Thursday, November 17, 2011

የማኅበረ ቅዱሳን ልኡካን ከአሰበ ተፈሪ ተባረሩ - - - Read PDF

እንደ እርጎ እንትን ጥልቅ ማለት የሚወደው፣ በአቶ ያረጋል አበጋዝ የተመራውና ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አባል የሆኑበት የማኅበረ ቅዱሳን አፍራሽ ቡድን ከአሰበ ተፈሪ መባረሩ ተሰማ፡፡ በዶልፊን ሚኒባስ በሰንበት ገስግሶ አሰበ ተፈሪ የደረሰው ቡድኑ ከዚህ ቀደም በእነ መጋቤ ሐዲስ በጋሻው አገልግሎት የተመሠረቱት የጽዮንና የናታኒም ማኅበራት ያዘጋጁትን ስልጠና ለማደናቀፍ አሰበ ተፈሪ እንደ ተጓዘ ተነግሯል፡፡

ማኅበረ ጽዮንና ማኅበረ ናታኒም በአሰበ ተፈሪና በዙሪያዋ እየተንቀሳቀሱ በተለይም በገጠር አካባቢ የእስልምናን መስፋፋትና የአብያተ ክርስቲያናትን መዳከም ከግምት ውስጥ በማስገባት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ለማጠናከርና በሃይማኖታቸው እንዲጸኑ ለማድረግ ባለፈው ዓመት ስብሰባ ተደርጎ የአሁኑ ስልጠና እንዲዘጋጅ በተወሰነው መሰረት ከኅዳር 4-7/2004 . ስልጠናው መዘጋጀቱን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ በአሰበ ተፈሪ ደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን በተዘጋጀው ስብሰባ ላይ 300 የሚያህሉ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ አባላት ተወካዮች፣ የየወረዳው የስብከተ ወንጌል ሀላፊዎች ሁሉ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ይህን ስብሰባ ለማደናቀፍና የራሱን አጀንዳ ለማስፈጸም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ላኩኝ የሚለው የማኅበረ ቅዱሳን ቡድን በስፍራው እንደ ደረሰ 50 ሺህ ብር እንሰጣለን፤ የባንክ አካውንት ቁጥራችሁን ንገሩን ብሎ ቁጥሩን የተቀበለ ሲሆን፣ ብሩን የምንሰጠው ስልጠናውን እኛ የምንሰጥ ከሆነ ነው የሚል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጦ ነበር፡፡ ነገር ግን ብሩን ወደ አካውንቱ ሳያስገባ ቀርቷል፡፡ በኋላም ብሩ በሞዴል 64 ለሀገረ ስብከቱ ገቢ ተድርጓል፡፡

ገቢ የሆነውን 50 ብር በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ "እነርሱ የማይገቡ ከሆነ ብሩ ይመለስላቸው" ቢሉም፣ የማኅበራቱ ተወካዮች ገንዘቡ በስማቸው ለተለመነባቸው የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ገቢ ይሆናል እንጂ ለእነርሱ ሊመለስ አይገባም፡፡ ከሕዝብ የተሰበሰበ ገንዘብ እንጂ ከማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ኪስ የወጣ አይደለም፡፡" በማለት ለብፁዕነታቸው አስረድተው ገንዘቡ ተመላሽ ሳይሆን ቀርቷል ብለዋል ምንጮቻችን፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ካለማግኘቱም በላይ፣ ማኅበረ ጽዮንና ማኅበረ ናታኒም እነአቶ ያረጋልን በመቃወም "በዚህ ስልጠና እንኳን ማገልገል መሳተፍም አትችሉም፤ እንደ እናንተ ድርጊት ቢሆን ሌላም ነገር ይከተላችሁ ነበር፡፡ ነገር ግን የተማርነው ቅዱስ ወንጌል አይፈቀድልንም፡፡ ስለዚህ 5 ደቂቃ ውስጥ ከተማችንን ለቃችሁ ውጡ" በማለት ከስብሰባው ቦታ አባረዋቸዋል፡፡ የከተማው በርካታ ባጃጅ ነጂዎችም ከከተማው በባጃጅ አጅበው አስወጥተዋቸዋል፡፡

ስልጠናውን እየመሩ ያሉት የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ሊቀ ብርሃናት በቃሉ ሲሆኑ፣ በተሳታፊዎች መካከል ከወረዳ የመጡና ተቀላቅለው የገቡ የማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ አባላት ሾልከው እንደተቀላቀሉና በፍርሃት ተሸብበው እንዳሉም ለመረዳት ተችሏል፡፡

የማኅበረ ጽዮንና የማኅበረ ናታኒም አመራሮችና አባላት በእነመጋ ሐዲስ በጋሻው አገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን መመለሳቸውንና ከተለያዩ ሱሶች ነጻ ሆነው ቤተ ክርስቲያንን በሚችሉት ሁሉ ለማገልግል ደፋ ቀና እያሉ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ተሐድሶ ናው እያለ እንደሚከሳቸው ተናግረዋል፡፡ ይህም የማኅበሩ ዋና ሥራ በመሆኑ ለእርሱ ስድብና ክስ ቦታ እንደማይሰጡና ቤተ ክርስቲያናቸውን ባላቸው አቅም እንደሚያገለግሉ እየተናገሩ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን የሲኖዶሱን ስብሰባ በገንዘብ ሀይል ለመለወጥ እንደሞከረው ሁሉ በአሰበ ተፈሪም ተመሳሳይ ድርጊት ለመፈጸም ቢንቀሳቀስም ገንዘቡን ከመክሰርና ውርደትን ከመከናነብ በቀር ያተረፈው ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ካህናት፣ የሰንበት ተማሪዎችና ምእመናንም ሁሉ ራሳቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን በሃይማት ካባ ከተሸፈነው የማኅበረ ቅዱሳን ድብቅ አጀንዳ፣ ወረራና አፍራሽ ተልእኮ ሊታደጉ እንደሚገባ ማኅበረ ጽዮንና ማኅበረ ናታኒም ትልቅ ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

19 comments:

 1. Waw aba selama,
  What a nice information did you post? Try your best to demolish this association and bring the new one which will be headed by the so called megabi hadis begashw and some more pastors. Then change your name from abba selama to . . . . . . . . . .

  ReplyDelete
 2. abet wushet!!!! beka kededededee new zimbilo tatachihu wuuuuuh ye kirstos telatoch nachihu enaten bilo degmo aba selama

  ReplyDelete
 3. እን በጋሻውና አዝታው መሰሎቻቸውን ጨምራችሁ በእግዚአብሔር ስም ልጠይቃችሁ እባካችሁ ቤተክርስቲያንን አታበጣብጡ ትክክለኛ የቤተክርስቲያን/የተዋህዶ/ ሰዎች ነን ካላችሁ እስቲ የመጣባችሁን ሁሉ እንደፈተና ቆጥራችሁ ከእግዚአብሔር ሁሉንም ጠብቁ እንጂ ጳጳሱ እንደዚህ አሉት ማህበረ ቅዱሳን እንደዚህ አደረገ እያላችሁ የውሸት ኘሮፓጋንዳ አትንዙ ቅዱስ ሲንዶስም ስንት በእግዚአብሔር የተመረጡ ሰዎች ያሉበትንና በጌታ ፈቃድ የተሾሙ አባቶችን በገንዘብ ኃይል እንደሚንቀሳቀሱ ማህበረ ቅዱሳን በገንዘብ ውሳኔአቸውን አስቀየር እያላችሁ አባቶችን በሀሰት ወሬ አትዝለፉ በእግዚአብሔር ስም እለምናችሁአለሁ አደራ፡፡

  ReplyDelete
 4. በቅዱሳን ስም የተሰባሰበው አሸባሪ ቡድን ከማይወጣበት አዘቅት ዉስጥ ገብቷል፡፡ ምዕመናን ሁሉ ቤተክርስቲያናችሁንና ሃይማኖታችሁን ከ"ማኅበረ ቅዱሳን" ተፅዕኖ አላቅቁ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡

  ReplyDelete
 5. Megabe Hadis Begashaw, who is the best preacher, in Ethiopian Orthodox church; however, Mk elements have accused him baselessly. With out formal church education they speaking together one single word that means Tehadesso, but and if those elements naive of any knowldge in the church; inaddition to, lack of spritual ethics. All those hateres have clear and concise plan in our church, to steal money, killing of church father and then to take power from the church and the government. Sadely, the one who was set fire him self in Southern region of Ethiopia Yenesew Gebre was fundemetalist elements of Mk.

  ReplyDelete
 6. oo amelake eserael minew mk wengel ayesfafa ne ende milut koy lemhonu Ato YAREGAL ABEGAZ behdebet betekeresteyan endizega new ende mifelegew be GERMEN FRANKFURT BE K: MAREYAM betkeresteyan yesebeka komite mercha benebrebet weket mk awede eryu azegajetew nebr endeagatami ke ethiopia yemetu memheranoch alu sibal yesemu meskin deg yewahe abat menkuse teru mesloachew ato mitekuna,abegazen gubayew lay yegabezuachewal min hone meselachehu wengel sebeken belew meemenun ers be esrs yemiyagach temhert astelalefu betekeresetyan west yemaheberu abalat banesut eweket kedemew bemender tederajetew kene abegaz gar tenegagerew bemegebat leastedadariew anu ensu bigabezuachew bemalet bematalel yesyetan sera seru ato yaregal lek taliyan yemilano betkeresteyan yemezegat eta befrankfert yemders yemeslegnal belo tenagere gin hasabu alsemerm yeghanem dejoch ayecheluatem bekentu atdekemu mk ahunem teru negr new yaderegachehut asebe teferiwoch menkat aleben hulachenem enzin awenabajoch bertu enbera ke Germen frankfurt H.M

  ReplyDelete
 7. wow that is good job God bless you Asebetefer prople

  ReplyDelete
 8. Don't you think that God send MK to pay for this important project?

  ReplyDelete
 9. gudd eko new misemaw awassa endeza yewha yehonewen hizeb siyabetabetu ahun degemo wedeasbeteferi gora alu egzioo minale sele ewenet belew binoru chegeru eko lemin yegna temehert weyem sebket kene Dn tezetaw, mertenesh weyem sebakeyanu beleto aletesemam new yenetela ser kereseteyanoch sirhat becha eko new negerachew ere egzioo ene balhubet hager be canada kanada malet new migermew senbet temhert bet west teru agelegay kale beka beziyam bezhi sim matefat new serachew yekinat menfes yaderebachew yiker yebelachew wenet yebtekeresteyan lijoch beretu wenet

  ReplyDelete
 10. Kehuletachihum yemisetew asteyayet menfesawi fiker yegodelew meslo siletayegn teamaninetu ateratari new.ebakachihun gira atagabun TG

  ReplyDelete
 11. abet wushet!!!! I will not come back to this website. It is just a liar.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ANTE/ANCHI NESHA YEMATMETAW/YEMATMECHIW.YEMISERAWUN DIRAMA SILEMINEGRUN BEYEKENU SANAYACHIHU MADER ANCHILIM.BERTU EWNETEGNA BIBLE AMAGNOCH.CHEER UP.(BORN AGAIN CHRISTIAN)

   Delete
 12. today u said 9 times ማኅበረ ቅዱሳን

  ReplyDelete
 13. God bless begashaww

  ReplyDelete
 14. Please remove our true fathers from your page up. I read your news and all are irilevant and are not our church teaching. Jut preach protestantism clearly. Why you fear? why not you disclose your self? You always talk irelevant issue and you are extremly lier. I never seen such a lier like you in earth. I know you will not post it but just read for your self.

  ReplyDelete
 15. በቅድሚያ ለአባራሪና ተባራሪ እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና እንዲሰጣቸው እመኛለሁ። አባራሪዎች ጠላት የሚሉት ኃይል እንዳላቸው የሚያሳይ እንቅስቃሴ ላይ ነበሩ። ተባራሪ የተባሉትም የሚመኩበት የጳጳስና የገንዘብ ኃይል እንደነበራቸው አንብበናል። ጥያቄ ብናቀርብ አግባብ ይኖረዋል ባይ ነኝ።
  ለአስበተፈሪያውያን፣--- ማኅበረ ቅዱሳን ጠላት ነው? ባለጋራ ነው? አይደለም፣ ባይ ነኝ። ጠላት ሆኖ ከተገኘም ልንጸልይለት ይገባል። ወንጌል የሚያስተምረን ያንን ነውና። ሰዎች የልባቸውን ፈቃድ ለመፈጸም ቢታገሉ ወይም ቢንቀሳቀሱ በራሳቸው አይደለም፤ ያንን ክፉ ዘር በልባቸው የሚዘራው ጠላት ሰይጣን ነው። «እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው» እንዳለው በማቴ13፣39 ላይ። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳንን በሰው ሰውኛነት ጠላት አድርገን እንድንዋጋው ሰይጣን ይፈልጋል። እርሱ ግን አድሮበትና ከኋላ ሆኖ ማኅበሩን ይልከዋል። ደጋፊዎቹን በግራም በቀኝም ያነሳሳል። እንዲጮሁለት አንደበታቸውን ይከፍታል። በየብሎጉ የሚቃወሙት ዝም እንዲሉ ይሰድባል፣ ያሰድባል፣ ያሽሟጥጣል፣ ይዘልፋል፣ ከዚያ ውጭ ግን የሰዎችን ልብ የሚያቀና የወንጌል ቃል አንድም መስመር አያስተምርም። የምስራቹን አይሰብክም።( ደጀሰላምን ልብ ይሏል? የሚታየው «ሰበር ዜና» ሲል ብቻ ነው)
  ስለዚህ አስበ ተፈሪዎች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያደረጋችሁትን ዘመቻ በጾምና በጸሎት ካልሆነ በሰልፍ አታሸንፉትም። ማኅበረ ቅዱሳን በራሱ ምንም ነው። ምድራዊ ኃይልን የታጠቀ ነው። በሚነዳው በዚህ ኃይል ግን የበለጠ ተጠናክሮ ሰውኛ ዘመቻችሁን ይሰብረዋል። እንደዚህ ዓይነቱን መንፈስ ለማሸነፍ «ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው» እንደተባለው በማቴ 17፣21በእነሱ አድሮ አስበ ተፈሪ የመጣን ስጋ ለበስ መንፈስ ለመዋጋት ይህንን ሰይፍ ያዙ ብለን እንመክራለን፣ በሰው ጉልበት አትታገሉ ነው የምንለው። ሌጌዎን ብዛት አለውና።
  ለማኅበረ ቅዱሳውያን---- ስራችሁ ምንድነው? እናንተስ እነማን ናችሁ? ማን ላካችሁ? አድራሻችሁ አዲስ አበባ፣ አስበተፈሪ ምናችሁ ነው? እግራችሁ ምን ያህል ይረዝማል? የሚስማሟችሁና የማይስማሟችሁ ጳጳሳት አሉን? እንዴት? ለምን? ብለን እንጠይቃችኋለን። የምታስተምሩት ምንድነው? ማንን ነው? የማይፈልጓችሁን የምታስተናግዱት እንዴት ነው? ሌላው በእናንተ ይመዘናል? እናንተስ በሌላው ትመዘናላችሁ? የማንኛው ሚዛን ትክክል ነው? በምን? መጽሐፍ ቅዱስን ታውቃላችሁ? ታምናላችሁ? ትፈጽሙታላችሁ? ከብዙ በጥቂቱ የምናነሳቸው ጥያቄዎች ናቸው። ግል'ጽ ያለ መልስ ያስፈልጋል፣ ግን እንደማይኖራችሁ ይታወቃል። በታሪክ አጋጣሚ በቤተክርስቲያን ውስጥ እንደተነሳችሁ በበጎም ይሁን በመጥፎ ለብዙ ነገሮች የምትጠሩ መሆናችሁ ግልጽ እውነት ነው። እንግዲህ አንድ ፍሬ መራርና ጣፋጭ ሊሆን አይችልም። የተቀላቀለበት ተግባራችሁ እንደቴዎዳስ ዘግብጽ ሆኖ ከሆነ ቀኑ ይጠርም ይርዘም ትጠፋላችሁ። የሐዋ 5፣36 በሌላ በኩል ምናልባትም የተከላችሁ ሰማያዊ አባት ሆኖ ከሆነ የአባታችንን ድምጽ ስለማሰማታችሁ ቃሉን ስትመሰክሩ፣ ሳትቀላቅሉ ስትሰብኩ፣ ሳታስቀኑት ስታመልኩ ማየት አለብን። ጸብና ክርክር፣ ጥልና የጥል ሰልፍ ሳይሰማባችሁ ሊታይ የግድ ነው። ገንዘብና የገንዘብ ወሬ፣ ሥልጣንና የሥልጣን ሽኩቻ የሚታገላችሁ እንዳልሆነ ሊመሰከርላችሁ ይገባል። ክፍፍልና መካሰስ፣ ልዩነትና መቧደን የማታስተናግዱ ስለመሆናችሁ ምን እናረጋግጥ?
  ሮሜ 16፣17 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤
  ቲቶ 3፣10 መለያየትን የሚያነሣ ሰው ጠማማ እንዲሆን በራሱም ላይ ፈርዶ ኃጢአትን እንዲያደርግ አውቀህ፥ አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜም ከገሠጽኸው በኋላ እንዲህ ከሚመስል ሰው ራቅ።
  1ኛ ቆሮ 5፣8 ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም
  1ኛጴጥ 2፥1 እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥
  የሚለውን ቃል በምን እናረጋግጥ?

  ReplyDelete
 16. mk, is a taliban they will abolish from the church soon . We are working hard to abolish them in United States in Atlanta, Dallas, Washigton. They are almost dead other states.

  ReplyDelete
 17. KeJermen H.M malet Haile Melekot new. Yedro simachewun metekemachew tiru new. Yewah mesayu Aba S. Ewnetawun melaw Jermen slemiawqew rasachewun new yagaleTut. Aynachewun beChew yatebu yebete krstian zerafi.
  Egnama enawqalen ewnet yalewun sew erswo endemaywedu. Lib endisetwot Egziaher kemetseley wedehuala anilim

  S.M Frankfurt

  ReplyDelete
 18. አባ ሰላማውያን
  ስለ አሰበተፈሪ ጉባኤ እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ስለነበረው ሁኔታ ለመዘገብ መሞከራችሁ እናንተን ሳይሆን የወዳጆቻችሁን ማንነት በርግጥም እንድናውቅ በድንግዝግዝ ላለነውም ይፋ አድርጋችሁልናል በእውነቱ ሳላውቀው ጥላቻን ይዤበት የነበረውን ማህበርም ንጹህ መሆኑን እና ኦርቶዶክሳዊነቱ አጠያያቂ እንዳልሆነ ጥሩ ማስረጃ ሆናችሁናል፡፡ እኔ እና መሰሎቼ በዚሁ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ በነዛችሁባት ከተማ የማህበረ ጺዮን እና ናታኒም ማህበር አባላት ስንሆን ረጅም ጉዞን አብረናችሁ ሳንጓዝ በአጭሩ የበላይ ፊታውራሪዎቻችንን ማንነት መገንዘቢያ አቋራጩን መንገድ እግዚአብሔር ስለገለጠልን ልናመሰግነው እንወዳለን፡፡ በአሰበተፈሪ ለምትገኙ የማህበረ ቅዱሳን አባላትም ከጀርባችን ሆነው እኛን ወደ ሌላ አላማ ማስፈጸሚያነት ይነዱን ስላሉት የውስጥ ተሀድሶዎች የመናፍቃን አርበኞች በቂ መረጃ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ስለሆን በጋራ አባቶች በተገኙበት ልንነጋገር የምነችልባቸውን መድረኮች ብታዘጋጁልን መልካም ነው እያልኩ አደራ የምላችሁ በጭፍን ማህበረ ናታኒም እና ጺዮን ማህበራት አባለት የሆነውን ሁሉ በአንድነት ከኒህ ተሀድሶዎች ጎራ እንዳትመድቡን አደራ ማለት እንወዳለን፡፡ እኛ ለዚህ እኩይ አላማ ማስፈጸሚያ መታሰባችን የገባን ከአመት በኋላ ነው፡፡ ስንሰባሰብም ከአጉል ሱስ ተላቀን በቤተክርስቲያን እንድንማር አልባሌ ቦታዎች ከማሳለፍ እንድንቆጠብ መታሰቡ ስቦን ቢሆንም የክፋት አርበኞች የኋላ ደጀን ለማድረግ ያሰቡን መሆኑን ካወቅንባት ከአሁኗ ክስተት በኋላ ተገቢውን መረጃ በማጠናቀር እንድንሰራ ሆነናል፡፡ አባ ሰለማ ተብዬው ብሎግ ኦርቶዶክሳዊ ሳይሆን የመናፍቃን ብሎግ መሆኑን ማንም ያለአንድምታ ሊረዳው የሚችል ብሎግ ነው፡፡ እኛ እኮ የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነትን የምንቀበል ኦርቶዶክሳዊያን ነን እንጂ መናፍቃን አይደለንም፡፡ እኛ እኮ የጻድቁ የአቡነ ተክለሃይማኖት ልጆች እንጂ ጻድቁን ከሚጠሉቱ ወገን አይደለንም፡፡ አዝማቾቻችን ግን እንኳን አወቅናችሁ፡፡

  ReplyDelete