Thursday, November 3, 2011

በአባ ሕዝቅኤልና በአባ ፊልጶስ ጠብ የተቋረጠው ሲኖዶስ ዛሬም ቀጥሏል፤ በሁለቱ ጳጳሳት መካከል ዕርቅ አልወረደም፡፡ - - - Read PDF

ትናንት ያለ ውል በጠብ ተቋርጦ የነበረው የሲኖዶስ ስብሰባ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ በአባ ፊልጶስና በአባ ሕዝቅኤል መካከል ዕርቅ አለመውረዱንና በሲኖዶሱ ላይ ስለትናንቱ ጠብ የተባለ ነገር አለመኖሩን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ አባ ፊልጶስን "የአገር ጋለሞታ ቀጥረው ቤተ ክህነቱን በጋለሞታ የሞሉት እርስዎ ነዎት" በማለት የዘለፉት አባ ሕዝቅኤል ዛሬ ወደ ስብሰባ አልገባም ብለው ሲግደረደሩ እንደ ነበረና "የሚፈልጉትን እንዲያገኙ እናደርጋለን" ተብለው በልመና እንደ ገቡ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ይሁንና ምን እንደሚፈልጉ ለማወቅ ምንጮቻችን ያደረጉት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ለወደፊት ተከታትለን ስለ ጉዳዩ ለመዘገብ እንጥራለን፡፡ እንደ አንዳንዶች ግምት ግን አባ ሕዝቅኤል የሚፈልጉትን ነገር ቢያገኙ ኖሮ ከመጀመሪያው የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ አይሆኑም ነበር ሲሉ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ለግል ጥቅም ሲባል የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና ጀንበር የጠለቀችበትን ማኅበረ ቅዱሳንን ዕድሜው እንዲራዘም ማድረግ ለቤተክርስቲያናችን ትልቅ ጥፋት መሆኑን ብዙዎች ይገልጻሉ፡፡

በአባ ፊልጶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅነት ዘመን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በርካታ መነኮሳዪያት (ሴቶች መነኮሳት) በጠቅላይ ቤተ ክህነትና በአዲስ አበባ የቤተ ክህነት ልዩ ልዩ ክፍሎች የተቀጠሩ መሆናቸው ሲታወቅ፣ ከእነዚህም መካከል አንዲቷ የእኅታቸው ልጅ እንደ ሆነች፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽዳት ሠራተኛነት እንደ ተቀጠረችና አራት ኪሎ በሚገኘው የቤተ ክህነት ሕንጻ ላይ ብዙዎች የማያገኙትን መኖሪያ ቤት እንደ ሰጧትም ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ ሕዝቅኤልም በጠቅላይ ቤተ ክህነት አባ ፊልጶስ የቀጠሯቸውንና እርሳቸው "ጋለሞቶች" ሲሉ የጠሯቸውን መነኮሳዪያት ወደ አድባራት እንዲበትኑ በደም ፍላት መናገራቸውን ተከትሎ ነበር ከአባ ፊልጶስ ጋር ዱላ ቀረሽ ስድብ ውስጥ የገቡት ተብሏል፡፡

በርካታ ቀናትን የፈጀው የዘንድሮው ስብሰባ ዛሬም አለ መጠናቀቁ ሲታወቅ፣ በሁለቱ ጳጳሳት መካከል የተፈጠረው ጠብ በማኅበረ ቅዱሳን አንቀራባጭነት የአባ ሠረቀንና የተሐድሶን ጉዳይ እንዲያጣራ ተቋቋመ የተባለው ኮሚቴ ማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ ያላቸውን ወገኖች በፍጥነት እንዲያወግዝ የተፈለገ ቢሆንም፣ ውግዘቱ እንደ ታሰበው አለመሳካቱንና በዚህም ሳቢያ በስብሰባው ዙሪያ ሲያንጃብቡ የነበሩ የማኅበረ ቅዱሳን ወኪሎችና ተላላኪዎች አንገታቸውን ደፍተው እንደ ዋሉ ለመታዘብ ተችሏል፡፡ በሌለው ሥልጣንና መብት ለውግዘት ቸኩሎና አሰፍስፎ የነበረው ማኅበረ ቅዱሳን የሁለቱ ጳጳሳት ጠብ የሲኖዶሱን ስብሰባ አቅጣጫ እንደ ቀየረበት ሲታወቅ፣ በተለይ በአባ ሠረቀ ላይ የተወሰነው ውሳኔ እንደ ሐውልቱ ውሳኔ እንዳይሆን ያሠጋል እያለ በመናገር ላይ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ቀደም ሲልም ምእመናንን በፈጠራ ወሬ ለመፍታት ሰፊ ዘመቻ በከፈተበት ደጀሰላም ድረገጽ ላይ ይህንኑ ሥጋቱን ገልጦ እንደ ነበረ የሚታወስ ነው፡፡

በዛሬው የስብሰባው ውሎ አባ ፊልጶስ ምንም እንኳ ከአባ ሕዝቅኤል ጋር ተኳርፈው የዋሉ ቢሆንም ማኅበረ ቅዱሳን የሰጣቸውን ተልእኮ ባለመዘንጋት "አባ ሠረቀ ሰው ስለ ጠላቸው መነሣት አለባቸው" ሲሉ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡ አባ ሠረቀን ማኅበረ ቅዱሳንና እርሱ በተሳሳተ መንገድ ያሳደማቸው ክፍሎች ካልሆኑ በቀር ማንም እንደልጠላቸው የታወቀ ሲሆን፣ ከጥቂት ቀናት በፊት ይቀርብባቸው የነበረው ክስ ሌላ እንደ ነበርና ዛሬ ግን "ሰው ስለ ጠላቸው መውረድ አለባቸው" መባሉ አስተዛዛቢ ሆኗል፡፡

5 comments:

 1. selam le enanete yihun wegenoche yihen blog yagegnehut andu wedaje setogn lemejemereya geze mayete neber neger gin betam asdesetognal lekam endezhi ayenete yebetekereseteyan tekorekuari ale beteleye yewendemoch kesash lehonu mahebre kidusan( mahebre seyetan ) lehonu sewoch afachewen yemeyazega Egziabher yeredan ke endenezhi ayenet yebetekereseteyan telatoch bertu ayezoachew wegenoche

  ReplyDelete
 2. ለቤተክርስቲያናችን ? yetu new yenat ቤተክርስቲያNe lol defar

  ReplyDelete
 3. አባ ሰረቀ ማለት’ኮ የሚለኔሙ ጀግና ተብለው መሸለም ያለባቸው ናቸው። ሌሎች የማደራጃው መምሪያ ሐላፊዎች ለእርኩሱ ማሕበር ውሽማ የነበሩ ናቸው።
  አባ ሰረቀ? ለሥራ የቆምክ ትጉህ ወታደር ነህና አይዞህ በርታ! ከአንዳንድ ጅላንጅል የማህበሩ ጭስ የጨሰባቸው ካልሆኑ በስተቀር ሌላው ሁሉ ካጠገብህ የቆመ ነው ። የማህበሩ አባላትም ቢሆኑ እውነቱን እየተረዱ ስለመጡ ከላይ ሆነው “ቁጭ-ተነስ በል” እያሉ ሲያስቸግሯቸው የነበሩ ዓላማቸውን ስለተረዷቸው” ወግድ! ዲሞርካችሁን ፈልጉ!” እያልዋቸው መሆናቸው የቅርብ የሆኑትን የማህበሩ ጓደኞቻችን እየነገሩን ናቸው።

  ReplyDelete
 4. Aba Sereke blamed Aba Selama as a Tehadeso site:-
  http://www.eotcssd.org/message/35-2011-02-08-21-34-46/184-blogs-for-gospel-or-crime-in-eotc.html

  I taught you were freinds:(

  ReplyDelete
 5. I know who and what the mission of Aba selama site is. you stand just on the side of CHURCH REFORMISTS and Sereke. No need of evidence for this as you told us in explicit words. Sorry for your fruitless struggle and unconditional defeat. You lost the game. We made every body know your evil deeds You are struggling to close the door of the Holy Gospel. Do you think you will be successful?

  ReplyDelete