Monday, November 14, 2011

የትቂቶችን ኪስ እያደለበ ያለው የድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን! - - - Read PDF

ሕንድን ከ 1632 አስከ 1653 ድረስ ያስተዳደረው ንጉስ ሙታዝ  በዓለማችን ወደር ያልተገኘለትን እና ከአለማችን 7 አስደናቂ ቅርሶች (seven wonders of the world) ተርታ የተመደበውን የታጅመሀል ግንብ (መስጊድ) በማስገንባቱ ይታወቃል፡፡ ታዲያ ይህ ንጉስ ከአስገራሚው ግንብ እኩል አስገራሚ ታሪክም ሰርቶ አልፏል፡፡ ታሪክ እንደዘገበው ከሆነ ንጉስ ሙታዝ ታጅመሀልን ካስገነባ በኋላ ሌት ተቀን የለፉትን፣ ለሕንፃው ውበት የማሰኑትን እና ላባቸውን አንጠፍጥፈው ሕንፃውን ሕንፃ ያደረጉትን ግንበኞች፣ አናጺዎች ወዘተ ሰብስቦ ‘የኔን ግንብ በገነባችሁበት እጃችሁ ሌላ ግንብ ስትገነቡ ማየት አልሻም’ ሲል ተናገረ። እናም ‘ሕንፃው አልቆ አርፈን ሕንፃው ቆሞ የታሪክ ተጋሪ ሆነን’ በማለት በጉጉት ሲጠባበቁ የነበሩትን ገንቢዎች በሙሉ ያን አስደናቂ ሕንጻ የገነቡበትን እጃቸውን እየቆረጠ እንደጣላቸው ታሪክ ዘግቧል፡፡
          አነሳሴ የዚህን ንጉስ ታሪክ ለመተረክ አይደለም፡፡ ዛሬ እየተፈጠሩ ስላሉት ኢትዮጵያውያን ሙታዞች ለማውራት እንጂ። ጊዜው እንደ እኛ አቆጣጠር 1998 ዓ.ም ነበር ወርሃ ጥቅምት ከቀዝቃዛ አየሯ ጋር ታላቅ የምስራችን ለምስኪኑ የድሬዳዋ ምዕመን ይዛ ብቅ አለች፡፡ ሕዝቡ ረጅም ዘመን ሲያልም የኖረውን እና ሲጓጓለት የከረመውን ዜና ሰማ፡፡ ‘ለረጅም ዘመን በቆርቆሮ መጠለያ ውስጥ የከረመው የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት ማረፊያ በምስራቅ ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ የሌለው ሕንፃ ቤተክርስቲያን ይገነባ ዘንድ መሰረቱ ተጀመረ፡፡ የቤተ-ክርስቲያን ሕመም ሕመሙ የሆነበት፣ የቤተ-ክርስቲያንን መከራ ከማየት ሞቱን የሚመርጠው ኩሩ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይህንን ብስራት ሲሰማ የበረከቱ ተካፋይ ለመሆን ቀስቃሽ አላስፈለገውም፡፡ ከአምስት ሳንቲም ጀምሮ እስከ ሺዎች ድረስ ከእያንዳንዱ ምዕመን ኪስ ወጣ፡፡ እናም እንደ ሕልም በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ሲመላለስ የነበረው ሕንፃ ተጀመረ፡፡
          ሕንፃው ተጀምሮ ወር እንኳን ሳይሞላው ግን ኢትዮጵያኑ ሙታዞች የሰራተኛውን እጅ ለመቁረጥ ስለታቸውን ማንሳታቸው ተሰማ፡፡ ለመጀመሪያ በበጎ ልብ ተነሳስተው እጅግ በአነስተኛ ዋጋ ቤተ ክርስቲያኑን ለመገንባት ቃል የገቡ ቤተ-ክርስቲያኗ ያፈራቻቸው መሃንዲሶች የስራ ስምምነት ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ አልፈርምም ማለታቸው በሰሚው ሕዝብ ዘንድ ግርታን ፈጠረ፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የመሀንዲሶች ስብስብ ቀጥሎ በአካባቢው ምዕመን ዘንድ መልካም ስም ያላቸው እና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ሌሎች ባለሙያዎች በነኢንጅነር ወንደሰን ብርሐኑ መሪነት ስራውን ተረከቡት፡፡ ተፈጥሮ የነበረው ውዥንብር በመጠኑም ቢሆን የተረጋጋ መሰለ፡፡ አስቂኙም አሳዛኙም ድራማ ከዚህ በኃላ ይጀምራል፡፡ ሁለተኛው የባለሙያዎች ስብስብም ገና ስራውን እንኳን አጠናክሮ ሳይጀምር ግንባታውን እንዲያቋርጥ ተነገረው፡፡ ለምን? ሲባል ---- ‘የፓትርያርኩ ዘመድ የሆነ የግንባታ ሰራተኛ ተመድቦ ስለመጣ’ የሚል አሰቃቂ ምላሽ ተሰጠው፡፡ እንግዲህ ይህንን ግለሰብ ሽፋን በማድረግ አላስፈላጊ ወጭ ከድሐው ምዕመን ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ እየተቀነሰ ይመዘበር ጀመር፡፡ የሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ ይሆኑ ዘንድ ከተመረጡት ሰዎች መሀከል ነገሩ ግራ ያጋባቸው ግለሰቦች ‘ለምን’ ማለት ሲጀመሩ አስተያየት በሰጡ እና ጥያቄ በሰነዘሩ ማግስት ያለ ሕዝብ እውቅና ከቦታቸው መነሳታቸው ይነገራቸው ጀመር፡፡ ነገሩን ዝም ብሎ መመልከት የከበደው ሰበካ ጉባኤ ጣልቃ ሊገባ ሲሞክር  ሌላ አስደናቂ ነገር ተከሰተ፡፡ የቤተክርስቲያን ቃለ አዋዲ ድንጋጌን በመተላለፍ የሕንፃ አሰሪ ኮሚቴው ለሰበካ ጉባኤው እንደማይታዘዝ እና ተጠሪነቱ በቀጥታ ለቅዱስ ፓትሪያርኩ መሆኑን አረዳ፡፡ ከሕዝቡ እውቅና ውጭ ከመጋረጃ ጀርባ የተራቀቁ ወንጀሎች እና አይን ያወጡ ምዝበራዎች በስፋት ቀጠሉ፡፡ ከተማዋን ያስተዳድሩ የነበሩ የሌላ እምነት ተከታይ የሆኑ ባለስልጣናት እስከ 13000(አስራ ሶስት ሺ) ብር የሚጠጋ ሞባይል ቀፎ እና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን በመቀበል የበረከቱ ተካፋይ ሆኑ፡፡ ለሕንፃው ማሰሪያ ይሆን ዘንድ ምዕመኑ ቃል እየገባ ያስመጣው ድንጋይ አሸዋና ሲሚንቶ ማታ ታይቶ ጧት የደረሰበት ይጠፋ ጀመር፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን እንዴት የደብሩ አስተዳዳሪ ዝም አሉ? እሺ የሳቸውስ ይሁን የሀገረ-ስብከቱ ስራ-አስኪያጅስ ብለው እንደሚጠይቁ አልጠራጠርም፡፡ ይህ በወቅቱ የሁላችንም ጥያቄ ነበር፡፡ አሁን አሁን እየተገኙ ያሉት መረጃዎች ግን ትክክለኛውን ምላሽ ሰጥተውናል፡፡
          ለመሆኑ ከዚሁ ሕንፃ መስሪያ ላይ ተቀንሶ የ20000 (ሃያ ሺ) ብር የሞባይል ቀፎ በቀድሞው የሐገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ስም መገዛቱን ብነግርዎ ይገረሙ ይሆን? ለፓትሪያርኩ ልዩ ፀሐፊ ለአቶ ሙሉጌታ በየጊዜው ሕንፃውን ለመመልከት ሲመጣ የተገዙለትን ስጦታዎች በገንዘብ ለመተመን ግን ተቸግሬአለሁ፡፡ ካሳዘንኩዎት አይቀር ሌላ መረጃ ብጨምርሎትስ ከዚሁ የፈረደበት ሕንፃ ማሰሪያ ላይ ለቅዱስ ፓትርያርኩ የጉበት በሽታ መድኃኒት መግዣ ተብሎ ሁለት ጊዜ ወጭ የተደረገው ብር 150000(አንድ መቶ ሃምሳ ሺ) ብር ደርሷል፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ነበረ 6 የኮሚቴው (የህንፃ አሰሪ ኮሚቴ አባላት) ነገሩ ከህሊናቸው በላይ ሆኖ ስላሳቀቃቸው ተገንጥለው በመውጣት ጉዳዩን ለታማኙ ምዕመን ያቀረቡት እንዲያ በጉጉት የተሞላው፣ እለት እለት እንደ ዓይኑ ብሌን እየሳሳ የሕንፃውን ቁመት እንደ እድሜው እርዝማኔ በግምት ሲመትር የኖረው ምዕመን ምን እንደሚሰማው መገመት የሚከብድዎት አይመስለኝም፡፡
          አሁን ግንቦት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ላይ ደርሰናል፡፡ ሕንፃው ሙሉ በሙሉ ስራ ካቆመ ወደ አንድ ወር ገደማ ሞላው፡፡ ምዕመኑ ከዚህ በላይ መታገስ አልቻለም፡፡ እናም ብሶቴን ይሰሙልኛል ችግሩን ከስር መሰረቱ አስፈትሸው ያቀርቡልኛል ያላቸውን 4 አባላት በመምረጥ ተገንጥለው ከወጡት 6 አባላት ጋር በመደበል 10 አባላት ያሉት ተሟጋች ቡድን ተዋቀረ፡፡ ይህ ኮሚቴ ነው እንግዲህ ሕንፃው ከተጀመረ ጀምሮ የገባውን ገቢና የወጣውን ወጭ ኦዲት እንዲደረግ ሐሳብ ከማቅረብ አልፎ ወደ ተግባር የገባው፡፡
          ይህ ጽሑፍ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ ላለፉት ሶስት ወራት ኦዲተሮች ገቢና ወጭውን ሲያስቡ ከቆዩ በኃላ ግን ለሰሚው ሁሉ አሳፋሪ፣ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ ወዘተ የሚሉት ቃላት ሊገልጹት የማይችለው ጉድ የተሰማው፡፡
ተስፋ እንዲቆርጡ ሳይሆን እየተሰራ ያለውን የቤትዎትን ጉድ እንዲያውቁ በውሸት ተደልለው እውነትን ለመቅበር የራሳቸውን የማይሞላ ከርስ ለመሙላት የሚሯሯጡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ቁጭ ብለው እንደ ራስ ላይ ተባይ የደሀውን ምዕመን ደም የሚመጡ፣ ከታቦቱ ጎን ‘ገንዘብ’ የተባለ ጣኦት ተክለው ሌት ተቀን ለሚያመልኩ አህዛብ መታለልዎት ያበቃ ዘንድ የሚመጣብንን መከራ ሁሉ ሳንፈራ የኦዲቱን ሪፖርት ልንነግሮዎ ተነስተናል እና ይዘጋጁ፡-
1.      ከምስረታው ጀምሮ ከውጭ እና ከሐገር ውስጥ ምዕመናን  የተሰበሰበው ገንዘብ ብዛት 11,388,096.23 ብር በላይ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
2.     ሕንፃው ሲጀመር 2,984,562.51 ብር ወጭ እንደሚያስፈልገው የተገመተ እና ውል የተገባለት ቢሆንም በግንባታ ቁሳቁስ ዋጋ መናር የተነሳ ይህ ግምት ወደ 4.8 ሚሊዮን አሻቅቧል፡፡
3.     በሒሳብ ምርመራ እስከ አሁን በአሳማኝም ሆነ አሳማኝ ባልሆነ መንገድ በደረሰኝ የወጣው ወጪ 5 ሚሊዮን ብር ሲሆን ይህ የሂሳብ ስሌት ጠቅላላ ገቢ ከሆነው 11.8 ሚሊዮን አንጻር የሚያሳየው ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የገባበት እንደማይታወቅ ነው፡፡

ብሩ የት ገባ?
ይህ የሁሉም ጥያቄ ነው፡፡ ለመገመት ይመችዎት ዘንድ ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ ከተመረጡት የሕንፃ አሰሪ ኮሚቴዎች መሀከል ከሕንፃ ተቆጣጣሪ ባለሙያ (ከመሐንዲሱ) ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው ከሚጠረጠሩት እና ሌላውን ኮሚቴ አባረው በመጨረሻ ብቻቸውን ሕንፃውን እናሰራለን ብለው በድፍረት ከተሰለፉት ሰዎች መሀከል የ3ቱን (በምስራቅ ሐረርጌ ቀዳሚ የተባለው ሕንፃ በ3 ሰዎች እየተገነባ መሆኑን ልብ ይበሉ) የአጭር ጊዜ የሕይወት ለውጥ ወይም የኢኮኖሚ እድገት እንመልከት
1.      አቶ ብርሃኔ መሐሪ ሕንፃው ከተጀመረ በኃላ ሽንሌ በተባለ የከተማዋ ክፍል ላይ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስዶ እያለማ የሚገኝ ግለሰብ ነው
2.     አቶ ይመር ገ/እግዚአብሔር በዚህ አጭር ግዜ ውስጥ የፎርስ መኪና ባለቤት ሆነዋል የገንዘቡን ምንጭ እግዚአብሔር ይወቀው
3.     አቶ ሲሳይ ፀጋዬ የብዙ ገንዘብ ባለቤት መሆናቸውን የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ፡፡
     ድሐው የዚህች ከተማ ምዕመን እና በሩቅ የምትታዘበው ኢትዮጵያዊ ወንድሜ ሆይ በእውነት እየተሰራ ያለው ምንድን ነው? በእውነት ይህቺ ንጽህት ቤተ-ክርስቲያን ወዴት እያመራች ነው? እኛስ የምንሰጠው ብር ከኪሳችን ከመውጣት እና ለነብሳችን ስንቅ ከመሆን ባለፈ እየወደቀ ያለው ምን ላይ ነው? ---- የሙታዝ ግልባጭ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በዚህ ዘመን እለት እለት ‘መለመን ሰለቸኝ’ ሳይል የቅዱሳን ታቦታት ማጀቢያ የሆኑት ጥላዎች እየተገላበጡ ገንዘቡን እየለገሰ ጉልበቱን እየመፀወተ ላቡን አንጠፍጥፎ የሚገነባቸውን ሕንፃዎች የገነባበትን እጅ በጭካኔ ሌላ ‘ሕንፃ እንዳትገነባ’ የሚል መልዕክት ባዘለ መንገድ እጆቹ እየተቆረጡ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ ለዚህ የቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ መሳካት ሌት ተቀን የደከማችሁትን ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈል፡፡ ‘ ከፊቱ ይልቅ በርቱ’ እንዲል የእግዚአብሔር ቃል ‘ ክፉ ስራዎችን’ ለማጋለጥ የደከማችሁ ወንድሞች እና አባቶችም እስከ ፍፃሜው ድረስ ትፀኑ ዘንድ በኃያሉ መልአክ በቅዱስ ገብርኤል ስም አደራ እንላለን፡፡

ለማጠቃለል ያህል በጉዳዩ ያገባኛል የሚሉ ወገኖች የተናገሩትን እና ስለ ሕንጻ ሥራው የተጠቃለሉ ዕውነቶችን እነሆ
·        ሥራ ተቋራጩ ከሀገር ጠፍቷል፣ አማካሪ መሐንዲስ የለውም- ምእመናን
·        እስካሁን 1.8 ሚሊዮን ብር ጉድለት ያሳያል የጠቅላይ ቤተክህነት ኦድተሮች
·        እስካሁን የተሰበሰበው 11 ሚሊዮን ብር በመሆኑ ጉድለቱ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ነው- ሰበካ ጉባኤው
·        የጎደለው 1.8 ሚሊዮን እንጂ 5 ሚሊዮን አልተሰበሰበም- ህንፃ አሰሪው ኮሚቴ
·        ይህንን 1.8 ሚሊዮን ብር የሰጠነው በፓትርያሪኩ ትዛዝ ነው - ህንጻ አሰሪው
·        ሪፖርቱ ገና የሚስተካከል ነው ለፓትርያሪኩ አመልክተናል - ህንጻ አሰሪው
·        እኛ ያየነውን ችግር አቅርበናል መሸፈን አንችልም- በኩረ ትጉሃን ዓለም አታላይ
·        ጠቅላይ ቤተክህነት የተሳሳተ ሪፖርት ነው የላከው - ህንጻ አሰሪው
·        ምንም ይሁን ምን ሪፖርቱን መስማት አለብን - ምእመናን
·        በሰላማዊ መንገድ እንዲያልቅ ጥረት እናደርጋለን - የደብሩ ሰ/ት/ቤት
·        ውል የተገባው በ19/01/1998 የውለታ ገንዘብ መጠን 2984562.51(ተ.እ.ታ.) ጨምሮ የመጠናቀቂያ ጊዜ 2 ዓመት በዚሁ መሠረት ሥራ ተቋራጩ በ2000 ዓ/ም ሥራውን አጠናቆ ማስረከብ የነበረበት ሲሆን ሥራ ተቋራጩ ግን ሥራውን ከመጀመሪያው አንስቶ ከውለታው ውጭ የሆኑ የይገባኛል ጥያቄዎችን በማንሳትና ከሥራ ተቋራጩ የሚጠበቀውን የውል ግዴታ ሳይወጣ ቤተክርስቲያኒቱና መላውን ህዝበ ክርስቲያን ከፍተኛ ለሆነ ወጭ ዳርጎት ይገኛል፡፡
ችግሮቹን ለመዘርዘር
1.      በዋናው ውል መሰረት የቅድሚያ ክፍያ የተከለከለ ቢሆንም የህንፃ አሰሪ ኮሚቴው የሥራ ተቋራጩ የሚያቀርበውን ጥያቄ በየወቅቱ የነበሩ የፕሮጀክቱ አማካሪ መሀንዲሶች ፍቃድና ይሁንታ ሳያገኝ በተጨማሪም ምንም ዓይነት ዋስትና (advance payment guarantee) ሳያቀርብ ከፍተኛ ገንዘብ በብድር ሰጥቷል ይህ አሰራር በተለይ ከነሀሴ 2002 መጨረሻ ጀምሮ እጃቸውን ባስገቡት የጠቅላይ ቤተክህነት መሀንዲስ በአቶ ሰለሞንና ብርሃኑ ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ እንዲቆጣጠሩ በቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ትዕዛዝ ከውድድር ውጭ በተቀጠረው አቶ  መስፍን ህጋዊ ሽፋን ሰጭነት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ለሥራ ተቋራጩ በቃል ትዕዛዝ እንዲከፈል ተደርጓል፡፡

2.     በመደበኛ የኮንስትራክሽን ስራዎች መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 መሰረት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና 10 በመቶ (10% performance bond) ስራ ተቋራጩ እንዲያሲዝ በተደጋጋሚ በነበሩ አማካሪ መሀንዲሶች ቢጠየቅም በሥራ ተቋራጩ አንቢተኝነትና በኮሚቴው ቸልተኝነት ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

3.     የዋጋ ግሽበትን በተመለከተ በውሉ መሰረት በቋሚ ኮንስትራክሽን መተዳደሪያ ደንብ ዲሴንበር 1994 በአንቀጽ 70 መሰረት የተፈቀደው ለሲሚንቶ፤ ብረትና ነዳጅ ሲሆን ጥያቄው በሥራ ተቋራጩ ከቀረበ በኃላ በአማካሪ መሀንዲስ ከውለታዎች ጋር በማገናዘብ፣ በመመርመር እና በማረጋገጥ ለአሰሪው የክፍያ ምስክር ወረቀቶችን ከማብራርያ ጋር መላክ ያለበት መሆኑን ይገልፃል። ነገር ግን ይህን ፕሮጀክት በተመለከተ ይቀርቡ የነበሩ ጥያቄዎች በተጠቀሱት ዋና ዋና ግብዓቶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የነጠላ ዋጋ ይሻሻልልኝ ጥያቄ የነበረ ሲሆን ይህን ጥያቄ እስከ ነሐሴ 2002 ዓ.ም የነበሩ መሀንዲሶች በአግባቡ ሰርተው ቢያቀርቡም በኮሚቴው ሊቀመንበር ወገንተኝነት ጥረታቸው መና ቀርቷል፡፡ በተጨማሪም የዋጋ ግሽበት ጥያቄ መቅረብ ያለበት በውለታ ጊዜ ውስጥ ላለ ፕሮጀክት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ከሶስት ዓመታት በላይ ያለ በቂ ምክንያት ለዘገየ ሥራ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከላይ በተጠቀሱት ግለሰቦች ሽፋን ሰጭነት ያለ በቂ ምክንያት ለሥራ ተቋራጩ እንዲከፈል ተደርጓል፡፡

4.     በአሁኑ ወቅት ለሥራ ተቋራጩ ጠቅላላ የተከፈለው ገንዘብ ብር 5፣302፣470.07 ሥራውን በአጠቃላይ ከነዋጋ ግሽበቱና ከአንዳንድ የለውጥ ሥራዎች ጨምሮ ፕሮጀክቱን መጨረስ የነበረበት ቢሆንም እስከ መስከረም 2004 ዓ.ም የተሰራው የሥራ መጠን በመቶኛ 65% ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህም በኋላ በዚህ አያያዙ ኮሚቴው ቤተክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ወጪ ሊዳርጋት እንደሚችል ይታሰባል።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ከውስጥ አዋቂዎች

17 comments:

 1. ውይ ምነው በሞትኩት የማህበረ ቅዱሳንን ስም ሳታነሱ? በሰላም ነው?

  ReplyDelete
 2. ቃለ ህይወት ያሰማችሁ አይዞን የእውነት የእምነቱ አባት አቡነ አብርሃም እየመጡ ነውና ተጠርገው ይወጣሉ መናፍቁም ሌባውም ወዮለት።

  ReplyDelete
 3. mkn kezerafiwochu wust endet alakatetachihutm? Eresachihut?

  ReplyDelete
 4. ውይ በሞትኩት ላልከው------- ማኅበረ ቅዱሳንን ሳታነሱ ብትል እኔ ላንሳልህ ከዚህ ጉዳይ ጋር ጨምሬ።
  ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ዓይነቱን ዓይነ ያወጣ ሌብነት የማያውቅ ይመስልሃል? ምንም ዓይነት እውቀት የለውም ብትል ዲያቆን ዳንኤል ክስረት የገለጸልን የማኅበረ ቅዱሳን የስለላ መዋቅር ስራውን አልሰራም ማለት ነው። የሆኖ ሆኖ ማኅበረ ቅዱሳን በደንብ ያውቀዋል።በድሬ ዳዋ የማቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኩል የሀገረ ስብከቱ የስራ ሪፖርት ወይም በደብሩ ሰንበት ት/ቤት በኩል እያንዳንዱ እስትንፋስ ይደርሰዋል። ይሁን እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን በየትኛውም ቤተክርስቲያን ገንዘብ ቢመዘበር ትንፍሽ አይልም።በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ሙዳየ ምጽዋት ሲገለበጥ ያውቃል ግን ማቅ ዝም ጭጭ ነው መልሱ። ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከአንዴም ሁለቴ በላይ ሙዳየ ምጽዋት ተዘርፏል፤ በኡራኤል ቤተክርስቲያን በአባ እዝራ አስተዳዳሪነት ሙዳየ ምጽዋት ተዘርፏል፤ ከህንጻው ግንባታ ውስጥ በሚሊዮኖች መጉደሉ ይታዋቃል። በቦሌ መድኃኔዓለም ህንጻ፤ በልደታ፤ በራጉኤል ህንጻዎች መዘረፉ ሀገር ያወቀው፤ጸሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። አባ አብርሃም(ቃለጽድቅ) የተባለው ዘመናዊ ሌባ የራጉኤል የበላይ ጠባቂ በሚል ስም አባ ዮናስ የተባለውን የአቡነ መልከጼዴቅ ዘመድ ከራጉኤል አስተዳዳሪነት ያስነሳው 500 ሺህ ብር ቼክ አልፈርምልህም በማለቱ ነው። ይህ ሌባ ጳጳስ የማቅ አባል ስለሆነ ይህንን ሐቅ ያወጣበት ማንም የለም። በ1994 የማቅ የዘረፋና ራሱን የቻለ የንግድ ተቋም እንዲሆን መተዳደሪያ ደንብ እንዲጸድቅለት ከፍተኛውን ስራ የሰራው ይህ አብርሃም የተባለው የቤተክርስቲያን መዥገር የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ በነበረበት ጊዜ መሆኑን እናውቃለን። ለቤተክርስቲያን መበጥበጥ መንገድ የከፈተ ሕግ እና አባ ሠረቀ ብርሃንም በዚህ መደዴ ህግ መቆጣጠር እንዳይችል የተደረገው በእነዚህ ሌባ ሰዎች የቆየ መጥፎ ስራ ነው። በአጠቃላይ ማቅ ዘረፋና ሌብነት በተመለከተ አንድም ጊዜ፤ በየትኛውም ቤተክርስቲያን ስላለው ተናግሮ አያውቅም። አይጥ እንደጎረሰ ድመት «እምምምምምም» ብቻ ነው ድምጹ። ለምን መሰላችሁ? ራሱ ነጋዴ ነዋ! ሸቀጡን የሚያራግፈው፤ እየዞረ በስብከትና በመዋጮ ስም የሚመዘብር ድርጅት ነዋ!! የትኛውንም ያህል ሌብነት ቢኖርና ቢሰማ ማቅ ትንፍሽ አይልም። ከሌቦች ጋር ተላትሞ ዓላማውን ከማሳካት ወደኋላ መቅረት ስለማይፈልግ በባሌም ይሁን በቦሌ አባ ጳውሎስን ፈንግዬ ፓትርያርክነቱን ለታማኝ አገልጋዬ ጳጳስ ከሰጠሁ ሌላው ሁሉ ቀላል ነው ከሚል ፈሊጥ የተነሳ ነው። እናም «ውይ በሞትኩት የማኅበረ ቅዱሳንን ስም ሳታነሱት» ላልከው አልቃሽ ተቆርቋሪ ይኸው እኔ አነሳሁልህ! አሁንስ ደስ አለህ ወይስ ከፋህ? ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ሁሉ ሌብነትና ምዝበራ ያውቃል፤ ግን ትንፍሽ አይልም። ተሃድሶ ለሚባሉት የድምጽ መቅጃና የሰው ሰላይ ሲመድብና ለማጋለጥ ሲደክም በግልጽ የሚሰራውን የማያውቅ አይምሰልህ።ራሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ የመሸገ ነጋዴ በመሆኑ «ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠ» ማቴ ፳፩፣፪ እንዳለው ይህንን ቀን የሚጠብቅ ስለሆነ እንደረበናተ አይሁድ ንግዱና ዘረፋው፤ በቤተመቅደሱ አደባባይ እየተሸጠ፤ እየተለወጠ እያዩ ዝም ብለው ነገር ግን ስለቤተክርስቲያን ሥርዓት ለመከራከር በሰንበት ያልተፈቀደውን ታደርጋለህ፤ በሰንበት ትፈውሳለህ፤ ህጋችንን ትቃወማለህ፤ በማን ስልጣን ይህን ታደርጋለህ? እንዳሉት ተሃድሶ ህጋችንን ይጥሳል፤ ያልተፈቀደውን ይሰራል፤ እኛን ይቃወማል በማለት እንደግብር አባቶቻቸው በመክሰስ ተጠምደዋል።
  ደግሞም በትንሽ በትንሹ ስለማቅ ነውራምነት የምትወጣው ጽሁፍ ዋጋ አላት። «የዝናብ ጠብታ ቀስ በቀስ ድንጋይ ይሰብራል»

  ReplyDelete
 5. ውይ ምነው በሞትኩት የማህበረ ቅዱሳንን ስም ሳታነሱ? በሰላም ነው?እነዴት አሰቻላችሁ ??? ማህበረ ቅዱሳንን ያኔ አልነበረም እነዴ ???

  ReplyDelete
 6. አባ ሰላማዎች ከጀርባው ማህበረ ቅዱሳን የለበትም? እባክችሁ አጣርታችሁ ሪፖርት አድርጉልን።

  ReplyDelete
 7. May God bless you who wrote this article

  ReplyDelete
 8. «ውይ በሞትኩት የማኅበረ ቅዱሳንን ስም ሳታነሱት» ላልከው አልቃሽ ተቆርቋሪ ይኸው እኔ አነሳሁልህ!

  ተሃድሶ ለሚባሉት የድምጽ መቅጃና የሰው ሰላይ ሲመድብና ለማጋለጥ ሲደክም በግልጽ የሚሰራውን የማያውቅ አይምሰልህ።
  I'm glad you mentioned MK! otherwise you don't paid for your post from mulu wonjel.

  wow! Last week you were crying for Aba Paulos. This week you are crying by Aba paulos??
  You want to get rid off him???

  Conffffuseeddd!!!!!
  tehadiso confused!

  ReplyDelete
 9. እኔ በጽሑፉ እረክቻለሁ በርቱ ለውጥ ያመጣል:: ግን ቅዱሳን ላይ ያላችሁ አመለካከት ጥሩ አይደለም:: በዚህ በኩል ማቅን እወደዋለሁ:: አሁን አሁን ግን በተለያዩ ብሎጎቹ የአባቶችን ክብር (ከአናቱ ጀምሮ) መዳፈሩ እና ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠቱ አልተመቸኝም:: እናንተንም ጨምሮ ማለቴ ነው:: የጳጳሳቱን ነውር እዚህ ላይ መጻፉ ማንን ይሆን የሚያስደስተው? ከካም ድፍረት የሴም ኃፍረት አይሻልምወይ?

  ReplyDelete
 10. ማቅ ማኅበሩ ራሱ አገባሻለሁ፤ ከድቼሻለሁ፤ ትቼሻለሁ በተባሉ መበለታትና የመበለታት ቀማሾች የተሞላ ነው። ማቅ የቤተክርስቲያን ጥቁር የሀዘን ልብስ ነው እንደስሙ። እምነት ሳይሆን ባህል የሚያመልክ የብልጦችና የጅሎች ስብስብ ነው። ብልጦቹ ገንዘብ የሚገኝበት መሆኑን አሳምረው ያውቃሉ፤ እየሰሩ ያሉት ትክክል አለመሆኑም ቢያውቁም በጥቃቅንና አነስተኛ ከመደራጀት ይህ ሃይማኖትን ከለላ ያደረገ ግብርና ታክስ የሌለው ተቋም ይሻላቸዋልና አመራራቸውን በጥበብ ይመሩታል። ጅሎቹ ሴቶችና ወጣት ወንዶች ገንዘባቸውን እየገፈገፉ፤ነጠላቸውን መስቀለኛ አጣፍተው ከበሮ ሲደልቁና ማቅ ቅዱሱ እያሉ ዋናዋን ቤተክርስቲያን ለማቅ የማትመች ደካማና የተሃድሶ መፈልፈያ ሲሏት ይውላሉ። እንግዲህ ማቅ ማለት ይህን ነው። ልጆቿ አልቀው የተረፋት ጥቁር የሀዘን ልብስ፤ማቅ!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. Thank You Aba for the information. Things are becoming very band in our church. MK in one side which is terrorizing the church, tehadiso in the other side working for others and corrupted people are are trying to destroy the church.

  ReplyDelete
 12. ስድብ እርኩሰት መሆኑን የማወቅ ልብ በሰጣችሁ። ወንድሙን የሰደበ የእግዚአብሔር መንፈስ የለውም ከሰደበኝ ደግሞ የነገረኝ ይባላል እና ይቅር ግን እንዲህ ያለእፍረት አባቶችን እና ለቅድስና የሚተጉ ክርስቲያን እህት ወንድሞችን በመሳደብ የራሰ ህሊና ፣ አንደበትና ፣ ልብ....ትገርማላችሁ ብገኑ እንጂ ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን አሳልፈን አንሰጥም።

  ReplyDelete
 13. @ anon 6:24
  You thank aba who work for tehadeso and corrupted people in our church. Seriously? You thank them for what? They involve in this shemless activity to get support from the patriaric.

  ReplyDelete
 14. In each single corruption mk might be behind the bar, furthermore mk a master mind of all fishy things that happened to the church.

  ReplyDelete
 15. ማ/ቅ አያውቅም ላልከው ምስኪን ወንድሜ በጣም ያውቃል ያልተማረውን በቅርብ ቀን ዲ/ን የሚል ቅጽል የተሰጠው ድንበሩ ነው ደንባራው የተባለውን የሐረርጌ የስለላ ሀላፊ በማድረግ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ያውቃል ይደርሰዋልም ግን ማቅ ምን አገባው ተሃድሶ እያለ ወንጌላውያንን ያሳድ እንጂ ቤተክርስቲያን ብትዘረፍ ምን እሱ ያጣል እሱስ ዘራፊ አይደለም እንደ ፡፡ የሚገርመው ሰሞኑን አንዲ ጋዜጠኛ ሲነግረኝ ህንጻው ሲዘረፍ ማቅ ምን ተሰማው ብሎ ድንበሩን ሲጠይቀው የጠቅላይ ቤተክህነትን እሪፖርት ሌሎችንም መረጃዎች ታቅፎ እኛ አልሰማንም ነበር ያለው አናውቅም ነበር ያለው ይህንን አለም ያውቀውን ድራማ ለምን ማቅ ደና ይሁን እንጂ እሱ ምን ቸገረው እንኳን ይህንን ትልቁን ጉዳይ አንተነህ ፣ ድርሻ፣ ወንደየ፣ ዮናስ እና ኤርሚያስ ሌሎችም ቅጥረኞችን በማሰማራት አለቃው ሁለት ድቃላ እንደወለዱ ያውቃል ግን ጉዳዩ አይደለም የሚገርመው ግን ሰ/ት/ቤት በመምጣት ወጣ ብለው የሚያገለግሉትን ሁለቱን ቴድሮሶች መ/ር ቢንያምን ተሃድሶ ናቸው አባሯቸው በማለት የሱ ቅጥረኛች ይችሉ ይመስል አሳብቆ ሔዶል ስለ ህንጻው ሲያነሱበት ግን ተው እሱን ካላይስ ቢሆን እየተበላ አይደል እነዚህስ ወንድሞቻችን ናቸው ይብሉት ነበር ያለው አቡነ ጳውሎስ 60000000 ብር አይደል እንደ የደፍት ብሏቸው ነው የሄደው ምስኪን ወንድሞችን አባሩ ሲል እኛን የቸገረንን ህንጻውን ግን ምንም አላለም ስለዚህ ማቅ አባላቶቹ ያውቃሉ ግን ለነሱ ሀይማኖታቸው ማቅ ደህና ይሁን እንጂ ምን ቸገራቸው ቤካ ነኝ

  ReplyDelete
 16. ስለ ህንጻ ነው የጨነቃችሁ ወይስ የማ.ቅ ጉዳይ
  ስለ ህንጻ ስነሳ ለማዘናጋት በአውደ ምህረት ተሳዳቢ ጋብዞ ማ.ቅን ሲያሰድብ የከረሙት
  አብረው ከበሉ በኃላ ማ.ቅ ለምን ዝም አለ ማለት ዝምታ ምንድነው
  አጀንዳውን እንደምንም ከማ.ቅ ለማገናኘት ከሆነ አይምሰላችሁ
  ሌባ መፍጨርጭ አመሉ ነው፡፡
  ስለ ህንጻ ነው የጨነቃችሁ ወይስ የማ.ቅ ጉዳይ
  ስለ ህንጻ ስነሳ ለማዘናጋት በአውደ ምህረት ተሳዳቢ ጋብዞ ማ.ቅን ሲያሰድብ የከረሙት
  አብረው ከበሉ በኃላ ማ.ቅ ለምን ዝም አለ ማለት ዝምታ ምንድነው
  አጀንዳውን እንደምንም ከማ.ቅ ለማገናኘት ከሆነ አይምሰላችሁ
  ሌባ መፍጨርጭ አመሉ ነው፡፡

  ReplyDelete
 17. ቤ/ንን መበዝበዝ በድሬዳዋ በግልጽ በኦዲት የተረጋገጠ መሆኑን
  ለመረዳት ተችሏል፡፡ በወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት አይን ያወጣ በአንድ መስሪያቤት
  በሁለትና በሶስት ፔሮል ደሞዝ መቀበል የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ እነ ዘሪሁን፣አለማየሁ፣ አስቻለው፣አፈወርቅ የመሳሰሉት በሦስትና አራት ፔሮል ሲከፈላቸው ነበር፡፡
  የደልቦ ገብርኤል አስተዳዳሪ ከዚያም የሀ/ስብከቱ ሥ/አስኪያጅ ከደልቦ ብቻ መኪና ገዝተው እንደነበር
  ይታወቃል፡፡ ብዙ ወጣቶች እነ አቡሎ የመሳሰሉት ሰሚ አጡ እጂ ተቆርቋሪ ነበሩ፡፡ የተ/ሃይማኖት
  ገዳም ህንጻ ከተጀመረ ስንት አመቱ፤እውነት ገንዘብ ጠፍቶ? የወላይታው ጉድ የሚያወጣው ጠፍቶ እንጂ፡፡ የሀገር ሀብት በሀይማኖት ሰበብ ሲመዘበር መንግስት ዝም ማለት የለበትም፡፡ ይሔ ጣልቃ መግባት አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete