Tuesday, November 8, 2011

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ የሆኑት አባ ፊልጶስ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ - - - Read PDF

የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ በመሆን የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ማኅበረ ቅዱሳን እንዳሻው እንዲፈነጭበት ሲያደርጉ የነበሩት፣ በዋና ሥራ አስኪያጅነት ዘመናቸው የእኅታቸውን ልጅ ጨምሮ 60 ያህል የራሳቸውን ሰዎች በዘመድ አዝማድ መንገድ የቀጠሩት፣ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ለከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ ዋና ቡራኬ ሰጪ የነበሩትና መፈንቅለ ፓትርያርክ የሚያሤረው የአነአባ ገብርኤል ቡድን አባል የሆኑት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ አባ ፊልጶስ በዋና ሥራ አስኪያጅነቱ አልሠራም ሲሉ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መልቀቂያ አስገቡ፡፡

አባ ፊልጶስ መልቀቂያውን ያስገቡት አባ ሠረቀ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸውን በመቃወም እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ በመጀመሪያ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እንዲነሡ ግፊት ሲያደርጉ ከነበሩት ሰዎች አንዱ አባ ፊልጶስ መሆናቸው ሲታወቅ፣ “ከዚያ ይልቀቁ እንጂ የምክትል ሥራ አስኪያጅነቱን ቦታም ቢሆን እንሰጣቸዋልን” ሲሉ እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች፣ ከዚያ እንዲለቁ ከተወሰነ በኋላ ግን አባ ሠረቀ የሃይማኖት ችግር አለባቸው የሚለው ነገር ከሕዝብ ሊያጣለን ስለሚችል የእርሳቸው ጉዳይ ይቆይ ብለው ነገር በመሥራት ፓትርያርኩን ያሳመኑ መሆናቸውን ለማኅበረ ቅዱሰን ልሳን ለደጀ ሰላም መረጃ ሰጥተው ደጀሰላምና ወንድሞቹ ገብር ሄርና አንድ አድርገን ድረ ገጾች “አባ ሰረቀ ከሹመት ታግደው ይቆያሉ፤” የሚል ያልተረጋገጠ ወሬ በሰበር ዜና ስም ሲያናፍሱ ነበር፡፡

ከዚያ አባ ፊልጶስ በራሳቸው ፊርማ ባረሩት ደብዳቤ የምክትል ሥራ አስኪያጅነቱን ቦታ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ለነበሩት ለአባ ገብረ ማርያም ጽፈው ሰጥተዋል፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ከተባለው ውጪ የተሠራውን ይህን ምደባ በመሻር አባ ሠረቀ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋቸዋል፡፡ በዚህ ያልተደሰቱትና የማኅበረ ቅዱሳን ሐሳብ ባለመፈጸሙ የተበሳጩት አባ ፊልጶስ ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ትናንት ለፓትርያርኩ አስገብተዋል፡፡ በደብዳቤው ገለጹት የተባለው ምክንያት “የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅን የሚሾመው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው እንጂ እርስዎ አይደሉም፤ አባ ሠረቀ የሃይማኖት ችግር ስላለባቸው ከእርሳቸው ጋር አልሠራም” የሚል እንደሆነ ምንጮቻችን ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና አባ ገብረ ማርያም የተሾሙት ያለ ሲኖዶስ ውሳኔ በአባ ፊልጶስ ደብዳቤ መሆኑ ሕጉ ለአባ ፊልጶስስ እንዴት ሠራላቸው የሚል ጥያቄን አስነሥቷል፡፡

ከዚህ ሁሉ በስተጀርባ ያለው ግን ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነና አንዳንድ የማኅበሩ አባላትና ቀኝ እጅ የሆኑት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት እንዲሠሩ በአባ ፊልጶስ በሕገ ወጥ መንገድ የተቀጠሩት ልዑል ሰገድ፣ በእምነትና ጽጌረዳ የተባሉት ሰዎች ከአባ ፊልጶስ ጋር ሲመክሩ እንደነበረና ከምክሩ በኋላ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አባ ፊልጶስ ደብዳቤ ያስገቡት ጫና ለመፍጠርና ውሳኔውን ለማስቀልበስ እንደሆነ የሚናገሩት ምንጮች፣ የእርሳቸው በፈቃዳቸው መነሣት የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን የሚናገሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆችም በርካቶች ናቸው፡፡ ደስታቸውንም እየገለጡ ይገኛሉ፡፡ ምክንያቱም አባ ፊልጶስ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር በእጅ አዙር ማኅበረ ቅዱሳን እንዲያዝበት ሲያደርጉ በመቆየታቸው እዚያ ቦታ ላይ መቀመጣቸው ለማኅበረ ቅዱሳን እንጂ ለቤተ ክርስቲያን አልጠቀመም፡፡
“የተኛ ቁጭ ብሎ ያየ አረገዘ” እንደ ተባለው ስንት ኑፋቄና የሥነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው እንደ አባ ሳሙኤል እያሉ ሰዎች ጉዳይ መጣራትና ውሳኔ ማግኘት ሲገባው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ሥርዐት ጠብቆ እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውን “ኑፋቄ” የሚል ሽፋን መሰጠቱና እነአባ ፊልጶስ ከአባ ሠረቀ ጋር አልሠራም ማለታቸው የማኅበረ ቅዱሳን ቅጥረኛነታቸውን በገሃድ አሳይቷል፡፡ የመልቀቂያ ደብዳቤውን እንዲያስገቡ ያደረገውም ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ሲታወቅ፣ ዐላማውም ሌላ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ግጭትና ብጥብጥ እንዲነሣ ለማድረግና በዚያ የሚገኝ ሌላ ዕድል ካለ ለመጠቀም መሆኑ ታውቋል፡፡ 

ይህ በእንዲህ እንዳለ የማኅበረ ቅዱሳኑ ዶ/ር ሙሉጌታን ጨምሮ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች በትናንትናው ዕለት ወደ አቡነ ሕዝቅኤል መጥተው “ምን እየተደረገ ነው? የባሳ ነገር እየሆነ ነው እኮ! አባ ሠረቀ እንዴት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ይሆናሉ?” ሲሉ ላሰሙት ተቃውሞ፣ አባ ሕዝቅኤል “አሁንስ አበዛችሁት! በአስተዳደሩ ጣልቃ ገብታችሁ ልታዙ ነው እንዴ ያሰባችሁት? በሉ ዘወር በሉ” ብለው ፊት እንደነሷቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

አንድ ጊዜ ከፓትርያርኩ ጋር በሌላ ጊዜ ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ነኝ እያሉ በሁለት ሐሳብ የሚያነክሱት አቡነ ጎርጎርዮስም፣ የተበተነውን የአባ ሠረቀን የሹመት ደብዳቤ አሰበስባለሁ፤ ሹመቱን አስቀለብሳለሁ በሚል ላይ ታች እያሉ መሆናቸውም ተሰምቷል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ብዙ ድል አገኝበታለሁ ብሎ ብዙ ገንዘብ ያፈሰሰበት፣ እነአባ ሳሙኤልና የእነአባ ሕዝቅኤል ቡድን ማኅበረ ቅዱሳንን ሽፋን አድርጎ የግል አጀንዳውን ለማስፈጸም በአድማ የተነሣበት፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ዳጎስ ያለ ገንዘብ የበላባቸውን አጀንዳዎች ለማስፈጸምና በሽፋንነት ለመገልገል ላይ ታች ያለበት የጥቅምት 2004 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ለቅጥረኛ ጳጳሳቱም ሆነ ለማኅበረ ቅዱሳን የሚፈለገውን ያህል ትርፍ እንዳላስገኘለት እየተነገረ ነው፡፡ ስብሰባው ሲጠናቀቅ ስብሰባው ሲጀመር የነበረው ብዙ ድንፋታና ፉከራ ረግቦና ማኅበረ ቅዱሳን ተወስኖልኛል እያለ በየድረገጾቹ ላይ ሲያራግባቸው የነበሩ ውሳኔዎች ሁሉ የእርሱ የልብ ሐሳብ እንጂ የሲኖዶስ ውሳኔዎች ሆነው አለመገኘታቸው እየተገለጸ ነው፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ልሳኖች ሆነው በማገልገል ላይ ያሉ አንዳንድ የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ለምሳሌ፣ ፍትሕ ጋዜጣ፣ ሎሚ መጽሔት፣ ቆንጆ መጽሔትና የመሳሰሉት ያስነበቧቸው ዜናዎችም፣ ማኅበሩ የፈለገው እንዳልተወሰነለት አመላክተዋል፡፡ የአባ ሠረቀን ከማደራጃ መምሪያው መነሣት ብቻ ሳይሆን አባ ሠረቀን አላሠራ ብሎ የነበረው የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሻሻል መወሰኑን ማኅበሩም ሆነ ሚዲያዎች አለማንሣታቸው በተለይ ሚዲያዎቹ ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን መቆማቸውን አመላካች ነው፡፡    

21 comments:

 1. selam aba selamawoch enkuan des yalen des yalachehu betam des yemil zena new yasemachehun ewenet hul gezim atemotem ye mahebere kidusan ( mahebere seyetan) yeweshet dejeselam sikeded EGZIABEHER gin aba serken wana bota asmedebe temesegen fetari ye betekereseteyanen lijoch menafik yemilu enesu man nachew? lemehonu gena mk tenekelo yewetal ke betkereseteyan egna tenkeren mekom aleben ke Germen weldegebreal

  ReplyDelete
 2. selam abaselama enkuan des alen hulachenn se le aba sereke

  Ribka ke Geremen abakesh niseha gibi yalebtekeresteyan serat kemender yeweledshaten lij beserat asadegi ke Germenawi baletedar kehone nech gar beserkot yemetadergiwen zimut akumi lemehonu anchi selebtekereseteyan setenageri alemafersh lengeru mahebere kidusan serachew new lib yesetachehu

  ReplyDelete
 3. ተረፈ አርዮሳውያን ሁሌም በቤተክርስቲያን ውድቀት ይደሰታሉ ነገር ግን መስዋእታቸ ሁልጊዜ እንድ ቃየል በአምላክ ፊት የተናቀ ይሆናል በምድር ላይ እንደተቅበዘበዙ ይቀራሉ ማረፊያም አገኝም

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማዎች እንደ ምን ናችሁ የምታወጡት ዜናዎች
  ጥሩ ናቸው ግን በሕይወት ያሉት የአባ ሳሙኤልን ከሞቱት
  ያባ ሚካኤልን ብቻ ሳይሆን ማንሳት ያለባችሁ የነአቡነ መለከሰዴቅን
  በሕይወት ካሉም የሌሎችን ገመና ለምን አታወጡም እውነት ካላችሁ
  ፍርድ ቤትና ቤተ ክህነት የሚከሰሱት ብዙ ናቸው ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን
  እንድትጸዳ የሁሉም ገመና መነገር አልበት ብየ አምናለሁ አለዝያ አንደ ሌላው
  ማኀበር የወዳጃችሁ ገመና የምትሸፍኑ የጠላታችሁ ገመና ብቻ የምታጋልጡ
  ከሆነ ከንቱ ናችሁ እውነት ተናገሩ እውነት ራሱ ዕግዚአብሔር ነው። እውነት
  እንድትናገሩ አምላክ ይርዳችሁ አምላ ይባርካችሁ አሜን። ይ

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማዎች እንደ ምን ናችሁ የምታወጡት ዜናዎች
  ጥሩ ናቸው ግን በሕይወት ያሉት የአባ ሳሙኤልን ከሞቱት
  ያባ ሚካኤልን ብቻ ሳይሆን ማንሳት ያለባችሁ የነአቡነ መለከሰዴቅን
  በሕይወት ካሉም የሌሎችን ገመና ለምን አታወጡም እውነት ካላችሁ
  ፍርድ ቤትና ቤተ ክህነት የሚከሰሱት ብዙ ናቸው ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን
  እንድትጸዳ የሁሉም ገመና መነገር አልበት ብየ አምናለሁ አለዝያ አንደ ሌላው
  ማኀበር የወዳጃችሁ ገመና የምትሸፍኑ የጠላታችሁ ገመና ብቻ የምታጋልጡ
  ከሆነ ከንቱ ናችሁ እውነት ተናገሩ እውነት ራሱ ዕግዚአብሔር ነው። እውነት
  እንድትናገሩ አምላክ ይርዳችሁ አምላ ይባርካችሁ አሜን። ይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርሶ የሚያውቁት እውነት ካለ ለምን አይነግሩንም። እርሶም እኮ አንዱ አባ ሰላማ ኖት። እዚህ ድር ገጽ ላይ ከመጡ ታዳሚ ኖትና የሚያውቁት እውነት ካለ ፊት ለፊት ለምን አይነግሩንም እንደ ክርስቲያን። አለበለዚያ ግን አቡነ ኢብራሂማዊ ኖት ማለት ነው። ቸር ያሰማን።

   Delete
 6. http://www.eotcssd.org/message/35-2011-02-08-21-34-46/184-blogs-for-gospel-or-crime-in-eotc.html

  This is what Abasereke has to say about Aba Selama blog.

  Administrators of this page, how do you react on this? Is he an MK now? lol

  ReplyDelete
 7. አባ ፍሊፖስ እለቃለሁ አሉ? ውይ በናትዎት እንዳይለቁ። ኪኪኪኪኪ ጥርግ ይበሉ ማን ይለምንዎት መሰለዎት?
  እግዚአብሔር ባወቀ ነው ይህንን ያሳሰበዎት። ካልደፈረሰ አይጠራምና ለገንዘብና ለፖለቲካው ማቅ የገዛቸው ሁሉ
  ተመንጥረው ይውጡልን። ዳሩ እኮ የኒያ የንፁህ መለኩሴ ግፍ ገና ምን አይታችሁ እግዚአብሔር ቤቱን ከአስመሳይ
  ክርስቲያንና ከሸቃጮች ያፀዳል። ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛ ሥራዋን እንዳትሠራ የሚበጠብጣትን ሁሉ መመንጠር
  ነው። እራሱን ከተመታ እባብ መርዙን ተፍቶ እንደሚሞት ሁሉ የእኩያን ማህበሩንም መርዙን ማስተፋት ያስፈልጋል።

  ወገኖቼ በጣም የሚገርመው ግን እነሱ የሚፈልጉት ሥራ ሲሰራና እነሱ የሚፈልጉት ሰው ሲሾም፤ አቡነ ጳውሎስን
  ሊያመሰግኑ፤ ለእነርሱ የማይመቹ የሚመስላቸውን ሥራና ሰው ሲሾም፡ አቡነ ጳውሎስን ሊሳደቡና ሊወነጅሉ ነው
  ማለት ነው? ታዲያ አባ ጳውሎስና ሌሎች ሐቀኛ አባቶች እንዴት እንዲሰሩ ነው የሚፈለገው? ማንኛውም ሰው የሚያውቀው ውሃ ከላይ ወደታች ይፈሳል እንጅ፤ ከታች ወደ ላይ አይፈስም። ለመሆኑ የአንድን ሰው ሐይማኖት የሚመረምረውና የሚያውቀው አንድ አምላክ ብቻ እንጅ ፣ ማን ስለማን መናገር ይቻላል? እንዴትስ? ለምሳሌ እኔ ካቶሊክ
  ክርስቲያን ነኝ ልበል፡ ካቶሊክ መሆኔን እኔና እግዚአብሔር ብቻ ነን የምናውቀው ነገር ግን ማንም ተነስቶ ካቶሊክ
  አይደለሽም ብሎ ሽንጡን ገትሮ ሲወነጅል ዉሎ ቢያድር ማንም አይሰማውም ምክንያቱም እምነቴን የማውቀው እኔ
  ነኝ። ይኼ በቀላሉ እንደኔ ላለው ክርስቲያን ነው ነገር ግን በታላላቅ የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት ላይ በኛ በመሐይሞች እምነታቸው ሊመረመር ቀርቶ ሊታሰብ የማይገባው ነበር። አንድ የመፅሐፍ ቀዱስ መልዕክት ትዝ አለኝ። በራስህ
  ላይ ሊደረግ የማትወደውን ነገር፤ እንዲሁ ደግሞ በሰው ላይ አታድርግ የሚለው፡ አሁን ማን ይሙት አንዱ ተነስቶ
  አንዱን የማህበረ ቅዱሳን አባልና የሥራ አመራር አንተ እንደው ሳይህ ምንህም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አትመስለኝምና ወይ ተሐድሶ ነህ ወይም ፕሮቴስታንት ነህ በሎ ድርቅ ቢልበት እንዴት ነው ማሳየት ያለበት ለኦርቶዶክስነቱ
  በመጀመሪያ የተጠረጠረው ሰው በጣም ይናደዳል፡ ምክንያቱም ተጠርጣሪው በኦርቶዶክስ የክርስትና እምነት ውስጥ
  መሆኑን ራሱ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ፤ በማያገባው ገብቶ ከጠረጠረው ሰው ጋር ፍቅር እየጠፋ ውዝግብ ይሆናል። መቼም
  ምን ለማለት እንደፈለግሁ አንባቢያን የምትረዱኝ መሰለኝ።

  ሌላው ደግሞ ከ12 ዕብዶች መካከል አንድ ጤነኛ ቢኖር ፤ ያንን ጤነኛ ሰው ማንም ሰው ጤነኛ አይመስለውም።
  ሌላው ደግሞ አንድን ሰው ሁልጊዜ ዕብድ፣ ዕብድ፣ዕብድ፣ ዕብድ፣ ቢሉት ሊያብድ ይችላል። ሰለዚህ ለምንድን ነው
  በሰው የግል ሕይወት ውስጥ እየገባን ጊዜ ስናጠፋና ሐጢያት ሥንሠራ የምንኖረው? የራሳችንን ሐይማኖት አጥብቆ
  መያዝ፤ የሌላውን ስንጎረጉር፣ ስናማ፣ ለውድቀቱ ድንጋይ ስንፈነቅልና እግዚአብሔር የማይወደውን ነገር ስናደርግ
  ለራሳችን ግን ምንም ሳናተርፍ ያ ሞት ይመጣና ይወስደናል ከዚያ በሥጋም በነፍስም ሁለቱንም ሞት እንሞታለን።

  ሐይማኖት የግል ነው አገር የጋራ ነው ይባል የለ ትክክል ነው።

  እኔም ወቀሳ አብዝቼ ከሆነ ይቅር በሉኝ።
  እስቲ ቀና እንሁን።
  ወስበሐት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 8. ለማኅበረ ቅዱሳን ያደሩ ሊቃነ ጳጳሳት ከማኅበሩ እሥራት ነፃ ይወጡ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡

  ReplyDelete
 9. ማኅበረ ቅዱሳን ተወስኖልኛል እያለ በየድረገጾቹ ላይ ሲያራግባቸው የነበሩ ውሳኔዎች

  በማህበረ ቅዱሳን ድረ-ገጽ ላይ ስለዚህ ነገር የሚናገር አላነበብሁም
  ምነው ምነው ታዴ(ተሃድሶ) እደዚህ ይዋሻል እንዴ

  ReplyDelete
 10. ምነው ማህበረ ቅዱሳን የሚባል ቡዳ በልቷችኋል እንዴ? በዚህ ጽሁፍ እንኳን 22 ጊዜ ጠርታችሁታል፡፡ ጻዕ ርኩስ መንፈስ፡፡

  ReplyDelete
 11. please le ewunet kumu eske meche eyewashachihu tinoralachihu be Egziabiher zend yasteyikachuhal

  ReplyDelete
 12. Aba Serke is an effective leader. Congradulation!

  ReplyDelete
 13. Debdabew lemin endasgeb tawkalachw አባ ሠረቀ ተሃድሶ የሆነ ተሃድሶ እንዲፈነጭበት ሲያደርጉ የነበሩ ቅጥረኛ ነው፡፡ VIVA MK MK ማኅበረ ቅዱሳንን ሲታወቅ ...... አባ ሰረቀ ከሹመት ታግደው ይቆያሉ

  ReplyDelete
 14. always, you talk about religion. why don't you talk about Jesus.you talk about this bishop that bishop's sin. please don't talk about religion through out your life. any one of religion can save but Jesus. always you talk about the for father of course, some of their footprints are good and good example. Jesus foot prints is more than any of them. so, why don't we talk and meditate his word rather than human life.
  yours woldsilase

  ReplyDelete
 15. እነ ዶር ሙሉገታ ደግሞ ምን ቤት ናቸው? የማህበራቸውን ሕግም ጠንቀቀው አያወቁትም አሁንስ ዱክትርና እኮ ድንቁርና እየሆነ መጣ መሰለኝ። ማህበራችሁ እኮ "በቤተክርስቲያኗ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ አንገባም" የሚል መተዳደሪያ አለው። ለናንተ አጥፊ ዓላማ ያላጎበደደ ሁሉ ከዚህች ቤተክርስቲያን መባረር አለበት እንዴ? ኦርቶዶክሳዊ እምነታችን እኮ የ2000 ዓመት ዕድሜ ያላት፣ እናንተ እና እኔ ሳንፈጠር የነበረች፣ ዛሬ እናንተ ብታምሷትም የማትሞት፣ ለያጠፏት የመጡትን ሁሉ አጥፍታ የምትኖር ነች። ክርስትና በዱክትርና እኮ አይደለም የተሰበረ ልብ ተይዞ እንጂ። ዶር ነኝና የፈለግሁት ይሁን በማለት አይሆንም። እባካችሁ ማህበረ ቅዱሳኖች ካህናቶችን እንተዋቸው እነርሱም እኮ ለሙያቸው ዶክተሮች ናቸው። ሰባት ቀናት ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው የሚያገለግሉትን ካህናት ቢሮ ተቀምጠን እየዋልን በትርፍ ሰአታችን የምንፈልገው ብቻ እንዲሆን ቡራ ከረዮ ማለት ምንኛ የዲያብሎስ መጫወቻ መሆናችሁን የሚያሳይ እንጂ የጌታ ልጆችማ ብትሆኑ ለናንተ የማይመች የመሰላችሁ ሰው ስልጣን ላይ ቢወጣ እንኳን እስኪ የእግዚአብሄር ፈቃድ ይፈጸም ብላችሁ ለእግዚአብሔርና ለመንፈስ ቅዱስ ጊዜ ትሰጡ ነበር። እኔ ልንገራችሁ ኦርቶዶክሳዊት እምነታችን እና ቤተክርስቲያኖቻችን በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የታጠሩ ስለሆነ ዲያብሎስ እናንተን እየጋለበ የፈለገውን ቢጥር ጥንትም ለነጉዲትና ለግራኝ ያልተበገረች ቤተክርስቲያናችን ዛሬም በኛ ዘመን በኛ ኃይል ሳይሆን በመድኃኔዓለም እርዳታና ኃይል ሃሳባችሁ እንደማይሳካ እወቁት። እንኳን ቤተክርስቲያናችንን በረት የሚሉትን እነ አቡነ ኢብራሂምን (አብርሃም) ይዛችሁ ቀርቶ እንዲሁም አይሆንላችሁምና ሳታውቁ በስህተት አውቃችሁ በድፍረት ከምትሰሩት ስህተት ብትመለሱ መልካም ነው አምላካችን ምህረቱ ብዙ ታጋሽነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ቢሆንም ቤቱን ስታጠፉበት ግን ዝም ብሎ የሚያይ እንዳይመስላችሁ አና እነዶክተር አባካችሁ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ እየገባችሁ አትፈትፍቱ። ቸር ያሰማን።

  ReplyDelete
 16. Hey! I just wish to give a huge thumbs up for the great data you could have here on this
  post. I shall be coming again to your weblog for extra soon.  Here is my homepage; 排名優化

  ReplyDelete
 17. Whats up! I simply want to give a huge thumbs up for
  the nice information you could have right here on this post.

  I will probably be coming back to your blog for more soon.


  Take a look at my web page; semikolon photo albums uk

  ReplyDelete
 18. Hiya! I simply wish to give an enormous thumbs up for the good info
  you might have here on this post. I can be coming back to your
  blog for more soon.

  Take a look at my web-site: yonghwa and seohyun we got married last episode eng sub

  ReplyDelete
 19. Hey! I simply want to give an enormous thumbs up for the nice info you’ve got here on
  this post. I will be coming again to your weblog for extra
  soon.

  Review my web-site ... yongsan gu seoul korea postal code

  ReplyDelete
 20. Good day! I just would like to give a huge thumbs up for the nice info you could have right here on this post.
  I shall be coming again to your weblog for more soon.


  my web page fecha semana santa 2013 puerto rico

  ReplyDelete