Saturday, November 12, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በወንጌል ስብከት ሳይሆን በወንጀል ድርጊት ሃይማኖቱን ለመጠበቅ በነደፈው አይሁዳዊ ስልት የቤተ ክርስቲያንን ልጆች እየደበደበና እያቆሰለ መሆኑ ተሰማ፡፡ - - - Read PDF

ነገረ ሥራው ሁሉ እንደ አይሁድ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ክርስቶስንና ቅዱስ ወንጌሉን ከመቃወም ዐልፎ የክርስቶስን ትምህርት የሚከተሉትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች በመደብደብና በማሳደድ ሥራ መጠመዱን በአዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ አድባራት ድብደባ የደረሰባቸው አገልጋዮች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ እስካሁን 4 የሚሆኑ ሰባክያነ ወንጌልና አገልጋዮች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ በወንጌል ሕዝቡን ማሳመንና መያዝ ሲገባ ይህን ማድረግ ያልቻለው ማኅበረ ቅዱሳን ለድብደባ በቀጠራቸውና ባሰማራቸው ወሮበሎችና ማጅራት መቺዎች የድብደባ ተግባሩን ገፍቶበታል፡፡ እስከ ኅዳር 1 ቀን 2004 .. ድረስ እንኳ በአራት ወንድሞች ላይ ድብደባ የተፈጸመ ሲሆን፣ የማኅበሩ የጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱን አገልጋይ በዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ቀድሶ ሲወጣ ጠብቀው ደብድበው ጉዳት አድርሰዉበታል፡፡ ሌላውን ሰባኬ ወንጌል ደግሞ በተለምዶ እስረኛው ሚካኤል በሚባለው ደብር ሰብኮ ሲወርድ ደብድበዉታል፡፡ በኮተቤ ገብርኤል አገልጋይ የሆነውን ወንድምም አውቶቡስ እየተሳፈረ እያለ በድንጋይ እንደፈነከቱትና እንደሸሹ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሌላውን በገርጂ እግዚአብሔርአብ ሰባኬ ወንጌል የሆነውን ወንድም ደግሞ ተሐድሶ ከሚባሉት መካከል ለምን ጋበዝህ በሚል በጩቤ ጉንጩን ሸንትረዉታል፡፡

ማኅበሩ በአሁኑ ጊዜ ዒላማ ያደረጋቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች በጥቅምቱ የሲኖዶስ ስበሰባ ላይ በማኅበረ ቅዱሳን እየደረሰባቸው ያለውን ጫናና የስም ማጥፋት ዘመቻ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲያስቆሙላቸው ለመጠየቅ ጥቅምት 11 ቀን 2004 .. በቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተሰባሰቡትን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሲሆን፣ በዕለቱ ዲያቆን ትዝታው ላይም ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት በመፈጸም በአዲስ መልክ እጃቸውን ያሟሹ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎም በደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት በሰርግ መርሐ ግብር ላይ አንዳንድ ዘማርያንን እንደደበደቧቸው የሚታወስ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የጥቅምት 11/2004 .. ትእይንት በቪዲዮ ካሜራ ቀርጾ ያሠራጨ ሲሆን፣ በየድረገጾቹም ማን ከማን ጋር ነው? በሚል ርእስ የተዘጋጀ ጽሑፍ በማሠራጨትም ቅስቀሳ አድርጓል፡፡ በዕለቱ በስፍራው የተገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች በየተያዙበት እንዲደበደቡ መወሰኑንና ይህን የሚያስፈጽሙ ወሮበሎች ከማኅበሩ የስለላ ክፍል ጋር በመቀናጀት እየሠሩ መሆናቸውን ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ ከላይ በተጠቀሱት አራት ሰባክያነ ወንጌልና አገልጋዮች ላይ የተፈጸመውም ይህን ውሳኔ ተከትሎ መሆኑን ምንጮቹ አክለው ያስረዳሉ፡፡ ዲያቆን ትዝታው ከአንድ መጽሔት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንደተናገረው ግን እርምጃው መወሰድ ያለበት በደብዳቢዎቹ ላይ ብቻ ሳይሆን በአስደብዳቢዎቹ ላይ መሆን አለበት፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ላነበበና እግዚአብሔርን አውቃለሁ ለሚል ሰው እነዚህ የወንጀል ድርጊቶች በምንም መስፈርት መንፈሳዊ ሊሆኑ እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እነርሱ ከዓለም ስላልሆኑ ዓለም እንደሚጠላቸውና እንደሚያሳድዳቸው መናገሩን ቅዱስ ወንጌል ይመሰክራል፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በተግባሩ ከዓለም መሆኑን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለ ክርስቶስ ስም በተቀበሉት መከራ ደግሞ የክርስቶስ ወገን መሆናቸው ተመስክሯል፡፡ ደብዳቢዎቹይህን ያደረግነው ስለ ሃይማኖታችን ቀንተን ነው፤ ከእኛ በላይ ክርስቲያን የለምቢሉም እንኳ የእግዚአብሔር ቃል ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። ይህንም የሚያደርጉባችሁ አብንና እኔን ስላላወቁ ነው።” (ዮሐ. 162-3) ሲል ከእርሱ ወገን አለመሆናቸውን ይመሰክርባቸዋል፡፡ ስለዚህ የክርስቶስን ተከታዮች በመደብደብና በማሳደድ እግዚአብሔርን ማገልገል የሚባል ነገር እንደሌለ ተረድተው ክርስቶስንና ተከታዮቹን ከማሳደድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት በማመንና ወንጌሉን በሙሉ ፈቃድ በመቀበል ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሊሰደዱ ወደሚገባበት የክርስትና ሕይወት እንዲመጡ ይጋበዛሉ፡፡ ሳውልን ሆነው የወጡ ሁሉ ጳውሎስን ሆነው እንዲመለሱም ልንጸልይላቸውና የመውጊያውን ብረት ብትቃወሙ ለእናንተ ይብስባችኋል በማለት በእግዚአብሔር ቃል ልንመክራቸው ይገባል፡፡ ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ በተባለው መሠረትም በጸሎት መጋደል ከክርስቶስ ተከታዮች የሚጠበቅ የወቅቱ ዋና ተግባር እንደሆነ ብዙዎች እያሳሰቡ ነው፡፡

ክርስትና የሚጠበቀውና የሚስፋፋው በፍቅር የክርስቶስን ወንጌል በመስበክና በማስተማር መሆኑ ቢታወቅም፣ ፀረ ክርስቶስና ፀረ ክርስትና ማኅበር የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ግን ለሃይማኖት መጋደል በሚል ሰበብ ሃይማኖቱን በወንጌል ስብከት ሳይሆን በወንጀል ድርጊት ለማስፋፋት በቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ልጆች ላይ ጂሃድ አውጇል ሲሉ አንዳንዶች እየተናገሩ ነው፡፡ መንግሥትም ለዜጎቹ ጥበቃ ማድረግ ያለበት ከመሆኑ አንጻር እንደ እነዚህ ባሉ ሕገወጦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ጥያቄ እየቀረበ ነው፡፡ መንግሥት ባለበት አገር ውስጥ የራሱን የስለላ መረብ ዘርግቶ ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ለማስፈጸም ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሠራ ያለውን ማኅበር ከአሁኑ ማስቆም ካልተቻለና ወደ ቤተ ክህነቱ ሰተት ብሎ ገብቶ ሲኖዶሱን ወደ ራሱ አቅጣጫ ለማምጣትና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመቆጣጠር እያደረገ ያለውን ሙከራ እንዲያሳካ ከተተወ፣ ነገ ፊቱን ወደ ቤተ መንግሥት ማቅናቱ የማይቀርና የጉዞው የመጨረሻ መዳረሻ መሆኑን ብዙዎች እየተናገሩ ነው፡፡ ስለዚህ ማኅበሩ ሃይማኖትን እንደ ሽፋን የሚጠቀም እንጂ ሃይማኖታዊ ማኅበር አለመሆኑ ታውቆ በሕጋዊ መንገድ እንዲመዘገብ፣ ግልጽ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኖ እንዲቀጥልና ለአላማው እንዲታገል እንዲያደርግ መንግሥትን እንጠይቃለን እያሉ ነው፡፡

19 comments:

 1. God please forgive them.

  ReplyDelete
 2. Yeah, lets pray for them , when Jesus was crucified, His first words were, "Father, forgive them, for they know not what they do." His own agony did not make Him forget others. The first of His seven sayings on the cross was a prayer for the souls of His murderers.

  ReplyDelete
 3. Aba selam

  You wrote truth for the first time. Well Addis Sunday school, Rember What our Lord did when you he get traders in the church. He riased His hand to clean.
  Ohh God we thank you for your presense in our Sinod this year. our fathers did great job.

  ReplyDelete
 4. በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት በማመንና ወንጌሉን በሙሉ ፈቃድ በመቀበል ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሊሰደዱ ወደሚገባበት የክርስትና ሕይወት እንዲመጡ ይጋበዛሉ፡፡

  አይኔ ነው!!? ባሌ ነው!!? አለች ሚስት፡፡ አሁን ለየላችሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አላዋቂ አጥማቂ ማለት አሱ ነዉ ፡ ማህበሩ እኮ መሰረቱ አይሁድ ነዉ አላማዉም ፖለቲከኛ መሆን ነዉ

   Delete
 5. ጉድ ነው እነሱ ብዙ ሆነው በወንጄል ሲቀጠቅጧችሁ እናተ ትቂቶቹ ወንጌል እያላችሁ ታልቁ
  ኧረ ተው ተጠንቀቁ ባይሆንም እንኳ ለመከላከል ያህል ተነቃቁ.በዘመናችን አልቃይዳዎች እጅ ጨርሳችሁ እንዳትወድቁ.

  ReplyDelete
 6. Aye Aba Selama lol

  ReplyDelete
 7. ይህን ጽሑፍ ለእይታ እንደማታበቁት አውቃለሁ፤ ምናልባት ካበቃችሁት ለሁሉም ካልሆነ ደግሞ ለመጻፌ መነሻ ለሆናችሁኝ የጡመራ መድረኩ አዘጋጆች ከዚህ የሚከተለውን አስፍሬአለሁ፡፡

  እውነትን መረዳት የሚፈልግ ካለ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ተደበደበ ስላላችሁት ልጅ እኔ ጥቂት መረጃ ልስጣችሁ፡፡ ልጁ ዲ/ን መዝሙር አደም ይባላል፤ በጥቅምት 11/2004 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተ ክስቲያን በተደረገው የሰንበት ት/ቤቶች “የድምጻችን ይሰማ” ትዕይንት ላይ “ሰንበት ት/ቤቶች የተሐድሶ መፈልፈያ ናቸው” የሚለውን የተሐድሶውያን አቋም ደግፎ ተሰልፎ በመታየቱ ቀድሞ በመማር ማስተማርም ሆነ በሌሎች አገልግሎቶች ከሰንበት ት/ቤቱ ጋር መልካም ግንኙነት የነበረውና በቀና አገልጋይነቱ የሚታወቅ ልጅ ስለነበር ከምን ተነስቶ እዚህ አቋም ውስጥ እንደተሳተፈ ለማወቅ በጨዋ ደንብ አነጋግረነዋል፡፡

  ይህም የፈለገውን አቋም የማራመድ ግለሰባዊ መብቱን ለመጋፋት ሳይሆን በተለያዩ ጫናዎች እንዲህ ዓይነት ተግባራት ውስጥ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚሳተፉ ብዙዎች እንዳሉ ስለምናውቅ እና ጉዳዩ እኛን የሚነካ እስከሆነ ድረስ የጠራ አቋሙ ምን እንደሆነ ማወቅ ስለነበረብን ነው፡፡ ይህን ማድረግ ደግሞ ምንም ነውር የሌለውና ሕጋዊ አካሔድ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ግን “እነ ቆርጦ ቀጥል” እንደምትሉት ምንም ዓይነት የድብደባ ወንጀል አልተካሄደም፤ ለዚህ ደግሞ በዕለቱ በአጋጣሚ በሥፍራው የነበሩ ቁጥራቸው ብዙ የሆነ ምእመናን ምስክር ናቸው፤ ልጁን ያናገረውም የሚመለከተው የፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን አይደለም፡፡

  እንደውም በተቃራኒው ልጁ ጥፋቱን አምኖ ከእኛ ጋር በመወያየት የሰንበት ት/ቤቱን አባላት ይቅርታ ለመጠየቅ በመዘጋጀት ላይ በነበረበት ሁኔታ “የደኅንነት አባል ነኝ” እያለ በመፎከር በሚታወቀው ሞኙ የደብራችን ፀሐፊ ሊቀ ሥዩማን ገብረ መስቀል እና ተወግዘው “አቶ” የተባሉትና በመሰሪነታቸው አርባ ምንጭ ላይ በገጠማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ በአባ ጳውሎስ አይዞህ ባይነት እኛ ደብር ላይ በተሾሙት ቆሞስ አባ ሚካኤል አቀጣጣይነትና አስተዳደራዊ ጫናዎች ተደርገውበት ሳይፈልግ በግድ ክስ መሥርቶ የሰንበት ት/ቤታችን አባላትና የሥራ ኃላፊዎች እንዲታሰሩና እንዲገላቱ ሆኗል፡፡ የሚገርመው ግን ልጁ ከነበረበት አስተዳደራዊ ጫና ውጪ ምንም ለዚህ የሚያበቃ ጉዳይ ባለመኖሩ በሕግ አካላት ፊት ነገሩን በእርቅ ለመቋጨት ተስማምቶ ክሱ እንዲዘጋ አድርጓል፡፡

  በሌሎች አድባራት ብላችሁ የጠቀሳችሁትም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ ኬዝ ነበር፡፡ እንግዲህ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የወሬውን ጫፍ ይዛችሁ የራሳችሁን ጭራ፣ ቀንድ እና ጅራት እያበጃችሁ ለመሳል የምታደርጉት ጥረት ያስተዛዝባል እንጂ በማኅበረ ቅዱሳን፣ በሰንበት ት/ቤቶቻችንም ሆነ በቤተ ክርስቲያናችን ማንኛውም መዋቅር ላይ የምታመጡት ለውጥ እንደማይኖር ልገልጥላችሁ እሻለሁ፡፡

  መሰናበቻ፡ አበው “ወፍ ባሕር ላይ ብትፀዳዳ የወፏ ብልግና ይታወቃል እንጂ ባሕሩ አይቆሽሽም” እንዲሉ እኩይ ሥራችሁ ሁሉ ማንነታችሁን ይበልጥ እንድናውቅ ከማድረግ ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡

  አምላከ ቅዱሳን ልቡና ይስጣችሁ!!!!!

  ReplyDelete
 8. Mk is hater. The enemy of our church including to our country. With out any knowldge of spritual education why they extemly hungery for power. Any time and any where those elememt will can be kill church leader.

  ReplyDelete
 9. የዚህን ጽሁፍ አነቀጽ 4 ከ13-14 ያለውን ዓረፍተነገር አንባቢው ያስተውል፡፡

  ReplyDelete
 10. አሽሟጣጮች በሞላበት አስተያየት ምንም የሚያዝ ቁምነገር የለም።(አ-ይ አባ ሰላማ!) ብሎ አስተያየት ምንድነው? መጻፍ መብት ቢሆንም ሰው ሲጽፍ ምን ሊጽፍ እንደፈለገና በተጻፈው ጽሑፍ ዙሪያ አስተያየቱ፤ትችቱና ጥቆማው ለሌላው የሚታይ መሆን ሲገባው (አ-ይ) ብሎ ነገር ለቅሶ አይሉት ሃሳብ ወይ ምሬትና እሮሮ እንዲያው ድፍን ያለ ነገር ምንድነው? አንዳንዶች ማሽሟጠጣቸው ከውስጥ የሚሰማቸውን ቁጭት ለመተንፈስ እንጂ በሚደግፉት ወይም በሚቃወሙት ነገር ዙሪያ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው የ«ሆ በለው» ዘማሪዎች አባላት ናቸው።
  ይህንን ያህል ካልኩ ስለ የወንድሞች ከሳሽ ማኅበር ተግባራት ዙሪያ የተጻፈውን የላይኛውን ጽሁፍ ተንተርሼ የበኩሌን ጥቂት ልጨምር። ለአባቶችን ወይም ምሁራን ለተባሉት አንዳንድ ያልገቡኝንን የቤተክርስቲያናችን ጥያቄዎች ግራና ቀኝ ተገላምጬ ሳቀርብ ያሉኝን ልንገራችሁ? አንተ አርፈህ ስራህን አትሰራም? ሰውዬው ስሜን አታስጠፋኝ! እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አታንሳብኝ! ከሚሉኝ አንስቶ ጥያቄህ ትክክል ነው፣ ግን ማን ይሰማሃል? ጴንጤ ወይም ተሃድሶ ብለው ያባርሩሃል! ስንት ዓመት የተቀመጠ ነገር ብትነካካ ይሄ ሕዝብ ሃይማኖታችንን ነካ ከሚልህ በቀር የሚሰማህ የለም፣ ይልቅ አርፈህ ተቀመጥ! የሚሉኝ ሞልተዋል። ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው አርፈህ ተቀመጥ! ማኅበረ ቅዱሳን እንዳይሰማህ በሚል ማስጠንቀቂያቸው ነው። አንድ ጊዜ አንድ ጳጳስን ከተአምረ ማርያም ጓደኛዬ ጠየቃቸው። እንዲህ በማለት«ተአምሬን አምኖ ቢሰማ ስጋውን ደሙን እንደተቀበለ ይቆጠርለታል» የሚለው ትክክል ነው ወይ? ቢላቸው የሰጡት መልስ «ውሸት ነው፣ ማርያም ይህንን አላለችም፣ ስጋዬን ያልበላ፤ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለውም ያለውን የልጇን ቃል እመቤታችን አትቃወምም፣ ስራ ፈት መነኩሴ የጨመረው ነው፣ ግን ይህ ይውጣ ማለት ቀርቶ እኔን እንደጠየቅኸኝ ሌላውን ብትጠይቅ ዛፍ ላይ ይሰቅሉሃል አሉት። ጳጳሱም አሉ፤ ጓደኛዬም አለ። እኔም አንድ ጊዜ ባስ ተሳፍሬ ወደቃሊቲ ስሄድ የዲያቆን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤልን «ማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ማኅበረ ሰይጣን» የሚለውን መጽሐፍ እያነበብኩ በነበረበት ወቅት ቆመው የማነበውን ገጽ ሲከታተሉ የነበሩ ሶስት ሴቶች «ማኅበረ ቅዱሳንን የሚሳደብ እሱ የቤተክርስቲያን ጠላት ነው» የሚል ንግግር ለእኔ እንዲሰማ እያደረጉ እርስ በእርሳቸው ይነጋገሩ ነበር።ማንበብ እንዳልችል ይረብሹንና አእምሮዬን ይሰርቁ ጀመር። ይህ እንግዲህ ለረብሻ መሆኑ ነው። በቃ እኔ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚነቅፍ መጽሐፍ ማንበብ የለብኝም ማለት ነው።ሌላ ጊዜ ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ካፊቴሪያ ካንድ ጓደናዬ ጋር ቁጭ ብለን ስለማቅ ጉዳይ ስናወራ ቀጥሎ ካለው ወንበር ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንድ ጀርባውን ለእኛ ሰጥቶ ጆሮውን ግን እንደሳተላይት ጠምዶ ያዳምጥ ነበር። የጫወታችንን ርእስ ቀይሬ በሹክሹክታ ስናገር ድምጻችን ስለራቀው ያልተመቸው ሰው መስሎ ወንበሩን ወደእኛ አንፋቅቆ ያንን ዲሽ ጆሮውን ጠመደብን። እኔ እዚያው ቤተክህነቱ አካባቢ ስለምሰራ ይህ ሰላይ ከስራዬ እንድፈናቀል ነገር ይሰራብኛል ብዬ ዝም አልኩ። ጓደኛዬ ግን የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ምኑም ያልነበረ ሹመኛ ስለነበረ «ማኅበረ ቅዱሳን ማለት እኮ ቅንጅት ማለት ነው» አለና አረፈው። ያ ጆሮውን ደቅኖ ያዳምጥ የነበረው ሰው እንዲህ ደፍሮ የሚናገረውን ሰው ጀርባ ከመስጠት ማን መሆኑን ማየት ሳይሻል አይቀርም በሚል ስሜት ፊቱን አዙሮ ተመለከተን። ጓደኛዬም ምነው ዞረህ አየኸን? ቅንጅት ነህ እንዴ? ከሆንክ ለቅንጅት የተዘጋጀ ስፍራ አለ! አለውና መርዶ ነገረው። የጓደኛዬን የቅንድቡን 11 ቁጥር ሲመለከት ሳይደነግጥ አልቀረም መሰለኝ እንዳልሰማ ሰው ዝም ብሎ ፊቱን መለሰ። እንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን ሌላኛው ሃይማኖታዊ መንግስት የስለላ ድርጅት ነው። በውሸት ያሰከራቸው ወጣቶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ይሟገቱለታል። ለድብድብ አይመለሱም። ማኅበረ ቅዱሳን በግል ወይም በቡድን የጓደኞች ምስጢራዊ ንግግር መጥላት ወይም መንቀፍ ይቻላል። የቤተክርስቲያን ሰራተኛ ሆነህ በግልጽ ጉባዔ ማኅበረ ቅዱሳን የማይጠቅምና ነጋዴ ቡድን ነው ብለህ መናገር አትችልም። ወይ ያስደበድብሃል ወይም ከስራህ እንድትፈናቀል ያደርግሃል። ይህ እውነት ነው። 100% ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክህነቱ አካባቢ እንደወያኔ የደህንነት ድርጅት የሚፈራ ኃይል ነው። ይህንን ኃይል አባ ጳውሎስም አልቻሉትም። አባ ሠረቀም እንዲሁ። የተደበደበው ጽጌ ስጦታው፤ ከድብደባ ባሻገር ለግድያ ሲፈልጉት ሀገር ጥሎ የተሰደደው ሙሉጌታ ኧረ ስንቱ? ይህ ማኅበር መንፈስ ሆኗል። መንፈሱ ሰው በመክሰስ፤ በመደብደብ፤ በመሰለል፤በማሳደድ፤በመነገድና በቤተመቅደሱ የተገኘ ርግብና ገንዘብ ለዋጭ በመሆን እየሰራ ይገኛል። እኛስ አውቀነዋል። መንግስትም አውቆታል። የገረመኝ ግን መንግስት ይህንን ተቋም ለስለላ ሥራ አሰማርቶት ይሆን? ዝምታው ነገር ቢኖረው ነው!!!!

  ReplyDelete
 11. 5:26 ላይ የፃፍከው ካንተ ግራ የተጋባ ፅሁፍ አይ አባ ሰላማ ብለው የፃፉት ይሻላሉ:: የፃፍከውን አስተውኸዋል:: አንተ የቤተ ክርስቲያን ደሞዝተኛ ግን መናፍቅ ነህ:: አላማህ ያልተሳካው በሰው ሰውኛ በማቅ ጥረት ነው:: የማቅ ስራ የሚደገፍ ነው::ያንተ ግን የሚያስነቅፍ ነው:: እንዴት ለገንዘብ ብለህ የማታምንበት የእምነት ቦታ ትቆያለህ:: አሳፋሪ ነህ::
  አትረባም ከምር:: በግልፅ ውጣ:: ላልካቸውም ጳጳስ ለእውነት እንዴት እንደቆምክ አሳያቸው:: ሙሉ ወንጌል ካልረዳህ እንኳን ለእምነትህ ተራብ ተጠማ እንጂ ዝም ብለህ ወንድሞች እምነታችንን ስለጠበቁ አትክሰስ:: የወንድሞች ከሳሽ ተሀድሶ መሆንህ እየነገርከን እንኳን መልሰህ ትከሳለህ ማፈሪያ::

  ReplyDelete
 12. ቂቂቂቂ!! ላንተ 2፤56pm ላይ ለጻፍከው ሰው። ለምን ይመስልሃል ከነበርኩበት መቆየት ያለበኝ? ቆሻሻውንና ግሳንግሱን ከንጹሁ የእግዚአብሑር ቃል ጋር የቀላቀሉትን ለማስወገድና በሂደትም ቤተክርስቲያን ወደቀደመ ክብሯና ለእግዚአብሔር የመታዘዝ ሕይወቷ ትመለስ ዘንድ ማስተማር፤ ውስጥ ላለው ማሳወቅ፤ ማስረዳትና እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ብቸኛው መንገድ«እንደእባብ ብልህ፤ እንደርግብ የዋህ» የሆነ አገልግሎት እንደሚያስፈልግ በማመን ነው ገባህ? የወጡና የተሰደዱት ለውጥ አላመጡም ባይባልም ለውጡ የሚፈለገውን ያህል አልፈጠነም፤ እኔንና እኔን የመሰልነው ግን እዚያው መቆየታችን በእውነት ነው የምነግርህ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ችለናል። ከጳጳሳት ጀምሮ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ጸሐፊዎች፤የወንጌል ሰባክያን፤ መሪጌቶች፤ቀሳውስት፤ዲያቆናትና እስከሰንበት ት/ቤት ድረስ በሺዎች ተለውጠዋል። ይህ እውነት ነው። ቤተክርስቲያን ቤታቸው ስለሆነች ወደየት መሄድ አለባቸው? ቤታቸውን የሞላውን ቆሻሻ ነገር ያጸዳሉ፤ እንዲጸዳ ይሰራሉ። ቆሻሻውን ያስገባው ጠላትና ቆሻሻው እንዳይነካ የሚፈልግ የቆሻሻውን የጠላት አገልጋይ መቋቋም የሚቻለው በጥበብና በእግዚአብሔር ኃይል በታገዘ እውቀት ስለሆነ በዚሁ ነው ያለሁት ገባህ? በእርግጥ ጠላት ስለስራው ይጨነቃል አንተና የግብር አባትህ ማቅ ትናደዳላችሁ፤ ትበሳጫላችሁ!! «ተአምር ከሰማ ስጋና ደሙን ተቀብሏል ማለት ነው» የሚል ተረትን ለእናት፤ ለአባት፤ለወንድም፤ለእህቶቻችን እየዋሸ እንዳይቆርቡ የሚከለክልን ጠላት የምንከላከለው እዚያው ሆነን በማስተማር ነው!! ባያስደስትህም ጥሩ መልስ እንደሰጠሁህ ተስፋ አደርጋለሁ።

  ReplyDelete
 13. ተአምረ ማርያምን ተረት? እምነት እምነት ነው ተረትም ተረት ነው። እምነት ለማያምኑት ተረት ነው። እምነትን ከመተቸት በፊት ግን እምነት ምንድነው? በእምነት ቦታ ተረት ምን እመጣው? በአማኞች መቅደስ ተጠራጣሪ ምን ይሰራል? እሳት በጭድ አይጠፋም።ድፍረት ለቅስፈት። ትህትና ለልዕልና። ለማጠብ መታጠብ።

  ReplyDelete
 14. Here is more about mq,

  ማቅ ማኅበሩ ራሱ አገባሻለሁ፤ ከድቼሻለሁ፤ ትቼሻለሁ በተባሉ መበለታትና የመበለታት ቀማሾች የተሞላ ነው። ማቅ የቤተክርስቲያን ጥቁር የሀዘን ልብስ ነው እንደስሙ። እምነት ሳይሆን ባህል የሚያመልክ የብልጦችና የጅሎች ስብስብ ነው። ብልጦቹ ገንዘብ የሚገኝበት መሆኑን አሳምረው ያውቃሉ፤ እየሰሩ ያሉት ትክክል አለመሆኑም ቢያውቁም በጥቃቅንና አነስተኛ ከመደራጀት ይህ ሃይማኖትን ከለላ ያደረገ ግብርና ታክስ የሌለው ተቋም ይሻላቸዋልና አመራራቸውን በጥበብ ይመሩታል። ጅሎቹ ሴቶችና ወጣት ወንዶች ገንዘባቸውን እየገፈገፉ፤ነጠላቸውን መስቀለኛ አጣፍተው ከበሮ ሲደልቁና ማቅ ቅዱሱ እያሉ ዋናዋን ቤተክርስቲያን ለማቅ የማትመች ደካማና የተሃድሶ መፈልፈያ ሲሏት ይውላሉ። እንግዲህ ማቅ ማለት ይህን ነው። ልጆቿ አልቀው የተረፋት ጥቁር የሀዘን ልብስ፤ማቅ!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. ውስጥ ዐዋቂ ምንጮች

  ReplyDelete
 16. ማኅበረ ቅዱሳን .... "ሃይማኖቱን ለመጠበቅ" ... በነደፈው ..
  እናንተስ ….ለማፍረስ!!!!!

  ReplyDelete