አንደበታቸው ‹‹የማኅበሩ ዘለቄታዊ ህልውና ሊጠበቅ የሚችለው የማኅበሩ አባላት በተለያዩ የመነግሥት መዋቅሮች መሳተፍ ሲችሉና ቁልፍ ቦታዎችን ሲይዙ ብቻ ነው›› ማለት ጀመሩ፡፡

በመሆኑም በከተማም በገጠርም ለነበሩት አባሎቻቸው ‹‹መንግሥት በተለያዩ የሥልጣን  መዋቅሮች በሚያካሂዳቸው ምርጫዎች አባላቱ እርስ በእርሳችሁ  በመደራጀት ከመካከላችሁ ለቦታው የሚሆነውን እንድትመርጡና እንዳታስመርጡ›› የሚል መመሪያ አስተላለፈ፡፡ የሚገርመው በወቅቱ የተላለፈው መመሪያ በተቻለ መጠን በገበሬ ማኅበር ከአመራሩ እስከ ሚሊሽያ፣ በከተማ ከላይኛው መዋቅር እስከ ደነብ አስከባሪ ባሉት የኃላፊነት እርከኖች የማኅበሩ አባላት እንዲገቡ አስፈላጊውን ሁሉ እንዲደረግ የሚያሳስብ ነበር፡፡

ከዚህ ጐን ለጐን ‹‹የግቢ ጉባኤ›› በሚል ሽፋን በከፍተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማትና ኮሌጆችን ጨምሮ በሁሉም የመንግሥትና የግል ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች በርካታ ተማሪዎችን ማሰባሰብ ጀመረ፡፡ ማኅበሩ እንዲህ በማድረጉ በርካታ ወጣቶች በእምነታቸው ጸንተው እንዲቆዩ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉ የማይካድ ቢሆንም የማኅበሩ ስውር ዓላማ ግን ከዚህ ባሻገር ሌላ ተልእኮ  ነበረው፣ አለውም፡፡ ይህ ስውር  የማኅበሩ ዓላማ ተሳክቶ በትረ መንግሥት ከጨበጠ አገዛዙ አልጋ ባልጋ እንዲሆንለት በማለት ጭምር የሚያከናውነው ተግባር መሆኑን ነው ውስጥ አዋቂዎች የሚናገሩት፡፡

ማኅበሩ በቅርቡ በሀገሪቱ የተዘረጋውን ነፃ ገበያ በመጠቀም የተለያዩ ከፈተኛ ንግድ ተቋማት ማቋቋም መጀመሩና የገንዘብ አቅሙን ለዘለቄታው ለማጠናከር በአክስዮን ሽፋን የራሱን ባንክ እስከ ማቋቋም መድረሱ የማኅበሩ የሩቅ ጊዜ ዓላማ እስከምን ድረስ እንደሆነ ማሳያ ምልክት ነው፡፡ ሌላው አስገራሚ ነገር በቅርቡ ከነባር የማኅበሩ አባላት አንዱ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት እንደተናዘዘው ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› የራሱ አባላትና ሌሎችም እግር ተወርች እየተከታተለ ሪፖርት የሚያቀርብ የስለላ መዋቅር ማበጀቱ ነው፡፡

ሲጠቃለል የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› በሃየማኖት ስም የተሸፈነ ፖለቲካዊ ስትራቴጂ በሦስት ዋና ዋና ስልታዊ ግቦች ላይ የተዋቀረ ነው፡፡ የመጀመሪያው የሕዝቡን ስነ ልቦና መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመታደግ ማለትም ስብከተ ወንጌልና የአብነት /ቤቶችን ለማጠናከር፣ የተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ገዳማትን ለመርዳት ወዘተ በሚል በሀገርና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ በማሰባሰብ የማኅበሩን የገንዘብ አቅም አስትማማኝ ማድረግ፤ ሁለተኛው በትምህርት ተቋማትና በየሠፈሩ ከሚያከናውነው የአባላት ምልመላ ባሻገር በጥናትና በምስጢር የተመረጡ አንኮበራዊያን በተመረጡ ገዳማት በማመንኰስ ቀስ በቀስ ለጵጵስናና ለፕትርክና መዓርግ ማብቃት፣ እስከዛው በተጠባባቂነት በጵጵስና መዓርግ ካሉት አባቶች መካከል ዳጎስ ባለ ገጸ በረከትና ሽንገላ  በመያዝ በቅዱስ ሲኖዶ ዘንድ አስተማማኝ ከለላ እንዲሆኑት ማድርግ፣ /ማኅበሩ በዚህ በኩል የተሳካ ሥራ ሠርቷል ማለት ይቻላል/ ሲሆን ሦስተኛውና የመጨረሻው ማኅበሩ ያሉትን አባላት ቁጥር ለሚፈልገው ዓላማ በቂ ሆኖ ሲያገኘው በሰበብ አስባቡ ተገፋሁ፣ መሥራት አልቻልኩም ወዘተበማለት ራሱን ከሃይማኖት ድርጅት በማግለል በአዲስ መልክ ፖለቲካዊ ድርጀት አቋቁሞ መቅረብና በምርጫ በትረ መንግሥትን መጨበጥ ነው፡፡

ማኅበረ ‹‹ ቅዱሳን›› ራሱን ወደ ፖለቲካዊ ድርጅት ቢቀይርም ሃይማኖታዊ ተግባሩን ይተዋል ማለት ግን  አይደለም፡፡ ዓላማው የአንኮበርን ሥርወ መንግሥት ለመመለስ በመሆኑ የቤተክርስቲያንዋ የፕትርክና ሥልጣን በራሱ እጅ እስካላስገባ ድረስ አርፎ የሚተኛ አይደለም፡፡ የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ጠንሳሾች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ለሞት አሳልፈው በመስጠትና አቡነ መርቆሬዎስን በኢህአዴግ ሽፋን ከመንበራቸው እንዳወረዱዋቸው ሁሉ ዛሬም አቡነ ጳውሎስን በማስወገድ የራሳቸው ፓትርያርክ ለመሾም ሌት ተቀን በመጣር ላይ ያሉት ይህን አንኮበራዊ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ነው፡፡ /በዚህ ዙሪያ በቀጣይ ሰፊ ትንታኔ ይቀርባል/፡፡

ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ምንጊዜም ሕዝቡን በሃይማኖት ሽፋን ከሰበሰበ በኋላ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የራሱን ፖለቲካዊ አቅጣጫ እንደይዙ መጣር ብቻ ሳይሆን ማኅበሩ የማይደግፈው የፖለቲካ ድርጅት ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ የቤተክርስቲያንዋ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ እንደማይቀር አበክሮ ነው የሚያሳስበው፡፡ 1997 . ምርጫ ለዚህ ዓይነተኛ ማሳያ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ማኅበሩ በዚህ ግዜ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ነበር በፖለቲካ እጁን ያስገባው፡፡

የማኅበሩ አመራር አባላት በቀጥታ በፖለቲካ ሥራ ትሳተፋላችሁ የሚለውን የመንግሥት ውንጀላ ለመከላለከል /ለመሸወድ/ በቅድሚያ የተወሰኑ አባሎቻቸውን በሥራ ድክመት፣ በአመለካከት ልዩነት፣ ወዘተ በሚል ከማኅበሩ አመራር እንዲወጡ ማድረጋቸውን አሳወቁ፡፡ ልብ በሉ እነዚህ የማኅበሩ ‹‹ዓይናማ ሰዎች›› ለይስሙላ ከአመራር ተነስተዋል ቢባሉም /ከማኅበሩ አባልነት ግን አልተነሱም/ የማኅበሩ አመራር አባላት ሌሊት ሌሊት ያካሂዱዋቸው በነበሩ ወሳኝ ስብሰባዎች እየተገኙ ድርሻቸውን ከማበርከታቸውም በላይ አንዳንዶች ማኅበሩን በመወከል በአውሮፓና በአሜሪካ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ተልእኮአቸውን በይፋ ያከናውኑ ነበር፡፡

ከሁሉ በላይ እነዚህ ከማኅበሩ አመራርነት ተነሱ የተባሉ ግለሰቦች ‹‹አዲስ ነገር›› የተባለ የማኅበሩ የፖለቲካ ልሳንን ጨምሮ /ዛሬ ዕንቊ መጽሔት አዲስ ነገርን ተክቶ በመሥራት ላይ ይገኛል/ የተለያዩ ድረ ገፆችን በመክፈት የማኅበሩ ፖለቲካዊ አመለካከት በሰፊው ማሰራጨት ተያያዙት፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ ከማኅበሩ አመራርነት ተባረሩ የተባሉት ግለሰቦች በሙሉ የሚዲያ ባለሞያዎች ነበሩ፡፡ ይህም ሂደቱ ምን ያህል በተጠና ሁኔታ እንደተከናወነ ያሳያል፡፡ አሁን ድረስ ማኅበሩ በራሱ ካደራጃቸው የሚዲያ አውታሮችና አባላት ሌላ አባላቱን በተለያዩ የግልና የመንግሥት መገናኛ ብዙኋን መዋቅር በመሰግሰግ ዓላማውን ያለከልካይ ሲያራምድ ቆይቷል፣ አሁንም ቀጥሎበታል፡፡ ማኅበሩን የሚነቅፉ ጽሑፎች ጭራሽ የማያስተናግዱ የግል ጋዜተኞችና መጽሔተኞች በርካታ መሆናቸው ይህንኑ ነው የሚያሳየው፡፡

በአንፃሩ የመንግሥት የመገናኛ አውታሮችን ጨምሮ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችና የግል የኅትመት ሚዲያዎች የማኅበሩ ተለዋጭ ልሳናት በመሆን ሲያገለግሉ ይታያሉ፡፡ የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› የሚዲያ ወረራ በዚህ በአገር ውስጥ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ በአሜሪካ ካቋቋሟቸው የራሳቸው ኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያዎችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በተጨማሪ በአሜሪካና በጀርመን ጽምፅ የአማርኛ ፕሮግራሞች ባሉት አባላቱ አማካይነት ማኅበሩ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አቋሙን  በይፋ ማራመድ ከጀመረ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በተለይ 1997 . ምርጫ ወቅትና ምርጫውን ተከትሎ በተነሱ ረብሻዎች ዙሪያ ለዚህ ሥራ በድብቅ የተመለመሉ የማኅበሩ አባላት ከነ አዲሱና አሉላ ጋር በመገናኘት፣ ለቃለ መጠይቅ የሚሆኑ ሰዎችን በመመልመል ወዘተ ሰፊ ሚና ተጫውተዋል፡፡ አንዳንዶቹም ሒዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ወዘተ ለመሳሰሉ የባሕር ማዶ ‹‹ሰብዓዊ መበት አስጠባቂዎች›› እንደ መረጃ ምንጭ በመሆን እየሠሩ እንደሚገኙ በሰፊው ይታማል፡፡

ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› በዚህ የምርጫ ማግስት ጎጠኝነቱንና ዘረኛነቱን አጉልቶ የሚያሳይ ሌላ አስነዋሪ ተግባርም ፈጽሞ ነበር፡፡ ይኸውም በወቅቱ ከአዲስ አበባ አድባራት ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ለመሳለም ተመዝግበው የነበሩ ምእመናንን በወኪሎቻቸው አማካይነት ‹‹በአሁኑ ወቅት ወደ አክሱም መሄድ የኢህአዴግን መንግሥት ሕጋዊነት ማረጋገጥ ማለት ነው፣ ስለሆነም ወደትግራይ እንዳትሄዱ በአክሱም ምትክ አዲስዓለም ማርያም አለችላችሁ›› እያሉ በግላጭ ይሰብኩና አንዳንዴም በማስፈራራት ጭምር ይናገሩ እንደነበር በወቅቱ ወደአክሱም ለመሄድ ተመዝግበው የነበሩና እንዲቀሩ የተገደዱ ምእመናን ምስክሮች ናቸው፡፡

ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› የአንኮበር ፖለቲካዊ ፍልስፍና አራማጅ ለመሆኑ ወደ ሌላ ሳንሄድ መጽሔቶቻቸውንና ጋዜጦቻቸውን በመከታተል ብቻ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይ በቅርቡ ከመንግሥት ‹‹ማስጠንቀቂያ››  እስክተሰጣቸው ድረስ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣና ሐመር መጽሔት ራሳቸውን የቻሉ በፖለቲካ የታሹ ሃይማኖታዊ አምዶች እንደነበሩዋቸው እናስታውሳለን፡፡ በዚህና በሌሎች ዙሪያ ማስረጃ እየጠቀሱ ብዙ ማለት ቢቻልም እንዲህ ማድረጉ መልሶ የማኅበሩ ጎጠኛ አመለካከትና ዘረኝነት ማራመድ ስነለሆነ በዚሁ አልፈዋለሁ፡፡ በቀጣይ የማኅበሩ አባለት በነገረ መለኮት ዙሪያ ያላቸው ዕውቅት ከተርብ እንጀራና የውሻ በለስነት ያልዘለለ አርሶ ፈረስ መሆኑን የሚያሳይና ደቂቀ አስጢፋኖስን የሚቃወሙበት ምስጢር እነሱ እንደሚሉት ሃይማኖት ሳይሆን የአንኮበር ፖለቲካ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ይዘን እንቀርባለን፡፡ ይህ ጽሑፍ በበርካታ ምዕራፎች ተከፋፍሎ በተከታታይ የሚቀርብ መሆኑንም ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

‹‹ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ጸጋ ከሌላው ዘንድ ሲያይ የሚቀና ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡

አባ አበከረዙን

ወለደአበከረዙን ነኝ

ይቀጥላል!

21 comments:

 1. Aba Kerezun!!! You nailed it. This is what the Ethiopian people need to know: knwoing the truth, and the truth will set everyone free. Knowingly or unknowingly, I must confess that I have been a sympathizer of MK. But now I confess I am no longer with them in any way. Enough is enough. I consider a waste of time and shame to have been a member of MK for a long time now. Now I lend my advice to fellow brothers and sisters to look into the truth and follow suite. Why should any one be tempted to subscribe to their evil aspirations at a time when truth is revealing itself as bright as the morning sun??????? Adios Mhabre Kidusan or Mahbre Seytan!!!

  ReplyDelete
 2. አባ አበከረዙን this is not true. Please grow to be a man.Don't be a lier like politicians.Whom are you trying to full? By the way if you fear God you would obey His commands-not to be a lier.

  ReplyDelete
 3. ማጣበቂያው ካልያዘ ልጥፉ ይወድቃል። ልጥፉ በበዛ ቁጥር ውድቀቱን ያፋጥነዋል። ከመለጠፍ የራስን ባጅ ባንገት ማንጠልጠል ጥሩ ማመላከቻ ነው።

  ReplyDelete
 4. Your hatered for Shoa will take you no where... Who installed Abune Tewoflos? It was the so-called Emperor HaileSelassie of Shoan descent.

  If you want critcize MK, do so. If you want to attack the accomplices for the killing of Abune Tewoflos, do so. However, you better refrain from attacking the innocent mass by just association. Weyane has been killing and attacking certain tribes because of its hate and guilty verdict by association. You are doing the same thing and seem to be a dangerous animal.

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ሃይላቸውን ያድሳሉ እንጂ አይፈሩም እንኳን አይደለም የአንኮበር ቀርቶ የሌላ አለም ሃይላትን ቢያሰባስብ የትም አይደርስም እንደ ዝግባ እየረዘመ ከሄድ መልካም ነው መጥፊያው ቀርቧልና ነው::ደግሞ ይህች ሴራ ለኢሃዴግ ምኑም አይደለችም እንኳን ይህችንማህበሩ ሞኝ ሆነ ይህንን እድል ተጠቅሞ ከቻለእውነት ስላልሆነ ማስፋፋት የሚፈልገው በጦርነት በረብሻ ነው::እውነት ግን ቢሆን ልክ እንደመድሃኒታችን ነበር::እኔኮ የሚገርመኝ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የተጻፈ የትኛው ወንጌል ነው እኛ ያለነበብነው ሰዎችን በመግደልና በማሰቃየት ሃይማኖታችሁን አስፋፉ የሚለው እነዚህ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱሱን እንደክርስትና ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ግራ ነው እንዴ የሚያነቡት??ሰማ አባ አበከረዙን ወየውላቸው የእግዚአብሔርን በትር አለማወቃቸው??እግዚአብሔር እኮ ከፈለገ በረዶ አውርዶም ጠላቶቹን መበቀል ይችላልና ለማንኛውም ጉደኛ ታሪካቸውን አስነብቡን እናንተ ደግሞ ልባችንን እያንጠለጠላችሁ ነገ ከነገወዲያ አትበሉ በርቱ!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 6. ለደጀ ሰላም ብሎግና ለ- ሃቢብ ለኢትዮጵያ፤ ኖቨምበር 11- 10 38 አስተያየት ሰጭ

  ፓትሪያሊኩን አቡነ ጳውሎስንና ሌሎች ጳጳሳትን እንዲሁም በቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚገኙትን ሁሉ
  እናንተ የሾማችሁአቸው መሰላችሁ እንዴ\ ምንም ቢሆን አባቶቻችን ማክበር ይገባን ነበር፤ ይህ ባይሆን ደግሞ
  አቡነ ጳውሎስ እኮ ከምንኩስና ጊዜያቸው እስከ ፕትርክና ብሎም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዘዳንት ድረስ
  ለመሆን የበቁት እኮ፡ 1ኛ\ በሥላሴ ፈቃድ፣ 2ለተኛ\ ባላቸው ሐይማኖታዊ ብሩህ አይምሮ፣ እውቀትና ትምህርት
  ነው፡ ይደልዎ።ይደልዎ፣ ተብለው የተሾሙት። ሰለዚህ እናንተ ማናችሁና ነው መፈንቅለ ፓትሪያሊክ ለማድረግ
  የምታስቡና ሌላውም በዚህ እኩይ ሃሳባችሁ እንዲተባበር ጥሪ የምታቀነባበሩት\ አድማ የምታደርጉት\

  ከላይ ቀደም ብየ እንደጠቀስሁት የተሾሙት በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ፡ በከንቱ ትደክማላችሁ እንጅ እግዚአብሔር በራሱ ሰዓት ከዚህ አለም በሚለያቸው ጊዜም ቢሆን የእግዚአብሔር ፈቃድነው የሚሆነው። ይህንን የማታምኑ
  ከሆነ፡ እንግዲያው እናንተ ከክርስቲያን ወገን አይደላችሁም።

  እንደው ለነገሩ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡ በብሎጋችሁ የምትፅፉትንም ሆነ የአስተያየቶችን መልዕክት እከታተላለሁ።
  ነገር ግን ሁልጊዜ ስመለከት በጣም የታዘብኩት 1ኛ\ የእናንተን የተደበቀ እኩይ አላማ የሚቃወማችሁን ያለ ምንም
  ማስረጃ ተሃድሶ መናፍቅ እያላችሁ በሌላችሁ እውቀትና ስልጣን አባቶችን ስታጥላሉ ፤ የእናንተን ስውር ደባ
  አስፈፃሚዎቻችሁን ደግሞ፡ስታመሰግኑና፡ ስታመልኩ ትታያላችሁ ፤ በውኑ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ\
  እንጃ\ አሁን አሁንማ እግዚአብሔር ነን ሳትሉ አትቀሩም። እያንዳንዱ እንደሥራው የሚፈርድ እግዚአብሔር እንጅ
  ሰው አይደለም። ይህንንም ከቅዱስ ቃሉ ተምረናል። ግን አሁን እንደማየው እንደ ሳጥኤል የእግዚአብሔርን ሥራ
  ለመቀማት የምትሩሩጡ ይመስላል። አይመስልም\ እስቲ ራሳችሁን በፅሞና ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ምን እየሠራን ነው
  ብላችሁ ጠይቁ\ በእርግጥ አሁን ለእናንተ የሚመስላችሁ ለቤተክርስቲያንና ለሐይማኖት እያሰባችሁ ሊሆን ይችላል።
  ክክክክ---- ትዝ ይላችሁአል ማርያም ነኝ ብላ የመጣች አንድ እናት\ አወ ምንአልባት እኮ ያ ጠላታችን ዲያቢሎስ
  ማርያም ነሽ ብሎ እየደጋገመ ስለነገራት በነገሩ አምናበት ሌሎችም እንዲያምኑ አድርጋ እንደዚያ ድርቅ ብላ
  ስትከራከር የነበረችው በኃላ ሐሰተኛ መሆንዋ የታወቀው፤

  ከዚህ በፊት ከእናንተ ጋር ያልተስማማውንና እግዚአብሔር በሰጠው ፀጋ የምትቀኑበትን ተሐድሶ መናፍቅ ነው\ናት
  እያላችሁ ከምዕመኑ ጋር ስታጋጩና ሥታስጠሉት ነበር፤ ምዕመኑም ከራሴ ጀምሮ በሐይማኖቱ የሚመጣበትን ሰው
  አይፈልግምና አምኑአችሁ ገለል ሲያደርጉት ይታይ ነበር። ነገር ግን ያ ህዝብ ወደ ተዋህዶ እምነት የመጣው እናንተ
  ተሐድሶ መናፍቅ በምትሉአቸው ወንድሞች ትምህርትና ስብከት ነው። ለመድሐኒያለም ክብር ምስጋና ይግባውና በፊት የተጠቀማችሁበትን የሥም ማጥፋት ሥራ፡ህዝቡ ሐሰት መሆኑን እያወቀና እየበላው ስለመጣ፡ \አንተ ርኩስ ሰይጣን ዘወር በል ከፊቴ ማለት ጀምሮአል፡ ማለትም የድሮው ዘፈናችሁ ስለተበላ ፡ አሁን ደግሞ አዲስ ዘፈን ጀመራችሁ።
  ይኸውም መፈንቅለ ፓትሪያሊክ\ በምን በምን\ በሐይማኖት\ እንዴት\ እንዴት\ ማነው መርማሪው\ እናንተ\ እንዴት ሆኖ\ -ምጥ ለእናታ አስተማረች- ነው የተባለው\ -ወይ ዘንድሮ ልጄ ሆነ ዝንጆሮ- አሉ። -ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ- ሆነ እኮ። ወገኖቼ ለማንኛውም - ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው- እላለሁ።

  በተረፈ እባካችሁ በአባቶች መሐል ጣልቃ አትግቡ። ድሮ እኮ አባቶች ተመካክረው ፣ተነጋግረው፣ ተግባብተው፣
  ተፈቃቅረው ነበር የሚኖሩት። አሁንማ ከመንገድ የመጣ ሁሉ ጣልቃ እየገባ በመከፋፈል፤ እንዳይግባቡና፡እንዳይከባበሩ \እንዳይዋደዱ\ እያደረጉ ነው። እባካችሁ እባካችሁ አባቶችን ለአባቶች ተው።

  ይህንን ፅሁፍ የምታወጡት አይመስለኝም። እንደተለመደው። ነገር ግን ካነበባችሁትም ይበቃል። እንደ እርሱ ፈቃድ
  ይሁን። አሜን።

  የድንግል ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ልቦናችን ይመልሰን
  የድንግል ማርያም ምልጃና በረከት አይለየን።

  ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 7. ere sel kerestyan amelake belacheu yesewe sega atebocheku,egezere yeferedal alubaletega yebuna werehene atelkeke agassese

  ReplyDelete
 8. LeSelam
  are you serious?
  man this site insult Maraim abune teklehaymanot zera yaqobe and so on and you are asking why aba paulos insulted???
  wow you are sleeping man! wake up. you are in tehadeso pente site.

  ReplyDelete
 9. mahbere qidusan seytannnnnnnnnnnnn

  ReplyDelete
 10. አባ ገ/መድህን በወቅቱ በነበሩት ፓትሪያሪክ አቡነ ቴውፍሎስ ተጠቁመው ለጵጵስና የታጩ ቢሆንም በሶስት ምክንያቶች የወቅቱ ሲኖድስ ሳይመርጡ ቀርተዋል ፡፡


  1ኛ.አባ ገ/መድህን ቆባቸውን ጥለው በምትኩ የህንዶችን ኩፍታ ያደርጉ ስለነበር (ይህ ስራቸው ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው)

  2ኛ.ቀሚሳቸውን ጥለው በምትኩ መኳንት ለመምሰል የመኳንቱን ዓይነት ካፖርት ይለብሱ ስለነበር

  3ኛ.ገዳማዊያን አባቶች ከሚኖሩበት ክልል ወጥተው በቡና ቤት ይኖሩ ስለነበር በወቅቱ በነበረው ሲኖድስ ሳይመርጡ ቀርተዋል ፡፡ይህ የሆነው በ1968 ዓ.ም ነው።


  ታዳያ በምን ተዓምር ጳጳስ ሁነው ተገኙ? የሚል ጥያቄ ሲመጣ ሁለት መላ ምቶችን በጊዜው የነበሩ ሰዎች ያስቀምጠሉ።

  ReplyDelete
 11. ሰላም ለዚህ ቤት!

  ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሁ በሰው ፈቃድና በተጥባበ ነገር የተጀመረ ከሆነ ማህበሩም ይፈርሳል፡፡ አባላቱም ይበተናሉ፡፡ ምን አስጨነቀን፡፡ ተራውንና ፍርዱን ለባለቤቱ ብንተውለት አይሻልም? አንድ የማይካድ ጉዳይ ግን ማ/ቅ በአገልግሎቱ እንደቀጠለ ብዙ ሺ አባላትና ደጋፊዎችን ይዞ ዘንድሮ ፳ኛ ዓመቱን የፊታችን ግንቦት ፩ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም የሚያከብር መሆኑ ነው ፡፡ ነገር ግን ባፍ በመጣፍ ብላችሁ ቢያቅታችሁ፣ አንዴ የመንግስት ደጋፊ በመምሰል ሌላ ጊዜ ደግሞ ለመቃወም እየሞከራችሁ እዚህና እዚያ ስትረግጡ ይታየኛል፡፡ ባልበላውም ጭሬ... እንዳለችሁ ዶሮ ማህበሩ በአገልግሎቱ ምክንያት በአማንያን ልብ ውስጥ ሥፍራ ስላገኘ ያበሳጫችኋል፡፡ ለምን? ስለዚህ እናንተ ልታፈርሱ አስባችሁና ሞክራችሁ ሳይሳካላችሁ ሲቀር መንግስት እናንተን ተክቶ ማ/ቅን በአክራሪ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅትነት ፈርጆ እንዲያጠፋላችሁ ትመኛላችሁ፡፡ ትልቅ ድፍረት ነው፡፡ ባታውቁት ነው እንጂ አገራቸውንና ቤተክርስቲያንን እንደናንተ ከመሰሉ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱና በጭፍን ጥላቻ የታወሩትን ተግቶ ለመጠበቅ ብሎም በተቀነባበረ ሴራ አገራችን ከድህነት እንዳትላቀቅ ከሚፈልጉና ከሚጥሩ ወገኖች እና የእነርሱን እርዳታ ብቻ እየጠበቀች እንድትቀጥል የሚሹ ጌቶቻችሁን በሁሉም የአገሪቱ ተቋማት ውስጥ ዓይንና ጆሮ ሆነው በሚያገለግሉና በርካታ ተጨባጭ ለውጥ ባስመዘገቡ አባላቱ አማካኝነት ሴራችሁ እየከሸፈ መሆኑን ማን በነገራችሁ!

  ይቆየን

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማ ብሎግ ሚዛናዊ ነው። የሚሰድቡትንና የሚተቹትን ሁሉ ፖስት ያደርጋል። ደጀሰላም እንኳን የሚሰድቡትንና የሚተቹትን በፍጹም አያወጣም። ደጀሰላም ለቤተክርስቲያን የአዞ እንባ የሚያነቡ፤ ውሸታሞችና ምንም የማያውቁ ጎጋዎች የሚያለቃቅሱትን ብቻ እየለቀመ ያወጣል። ድሮስ ደጀሰላም ግብረ በላ ደብተራዎችና ቢምር ይማራት፤ ባይምር እንጦሮጦስ ይጨምራት፤ እኛ ማራት፤ ማራት ብለን ተዝካራችንን እንብላ እንዳሉት አለቃ የሚሰበሰቡበት አዳራሽ ምሳሌ ሆኖ ዛሬም የኢንተርኔቱ ደጀሰላምም እንደዚያው ሆኖ ከደጀሰላም ደጃፍ አንዳች ፍርፋሪ ቢወድቅልን ብለው የረሃብ ዓይናቸውን እንደሚያቁለጨልጩና ባለረጅም ጠምጣሚዎች እየጠቀጠቁ እንደሚያልፉት ሁሉ ይህ የድረገጹ ደጀሰላምም የግብር አባቶቹን ተልዕኮ በመፈጸም የኛን የጽሑፍ ድምጽ መስማት ስለማይፈልግ እየጠቀጠን ይተወናል። ቁጭቱ ቢበዛብን ሳንወድ የራሳችንን ብሎግ ለመክፈት ተገደድን። እንደእኔው ቁጭት የነበራችሁ በነጻ እንድታወጉበት እጋብዛችኋለሁ። ከአባ ሰላማ ብሎግ ጋር የሃሳብ አንድነት ስላለን ተጠቀሙ!http://yeshuwa.blogspot.com

  ReplyDelete
 13. ፈሪ ቦቅቧቃ፣ እውነት ከያዛችሁ ወደ መድረክ አትወጡም፡፡ የማይጥማችሁን አስተያየት ሌሎች እንዳይመለከቱት የምትጋርዱ፣ ሲያደርጉ አይታችሁ ብልግ ከፍታችሁ፣ ሐተታ ሐትታችሁ አስተያየት እንዲሰጥ ስትጠብቁ አታፍሩም፣ አትፈሩም፣ ደግሞ " ከእያንዳንዱ ጽሑፍ ስር COMMENTS የሚለውን በመጫን ስላነበቡት ነገር የተሰማዎትን እንዲገልጹ እንጋብዛለን፡፡ " ይባልልኛል፡፡ ድንቄም!የሌባ ዓይነ ደረቅ!!! ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 14. Aba Abekerezun I greatly appreciate your writing it is academic writing I am eager to read the series of your writing God bless You!

  ReplyDelete
 15. አባ ሰላማ የትልቁ አባት ስም ሲሆን በእርሱ ስም በሬ ወለደ መናገር አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን ኅጢአት መሆኑን ስነግራችሁ በፍጹም እህትነቲ ነው:: ለመሆኑ የወደዳችሁትን እንዳታመልኩ እንዳትሰብኩ ማን ከልክሏችሁ ነው? ጥያቄው በተዋህዶ ቤት ሁናችሁ የፕሮቴስታንቱን አታስተምሩ ነው:: ማኅበረ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመስርቶ ያለ መሆኑ ምስክር አያሻውም የአገልግሎት ውጤቱ ምስክር ነው::ማኅበሩን ለቀቅ አድርጉት ካለዚያ ከእግዚአብሔር ጋር እየተጋጫችሁ ነው :: 2ኛ ሳሙ 2፥10

  ReplyDelete
 16. በዚህ አይነት ሁኔታ አጺ ቴድሮስን ለማስገደል መንገድ እየመሩ የመጡት፣ በውጫሌው ውል ላይ ሙስናን የፈጸሙት፣ ሙሶሎኒን በመደገፍ የመርዝጭስ የሚረጩ ጥያራዎችን፣ የ1953 ቱን መፈንቅለ መንግሥት አቀነባብረው ያንሁሉ መኳንንት ያስፈጁት፣ በ66 አብዮት ላይ ግንባር ቀደም ሁነው ንጉሡን ያስገደሉና ከዛም ያንሁሉ ወጣት ያስፈጁ፣ ከዛም በ83 ለውጥ ደርግን ከድተው ወያኔን ያስገቡና የጎሳ ክፍፍሉን ያከናወኑ እና ሌላም ሌላም እያላችሁ ጻፉባቸው:: ምንያህል አንባቢዎቻችሁን ብትንቁ እና ብትዘባበቱባቸው ነው እንድህ ያለ የዘቀጠ ሥራ የምትሰሩት:: ለነገሩ በጥላቻ እና በባንዳነት የተሰለፋችሁ ስለሆነ ከዚህ የከፋም ብትጽፉ አይደንቀንም:: በየአንዳንዷ ጽሁፋችሁ እውነተኛ የምትመስሏቸው የዋሃን ሳይቀሩ በቅዱሱ ስም የተሸፈናችሁ ባንዳዎች መሆናችሁን እንድረዱ እየረዳችኋቸው ነው:: አድናቂዎቻችሁ እነ ፓስተር እከሌ እና እነ መሰሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ጉዶች ናችሁ እዚህ አሜሪካ እኮ የአለቆቻችሁ አዳራሾች እኮ የሌሊት መጨፈሪያ ሁነዋል:: ለምን የስምሪት አለቆቻችሁን አትታደጓቸውም:: ብትችሉስ ውለታቸውን አሁኑኑ ብትከፍሉ በበጃችሁ ነበር:: ተዋኅዶን እና ልጆቿን ማ/ቅዱሶችን ለቀቅ አድርጓቸው:: እነሱ እያበቡ እናንተ እውነት ሳይሆን ውሸቱም ያልቅባችሁእና ገና ታብዳላችሁ::
  ተጠምቀ መድኅን

  ReplyDelete
 17. selam aba selama be ewenet betam des yemil neger new mahebre kidusan endhi ayenet tegbar eyefetseme neber wengel ensebekalen yemilew?? egziooo lengeru ayedenkim be Geremnem betam tenkesakesew neber Egziabher hayal new be abatochachen tselot keshfoal aba kerzun yetsafut neger weshet ayedelem betam yemitamen neger new beayenachen eyayen new be Germen frankfurt mareyam betekereseteyan Asetedadariwen menkuse be wengel sim wengel kelekelu eyalu yewahe kereseteyanochen eyasademu yemibetebetu poletikegna mahebere kedusanoch neberu gin aletesakalachewem eske polic mekeses dersew neber weladite amelak emebtachen awaredechachew gena yiwaredalu yebtekereseteyan lijoch gin mebanen alebin menfesen hulu mermeru yetebalewen mastewal alebinn bertu abaselam ke gonachu nen Egziabeher yiredann amen

  ReplyDelete
 18. If you post it post it, if not there are lots of blogs where I could post. I am happy that at least you would read it.
  Here is the truth. With what ever false acquisitions you write, at least MK is working day and night for the betterment of the church with the motto of TEWAHIDO.
  And you, working day and night to dismantle our church with the motto of TEHADISO (to bring protestantism to our beloved church).

  Wondimoche ehitoche bezih beyanis ensamam: mahebere kidusan betechalew hulu lebetekirstian eminet metebek yiseral:: yezih blog balebetoch gin pentewoch (tehadisowoch) mehonachewin kemiyawetut tsuhuf teredu:: Beteleyaya mikiniyat MK betiweksu enqua yenezih meseri blog tsehafiwoch seleba atihunu::

  ReplyDelete
 19. እውነት እውነት ግን ቸሩ መንግስት ቪኦኤን እና ዶቼቬሌን ጥምድ አድርጎ የያዘው በነዚሁ የተረገሙ ሰዎች ምክንያት ይሆን እንዴ ?

  አቶ አዲሱ አበበ የቪኦኤው ለካንስ የማ/ቅ ንክኪ ነህና ? _ሞት በተሻለህ ከ ከ ከ ወይ ነዶ ወይ ነዶ የት ሄደን እንሙት ጃል ? አሉላ አሉላ ወይ ነዶ ወይ ነዶ ! ጎበዝ

  እያንዳንዱ እንደሥራው የሚፈርድ እግዚአብሔር እንጅ ሰው አይደለም። ይህንንም ከቅዱስ ቃሉ ተምረናል

  ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሁ በሰው ፈቃድና በተጥባበ ነገር የተጀመረ ከሆነ ማህበሩም ይፈርሳል፡፡ አባላቱም ይበተናሉ፡፡ ተራውንና ፍርዱን ለባለቤቱ ብንተውለት አይሻልም?

  እኛ ግን መጀመሪያ በዓይናችን ያለችውን ምናምን እናስወግድና ባለቤቱ እግዚአብሄርን ፍረድ ቤትህን አስከብር እንበለው _አይሻልም ? መንግስትንም ማኅበረ ቅዱሳንንም የሚያውቁ እውነተኛ ታዛቢዎች እንዳይታዘቡን ?

  ReplyDelete
 20. No question that MK is the biggest liability of the church! It needs to be reformed or dismantled. It is as evil as the Protestant Tehadso wings that are working day and night to destroy the church.

  What is sad is that other evil groups, the likes of Abekerezun, are trying to execute their other evil agenda in name of attacking MK. I pray that our Creator give us good leaders who can take us out of these crises.

  ReplyDelete
 21. why don't you give us tangible information? This is not enough to us because it has no real information. Sim matifat yasmesilibachihual enji atigabi mrja alachihu ayasibilim. Silezih ewunet kehon ewunetun asayun enji zim bilachihu mrja enaqrebalen eyalachihu libachinin atabakinubin. Yours

  ReplyDelete