Thursday, November 10, 2011

በብፁዕ አቡነ አብርሃም እና በብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ አህጉረ ስብከት የተሾሙትን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ለመቀበል በዋሽንግተን ዲሲ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡ - - - Read PDF

ማኅበረ ቅዱሳን በአገር ቤት ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈተባቸውና በማኅበሩ መሠሪ ተግባር ከሀገረ ስብከታቸው ለመነሣት የተገደዱትና ከዚህ ቀደም ብሎ “የት እንመድብዎ” ሲባሉ “ማኅበረ ቅዱሳንን የማላይበት ቦታ” ሲሉ በምሬት የመለሱትንና፣ በአሁኑ የሲኖዶስ ስበሰባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት የተመደቡትን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ለመቀበል በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ፡፡

ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአሁኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ካለመገኘታቸውም በላይ፣ ደብዳቤ ጽፈው ፓትርያርኩን ዘልፈዋል፡፡ ለቅዱስ ሲኖዶስ የላኩት ደብዳቤም በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ ከተነበበና ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው ከአሜሪካ እንዲነሡና በአገር ቤት በተሰጣቸው ሀገረ ስብከት እንዲሠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ መወሰኑ የሚታወስ ነው፡፡ በተለይም ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ ከዚህ ቀደም የአቡነ ጳውሎስ ስም ከማይጠራበት ደብር አልደርስም በማለት ሲመጻደቁ እንዳልነበረ፣ አሁን ግን ከዚህ በተቃራኒ ሕዝቡን በአቡነ ጳውሎስ ላይ ለማሳመፅና ቤተ ክርስቲያንን ወደ ባሰ ክፍፍል ለመምራት በሙከራ ላይ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ከሲኖዶስ ስብሰባ መቅረታቸውና በፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ ላይ ሰዎችን ለማሳመፅ መንቀሳቀሳቸው ከሕዝቡ ተቃውሞ እንዳስነሣባቸው ከስፍራው የሚወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከእርሳቸው ጋር ያሉትም በምድረ አሜሪካ ከየቤተ ክርስቲያኑ በመሠሪ ተግባራቸው የተባረሩና ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ያልተሰጣቸውን “አብያተ ክርስቲያናት” በአቡነ አብርሃም ቡራኬ እንደ ኪዮስክ እየከፈቱ ቤተ ክርስቲያን የባሰ እንድትከፋፈል ከፋፋይ ሥራቸውን እየሠሩ የሚገኙት እንደ ብርሃኑ ጎበና ያሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ሁለቱ ጳጳሳት ከአሜሪካ መነሣታቸውን ተከትሎ የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጾች በአቡነ ፋኑኤል ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን፣ ይህም ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝቡን በወሬ ለመፍታት የቀየሰው የተለመደ ስልቱ እንጂ በአሜሪካ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከመሰሎቻቸው በቀር አቡነ ፋኑኤልን የሚቃወሙ ክፍሎች እንደሌሉ እርሳቸውን ለመቀበል እየተደረገ ካለው ዝግጅት መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአሜሪካ በአገር ውስጥ ሲኖዶስ ሥር ባሉት አብያተ ክርስቲያናትና ገለልተኛ በተባሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተቀባይነት እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ግን የእርሱን ጩኸት የጠቅላላው ሕዝብ ተቃውሞ አስመስሎ ማቅረቡ አዲስ እንዳልሆነ ሲታወቅ፣ አላማውን ያልደገፉትን፣ የክርስቶስን ንጹሕ ወንጌል የሚሰብኩትን ሁሉ የተለያየ ስም እየሰጠ ማሳደዱ ማኅበሩ የተካነበት የተለመደ አሠራሩ ስለሆነ ማንነቱን የተረዱ ሁሉ በእርሱ የወሬ ዘመቻ እንዳይፈቱ ራሳቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡

19 comments:

 1. ለዚህ ድህረ ገጽ ያለኝ አስተያየት እያቆለቆለ ነው
  I have lost my respect for this site when you write

  "በአሜሪካ ከማኅበረ ቅዱሳንና ከመሰሎቻቸው በቀር አቡነ ፋኑኤልን
  የሚቃወሙ ክፍሎች እንደሌሉ እርሳቸውን ለመቀበል እየተደረገ ካለው ዝግጅት መገንዘብ ይቻላል፡፡ በአሜሪካ በአገር ውስጥ ሲኖዶስ ሥር ባሉት አብያተ ክርስቲያናትና ገለልተኛ በተባሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተቀባይነት እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡"

  Where is your evidence that ፋኑኤልን is accepted in America.

  ለማቅ ያላችሁ ጥላቻ ከክርስትና ጸባይና አመላለክ እያራቃችሁ ነው
  አባመላኩ ፋኑኤል ለጵጵስና የሚያበቃ እውቀቱም መንፈሳዊነቱም የላቸውም
  በብልጠት ብሎም በገንዘብ ጉቦ ጳጳስ ተብየው ሆነዋል
  ማቅ ብቻ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲኑ ለቀና ኦርቶዶክስ ክርስትና የቆመ
  የአባመላኩ ፋኑኤል ጵጵስናና አዲሱን ሹመት መቃወም ተገቢ ነው
  ማቅ የሚያደርገው ብዙ ስህተት መታረም አለበት እንጂ የይሁዳ የግብር ልጅ ነው ማለት ከመስመር መውጣት ይሆናል

  መሰረታዊ ችግራችን ያልተማሩ ቢማሩም መንፈሳዊነት የሌላቸው - ዶክተር ነኝ ባዩ አባ ጳውሎስ ለምሳሌ በቤተክርስቲያናችን ተሰግስገው ከጌታችን ኢየሱስ ወንጌል እያራቁን ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማንም ማንንም ከጌታችን ወንጌል የማራቅ ኃይል የለውም ወገኔ እርሶ ግንኙነትዎን በግል ማጠናከር ነው የጌታችን ነገር ሰው ላይ በማመካኘት የሚሆን አይደለማን ለራስዎ ይወቁበት።

   Delete
 2. selam abaselamawoch enkuan des yalachehu betam des yemil zena new yasemachehun beretu yebtekereseteyan lijoch enezhi kanser yehonu mk matefat aleben abune fanueal eko be likawent egr ser tekemetew temerew new yihen kinet yagegnut mahebre kidusan malet kewetader bet metew diyakon egle kes egele eyetebalu miterut mafereyawoch abune abrham wede ethiopia new mihedut enji wede tor meda ayedelem min alebet bikeyayeru negeru mahebre kidusan kenu selemichelembet new dikon hefrem eshete brhanu gobena .. lelochem abatochen masaded ahun yikum aba selama bertu egnam kegonachehu nen egziabeher yiredan amen weldegebreal ke Geremen

  ReplyDelete
 3. I am living in DC,
  we have to respect the assignment of abune Fanuel, and hope both bishops will back to their new diocese.

  We have no problem with abune Fanule and we any right to ask legally if Mahabre Kidusan leaders do any thing against the new bishop.

  ReplyDelete
 4. Ilike Aba Fanual,idnot like Aba abrham.good luck aba Fanuel.from usA.

  ReplyDelete
 5. betam yemtasazen sew neh megemereya le abatoch keber yenureh yedegefuehn yemetamelek yenkefuehn yemetawared ke keresteyan wegenem ayedeleh engedeyaw yetemarewen asayen melkeyaweko gebrena ayedelem almen neko lekerstos mesetet new aba fanueal bemenkusena zemenachewm sebeketewengealen seyasefafu yeneberu talak abate nachew ye addis ababan memen teyek yemetehw kegeter kehon lekerstenawem engeda selhonk ayferdebehem gen sndebetehen lemekoteb tar YEH MELEKT ASTEYAYET LESETEW NEW.

  ReplyDelete
 6. ወገኖቼ ለምን እውነትን አትነግሩንም ? ይህ ዌብ ሳይት ማኅበረ ቅዱሳንን ለመቃወም የተከፈተ እየመሰለ መጣ:: ሊተች የሚገባውን በአግባቡ መተቸት መልካም ሲሆን በእየ ጹሑፎቻችሁ ማኅበረ ቅዱሳንን አዝማች ካላደረጋችሁ እንዳትጽፉ የተባላችሁ ይመስል ማኅበረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱሳን ማለት ተገቢ አይደለም:፡ እውነተኞች ከሆናችሁ አለን የምትሉትን በጎ የሆነ የቤተ ክርስቲያን መረጃና ትምህርት አስፍሩልን ::
  የእውነት ባለቤት ሁላችንንም ይርዳን ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወገኔ ያልተፈሳ አይሸትም እኮ ይህ መሃበር ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ነው ኦርቶዶክሳዊት እምነታችን ፈተና ላይ የወደቀው። ከዚህ በፊት ከለየላቸው ጸረ ማርያሞች ጋር ነበር ልዩነታችን አሁን ግን በቤተክርስቲያን ውስጥ ነው ያደግነው በሚሉ ነገር ግን አንዲት የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ የማይጠቅሱ ጨዋዎች እኮ ናቸው እግዚአብሄር በኪነጥበቡ ያስነሳልንን ወጣት ሰባኪያን መንፍቅ አባቶችን ተሃድሶ የሚሉን እኮ የድርጅታቸው ፍቅር ያቃጠላቸው ማህበረ ቅዱሳን ነን ባዮች አይደሉ እንዴ። ሕዝበ ክርስቲያኑ በግልጽ እነርሱን ማወቅ አለበት ይህ ዌብሳይትም ሃላፊነት አለበት እኮ እናንተም ጻፉ የማህበረ ቅዱሳን ተቃዋሚም እውነት ያለውን ይጻፍ ሕዝበ ከርስቲያኑ እውነትን ይምረጥ። ባለፉት 15 እና 16 ዓነታት አጭበረበራችሁን አይበቃም። አሁን አማራጭ ስላለ ስለኛ አታውሩ ማለት ተገቢ አይደለም የናንተን (የማህበረ ቅዱሳንን) የመለያየትና የመከፋፈል ጽዋ በሚገባ ተጎነጨን አቃረን አሁን ደግሞ ስለማንነታችሁ ከሚያውቋችሁ እንስማ። ቸር ይግጠመን።

   Delete
 7. awo MK kechhet weche america lay tesfa yelelew derejet new. beselam nu abatachen

  ReplyDelete
 8. Abune Fanuel is one of the greatest father in our church. Because, he love all members of our church with out discrimenation,but Abrham (Kaletedeke) represent him self and MK.

  ReplyDelete
 9. በእየ ጹሑፎቻችሁ ማኅበረ ቅዱሳንን አዝማች ካላደረጋችሁ እንዳትጽፉ የተባላችሁ ይመስል u always write about MK. Are jealous about it? What is your problem? Show in action that you excel MK! Cheap talk doesn't take you any further.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወገን ጀለስነት አይመስለኝም ነገር ግን እናንተን ያላውቅን ሁሉ ካሁኑ ካላወቅናችሁ የበለጠ ችግር ትፈጥራላችሁ። ሳታውቁ ለዚህ ድርጅት የምትከራከሩ ካላችሁ ዓይናችሁን የመክፈቺያ ጊዚያችሁ አሁን ነው። "what is your problem?" ብልዋል ጸሃፊውን እንደሚመስለኝ የአንድ ሰው ችግር አይደለም ችግሩ ክ2000 ዓመት በላይ የቆየች እምነታችንን ዛሬ ከ15 እና 16 ዓመት በፊት በተመሰረት ድርጅት ካልተመራ ማለታችሁ ነው። ችግሩ እግዚአብሄር አምላክ ያፈላልንን የወንጌል መምህሮቻችን እናንተን ካልመሰሉ የምታውጡላቸው ስም ነው። ችግራችን ካለኛ አዋቂ የለም ማለታችሁ ነው። እርሶ እንዳሉት "cheep talk" አይመስለኝም ነገሩ። ቁም ነገሩ ቆማጣን ቆማጣ ለማለት የወጣ ጽሁፍ ነውና የእግዚአብሄር መንፈስ አነሳስቶት የናንተን ማንነት የገለጸ ሁሉ ርካሽ ነው ለናንተ ። ጉድ ሳይባል...አሉ አለቃ ገብረሃና። ለማንኛውም እንረጋጋ እግዚአብሄር የሚሰራውን ሁሉ ማህበረ ቅዱሳን ሰራ እያላችሁ ለማውራት አትጣደፉ ክብር ለሚገባው ብቻ ክብር እንስጥ። ማህበረ ቅዱሳን ምንም ሃይል የሌለው ተራ የሰንበቴ ማህበር ነው በቤተክርስትያናችን ውስጥ የሚፈጸም ነገር ሁሉ በእግዚአብሄር ፈቃድ እንጂ በናንተ ማህበር ፈቃድ አይደለም፣ አይሆንምም። እግዚአብሄር አምላክ የተመሰገነ ይሁን። በናንተና ሳያውቁ እናንተን በተከተሉ እየሱስን በሰበኩ ብቻ ያልሆነ ስም የሰጣችሁዋቸው ሁሉ እግዚአብሄር መንፈሳቸውን ያጠንክርልን። አስተማሪዎቻችን ያውቁታል ጊታቸውን ሲያገለግሉ አልጋ በአልጋ ተራምደው እንዳልሆነ የቀደሙት የጌታ አገልጋዮች የገጠማቸውን ሁሉ ከመጽሃፍ ቅዱሳችን ያውቁታል እነርሱም ለናንተ ስድብ አይደለም ለዱላችሁም ዝግጁ ናቸውና ለመረጣቸው አምላክ ሲሉ የሚመጣውን መከራ ሁሉ ይችሉታል። "ሁሉን በሚያስችለኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ" እያሉ በቸር ይግጠመን

   Delete
 10. mk atenageru belhe yetsafekew asteyayet sechi mk legna kum neger hono ayedelem azimach yadergenew negeru endetaweki abatochachenen eyasadedu, yebtekeresteyan wendmoch, ehetochen yalesemachew bekinat menfes eyasdeduachew ensun yedgefe becha kerseteyan lelawen menafik adergew selemiwenjelu serachewen begelits endeyawekut ena betekeresteyanen eyekefafelu, hezibun selemiyaweku new leban leba. komatan komata kalalekew ayegebawem , lemin tadeya leloch maheberat alu be betekereseteyan lemin abatochen ayasadedem mk becha new tsadik yihe new ewenetu, yihe web sit ende dejeselam yemayadala ewenetegna web new dejeselam eko chegrachewen tekesen asteyayet senlekelachew eko ayawetum mikenyatum selemiyawekut bertu ye ebtekereseteyan lijoch lenezi yebetekereseteyan ayetoch yedingel mareyam amalajenet ayeleyen weldegebreal ke Germen

  ReplyDelete
 11. መናፍቆቹ እንክዋን ደህና መጡላችሁ:: የታምረ ማርያምን መነበብ ያስቀሩላችኃል? እየሱስ አማላጅ ነው ይሉላችሃል? ምስኪን አጨብጫቢዎች::

  ReplyDelete
 12. Aba Fanuel's appointment to North America is delicate, to my opinion. Why? The peace process between the exiled Synod and the one in Addis is in balance. This naturally persuasive figure, Abuna Fanuel, is facotored in the process implying that his thirst for power might possibly stand in the way of the peace round of talks between Addis and Washington. Some Synod members in exile don't think Abuna Fanuel is their best choice to help play the role of a "Catalyst of Peace" . HE just cares for himself, period, according to a vetreran Archbishop!!! Let's pray on it!!!

  ReplyDelete
 13. What you are talking about? Long live for Abune Pawlos (Phd) and other true father that accussed by MK with out any point.

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጳውሎስ ከመጣማ ፖይንት አለ ማህበረ ቅዱሳንን ለዚህ ያበቃቸው እኮ የጳውሎስ አስተዳደር ነው ዛሬ እነ አቡነ አብርሃም መፈንቅለ ፕትርክና ለማድረግ ከልጆቹ ጋር ሲያደብ ስለተደርሰባቸው እንጂ ብሌላ በኩልማ ጳውሎስ እኮ ነው ምዕመናኑን እንዲከፋፍሉለት ያደረጃቸው ዛሬ ከእጁ ውጡ እንጂ።

   Delete
 14. የማኅበረ ቅዱሳን አባል ባልሁንም የሚሰሩትን እናውቃለን የቤተክርስቲያን ልጀ እነደዚህ ዲያብሎስ አየሁንም:: መናፋቃን ሁሌም እኮ ቅዱሳን ሲባል የበረግጋል ስለዚህ ያለዉን ሁሉ ያወረውራል ግን የፈሪ ስለሁነ ያለፈናል ሰው ለምን ሲባል ኦርቶዶክስን እንተዋለን እንሱ ምን እተረፉ ርግማን ብቻ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ዝም አይበል::

  ReplyDelete