Sunday, November 27, 2011

በአዲስ ኪዳን ጽላት እንዴት? - - - Read PDF


ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በዲያቆን ዓባይነህ ካሴ የተሰጠውና ስለጽላት የአዲስ ኪዳን ዘመን አስፈላጊነት ስብከቱ የተነሳ ነው። አባይነህ ካሴ ያልገለጻቸው፣ ያልመለሳቸውና ያላብራራቸው፣ ነገር ግን በምንም መልኩ ሊታለፉ የማይገባቸው ነጥቦች ስላሉ በዚህ ጽሁፍ ይዳሰሳሉ። ምክንያቱም ለክርስቲያኖች ከየትኛውም መረጃ በላይ የእምነታቸው መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ሲሆን እሱም ሳይሸፋፍን ለብሉይ ኪዳኑ ሥርዓትም ይሁን ለአዲስ ኪዳኑ ዘመን እምነት መመሪያን፣ትእዛዛቱንና መንገዶቹን በግልጽ አስቀምጦት ስለሚገኝ ነው።


   ዓባይነህ ካሴ ስሜቶቹን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እያዛመደ በዚህ የጽላት ዓለም እምነት ላሉ፣ በዚያው እንዲጸኑ፣ ይህንን ለማይቀበሉት ደግሞ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት የሁለት ወገን ስራውን ለመስራት ሞክሯል። ይሁን እንጂ መረጃውን በማብራሪያ ለማጠናከር ከመሞከር ባለፈ በተጨበጠ ማስረጃ ማስደገፍ ባለመቻሉ ግልጽ እውነቶችን እያነሳን ሥነ አመክንዮ «Give reasons or cite evidence in support of an idea, action, or theory, typically with the aim of persuading others to share one's view» እንሰጥበታለን።
   ታቦት ለእስራኤል ዘሥጋ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት
ነብዩ ሙሴ ከእግዚአብሔር ቃል እየተቀበለ ለሕዝቡ መልእክቱን ያደርስ ነበር። ዘጸ 315 እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው። ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
ዘጸ 18 15-16 ሙሴም አማቱን። ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው። እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
   ይህ ሙሴ ብቻውን ከእግዚአብሔር ቃል እየሰማ የሚያስተላልፈው መልእክት ከሕዝቡ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ስለሌለው፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን የኔ አምላክ ከማለት ይልቅ የሙሴ አምላክ ወደማለትና የሚሰጠውን ቃል ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ ያህል ገምቶ መጠራጠርን በመፍጠሩ የተነሳ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ያለውን ግንኙነት መግለጽ ስላለበት የመጣ ሕግ ነው።  ከሕዝቡ እንጉርጎሮዎች መካከልም እነዚህ ይጠቀሳሉ።
ዘጸ 1523 «ወደ ማራም በመጡ ጊዜ የማራ ውኃ መራራ ነበረና ሊጠጡ አልቻሉም ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም ማራ ተብሎ ተጠራ»ዘጸ 163 «እስራኤልም ልጆች። ይህን ጉባኤ ሁሉ በራብ ልትገድሉ እኛን ወደዚች ምድረ በዳ አውጥታችኋል በሥጋው ምንቸት አጠገብ ተቀምጠን እንጀራ ስንበላ ስንጠግብ ሳለን በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን! አሉአቸው
   ዘጸ 172 «ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት። የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው»ዘጸ 177 «ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር። እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው»
   ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ባለመቻሉ ማንጎራጎር ፣መጠራጠርና ረጅሙን የእግዚአብሔር ዓላማ ለመረዳት ባለመቻላቸው እየመራቸው ያለው እግዚአብሔር መሆኑን እንዲያውቁ ከፊት ፊት መሪ ምልክት መስጠት አስፈልጓል። ለዚህም ሲባል ለሙሴ የሚመጣውን ድምጽ እነሱም እንዲሰሙ በማስፈለጉና ከማንጎራጎር ይልቅ ቃሉ የእግዚአብሔር እንደሆነ ራሳቸው አምነው እንዲቀበሉ እግዚአብሔር በመካከላቸው እንደሆነ እንዲረዱና እግዚአብሔር ርስት ምድርን የማውረስ ቃሉን ስለመጠበቁ፣ ሕዝቡም የእግዚአብሔር ሕዝብ መሆኑን ለመቀበል ቃል ኪዳንና የክብሩ መገለጫ ጽላት መስጠት እግዚአብሔር መርጧል።
   ይህ ሥርዓት የተሰጣቸው ከግብጽ ምድር ከወጡ ከሦስት ወር በኋላ ነው። ዘጸ 191 «በሦስተኛውም ወር የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በዚያ ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ»ስለጽላቱ አሰራር ወደኋላ ላይ የምንመጣበት ሆኖ በምክንያቱ ላይ አትኩሮታችንን ስናደርግ ሙሴ በእግዚአብሔር ጥሪ ሲና ተራራ ላይ ወጥቶ እስኪመለስ ድረስ ችኩል ሕዝብ ድምጽ ያመጣላቸው የነበረው ሰው ነብዩ ሙሴ ከፊታቸው በመጥፋቱ ምክንያት በቀደመው ዐመጻቸው ማስቸገራቸው አልቀረም።
    ዘጸ 321 «ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው። ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉት»ጣዖት ሰሩ፣አመለኩ። ሙሴም ሲመለስ የዘፈን ድምጽ ሰማ፣ጽላቶቹንም በጣዖቱ ላይ ሰበረ።         የመጀመሪያው ጽላት መሰበር
1/ የሕዝቡን የጣዖት ልብ የሚሰብር
2/
ከህዝቡ ዐመጸኞችን የሚሰብር
3/
ሕዝቡ ከእግዚአብሔር የራቀበትን ድልድይ የሚሰብር ነበር።
ይህም በእነዚህ ጥቅሶች ታይቷል።
   ዘጸ 3227 «ርሱም፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእናንተ ሰው ሁሉ ሰይፉን በወገቡ ላይ ይታጠቅ፥ በሰፈሩም ውስጥ በዚህና በዚያ ከበር እስከ በር ተመላለሱ፥ የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም ይግደል አላቸው»
    ዘጸ 336 «የእስራኤልም ልጆች ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ጌጣቸውን አወጡ»ዘጸ 338 «ሙሴም ወደ ድንኳኑ በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይነሡ ነበር፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ ይቆም ነበር፥ ሙሴም ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር»
   እግዚአብሔር ለሙሴ ጽላቱን ከሰጠ በኋላ እንደሥርዓቱ መደረግ የሚገባውን ሁሉ እያደረገና እያስደረገ ሕዝቡን ወደርስት ምድር ይመራ ነበር። ሙሴ የእግዚአብሔርን ቃል ለመቀበል የትም መሄድ አያስፈልገውም። ሕዝቡም ሙሴ፣ ሄደ-መጣ እያለ በመለያየት ሃሳብ አልኖረም። ይልቁንም ሙሴ ብቻ ይሰማ የነበረውን ድምጽ በቀጥታ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እያየ እንዲቀበልና እንዲፈጽመው ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ክብር ማየት የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህንንም ይህ ቃል ይነግረናል።
   ዘጸ 338-10 «ሙሴም ወደ ድንኳኑ በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይነሡ ነበር፥ እያንዳንዱም በድንኳኑ ደጃፍ ይቆም ነበር፥ ሙሴም ወደ ድንኳኑ እስኪገባ ድረስ ይመለከቱት ነበር። ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር። ሕዝቡም ሁሉ የደመናው ዓምድ በድንኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር»
  አሁን በሙሴና በእግዚአብሔር፣ በሙሴና በሕዝቡ መካከል ያለው የግንኙነት መስመር በቃልኪዳኑ ታቦት በኩል እየተከናወነ መገኘቱን እናያለን። ሕዝቡ ከዚህ ግንኙነት በኃጢአት ሲከለከል ራሱን የሚያድስበት የመንጻት መንገዱን ይጠቀማል።  የሚጓዙትም በመገኛው ድንኳን ያረፈው ደመና ሲነሳ፤ የሚያነጋግራቸውም በመገኛው ድንኳን የእግዚአብሔር ደመና ሲያርፍ ነበር።
ዘጸ 4035 ደመናውም በላዩ ስለ ነበረ የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ስለ ሞላ ሙሴ ወደ መገናኛው ድንኳን ይገባ ዘንድ አልቻለም።
ዘጸ4036 ደመናውም ከማደሪያው በተነሣ ጊዜ የእስራኤል ልጆች በመንገዳቸው ሁሉ ይጓዙ ነበር።
   ኦሪት ዘፍጥረት የስነፍጥረትን መነሻና ከስነፍጥረት የሰውልጅ ታሪክ ውስጥ የእስራኤል ዘሥጋ መመረጥ፣ኦሪት ዘጸአት ዐመጻንና የዐመጻን ልብ በመሻርና በመምራት ለእስራኤል ዘሥጋ የቃል ኪዳን ጽላት መስጠት፣ ኦሪት ዘሌዋውያን ቃልኪዳኑ የሚጠበቅበትን ሥርዓት የማሳወቅ ሕግ መሆኑን እንመለከታለን።
እንግዲህ ጽላቱ ለእግዚአብሔር ሕዝብ መስጠት ያስፈለገው እግዚአብሔር ቃሉን ስሰጥ የሚገለጽበት፣ ሙሴም ሕዝቡም ትእዛዙን የሚሰሙበት ሲሆን ሙሴ መካከለኛ ድልድይ ሆኖ ህዝቡን ከእግዚአብሔር፣ እግዚአብሔርን ከህዝቡ የሚያገናኝና ከምድራዊዋ ርስት የሚያደርስ ነብይ ነበር።
የጽላቱና የታቦቱ ሥርዓት ምን ይመስላል?
    የጽላቱን ዓላማ ከላይ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ለማየት ሞክረናል። አሰራሩስ የሚለውን ደግሞ ለቀጣይ ሃሳቦቻችን ማጠናከሪያ በአጭር በአጭሩ ለማየት እንሞክራለን።
 
    የመጀመሪያዎቹን የእግዚአብሔር ጽላት ሙሴ ከሰበራቸው በኋላ ዳግመኛ እርሱ ራሱ ቀርጾ ወደ ሲና ተራራ ይዞ እንዲወጣ ተነግሮታል።
ታቦቱ( ማኅደሩ)ርዝመቱ 2 ክንድ ተኩል፣ ወርዱ 1 ክንድ ተኩል፣ ከፍታው 1 ክንድ ተኩል ከግራር እንጨት የተሰራ ነበር። (ዘጸ 2510)ውስጡና ውጪውም በንጹህ ወርቅ የተለበጠ ነው። 4 የወርቅ ቀለበቶች የተንጠለጠሉበትና 2 መሎጊያዎች ለመሸከሚያ የሚሆኑ በወርቅ የተለበጡት ግራና ቀን ነበሩ።  የታቦቱ መክደኛ 2 ክንድ ተኩል ርዝመት፣ 1 ክንድ ተኩል ወርድ የሆነ ሲሆን፣ ዳርና ዳር ከወርቅ የተሰሩ ኪሩቦች እንደሚናተፍ አውራ ዶሮ ፊት ለፊት አተያይቶ እንዲሰራ ተደርጓል።
   የህብስቱን ማስቀመጫ(ዘጸ2523) የመብራቱን መቅረዝ (ዘጸ 2532) የማደሪያውን ድንኳን (ዘጸ 2526)የሚቃጠል መስዋእት ማቅረቢያ (ዘጸ 271) የመቅረዙ ዘይት (ዘጸ 2720) ኤፉድ (ዘጸ 2815) የዕጣን መሠዊያ (ዘጸ 301) የመታጠቢያ ሰን ወዘተ ለታቦቱ ሥርዓት የግዴታ ሕጎች ሁሉ ተሰርተዋል። እነዚህን ለማሳያ ያህል ጠቀስናቸው እንጂ ከታቦቱ ሥርዓት ጋር የሚደረጉት ሕጎች እነዚህ ብቻ አይደሉም።
   እንግዲህ ሙሴ ቀርጾ ወደተራራው ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር በጣቱ በጽላቶች ላይ 10ቱን ትእዛዛት ጽፎ እንደሰጠውና (ዘዳ104) ከዚያም በታዘዘው መሰረት እየፈጸመ ወደርስት ምድር እንደመራቸው እንረዳለን።
በአጭሩ ካስቀመጥናቸው ኦሪታዊው ሕግና ሥርዓት አንጻር በመግቢያችን ላይ እንዳመለከትነው ዲያቆን ዓባይነህ ካሴ ወዳስተማራቸው የአዲስ ኪዳን ታቦትና ጽላት ጉዳዮች የምናነሳቸው ተጨባጭ ነጥቦች ከታች የተቀመጡት ናቸው።
1/ የኦሪቱ ታቦትና ጽላት ወደአዲስ ኪዳን ተሻግሯል የሚለን ከሆነ የአዲስ ኪዳኑ ታቦት ወርድ፣ ቁመት፣ርዝመት የኦሪቱን የጠበቀ ነው ወይ?
2/ቀለበቶቹ፤ መሎጊያዎቹ፣ ኪሩቦቹ፣ የስርየት መክደኛው ወዘተ ሁሉ አሁን አሉ? የካህናቱ ኤፉድ፤መጋረጃ፤የመቅደሱ የወርቅ ሳህኖች ዋንጫዎች ሁሉ እንደዚያው እንደጥንቱ ነው?
 
3/ጽላቶቹን በተመከተ ሙሴ ከእብነ በረድ ቀርጾ ወደተራራው ወጥቶ እግዚአብሔር እንደጻፈባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ከሚናገር ውጪ ሙሴ ጻፈባቸው አይልም። ዛሬስ ከእብነበረድ እየጻፋችሁ ሲና ሄዳችሁ ወይም እግዚአብሔር የሚጽፍበት የሰራችሁት ሲና ኖሮ እዚያ እየሄዳችሁ ነው የምታስጽፉት?
4/ የሙሴን ጽላቶች እግዚአብሔር ጽፎባቸው የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ጽላቶች ተብለዋል። የዛሬውን ማን ጽፎባቸው ነው የቃልኪዳን ታቦት የሚባሉት? ማን ከማን ጋር የገባበት ኪዳን ነው?
5/ሙሴ እንዲቀርጽ የተነገረው ሁለት ጽላት ብቻ ነበር። እግዚአብሔርም የሰጠው ሁለቱን ብቻ ነው። 12 ነገደ እስራኤል ርስት ምድራቸው ከገቡ በኋላ ያመልኩ የነበረው በማዕከል ባለው የእግዚአብሔር ኪዳን ላይ ብቻ ነው። ለምን 12 ነገደ እስራኤል ከድካምና ከጉዞ እንዲያርፉ እግዚአብሔር ብዙ ጽላትን አልፈቀደም? የዛሬውስ ስራ የኦሪቱን ይከተላል ከተባለ ለምን ኦሪቱ ሲሰራባቸው ከነበረውና ሙሴ ከተቀበለው ተላልፎ በሺዎች የሚቆጠር ሆነ?
6/የሙሴን ሥርዓት ተረክበናል ካልክ የሙሴን የመቅደስ ሥርዓት አለመጠበቅህ መሻርህን አያሳይም?
7/ በኦሪቱ የስርየት መክደኛ ላይ የእግዚአብሔር ክብር ከመገለጹ በፊት ደመናው በዓምዱ ላይ ሲወርድ ሕዝቡ ሁሉ ያይ ነበር። ዛሬስ ህዝቡ እንደያኔው ያያል?
8/
ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ሊቀካህናቱ በዓመት አንድ ቀን ለራሱም ሆነ ለሕዝቡ መስዋእት አድርጎ ይገባ ነበር። ዛሬስ ይህ ሥርዓት በታቦታችሁ ላይ ይደረጋል?
9/እግዚአብሔር 10ቱን ትዕዛዛት በጽላቶቹ ላይ መጻፉን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። የሙሴን የጽላት ስርዓት ተከትለናል ካልክ ሙሴ ያላደረገውን 10ቱን ትዕዛዛት ሽረህ የራስህን ፈቃድ ስእልና ስም ዛሬ የምትቀርጸው ለምንድነው? ለቅዱሳን መታሰቢያ በጽላት ቀረጻ አድርጉ የሚል ትእዛዝ ከየት መጽሐፍ የተገኘ ነው? ፍጡርና ፈጣሪ በአንድ ሰሌዳ(ጽሌ) ላይ እንዴት ይከብራሉ? ኦሪት ያንን አሳይታለች?
10/ አክሱም አለች የምትባለው ጽላተ ሙሴ የሰሎሞን ቤተመቅደሷ ጽላት ከሆነች እንዴት እርሷ የነበራትን ስርዓት የጣሰ የጽላት ቀረጻ በመላ ኢትዮጵያ ይከናወናል?
11/ በአንድ በኩል ክርስቶስ ሕግና ነብያትን ለመሻር አልመጣሁም ብላችሁ ስታስተምሩ በሌላ በኩል ደግሞ የኦሪቱን የታቦት ሕግ የሻረ ስርዓት ለምን ትሰራላችሁ?
ማጠቃለያ፣
   ዲያቆን ዓባይነህም ሆነ ማኅበሩ የእግዚአብሔርን ቃል ወደልባቸው መሻት ለማጣመም የተልዕኰ ሰዎች ይመስሉኛል። ትንሽ የቃል ሽታ ያላቸውን ደጋፊ ጥቅሶችን ፈልጎ በመልቀም መዓዛ ያለው ዘይት ጨምቆ ለማውጣትና እንዲያሸቷቸው የማይቆፍሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ገጽ የለም። እውነቱ ግን አፍጥጦ ይታያል፣ የኦሪቱን የታቦት ሥርዓት ሽራችሁት ፣የራሳችሁን ስርዓት ተክላችኋል ፣ያም የሚመዘነው በመጽሐፍ ቅዱሱ የሥርዓት ሕግ ነው።
በሰውና በእግዚአብሔር መካከል አስታራቂና አገናኝ የነበረው የእስራኤል ዘሥጋ ነብይ ሙሴ ነበር።
  የእስራኤል ዘነፍስ አስታራቂና መካከለኛ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሙሴ ቃሉን ከእግዚአብሔር እየተቀበለ ለሕዝቡ ያደርስ ነበር። ኢየሱስ ግን ለህዝቡ የደረሰ ራሱ እግዚአብሔር ቃል ነው። ሙሴ ከርስት ምድር ውጭ ሞቶ ተቀበረ። ኢየሱስም ከቅድስቲቱ ከተማ ውጭ ሞቶ ተቀበረ። ሙሴ የተቀበረበትን እስራኤል ዘሥጋ አላወቀም። እስራኤል ዘነፍስ ሞቶ ያልቀረውና በአብ ቀኝ የተቀመጠውን ነቢይ ያመልካል። ቃሉን የሚሰሙበትና ክብሩን የሚገልጽበት የታቦት ኪዳን እስራኤል ዘሥጋ ተሰጠው። ቃሉን ራሱ የሚሰጥና ክብሩንም በሞቱ ለሕዝቦቹ የገለጸ ሰማያዊ ጽላት ኢየሱስ ነው።
 
ዘዳ 1818 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ ቃሌንም በአፉ አደርጋለሁ፥ ያዘዝሁትንም ቃል ሁሉ ይነግራቸዋል 2 ቆሮ 33 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
የኦሪቱን የታቦት ሥርዓት ሳይጠብቁ ሙሴን የውሸታቸው ምስክር አድርገው የሚጠሩ ሰዎች ምን ይባላሉ?እግዚአብሔር ፍርዱን ያሳይ!! ከምንል ሌላ የምንለው የለም።
ሊላይ

34 comments:

 1. Mulugeta-lelay
  I think protestant does not have Teslat. so,why don't you go there? We need it today and tomorrow.
  This is not MK's teaching.its our church teaching.I know Mk is a code word for you to describe our church. our church teaching. you are trying to feed us pente teaching. go to their hall.

  ReplyDelete
 2. አባይነህ ካሴ የተባለ የቀድሞ የቡድኑ አመራር ከሊቃውንት ገልብጦ በጻፈው ጽሑፍ ሲገለብጥ ተሳስቶ ይሁን ወይም በራሴ አብራራለሁ ሲል // የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ብሎ ባሳተመውና ብዙ በነገደበት መጽሐፍ የሚከተሉትን ጽፏል
  • ገጽ 124 // 2.4.2// ከየት እንዳመጣው አይታወቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግነት ይጠቀማል ብሎ ተናግሯል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ቅዱሳን የጻፉትን መጽሐፍ አጋናኝ ብሎ መሳደብ ምን ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አጋናኝ ካለ ገድላትንና ድርሳናትን፣ ተአምራትን ምን ሊላቸው ነው፡፡ ምሳሌው ደግሞ በገጽ 125 ከጩኸታቸው የተነሳ ምድር ተናወጠች የሚለው ተጋነነ አቀራረብ ነው እንጅ ምድር አልተናወጣችም ይለናል፡፡
  • በገጽ 217 ደግሞ ይባሰ ምን ይላል መሰላችሁ /// ነፍስ አትጾምም /// የሚጾም ስጋ ነው ዳዊት ነፍሴን በጾም አደከምኳት ሲል ስለ ስጋው ነውእንጅ ነፍስ አትጾምም ብሎ የክፋት ትርጎም ያስተምራል
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዳለ ገልብጦ ከጻፈው ምእራፍ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ትውፊት ሳይረዳና ምንጩን የማን እንደሆነ ሳይጠይቅ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው ብሉ አስከፊ ስህተትን ምናልባትም ከእነሱ ቡድን ውጭ መዋጮ የማይከፍል ወይም አብሮ የማይነግድ ነው ቢሳሳተው ኖሮ እስከ አሁን ተሐድሶ መናፍቅ ተብሎ ነበር፡፡
  ገና ይቀጥላል ይህ እንደው ገለጥ ገለጥ ተድርጎ በማየት የተገኘ ስህተት ነው፡፡ ሊቀውንት ቁጭ ብለው ቢመረምሩትማ ምን ያህል ስህተት ይገኝ ይሆን በእኛ አቅም እንኳ ይህን ያህል ከተገኘ፡፡
  ጎበዝ አሁን እንግዲህ // ዲን አባይነህ ካሴን // ምን እንበለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያጋናል፣ ነፍስ አትጦምም፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆን ነው ብሏል፡፡ እኛ እንደእነሱ ባለጌአይደለንም ሲኖዶስ ይፈረድበት፡፡
  አንድ አጭር መልእክት ትናንት የደረሰኝ አባይነህ ካሴ የተባለ የቀድሞ የቡድኑ አመራር ከሊቃውንት ገልብጦ በጻፈው ጽሑፍ ሲገለብጥ ተሳስቶ ይሁን ወይም በራሴ አብራራለሁ ሲል // የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ብሎ ባሳተመውና ብዙ በነገደበት መጽሐፍ የሚከተሉትን ጽፏል
  • ገጽ 124 // 2.4.2// ከየት እንዳመጣው አይታወቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግነት ይጠቀማል ብሎ ተናግሯል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ቅዱሳን የጻፉትን መጽሐፍ አጋናኝ ብሎ መሳደብ ምን ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አጋናኝ ካለ ገድላትንና ድርሳናትን፣ ተአምራትን ምን ሊላቸው ነው፡፡ ምሳሌው ደግሞ በገጽ 125 ከጩኸታቸው የተነሳ ምድር ተናወጠች የሚለው ተጋነነ አቀራረብ ነው እንጅ ምድር አልተናወጣችም ይለናል፡፡
  • በገጽ 217 ደግሞ ይባሰ ምን ይላል መሰላችሁ /// ነፍስ አትጾምም /// የሚጾም ስጋ ነው ዳዊት ነፍሴን በጾም አደከምኳት ሲል ስለ ስጋው ነውእንጅ ነፍስ አትጾምም ብሎ የክፋት ትርጎም ያስተምራል
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዳለ ገልብጦ ከጻፈው ምእራፍ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ትውፊት ሳይረዳና ምንጩን የማን እንደሆነ ሳይጠይቅ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው ብሉ አስከፊ ስህተትን ምናልባትም ከእነሱ ቡድን ውጭ መዋጮ የማይከፍል ወይም አብሮ የማይነግድ ነው ቢሳሳተው ኖሮ እስከ አሁን ተሐድሶ መናፍቅ ተብሎ ነበር፡፡
  ገና ይቀጥላል ይህ እንደው ገለጥ ገለጥ ተድርጎ በማየት የተገኘ ስህተት ነው፡፡ ሊቀውንት ቁጭ ብለው ቢመረምሩትማ ምን ያህል ስህተት ይገኝ ይሆን በእኛ አቅም እንኳ ይህን ያህል ከተገኘ፡፡
  ጎበዝ አሁን እንግዲህ // ዲን አባይነህ ካሴን // ምን እንበለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያጋናል፣ ነፍስ አትጦምም፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆን ነው ብሏል፡፡ እኛ እንደእነሱ ባለጌአይደለንም ሲኖዶስ ይፈረድበት፡፡

  ReplyDelete
 3. ራእይ 19:11 ጽላቱ በሰማይ በቅዱስ ዮሐንስ የታየው በሰማይ በልብ ጽላት የተቀረጸ የክርስቶስ መልእክት የክርስቶስ መንፈስ ስለለ ይሆን ወንድም?አይደለም አስተውል።በሰማይ ጽላት ካለማ በምድር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጽላቶች ያስፈልጉን ነበር።
  ማተ23:1-3 ...በሙሰ ወንበር ጠቀምጠዋል።ይልብሃል ስለዚህ በሙሰ ወንበር የተቀመጡ አባቶች እንደ ሙሰ ጽላት መቅረጽ ይችላሉ።ያሠራሩን ሁለታ አባቶች በእግዚአብሐር ፈቃድ መለወጥ ይችላሉ።ዋናው የክርስቶስ ስም አለበት።እንዲያዉም ከብሉይ ጽላት የሐዲሱ የክርስቶስ ስም ስለተገለጠ ስለሚጻፍበት እጅግ የከበረ ነው።አስርቱ ትእዛዛትም በአጭሩ ይጻፉበታል።ቅ ጳውሎስ እንዳለው ጉልበት ሁሉ ለክርስቶስ ይንበርከክ ባለን መሰረት በክርስቶስ ስም ለከበረው ጽላት ተንበርክከን እንሰግዳለን።አንተ በክንቱ ደከምክ እንጂ እዉነተኛ የተዋሕዶ አማኝ አይቀበልህም

  ReplyDelete
  Replies
  1. በሰው እጅ ሊጻፍበት?ተው ቀልድ ይቅር? እቃቃ አስመሰላችሁት::

   Delete
 4. 'እስራኤል ዘነፍስ ሞቶ ያልቀረውና በአብ ቀኝ የተቀመጠውን ነቢይ ያመልካል'። ምን ማለት ነው? የኛ አምላክ የነቢያት አስገኝ የነቢያት ፈጣሪ የነቢያት ጌታ ነው።ይኸ የእስማኤል ወገኖች ኣባባል እንጂ የሌላ አይደለም።አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? እባክህን የጥፋት ልጅ መሆንህን ስላወቅንህ አትድከም። ለእውነት ነው እንደዚህ የተንገበገብከው? አስመሳይ።

  ReplyDelete
 5. is there anyone who can tell me why the copt (egypt) orthodox are not accepting/using tabot ?

  ReplyDelete
 6. hoo endet new negeru yihe blog ye menafekan new endee ere gudd??

  ReplyDelete
 7. ኢየሱስ ነቢይ፤ ሊቀካህንና የነገሥታት ንጉስ ነው።
  ስለነቢይነቱ አንተ እንደዘመዶቹ አይሁዳውያን ስለማታከብረው ራሱ እንዲህ ይልብሃል። ማቴ13፥57 ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። የኢየሱስ ነቢይነት እንደኦሪቱ ነቢያት በሞት የማይሸነፍ ሰማያዊ ነው።
  ዮሐ6፥14 ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ። ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።
  ኢየሱስ ሊቀካህናት ነው።ዕብ 8፤1 ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤
  ኢየሱስ የነገሥታት ንጉስ ነው። ራእ 17፣14 እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፥ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።
  1/ኢየሱስ ከነቢይም ነቢይ የሚያሰኘው- ትምህርት፣ ትእምርትና ትንቢት የፈጸመው እንደኦሪቱ ነቢያት ከሌላ እየሰማ ሳይሆን ራሱ ቃል እግዚአብሔር በመሆኑ የነቢይነት ፍጻሜ ነው።
  2/ኢየሱስ ሊቀካህናት የተባለው- እንደኦሪቱ ሊቀካህን ለራሱና ለሕዝቡ የበግ መስዋእት ለማቅረብ በበጎች ማጠቢያ (ቤተሳይዳ) ምንጭ በጎችን እያጠበ ደም የሚያፈስና ለዚያውም ሁልጊዜ ይህንን ለማድረግ እንደሚደክመው ሊቀካህን ሳይሆን ራሱ ንጹህና ቅዱስ ለዚያውም ከሰማይ የወረደ በግ፣ ደግሞም አንዴ ታርዶ ያመነውን ሁሉ ለዘለዓለም የሚያነጻ ሲሆን የኦሪቱ ሊቀካህን ግን ለህዝቡ ራሱ መታረድ ስለማይችልና እታረዳለሁም ቢል ሞትን ስለማያሸንፍ ከሱ ሌላ በግ እንደሚያስፈልገው ዓይነት አይደለም የኢየሱስ ሊቀካህናትነት። እሱ ራሱ ሊቀካህን ሆኖ፣ ለህዝቡ የታረደ በግ፣ከመሆኑም በላይ ሞትን ያሸነፈ፣ በዚህ በግ የታመኑ ሁሉ የሞት መውጊያን ሰብሮ በሰማይ ለተከተሉት በአባቱ ቤት መኖሪያን ያዘጋጀ ሊቀካህናት ነው። ኢየሱስ የሊቀካህናት መጨረሻና ፍጹም ማጠቃለያ ነው።


  ጥቅሱን አላነሳም። በጥቅሉ በሰማይ ስላለው የኪዳኑ ታቦት በራእይ መጽሐፍ ላይ ዓባይነህም ሆነ እዚህ ብሎግ ላይ አስተያየት በመስጠት የምድሪቷም ያንን ትመስላለች ለማለት ፈልገዋል?
  1/ በሰማይ በእግዚአብሔር መቅደስ ያለችው የኪዳኑ ታቦት ምን ትመስላለች?
  2/ የሰማያዊቷን ታቦት አምሳያ ነው እናንተ አሁን የምታመልኩት? አዎ በሉና ክህደታችሁን ግልጽ አውጡት። (እኔ ግን ሎቱ ስብሐት እላለሁ) ያለእርሱ ያንን የሚያውቅ የለምና።
  የምድሪቷን ግን ልነግራችሁ እችላለሁ። ምድራዊቷን ጽላት ከጠቅላይ ቤተክህነት ቅርሳቅርስ መምሪያ 600 ብር በሞዴል 30 እንደሚሸጥ አውቃለሁ። ምናልባት የኑሮው ውድነት ዛሬ ስለጨመረ የሷም ዋጋ ጨምሮ ሊሆን ይችላል። ለማረጋገጥ ሄዶ መጠየቅ እውነታውን ያረጋግጥላችኋል። ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከወሎና የሚሰረቁትንና ከአንዱ ደባል ጽላት ወደሌላ ቦታ የሚዘዋወረውን ሳይጨምር ማለት ነው። በየጓሮው እነመሪ፤ እንደደብተራ እየቀረጹ የሚሸጡትንም ሳያካትት ነው። ሲፈልግ ከግራር፣ ሲፈልግ ከዋንዛ፣ ሲያሻውም ከጥድ ካገኘም ከኮሶ እንጨት እየቀረጸ የሚቸበቸውን በራእይ ታየ ከተባለው ጋር ለማመሳሰል መሞከር ክህደት ብቻ ሳይሆን ሰይጣን የእግዚአብሔር ክብር ለማቃለል ምን ያህል እየሰራ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ሳጠቃልል አንድ ጥያቄ ላንሳ የሰማይና የምድር ንጉሥ ክርስቶስ እንኳን በ30 ብር ነው ነው የተሸጠው፣ እናንተ እነማን ሆናችሁ ነው በ600 ብርና ከዚያ በላይ ጽላቱን የምትሸጡት?

  ReplyDelete
 8. ኣባ ሰላማወች የእናንተን ማንነት ለማወቅ ተችግረናል። እነማን ናችሁ? ጴንጤ? ወይስ ተሐድሶ? እራሳችሁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ለማስመሰል ክብሎጋችሁ እራስጌ ላይ የብፁአን አባቶችን ፎቶወች ለጥፋችሁ ወርቃማ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንደነበሩም መስክራችኋል።
  ለመሆኑ እነዚህ አባቶች፡
  1. ገድላትንና ድርሳናትን ይተቹ ነበር?
  2.ቅዱሳን፡እመቤታችን ቅ.መላ እክትን ነቢያትን ሐዋርያትን ጻድቃን ሰማ እታትን አያማልዱም ይሉ ነበር?
  3.ታቦት ወይም ጽላት አያስፈልግም ይሉ ነበር ወይ?
  እናንተ እንደምትሉት እነዚህ አባቶች ከእናንተ እምነት እና ሐሳብ ጋር በፍጽም አይገናኙም።
  ዝም ብላችሁ ስማቸውን አታጥፉ።

  ReplyDelete
 9. ግብጾች እንደ ኢትዮጵያዉያን በብሉይ ዘመን ብሉይ ኪዳንን ስላልተቀበሉ የጽላትና የታቦት ሥርዓት ስላልተቀበሉት አሁን በጽላት ፈንታ(ሥፍራ) የቅዱሳንን አጽም በመጠቀም ቅዳሰ ይቀድሳሉ።ያልነበሩበት ስለሆነ እንጂ አያስፈልግም አላሉም።ትክክል ባይሆን ኖሮ 1600 ዓመታት በእነርሱ ሥር ስንኖር አጥፉት ይሉ ነበር።ስለዚህ በዚህ እኛ ለየት ያለ፡ጥንታዊ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓቱን ጠብቀን እንገኛለን።በተ ክህነት 600 ብር ተቀብሎ ለአዲስ ህንጻ በተ ክርስቲያን ጽላት ይሰጣል።ይህንን ትንሽ ግንዘብ ማስከፈላቸው ምንም አያስገርምም።ምክንያታቸውንም እናውቀዋለን እንቀበለዋለን።አስፈላጊም ነው።አንተ ባይገባህም። የአንተ ዘመዶች(ፕሮተስታንቶች) ግን አታለው 60000፣100000 ብር ከዚህም በላይ እየገዙ የሚወስዱት የሚሰርቁት ለምን ይመስለሃል።ዋጋ እንዳለው እኮ ዘመዶችህን ጠይቃቸው ይነግሩሃል።ብቻ የሰማዩን ታቦት ፎቶ ኮፒ ነው አላልንም።ግን አስፈላጊነቱን ካመክ መኖሩን ማመንህም ትልቅ ነገር ነው።

  ReplyDelete
 10. ነጭ ውሸት!! ይላል ያገሬ ሰው ትንሽ እንኳን የተቀላቀለ እውነት ሲያጣበት። ግብጾች የማንን አጽም ነው የሚጠቀሙት? በዴር ማር አንቶንዮስ ነው ወይስ በዴር ማር ባውሎስ(በእነሱ ፓ እና ጳ) የለም፤ በካይሮው ዴር ዋዲ አል ናትራን ነው ወይስ ሶሃግ በሚገኘው ዴር ኤል አቢያድ? ወይስ ለክሰር ባለው አንቶንዮስ ገዳም?
  በውሸት ጀምረህ በውሸት ለመጨረስ ካልሆነ በስተቀር በነዚህና በሌሎቹም ገዳማትና አድባራት የሰው አጥንት ብሎ ነገር የለም። የማርቆስ ወንጌላዊ ሀገረ ስብከት ሀገረ ኮፕት
  ባይገርህ ጽላት ብሎ ነገር የላትም። የሚቀድሱት በክር ጥልፍ በተሰራ የክርስቶስ ምስል ያለበት ጨርቅ ላይ ነው። ዛሬም አንተ የምታወራው አጥንት የለም። ከቅዳሴ በኋላም አንተ በሀገርህ ላይ መቅደስ ያረክሳሉ የምትላቸው ሴቶች ገብተው ማጽዳት ይችላሉ። በሀገርህ ለቄሶች ብቻ የተባለው ተረፈ መስዋእት ሴቶቹ መቀበል ይችላሉ። 5 ኪሎ ቅድስት ማርያም ሲቀድሱ ሂድና ግብጾቹን ጠይቃቸውና ውሸት ከሆነ አረጋግጥ።1600 ዘመን ሲመሩን ሳይሆን ሲገዙን( ወርቁንና ብሩን እየጫንን) ቋንቋ የሚያውቅ፣ የማይሰብክ ሲብስም የሚመጣ ጠፍቶ ለማእረገ ዲቁና ኦክሲጅን በስልቻ መንፈስ ቅዱስ ነው እያሉ የሚልኩልንን ቁም ነገር ቆጥረኸው ነው?
  አረቦቹ ጽላትን በጣም እንደሚፈልጉት አውቃለሁ። ምክንያቱም ለአስማት ስራ በጣም አስፈላጊና በሱ ከተቀራበት ይሰምራል ይላሉ። ፈረንጆቹ ኢትዮጵያውያን የሚሰግዱበት ጽላት እያሉ በሙዚየማቸው ለማስጎብኘት ነው። 130 ዓመት ከለንደን ሙዚየም በጎብኚዎች ገቢ ስታመጣ የነበረችውና ከ4 ና 5 ዓመት በፊት ቅድስት ሥላሴ የገባችውን ዓይነት ማለት ነው። እንደነመምሩ ፕሮቴስታንቶች ጽላት ይሰርቃሉ አልሰማሁም። ባይሆን ይዘላሉ፤ ይደንሳሉ፣ ቋንቋ ነው ብለው ይለፈልፋሉ ነው። እንዲህ ካደረጉ የላሊበላ ጽላት ተሰርቆ ያወጣውን ዋጋ አይተው እነሱም እነመምሩን ሆነዋል ማለት ነው።
  ደግሞ 600 ብር አዲስ ጽላት ለአዲስ ቤተክርስቲያን ብንገዛ ምን ያስገርማል ነው ያልከው? በእርግጥ አያስገርምም፣ ግን ሙሴ በ600 ሰቅል የገዛ ይመስል እኛም እንደሙሴ እያደረግን ነው አትበል!! ብታምንም ባታምንም ኦርቶዶክስ ሃይማኖታዊ መሠረቷ እንደእንግዳ ደራሽ፣ እንደጎርፍ ፈሳሽ አይደለም። መሠረቷ ንጹህ፣ አስተምህሮዋ የጠራ ነበር። ዳሩ ምና ያደርጋል፣ ቀሳውስቱ ዝክርና ፍታት ሲቃርሙ ህዝቡን ወንጌል የሚያስተምር ጠፍቶ ባእድ አምልኮውን ከሃይማኖት ጋር እያቀላቀለ እስከዛሬ አለ፣ ደብተራ ገለፈት የቤተመንግሥት ጠጅ እየለበለበ ነገስታቱን ሲያወድስ፣ ቅኔና መልካ መልክእ ሲጨነቁርና ሲጠነቁል ጴንጤ እስኪመጣ ድረስ መጽሐፍ ቅዱስ እቃ ግምጃ ቤት ተቀመጠ። አፄ ቴዎድሮስ ካህናቱ ተቀምጦ ከበዓታ እስከበዓታ እያስደገሰ ሲበላና ባህር ተሻግሮ ወንጌል የሚሰብክ ሲመጣባቸው በሰሞን 5 ካህን ይበቃል፣ሌላው ስራ ይስራ፣ ወንጌል ያስተምር ቢሉ በስጋ ወደሙ መርዝ ነስንሰው ሊገድሏቸው እንደነበር ይታወቃል። ካህኑን ያኔ ስለፈጁትና ራሳቸውን በራሳቸው ለሀገራቸው የሞቱ ዋጋ አጥቶ ስማቸው በፍታት እንዳይጠራ ተደርጓል።
  በይበልጥም አፍንጫና ጆሮ ከቆረጠው የክርስቶስ ወዳጅ ተብሎ ከሚወራለት ከዘርዓ ያዕቆብ ወዲህ ወንጌል ሞቶ ድርሳንና ገድል ነግሶ ኖሯል።

  ReplyDelete
 11. 100% menafeke is Mk.

  ReplyDelete
 12. ነጭ ውሸት!! ይላል ያገሬ ሰው ...i like the way you comment with evidence ,,,, please i need to hear more from you , keep posting

  ReplyDelete
 13. Thanks to God, the power of God has revealed you.I had some problem with MK, now the issue is totally clear to me, you guys (Abaselam) have surely sponsored by westerns to fight our church. The other things really surprised me that you guys unexpectedly disclose the genuine of MK, I relay thank you for good things you did for me despite not intentional. I don't care whether you post it or not.
  AM

  ReplyDelete
 14. PLEASE,EXAMINE YOUR SELF.YOU ARE THE CREATURE OF JESUS CHRIST. MY FATHERV AND I ARE THE SAME .JN.10;30

  ReplyDelete
 15. አባይነህ ካሴ
   መጽሐፍ ቅዱስ ያጋንናል ብሎ ከጻፈ
   ነፍስ አትጾምም ብሎ ካስተማረ
   ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ያጠመቀው ዲያቆን ነው ብሎ ከተናገረ ማህበረ ቅዱሳን ምን አሉት ሲኖዶስስ

  ReplyDelete
 16. በእናታችሁ ማህበረ ቅዱሳን እኮ የቤተ ክርስያንን ገንዘብ ለመመዝበር የተቋቋሙ አንጅ የሃይማኖት ተቋም አይደሉም

  ReplyDelete
 17. exodus
  ምዕራፍ 40።

  1፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው።

  2፤ ከመጀመሪያው ወር በፊተኛው ቀን የመገናኛውን ድንኳን ማደሪያ ትተክላለህ።

  3፤ በእርሱም ውስጥ የምስክሩን ታቦት ታኖራለህ፥ ታቦቱንም በመጋረጃ ትጋርዳለህ።.....
  12፤ አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ አቅርበህ በውኃ ታጥባቸዋለህ።

  13፤ የተቀደሰውንም ልብስ አሮንን ታለብሰዋለህ፤ በክህነትም ያገለግለኝ ዘንድ ቀብተህ ትቀድሰዋለህ።

  14፤ ልጆቹንም አቅርበህ ሸሚዞችን ታለብሳቸዋለህ፤

  15፤ በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አባታቸውን እንደ ቀባህ ትቀባቸዋለህ፤ መቀባታቸውም ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ክህነት ይሆንላቸዋል።.....

  ReplyDelete
 18. Anonymous said...

  exodus
  ምዕራፍ 40። ለጠቀስከው ሰው---------
  ዛሬም የኦሪቱ የክህነት አገልግሎት አለ ብለህ ነው የምታምነው? እንዲያ ከሆነ በአሮጌው አቁማዳ ላይ አዲሱን ለመጣፍ መሞከር አቁማዳውን የባሰ እንዲቀዳደድ እያደረገው እንዳለ የሚያሳይ ነው። ሮሜ ሮሜ 7፤6 አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም» ይልብሃል
  አብዬ ኤክሰደስ-------
  የሙሴ ሕግ ጥላ ናት። አካሉ ከተገለጸ በኋላ በጥላው ለመኖር ወስነሃል ማለት ነው?
  የሙሴ ሕግ አያጸድቅም። የሐዋ 13፣38«እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን»
  ሮሜ
  3፥20 «ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና»
  ወንድሜ ኃጢአት መኖሩ የታወቀው በሕግ ነው። ሞት ደግሞ የኃጢአት ውጤት ነው። ሞት ካልተሸነፈ ሕይወት የለም። ስለዚህም የሕግን ሁሉ ትእዛዝ ፈጽሞ፣ የሕግን የኃጢአት ሞት ያለኃጢአት ሞቶ፤ ሞት በማያሸንፈው ትንሳዔ ከሕግ አገዛዝ ነጻ ያወጣንን ትንሳኤ ክርስቶስን የሚይቀበልና ወደቀደመው የሕግ ሥርዓት የሚመለስ እሱ ገና ወደሕይወት አልተሻገረም።

  ወደ ገላትያ ሰዎች2፥16
  «ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል»
  ይልብሃል፣ ይመሰክርብሃል። ምን ትሆን?
  የኦሪቱ የክህነት አገልግሎት ማንንም ፍጹም ማድረግ አይችልም። ካህናቱ ፍጹም ማዳን ስላይደሉና ፍጹም አድርገው ማዳን ስላልቻሉ እኮ ነው፣ ራሱ መድኃኒት የሆነና ሌሎችንም ማዳን የሚችል ሊቀካህን ክርስቶስ ወደምድር ሥጋ ለብሶ በዘላለማዊው የመልከ ጼዴቅ መልክ የመጣው። ሐዋርያው እንዲህ ሲል ይጠይቅሃል፣ ምላሽህ ምን ይሆን? ዕብ 7፣11 «እንግዲህ ህዝቡ በሌዊ ክህነት የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና በዚያ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ቢሆን፥ እንደ አሮን ሹመት የማይቈጠር፥ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ግን የሆነ ሌላ ካህን ሊነሳ ወደፊት ስለ ምን ያስፈልጋል» አይገባህም እንጂ መልሱን እዚያው በግልጥ አስቀምጦልሃል። እያዩ የማያስተውሉ ከሚባሉት አንዱ አንተና መሰሎችህ እንዳትሆኑ እሰጋለሁ።
  ዕብ 7፣18 «ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል» ምክንያቱንም ጳውሎስ እንዲህ ይነገናል። ዕብ8፣7«ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር»
  እዚህ ላይ ቃሉን እየጠቀሱ ግን በተግባር የማይጠብቁ ሰዎች ደረቅ መከራከሪያ «ሕግንና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም» የምትለዋን ቃል ማንሳት ያስፈልጋል። መሻር ሲባል ብዙ ጊዜ መፋቅ፣ መደምሰስ፣ መሰረዝ፣ ማስቀረት አድርገው የሚገምቱ ሞልተዋል። ክርስቶስ ግን መሻርን ሲያነሳ ቃሉ የሚጠቁመው፤ በሕግ በኩል የገባውን ኃጢአት የሚያስከፍለውን የሞት ዋጋ ሳልከፍል፣ ሰዎች መጠበቅ ያልቻሉትን የሕግ ትእዛዝ ሁሉ ሳልፈጽም፣ በነቢያት የሰጠሁትን የማዳን ትንቢት ፍጻሜ ሳላሳይ ሕጉን ለመሻርና አዲስ ሕግ ለመስጠት አልመጣሁም ሲል ነው።
  ሥጋ የለበሰው ያንን ሊፈጽም መሆኑን ሲናገር ልንረዳ ይገባል። የትንቢቱ ፍጻሜንና የሕግ ሞትን ከፈጸመ በኋላ ግን ይወርዳል፣ይወለዳል፣ ይሞታል፣ ያረጋል የተባለውን ትንቢት ሁሉ በተግባር አሳይቶ አሳልፎታል። የህግንም ሞት፣ ሞቶ ሞትን ሽሮታል።
  ለዚህም ነው በማቴ 5፣15 ላይ እንዲህ ያለው።«እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም»
  የቀደመችው ሕግና ሥርዓት፣ ትንቢቶቹም ሁሉ በክርስቶስ ተፈጽመዋል። ስለዚህም ጳውሎስ ሲመሰክር «ዕብ 8፣13 አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል» ዕብ 7፣18ጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል

  ReplyDelete
 19. በአሮጌው አቁማዳ ላይ አዲሱን ለመጣፍ መሞከር አቁማዳውን የባሰ እንዲቀዳደድ እያደረገው እንዳለ የሚያሳይ ነው።

  So, why are you mending in our business? Go create NEW church which doesn't have 'አሮጌ አቁማዳ'.

  ReplyDelete
 20. rom-02
  ምዕራፍ 2
  11 እግዚአብሔር ለሰው ፊት አያዳላምና።

  12 ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤

  13 በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና።

  14 ሕግ የሌላቸው አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤

  15 እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።

  16 ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።

  17 አንተ ግን አይሁዳዊ ብትባል በሕግም ብትደገፍ በእግዚአብሔርም ብትመካ፥

  18 ፈቃዱንም ብታውቅ ከሕግም ተምረህ የሚሻለውን ፈትነህ ብትወድ፤

  19-20 በሕግም የእውቀትና የእውነት መልክ ስላለህ፥ የዕውሮች መሪ፥ በጨለማም ላሉ ብርሃን፥ የሰነፎችም አስተማሪ፥ የሕፃናትም መምህር እንደ ሆንህ በራስህ ብትታመን፤

  21 እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?

  22 አታመንዝር የምትል ታመነዝራለህን? ጣዖትን የምትጸየፍ ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህን?

  23 በሕግ የምትመካ ሕግን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ታሳፍራለህን?

  24 በእናንተ ሰበብ የእግዚአብሔር ስም በአሕዛብ መካከል ይሰደባልና ተብሎ እንደ ተጻፈ።

  25 ሕግን ብታደርግ መገረዝስ ይጠቅማል፤ ሕግን ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ አለ መገረዝ ሆኖአል

  ReplyDelete
 21. Why should I leave my home? My home is my home! If it breaks I will fix it. If it collapsed i repair! if there is dirty I wipe it! And i make him back to its original. That is my home!!!!!!!

  ReplyDelete
 22. rom-03
  ምዕራፍ 3
  1 እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው።

  2 አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው?

  3 የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?
  ..............
  31 እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።

  ReplyDelete
 23. የሙሴ ሕግ አያጸድቅም። የሐዋ 13፣38«እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፥ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ፥ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን
  3፥20 «ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፤ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና»
  ውድ ወንድሜ ሁለት ነገሮች የተደበላለቁብህ ይመስለኛል የእግዚአብሄር ህግ ፤የሙሴ ህግ፤ የህግ ማስፋፀሚያ ትእዛዛት
  1/ የእግዚአብሄር ህግ
  2/የሙሴ ህግ
  እያለ የተፃፈውን አትደበላልቅ
  ስለ ሙሴ ትእዛዝ ና ስለ እግዚአብሄር ህግ እንዲህ ይነበባል
  ኦሪት ዘፍጥረት ም፦13 ቁ1-3
  እግዚአብሄርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተነገረው ......አንተ አንብበው
  ሙሴም ህዝቡን አለ ኦሪት ዘፍጥረት ም፦13 ቁ3-መጨረሻው .......አንብበው
  ልብ በል እነዚህ የእግዚአብሄር ፍፁም ህግና ትእዛዛት በአዲስ ኪዳን ፍፁም ፀኑ እንጂ አልተሻሩም የክርስቶስን መሰቀል ከቃልኪዳኑ ታቦት ጋር አታመሳቅለው የክርስቶስ ደም የቃልኪዳኑን ታቦት ያስከብር ዘንድ ፅላቱ በእርሱ/በክርስቶስ/ ደም ተፅፏል እንጂ አንተ እንደምትለው የእርሱን ቦታ አልወሰደም

  የእግዚአብሄር ህግ ፍፁም የማይሻር ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ፍፁም የሚፀና ለምሳሌ
  1/10ቱ ትእዛዛት
  2/የቃልኪዳኑ ታቦት

  1/የሀጢያት ማስተስረያ መስዋእት /የበጉ ደም /
  በኦሪት እንሰዋው የነበረው የበግ ደም ሃሬ በአዲስ ኪዳን በሀያሉ ጌታ እናንተ ዛሬ አማላጅ /ተጠሪ/በምትሉት በእየሱስ ክርስቶስ ደም ተተክቷል::የተሰዋው የክርስቶስ ማህተም/ጽላት/ዛሬም በአዲስ ክዳን ይከበራል ይወደሳል::

  የኦሪቱ የክህነት አገልግሎት ማንንም ፍጹም ማድረግ አይችልም። ካህናቱ ፍጹም ማዳን ስላይደሉና ፍጹም አድርገው ማዳን ስላልቻሉ እኮ ነው፣ ራሱ መድኃኒት የሆነና ሌሎችንም ማዳን የሚችል ሊቀካህን ክርስቶስ ወደምድር ሥጋ ለብሶ በዘላለማዊው የመልከ ጼዴቅ መልክ የመጣው።
  ፣ ሰዎች መጠበቅ ያልቻሉትን የሕግ ትእዛዝ ሁሉ ሳልፈጽም፣ በነቢያት የሰጠሁትን የማዳን ትንቢት ፍጻሜ ሳላሳይ ሕጉን ለመሻርና አዲስ ሕግ ለመስጠት አልመጣሁም ሲል ነው።
  ታዲያ ትላንት በሃዋርያት ዛሬ በቅዱሳን እንዲሁም በተመረጡ ካህናት እያደረ የተአምራቱን ስራ የሚሰራው መሰለኝ አንተም ተመርጫለሁ እጅ ጭኜ አድናለሁ ስትል የሰማሁ መሰለኝ ተዲያ የምታድነው አንተው ነህ አዳኙ ወይስ አንተን የመረጠህ?
  ታዲያ ካልተመረጥክ ወይም ካህናት ከሌሉ ክርስቶስ አሁንም በስጋ እየወረደ ያድናል እንዴ?
  ሎቱ ስብሀት

  እዚህ ላይ አንተው እራስህ በስተመጨረሻ ላይ ስላስቀመጥከው እንድታንበው ነው ደግሜ የፃፍኩት ::
  በመጨረሻ
  ወንድሜ ኃጢአት መኖሩ የታወቀው በሕግ ነው። ሞት ደግሞ የኃጢአት ውጤት ነው። ሞት ካልተሸነፈ ሕይወት የለም። ስለዚህም የሕግን ሁሉ ትእዛዝ ፈጽሞ፣ የሕግን የኃጢአት ሞት ያለኃጢአት ሞቶ፤ ሞት በማያሸንፈው ትንሳዔ ከሕግ አገዛዝ ነጻ ያወጣንን ትንሳኤ ክርስቶስን የሚይቀበልና ወደቀደመው የሕግ ሥርዓት የሚመለስ እሱ ገና ወደሕይወት አልተሻገረም

  ReplyDelete
 24. You should leave because
  it's not your home. It's your fathers home. However, you grow up now and you started dispise them and their house. You insult them and expect them to inherent their house to you? But infront of this house there is a house full of people who is trying to dust, fix, repair their hall and many social issue like gays, that is PENTE house. It wellcome you.

  ReplyDelete
 25. http://ethiopianorthodox.org/amharic/archivee/stmary/tabotetsion.pdf

  ReplyDelete
 26. wondimochachin leimnet kentachihuna tekorkurachihu kehone sile tabotuna tsilatu aserarna meten tikikil aydelem ahun yalew yemitilut egziabher yibarkachihu.enante wondimochachin betabotuna betsilatu aserarna meten mikniat kehone metifatachihu sile-ewnet new yemilachihu ye-Ethiopia orthodox tewahido betekirstian wodekedemew meten tikeyirilachihualech enante bicha behiguna besiriatu ewnetegna amagn hunu.Enie gin aymeslegnim latamnubet min ale sew gira batagebu. Mejemeria sile tabotuna tsilatu aserarna meten lemekorkorim hone lemawrat bekiristos kiristian mehon silemiasfelig yekebero bahitawi mehonachihun new yemitinegrun. silehonem befinachihu tenbochareku.
  litaminubetna litakebrut endemigeba

  ReplyDelete
 27. kehadi bemehonachu wushet libsachu new. ewnetegna bitihonu mech teleytachu twetalachu

  ReplyDelete
 28. አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ ፥ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ ፤ » መዝ ፸፰ ፥፩ ።

  ReplyDelete
 29. ewnet teshefno aykerim.bewengel anafrim.wengel yashenfal.eyesus bicha yadinal watewim tifawim ewnetu yihe new.halelujah which means EGZIABHER YIMESGEN.

  ReplyDelete
 30. Yes!!!
  This is the beginning God is on duty!
  The truth is shining upon the Generation! It is time to proclaim that Jesus is the Only way top heaven it is the new covenant the old one is passed and over with the Holy Blood of Jesus!
  Jesus is Lord!!

  ReplyDelete
 31. This is the real time to get back to Jesus! He is enough to get in heaven the rest is for the practice of religiousness. Jesus is the real way to heaven.......
  This Generation should seek his glory its over we have not to live to study history of somebody but to do history.
  God is able!

  ReplyDelete