Thursday, November 17, 2011

ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠ የፈጣሪ ስፍራ - - - Read PDF

የተቀበረ መክሊት ከተሰኘው መጽሐፍ ገጽ 52-57 የተወሰደ
ስለዚህ ጉዳይ ከመመልከታችን በፊት ስለ መላእክት ጥቂት ግንዛቤ መጨበጡ ተገቢ ነው፡፡ መላእክት በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ረቂቃን መናፍስት ሲሆኑ የተፈጠሩበትም ዓላማ እግዚአብሔርን እያገለገሉ ፈቃዱን ለመፈጸም እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል (ዕብ. 1፥7፡10፤ መዝ. 102፥ 20) ፡፡ የሚሰጡትም አገልግሎት የተለያየ ነው፡፡ ይኸውም፡-
 • v  እግዚአብሔርን ዘወትር ያለ እረፍት በምስጋናና በስግደት ያመልኩታል (ኢሳ. 6፥2-3 ፤ ዳን. 7፥9-10፤ ሉቃ. 2፥13 ፤ ራእ. 5፥11-14 ፤ 7፥11-12 ፤ ዕብ. 1፥6)
 • v  የእግዚአብሔርን መልእክት ለሚመለከታቸው ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡ ወደ ቅዱሳን ሰዎች የሚመጡት ግን ከእግዚአብሔር ሲላኩ ብቻ ነው (ሉቃ. 1 ፥11-20፤ 26-38፤ ዳን. 9፥23 ፤ 10፥12) ፡፡
 • v  እያንዳንዱን ምእመን ይረዳሉ፤ ክፉውንም ተከላክለው ያድናሉ (መዝ. 33፥7፤ 90፥12፤ ዕብ. 1፥14)፡፡
 • v  የሕጻናትን ነፍስ ይጠብቃሉ (ማቴ. 2፥13 ፤ 20፥ 18፡10)፡፡
 • v  በዓለም የእግዚአብሔርን ፍርድ ያከናውናሉ፤ ኃጢአተኞችንም ይቀጣሉ (2ሳሙ. 24፥16፤ የሐዋ. ሥራ 12፥23፤ ዘፍ. 19፥2፤ 2ነገ. 19፥35)፡፡
 • v  ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ በብዛት ሆነው ያጅቡታል (ማር. 8፥38 ፤ 2ተሰ. 1፥7)፡፡
 • v  የተፈረደባቸውን ወደ ዘላለም ኩነኔ በመጣል የተመረጡትን ደግሞ ይሰበስባሉ (ማቴ. 13፥39፤ 49) ፡፡
 • v  ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልጋትን ይመለከታሉ (የሐዋ. ሥራ 5፥19፤ 8፥26 ፤ 1ጢሞ. 5፥21)፡፡
 • v  ንሰሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ ደስ ይላቸዋል (ሉቃ. 15፥10)፡፡
 • v  በክርስቶስ ለሰዎች የተደረገውን ጥበብ ሊመለከቱ ይሻሉ (ኤፌ. 3፥10 ፤ 1ጴጥ 1፥12) ፡፡
ይህን ተግባር ከሚያከናውኑት መካከል አንዱና በመላእክት ላይ አለቅነት ያለው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ የመላእክት ማንነትና አገልግሎት ከላይ እንደ ተገለጸው ሆኖ ሳለ ለቅዱስ ሚካኤል የአምላክን ስፍራና ክብር መስጠት በሌላም በኩል ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያላደረገውን ነገር ሁሉ አድርጓል በማለት መዋሸት በእውነት ሚዛን ላይ ተመዝኖ ቀሎ መገኘት ነው፡፡
          መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገውን ነገር ሲናገር ስሙን ጭምር ይጠቅሳል (ዳን. 10፥13-21፤ 21፥1፤ ይሁ. 9፤ ራእ. 12፥7)፡፡ ሚካኤል በተጻፈው መሠረት እንጂ በውሸት የፈጠራ ድርሰት አይከብርም፡፡ እስቲ በመጽሐፈ ዚቅ ለእርሱ የተሰጠውን የእግዚአብሔር ስፍራ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማነጻጸር እንመልከት፡፡
ሀ/ “ቦኑ ኢትክል አድኅኖ እዴየ ወቦኑ ዘኢይሰምዕ በእዝንየ አክብሩ በዓልየ ወሑር በሕግየ ትበልዑ ከራሜ ፥ ከራሜ፥ ከራሜ እምበረከቱ”
ትርጓሜ፡- “ሚካኤል አለ፥ በውኑ እጄ ማዳን አትችልምን? በጆሮዬስ የማልሰማ ነኝን? በዓሌን አክብሩ፥ ሕጌንም ጠብቁ፥ ከሥራዬ ፍሬ ከበረከቴም የከረመውን ትበላላችሁ” (የመስከረም ሚካኤል ዚቅ)
እንደ ደራሲዎቹ የሐሰት ምስክርነት ይህን ቃል የተናገረው ሚካኤል ሳይሆን የሚካኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡ (ዘሌዋ. 24፥ 18-22፤ ኢሳ 59፥1) “በዓሌን አክብሩ፤ ሕጌንም ጠብቁ፤ ከሥራዬ ፍሬ ከበረከቴም ትበላላችሉ” ለማለት የተገባው ከአንዱ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር በቀር ማነው? (መዝ. 103፥13)፡፡
 “ሚካኤል በዓሌን አክብሩ” አለ ብለው እየዋሹ እውነቱን እንድንመሰክር ካነሳሡን የሚካኤል በዓል አከባበር በተለይም የኅዳር ሚካኤል እንዴት መከበር እንደ ጀመረ ታሪካዊ የት መጣውን ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ማስረጃ በማቅረብ መመልከት እንችላለል፡፡
“በግብጽ አገር ‘ዙሐል’ ተብሎ የሚጠራ ጣኦት ነበር፤ የግብጽ ሰዎች ከሌሎች ጣዖታት እጅግ አደርገው ያከብሩታልና ያመልኩት ነበር፡፡ ከሐዋሪያው ቅዱስ ማርቆስ ቀጥለው የተሾሙ ብፁዓን ጳጳሳት ቅዱሳን አበውም ሁሉ የዙሐልን ተመላኪነትና ተከባሪነት ማስቀረት ሳይቻላቸውም እስከ 320 ዓ.ም. ያህል የግብጽ ሰዎች ሲሰግዱለት ሲያመልኩት ኖርዋል፡፡
“ዙሑል ከቀሩት ጣዖታት የበለጠ ተአምራታዊ ኃይል ወይም የተለየ ምትሀት ኑሮት ሳይሆን የቀሩት ጣዖቶች አንድ በአንድ ሲወድቁና ሲደመሰሱ የግብጽ ሕዝብ አልተጋፋም ነበር፡፡ ዙሐልን የደፈርን እንደሆነ ግን ሕዝብ ይነሣብናል በማለት ፈርተው ነበር፡፡ በተጠቀሰው ዓ.ም ግን የእስክንድርያው ሊቀጳጳስ አባ እለእስክንድሮስ እንደምንም ብሎ ሕዝቡን እያግባባና እያስተባበረ እያባበለም ብዙዎችን በማስረዳትና በማሳመን “ዙሐል” ከምኩራበ ጣኦትነቱ ተነሥቶ በምትኩ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት እንዲገባበት አድርጎ የዙሐል በዓል በየዓመቱ ኅዳር 12 ቀን ይከበር ስለ ነበረ ‘ኀዲገ ልማድ ጽኑዕ ውእቱ’ ነውና ሕዝቡን ለማስደሰት ሲል በዚያው በተለመደው ኅዳር 12 ቀን ይከበር ብሎ ዐዋጅ አስነግሮ ዐዋጁም ጸደቀ (መርሐ ጽድቅ ባህለ ሃይማኖት ገጽ 152-153)
የእግዚአብሔር እውነተኛና ታማኝ አገልጋይ ምንግዜም ቢሆን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ለማስደሰት ሲል አይኖርም፡፡ አሊያማ የእግዚአሔር አገልጋይ ሊባል አይችልም፡፡ “ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም፡፡” (ገላ. 1፥10፤ 1ተሰ. 2፥4)፡፡ 
የኅዳር ሚካኤል በዓል አከባበር የት መጣው እንዲህ ሆኖ ሳለ ዛሬ ግን በዕለቱ የሚነገረው የዙሐልን በዓል ለማስቀረት ባለመቻሉ በምትክነት የተሠራ በዓል መሆኑ ሳይሆን “ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ያወጣበት ቀን” ተብሎ ነው የሚከበረው፡፡ ከመጽሐፍ ዚቅ የሚዘመረውም እንዲህ ይላል “አንተኑ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ለእስራኤል ዘአውረድከ መና ” ትርጉም “ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሆይ ለእስራኤል መና ያወረድህላቸው እኮ አንተ ነህ” አቤት ክህደት! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋእለ ስብከቱ ለእስራኤል መና ያወረደላቸው አባቱ መሆኑን በግልጥ ተናግሯል ዮሐ 6፥31-32 ደብተራዎቻችን ህዳር 12 በሚከበረው የዙኃል በአል ሚካኤልን ለእስራኤል መና ያወረድህላቸው አንተ ነህ እኮ እያሉ የእግዚአብሔርን ምሥጋና ለፍጡር እየሰጡ ሲዘባበቱ እንደሚያድሩ በእለቱ በዓሉ ወደሚከበርበት ቦታ በመሄድ መታዘብ ይቻላል።
መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ማውጣቱን አይናገርም፡፡ እርግጥ እግዚአብሔር ሚካኤልን ልኮ ህዝቡን ከግብጻውያን እጅ ሊያድናቸው ይችላል፡፡ እንዲያውም በዘመኑ መጨረሻ በክርስቶስ አዳኝነት አምነው ለሚድኑት የእስራኤል ቅሬታዎች ሚካኤል እንደሚቆም [እንደሚዋጋላቸው] የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል (ዳን. 12፥1 ፤ ራእ. 12፥7)፡፡ ነገር ግን ህዝበ እስራኤል ከምድረ ግብጽ ሲወጡ በፊታቸው የወጣው መልአክ ሚካኤል ነው አይልም (ዘጸ. 3፥2-6 ፤ 23፥20-23 ሐዋ. ሥራ 7፥30-34)፡፡ ስሙ በግልጽ ያልተጠቀሰው ይህ የጌታ መልአክ ፍጡር የሆነ መልአክ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ወልድ፣ በአርአያ መልአክ ተገልጾ መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ስፍራ ያስተምረናል (ዘዳ. 32፥12፤ መሳ. 2፥1-5፤ 6፥8-9፤ መዝ. 135፥16፤ 104፥43፤ ኤር. 32፥21፤ ሆሴ. 12፥14) ፡፡
ሰይፈ ስላሴ የተሰኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ የጸሎት መጽሐፍ ገና በምድረ በዳ በቁጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ለሙሴ የታየውና ህዝቡን የመራ የእግዚአብሔር መልአክ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን እንዲህ በማለት ገልጾታል፡- “ስብሐት ለመልአከ እግዚአብሔር ዘአስተርአዮ ለሙሴ በነደ እሳት በኀበ ዕፀ ጳጦስ መልአክኒ ወልደ እግዚአብሔር ውእቱ ”
ትርጓሜ፡- “በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል በእሳት ነበልባል ሙሴን ለታየው ለእግዚአብሔር መልአክ ክብር ይሁን፡፡ መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው፡፡” (ሰይፈ ስላሴ ዘረቡዕ)
ሙሴና ህዝበ እስራኤል ፍጡር መልአክ (ሚካኤል) ሳይሆን ጌታ ራሱ ነጻ እንዳወጣቸውና የሚመራቸውም እርሱ ራሱ መሆኑን ተረድተዋል፡፡ በጣኦት አምልኮ እስካሳዘኑት ጊዜ ድረስም አብሮአቸው የተጓዘው እግዘአብሔር እንደነበር፥ ከዚህ በኋላ ግን እርሱ አብሮአቸው እንደማይወጣና ሌላ ፍጡር የሆነ መልአክ እንደሚልክላቸው መናገሩ ብቻ እንኳ በቂ ማስረጃ ሲሆን፣ ይህን ሁኔታ የሰሙት ሙሴና ወገኖቹ በፍጡር መልአክ በመመራትና በራሱ በእግዚአብሔር በመመራት መካከል ታላቅ ልዩነት አለና በሰሙት ክፉ ወሬ ማዘናቸው የነገሩን እውነተኛነት ያረጋግጥልናል (ዘጸ. 33፥1-4) ፡፡
ሙሴ እግዚአብሔር የተናገረውን ከሰማ በኋላ “አንተ ከኛ ጋር ካልወጣህስ ከዚህ አታውጣን” በማለት መለሰ፡፡ እግዚአብሔርም የሙሴን ጥያቄ ተቀብሎ ራሱ አብሯአቸው ለመውጣት ተስማማ (ዘጸ 33፥ 14-17) ፡፡
እርሱም ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ የሆነ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ በተለየ ግብሩ ልጅ ነውና ልጅነቱን ለአባቱ የሚታዘዝ፥ የሚላክ፥ ጻድቅ ባሪያ፥ ቅን አገልጋይ፥ ፈቃድ ፈጻሚ በመሆን አስመስክሯል፡፡ (ኢሳ. 42፥1፤ 52፥13-15፤ 53፥11፤ ዮሐ. 17፥1-5፤ ዕብ 5፥8)፡፡
ቃሉን ላከ ፈወሳቸው ተብሎ እንደተጻፈው (መዝ. 106፤20) እግዚአብሔር በአርአያ መልአክ ወደ ሕዝቡ የላከው አካላዊ ቃሉን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ እርሱም በዘመነ ሥጋዌው አይሁድ “አንተ ማነህ?” በማለት ላቀረቡለት ጥያቄ ሲመልስ “ከመጀመሪያ ለእናንተ የተናገርሁት ነኝ” በማለት እርሱነቱን ገልጿል (ዮሐ. 8፥25)፡፡ በዚህም ሕዝቡን በክርስቶስ ያሉ የክርስቶስ ሕዝብ አሰኝቷል (በኤፌ. 2፥12፤ ዕብ. 11፥25-26) ፡፡
መላክ የልጅነት ግብሩ መሆኑንም በቃሉ አረጋግጦአል (ዮሐ. 7፥28-29፤ 8፥26) በሌላም አኳኋን ቅዱስ ጳውሎስ ሕዝበ እስራኤልን በምድረ በዳ እየተከተለ ውሃ ያጠጣቸው ዐለት ክርስቶስ መሆኑን መስክሯል (1ቆሮ. 10፥4)፡፡
ይህም ብቻ አይደለም ሙሴ “እባክህን ክብርህን አሳየኝ” ሲል ላቀረበው ጥያቄ “ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም … እነሆ ስፍራ በእኔ ዘንድ አለ፡፡ በዐለቱም ላይ ትቆማለህ፥ ክብሬም ባለፈ ጊዜ በሰንጣቃው ዐለት አኖርሃለሁ፡፡ እስካልፍ ድረስ እጄን በላይህ እጋርዳለሁ፡፡ እጄንም ፈቀቅ አደርጋለሁ፡፡ ጀርባዬንም ታያለህ ፊቴን ግን አታይም” የሚል መልስ ከእግዚአብሔር ተሰጠው (ዘጸ. 33፥18-23)፡፡
እግዚአብሔር በመለኮታዊ ባሕርዩ ለመታየት ባይችልም የክርስቶስ አምሳል በነበረው ዐለት ለሙሴ ክብሩን አሳይቷል፡፡ ዛሬም ቢሆን እግዚአብሔርን ለማየት የሚችል የለም፡፡ ለሙሴ በምሳሌው ዐለት ላይ ክብሩን እንዳሳየ ሁሉ በአማናዊው፥ በእቅፉ ባለውና የመለኮቱ ሙላት በተገለጸበት የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ በሆነው ሥጋን ለብሶ በመጣው በክርስቶስ እግዚአብሔር ተገልጧል (ዮሐ. 1፥18 ፤ ቁላ. 2፥9፤ ዕብ. 1፥3 ፤ዮሐ. 14፥9፤ 1፥14) ፡፡
እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያለብን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአርአያ መልአክ፣ በአርአያ ኰኲሕ ተገለጸ ማለት እርሱ ፍጡር መልአክ ነው፥ ወይም ደግሞ የዘመኑ አርዮሳውያን አፋቸውን ሞልተው እንደሚናገሩት “ኢየሱስ ሚካኤል ነው” ማለት አይደለም፡፡ (ሎቱ ስብሐት! ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን!) ነገር ግን በመልአክ አምሳል ተገልጾ ሕዝቡን መራ፤ እኛንም ሰው ሆኖ አዳነን እንጂ፥ “ወበእንተ ዝንቱ ተሰምየ ውስተ መጻሕፍት ወልደ እጓለ እመሕያው በእንተ ሥርዓተ ትስብእቱ፤ ወዓዲ ተሰምየ እግዚአብሔር፥ ወልደ እግዚአብሔር፥ ወመልአከ፥ ወመዝራእተ፥ ወነቢየ፥ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ አምላክ፤ ወዓዲ ብዙኀ ጊዜያተ የዐውቆ ከመ ውእቱ ሰብእ

ትርጓሜ፡- “ስለዚህም ሰው ስለሆነ በመጻሕፍት ውስጥ የሰው ልጅ ተባለ፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ልጅ፥ መልአክ፥ ክንድ፥ ነቢይ፥ ተባለ፡፡ አምላክ እንደሆነ መላልሶ መጽሐፍ ያስረዳል፡፡ ሰውም እንደሆነ መላልሶ ያስረዳል” (ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 83 ቁ. 12 ፤ ጮራ መንፈሳዊ መጽሔት ቁጥር 6 እና 7)፡፡

   እግዚአብሔር መላእክቱን ያከብራል ምስጋናውንና ክብሩን ግን ለሌላ እንደማይሰጥ ተናግሯልና እንጠንቀቅ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው ክብሬን ለሌላ፤ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም” ኢሳ 42፥8፤ 48፥11።

 ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን አሜን!

17 comments:

 1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን አሜን

  ReplyDelete
 2. good job , i like O my God

  ReplyDelete
 3. ደጀ ሰላማዎች እንዴት ናችሁ ስለ ቅዱሳን መላእክት የጻፋችሁት ጥሩ ነው ይበል ብለናል። ነገር ግን አማላጅነታቸውን ለምን ተዋችሁት????????

  ReplyDelete
 4. I went through the article found it that you do really have well planed message to transfer, ...I couldn't find the main duty of holy angles i.e. intercession (yekedusan melaekte meleja)among the 10 listed duties. I don't think that it is unintentional, so I can easily guess who you guys really are. In fact I do have several suspect on you, now your article reveals the whole issue.
  Why don't you practice what you believe plainly by wearing your own cloth, rather than hiding your self this way.
  AmdeMariam!

  ReplyDelete
 5. መናፍቅ ማለት
  መና፦ ከንቱ
  ፍቅ ፦እየፋቀ የሚወስድ
  ይህ ከላይ የተሰጠው ትርጉም ባህታዊ ነን የሚሉ አስተማሪዎች ነው :ይሁንና ትርጉሙ ለእናንተ ይሰራል::

  ReplyDelete
 6. I can't leave you today by reading only. Whether you post it or not I am going to give you some advice for you about your fault here.
  Do You know What you have written in this sentence? You are insulting and telling us that Our Lord Jesus Christ is as in this sentence which is completely out of the true Bible words.
  You <Kehadiwoch< it is better to think than sink in to the fire. It was better for you ask some one who knows better than you before you post this article. The article exposes your identity on the sun than educating others to be your followers.

  ReplyDelete
 7. open you mind hear,analyses then follow the truth.

  ReplyDelete
 8. where is my comment?

  ReplyDelete
 9. መልአክ የሚለውን ለማየት የግስ ዘሮቹን መመልከት ይጠቅማል። ይህንን በተመለከተ ዓይናማው የቤተክርስቲያን ሊቅ የነበሩት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(በማቅ ተሃድሶ ተብለዋል) «መጽሐፈ፡ሰዋስው፡ወግስ፡ወመዝገበ፡ቃላት፡ሐዲስ» በተሰኘው መጽሐፋቸው ገጽ 549 ላይ እንዲህ ሲሉ አትተዋል። ልኢክ፤ ልኢኮት(ለአከ፤ይልእክ) መላክ፤መስደድ ማለት ሲሆን ባለቤቱን ሲያመልክት ለአኪ ማለት ላኪ፤ ሰዳጅ ማለት ነው። መልአክ ማለት በቁሙ ሹመኛ፣ አለቃ ሲሆን በረቂቃን ፍጥረታት አጠራር ደግሞ በእለተ እሁድ ተፈጥረዋል የሚባሉትን የእግዚአብሔር መላእክቶችን ስም ይወክላል። ከዚህ የትርጉም ጽንሰ ሃሳብ የምንረዳው መላእክት ማለት የሚላኩ፣ የሚታዘዙ ፍጥረታት ሲሆኑ ላኪያቸው ወይም ሰዳጃቸው የፈጠራቸው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። በእለተ እሁድ ተፈጥረዋል የተባሉት መላእክት ማለት እንግዲህ የወደቁትንም መላእክት ጨምሮ ነው። የወደቁት መላእክት ላኪያቸውንና ሰዳጃቸውን ለመታዘዝ ባለመፈለጋቸው ከእግዚአብሔር ቅዱሳን የመባል ሀገር ወጥተው በጭለማ ሀገርና አሰራር ወዲያና ወዲህ እያሉ የሚኖሩ መላእክት ሆነዋል። ቅዱሳኑ መላእክት በጌታ ሲላኩ አይተናል። «ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ፦ ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ አለ» የሐዋ 12፣11 ጴጥሮስን ሄዶ እንዲያድን የላከው ጌታ ነው። መልአኩ የተላከውም ጴጥሮስን እንዲያድን ነው። ቅዱሳን መላእክት እንደስማቸው ለሚገዙለት ጌታ ይላካሉ። አድኑ የተባሉትን ያድናሉ። እንዲሁም በመጨረሻው ዘመንም ቅዱሳኑ መላእክት እንደሚላኩ እናነባለን። «በዚያን ጊዜም መላእክትን ይልካል ከአራቱ ነፋሳትም ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ የተመረጡትን ይሰበስባቸዋል» ማር13፣27 እንዲህም የሚል አለ፤ «በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ»ዘጸ23፣20
  እንግዲህ ቅዱሳኑ መላእክት ከምስጋና ከተማቸው፤ ሊታዘዙና ሊገዙለት ከወደዱበት የአምላካቸው ቃል (ልኢክ፣ልኢኮት) ሲደርሳቸው ብቻ ይወጣሉ እንጂ እንደወደቁት መላእክት በገዛ ፈቃዳቸው ወዲያና ወዲህ አይዞሩም፤አይሄዱም።
  የወደቁት መላእክት ግን የሚከሱትንና የሚወነጅሉትን ሲፈልጉ፣ ሲያሳስቱ በገዛ ፈቃዳቸው ሲዞሩ ይኖራሉ። ሲዞሩ ነበር፣ ማሸነፍ ያልቻሉትን የእግዚአብሔር ሰው ኢዮብን መልካም ስራ አይተው የቀኑበትና ለክስ ያቀረቡበት።«እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ከወዴት መጣህ? አለው። ሰይጣንም። ምድርን ሁሉ ዞርሁአት፥ በእርስዋም ተመላለስሁ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ»ኢዮብ 1፣7 እንግዲህ ራሱ ሰይጣን እንደተናገረው ዟሪና ምድርን ለክፋት ስራው የሚያስሳት፣ በራሱ ፈቃድ የሚመላለስ ሲሆን ቅዱሳኑ መላእክት ግን ስራቸው ፈጣሪያቸውን ማመስገን«...ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም» ራእይ4፣8 እንዳለው ምስጋና መስጠት ነው። መልእክት ሲደርሳቸው ደግሞ በመላእክት አለቃ ሚካኤል በኩል (1ኛ ተሰ4፣16 እና በይሁዳ መልእክት 1፣9) እንደተመለከተው ትእዛዙ ተፈጻሚ ይሆናል።
  እንግዲህ ይህ ያለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታ ይህ ነው። ቅዱሳኑ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ትእዛዝ ሲኖር ሰዎችን ያድናሉ፤ይረዳሉ፤ይታደጋሉ፤ይነግራሉ፤ ያስተምራሉ፣ በቅዱሳንና ንስሃ በሚገቡ ሰዎችም ይደሰታሉ። ያለእግዚአብሔር ትእዛዝ ግን የትም አይሄዱም፤ አይዞሩም። ይህንን የሚያደርግ ሰይጣን ብቻ ነው። ራሱ ምድርን አሰስኳት፣ዞርኩባት እንዳለው በኢዮብ 1፣7 ላይ። ምክንያቱም ከአገዛዙ ውጭ ለመሆን ባይችልም ከአገልግሎቱ ቁጥጥር ውጭ ያለው እሱ ስለሆነ ነው። በዚህ ዓለም እንኳን ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ በመጥፎ ስነምግባሩ የተባረረ ልጅ ውሎና አደሩ እንደልቡ ሲሆን በስርዓት ያደገው ግን ቤተሰቡ ከሚያሰማራውና ከፈቀደለት ወይም ከሚገባው ቦታ ውጭ አይዞርም።
  በመጨረሻም ሊሰመርበት የሚገባው ነገር እኛ የሰው ልጆች የትኛውንም መልዓክ ስለጠራነው ወይም ስለጨቀጨቅነው በምንፈልግበት ቦታ ሁሉ ስሙ ስለተጠራ አይመጣም። ምናልባት ዟሪውና ምድርን የሚያስሰው የክፉ መልአክ
  ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ «የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና»2ኛ ቆሮ 11፣14 እንዳለው እኔ ሚካኤል ነኝ፤ እኔ ገብርኤል ነኝ ብሎ ሊመጣ ይችላል። ቅዱሳኑ መላእክት ግን ለሰዎች የሚደርሱት ጸሎታችን ወይም ጥያቄያችን ወይም ለቅሶአችንና ሀዘናችን በእግዚአብሔር ዘንድ ሲሰማና ምላሽ የሚሰጠን ሲሆን መላእክቱ ይመጣሉ። ጸሎታችንና መልካም ስራችን በእግዚአብሔር ዘንድ ሲወደድ እንኳን ቅዱሳን መላእክት ቅዱሳን ሰዎችም ሊላኩልን ይችላሉ። ልክ ለቆርኔሌዎስ ጴጥሮስ እንደተላከለት ማለት ነው። «ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ»የሐዋ10፣31
  ከዚህ ውጭ ቅዱሳን መልእክትን ስንጠራ ከተፍ ይላሉ ማለት ስለቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮና ተግባር ያለማወቅ ብቻ ሳይሆን ከተፍ የሚለው ብርሃንን የሚመስለውን ከተፎ ዟሪ ማንነት ያለመረዳትም ጭምር መሆኑ ያሳዝናል። ቅዱሳን መላእክት እኛ ለእግዚአብሔር በምናቀርበው ጸሎትና ልመና ከእግዚአብሔር ቃል በሚወጣ ትእዛዝ ብቻ ለዚያውም እኛ ይህኛው ጠንካራ ነው፤ ያኛው ሰይፍ አለው፤ያኛው ደግሞ ቁጡ ነው፣ይህኛው ርኅሩኅ ነው ብለን ስለመረጥን ሳይሆን እኛ የማናውቃቸው ከእልፍ አእላፍ መላእክቱ መካከል እሱ የፈቀደውን ይልካል። ያኔም ይራዱናል፤ያግዙናል፤ የታዘዙትን ሁሉ ለእኛ በደስታ ይፈጽሙልናል። ከዚህ ውጭ ግን ቁጡ ወይም ርኅሩኅ ወይም ዓለምን በእጁ ሊገለብጣት ነበር፤ የወረወረው ጦር እስከምጽዓት ይወርዳል ወዘተ የሚሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ ድምጾች ከዚያ ከተፍ ከሚልና የብርሃንን መልአክ ከሚመስለው የሚወጣ መሆን አለበት። ቅዱሳንን መላእክት ተልእኰና ተግባር የሚያውቅ ልቡናን ከላይ ይስጠን።አሜን።

  ReplyDelete
 10. Now this is the best biblical explanation given above by "Birhan". Angels are not omnipresent like GOD. You can not pray to them and ask them to intercede b/n God and You. Jesus did that on Calvary. Please guys read the BIBLE instead of "Ye Debterawoch Dirset".
  God Bless You Birhan

  ReplyDelete
 11. thank you Abaselama and Birhan. I have been wishing to read an article supported by evidences from Bible, here I got it , please keep posting articles like this.

  ReplyDelete
 12. belibachew hasab yemikoru tibitenyochin betatenachew(luk.1:51) yezih tsihuf drasi mtshafin inde libu minyot tenetene liki inde ariyos lijuu newuna.lemehonu yihin hulu sitimar igziabiher bemiserabet bota hulu melaikt indemiseru indet zelelkew ajire indatsema azim adirgobih inji.misale litikesilih;lemin Daniel kemikael beker yemiredany yelem ale tesasto new?irsu igziabiher begilts yawekew ante indet litawuk chalk;yohanis lemin lemelaku segede?menfes kidus werdolet bale wengel,meliktna raiyi balebet yalawekewun ante yegiraw wenbede indet awek;silase Abrahamin anagirew siwetu wede sedom hidew inde hulet melaikt kerbew lotin anagerut;igziabiher sewun indemelkachina misaleyachin inifter lemin ale?Kidus gebriel ineho bewktu yemihonewun KALEN silalamenh dida tihonaleh lemin ale?inenyih hulu yeigziabiher mengist and mehonwan yasayal.Iyesus Kirstosim lemiyamin hulu yichalewal ine kadereghut teamirat belay tadergalachihu bilual.Inante gin belibachihu hasab iyehedachihu beyadarashuu tebetatnachihu tikeralachihu inji Tewahido 2000 zemen yekoyechibetin tiketilalech.tesfa kuretu.betenesachihubat kutir yemitsefa natina

  ReplyDelete
 13. I agree with all your writings and your principle to stand by the truth even though the church is soaked with so much false teachings and ADDIS WONGEL. However, i did not like this particular sentence "በተለየ ግብሩ ልጅ ነውና ልጅነቱን ለአባቱ የሚታዘዝ፥ የሚላክ፥ ጻድቅ ባሪያ፥ ቅን አገልጋይ፥ ፈቃድ ፈጻሚ በመሆን አስመስክሯል". As an EOTC member i do not believe the above assertion. I don't think it is true before 'TEWAHDO'. I agree if it was meant to say after TEWAHDO, "የሚታዘዝ፥ የሚላክ፥ ጻድቅ ባሪያ፥ ቅን አገልጋይ፥ ፈቃድ ፈጻሚ" is said for the human person (LESGA YETENEGERE) of our Lord Jesus christ. AlL those terms are not appropriate 'LEMELKOT". How can we say that before TEWAHDO the, son of God was የሚታዘዝ፥ የሚላክ፥ ጻድቅ ባሪያ፥ ቅን አገልጋይ፥ ፈቃድ ፈጻሚ, it will destroy our belief in TRINITY, ONE GOD,THREE PERSON, BEMELEKOT, BEAGEZAZ, BESILTAN ONE,

  ReplyDelete
 14. እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ:ባትለጥፈዉም ላንተ ትምህርት ይሆንህ ዘንድ እጽፋለሁ።እንደት ያለ ዉሸት ነው የምትጽፈው ተስፋ!በመጀመሪያ ዕዝራ ካልዕ 15 ምእራፍ የለዉም እስከ 9 ምዕራፍ ነው ያለው የሌለ ምዕራፍ ቀጠልክ::ዕዝራ ሱትኤልም ሆነ ዕዝራ ካልዕ ታቦተ ጽዮን የሚል አልጻፉም።አንዳንዶች እየቀጣጠሉ እንደሚዋሹት የለለ ነገር እየጨማመርክ ዋሸህ።ጽዮን ጠፋች ነው የሚለው እዚህ ጽዮን ጠፋች ሲል ሀገሪቱን ጽዮንን እንጂ የለለ ነገር ጨምረህ ነገር ለማጣፈጥ ታቦት የሚል ጨምረህ ለምን ታምታታዋለህ።ጻድቁ ተክለ ሀይማኖት ጵጵስና እና ክህነት ከእነ ወገን እንዳይወጣ ብለዋል አልክ፤እኒያ የመረጧቸው 12 ተማሪዎቻቸው ዘራቸው ዉስጥ ነው ያሉት?ታሪክ የሚነግረን የግብጽ ጳጳስ ሲመጡ አስረክበው ወደ አገልግሎታቸው ሂዱ ነው የሚለው።አንተ ባታከብራቸውም የግብጽ ክርስቲያኖች በተ ክርስቲያን ሰረተዉላቸው የልደት መታሰቢአቸው በደንብ ያከብሩላቸዋል።በተጨማሪ ሥልጣንን ከአንዱ ወደ እግዚአብሐር ወደ ፈቀደው ማሸጋገር እኮ የነብዩ ሳሙእልም ሥራ ነበር።ከሳኦል ወደ ዳዊት ሥልጣን ሲተላለፍ እግዚአብሐር ለነብዩ ያለው ሳኦል ከሰማ እንዳይተናኮልህ በምሥጢር በጥበብ ሂደህ የእሲይን ልጅ ዳዊትን ቅባልኝ ነው ያለው።ተስፋ በአንተ አተረጓጎም ነብዩ ሳሙእልም ፖለቲከኛ ፖለቲካ ዉስጥ የገባ ሳኦልን አዉርዶ ዳዊትን የሾመ የመጀመሪያው ተክለ ሃይማኖት እሱ ነው በለዋ በነካ አፍህ።ሳሙእል የሰራዉን ሳኦል ቢያውቅ ኖሮ ምን እንደሚያደርገው ገምት።ይገለው ነበር፡ስለዚህ እግዚአብሐር በዘደ እንዲሀድ ነገረው።እንዳልከው አቡነ ተክለ ሃይማኖትን የይትባረክ ጦር ወይም ዘመድ ቢያገኛቸው ኖሮ፤እግራቸዉን ብቻ ቆርጦ እንደማይተዋቸው አንተም አይጠፋህም!ምክንያቱም አንተ እንዳልከው ለመንግሥቱ መወሰድ ዋነኛ ሰው ናቸውና።አየህ እንደት ያለ ትልቅ ዉሸትና ክህደት ዉስጥ እንዳለህ?ለላው ታቦተ ጽዮን ጋር ታቦተ ሚካእል አለመኖሩን በምን አረጋገጥክ?ታቦተ ጽዮንን የቀረጸ እኮ ሙሰ ነው፤ለላ ጽላት በተጨማሪ ቀርጾ እንደሆነስ ማን ያዉቃል?በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፈ ነገር ግን እነ ሙሰ ለሎች ነብያት የተናገሩት የሠሩት ስንት ነገር አለ መሰለህ?መጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ ስላልተጻፈ ብለህ አፍህን ሞልተህ የለም ማለት አትችልም።ላለመኖሩ መረጃ የለህም።ንጉሱ ኢዮስያስ አባቱ ምናሰ በእግዚአብሐር በተ መቅደስ ጣኦት ሲያቆም ታቦት አለመኖሩን ግልጽ ነው።አንተ እንደፈጠርከው ተረት ካህናቱ ታቦቱን በበታቸው አስቀመጡት የሚል የትም ቦታ አልተጻፈም።ኢዮስያስ በተ መቅድሱን ካጸዳ በኋላ ታቦቱን አስቀምጡት አለ።እሱ ያልገባው ነገር ታቦቱ ያለ መስሎት ነው።ከሰሎሞን ዘመን በኋላ ሰለ ታቦተ ጽዮን መኖርና ሰለተደረገ በዓል የትም ቦታ አልተጻፈም፡ አሁን አንተ አምታተህ ከተረጎምካቸው ጥቅሶች ውጭ።እነዚም መልሰው የአንተን መሳሳት ነው የሚናገሩት፡እንጂ በንጉሡ ትዕዛዝ ታቦቱ በበተ መቅደስ ተቀመጠ የሚል መረጃ እስቲ አምጣ ከቻልክ?የለህም እንጂ፤ነብዩ ኢርምያስም እስራእል ልብ ስለለላቸው ታቦቱን ረስተዉት እንደሚቀሩ፤እንደማያሳታዉሱት ተናገረ እንጂ።ታቦቱ ወደ ባቢሎን ተወሰደ አላለም።ይገርማል ለ10 ዓመት የተመራመረው እዉቁ ተመራማሪና ጋዘጠኛ ታቦቱ ያለው ኢትዮጵያ ዉስጥ ነው ብሎ ሲደመድም(ምንም እንኳ የዓመት አቆጣተር ከእኛ ጋር አንድ ባይሆንም) አንት ግን ፈጽሞ የለም አልክ።እጅግ ገረመኝ።ይህ ተልኮ የኢትዮጵያን በተክርስቲያን ማጥፋት ብቻ ሳይሆን አገሪቱንም ለማዉደም ነው የተነሳችሁ ማለት ነው።ስለዚህ የጠቀስካቸው ጥቅሶች አራቦና ቆቦ ናቸው።አሁን አለተሳካልህም፤የማያነቡ መስሎህ ነው እንዲህ የዋሸህው አይደል።

  ReplyDelete
 15. Beewunet egiziabiher abizito yibarikachihu. kale hiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 16. yehalik ekeyomu lehate'an! abune selamawoch christianun endezih kemitawozagbutina behaset timirt kemitasitut lemin begilits wotitachihu teketay atifeligum, hiyen gin madreg atichilum mikniatum yekihidet timihirtachihun manim selemayikebel betekristian wust honachihu kihidetachihun tizeralachihu. Egziabher gin sayizegey firdun yisetal.

  ReplyDelete