Wednesday, November 9, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን የይሁዳ የግብር ልጅ - - - Read PDF

አሁን የምንገኘው በወርኀ ጽጌ መገባደጃ ላይ ነው፡፡ ወቅቱ በቤተ ክርስቲያናችን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስና የቅድስት እናቱ ስደት በማኅሌት የሚዘከርበት ጊዜ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ መሠረት ደግሞ ስምንተኛው የጾም ወቅት ነው፤ - የጽጌ ጾም፡፡ ታዲያ በወርኀ ጽጌ ማኅበረ ቅዱሳንን የይሁዳ የግብር ልጅ ማለት ለምን አስፈለገ? ቢሉ ምላሹን ከሚቀጥለው አንቀጽ ጀምሮ ሲያነቡ ያገኙታል፡፡

ጌታን ለሠላሳ ብር አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ በፍቅረ ንዋይ ከመስከሩ የተነሣ ነገሮችን ሁሉ የሚያሰላው አገኘዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ትርፍ አንጻር ብቻ ነበር፡፡ ማርያም የተባለች ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ጥሩ የናርዶስ ሽቱ ወስዳ የኢየሱስን እግር በቀባች ጊዜ፣ ይሁዳ “ይህ ሽቱ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ያልተሰጠ ስለ ምን ነው? አለ።” ይህን ያለበትን ምክንያት ወንጌላዊ ዮሐንስ ሲያብራራ፣ “ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።” ይላል (ዮሐ. 12፥1-6)፡፡

ቤተ ክርስቲያናችንን እያወከ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳንም ለቤተ ክርስቲያናችን ያሰበ፣ ላባህሏና ለሥርዐቷ የተቆረቆረ በመምሰል በልዩ ልዩ ስልቶች የራሱን ጥቅም እያስከበረ ይገኛል፡፡ ጥቅም የሚያስገኝለት ሆኖ እስከ ተገኘ ድረስም የቤተ ክርስቲያንን ቀኖናና ሥርዐት ከመጣስ ወይም ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ቀኖናዎችን በይሁዳዊ ስልት ከማሻሻል ወደ ኋላ እንደማይል ከዚህ ቀደም የፈጸማቸው የቀኖና ጥሰቶች ምስክሮች ናቸው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳን የጣሰውን አንድ ቀኖና እና ቀኖናውን የጣሰበትን ምክንያት ከነይሁዳዊ ስልቱ እናቀርባለን፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቀኖናዋ የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሏት፡፡ ከሰባቱ ውጪ በቀኖናዋ ውስጥ እንዲጾም ያልተቀነነና በልማድ ጾመ ጽጌ የሚባል ወቅት አለ፡፡ ወርኀ ጽጌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ጋር መሰደዱ የሚታሰብበት ወቅት ሲሆን ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ድረስ ያለው ጊዜ ነው ወርኀ ጽጌ የሚባለው፡፡ በዚህ ወቅት ማኅሌተ ጽጌ እና ሰቈቃወ ድንግል በተባሉ ድርሰቶች አማካይነት በየወርኀዊና ዓመታዊ  እንዲሁም በየእሑዱ ማኅሌት ይቆማል፤ ቀሳውስትም ተራ ገብተው የንስሓ ልጆቻቸውን በማስተባበር ድግስ እያስደገሱ በማሕሌት ሲያገለግሉ ያደሩትን አገልጋዮች ያበላሉ፤ የሚበላውም የፍስክ ምግብ ነው፡፡ ከረቡዕና ከአርብ በቀር ቅዳሴ የሚቀደሰው በጥዋት ነው፡፡ ይህም የኖረ ሥርዐት ወርኀ ጽጌ የጾም ወቅት አለመሆኑን ያስረዳል፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በወርኀ ጽጌ የሚጾሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይም ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ ያላቸው ወጣቶችና ሌሎችም ወርኀ ጽጌን እንደ አንድ ጾም መጾም ጀምረዋል፡፡ ይህን ጅምር ለማሣመር ይመስላል ማኅበረ ቅዱሳን ቀደም ብሎ በ1987 የነሐሴ ዕትም ሐመር መጽሔት ላይ፣ የ1988 ዓ.ም. አጽዋማትን ይዞ በወጣው ፖስት ካርድ ላይ በተራ ቁጥር 8 ጾመ ጽጌ መስከረም 26 ይጀመራል ብሎ የጠቀሰው፡፡ በጊዜው ማኅበሩ ለፈጸመው ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የመጣስ ተግባር አስቸኳይ እርምት እንዲሰጥና ለወደ ፊቱ እንዲህ ያለ ስሕተት እንዳይፈጽም የኅትመት ውጤቶቹን በጊዜው በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ እያሳየ እንዲያወጣ በቁጥር 6738/8513/87 በቀን 2/13/87 በተጻፈ ደብዳቤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መመሪያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበሩ በጉዳዩ ላይ የወሰደው የእርምት እርምጃ ካለመኖሩም በላይ ጾሙ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረገ ይገኛል፡፡

መቼም እዚህ ላይ “ታዲያ አብዝተን ብንጾም ምንድን ነው ችግሩ? ደግሞም ደብዳቤው ጽጌ ጾም የፈቃድ ጾም ነው ብሏልና በፈቃዳችን ብንጾም እንደ ስሕተት ለምን ይቆጠራል” የሚሉ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እርግጥ ማኅበረ ቅዱሳንም ቢጠየቅ ሊል የሚችለው ከዚህ ያለፈ አይሆንም፡፡ "አድልዉ ለጾም" (ለጾም አድሉ) የሚለውን ኅሊናዊ ብይን ሊጠቅስም ይችላል፡፡

ነገር ግን ማኅበሩ ይህን ጾም 8ኛ ጾም አድርጎ በግሉ ማወጅ፣ መጻፍና ማሠራጨት ለምን አስፈለገው? ጉዳዩ አስፈላጊ ከሆነስ ለምን ቅዱስ ሲኖዶስ እንዲመክርበት አላደረገም? ነው ወይስ ከዚህ ጾም የሚገኝ ሌላ ጥቅም ኖሮ ነው እንዲህ ያደረገው? ምናልባትስ ይህቺ ይሁዳዊ ስልቱ ትሆን?

ይሁዳ ስለ ሽቶው “መባከን” ሲናገር ራሱን ለድኾች አሳቢ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ እውነታው ግን ከሽቶው ሽያጭ የሚያገኘውን ትርፍ በማስላት ያቀረበው የጥቅም ክርክር እንጂ ለድኾች በማሰብ የሰነዘረው በጎ አስተያየት አይደለም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳንም አጽዋማታችን 8 ናቸው ሲል፣ ለሌሎች አድልዉ ለጾምን የያዘ ይመስላል፤ ስለዚህ "አብዝተን እንጹም ባለ ስለ ምን ይወቀሣል?" የሚሉ ቀና ደጋፊዎችንም ሊያተርፍበት ይችላል፡፡ እኛ እንደ ደረስንበት ግን፣ ማኅበረ ቅዱሳን የአጽዋማቱን ቁጥር 8 ያደረሰው ለጾም አድልቶ አይደለም፡፡ በጾሙ ሰበብ የሚገኝ ከቀረጥ ነጻ የሆነ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ መንግሥትና ሕዝብ የማያውቁት ዳጎስ ያለ ትርፍ ስላለው ነው፡፡ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? የሚል ካለ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን እውነታ በጽሞና ያንብብና ኅሊናዊ ፍርድ ይስጥ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን መሠረት ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ማለትም አባላቱ በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ማኅበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ወደነዚህ የትምህርት ተቋማት ሲገቡ ቶሎ በማጥመድ የእርሱ ተከታዮች ያደርጋቸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲ በሚኖራቸው ቆይታም በተረታተረት አእምሮአቸውን ጥቅጥቆ ፍጹም ፈሪሳውያን አድርጎ በአርኣያውና በአምሳሉ ይቀርጻቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ካወጀቻቸው አጽዋማት በተጨማሪ በራሱ ፈቃድ ለጥቅሙ ሲል የጨመረውን የጽጌ ጾምም እንዲጾሙ ያደርጋል፡፡ የዋሃን ተማሪዎችም ለጽድቅ አደላን ብለው ጾሙን ይጾማሉ፡፡ ከጀርባ የሚፈጸምባቸውን ዘረፋ ግን ቆይተው እንጂ ወዲያው አይገነዘቡትም፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፤ የማኅበረ ቅዱሳን ተከታይ የሆኑ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች በሚጾሙበት ወቅት በመመገቢያ ካርዳቸው ላይ "የግቢ ጉባኤ" የሚል የማኅበሩ ማኅተም ይታተምበታል፡፡ ማኅተሙን በካርዳቸው ላይ ያተመላቸውን ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይዞ በመሄድ ከዩኒቨርሲቲው የምግብ ዝግጅት ኀላፊዎች ጋር በመመሳጠር ማኅበሩ የምግብ በጀቱ ወጪ እንደ ተደረገ አስቆጥሮ ለእርሱ 75% ለተባበሩት ኀላፊዎች ደግሞ 25% ይካፈላሉ፡፡

ጾም በሚሆንበት ወቅት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሆኑት ተማሪዎች ሁሉ ቁርስ አይበሉም፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ዩኒቨርሲቲን ብንወስድ፣ 20 ሺህ ያህል ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ይኖራሉ ቢባል፣ ከእነዚህ ውስጥ 10 ሺህ ያህሉ ኦርቶዶክሳውያን ይሆናሉ፡፡ ቁርሳቸው ዳቦ በ1 ብር ቢሰላ በአንድ ቀን ቁርስ ብቻ 10 ሺህ ብር ይገኛል ማለት ነው፡፡ የሻይ ወጪን በ0.50 ሣንቲም ብናሰላው 5 ሺህ ብር ይሆናል፡፡ ሁልጊዜ ደግሞ ቁርሱ ዳቦ አይደለም፤ ሌላ ዐይነት ቁርስም ይዘጋጃል፤ በዚህ ጊዜ የቁርስ ወጪ ስለሚጨምር የማኅበረ ቅዱሳን ገቢም በዚያው መጠን ይጨምራል፡፡

በየዩኒቨርሲቲውና ኮሌጁ ያለው የአመጋገብ ሕግ ይለያያል፡፡ ለምሳሌ፡- የአንድ ዩኒቨርሲቲን የአመጋገብ አቅርቦት ከግምት ብናስገባ በሣምንት ለ4 ቀናት ሥጋ የሚበላበት ዩኒቨርሲቲ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ሥጋ በሚበላበት በአንዱ ቀን ብቻ 20 በሬ የሚታረድ ሲሆን፣ ከ20ዎቹ በሬዎች ውስጥ ከ10-12 የሚሆኑት ለኦርቶዶክሳውያን የሚታረዱ ናቸው፡፡ የበሬዎቹ መግዣ ወጪ ሆኖ ለተማሪዎች ግን በጾም ምክንያት ሽሮ ነው የሚቀርብላቸው፡፡ ከዚያ ለሽሮ የወጣው ተቀንሶ ቀሪው ብር ለማኅበሩ ገቢ ይሆናል፡፡

አንድ በሬ በትንሹ 4 ሺህ ብር ቢገዛ፣ በቀን ብቻ ከ40-48 ሺህ ብር ይደርሳል፡፡ ይህን ከሚያህል ገንዘብ ላይ የሽሮ ወጪዋ ተቀንሳ ሌላው ማንም ሳያይ ወደ ማኅበሩ ካዝና ይገባል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በዚህ መንገድ በመንግሥትና በሕዝብ ሀብት ላይ ስልታዊ ዘረፋ ያካሂዳል፡፡ የተዘረፈው ገንዘብ ወዴት እንደሚደርስ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ምናልባት ተመልሶ የቤተ ክርስቲያንንና የአገርን ሰላም ለማደፍረስ፣ የእርሱን ዓላማ ያልደገፉትን አገልጋዮች በተለያየ መልክ ስም ለማጥፋትና ለልዩ ልዩ የውንብድና ሥራ እንደሚያውለው ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ በእነ በጋሻው ላይ ለከፈተው ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ከአንዳንድ ለሆዳቸው ላደሩ "አገልጋዮች" ገንዘብ በመስጠት በበጋሻው ላይ ሦስት የተለያዩ መጻሕፍት ያጻፈው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ለዚህ ዐላማ የሚያውለው ገንዘብ ምንጩ ከላይ የተጠቀሰው ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚገኝ ሊሆን እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ የሚገርመው ግን ይህን ገቢ ቤተ ክርስቲያን አታውቀውም፡፡ ማኅበሩም በየጊዜው ገቢና ወጪህን አሳውቅ፣ ሂሳብህን በገለልተኛ አካል አስመርምር ሲባል ወገቤን ይላል፡፡

ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካላት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት የፐርሰንት ፈሰስ እንደሚያደርጉት ማኅበረ ቅዱሳን ለአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎችና ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሆድ ግብር ከሚያገባ በቀር አንድም ፈሰስ አያደርግም፡፡ ይህም በአካፋ አስገብቶ በመንኪያ የማውጣት ያህል ነው፡፡
መንግሥት በማኅበረ ቅዱሳን በሕገ ወጥና በይሁዳዊ ስልት እየተዘረፈ ስላለው ገንዘብ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያንም ሆነች መንግሥት የሚሰበስበው ገንዘብ የት እንደሚደርስ ሊያውቁና ማኅበሩን በዚህ አቅጣጫ ሊቆጣጠሩ ይገባል፡፡ አሊያ ማኅበሩ ባለው ጠንካራ የገንዘብ አቅም ለመንግሥትም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን ሥጋት እየፈጠረ መሄዱ አይቀርም፡፡ ምናልባትም ሊቀለበስ የማይችል አደጋ ወደ መሆን ሊሸጋገርም ይችላል፡፡

በዚህ ዝርፊያ ውስጥ ቀጥተኛ ተበዳዮቹ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በእነርሱ ምክንያት የሚያገኘውን ገቢ ለማሳደግ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን ካወጀቻቸው ሰባት አጽዋማት ሁለቱ ዩኒቨርሲቲ በሚዘጋበት ወቅት ላይ ስለሚጾሙ፣ ለማካካሻ በሚል ጽጌ ጾም ስምንተኛ ጾም ሆኖ እንዲጾም በራሱ ሥልጣን መደንገጉን ውስጥ ዐዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ለግል ጥቅሙ ሲል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤተ ክርስቲያን ያልደነገገችውን ጾም ያጾማቸዋል፡፡ በተመልካች ዘንድ "አቤት መንፈሳዊነታቸው" የሚል ከንቱ ውዳሴ እንዲጎርፍላቸው ያደርጋል፡፡ ይሁን እንጂ በተማሪዎች ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ ነው፡፡ በጥናትና ምርምር ላይ ያሉ ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ቁርስ እንዲበሉ በ2000 ዓ.ም. በተዘጋጀው የሚሌኒየሙ መጽሐፍ ላይ ቤተ ክርስቲያን ያደረገችውን ማሻሻያ ማኅበሩ ሲያጥላላው እንደ ነበረ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ማሻሻያው የማይነጥፈውን የገቢ ምንጩን ያደርቅበታልና፡፡ ይሁን እንጂ ተማሪዎችን ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ለግል ጥቅሙ በማጾም ልብ የሚሰብር በደል እየፈጸመባቸው ይገኛል፡፡

በተማሪዎቹ ላይ የሚፈጸመው በደል መች ይህ ብቻ ሆነ! በእነርሱ ስም በጾሙ ወቅት ይህን በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦ ሲያበቃ፣ ጾም ሲፈታ ደግሞ ለማስፈሰክ በሚል ምክንያት ማኅበሩ ለገቢ ማስገኛ መንገድ ቀይሶ ሌላ የዘረፋ ስልት ይዘረጋል፡፡ በየባቹ በዘረጋው መረብ ከእያንዳንዱ ተማሪ ለመፈሰኪያ በሚል 10 ብር እንዲያወጣ ያደርጋል፡፡ 10 ሺህ ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎች ባሉበት ዩኒቨርሲቲ 100 ሺህ ብር ይሰበስባል ማለት ነው፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ ለመፈሰኪያ የሚውለው ግን ከ30 ፐርሰንት እንደማይበልጥ ይታወቃል፡፡ ቀሪው 70 ፐርሰንት የማኅበሩ ተጨማሪ ገቢ ይሆናል፡፡ ይህ እጅግ የከፋ ግፍ ነው፤ እጥፍ ድርብ የሆነ የሚያንገፈግፍ ግፍ፡፡
በዓመት ውስጥ ባሉት የጾም ቀናትና ራሱም በደነገገው የጽጌ ጾም በጠቅላላው 151 ከፍተኛ ገቢ የሚያገኝባቸው ቀናት አሉት፡፡
·        የጽጌ ጾም                   ከመስከረም 26 - ኅዳር 6                             40 ቀናት
·        ጾመ ነቢያት                ከኅዳር 15 - ታኅሣሥ 28                              43 ቀናት
·        ጾመ ነነዌ                                                                              3 ቀናት
·        ዐቢይ ጾም                                                                           55 ቀናት
·        ጾመ ሐዋርያት (ትምህርት የሚዘጋበት ወቅት ስለሆነ) በትንሹ          10 ቀናት
                                      በድምሩ                                                 151 ቀናት

በጥቂቱ በቀን ከቁርስ፣ ከምሳ እና ከራት 50 ሺህ ብር ድርሻው ቢሆን፣ 151 X 50,000 = ብር 7,550,000 /ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ኀምሳ ሺህ ብር/ ይሆናል፡፡ ይህ ገንዘብ የሚገኘው ማኅበሩ የዘረፋ መዋቅሩን ከዘረጋበት ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሠራው ተመሳሳይ የዝርፊያ ሥራ ቢኖርም በ10ሩ ዩኒቨርሲቲዎች እንኳ በአማካይ 10 ሺህ የኦርቶዶክስ ተማሪዎች ይኖራሉ ብለን ብናስብ፣ ከ100,000 ተማሪዎች በዓመት ሊያገኝ የሚችለው ብር 75,500,000 /ሰባ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር/ ይሆናል፡፡

ታዲያ ማኅበረ ቅዱሳን እየሠራ ካለው ከዚህ ሥራው አንጻር የይሁዳ የግብር ልጅ ነው ቢባል ምን ስሕተት አለው? በየዓመቱ የሚያገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግና በጾመ ሐዋርያት ወቅት ትምህርት የሚዘጋ በመሆኑና ከዚያ የሚቀርበትን ትርፍ ለማካካስ ሲል ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያሏት አጽዋማት 8 ናቸው ብሎ ያወጀ ደፋር ማኅበር እንዴት መንፈሳዊ ሊባል ይችላል? ከዚህ አንጻር ሃይማኖት ሽፋኑ እንጂ ትክክለኛ ማንነቱ አይደለም፤ ትክክለኛ ማንነቱ   ብፁዕ አቡነ ማርቆስ አሉ እንደተባለው ሕገ ወጥ ነጋዴ ነው፡፡

42 comments:

 1. That's 100% true.

  ReplyDelete
 2. The Ridiculous story (article) ever in my life and won't expect another one for the rest of my life in the future. Abaselamoch gira gibit alachihu ayidel????

  May GOD give you grace and blessing to have rational thinking.

  ReplyDelete
 3. አብዳችኋል እንዴ? አሁንስ ለየላችሁ። ውሃ የማይቋጥር እና ከፍጹም ጥላቻ የመነጨ ክስ! በጻፋችሁ ቁጥር ማንነታችሁን እያሳወቃችሁን ነው።

  ReplyDelete
 4. I told my nephew to distance him self from this nonsense mehaber, "he is a medical student."

  ReplyDelete
 5. አንደበታችሁ ኦና ኦና ይላል ወይ ሰው አላደረበትም አለዚያ የሆነ ነገር ደፍታችሁበታል

  ReplyDelete
 6. be smart like mhaber kidusan long live for mhaber kidusan ABA SELAMA why you are not work like mhaber kidsuan you guys you do't like Mehaber kidsuan that why but aba selam you just talk talk talk just to much talk pls STOP!!!

  ReplyDelete
 7. MK took the beef for the money but where is the BEEF, EVIDENCE, to this story,

  If no evidence, this kinda story will make you guys look bad and it doesnt help the cause you all stood for.

  Show us some evidence

  ReplyDelete
 8. Waw MK you are doing the unthinkable. God bless you. Yesterday this same Menafeqane site said you don't have a member. Today this same site, which is a lie fabricator tells us you have many devoted members who are willing to sacrify their food to our church. God bless you. I'll accept 9th fast season for this good work. This tehadeso's paid hefty money from mulu wonjele. They don't like church let alone fasting. I am willing to cotribute money through your US site paypal account. So you'll make another million from us too.
  Keep up the god work.

  ReplyDelete
 9. THE LAST Anomes, your nephew will be 'empty' when he finish his study. Try to advise him to go church...

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማዎች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር እስከ መጨረሻው ድረስ ያቆያችሁ። የንፁሃን አባቶቻችን አምላክ ይጠብቃችሁ። እግዚአብሔር እኮ ብዙ ጊዜ ዝም ብሎ የሚያይ ይመስለናል እንጅ እርሱ እኮ በራሱ ጊዜ የራሱን ሰዎች እያስነሳ እውነት እንድትመሰከር ያደርጋል። ይኼው እናንተንና እናንተን የመሳስሉ አባቶችን፣ ወንድሞችን፣ እህቶችን እያስነሳ ቤቱን ያፀዳል። ምን ብየ እንደማመሰግናችሁ ቃላቶች ያጥሩኛል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ
  በእናንተ ላይ በእውነት መኖሩን አሳውቆናል። ሣይደፈርስ አይጠራምና አይዙአችሁ በርቱ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ችሎታና ጥበብ እስከ መጨረሻው ተጠቀሙበት። በእውነት እላችሁአለሁ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሥራ እየሠራችሁ በመሆኑ ልትደሰቱ ይገባል። እኔም ሆነ ሌሎች እውነተኛ ክርስቲያኖች በሙሉ ከጎናችሁ ነን።

  እንደኔ እንደኔ ግን ብትችሉ ለቅዱስ ፓትሪያሊኩ ለአቡነ ጳውሎስም የዚህን የነጋዴ ማህበር አፀያፊ ሥራቸውንና መሠሪ አላማቸውን አጋልጣችሁ ማህበሩ በኦርቶዶክስ ሐይማኖት ሽፋን ቤተ ክርስቲያንንና መንግሥትን አፈራርሶ እራሱ የሚፈልገውን የዘረኝነት እኩይ ተግባሩን ለማሳካት በውድቅትና በሌሊት እንደ ጅብ በመሰብሰብ ሲዶሉቱ እንደሚያድሩ ፤ ከነሱ ጋር ያልተባበሩትን አባቶች ሁሉ ለምሳሌ ዘወትር የሚሰድቡአቸው መናፍቅ ምናምን እያሉ ቅዱስ ፓትርያሊኩንና አባ ሰረቀን፣ እንዲሁም ሌሎች እውነተኛ አባቶችን ሁሉ በተለይም በየሰንበት ት\ምህርት ቤት የምንገኘውን የቤተክርስቲያን ልጆች የነሱ እኩይ ተግባር ተባባሪ ካልሆንን የሐሰት ሥም በመስጠት ከምዕመናንና ከአግልጋዮቹ ጋር ለማጣላት የማያደርጉት አድማ የለም። ስንቱን ፅፌ እችላለሁ በጣም ብዙ ነው ጉዳቸው ያው እየታወቀ ነው።

  ስለዚህ ይህ ማህበር ለቤተክርስትያንም ሆነ ለመንግሥት ከጥቀሙ ጉዳቱ በጣም የበለጠ ስለሆነ በደንብ ደብዳቤ ለፓትሪያሊኩና ለመንግስት ማህበሩ እንዲዘጋ ፅፋችሁ አስገቡ። የድጋፍ ሰጭ የህዝብ ሥም ሊስት ካስፈለገ ደግሞ በየእስቴቱ ተወካይ ተወካይ አድርጎ ማስተባበር ይቻላል። ማንም እውነትን የያዘ ሁሉ አይፈራምና።

  በርቱ የተሻለ ሐሳብ ያለው ሰው ካለ ደግሞ ተመካክራችሁ እንደሚሆን አድርጉ ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገበቶ ይፈተፍታልና ።

  የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ፀጋና በረከት አይለያችሁ፣ አሜን።

  ReplyDelete
 11. ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ብሎናል እና ዘመኑን እናስተውል

  2ጢሞ 3: 1-5

  1 ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።

  2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥

  3 ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥

  4 ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤

  5 የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

  ReplyDelete
 12. Deje slam,
  የፈለጋችሁትን ብትሉ የሚሆነው የእግዚአብሔ ፈቃድ ብቻ ነው። ቅዱስነታቸውንም ሆነ አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤልን
  አቡነ ፋኑኤልን እንዲሁም በእናንተ ሥራ ያልተባበሩትንም ሁሉ እንደምትፈልጉት ብትሳደቡ፣ ጮቤ ብትረግጡም
  የሚሆነው ከሚሆነው አያልፍም፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እሱ የፈቀደውን ነገር ማንም በምንም
  አያስቀረውምና በከንቱ አትድከሙ።

  ReplyDelete
 13. MK is one of the biggest threats for the health and survival of EOTC. The next threat is Pentecoste.

  ReplyDelete
 14. MK is looks like terrorist.

  ReplyDelete
 15. ቤተክህነቱ እኮ የሚታመሰው ማኅበረ ቅዱሳንን በሚደግፉ የጳጳሳት ቡድንና የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳትን ለማዳከም በሚታገሉ አቡነ ጳውሎስና ደጋፊ ጳጳሳት መካከል በሚነሳ አምባጓሮ ነው። የትኛው አጀንዳ ለደረቅ ክርክር እንዲቀርብ ማቅ ጭኖ በሚልካቸው ቅጥረኞች እና የሚመጣውን አድማ በማስቆምና በማዳከም ያላቸውን ሥልጣን አጠናክረው በሚቋቋሙት ለመቀጠል በሚፈልጉት መካከል የሚደረግ ጦርነት ነው። አቡነ ጳውሎስ ወርቅ የሚያዘንብ ሃሳብ አለኝ ቢሉ እንኳን የማቅ የጳጳሳት ቡድን ተዘጋጅቶ የሚገባው አባ ጳውሎስን ሃሳብ ሁሉ በአድማ የድምጽ ጽልጫ ውድቅ ለማድረግ ስለሆነ ፓትርያርኩ ወደእልክና ሴራውን የማፍረስ ትግል ይገባሉ። ያኔ የማይፈለግ ስራ ይሰራል። ነገሩ ሁሉ አድመኞች የሚባሉትን አንጀት ወደማሳረር ይሸጋገራል። በመካከል ግን ቤተክርስቲያን ትበደላለች፤ ምእመናንና ምእመናት ያዝናሉ። ተስፋ ይቆርጣሉ። በተቃራኒው ዜና እየተሰራ ጋዜጦችና መጽሔቶች ይቸበቸባሉ። የማቅ የሆቴሎች፤ የመጻህፍቶች፤ የጧፍና የጃንጥላ ገበያዎች ይደራሉ። የተወሩ ደጋፊዎቹ ይህንን በማድረግ ያጽናኑታል። እንጸልይ፤ የፈተና ወቅት፤ ለቤተክርስቲያን የሚያስፈልግ መዋቅር፤ ችግሮችን የመፍቻ ዘዴ ወዘተ ዓይነቶችን መጣጥፍና ጽሑፍ መንፈሳዊ ስምና መልክ እየሰጠ ይህን ለደጋፊዎቹ በችግሯ ወቅት እንደማቅ የደረሰላት የሃሳብ ሰው የለም ብለው እንዲያስቡ መንገዱን ይመራቸዋል። ተላላኪ ጳጳሳቱን ደግሞ «ተቀመጥ በወንበሬ፤ ተቀመጥ በከንፈሬ» እንዲሉ ማቅ ከሌለ ይቺ ቤተክርስቲያን የለችም እኮ ብለው እንዲታገሉ ይልካል፤ ያስልካል። መንፈስ ቅዱስ ይመራታል በምትባለዋ ቤተክርስቲያን ማቅ ከሌለ ማን አለን? የሚሉ ጳጳሳት እንዴት ሰላምን የሚያመጡ መንፈሳውያን ሊሆኑ እንደሚችሉ አይገባኝም። በሚሊዮን ብር መሸጥ የሚችል ቤት ያላቸው ጳጳሳት በሙዳየ ምጽዋት በምትተዳደር ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። እንግዲህ እነዚህ በዘረፋ ካልሆነ አሁን እያገኙ ያለውን ደመወዝ 5ሺህ ብር ገደማ ለሚበላ ለሚጠጣም እንኳን ምንም ሳይቀንሱ ያስቀምጡ ቢባል በዓመት 60ሺህ፤ በአሥር ዓመት 600ሺህ ብር ይሆናል። እንግዲህ አሥር ዓመት ሳይበላ ሳይጠጣ ደመወዙን አስቀምጦ ህንጻ የገነባ ጳጳስ መቼም አይኖርም። እነአብርሃም (አሜሪካ የከዳው ጳጳስ) ሲኤምሲ የሰሩት አፓርትማ ከራጉኤል ያገኙት ካልሆነ ጎጃም ኢንቨስት ያደረጉት ኖሮ አይደለም። እንግዲህ እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ነውራሞች ናቸው አባ ጳውሎስን የሚታገሉ፤ ማቅን የሚደግፉት!! ቤተክርስቲያንን ከሙስና እናስጥላለን የሚሉ ግን እነርሱ ከዚያው ከሙስና ባሕር የሰጠሙ!!! የ500 ሺህ ብር ቼክ አልፈርምልህም ያለውን መነኵሴ ከራጉኤል ያስባረረው ማነው? አብርሃም አይደለም? መነኵሴውም አለ፤ አብርሃምም በሌላ ሰው በኩል ገንዘቡን አግኝቶታል። ይህ የሚረጋገጥ ሃቅ ነው። እስኪ እውነተኞች ከሆኑ እነአብርሃም፤ እነሳሙኤል አረ ሁሉም ጎበዝ ከሆኑ አድማውን ትተው፤ በቃለጉባኤ ተስማምተው ጸረ ሙስና ኰሚሽንን ለምርመራ ይጥሩት እስኪ! ማቅከሌለ ቤተክርስቲያን ማን አላት እያሉ ከሚጮሁ እስኪ ኮሚሽኑ ምርመራ ያድርገን ብለው ሲጣሩ እንያቸው! ዳሩ ግን የሲኖዶስ አባላት የሚመራቸው መንፈስ ቅዱስ አይደለም። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የሰላም እንጂ የሁከት አምላክ አይደለምና። በዚህም ይሁን በዚያ የትኛውም ወገን የራሱን ጥቅምና ሥልጣን ለማስጠበቅ፤ በሌላ በኩልም ጋሻውን ማቅ ለመከላከል በሚደረግ ትግልና በሌላኛው በኩልም እንዲሁ የራሱን የስልጣን ኃይል ለማሳየት፤ የሚቀናቀኑትን ድባቅ ለመምታት የሚደረገው ጉባዔ የሽኩቻ መድረክ ካልሆነ በስተቀር ለቤተክርስቲያን ከመቆርቆር የሚሰራ አይደለም። ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ በአማኞች ዘንድ ከማኅበርና ከድርጅት ባለፈ ለእግዚአብሔር ቃል የሚታዘዝ፤ በሕይወቱም ቅድስናን የሚፈጽም ስጋውንና ነፍሱን ከእድፈት የሚጠብቅ ትውልድ በመጥፋቱ እግዚአብሔር በማዘኑ የመጣ ነገር ነው። ፩ኛ ሳሙ ፲፪፤፲፬ እንዲህ ይላል፤«እግዚአብሔርን ብትፈሩ ብታመልኩትም፥ ቃሉንም ብትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ባታምፁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ፥ መልካም ይሆንላችኋል»

  ReplyDelete
 16. ለምን ይዋሻል ?

  ReplyDelete
 17. i beleive MK is doing right. I have been through that process but your fabricated story doesnot reflect the truth. we collected our breakfast money and we build a big hall for sundayschool.
  i remember also we, students went to monastry and maintained the houses for monks. so wjat is wrong? it is not your money, it is ours. why dont you raise concern on spending billions of birr on corruption at betekihnet? i would suggest you to fight against corruption and maladministration at head of teklaybetekihnet. dont fight with something you cannot fight.

  ReplyDelete
 18. ወልደ ትነሳኤNovember 9, 2011 at 11:44 PM

  አይፈረድባችሁም ምክንያቱም የማቅ ተግባራትን ስለማታዉቁት። "አንደበታችሁ ኦና ኦና ይላል ወይ ሰው አላደረበትም አለዚያ የሆነ ነገር ደፍታችሁበታል"
  ማቅ በተለይ እኛ ገጠርቱ የአገራችን ክፍል ያለነው ባለውለታቸን ነው ስለዝህ በእነሱ መጣችሁ ማለት በቤ/ክ አይን ብሌን መጣቸህው ይሆናልና ብታርፉ ይሻላቸዋል። እነ አንደ ለስራ ወደ ም/ወለጋ በሄድኩበት ግዜ ያስተዋልኩት ላካፍላቸህሁ በተለይ በመናፍቅ የተወረረዉን ሕዝብ መሃከል በቅልጡካራ ገዳም አሰርቶ ብዙ የሚሆኑ ወጣቶቸህ በራሳቸዉ ቐንቐ ስማሩ በማየቴና ብዙየሚሆኑ ምዕመናን እነሱ በመምያስተምሩት ት/ት ከመናፍቅነት ተመልሶ ቆራብያን በወረፋ የሁነበት አጋጣም በጣም ደስ የለኝ ነገር ነው ስለዝህ እነም 75000000 ሰባ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ አየደለም እይወቴንም ጭምር ለመስጠት ተዘጋጂቸዋለው። ይቀጠላል......

  ReplyDelete
 19. we are member of mk graduated from university and we know all, you are illegal to talk about orthodox b/c you are protestant .
  የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።

  ReplyDelete
 20. Hod amlakoch yemtlut sitatu degmo bezih metachu egna lesetenew egna letsominew enant min akatelachu erir dibin tilalachu inj mestetachinm metsomachinin anitewm sile mahiberu yemtitsfut hulu yenante sira mehonu gilts new yemayen wede abaye new negeru

  ReplyDelete
 21. ዛሬ 19 ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ብላችኋል፡፡
  ጥሩ ነው ከትናንትናው በ 3 ቀንሳችኋል፡፡
  ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ X ብር 75,500,000

  ReplyDelete
 22. አብዳችኋል እንዴ? አሁንስ ለየላችሁ። ውሃ የማይቋጥር እና ከፍጹም ጥላቻ የመነጨ ክስ! በጻፋችሁ ቁጥር ማንነታችሁን እያሳወቃችሁን ነው።

  የፈለጋችሁትን ብትሉ የሚሆነው የእግዚአብሔ ፈቃድ ብቻ ነው። ቅዱስነታቸውንም ሆነ አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤልን፣አቡነ ፋኑኤልን እንዲሁም በእናንተ ሥራ ያልተባበሩትንም ሁሉ እንደምትፈልጉት ብትሳደቡ፣ ጮቤ ብትረግጡም የሚሆነው ከሚሆነው አያልፍም፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። እሱ የፈቀደውን ነገር ማንም በምንም አያስቀረውምና በከንቱ አትድከሙ።

  ReplyDelete
 23. The Ridiculous story (article) ever in my life and won't expect another one for the rest of my life in the future. Abaselamoch gira gibit alachihu ayidel????

  ReplyDelete
 24. በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የአንድ ተማሪ የቀን በጀት 8 ብር ብቻ መሆኑን ታወቃላችሁ
  ከዚህም ውስጥ የቁርስ በጀት አንድ ብር ከ 65 ሳንቲም ነው፡፡ የሂሳብ ቀመራችሁን አስተካክሉ፡፡ ውሸታም ሁሉ፡፡

  ReplyDelete
 25. In every government universities the daily food coast for a student is 8 Ethiopian Birr only. Out of this 1.65 Birr is breakfast share. Please Abaselama correct your pseudo-calculation.

  ReplyDelete
 26. The grandfather of MK is Taliban,and collect money to kill our church father. AS this result the only solution is one which is shutdown ilegal organization. Death to Mk!

  ReplyDelete
 27. You Nonsense guys!! Did you get any rest by taking such nonsense talk. I am one of the instructors and on positon. I know the reality which is 100% opposite to what you have said. I was reading ur blog still but bye after this time b/c I have assured that you simply are "mafias" who don't have any job but simply get mony by corraption.

  ReplyDelete
 28. Your job is killer of our innocent church father.

  ReplyDelete
 29. ትናንትና ለክስ
  ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማህበር

  ዛሬ ለሌላ ክስ
  በትምህርት ቤት ብቻ ከ100,000 ተማሪዎች በላይ አባል ያሉት ማህበር::

  ምን????
  ማነው የወንድሞች ከሳሽ???? ገባችሁ??

  ReplyDelete
 30. ገዳማትን ይርዱ
  http://mkus.org/

  ReplyDelete
 31. የስራ ሪፖርት
  http://mkus.org/Default.aspx?tabid=101&ctl=Details&mid=371&ItemID=369

  ReplyDelete
 32. የአብነት ት/ቤቶችን እንርዳ

  ገዳማትና አድባራት፤የአብነት(የቆሎ) ት/ቤቶችንና ሊቃውንት መምህራኑን በመርዳት የሺህ ዓመታት ታሪክ ይጠበቃል፡፡ በታሪክ ፊት መልካም ስም የሚያተርፈውን ይህንን በጎ አገልግሎት ይራዱ፡፡ በአበው ጸሎት ይጠበቃሉ ፤ በእግዚአብሔር በረከት እርስዎና ቤተሰብዎ ይትረፈረፋሉ፡፡

  http://mkus.org/Default.aspx?tabid=101&ctl=Details&mid=371&ItemID=132

  ReplyDelete
 33. ስለ ይሁዳነትህ የፃፍኩልህን አየህ አይደል:: ይሁዳው አሳማኝ አይደል? ባታወጣውም ካነበብክው ይበቃል::

  ReplyDelete
 34. አባ ሰላማዎችም ሆነ የዚህ ብሎግ ተከታታዮች ቀደም ሲል ደጀ ሰላም ለተባለው ብሎግ የሰጠሁትን አስትያየት ኮፒ አድርጎ አንድ አናኒመስ ቆርጦ አውጥቶ ይህንን ብሎግ እንደተቃወምኩ አድርጎ ፅፉአል፣ ይኸውም የሚለው የፈለጋችሁትን በትሉ ጮቤ ብትረግጡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ ነው የሚሆነው ብየ ስለነ አባ ጳውሎስ፣ ስለነ አባ ሰረቀ፣ ሰለነ አቡነ ፋኑኤልና እንዲሁም ለሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ማቅ ስላለው ጥላቻ ነበር የፃፍኩት፣ አያችሁ የዚህ ማፍያ ማህበር ሥራ በትንሹ እንኩአን እንዴት እንደሚያጭበረብር፤ ታዲያ እኮ እጅ ከፍንጅ ቢያዝም የሌባ አይነ ደረቅ መሶ ልብ ያወልቅ፣ ይኸውላችሁ እነበጋሻውንም እንዲህ እየቆረጡ እየቀጠሉ ነው እንዲህ አሉ፡ እንዲህ አደረጉ የሚሉአችሁና በፍፁም የሚታመኑ አይደሉም። ሠይጣንን የሚያምን አለ አሁን አሥር ጊዜ የአምላክን ሥም ቢጠራ? መልሱን ለናንተ። you can see the comment Nov. 10,2011 at 2:45 AM. mine was LeSelam in this blog and deje- blog. you can see the original.

  ReplyDelete
 35. MK yhin bicha sayhon zetenegna (9) tsome b pagume asjmiro bizu bota sew gira tgabtoal. neger gin ymigrmew amrarochu ytunm alamtsomachew new.

  balafew abiy tsom 2 tawaqi amraroch bole menged babiy tsom siga sibalu taytew sitayaqu hakim faqdolin new alu............ any way

  ysaytan mhaber hule asasach aydel? endantalel yasfaligal

  ReplyDelete
 36. ማቆች በማይሆን ቃላት ስንጠቃ አታደናገሩ፤ ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማኅበር ብሎ የጻፈው ሰው ማኅበሩ አሁን የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡ ጽሑፉ በመጀመሪያ የወጣም በእናንተው ደጀሰላም ላይ ነው፤ አባ ሰላማ የወሰደው ከዚያ ነው፡፡ ደግሞም በርካቶች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተመርቀው እስኪወጡ እንጂ ከማቅ ጋር እንደማይቆዩ የታወቀ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዘረፋው ከዚህ በላይ እንጂ ያነሰ አይደለም፡፡ በየገዳማቶቻን ስም እንኳ ፕሮጀክት ቀርጾ ከፕሮቴስታንት ድርጅቶች ሳይቀር የሚዘርፈው ገንዘብ የትየሌለ ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ እንኳ ለዋልድባ ገዳም 5 ሺህ ብር ሰጥቶ በቪዲዮ ቀርጾ የወሰደው የገዳሙን ይዞታ የሚያሳይ ምስል ስንትና ስንት ሚሊዮን እንደሚዝቅበት የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ አታደናግሩን፡፡

  ReplyDelete
 37. አባ ሰላማዎች ስታደቡበት የነበረው ቤተ ክርስቲያንን የማደስ ስራ ሲሰናከልባችሁ የምትይዙትን የምትጨብጡትን አሳጣችሁ:: የብዕር መፍቻችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ነው:: ማ/ቅን በሰፊው እያስተዋወቃችኋት ነው:: ደግሞ ስለሙስና ታወራላችሁ፣ አባ ጳውሎስ ዘርፈው ለዘራፊ እንደሰጧት እያወቃችሁ:: ነገር ግን ዝርፊያው ቤተ ክርስቲያንን የሚያዳክም እስከሆነ ድረስ ምን ቸገራችሁ:: በተዘዋዋሪ የምትፈልጉትን ያስገኝላችኋል:: ማ/ቅ ግን ገና ከምታስቡት በላይ ብዙ ይሰራል:: ለዚህ ሁሉ ስድባችሁ ያሳየው ትእግሥት ልዩ ነው:: ብራቮ ማ/ቅ

  ReplyDelete
 38. Abaselamawoch, are you out of mind?
  Do you know how to make analysis?

  This is trush talk.

  May God forgive you all.

  ReplyDelete
 39. ማቆች በማይሆን ቃላት ስንጠቃ አታደናገሩ፤ ደጋፊ እንጂ አባል የሌለው ማኅበር ብሎ የጻፈው ሰው ማኅበሩ አሁን የሚገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳይ ነው፡፡

  crazy!!!!

  በትምህርት ቤት ብቻ ከ100,000 ተማሪዎች በላይ አባል ያሉት ማህበር::
  so are you talking about yesterday?
  tehadeso confused!

  ReplyDelete
 40. The lion share of Mk elements are not fasting,on the contrary even they eating pork. Majority are pretender.

  ReplyDelete
 41. የአብነት ት/ቤቶችን እንርዳ

  ገዳማትና አድባራት፤የአብነት(የቆሎ) ት/ቤቶችንና ሊቃውንት መምህራኑን በመርዳት የሺህ ዓመታት ታሪክ ይጠበቃል፡፡ በታሪክ ፊት መልካም ስም የሚያተርፈውን ይህንን በጎ አገልግሎት ይራዱ፡፡ በአበው ጸሎት ይጠበቃሉ ፤ በእግዚአብሔር በረከት እርስዎና ቤተሰብዎ ይትረፈረፋሉ፡፡

  ReplyDelete
 42. lelaw letsomew enate rabachu

  ReplyDelete