Friday, November 25, 2011

ስሕተቶቻችን ይታረሙ - - - Read PDF

ቤተ ክርስቲያናችን ፊልጶስ ባጠመቀው ጃንድረባ አማካኝነት በኢትዮጵያ ከተመሠረተች በኋላ በአባ ሰላማ መሪነት እያደገች እየተስፋፋች መሄዷን፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የሰሜን አፍሪካ መናፍቃን ወደ ኢትዮጵያ እየተሰደዱ መጥተው ልዩ ልዩ ባዕድ ነገሮችን ተክለውባት እንዳለፉ ታሪክ ይናገራል አሁን እያየን ያለነውም ይህንን እውነት ነው።

ለምሳሌ የጥንቆላ ሥራዎች በቤተ ክርስቲያን ሰዎች በስፋት ሲሰራባቸው ይታያል። ጥንቆላው የሰሎሞን ጥበብ እየተባለ ስለሚነገር ብዙ ሊቃውንት ተብለው የሚጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት ነገር ነው። አቃቤ ርእስ፤ ግርማ ሞገስ፤ መስተፋቅር፤ መድፍነ ጸር፤ ወዘተ እየተባሉ የሚጠሩ ድግማቶች በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የሚዘወተሩ ናቸው። አሁን አሁን ደግሞ የገብያ፤ የፍቅር ተብለው ተሰይመው በዘመናዊ መሣሪያ እየታተሙ ለምእመናኑ እየተሰራጩ ነው። በተጨማሪም ሕልመ ዮሴፍ፤ ምሕሳበ ቅዱሳን፤ ምህሳበ መላእክት የሚባሉ ድግማቶች አሉ እነዚህ ድግማቶች በስፋት የሚዘወተሩት በባሕታውያኑ ነው።

ሕልመ ዮሴፍ የሚደገመው አንድ ሰው እጣ ፋንታውን ለማወቅ በሚፈልግበት ጊዜ ባሕታዊ ወይም መነኩሴ ወይም መናኝ ወደ ተባለው ሰው ሄዶ ጸልይልኝ ሲለው ባሕታዊው ሕልመ ዮሴፍን በጠያቂው ስም ደግሞ ሲተኛ ስለ ሰውየው ሕልም ይታየዋል ይባላል። ይህ በብሕትውና ስም የተሸፈነ ጥንቆላ መሆኑ ነው።

ምሕሳበ ቅዱሳን የሚባለው ድጋም ደግሞ የሞቱ ቅዱሳንን ለማናገር የሚደገም ነው። ይህን ድግማት ለመድገም ብዙ ውጣ ውረድ አለው። በመጀመሪያ ውርሻ መዋረስ አለበት፤ ከሴት መራቅ አለበት፤ ሁልጊዜ ሽቶ አይለየውም፤ ሥጋም መብላት የለበትም። ይህ ሙታንን የማናገር ሥራ በባሕታውያን የሚዘወተር ነው። እግዚአብሔር ግን ሙታንን መሳብ ርኩሰት መሆኑን አስቀድሞ ተናግሯል።

"አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ" ዘዳ 1811

በቤተ ክርስቲያናችን ሥር የታቀፈው ምእመን በነዚህ ደጋሚዎች ምክንያት ከመጣበት የመንፈስ እሥራት ለማላቀቅ ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል። ብዙ የመናፍስትን ሥራ የተለማመዱ ወገኖች መርጌታ፤ ደብተራ፤ ሊቅ፤ የሚለውን ስም በመያዝ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ስለሆኑ አምልኮተ እግዚአብሔር ከአምልኮተ ባዕድ ጋር ተቀላቅሏል። ዝማሬው፤ ማህሌቱ፤ ጸሎቱ፤ ስግደቱ፤ ስእለቱ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት ስለሆነ መጥራት አለበት።

ለምሳሌ ጸሎቱን ብንመረምረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ሆኖ እናገኘዋለን። ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት ነው እንጂ ከመላእክት፤ ካረፉ ቅዱሳን፤ ከማርያም ጋር መነጋገር ማለት ግን አይደለም። እግዚአብሔርን የምናመልከው በጸሎት አማካኝነት ነው። በአምልኳችን ጊዜ ወደ መላእክትም ወደ ማርያምም የምንጸልይ ከሆነ እነርሱንም እያመለክን ነው። ጸሎት እራሱ አምልኮ ነው።

ጌታ ስለጸሎት ሲያስተምር "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ..." በሉ ብሎ የጸሎታችንን አቅጣጫ አሳይቶናል። በማቴ 66 ላይ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትሕ በግልጥ ይከፍለሃል በማለት በሥውር ላለው አባታችን እንድንጸልይ በግልጥ አስተምሮናል።

ሐዋርያትም "በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምሥጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ሲሉ አስተምረዋል ፊልጵ 46 ልመናችንን ማስታወቅ ያለብን፤ ጸሎትና ምልጃ ምሥጋና የሚቀርበው ለእግዚአብሔር ነው፤ የሚያስጨንቀንንም የምናስታውቀው ለጌታ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ቅዱሳን ነቢያት አባቶች ሁሉ ጸሎታቸው ወደ እግዚአብሔር ነበር፤ ኃጢተኞች እንኳ ሲጸልዩ የኖሩት ወደ እግዚአብሔር ነው። ምክንያቱም ጸሎትን ሊሰማ የሚችለው በሁሉ ሥፍራ የሚገኝ ሁሉን የሚችል ሁሉንም የሚሰማ እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ ነው።

በኛ ቤተ ክርስቲያን ግን ወደ መላእክት፤ ወደ ማርያም ወደ አረፉ ቅዱሳን ይጸለያል። ድርሳነ ሚካኤል፤ ድርሳነ ገብርኤል፤ ወደ መላእክት የሚጸለዩ ጸሎቶች ናቸው። የሰኔ ጎልጎታ፤ መልካ ማርያም፤ የህሊና ጸሎት፤ መጽሐፈ ሰዓታት ወዘተ ወደ ማርያም የሚጸለዩ ጸሎቶች ናቸው። በጠቅላላው መልካ ጉባኤ የሚባለውን ትንሣኤ ዘጉባኤ እና ተስፋ ገብረ ሥላሴ የሚያሳትሟቸውን እየተጠረዙ የጸሎት መጽሐፍ ተብለው ለሕዝብ የሚከፋፈሉትን ድርሰቶች ሁሉ ብናስተውላቸው ባዕድ አምልኮ የተሞላባቸው፤ ነውር የበዛባቸው፤ በመናፍስት ጠሪዎችና በሙታን ሳቢዎች የተደረሱ ናቸው።

ሕዝቡ እነዚህን ጸሎቶች ጀምሮ መተው ወይም ማቋረጥ፤ መቅሰፍትን ያመጣል ተብሎ ስለሚነገረው በመንቀጥቀጥና ብዙ ሰዓት በመቆም ቢደክመው እያዛጋ በግድ ሳይወድ ይጨርስዋል። በትራስህ ስር አርገው፤ ባንገትህ አንጠልጥለው ስለሚባል ብዙ የጸሎት መጽሐፎች በምመናን አንገትና በየግድግዳው ተንጠልጥለው ይገኛሉ።

ወደ ማርያም የሚጸለዩ ጸሎቶች፥

"እግዝእትነ ማርያም አዕርጊ ጸሎተነ ወአስተስርዒ ኃጢአተነ ቅድመ መንበሩ እግዚእነ" ትርጉም፦ "እመቤታችን ማርያም ሆይ ጸሎታችንን አሳርጊልን፤ በጌታችን መንበር ፊት ኃጢአታችንን አስተስርይልን"

እመቤታችንን ጸሎታችንን አሳርጊልን ስንል ምን ማለታችን ነው? እግዚአብሔር ጸሎታችንን አልተቀበለውም ማለት ነው? በእምነት የምንጸልየውን ሁሉ እግዚአብሔር በቀጥታ እንደሚቀበለው መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። እመቤታችን ተቀብላ እንደምታሳርገው የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ግን የለም። በሌላ ጊዜ ደግሞ "መላከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰዓል ወጸሊ በእንቲያነ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ አቢይ" ትርጉም "የሰላማችን መላክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ሆይ ስለኛ ጸልይ ለምን ጸሎታችንንም በጌታችን መንበር ፊት አሳርግልን" በማለት እንቀባጥራለን።

ማርያምን አሳርጊልን ስንል መቆየታችንን እረስተን እንደገና ሚካኤልን አሳርግልን እንላለን አንዱን ሥራ ለሁለት መስጠታችን ይሆን? አብሾ ባሳበዳቸው ደብተራዎች የተደረሰ በመሆኑ ግራ የሚያገባ ባዶ ቃላት ነው።

ኃጢአታችንን አስተስርይልን የሚለውም የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት የሚቃወም ነው። ኃጢአት የሚሰረየው ንስሐ ስንገባ እና በጌታ ፊት ወድቀን ይቅርታ ስንጠይቅ ብቻ ነው፤ ማርያም ግን ኃጢአትን እንደምታስተሠርይ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፈጽሞ የለም። እኛ ማርያምን እንድታማልደን እንጠይቃታለን እንጂ ወደ እሷ አንጸልይም እያሉ የሚከራከሩ የቤተ ክርስቲያናችን መናፍቃን "ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንበሻል ስለ አባትሽ ስለ ሃና ብለሽ ስለ እናትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ" የሚለው የማን ጸሎት ነው? እዚህ ላይ እመቤታችንን "አድኚን" በማለት ደብተራዎቹ አዳኝ አድርገዋታል፤ መዳንም በሌላ በማንም የለም የሚለውን ቃል ፈጽመው ክደውታል

በታሕሳስ ገብርኤል ዚቅ ላይ ደግሞ "አድህነኒ ዘአድሃንኮሙ ሊቀ መላእክት" እያልን ስንጸልይ እናድራለን። አዳኝ እግዚአብሔር ነው ነገር ግን ራሱ እግዚአብሔር በመላእክ ወይም በሌላ ሊያድነን ይችላል፤ እግዚአብሔርን ትቶ ገብርኤልን አድነኝ ሲሉ ማደር ግን ትልቅ ክህደት ነው።

ሉሌ

20 comments:

 1. ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው በብሎጋቸው ካስተማሩት የተወሰደ....

  «እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው፥ መና ከሰማይ ያወረደላቸው፥ ተአምራትን ያደረገላቸው፥ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው፥ በደመና መጋረጃ የጋረዳቸው፥ በክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው»
  ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው- ይህንን ከየትኛው መጽሐፍ ላይ አገኙት? ሚካኤል ነው የሚል ተጽፏል? ወይስ ነገረ ሥራው ሚካኤልን ይመስላል ብለው ያልተገለጸውን አቅኚ ሆነው ነው? እግዚአብሔር ሚካኤል ስለመሆኑ ያልገለጸው ረስቶ ወይም ተሳስቶ እርስዎ ግን በትርጉም ፈትተውት ያገኙት እውቀት ነው?
  መቼም እንደማይቀበሉኝ አውቃለሁ፣ እኔን ሳይሆን ለዚያውም መጽሐፍ ቅዱስን።
  ዘፍ 21፥17
  31፥11
  48፥16
  ዘጸ 3፥2
  14፥19
  33፥1-3
  ዘኁ 22፥22 - 22፥23 - 22፥24 - 22፥25 - 22፥26 - 22፥27 - 22፥31 - 22፥32 22፥34 22፥35
  አንድም ቦታ ሚካኤል የሚል ስም ተጠቅሶ አይገኝም። እግዚአብሔር ስሙን ያልጠቀሰው ለምን ይመስልዎታል? እኛስ ስሙን መጥቀስ ለምን ይገባናል? የኛ መጥቀስ እግዚአብሔር ያልጠቀሰውን ጉድለት ለመሙላት ነው ወይስ ስውር የሆነውን ሚካኤል በትርጉማችን ገልጸን በማውጣት መልአኩን ለማክበር?
  ለዚያውም ስሙ ባልተገለጸ መልአክ እጅ እግዚአብሔር ያደረገውን ድንቅና ተአምራት ለሚካኤል ለመስጠት «እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው፥ መና ከሰማይ ያወረደላቸው፥ ተአምራትን ያደረገላቸው፥ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው፥ በደመና መጋረጃ የጋረዳቸው፥ በክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው» ማለት በፍጹም ትልቅ ስህተትና ክህደት ነው።
  እርስዎ እግዚአብሔር ያለውን ለምን መተው ይወዳሉ?
  ዘፍ 28፣15 «እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና»
  ዘጸ 6፣6 «ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ»
  ዘጸ 6፣8 «ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁባት ምድር አገባችኋለሁ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ»
  ዘጸ 10፣3 «ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ አሉትም። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ»
  ዘጸ 13፣21 «በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ»
  ዘጸ 14፥24
  ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ ሆኖ የግብፃውያንን ሠራዊት ተመለከተ፥ የግብፃውያንንም ሠራዊት አወከ። 25 የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አገባቸው ግብፃውያንም። እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ አሉ»
  ዘጸ 15፥3 «እግዚአብሔር ተዋጊ ነው፥ ስሙም እግዚአብሔር ነው»
  ዘጸ 16፥15
  የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደ ሆነ አላወቁምና እርስ በእርሳቸው። ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ። ሙሴም፦ ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው»
  ከብዙ በጥቂቱ እስራኤል ዘሥጋን የመገባቸው፣የጠበቃቸው፣ያሻገራቸው፣ የጋረዳቸው እግዚአብሔር እንጂ እርስዎ እንዳሉት ሚካኤል የሚባል መልአክ አይደለም። ዘሌ20፥24
  ነገር ግን እናንተን፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ» ዘዳ 26፣8 እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን
  26፣9 ወደዚህም ስፍራ አገባን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን።
  ቀሲስ- እርስዎ ግን በድፍረት በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀው ላልተገለጠና ላልተጻፈ የመልአክ ስም ሰጡት!!
  ላልተገለጠና ላልተጻፈ የመልአክ ስም ክብሩን ሁሉ መስጠትዎ ሳያንስ ሌሎችም ይህንኑ ስህተትዎን እንዲቀበሉ አስተማሩ!!
  ለዘለበ ምላስ የሚጽፉትን ለራስዎ እንዲመች ተርጉመው የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ካዱት!!
  ምናልባት እግዚአብሔር ይቅር ቢልዎ ንስሐ ይግቡበት!! ምክንያቱም እኔ ሰራሁ ያለውን ላልተጻፈ መልአክ ሰጥተው፣ አስቀንተውታልና!!
  እርስዎ እግዚአብሔር ያደረገውን ተአምራት ሁሉ ለሌላ አውለው እንዳስቀኑት ሰዎች ሆነዋል።
  ዘኁ 14፣22-23 በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ አሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥
  ነገሬንም ስላልሰሙ፥ በእውነት ለአባቶቻቸው የማልሁላቸውን ምድር አያዩም ከእነርሱም የናቀኝ ሰው ሁሉ አያያትም» ይላልና ያስቡበት!!!!!!
  አስተያየቴ ደስ ስለማይልዎ ፖስት ላያደርጉት ይችላሉ ብዬ ብገምትም እግረ መንገዱን የተለየ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሃሳብ አለኝ የሚልን ሰው ኮሜንት እንደሚቀበሉም ለማየት እችል ዘንድ ይኸው ላኩልዎ!

  ReplyDelete
 2. bado yadirgih bado aderekegn Menafiq

  ReplyDelete
 3. አይ እናንተ ምናለ ከቤ/ክርስቲያናችን ወጣ ብላችሁ የራሳችሁን ቢስነስ ብትሰሩ? ጥንቁልና እኮ በቤ/ክርስቲያን ውስጥ እንደ መደበኛ ትምህርት የሚሰጥ አይደለም የተወገዘ ነው እንጅ፡፡ ስለዚህ እርጥቡንና ደህናውን ቀላቅላችሁ ቤ/ክርስቲያን እንዲህ ናት አትበሉ፡፡ አንድ ግለሰብ ጠንቋይ ቢሆን ሰውየው እንጅ ቅድስት ቤ/ክርስቲያንን አይወክልም፡፡ እናንተስ እያንዳንዳችሁ በዚች በተቀደሰች ቤ/ክርስቲያን ስር ሆናችሁ ቁራሽ እየለመናችሁ አድጋችሁ አይደል አሁን እንደገና የጭቃ እሾህ ሆናችሁ መከራ የምታበሉን፡፡
  ምነ እንግዲያ እውነት ለኃማኖታችሁና ለቤ/ክርስቲያን ከተቆረቆራችሁ እዚች ቤት ሁናችሁ እናንተ ጥሩ ሁናችሁ ለሌው አርያ ያልሆናችሁ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. MENAFIK,TEHADSO EYALACHIHU ABARERACHIHUACHEW GETA MANAFIK MAN ENDEHONE BIAWKEWUM.ENDET ARAYA YIHUNU?MEKOMIA,MAKEMECHA ATU MIN YIHUNU?AHUNIM GIN LEGNA LEMINDIN ENA EWNETUN BIBLE BEMAYET FETNEN LEMNIKEBEL GIN BETAM ARAYA NACHEW.GETA YIBARKACHU.(FROM BORN AGAIN CHRISTIAN)

   Delete
  2. FIRST OF ALL U R BUSINESS MINDED HOW CAN U B RIGHT?HODACHEW AMLAKACHEW KIBRACHEW BENEWRACHEW,YETEBALUT ENDANTE AYNETOCH YIHONU?ENIE ENJA.GETA WEDEMASTEWALACHIN YIMELSEN.

   Delete
 4. But you are critisizing MK bieng such identified protestant followers. One day there will be time that God will clear you all from our beloved church. We didn't talk aboute you being a protestant. Please leave our church and warship what you chice. You can believe even in "sayitasn" if you need, you have such a freedom. If you think that you can do this by the cover of religius freedom, let me tell you you can't except for few time. So Ps..Ps..Ps... be in your place and don't use our church's name in your saying.

  ReplyDelete
  Replies
  1. EGRIABHERN ENAMLIK EYALU ENDET SEYTANIN AMLKU TIYALESH/TILALEH?ERASH GIN "MADAN BEMAYCHLU SEWOCH ENA ALEKAT ATTAMENU"MEZMUR 146 YALEWUN KAL BEMESHAR AMELKALEHU TILALEH.ENERSUS BETAMMMMMMMMMMM TIKIKIL NACHEW.THEY R A REAL CHRISTIANS WHO FOLLOW GOD BASED ON BIBLE.ALTESASATACHIHUM KETLU.YEMIKEBEL YIKEBELAL LETIFAT KEN YETEMEDEBU AYKEBELEM.

   Delete
 5. Apocalpse8:3-8,The angle helps the saints to ascend their prayers from the hands of the Angel in the face of God..But you denied it.If this angel ascend the prayers,why not Saint May,why not saint Michel.
  Zekarias 1:12 the angle asks "why do you give your mercy for the cities of Jerusalem and Jude" God replays with humility.He returns to Jerusalem with His Pardon::
  I have practice this kind of praying whether you oppose or not,lule.Why are you afraid these evidences.We practice like these,this is the will of God.This means your explanation has big contradiction and it is teret teret

  ReplyDelete
 6. baewenate lebonathehun yadefanawe yamenafeke manefase madehaneyalam yegasetelathu sela bitakereseteyane asetamehero tathi lamahone komathu men yahele tamerathu yehun? wayese eneda lilothu eneda eni maradate belathu yehun yatereter manefas kawesetathu gabetual masetawalune yesetathu AMEN .

  ReplyDelete
 7. Even though I need somethings to be improved in our church, this site is very confused. You are really under heretic not following the Orthodox teachings.

  ReplyDelete
  Replies
  1. they only follow bible.which is right.

   Delete
 8. qale hiwet yasemalin lule

  ReplyDelete
 9. ቃለህይወት ያሰማልን። የእግዚአብሔርን ስራ ለሚቀሙ ፍርድ አለባቸው። በምድርም በሰማይም። እግዚአብሔር እውቀትን ካልገለጸ በስተቀር እውነቱ እንዳይገባ የልቡናቸው በር በተረት ተዘግቷል። መቅረዙን ይወስዳል። አትጠራጠሩ!!

  ReplyDelete
 10. Kebatari hula! Whoever is a true believer of Christ is called "adagne" as he/she has the medhanit in him/her. Also, whoever has Christ can do whatever Christ does and even more. Read the Bible - you liars and contaminators of the word of God. All true Christians and the Angels are adagnoch because of Christ's adagne power that is with them.

  So, what great adagne St. Mary is if any true believer can be called adagne. St. Mary is the very source of the ADAGNE AMLAK, Who is borne of her.

  Yes, we ask Sts. Mary and Michael to save us, protect us, and pray for us. Go to hell with your sandy heart. It cannot hold water and grow the true plant of God.

  I recommend that you listen to Aba Wolde-Tensae's sermon on the matter. However, I am afraid that sandy hearts would have difficulty understanding the truth.

  ReplyDelete
 11. ኧረ ለመሆኑ እናንተ እነማናችሁ የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ምእመናን ነጻ ለማውጣት የተሰለፋችሁ የምትመስሉ ፤ ማን የሚባል የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ነው በጥንቆላ ሥራ ተሰማርቶ አየነው የምትሉት እናንተ ራሳችሁ አስጠንቁላችሁ ወይስ ያስጠነቆሉት ነግረዋችሁ
  እመቤታችንን ድንግል ማርያምን አማልጂን ብለን እንጠይቃታለን እንጂ ወደሷ አንጸልይም ብልችኋል ፤ ታዲያ በትዕዛዝ ነው አማላጅነትዋን የመትጠይቁት ፤
  ስለ ድጓ ፥ ጾመ ድጓ፥ ስለ ዚቅ ፤ በአጠቃላይ ስለቤተ ክርስቲያናችን ዜማ የማትደረድሩት የነቀፋ ዓይነት የለም ። ታዲያ የናንተ የዜማ ዕውቀታችሁ ልክ ምን ያህል ይሆን ፤ እነዚህ የምትነቅፉዋቸው ሊቃውንት እዚህ የደረሱት እንደናንተ የገንዘብ ማግኛ አቋራጭ መንገድ ሳይፈልጉ መሆኑን ልብ እንድትሉ ያስፈልጋል ።
  የጳጳሳትን ምስል በብሎጋችሁ ራስጌ ደርድራችሁ ጳጳሳት ሚስት ያግቡ እያላችሁ ጵጵስናንና ሚስት ማግባትን በማጣመር ትመኛላችሁ ፤ ከዚህ ሁሉ ሰልፋችሁን ከሚመስሉዋችሁ ጋር አድርጉና ምኞታችሁን በዚያ በኩል መፈጸም ትችላላችሁ ። ቤተ ክርስቲያኑዋን ለቀቅ አድርጉዋት ፤ የሚሰማችሁ የለምና ።

  ReplyDelete
 12. WHAT ABOUT WODE NEGESTE , RAGUEL TELESEM , MESEF BARTOS ETC..... TO MUCH MAGIC BOOKS IN OUR CHURCH , THE CHURCH IS OUT OF APOSTOLIC TEACHING . This is happened by debtera, and behetawen are practicing it and some monks , priests and deacons. Guys ! be awake up ! devil is attacking this church by their servants, we have a chance to read holy bible. Jesus is the only way, truth and life ( john 14 : 6). No way becareful , nobody enter to heaven except through jesus christ.

  ReplyDelete
 13. Bebetecheristian seme yemetenegedu asemesay menafekoch nachu!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 14. sle Egziabher blachihu mejemeria yedogma sihtetochachihun armu!

  ReplyDelete
 15. Nathan, I can understand what you want to say on the last paragraph which you wrote "I recommend that you listen to Aba Wolde-Tensae's sermon on the matter. However, I am afraid that sandy hearts would have difficulty understanding the truth."

  ReplyDelete
 16. Tewahidowoci Neqtewal
  inkuwanis yemayireba sew ke afu yameletew irkus Qal Qerto Minim yemineqeniqacew yale ayimesilegnim. SILEZIH ATILIFU. MOKIRACIHUWAL GHIIIIIIN ALTESAKAM.

  ReplyDelete