Monday, November 7, 2011

ድርስሳነ ሚካኤል ከራሱ ጋር መጣላቱ አልበቃ ብሎት ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር ለመጋጨት ጠብ ሲጭር - - - Read PDF

ይህ ጽሑፍ ከአሁን በፊት (የዛሬ 10 ወር ገደማ) የቀረበ ሲሆን። በርከት ባሉ አንባብያን ጥያቄ መሰረት እንደገና አቅርበነዋል
በሀገራችን በኢትዮጵያ ወንድም ከወንድሙ ወገን ከወገኑ አልስማማ እያለ ነገሩ ምን ይሆን እያልሁ ማሰብ ከጀመርሁ ሰንብቻለሁ። ኢሐፓ እርስ በርሱ ባለመስማማቱ ያን ሁሉ የተማረ ትውልድ እንድናጣ ተገደድን፤ ደርግም ከራሱ በመጣላቱ ሕዝብን ሲያጠፋ ኖረ፤ ወያኔ እርስ በርሱ ባለመስማማቱ ከሻቢያ ጋር ባደረግነው ጦርነት ልናገኝ የነበርነውን ወደብ አጣን፤ ተስፋ ያደርግነው ከሕጻናት እስከ ሽማግሌ የተማመንንበት ቅንጅት ለአንድነት ለዲሞክራሲ እርስ በርሱ ባለመስማማት ጨለማ ውስጥ ከቶን ድራሹ ጠፋ፤ አንድነት የተባለው አዲሱ የፖለቲካ ድርጅት ፕሮፌሰር መስፍንን እስኪያጣ ድረስ እርስ በርሱ አልተስማማም። አሁን ደግሞ መኢአድ የተባለው ድርጅት እርስ በርሱ አልስማማ ብሎ እየታመሰ ነው። አሁን ቁጭ ብለን ነገሩ ምን ይሆን ብለን እራሳችንን የምንመረምርበት ወቅት ላይ ነን።
ችግሩ ከአስተዳደጋችን ይሆን? አስተዳደጋችንና እየተማርን የምናድገው ነገር መጠናት አለበት እላለሁ። የበላይነት ስሜትን የሚያንጸባርቅ ከማን አንሼ የሚል የእልከኝነት አስተሳብ በደማችን ውስጥ ያለ ይመስለኛል። የእምነት ድርጅቶችን እንኳ ስንመለከት በክርስቶስ እናምናለን የሚሉት ኢትዮጵያውያን ፕሮቴስታንቶች እናኳ ባለመስማማት እና በመከፋፈል ዋነኛውን ደረጃ ይዘዋል።
 ከሁሉ የሚገርመው በሰዎችና በቡድኖች መካከል ያለው አለመስማማት ወደ አንጋፋዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ከጊዜ በሁዋላ በተበረዙና ሰርገው በገቡ ድርሳናትና ገድላት ማካከልም ይንጸባረቃል። ብዙዎቻችን ኢትዮጵያውያን እነዚህን መጻህፍት ስለምንደግማቸው፤ ስለምናነባቸው፤ ስለምንሳለማቸው እና ጸበል ስለምንጠቀምባቸው ከመጻሕፍቱ ባህርይ የወረስን ይመስለኛል።  ለሚያነባቸው መጻሕፍቱ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ በማለት ጦርነት ውስጥ የገቡ ይመስላል። እነዚህን መጻሕፍት እየተማረ ያደገ ትውልድ ጤነኛ አስተሳሰብ ይኖረዋል የሚል እመነት የለኝም። የአብዛኛዎቻችን ችግር መንፈሳዊ ነው ባይ ነኝ። መንፈሳችን መጥራት አለበት አለባለዚያ ጥራት ያለው መሪ ልናገኝ አንችልም።
ለምሳሌ ድርሳነ ሚካኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያወጣቸው ሚካኤል ነው ሲለን፤ ድርሳነ ገብርኤል ግን ገብርኤል አዳናቸው ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን ሁለቱን ሳያነሳ እግዚብሔር ስሙ ባልተገለጠ መልአክ እንዳዳናቸው ይነግረናል። የማሕበረ ቅዱሳን አባላት ይህን ግልጽ የሆነ የድርሳነ ሚካኤልን እና የድርሳነ ገብርኤልን ጠብ ለማብረድ ወይም የይገባኛል ጥያቄ ለመመለስ ሚካኤል ባለበት ገብርኤል፤ ገብርኤል ባለበት ሚካኤል አለ በማለት ለመገላገል ሞክረዋል። ትንቢተ ዳኔኤል ም 3 ቁ 25 ላይ እነሆ በእሳት ውስጥ የሚመመላልሱ አራት ሰዎችን አያለሁ አራተኛውም የአማላክትን ልጅ ይመስላል ይላል በዚህ ቃል ሦስት ወጣቶች እና አንድ ስሙ ያልተገለጠ መልአክ ይሁን እግዚብሔር አራተኛ ሆኗል። ነገር ግን ሚካኤል ባለበት ገብርኤል ካለ አምስት መሆን ነበረባቸው ግን አራት ብቻ ናቸው። በዚህ ታሪክ ውስጥ ሚካኤል ወይም ገብርኤል ከሁለት አንዱ ተገኙ እንበል፤ ነገር ግን የሁለቱ ድርስናት የታሪክ ሽሚያ [የኔ እበልጥ ጦርነት] ግን ቅንጅትን እንድናስታውስ ያደርገናል። እንደዚህ ዓይነት ውሸቶችን ማረም ማስወገድ ይጠበቅብናል።
በጣም አሳሳቢ በሆነ መጎሻሸም ላይ የሚገኙት የገድለ ላሊበላ እና የገድለ ተክለ ሃይማኖትን እንመልከት። በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተረበሸ ያለበትን የጠለቀ ምሥጢር እናስተውላለን። የልደቱ አያሌውን እና የኢንጀነር ኃይሉ ሻውልን ያለመስማማት ምሥጢር ገድለ ላሊበላን እና ገድለ ተክለሃማኖትን በማንበብ መረዳት ይቻላል። እነዚህ መጻሕፍት ቤተ ክርስቲያናችንን ብቻ ሳይሆን ፖለቲካችንንም እየረበሹ ይገኛሉ ግን ማን ያስተውላል? ይህን የምጽፈው የችግራችንን መሠረት በደንብ እንድናውቀው ስለፈለግሁ ነው።
ለምሳሌ ገድለ ተክለ ሃይማኖት የላስታ ነገስታትን የሚኮንን፤ መንግሥት የማይገባቸው፤ እያለ የሚፎክር ሲሆን ገድለ ላሊበላ በበኩሉ የይኩኖ አምላክን መንግሥት እጅግ ያንቋሽሻል። ገድለ ተክለ ሃይማኖት መንግሥት በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ሶሎሞን ዘር ወደ ይኩኖ አማላክ ተዛወረ  ሲል ገድለ ላሊበላ ግን በተንኮል እና በጦርነት ነው ይላል።
በላሥታ መንግሥት እና በይኩኖ አምላክ መካከል ከባድ ጦርነት መካሄዱን ገድለ ተክለ ሃይማኖት አይክድም ሆኖም ተክለሃይማኖት የዚህ ጦርነት ተዋናይ እንደነበሩ ገድለ ተክለሃይማኖት ይናገራል። ይህ ያለፈ ታሪክ ነው ነገር ግን መጽሕፍቱ በየእለቱ እየተነበቡ ስለሆነ በፖለቲካው ላይ ከባድ ችግር በመፍጠር ላይ ናቸው። ይህ ጥንታዊና ዘርን መሠረት ያደርገው የሥላጣን ሽሚያ በነዚህ በሁለቱ ገድላት ላይ በግልጥ ይታያል ወደፊት አቀርባለሁ። እነዚህን መጻሕፍት በመሳለም በረከት ለማግኘት የሚጋደለው የኢትዮጵያ ሕዝብ በእርግጥ በረከትን አምጠውለት ይሆን? ወይስ መለያየትን፣ ሕብረትን ወይስ ዘረኝነትን? አባ ጳውሎስ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተባሉበት ምክንያት ስልጣን አምሯቸው አንዳይመስላችሁ ምሥጢሩ የተክለሃይማኖት መንበር ይገባናል እያሉ ሲበጠብጡ የነበሩትን አባ.. እንተናን፤ አፋቸውን ለማዘጋት የተደረገ ፖለቲካዊ ምሥጢር ነው።  በቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ውስጥ በተክለሃማኖት ዘሮች እና በላሊበላ ዘሮች መካከል ውስጥ ለውስጥ የሚካሄድ መጎሻሸም መኖሩን ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ? ግን ማወቅ አይጠበቅባችሁም አያስፈልጋችሁምም ነገር ግን እነዚህ መጻሕፍት እርግማንን እንጂ በረከትን እንደማያመጡ ማወቅ አለብን። እነዚህ መጻሕፍት በውስጣቸው የያዙትን ወደ ፊት አቀርባለሁ የጦርነት ምንጭ ሆነው ኢትዮጵያን ሰላም የነሱ መጻሕፍት ናቸው።
በድርሳነ ሚካኤልን ችግሮች ከማየታችን በፊት እስኪ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንን መጻሕፍት እንዳሳቸው
1ኛ) የቅዱስ ያሬድ የዜማ መሳሕፍት
·        ድጓ
·        ጾመ ድጓ
·        ዝማሬ
·        መዋሥእት
·        ምዕራፍ ናቸው።
እነዚህ መጻሕፍት የክርስቶስን የማዳን ሥራ የሚያደንቁ የቅዱሳንን መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚያስታውሱ ለእግዚአብሔር ክብር የተዘመሩ ድንቅዬ ሀብታችን ናቸው። ሆኖም በኋላ ዘመን የተነሱ ደብተራዎች ይህን ንጹህ የያሬድ ድርሰት በራሳቸው ድርሰት መበከላቸው አልቀረም። የራሳቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌላቸው ድርሰቶችን በያሬድ ስም አስገብተው ዚቅ ብለው ሰይመውታል ለምሳሌ ያህል የጥቅምት መርቆርዮስን ዚቅ ማየቱ በቂ ይሆናል።
2ኛ መጽሐፈ ቅዳሴ፦ ይህ መጽሐፍ በጥቅሉ የቁርባን ምስጋና የያዘ ነው የእግዚአብሔርን ታላቅነት ምስጋና የንሥሐ ጸሎት የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ቤዛነቱን የስሙን ታላቅነት ይናገራል እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ እውነተኛ የአምልኮ መጻሐፋችን ነው። አንዳድ ቅዳሴዎች ለምሳሌ እንደ ቅዳሴ ማርያም ያሉት ግን በጥቂቱ ብክለት አለባቸው።
3ኛ መጽሐፈ ሰዓታት፦  በየሰዓቱ የሚጸለይ ሰዓቶችን ጠብቆ የሚደርስ ጸሎት ነው። መጽሐፉ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ነው ቢባልም የሁለት ሰው ድርሰት ይመስላል። ይህን ያልንበት ምክንያት የሚከተለው ነው
ለምሳሌ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር አርፍተ ጽርሑ ዘነድ ወጸፍጸፈ ቤቱ በረድ ኅቡር ኅላዌሁ ዘኢትበአድ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ሰጊድ ትርጉም የአዳራሹ ግድግዳ እሳት የቤቱ ንጣፍ በረድ የሚሆን እግዚብሔር ጽንኡ ልዩ ነው የማይለይ አኗኗሩ አንድ ነው ለ እርሱ ብቻ ሊሰገድለት ይገባል 
ለእርሱ ብቻ ስግደት ይገባል የሚለው ትክክል ሲሆን የዚህ እውነት ተቃራኒ ደግሞ በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ይላል ንኡ ንስግድ ለባሕቲታ ለማርያም ድንግል ስመ መንታ ለአግብርታ ወለአእማታ ትኩነነ ወልታ ትርጉም ስመ መንታ ለሆነች ለድንግል ማርያም፤ ለእርሷ ብቻ ኑ እንስገድ ለወንዶች እና ለሴቶች ባሮቿ ጋሻ መከታ ትሆነን ዘንድ ይላል  እንደዚህ ያለ ብዙ ግጭት የሚገኝበት መጽሐፍ ነው። ለእግዚአብሔር ብቻ እንስገድ ሲል ቆይቶ እንደገና ለማርያም ብቻ ኑ እንስገድ በማለት የመጀመሪያ እምነቱን ያፈርሰዋል።
መጽሐፉ ያንድ ሰው ድርሰት አይደለም ያልሁበት ምክንያት እርስ በርሱ የሚጋጭ በመሆኑ ነው።
4ኛ ሃይማኖተ አበው፥  የሊቃውንት መጽሐፍ ነው የተለያዩ ጥንታዊ ሊቃውንት ለመናፍቃን መልስ የሰጡበት፤ የተጻጻፉት ደብዳቤ፤ ሲሆን መጻሕፍትን የተረጎሙበት መጽሐፍ ነው ለምሳሌ እነ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ እነ አትናቴዎስ እነ ቄርሎስ የመሳስሉ አባቶች ይገኙበታል።
5ኛ ድርሳናት፦ እነዚህ ድርሳናት የሊቃውንት ሥነ ጽሑፎች ሲሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን የተረጎሙበት እምነታቸውን የገለጡበት ጽሑፎች ናቸው። ለምሳሌ ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ።
6ኛ የብሉይ እና የሐዲስ አንድምታ፦ ይህ መጽሐፍ ብዙ ተረታ ተረት የበዛበት ሐሳብን በሐሳብ እያፈረሰ በአንድ የማይረጋ ተጨባጭነት የሌለው በአንድ ቃል ብዙ ትርጉም ለመስጠት የሚጨነቅ ያልተረጋጋ መጽሐፍ ነው። ሆኖም ግን አልፎ አልፎ ቁም ነገር ይገኝበታል።
7ኛ አዋልድ መጻሕፍት፦ እነዚህ መጻሕፍት ማን እንደ ደረሳቸው አይናገሩም ለቁጥር የሚያዳግቱ ሲሆኑ ነገር የሚያጋንኑ ታሪክ የሚያፋልሱ፤ የመዳንን መንገድ የሚያሳስቱ ናቸው። በብዛት ስምሕን ስምሽን የጠራ ዝክርሽን የዘከረ ቦታህን የተቀበርህበትን የሞትህበትን ያሰበ የተሳለመ  ከሰባት እስከ አሥራ ሁለት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ እያሉ የሚቀልዱ እና አጉል ተስፋ የሚሰጡ መጻሕፍት ናቸው። እነዚህ መጻሕፍት ዋና የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊ፣ ፖለቲካዊ መንፈሳዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ያመጡ ደንቃራዎች ናቸው።
 8ኛ በተለያዩ መምሕራን የተጻፉ መጻሕፍት፦ እነዚህ ብዙ ጠቃሚ እውቀትን ይሰጣሉ ለምሳሌ የአለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት፥ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ መጽሐፈ አቡሻክር ወዘተ..
ከአንድ እስከ ስምንት ከዘረዘኋቸው መጻሕፍት ውስጥ ተሃዶሶዎች የሚቀበሏቸው 1ኛ የያሬድ የዜማ መጻሕፍትን
           2ኛ መጽሐፈ ቅዳሴውን
           3ኛ ሃይማኖተ አበውን
           4ኛ የነዮሐንስ አፈወርቅ ድርሳናትን
           5ኛ በተለያዩ መምህራን የተጻፉ መጻሕፍትን ነው። እነዚህ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማሙ በመሆናቸው ይቀበሏቸዋል።


በድርሳነ ሚካኤል  የሚገኙ ግጭቶች
ወንድሞቼ ሆይ ያለመላእክት ልመና እና ምልጃ ይልቁንም ይህ  የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሁልጊዜ በሚያስፈራ እና ግሩም በሆነ የእሳት ሠረገላ ፊት ስለ ሰው ልጅ ከሚለምነው ምሕረት በቀር ማንም ሰው የመዳን ተስፋ ፈጽሞ የለውም መቅድም ቁ 4 ይመልከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ ግን በክርስቶስ ካልሆነ መዳን የለም ይላል ዮሐ 14 ቁ 6 ነገሩ እንዴት ነው?
የመላእክት አለቃ የምትሆን ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አመሰግናሀለሁ በአንተ ጸሎት እና ምልጃ ምድር ጸንታ ትኖራለችና ሚያዚያ ቁ 44።
መጽሐፍ ቅዱስ ምድር እና ሰማይ በእግዚአብሔር ቃል ጸንተው እንደሚኖሩ በብዙ ቦታ ይናገራል መዝ 32 ቁ 6። ታዲያ ድርሳነ ሚካኤል የእግዚአብሔርን ምስጋና ለመውሰድ ለምን ይጣደፋል እረጋ ብሎ ያስተውል እንጂ!
የድርሳነ ሚካኤልን ውሸት የሚያጋልጠው ደግሞ ሚያዚያ 12 የሚካኤል በዓል የሚታሰብበት ምክንያት ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ነቢዩ ኤርምያስን ንጉሥ ሴዴቅያስ ካስጣለበት ቦታ ስላወጣው ነው ብሎ ይተርካል፤ ድርሳን ዘሚያዚያ ያንቡ።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን ኤርምያስን ከተጣለበት ረግረግ ያወጣው ሚካኤል ወይም ሌላ መልአክ ሳይሆን ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ እንደሆነ ይናገራል። ኤር 38 ቁ 5-13።
ድርሳነ ሚካኤል እርስ በርሱ የማይስማማበት ቦታ ብዙ ነው። ለምሳሌ እኛ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአርአያችን እና በምሳሌያችን ሰውን እንፍጠር ብሎ ሰውን ፈጠረው ስሙንም አዳም ብሎ ሰየመው የእግዚአብሔር መልአክት ሁሉ ይሰግዱለታል ብሎ ነቢዩ እንደተናገረው መላእክቱም ለአዳም እንዲሰግዱለት አዘዛቸው በአርአያው የተፈጠረ ነውና ካለ በኋላ ቀጥሎ ሚካኤል ለእጆቼ ፍጥረት ስገዱ ሲል የአብን ቃል ሰምቷልና ፈቃደኛ ሆኖ በአዳም ፊት በጉልበቱ ሰገደ .. ለፈጣሪው ያለ ፍጥረቱም ለአዳም ያልሰገደ ግን ከሹመቱ ተሻረ ከልእልናው ተዋረደ ይላል ድርሳን ዘሚያዚያ ቁ2-6።
ይህን ከላይ ያየነውን አባባል የረሳው ድርሳነ ሚካኤል በጥር ድርሳን ላይ ቁ 100-103፤ እንዲህ በማለት በሥካር ይንገዳገዳል ፈጣሪያችን ከሥጋዌው አስቀድሞ ለፍጥረቱ ይሰግዱ ዘንድ መላእክትን አላዘዛቸውም ከሥጋዌው በኋላ ግን ፍጥረት ሁሉ ለእርሱ ሥጋ ሰገዱለት ሥጋ የባሕርይ አምላክ ሆኖ በአብ ቀኝ ተቀምጧልና ይላል።
በሚያዚያው ላይ መላእክቱ ለፍጥረቱ እንዲሰግዱ ታዘዙ ይላል በጥሩ ላይ ግን መላእክት እንዲሰግዱ አልታዘዙም ይላል። የሰከረ ሰው እንኳ ይህን ያህል የሚረሳ አይመስለኝም። ድርሳነ ሚካኤል ከራሱ ጋር ያለበት ግጭት አልበቃ ብሎት ከወንድሙ ከገድለ ጊዮርጊስ ጋር ለመጋጨት ጠብ ሲጭር እናገኘዋለን፤ ወደፊት አቀርባለሁ። ይህ ሁሉ ችግር እውነተኛዋን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አይወክልም የተሳሳቱ ሰዎች በጉልበት እና በሥውር ያስገቡት ስሕተት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህን አታስተምርም ነገር ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ማንም የማይቆጣጠራቸው ደፋሮች እየጻፉ እያሳተሙ በሕዝቡ ውስጥ ስላሰራጩት ቤተ ክርስቲያናችን ይህን የጠላት ተንኮል ለማስወገድ በታላቅ ትግል ላይ መሆኗን ሳልናገር አላልፍም።
ኢትዮጵያዊው ወገኔ ይህን ድርሳን በማንበብ ጊዜውን ሲያቃጥል አያለሁ። አንዳድ ወገኖቼ ከቅዠት ለመዳን እያሉ መጽሐፉን ትራሳቸው ላይ ያደርጉታል፤ መጽሐፉ ግን እንኳንስ ወንድሞቼን እራሱንም ከቅዠት ያላደነ መሆኑን ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች አስተውለናል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ይህን ስሕተት ለማረም እየታገለች ያለችው ዝም ብላ አይደለም የችግራችንን ጥልቀት አጥብቃ ስለተረዳችው እንጂ።
 የሀገራችንን ችግር ለመፍታት ደፋ ቀና የሚሉ ወገኖች ሁሉ የሀገሪቱን ጠቅላላ ሁኔታ በሚገባ ተረድተው ቢታገሉ ውጤት ያገኛሉ የሚል እምነት አለኝ። ሥራ የሚሠራው ከሕዝብ ጋር ነው ሕዝብ ከመንፈሳዊ እሥራት ካልተፈታ እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት አይቻልም። ወያኔም በኃይል ለመግዛት የሚያድርገው ሙከራ የመንፈስ ችግር ስላለበት እንጂ የፖለቲካ ትምህርት ስላነሰው አይደለም።
እውነት ታሸንፋለች ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።
ማሳሰቢያ ከእውነት ጋር ለተጣሉ ሁሉ
በዚህ ጽሐፍ ውስጥ የጨመርሁትም ሆነ የቀነስሁት ወይም የደበቅሁት የለም ድርሳነ ሚካኤልን በማንበብ ትክክለኛ መልስ ብትሰጡኝ እቀበላለሁ እንደ ባዶ በርሚል ዝም ብለን ብንጮህ ግን ምንም ለውጥ አናመጣም እውነት አይኗን አፍጣ መጣለች ብንሸፋፍነውም የሚገልጥ ትውልድ አለ። ይልቁን ጥራት ያለው እና የማያሳፍር ነገር ለትውልዳችን ለማቆየት ብናስብበት ይሻላል።
በተስፋ አዲስ

22 comments:

 1. Good job, Tesfa. Keep up the blessed work. We desperately need the truth of these centruy-old mess. Time to clean up our house!!!

  ReplyDelete
 2. ይህ ጽሑፍ ከአሁን በፊት (የዛሬ 10 ወር ገደማ) የቀረበ ሲሆን። በርከት ባሉ አንባብያን ጥያቄ መሰረት እንደገና አቅርበነዋል

  ድንቄም በድጋሚ ይቅረብ ውሸት አለቆባችሁ እየገረቸሁ ነው እንዴ?

  ReplyDelete
 3. 12:20
  ምስጋና ይገባሀል:: እውነት ብለሀል:: እኔ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ መቼ ይደርሳል ብዬ እጠብቃለሁ አጅሬ አንድ ነገር ይደጋግማል:: ቶሎ ብሎ ቢነግረን ጥሩ ነበር::

  ReplyDelete
 4. enkuan des alachehu abasereke yetekelay betekereseteyan astedadari honu esy esy esy mk abedu Rebeka ke Germen abedech yemigeremew neger Erbka mitebal set ke Geremen mk asabedewat meemenanen betebeta letecheres new ebakachehu tselot adergulat enzhi mahebere kidusanoch atemekewat lebesuan tila lethed new lelochem alu ere wegen enzhi mahebre kidusan and lenelachew yegebal be Germen frankfurt hezebe kereseteyanen wengel enasetemer eyalu be poletika eyaseru gemashun meemen eyawezagebu new neger gin hizebum eyenekabachew new le mk tselot yasefelegal weldegbreal negn ke Geremen

  ReplyDelete
 5. አይ ክርስትና? አንዳንዶች ለመተቸት ካልሆነ ራሳቸው ለማሰብ የተሰራ አይመስልም። አዲስ ተስፋ የመጽሐፎቹን የስህተት ነጥብና ስፍራ እየጠቀሰ አሳይቷል። የገለጸበት መንገድ ስህተት ነው የሚል ካለ ይህ ማለት እንደዚህ ነው፤ ያንንም ያለው እንደዚያ ነው እያሉ በመረጃ መልስ መስጠትና አንባቢው ግራና ቀኝ ያለውን አንብቦ እንዲፈርድ ማድረግ ሲገባ አባ ሺኖዳ እንዲህ አሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስም ተሳስቷል ልትል ነው፤ እስላም እስላም ትሸታለህ ወዘተ ዓይነት የህጻናት ቀልድ አይሉት ጅምላ የሃይማኖት ሸማቾች ማኅበር ዜና እንደሆነ ግራ የሚገባ ምላሽ ነው። ሚካኤል ሰለስቱ ደቂቅን ያዳንኩት እኔ ነኝ ሲል፤ ድርሳነ ገብርኤል ደግሞ የለም ያዳንኳቸው እኔ ነኝ እያለ ይገኛል። ጥላቸው ይገርማል፤ ይህንን ጸብ ሽማግሌ ሆኖ ለማስታረቅ ማኅበረ ቅዱሳን ገብርኤል ባለበት ሚካኤል አለ፤ ሚካኤል ባለበት ደግሞ ገብርኤል አለ ሲል የሽምግልናውን የውል ደብዳቤ ሊያስነብበን ሞክሯል በማለት ነው አዲስ ተስፋ የተባለው ጸሐፊ የተናገረው። እንደ ማቅ አባባል ደግሞ ከሰለስቱ ደቂቅ ጋር እሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ መገኘት ያለባቸው 5 መሆን ሲገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ 3ቱ ልጆችና 1 የአማልክት ልጅ በድምሩ 4 ሲመላለሱ አያለሁ በማለት የማቅ ሽምግልና የውሸት መሆኑን ያረጋግጥልናል። ለዚያውም ስሙ ስላልተጠቀሰ መልዓክ ነው ቅዱስ መጽሐፍ የሚናገረው። ሚካኤልና ገብርኤል ናቸው የሚለውን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሌለው መረጃ ምንጩ ምንድነው? የተጠየቀው ከብዙ ሃሳቦች መካከል አንዱ ነጥብ ይህ ሲሆን እስኪ ሱሪ ያለው ተካራካሪ ይመልስ። ያለሱሪ(ያለኃይል) በእውቀት ሊመልስ የሚችል ስለሌለ ማለቴ ነው።
  እዚህ ላይ እኔም አንድ ነጥብ ላንሳ በኢቢኤስ ቲቪ ባለፈው ጊዜ አንድ የማኅበረ ቅዱሳን ዲያቆን ለማታለል የሚሞክር የህጻን ጫወታውን ገንዘብ ከፍሎ በቲቪ ሲቀልድ አየሁት። በ2ኛ ጢሞ 3፤8 ላይ የተጠቀሱትን የፈርዖን አስማተኞች «ኢያኔስና ኢያንበሬስ» የተባሉት ሰዎች ስም በብሉይ ኪዳን አልተነገረም፤ ጳውሎስ ግን የሰማው ስለሆነ ጠርቷቸዋል፤ ስለዚህ እኛም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስማቸው ባይጠቀሰም የሰማነውን ስም እየጠቀስን መጽሐፍ ቅዱስን የተሟላ እናደርገዋለን ሲል ተሰምቷል። ጳውሎስ የተናገረው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የፈቀደው ሆኖ ተጽፏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጻፈውን ልክ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተጻፈው እንደጳውሎስ ቃል አድርጎ ለመቀበል የሚያስችለው ሎጂክ ምንድነው?
  እንደዚያ ከሆነ አራት ሰዎች ሲመላለሱ አያለሁ ያለውን ቃል እኔ ነኝ ያዳንኩት እኔ ነኝ እያሉ በሚጣሉት ድርሳኖች ውስጥ ያሉትን ሚካኤልና ገብርኤል ናቸው ብላችሁ ስማቸውን ገልጻችሁ ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ ጨምራችሁ መጽሐፍ ቅዱስን የማታሳትሙት ለምንድነው? ብዬ ጠየቅሁ። የሚያሳምን ምላሽ ባላገኝም ለመሳደብና ለማንጓጠጥ ዘወትር ዝግጁ የሆነውን አፋቸውን አላጣምና የጻፍኩትን ጽፌአለሁ። ሳጠቃልል ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ተሰበረ፤ ሲሉ ሞተ ብለው የሚaw,ሩ ማቆችና ደጋፊዎቻቸው ተሃድሶዎች መላእክትን፤ ጻድቃንን፤ ቅዱሳንን፤ በተለይም ቅድስት፤ንጽሕትና ብጽእት ድንግል ማርያምን የሚክዱ ናቸው፤ አያከብሯቸውም እያሉ ስም ሲያጠፉ ይውላሉ። በዚህ ዙሪያ እግዚአብሔር የፈቀደውን ያህል ለመጻፍ እሞክራለሁ። «እናትህንና አባትህን አክብር» «ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ» ያለ እግዚአብሔርን እናመልካለን እያልን ክብር ለሚገባው ክብር እንደማንሰጥ አድርጎ ማሰብና ሰውን ማሳሳት ኃጢአት ነው። የእኛ ጥያቄ እግዚአብሔር ያከበራቸውን እናክብራቸው፤ ግን የሰውን ክብር ለእግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔርን ክብር ለሰው አንስጥ ነው። የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስ ሳንሰራበት ያልተሰጠውንና የማይታወቀውን ይልቁንም ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጋጨውን እንድናነብ አታስገድዱ ነው የምንለው። ድንግል ማርያም ርኅርኅት ናት፤ ርኅርኅናዋ ግን ከክርስቶስ አይበልጥም። ምክንያቱም በፍቅሩ ሞቶ ያዳነን ክርስቶስ እንጂ እናቱ አይደለችም። ማርያምን ርኅርኅት፤ ክርስቶስን ጨካኝ የሚያደርግ አንድም ቀን ታጉሎ የማያውቅ ዘወትር በቤተክርስቲያን ለ500 ዓመታት ሲጮህ የቆየው የውዳሴ ማርያም መርገፍ «ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ያድኅነነ እመዓተ ወልዳ» የሚባለው ነው። ትርጉሙ « የማርያም ጸሎትና ልመና ከልጇ(ከኢየሱስ) ቁጣ ያድነን» ማለት ነው። እንዴት ሆኖ ነው 500 ዓመት ሙሉ ክርስቶስ ሲቆጣንና መዓት ሲያወርድብን እንደኖረ የምናስበው? ችግር ሲመጣ የሚለመን ነው እንዳይባል ይሄ አንድም ቀን ሲመሽና ሲነጋ ተቋርጦ አያውቅም።በፋሲካ ሆነ በልደት፤ በፍልሰታ ሆነ በበዓታ፤ በደስታ ሆነ በእልልታ የክርስቶስ ሥራ እኛን መቅጣት፤ ማርያም ግን ይቅር ማለት ምን የሚሉት ነገር ነው። ማርያምም ይህንን ብትሰማ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ትላለች እንደምትል አይጠረጠርም።

  ReplyDelete
 6. ጥላቻ፡ድንቁርናን፡ያመጣል፣ምስጢርን፡ይሰውራል፡፡አንተም፡ዲያቢሎስ፡በጥላቻ፡ስለሞላህ፡የመጻሕፍትን፡ትርጉም፡ወይም፡ምስጢር፡ረጋ፡ብለህ፡መመርመር፡ ወይም፡መገንዘብ፡አትችልም፡፡የተቀደሰው፡ደግሞ፡ለቅዱሳን፡ነው፡የሚሰጠው፡፡ ይሄን፡ስል፡ቅዱስ፡ነኝ፡ለማለት፡አይደለም፡፡ቸሩ፡አምላክ፡ይግለጽልህ፡ይቅር፡ ይበልህ፡፡

  ReplyDelete
 7. አየ ማህበረ ከርስቲያን\| ስማችሁን በጣም እየቀያየራችሁም ብትመጡ ያው የማቅ ቡችሎች እንደመሆናችሁ በጥላቻና በድንቁርናችሁ እናውቃችኃለን። ለማቅም ሆነ ለገብረ አበሮቻቸው የሚሆን ትክክለኛ አገላለፅ ሰጥተህ ፤ እግዚአብሔር
  ባወቀ ደግሞ ባንተ ላይ ያለውን አንተ አልክ።ክክክክክክክክክክክክክክክክክክክክክኪኪኪኪኪኪ ኪኪኪኪኪኪኪኪ

  ውልህ ያለባችሁ የእውነት ጥላቻና ድንቁርና ምንም ሚስጥር ሊገልፅላችሁ አይችልም። ለእናንተ ምናልባት የተገለፀላችሁ መስሎአችሁ ከሆነ ፤ ዲያቢሎስ በእባብ ተመስሎ ለሄዋን ሚስጥር የገለፀላት መስሎ እፀ በለሱን ብትበሉ እኮ አይናችሁ ተገልጦ እንደ ግዚአብሔር አዋቂ ትሆኑ ነበር አላት እሱዋም የእባቡንና የሰይጣንን ምክር ሰምታ ለራሱዋም በላች
  አዳምም አበላች።

  በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደጣሱና ሰይጣን እንዳታለላቸው አይናቸው ተከፍቶ አዩ። ሰይጣንም ይህንን
  አይቶ በጣም ተደሰተ። እነርሱም በጣም ፈርተው ተደበቁ፣ ቀድሞውንም የእግዚአብሔርን ቃል ቢያከብሩና ለአስመሳዩ ሰይጣን ደግሞ ባይታለሉ ጥሩ ነበር ፤የሆነው ሆኖ ምሳሌው ከገባን ይህን ይመስላል ፤ እራሱን ማቅ እያለ የሚጠራው የሰይጣን ድርጅት በምዕመናንና በክርስቲያኖች ላይ ከሰይጣኑ ሥራ ያልተናነሰ ነገር እየሰራ ይገኛል። ጥላቻና ድንቁርናም እውነተኛውን እግዚአብሔርን ሊገልፅለት አልቻለም። አንድ ቀን ግን በቅርቡ አለቃችሁ ዲያቢሎስን ማቅ እንደ አዳምና ሄዋን ፀጋችሁን ያስገፍፍና ከሩቁ ቆሞ ይስቅባችኃል። በማታውቁት ነገር አዋቂ አድርጎ ሲያሳያችሁ የነበረውን ሁሉ አይናችሁ ተከፈቶ ታያላችሁ። ያን ጊዜ ግን የጥርስ መፋጨት ብቻ ይሆናል። ከዚያማ ተወኝ ምን ልበልህ መቀባጠር ብቻ፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
  በማህበረ እከሌ ፣ በማህበረ እከሌ ፣ በሰንበት ት\ቤት ና እንዲሁም በተለያየ ሥም ብትመጡም እናውቃችኃለን ያው
  አላማው ጥፋት የሆነው ማቅ ነው።
  እግዚአብሔር ማስተዋሉን እንደ ተስፋ አዲስ ይስጣችሁ። አሜን።

  ReplyDelete
 8. እኔ እኮ ግርም ይለኛል። ምኑ ትሉኝ ይሆናል ፡ እንደው ሁል ጊዜ ግርም ይለኛል። እንደው ምንድነው እሱ እያላችሁ
  ነው አይደል\ የቤተክርስቲያናችንን ነገር ሳስበው ነዋ። እንደው ምን ተፈጥሮ ነው እንደዚህ የሚያባላን\ ይኼ ሁሉ
  -------------- ሽኩቻ፣ ይኼ ሁሉ ሽብር፣ ይኼ ሁሉ ጥላቻ፣ ይኼ ሁሉ ግርግር፣ ይኼ ሁሉ አድማ፣ ይኼ ሁሉ ንዴት፣
  ይኼ ሁሉ ጦርነት፣ እረ ስንቱ፤ እንደው ዝም ብላችሁ ብታስተውሉት እኮ እዚህ ሁሉ የሚያደርስ ከባድ ነገር እኮ
  የለም። እንደው ብቻ ፈርዶብን የትንቢት መፈፀሚያ ሊያደርገን የተመረጥን ህዝቦች ሆነን ይሆን\ ያውም ለአንድ
  ቤተክርስቲያን የምንሠራ፣ በአንድ አምላክ የምናምን፣ አንዲት ሐይማኖት ያለን፣፣ ባንዲት ጥምቀት የምናምን፣
  አንድ እርስት የምንወርስ፤ ሆነን ሳለን እንዲህ ዝብርቅርቃችን የወጣ ለምን ይሆን እያልኩ ዘወትር አስባለሁ።

  በመጨረሻም አንድ ነገር በኃሳቤ መጣ። አገራችን እኔ ነፍስ ካወቅሁበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ
  1982 ድረስ ኢትዮጵያ ነበርኩ፣ በቤተክርስቲያንም የነቃ ተሳትፎ ነበረኝ። በተለይም በደርግ ጊዜ ወጣቱ
  የነበረውን የማርክስና የሌኒን ፍልስፍና መከተል አለበት ተብሎ ጫና ሲደረግብን የነበረው ትዝ አለኝ። ነገር ግን
  ያን ጊዜ እንኩአን የቤተክስቲያን አባቶች ሊጣሉ ቀርቶ በአመለካከት እንኩአን የምንለያይ ወጣቶች አንድም ቀን
  በሐይማኖትም ሆነ በምንም ነገር ተጣልተን አናውቅም። ያውም የሐይማኖት ነፃነት እንዳሁኑ ባለነበረበት ሰዓት።
  ከ16 ዓመት ወዲህ ግን ቀስ በቀስ ሰይጣን በጥቅምና በፖለቲካ የተያያዘ ማህበር በቤተክርስቲያኑ ውስጥ አቁዋቁሞ
  ከሥር ጀምሮ ቅንቅን መልቀቅ ጀመረ። ያም ቅንቅን የሰዎችን አይምሮ እየበላና አየተባዛ ክርስቲያኑን መከፋፈል
  ጀመረ፤ ከዚያም ውስጥ ውስጡን ሳይታወቅ ካንሰር እንደሚሰራጨው ሁሉ አባቶችን ከአባቶች፣ ወንድሞችን ከወድሞች፣
  ሰንበት ት\ቤቶችን ከሰንበት ት\ቤት፣ ካንሰሩ መብላት ጀመረ። ሰይጣንም የሥራውን ውጤት እያየ ሲመጣ ሞቅ
  እያለውና እየታበየ መጣ። ሁሉንም አነካካና ሥልጣን ሁሉ ከእግዚአብሔር መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰይጣን
  አቡነ ጳውሎስን በማህበሩ ላይ አድሮ ጠዋት ማታ ይፈታተናቸው ገባ ፣ እግዚአብሔር ደግሞ አዋቂ ነውና ከፅናትም
  ፅናት ከብርታትም ብርታት እየሰጣቸው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከፍ ከፍ እያሉ መጡ፣ በእርግጥም የማንክደው ነገር
  ቢኖር አቡነ ጳውሎስ በጣም የተማሩ ሊቅ ናቸው። ነገር ግን የኛ ህዝብ የኖረው ና የሚያውቀው ባካባቢው ያለችውን የተወሰነች ነገር እንጂ ሰፋ ያለ አመለካከት ያለነበረው መሆኑን እናውቃለን። በተለይም በቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ
  ሊቃውንት አንድም እንኩአ እንደ አቡነ ጳውሎስ ያለ የተማረ ሰው አልነበረም፤ ከአቡነ ቴዎፍሎስ በቀር።

  ያም ሆነ ይህ ከላይ ለጠየቅሁት ጥያቄና ለሚገርመኝ ነገር መልስ ያገኘሁ ስለሆነ በመንፈሳዊ ህይወቴ ፀንቼ እንድኖር
  እግዚአብሔር አስተምሮኛል። ማህበሩ ግን ያልሆነውን ሆነ፣ ያልተፈጠረውን ተፈጠረ፣ ነጩን ጥቁር፣ ጥቁሩን ነጭ
  እያደረገ፣ ነጠላ ለብሶ መንደር ለመንደር እየተሽሎከለከ አባቶችን ከአባቶች፣ ወጣቶቹን ከአባቶች፣ እያናኮረ እንዲሁ
  ወለም ዘለም እያለ እዚህ የደረሰው ማቅ ነው። በመጨረሻው ዘመን ፍቅር ትቀዘቅዛለች የተባለው ትንቢት በኛ ላይ
  እየተፈፀመ ነው። እባካችሁ ወገኖቼ አሁን ሰማንያ በመቶ ያህል ህዝብ በሽታውን አውቆታል ስለዚህ መድሐኒቱ ፍቅር
  ነውና በፍቅር ሆነን ሁሉን እንችላለን። ደግሞም ክርስቲያን ዘረኛ አይደለም። ከርስቶስ እኮ የሞተው ለአለም ህዝብ
  ሁሉ ነው። አቡነ ጳውሎስን ለቀቅ፣ ፍቅርን ጠበቅ አድርጉ።

  እግዚአብሔር ፍቅር ነውና
  እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ብቻ እንድርግ።

  ReplyDelete
 9. You call yourself Orthodox Tewahdo. I really don't think so. Shame on you.

  ReplyDelete
 10. አሁን በምድሪቱ የሚታየው መዓት፤ጦርነት፤ድርቅ ወዘተ የሚመጣው በማን አማካኝነት ነው?በድንግል ማርያም ወይስ በክርስቶስ?በኃጢያታችን ምክንያት የመጣውን የሚመጣዉን አስቀድሞ በርስዋ ምልጃ በጸሎት መጠየቅ ምኑ ነው ክፋቱ አንተ ተሀድሶ?ማቅ ድንግል ተሰቅላለች፤የርስዋ ርኅራኀ ይበትጣል ሲል የት ነው የሰማሃው?ቀጣፊ ስለሆናችሁ እየጨማመራችሁ ታታልላላችሁ።አወቅሽ አወቅች ሲልዋት መጽሀፍ አጠበች እንደተባለው እናንተ ትልቅ ጥላቻ ስላላችሁ የኦርቶዶክስን መጻሕፍት ታጥባላችሁ(አጥባችሁ ለማጥፋት ትሞክራላችሁ) ግን አይሳካላችሁም።

  ReplyDelete
 11. ebacachihu zim belu amlak yiferdal.

  ReplyDelete
 12. የሚረዳኝ ሚካኤል መጣ

  ReplyDelete
 13. Betebit Bekidusan lay Yeminager Andebet DIDA yihun

  ReplyDelete
 14. afere bela asetemerehe motehal. mane lesemahe tefegalehe dyabelose yedyabelose welaje

  ReplyDelete
 15. aderashahen aweta mane endehonkeme atedebeke.feri yehasete yrmhertehen zera yemikebelehe gen atagegem

  ReplyDelete
 16. i think we need to know the truth rather than hiding the fact, that would revealed ....over time. indeed many of the books are controversial each other . this was not the orthodox teaching what was thought by our elders or forefathers.
  please guys watch out. why we do not try to defend from the holy scripture. why do not try to show us by saying what was being written about DERSANE MICHAEL is wrong because the holy scripture endorse its idea. so and so forth. however, if your response is insulting what i could understand is you are still under the yoke of devil the father of lie. please give us some defiant words based on your knowledge. i suppose gone are the days to disguise fellowships any more if we are not able to give adequate reply from the holy scripture.we are all under one umbrella(orthodox) but in no circumstances we could spill out the truth. or support the deeds of devil(accusing brothers and sisters ) with out having substantial reason. yes one think is loud and clear many of the ecclesiastical books stand against the holy bible. but how are we expelled them out. how long will remain silent? some of the words are so embarrassing. read through the hagiography of Tekelehaimanot. i would not repeat it here again.eventually i would say let us try to play our roll in this regard. never stop revealing the truth. the time has come .........to stand shoulder to shoulder to fight the deeds of our enemy devil.
  glory to almighty God.

  ReplyDelete
 17. Betebit Be kidusan lay yeminager andebet DEDA yehonal
  Kale hiwot yasemalen

  ReplyDelete
 18. Hey,
  you look great on your analysis but still you lack the core. You tried to convince by your literal interpretation. First of all pick the pictures of the true fathers you posted as disguise to be judged as the true hero.
  I knew well Aba Melketsadik, Aba Gorgorious all the rest you posted but they have no any connection with your Agenda. They tried to teach the true way but because there are 'sorgogebs' like you no body heard them even mahbere Kidusan, but still they never get offend because they knew that some are working hard for the sake of our church. They want to exercise as our forefathers did long long time ago. Unfortunately, Nasty 'Hodamoch' like Tehadiso confused all changing their colors like chameleon.
  I understand that politicians joined Mahbere kiqusan through their hidden Agenda and attacked every innocent people who are fighting for true salivation in our church.
  I think you are one of them. If you were not, you shouldn’t write accusing on public the church doctrine and fathers without shame. Those issues you mentioned were able to be corrected inside the church. That was the responsibility of the church fathers not ordinary people like you. Besides we all know that the help of St Michael or St. Gabriel is not due to the script we read but we all exercised through our life. So what? Did you save yourself by writing this? Don’t twist yourself rather pray crying to understand the true confession. I knew my people run to our church when we are in trouble but when we feel we are ok just we would like to act as an outsider.
  There might be some manmade problems in the church that can be corrected through time without our knowledge. As far it doesn’t affect your salvation. Our forefather did a lot of great things through their belief. Go back to the beginning what St. Yared was enjoying while others were still running naked. St. Yared was running from Axum to Gondar and vise versa teaching with guide of the holy spirit. While the western where still looking for the True God, our fathers were enjoying with grace and Holy Spirit. They never run for accusation. They resolve issues inside with ‘Armimo’ not exposing to outsiders. You Gossip the church and act like the true hero. Aba melketsadik never complain infront of the outsiders or in front of others who are ignorant to the church though accused wrongly. They never worry about their name while they are accused throughout their life but for the Dignity of the True God. I knew that they are hardliner but it is for good.
  I knew a lot of tehadiso finding shelter like you but soon things will change God will reveal the true path and Mahbere kidusan will find the true members as before who were working for the church from the bottom of their heart.

  ReplyDelete
 19. Kegna gar neberk 40wen zemen,
  Enterahalen Michael belen!


  ReplyDelete
 20. Emebetay Mariam ena melaku Kidus Michael endayqotu ferahugn....

  ReplyDelete
 21. This page aba selama is very tplf mafia cadres page which rejects all and its main aim is to bring confusion and hate among the tribes forget it i wish i cancel the page from web which is no use ppl open ur eyes

  ReplyDelete
 22. It is so sad. Please refer to the Holy Book Mathew 24. It all tells us about such cheaters. They are well financed by the Devil agents. They do not see ahead about the life they will face after death. Such a finance will not help them by then. They are barking like dogs for their lords (the Devil and Illuminati community). I wonder how dare they use such bold words on such Sacred angels and Kidusan Abatoch! HErodes has felt he could kill Jesus Christ. When the time comes, he has fallen down. Truth always prevails. Their will be time again for such betrayals to drop their heads down. May St. May bless our country, our people and our sacred Religion - Orthodox Tewahdo. May St. Michael help us get the mercy of the Almighty - God. May the Trinity protects us all from such evil missonaries!

  ReplyDelete