Saturday, November 19, 2011

የመጽሐፍ ቅዱስና የመልክአ ሚካኤል አለመግባባት - - - Read PDF

መጻሕፍት በመንፈስ ቅዱስ አሳሳቢነት በቅዱሳን አባቶች የተጻፉ የእግዚአብሔር መልእክት ናቸው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የታቀፉ እና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የሃይማኖት ማስተማሪያ ሆነው የኖሩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስድሳ ስድስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተወስነው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት መመሪያዎች ግን ሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ናቸው።አንድ ሰው ሃይማኖቱ ትክክለኛነት ተመዝኖ ሊወገዝም ሆነ ሊመሰገን የሚችለው በነዚህ መጻሕፍት መሠረት ነው። ነገር ግን በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያናችን በቀኖና የማይታወቁና  ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና ውጭ የሆኑ መጻሕፍት በቤተ ክርስቲያናችን ስም ወደ ሕዝብና አገልጋዮች ሾልከው ገብተው ቦታውን በመቆጣጠር፣ በአገሪቱ መጽሐፍ ቅዱስ የሌለ እስኪመስል ድረስ ውሸታቸውን አጋነው በማቅረብ አገሪቱን በክለዋል።

መልክዐ ሚካኤል የሚባለው ድርሰት በአጼ ዘራአ ያዕቆብ ዘመን እንደተደርሰ ይገመታል፣ መጽሐፉ በየወሩ የሚካኤል ማህሌት በሚቆሙ የቤተ ክርስቲያችን ተቀጣሪዎች በየተራ በቅብብሎሽ እየተዜመ ሚካኤል የሚመለክበት፣ የሚመሰገንበት ድርሰት ነው። ይህን መጽሐፍ ሁልጊዜ በመድገም ወደ ሚካኤል የሚጸልዩ ምእመናንና ደብተራዎች በርካታ ናቸው። የሚካኤል በአል ሲሆን ካህናቱ ሌሊቱን ሙሉ ሲዘምሩና ሲያሸበሽቡ ዚቅ የሚባለውን ሌላ ድርሰት ጨምረውበት ሲዘሉበት የሚያድሩት ይህን ድርሰት ነው። ምእመናን ግን ይህን በቤተ ክርስቲያን እና በእግዚብሔር ላይ ሲካሔድ የሚያድረውን አመጽ ስለማያውቁ ካህናቱ ረጅም ሌሊት ሲጸልዩ በማደራቸው ይደክማቸዋልና ምርጥ ምርጡን፥ ቁርጥ ቁርጡን እንጋብዛቸው በረከታቸውን እንካፈል እያሉ ይሽቀዳደማሉ። በነገው ዕለት በሚከበረው የህዳር ሚካኤል ወደ አንዱ ቤተ ክርስቲያን ጎራ በማለት ይህን ድርሰት ማዳመጥ የሚቻል መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም። ነገር ግን በግዕዝ ብቻ ስለሚባል እግዚብሔር እና እነሱ ብቻ ናቸው የሚሰሙትና ላይገባችሁ ይችላል። ለሁሉም በመልክአ ሚካኤል እና በመጽሐፍ ቅዱስ መካከል ያለውን አለመግባባት እንዲህ አቅርበነዋል።

ከመልካ ሚካኤል፦


ሰላም ላአእዛኒከ እለ ያጸምአ ንባበ፣
ወጸሎተ ኩሉ ዘተመንደበ፣
ሚካኤል አቅልል እምላእሌየ እጸበ፣
ከመ ትመአድኒ ውትምህረኒ ጥበበ፣
ረስየኒ ወልደ ርሰይኩከ አበ፤

ትርጉሙ፦

ለጆሮዎችህ ሰላምታ አቀርቫለሁ፤
የተቸገረን ሁሉ ጸሎትና ልመናን ያዳምጣሉ፣
ሚካኤል ሆይ ችግሬን አቅልልኝ፣
ምከረኝ እውቀትንም አስተምረኝ፤
አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ፤

ይህ ለሚካኤል የቀረበ ጸሎት እና ምልጃ ቤተ ክርስቲያናችን በተቀበልችው ሰማኒያ አንድ መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም ወይንም ይህን ሐሳብ የሚደግፍ ንባብ የለም። ቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎታቸውን ያቀረቡት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላእክት አልነበረም። ወደ መላእክት ጸሎት ያቀረበ የእግዚአብሔር ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም። የኛ ደብተራዎች ግን ሚካኤልን እናነግሳለን በሚል ፈሊጥ እግዚአብሔርን ሲያስቀኑ እያደሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊመስሉ ይሞክራሉ። ሚካኤል የእግዚአብሔር ክቡር መልአክ አገልጋይና ተላላኪ የመላእክት አለቃ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚናገር ይህን ማንም አይክድም። ነገር ግን ጸሎትን የሚሰማና ጸሎትም ወደ እርሱ መቅረብ እንዳለበት የሚናገር ክፍል ፈጽሞ የለም። ደብተራዎች ለሚካኤል የሰጡትን ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማን እንደተሰጠ እንመልከት፤

መጽሐፍ ቅዱስ፦

«ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» መዝ 652 እግዚብሔር በዓለም ምሉዕ በመሆኑ የሥጋን ሁሉ ጸሎት መስማት ይችላል። ቁራዎች እንኳ ወደ እግዚአብሔር ከጮኹ ያገሬ ሰዎች ምን ነካቸውና ነው ወደ ሌላ የሚጮኹት? ወይስ ያክብሮት ጩኸት ነው?

ታዲያ መነፍቃን ደብተራዎች «የተቸገረን ሁሉ ጸሎት የምትሰማ» በማለት ለሚካኤል የሰጡት ከምን አምጥተውት ነው? ዛሬ የቤተ ክርስቲያናችን ሕዝብ በዚህ ክህደት እንዲተባበር የሚደረገውስ ለምንድን ነው? «ሥጋ ሁሉ ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ይመጣል» ሲል የኢትዮጵያን ሕዝብ አይጨምርምን? ሥጋ ሁሉ ካለ ኃጥአንም ሆኑ ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ እንዳለባቸው የሚናገር አይደለምን? እንስሳት እንኳ ወደ ማን ማንጋጠጥ እንዳለባቸው የሚያውቁ መሆኑን እንዲህ ተብሎ ተጽፏል።

«እጓለ አንብስት ይጥህሩ ወይመስጡ ወይስእሉ ኀበ እግዚአብሔር ሲሳዮሙ»

«የአንበሳ ግልገሎች ለመንጠቅ ይጮሃሉ፣ ምግባቸውንም ከእግዚአብሔር ይለምናሉ» መዝ 10321

«ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጭቶች ለእንስሳትም ምግባቸውን ይሰጣል» መዝ 1479

በጣም ትናንሽ የሆኑ የቁራ ጫጭቶች እግዚአብሔርን እንደሚጠሩ በዚህ ቃል ይታወቃል። በእግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረው ያገሬ ደብተራ ግን ወደ ሚካኤል በመጸለይ የአምልኮ ዝሙት ይፈጽማል። ይህ እጅግ ያሳዝናል። ችግሬን አቅልልኝ መባል ያለበት እግዚአብሔር ነው። ዳዊት «ሕግህን አልረሳሁምና ችግሬን ተመልከት አድነኝም» ብሏል። ችግርን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ መፍትሔን ያስገኛል። ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ሲላክ ብቻ ተልኮውን ይፈጽማል እንጂ እኛ ወደ እርሱ ስለጸለይን ደስተኛ አይሆንም ያለ እግዚአብሔርም ፈቃድ አንዳች ነገር ሊያደርግ ይችልም።

«በትእዛዛትህ ታምኛለሁና መልካም ምክርና እውቀትን አስተምረኝ» መዝ 11966

ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ምክርንና እውቀትን ይሰጣል፤ እርሱ ልብና ኩላሊትን ይመረምራል፣ ለሁሉም የሚያስፈልገውን ያውቃል፣ ሶሎሞን «ማስተዋልን ስጠኝ» በማለት የለመነው እግዚአብሔርን ነው። የኢትዮጵያ ደብተራዎች ግን የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ሥራ ለፍጡር በመስጠት «ሚካኤል ሆይ ምከረኝ እውቀትን አስተምረኝ» እያሉ ወደ ሚካኤል ሲጮሁ ያድራሉ። ሚካኤል ግን ከእግዚአብሔር ሲላክ የእግዚአብሔርን ምክር ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሊያስተምርና ሊናገር ይችላል። በዳንኤል እንደተጻፈው የእግዚአብሔርን ምሥጢር መላእክት ይናገራሉ። ሆኖም ግን ዳንኤል የጸለየው ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መላኩ አልነበረም፤ ይህን እራሱ መላኩ እንዲህ ሲል ያረጋጣል፦

«እነሆም አንዲት እጅ ዳሰሰችኝ፥ በጉልበቴና በእጄም አቆመችኝ። እርሱም እጅግ የተወደድህ ሰው ዳንኤል ሆይ እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁና የምነግርህን ቃል አስተውል ቀጥ ብለህም ቁም አለኝ። ይህንም ቃል ባለኝ ጊዜ እየተንቀጠቀጥሁ ቆምሁ። እርሱም እንዲህ አለኝ፣ ዳንኤል ሆይ አትፍራ፣ ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቷል እኔም ስለቃልህ መጥቻለሁ» ዳን 1010-12

«እኔ ዛሬ ወደ አንተ ተልኬያለሁ»  የሚለው ቃል የመላኩን ዋና ሥራ ያመለክታል፣ «ልብህ ያስተውል ዘንድ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደርግህበት ቀን ጀምሮ» የሚለው ዳንኤል በአምላኩ ፊት እንጂ በመላኩ ፊት አለመውደቁን ያመለክታል። «ቃልህ ተሰምቷል ስለቃልህ መጥቻለሁ» የሚለው ደግሞ የዳንኤል ጽሎት በጌታ ዘንድ መሰማቱን እና መልሱ በመላኩ እጅ መምጣቱን ይናገራል። እናም ሰው መጸለይ ያለበት ወደ እግዚአብሔር እንጂ ወደ መልክተኛው መሆን የለበትም። ዛሬ ደብተራዎች በቤተ ክርስቲያችን ገብተው በጉልበት የሚያደርጉት ባዕድ አምልኮ ከሰማኒያ አንድ መጻሕፍት ውጭ ነው።

«አባት አድርጌሃለሁና ልጅ አድርገኝ»

በዚህ የደብተራዎች አባባል አባታቸው ሚካኤል እንጂ እግዚብሔር አይደለም። እንዲህ ባለ እምነት ግን ክርስቲያን ሊሆን አይሞከርም። ክርስቲያኖች በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚብሔር ልጆች ናቸው።

«ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከወንድ ወይም ከሥጋ ፈቃድ አልተወለዱም» ዮሐ 112-13

«አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና» ማቴ 239

አንድ ሰው ከሁለት አባት ሊወለድ እንደማይችል ሁሉ ክርስቲኖችም አባታቸው አንዱ እርሱም የሰማዩ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት አብ ነው። ከመንፈስና ከውሃ ዳግም የተወለድን ሁሉ አባታችን አንድ ነው፤ እርሱም መንፈስ ስለሆነ በመንፈስ ወልዶናል። ታዲያ መናፍቃን ደብተራዎች ሁለተኛውን አባት ከየት አመጡት? እንዴትስ ወለዳቸው?  መጽሐፍ ቅዱስ ሚካኤል አገልጋይና ከኛ ጋር አብሮ የእግዚአብሔር ባሪያ መሆኑን ይናገራል እንጂ የክርስቲያኖች አባት መሆኑን አይናገርም።

«ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምሥክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ.. አለኝ»  ራእይ 1910

በምድር ላይ በመንፈሳዊ ምክር ያሳደጉንን የምናውቃቸውን ቀሳውስትን አባቶች እንላቸዋለን። ይህ ከነርሱ ጋር ስለምንተዋወቅ  ምንም ነውር አይኖረውም ምክንያቱም እነሩሱን[ቀሳውስትን] ስለመንፈሳዊ ሕይወታችን እናማክራቸዋለን እንጂ ወደ እነርሱ እየጸለይን አንሰግድላቸውም።

በሰማይ የሚኖሩ መናፍስትን አባት እያሉ መጥራት መጸለይና መስገድ ግን ባዕድ አምልኮ ስለሆነ ቅዱሳን የሆኑ መላእክትም አይቀበሉትም። ትሑቱ ሚካኤል «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ» ይላል እንጂ፤ አይቀበለውም።

አንዳድ ደብተራዎች በተለኮሰው የወንጌል እሳት ምክንያት ማስተዋል ጀምረዋል። አሁን የሚካኤልን ታቦት እናነግሣለን እያሉ ሕዝብ እንዲሰበሰብ የሚያደርጉት ያመት ቀለባቸውን ለመሰብሰብ የሚሠሩት ድራማ እንጂ እውነት እንደዚህ ከሐዋርያት እምነትና ሥርዓት ውጭ በሆነ ልምምድ ሚካኤልን ለማንገሥ እየሞከሩ አለመሆኑን አውቀውታል። ይህን ምሥጢረ ገንዘብ የማያውቁ ምእመናን ግን እጅግ ያሳዝናሉ፤ የሚያደርጉትን አያስተውሉምና አምላካችን ይግለጥላቸው።

ማንገሥ ምንድር ነው?

ማንገሥ መሾም! ይሁን! ይሁን! ይገባዋል ማለት ነው፤ ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ከተሾመ እጅግ ብዙ ዘመን አለፈ፤ እርሱ የመላእክት አለቃ እንጂ የሰው ዘር አለቃ አይደለም። በሰውና በመላእክት በፍጥረት ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው በተዋሕዶ የከበረው የድንግል ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው። አምልኮ ክብር ምስጋና ለርሱ ይገባዋል። ሚካኤልን «ማንገሥ» ማለት ምንድር ነው? « ማምለክ» የምተለዋን ቃል ዘወር አርገው «ማንገሥ» ይላሉ መናፍቃኑ እንዳይንቃባቸው የፈጠሩት ይመስላል። ማንገሥ ማምለክ ነው፤ ሌላ ምንትርጉም ሊኖረው አይችልም። እልል እየተባለ የሚሰገደው ለሚካኤል ታቦት አይደለምን? ሚካኤልን በአካል እንደ ዮሐንስ ቢገለጥልን በእውነቱ ዝቅ ብለን ተንበርክከን ልንቀበለው እንችላለን፣ ነገር ግን ታቦቱ የሚካኤል ነውና እንስገድለት የሚለው አስተሳሰብ ፍጹም ከሰማኒያ አንዱ መጻሕፍት ውጭ ነው።

ሌላ መልክአ ሚካኤል፦

ሰላም ለእመትከ ዘይሜጥን ተራድኦ፣
አኮ ሰንዱነ ወአልባሰ ረፍኦ፣
ሚካኤል ኀቤከ አወዩ በአስተቍዖ፣
ከመ ታድኅነኒ ሥመር እግዚኦ፣
እስመ ኩሉ ይትግህ ከመ ያድኅን ሰብኦ፤

ትርጉም፦

እርዳታን ለሚሰጥ ለክንድህ ሰላምታ አቀርባለሁ፣
የበፍታ ልብስም ሆነ የልብስ እራፊ አለምንህም፤
ሚካኤል ሆይ በምልጃ ወደ አንተ እጮሃለሁ፤
አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
ሰው ሁሉ ዘመዱን ለማዳን ይተጋልና፤

በቅዳሴያችን ሰዓት "ሥመር እግዚኦ ከመ ታድኅነነ ሥመር እግዚኦ ከመታድኅነነአቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ አቤቱ ታድነን ዘንድ ውደድ እንላለን መባል የሚገባውም እንዲህ ነው። ደብተራዎች ግን ሚካኤልን «እግዚኦ አቤቱ» ታድነን ዘንድ ውደድ ብለውታል። ደብተራዎች የጌታን ለሚካኤል ይሰጣሉ። ይህ ባዕድ አምልኮ አይደለምን? ይህ ባዕድ አምልኮ ያለፈ እና የተተወ ነገር ቢሆን ኖሮ ዝም ባልን ነበር፤ ነገር ግን ዛሬም የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ባለበት እና በበአሉ ቀን የሚባለው እና የሚጸለየው ይህ ስለሆነ ምእመናንን ማንቃት ማስጠንቀቅ ግዴታ ሆኖብናል።

ለቤተ ክህነቱና ለጳጳሳቱ ስናቀርብ እባካችሁ ዝም በሉ ይህን ሕዝብ ታስገድሉናላችሁ ጊዜ ይፈታዋል ይሉናል። ማህበረ ቅዱሳንን ይህ መታረም አለበት ስንለው መናፍቅ ናችሁ እያለ ስማችንን ያጠፋል ከዚያም አልፎ በማጅራት መች ያስደበድበናል። በዚህ ምክንያት ስንት የቤተ ክርስቲያን ልጆች መከራና ችግር ደርሶባቸዋል! ይህ እልከኝነት ግን ችግር አይፈታምስሕተታችንን ብናርም ይሻላል እንጂ ስም ማጥፋቱና ማባረሩ አይበጅም።
ሰላም እብል ለመልክአቲከ ኩሎን፣
በበአስማቲሆን፣
ሚካኤል ሥርግው በልብሰ ብርሃን፣
ሠናይ ተአርኮትከ በኩሉ አዝማን፣
ሠራየ ኃጢአት አንተ አርከ ነፍስ መመን፤

ትርጉም፦

ለመልኮችህ በሙሉ በየስማቸው ሰላም እላለሁ፣
ሚካኤል ሆይ አንተ በብርሃን ልብስ የተሸለምክ ነህ፣
በዘመናት ሁሉ ያንተ ወዳጅንት መልካም ነው፣
የአማኝ ወዳጅህን ነፍስ ኃጢአት የምታስተሠርይ አንተ ነህና፤

ኃጢአትን የሚያስተሥርይ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ኃጢአታችንን ያስተሠርይልናል። ደሙ ለዘላለም ሕያው ነው መለኮት ብቻውን የሚሠራውን የኃጢአት ሥርዬት ሥራ ከሚካኤል መለመን ምን የሚሉት ነው? ይህ ክህደት ከቤተ ክርስቲያናችን መነቀል አለበት። ሚካኤልን እያመለኩ ሲያስመልኩ የኖሩ ሰዎች ፍርዳቸውን እንደሚያገኙ ባንጠራጠርም ዛሬ ግን በቃችሁ ሊባሉ ይገባል።

ሰላም እብል ለአክናፊከ ስፉሐት፤
ምስካቤ ኩሉ ፍጥረት፣ ሚካኤል ክቡር ሊቀ ካህናት፣
አድህነነ እምዕለት እኪት፣
ወባልሃነ እምኩሉ መንሱት፤

ትርጉም፦

ሰፋፊ ለሆኑ ክንፎችህ ሰላም እላለሁ፣
የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ናቸው፣
ሚካኤል ሆይ አንተ የከበርህ ሊቀ ካህናት ነህ፣
ክፉ ከሆነች ቀን አድነን፣
ከጥፋትም ሁሉ ታደገን፤

የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ እግዚብሔር ነው ወይስ የሚካኤል ክንፍ? ሚካኤል የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ ከሆነ አምላክ ሆኖአል ማለት ነው። ሁለት አምላክ የለም፤ የፍጥረት ሁሉ መጠጊያ እግዚአብሔር ብቻ ነው "ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውናመዝ 3320 ተብሎ ተጽፏልና የእግዚአብሔርን ለሚካኤል አንሰጥም።

ሊቀ ካህናትስ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? "በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናልየተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ የት ሄዶ ነው ሚካኤል ሊቀ ካህናት የሆነው? ወይስ የትኛውን መስዋእት አቅርቦ ይሆን? እራሱን ነውን? ወይስ እንስሳትን? መስዋእት ማቅረብ የሊቀ ካህናት ሥራ እንጂ የመላእክት አይደለም። መላእክት ኃጢአት የለባቸውምና መስዋእት ማቅረብ አይጠበቅባቸውም ስለዚህ "ሊቀ ካህናት ካህነ ምስዋዑየሚለው ጌታን ብቻ ይመለከታል።

ከክፉ አድነን ብለን መጸለይም ወደ እግዚአብሔር ነው፣ ጌታ "ከክፉ ሁሉ አድነንብላችሁ ጸልዩ ብሎ ሲያስተምረን ወደ ሚካኤል ነውን? ወይስ በሰማይ ወደሚኖረው አባታችን? ይህን ጥያቄ አንባቢ ይመልሰው።

ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ሃያ አራት ሰዓት የሚጸልዩ አባቶች አሉን እያለ የሚመካባቸው ደብተራዎች የሚጸልዩት ጸሎት ይህን ይመስላል።

ይህን አባባል አሜን ብለን ብንቀበል እንኳ የሚጸለየው ጸሎት ግን ከላይ ያየነውን ስለሚመስል ዋጋ የለውም።  የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚጋብዝ እንጂ ኢትዮጵያን ከድህነት፣ ከጦርነት፣ ከእርስ በእርስ ንትርክ፣ አውጥቶ ትውልዱን ከስደት የሚያሳርፍ ጸሎት አይደለም።

እንግዲህ በየወሩና በየአመቱ ሚካኤል ሲነግሥ ደብተራዎች ሲዘሉበት የሚያድሩት ማህሌት ከዚህ በላይ በጥቂቱ ያየነውን የሚመስል ነው።

ውድ አንባብያን፥ ከዚህ በፊት እንደጠቆምኩት ከላይ ያየናቸው ሰይጣን በየጊዜው ያስገባብን የስህተት ትምህርትች የጥንታዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ አይደለም። ክቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን አካባቢ ጀምሮ በነገስታቱ ጣልቃ ግብነትና ባልተማሩ ደብተሮች አማካኝነት ሰይጣን ቤተ ክርስቲያናችንን በክሎብናል። እነ አባሰላማ እና ሌሎች ጥንታውያን አባቶች የሰበኳት ክርስትና እንዲህ አይነት መላ ቅጡ የጠፋ ባዕድ አምልኮን ያዘለ አልነበረም።


በዲያቆን ሉሌ50 comments:

 1. ሊላ yelattume enda stupid protasetant

  ReplyDelete
 2. የናንተ ብሎግና ከላይ የተቀመጠው የብፁአን ፎቶግራፍ አለመግባባት ሁሌ ይገርመኛል። ጭንብል መሆኑ ነው? ቅድስት አፎምያን ሊያሳስት የነበረውን በናንተ ውስጥ አያለሁ። ....አፎምያም እንተ ማነህ ስምህስ ማነው አለችው።....ዲያብሎስ ማሳሳት ልማዱ ነው። ወልደ አፎምያ ነኝ።

  ReplyDelete
 3. why are you tring to pretend orthodox. we all know you are protestant so leave orthodox alone cuz that is the only religion speak the truth. you are working for devil and worship devil but we worshiping our lord Jesus Christ so go to hell devil.

  ReplyDelete
 4. ke muluwongeloch sint tekefeleh? Ay tehadiso bekentu atdikemu.

  ReplyDelete
 5. Ay yenante neger... alemaferachihu!
  endezih endemitilu meche Tefanina qedmowunu. Metshaf qidusin aTamachihu yemititeregumu menafiqan. "YeEgziabher mel'akbemiferut sewoch zuria ysefral yadnachewumal" Mez 33:7. Yihenin amlak yeseTewun tsega enante silalachihu atineTiqutim. Awon qidus Michael egna yemnferawun Orthodoxawyan yadnenal, enante yematferutin Protestants gin zor blom ayayachihu.

  Libuna yisTachihu!

  ZeTewahedo

  ReplyDelete
 6. ሉለ እስቲ መጻሕፍት ምን እንደሚሉ አንብ።ደስ ያለህን ብቻ ሳይሆን የሚቀጥሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብ ባትቀበላቸዉም።
  ነብዩ ኢልያስ እልሳን ወደ እነ ለምን ያለውና የሱን መንፈስ እጥፍ ለምኖ ማግኘቱን አላነበብክምን?2ነገ2:9-11 እኛም ቅዱሳንን ቀጥታ ወደ እነሱም እንለምናለን፤ከነብያቱ ተምረናልና።
  ዘፍ2:7፡እግዚአብሐር አዳምና ሚስቱን"...በምድር የሚንቀሳቀሰዉን ሁሉ ግዟቸው"አላቸው።ፍጥረት የተፈጠረ ለእኛ ነው።ድንግልማ፤ቅዱስ ሚካእልም ምን ይጠየቃል ገዥዎቻንን ናቸው
  ዘጸ7:1-እግዚአብሐርም ሙሰን "እይ እነ ለፈርኦን አምላክ አድርጊሀለ።እልቅስ ቅ/ሚካእል አምላክ ሆኖ ተሽሞብህ እንደሆነ በምን ታዉቃለህ?እንደ ፈርኦን ትቢተኛ በሆነ ሰው ላይ አሁንም እግዚአብሐር ወደጆቹን ከመሾም ማንም አይከለክለዉም።
  ኢያሱ5፡13-15፡ኢያሱ የሙሰ ምትክ ለእግዚአብሐር የሰራዊት አለቃ ሰገደ።መል አኩም ጫምህንም አዉልቅ መስገድህ ብቻ በቂ አይደለም ነው ያለው።
  ዮሐ14:12 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእነ ያመነ እነ የማደርገዉን ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ።
  ማተ10፡40"እናንተን የሚቀበል እነን ይቀበላል...
  ማተ16:19፤...የመግስተ ሰማያትን መክፈቻ እሰጣሃለሁ...
  ማተ17:20 የሰናፍጭ ያህል እምነት ቢኖራችሁ...የሚሳናችሁ ነገር የለም።
  ማተ19:28"...በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በመጣ ጊዘ እናንተም(12 ሐዋርያትን) 12 ዙፋን ተቀምጣችሁ...ትፈርዳላችሁ።

  ReplyDelete
 7. Enante ye aganent legoch weyewelachu!

  ReplyDelete
 8. for the above comment: do you think by insulting bad word, you feel like you serve God or Jesus? let me tell you Saint Micheal will mad on you.

  ReplyDelete
 9. hoo endet new negeruu ???

  ReplyDelete
  Replies
  1. mastewal saygeban aykerm.

   Delete
 10. No doubt you are stuppid for this reason stuppid does as a stuppid.

  ReplyDelete
 11. why don't put your reference from the bible for your argument instead of insulting. I have not seen any problem on the article. it is more informative, I do not understand "why some people do not like to know about the bible." we have to accept that our church is not orthodox, but there are some orthodox followers "true orthodox" who know bible and based their life on it.
  Any one who oppose this article is "a protestant."

  ReplyDelete
 12. በእናንተ እና በማቅ መካክል ያለው ልዩነት ለካ ስለ ቅ/ሚካኤል አማላጅነት ሁሉ ነዋ::ጃል ይህ ነገር ማወቄ በጣም ይጠቅማል::

  ReplyDelete
 13. የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ አሉ እንደዚህ ነው የሆናችሁት ትንሽ የተሻለ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም ሃሳብ ታመጣላችሁ የሚል ተስፋ ነበረኝ ስትታዩ ግን ለማፍረስ የተነሳችሁ የጥጃት ልጆች ሆናችሁ አገኘዋችሁ። ከፍሬያችሁ እፍሬሆሙ ተአዕምሩ እንዲል ጌታ

  ReplyDelete
 14. ጨዋ/ጥራዝ ነጠቅ....is a word for you how can protestant understand such a great mystery?! kentu...

  ReplyDelete
 15. yemiadergutin ayawukumna yikir belachew

  ReplyDelete
 16. «ንዑ ንስግድ ወንግነይ ላቲ፤ ለመድኃኒትነ ማርያም ድንግል ለዘገብረት ብርሃናተ ዐበይተ ለባሕቲታ» ትርጉም- መድኃኒታችን ለሆነችና ታላላቅ ብርሃናትን ብቻዋን ለፈጠረች ለድንግል ማርያም ኑ እስገድ፣ እናመስግናት» ማለት ነው።(የየካቲት ኪዳነምሕረት ዚቅ)
  እንግዲህ ይታያችሁ! ማርያም ቅድስት፣ንጽሕትና ብጽእት ናት ቢባል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃን መሠረት አድርጎ ነው። ይህ አንድ ነገር ነው። ማርያም መድኃኒታችን ናት፣ የሰማይ ታላላቅ ብርሃናትን ለብቻዋ የፈጠረች ስለሆነች ኑ እንስገድላት ማለት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌለውና ውሸት የሆነ ቃል ነው። ይህ ደግሞ ሌላ ነገር ነው። የትኛውን ብርሃን አልፈጠረችም፤ መድኃኒትም አይደለችም ብንል ማርያምን እንዳቃለልን ይቆጠራል? እርሷ ራሷ «ሉቃ 1፣47 ላይ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች» ያለችውን የሚሽር ቃል ምን ይሉታል? ማርያም የሐናና የኢያቄም ልጅ ናት የሚሉ ሰዎች «እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ»ዘፍ 1፣16 የሚለውን ሽረው ማርያም ታላላቅ ብርሃናትን ብቻዋን ፈጠረች ማለት ምን ማለት ነው? እንደሰዎቹ አባባል ማርያም ሰው ሳትሆን አምላክ ናት። ከሐናና ከኢያቄም አልተወለደችም፣ ይልቁንም ዘላለማዊ መንፈስ ናት ማለታቸው ነው። ይህ ደግሞ ክርስቶስ ከእርሷ የለበሰውን ስጋ መካድ ነው። ባንድ በኩል ቃል ስጋ ሆነ እያሉ እያስተማሩ በሌላ በኩል ከማርያም የለበሰው ስጋ ብርሃናትን ከፈጠረ መንፈስ ነው ማለት ምን የሚሉት ነገር ነው? በእርግጥም እብደት ነው!! ይህንን የስህተት ቃል ብንናገር ልብና ኩላሊት ያመላሰውን የሚያውቅ አምላክ በቅድስት ማርያም ላይ የድፍረት ወይም አክብሮቷን በመቀነስ የምንናገረው እንዳልሆነ ያውቃል። ማርያምን እናከብራለን የሚሉ ግን እሷ ያላለችውንና የማትለውን እንዲሁም «ጌታዬና መድኃኒቴ»የምትለው ልጇ ያልተናገረውን ቃል ፈጥረውና የሰይጣን ሃሳብ ይዘው ታላላቅ ብርሃናትን የፈጠረች መድኃኒት ናት ማለት ክርስትና ሳይሆን ክህደት ነው። ዲያቆን ሉሌ ከላይ የገለጸው እውነት ቅዱሳንን ለማቃለል ሳይሆን ስለቅዱሳን የሚጻፉት ክህደቶች ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ናቸው ብሎ ያሳየን ነው እንጂ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚቀባጥሩት ወይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አቅርበው አያስረዱ ወይም ደግሞ የቀረበውን እውነታ አይቀበሉ፣ ብቻ ለምን ውሸቱ እውነት እንደሆነ አይቀጥልልንም? ለምን ትነካኩብናላችሁ? እኛ የምለው ሁሉ ሀቅ ነው! ወዘተ ዓይነት ለመከላከል የሚደረግ ሩጫ መሆኑ ያሳዝናል!!!!
  ዙሐል የጣዖት ስም ነበር? አዎ ነበር። ዙሐል በየወሩ በ12 ቀን ይከበር ነበር? አዎ ነበር። የዙሀልን አምልኮ ቤትና እለቱን እንዳለ ተቀብሎ ነው ወደሚካኤል ስም የተቀየረው? አዎ!! ይህንን የሚናገረን ራሱ ድርሳነ ሚካኤል ነው። በ12 ቀን የተደረገው ተአምር ይህ ነው እንጂ ሚካኤል ስለተባለው የሰዎቹ መልአክ በየወሩ በ12 የተደረገ ሌላ ነገር የለም። አዎ፣ ይህንን ራሱ መጽሐፉ ያስረዳል። ታዲያ ሉሌ ምን ያጠፋው ነገር አለ? ዛሬ በየወሩ በ12 ቀን የሚከበረው የዱሮው የዙሐል በዓል ነው። ይህ የሆነው ልማደ ኀዲግ ከባድ ነውና የዙሐልን ለሚካኤል ሰጠነው ይላል መጽሐፉ!! ይህን ነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ወይስ ይህንን እውነት መናገር? ልቡና ያለው ይፍረድ!
  ማርያም በድንግልና ጌታን ወልዳለች፣ ቅድስትና ንጽሕት ናት፣ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይላታል? አዎ ይላታል!! ባይላትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታውን አያስቀርባትም። ማርያም ታላላቅ ብርሃናትን ፈጥራለች የሚለው የኦርቶዶክስ መጽሐፈ ደብተራ ትክክል ነው? አይደለም፤ ይህ ክህደት ነው!! ማርያም የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ናት? አይደለችም፣ ይህም ክህደት ነው!! እርሷ መድኃኒታችንን ወልዳለችና ክብር ይገባታል። ያማ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ ከእርሷ ሳይወለድ እሷው በሞተችልን ነበር!! እሷ ራሷ «በጌታዬና በመድኃኒቴ»ሉቃ 1፣47 አለች እንጂ እኔ መድኃኒታችሁ አላለችም። እነዚህ ሰዎች ከየት አመጡት? ከመጽሐፈ ገለፈት!!
  ቅዱሳን ሰዎችን፣ ቅዱሳን መላእክትን እናከብራለን፣ በእግዚአብሔር የጸጋው ኃይል ይሰራሉ። ተአምራትንና ድንቅን ቢያደርጉ የሚከብረው እግዚአብሔር በእነሱ እጅ ያደረገ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው። በኢቆንዮን ከተማ በልስጥራንን ባዳኑ ጊዜ ኢቆንያውያን መስዋእት ሊያቀርቡላቸው መሻታቸውን አይተው ልብሳቸው ከቀደዱ በኋላ «እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን»የሐዋ 14፣15 አሉ እንጂ ይህ ከእግዚአብሔር በተጨማሪ ለእኛም የተፈቀደ ነው አላሉም። ይልቁንም ይህንን በእኛ እጅ ስላደረገው ነገር ፊታችሁን ወደእርሱ መልሱ ነው ያሉት።
  እነዚህ ግን ፊታችሁን ወደዙሐል 12ኛው ቀን ብትመልሱ ትድናላችሁ ይላሉ። የለም ይህ ስህተት ነው ስንል መላእክትን ታቃልላላችሁ፣ታሳስታላችሁ ብለው በክፉ ወሬ ሊከሱን ይወዳሉ። እኛ ግን «በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን» 2ኛ ቆሮ 6፣8

  ReplyDelete
  Replies
  1. realy yihin ye'Egriabher menfes enji sigana dem algeletselhim.

   Delete
 17. «ንዑ ንስግድ ወንግነይ ላቲ፤ ለመድኃኒትነ ማርያም ድንግል ለዘገብረት ብርሃናተ ዐበይተ ለባሕቲታ» ትርጉም- መድኃኒታችን ለሆነችና ታላላቅ ብርሃናትን ብቻዋን ለፈጠረች ለድንግል ማርያም ኑ እስገድ፣ እናመስግናት» ማለት ነው።(የየካቲት ኪዳነምሕረት ዚቅ)
  እንግዲህ ይታያችሁ! ማርያም ቅድስት፣ንጽሕትና ብጽእት ናት ቢባል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃን መሠረት አድርጎ ነው። ይህ አንድ ነገር ነው። ማርያም መድኃኒታችን ናት፣ የሰማይ ታላላቅ ብርሃናትን ለብቻዋ የፈጠረች ስለሆነች ኑ እንስገድላት ማለት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌለውና ውሸት የሆነ ቃል ነው። ይህ ደግሞ ሌላ ነገር ነው። የትኛውን ብርሃን አልፈጠረችም፤ መድኃኒትም አይደለችም ብንል ማርያምን እንዳቃለልን ይቆጠራል? እርሷ ራሷ «ሉቃ 1፣47 ላይ ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች» ያለችውን የሚሽር ቃል ምን ይሉታል? ማርያም የሐናና የኢያቄም ልጅ ናት የሚሉ ሰዎች «እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቆች ብርሃናትን አደረገ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲሠለጥን፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲሰለጥን ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ»ዘፍ 1፣16 የሚለውን ሽረው ማርያም ታላላቅ ብርሃናትን ብቻዋን ፈጠረች ማለት ምን ማለት ነው? እንደሰዎቹ አባባል ማርያም ሰው ሳትሆን አምላክ ናት። ከሐናና ከኢያቄም አልተወለደችም፣ ይልቁንም ዘላለማዊ መንፈስ ናት ማለታቸው ነው። ይህ ደግሞ ክርስቶስ ከእርሷ የለበሰውን ስጋ መካድ ነው። ባንድ በኩል ቃል ስጋ ሆነ እያሉ እያስተማሩ በሌላ በኩል ከማርያም የለበሰው ስጋ ብርሃናትን ከፈጠረ መንፈስ ነው ማለት ምን የሚሉት ነገር ነው? በእርግጥም እብደት ነው!! ይህንን የስህተት ቃል ብንናገር ልብና ኩላሊት ያመላሰውን የሚያውቅ አምላክ በቅድስት ማርያም ላይ የድፍረት ወይም አክብሮቷን በመቀነስ የምንናገረው እንዳልሆነ ያውቃል። ማርያምን እናከብራለን የሚሉ ግን እሷ ያላለችውንና የማትለውን እንዲሁም «ጌታዬና መድኃኒቴ»የምትለው ልጇ ያልተናገረውን ቃል ፈጥረውና የሰይጣን ሃሳብ ይዘው ታላላቅ ብርሃናትን የፈጠረች መድኃኒት ናት ማለት ክርስትና ሳይሆን ክህደት ነው። ዲያቆን ሉሌ ከላይ የገለጸው እውነት ቅዱሳንን ለማቃለል ሳይሆን ስለቅዱሳን የሚጻፉት ክህደቶች ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ናቸው ብሎ ያሳየን ነው እንጂ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚቀባጥሩት ወይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አቅርበው አያስረዱ ወይም ደግሞ የቀረበውን እውነታ አይቀበሉ፣ ብቻ ለምን ውሸቱ እውነት እንደሆነ አይቀጥልልንም? ለምን ትነካኩብናላችሁ? እኛ የምለው ሁሉ ሀቅ ነው! ወዘተ ዓይነት ለመከላከል የሚደረግ ሩጫ መሆኑ ያሳዝናል!!!!
  ዙሐል የጣዖት ስም ነበር? አዎ ነበር። ዙሐል በየወሩ በ12 ቀን ይከበር ነበር? አዎ ነበር። የዙሀልን አምልኮ ቤትና እለቱን እንዳለ ተቀብሎ ነው ወደሚካኤል ስም የተቀየረው? አዎ!! ይህንን የሚናገረን ራሱ ድርሳነ ሚካኤል ነው። በ12 ቀን የተደረገው ተአምር ይህ ነው እንጂ ሚካኤል ስለተባለው የሰዎቹ መልአክ በየወሩ በ12 የተደረገ ሌላ ነገር የለም። አዎ፣ ይህንን ራሱ መጽሐፉ ያስረዳል። ታዲያ ሉሌ ምን ያጠፋው ነገር አለ? ዛሬ በየወሩ በ12 ቀን የሚከበረው የዱሮው የዙሐል በዓል ነው። ይህ የሆነው ልማደ ኀዲግ ከባድ ነውና የዙሐልን ለሚካኤል ሰጠነው ይላል መጽሐፉ!! ይህን ነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው ወይስ ይህንን እውነት መናገር? ልቡና ያለው ይፍረድ!
  ማርያም በድንግልና ጌታን ወልዳለች፣ ቅድስትና ንጽሕት ናት፣ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይላታል? አዎ ይላታል!! ባይላትም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታውን አያስቀርባትም። ማርያም ታላላቅ ብርሃናትን ፈጥራለች የሚለው የኦርቶዶክስ መጽሐፈ ደብተራ ትክክል ነው? አይደለም፤ ይህ ክህደት ነው!! ማርያም የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ናት? አይደለችም፣ ይህም ክህደት ነው!! እርሷ መድኃኒታችንን ወልዳለችና ክብር ይገባታል። ያማ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ ከእርሷ ሳይወለድ እሷው በሞተችልን ነበር!! እሷ ራሷ «በጌታዬና በመድኃኒቴ»ሉቃ 1፣47 አለች እንጂ እኔ መድኃኒታችሁ አላለችም። እነዚህ ሰዎች ከየት አመጡት? ከመጽሐፈ ገለፈት!!
  ቅዱሳን ሰዎችን፣ ቅዱሳን መላእክትን እናከብራለን፣ በእግዚአብሔር የጸጋው ኃይል ይሰራሉ። ተአምራትንና ድንቅን ቢያደርጉ የሚከብረው እግዚአብሔር በእነሱ እጅ ያደረገ እግዚአብሔር ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው። በኢቆንዮን ከተማ በልስጥራንን ባዳኑ ጊዜ ኢቆንያውያን መስዋእት ሊያቀርቡላቸው መሻታቸውን አይተው ልብሳቸው ከቀደዱ በኋላ «እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን»የሐዋ 14፣15 አሉ እንጂ ይህ ከእግዚአብሔር በተጨማሪ ለእኛም የተፈቀደ ነው አላሉም። ይልቁንም ይህንን በእኛ እጅ ስላደረገው ነገር ፊታችሁን ወደእርሱ መልሱ ነው ያሉት።
  እነዚህ ግን ፊታችሁን ወደዙሐል 12ኛው ቀን ብትመልሱ ትድናላችሁ ይላሉ። የለም ይህ ስህተት ነው ስንል መላእክትን ታቃልላላችሁ፣ታሳስታላችሁ ብለው በክፉ ወሬ ሊከሱን ይወዳሉ። እኛ ግን «በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን» 2ኛ ቆሮ 6፣8

  ReplyDelete
  Replies
  1. "«በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን» 2ኛ ቆሮ 6፣8" eg/r ahunim kelibunachihu wede kalachihu yimelisachihu!!!

   Delete
 18. በጣም ያሳዝናል ብሎጋችሁን እከታተል ነበር ነገር ግን ዛሬ ገና ማንነታችሁን ገለጣችሁ፡፡ ጨርሼ አላነበብኩትም ቅዱስ ሚካኤልን የሰደብኩ ያህል ስለተሰማኝ ተውኩት ትንሽም ብትሆን ላነበብኩት እፀፀታለሁ፡፡ እግዚያብሔር ልቦና ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 19. Lule

  Yemelakt sira enqan mn endehone atawkim.... sitgrim... Hedeh andus senbt timhrit bet kedamy temar....
  "Ye egziabher melak bemfrut sewoch zuray yesfral yadnachewmal"

  ReplyDelete
 20. I think taht if we want to follow the right pass, we have to be open minded. Furthermore we should try to understand others' view and analysis it freely . we have mind and edicated enough, I am not member of any group, but I am a follower of truth.

  ReplyDelete
 21. Ewunetaw tegeletse... Enante Menafikan hulu...

  ReplyDelete
 22. Mndnaw sadbu, awnatayanat bamaraga anji basdb aydalam waym balakso aydalam.
  First of all, we have to know that the true religion is based on true knowledge. If we denied this reality, we are not only wrong but we might be the source of evil. I am wonder that if we can not distinguish the right of God which is to worship him alone, from the right of His angel, which is respect, How we can distinguish cultuer from religion. In fact, for some people difficult to leave what they believed eventhough that is absolutely wrong.
  Yahonaw honow fsum snamgbar batamolaw mangad bnmamar awnatayawun mangad anmaralan/
  peace and blessing on all who research and love the truth.

  ReplyDelete
 23. "ሰይጣን ላመሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል" ይቺ ተረት ድሮም የነበረች ናት። ጥቅስ መጥቀስማ ሰይጣንም ይጠቅሳል። ክፉና ደጉን መለየት እንዴት አቃታችሁ? ዮሀንስ ሊሰግድ ተደፋ ትህትናን አስተማረን። መልአኩም ባርያ ነኝ አለ ትህትናን አስተማረን። እስቲ እንደ መልአኩ ራሳችንን ዝቅ እናድርግ። እንደ ዮሀንስም ቅዱሳንን እናክብር። "አንጋጠው ቢተፉ ተመልሶ ባፉ"ይቺ ተረት ድሮም የነበረች ናት። ትዕቢት ክፉ ነው። ትህትና ደግ ነው። ቢጠቀስም ባይጠቀስም። ክፉውን ደግ ነው ብሎ ጥቅስ በመጥቀስ ለማሳመን መሞከር ይቺ የሰይጣን ዘዴ ነች። "ሰይጣን ያረቀቀውን መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን..." ይሉ ነበር አባ ሰላማ ሲያሳርጉ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. TIHITNA YELIB NEW.ATSGEDLIGN DEGMO ATSGEDLIGN ENJI TIHTNA AYDELEM.NEGERUN ZIM BLACHIHU ATAWESASBUT.YETEBALEWIN BERASIH ABABAL MEKEYER LEMIN ASFELEGEH?Z ANGLE SAYS"ENIE ENDANTE BARIA NEGNINA ENDATEDERGEW".BEKA NEGERU YEMOTEW EZIGA NEW.!!!ENDATADERGEW!!! YIHININ EYETAZEZK ADERGALEHU KALK THAT'S UR CHOICE BUT I CAN'T.ALADERGEWUM!!!!!(BORN AGAIN CHRISTIAN & FOLLOWER OF Z ONLY Z HOLLY BIBLE)

   Delete
 24. 1. As Paul the Apostle advises, let's search, study everything in our power until we find out the truth. One thing is for sure. Truth is ultimately triumphant. Are we going to give God's glory to the work of his own hands, including Angels and mere mortal man? Are we comparing God with the dust and the wind?

  Let me challenge everyone here? Why did the now fallen Archangel Satnael came down from his post? Is it not because he was attempting to elevate himself to God himself and be worshiped by fellow Angels who all fell of their grace all at once? It just happens that if we keep doing what we do now, close to "worshiping" Angels and Saints, what does that mean to the Holy one of Israel? This is adultery !!! I believe it is HIS infinite mercy that kept us alive. IF not we never deserved to live even a single day day here one earth and on the new life to come!!! How merciful you are everlasting God, and wicked we are we human beings for distorting your truth which is as pure as anything!!!

  ReplyDelete
 25. ግራ ግብት ይለኛል የእናንተ ነገር።ይህንን ከፈጸመው ከቅዱስ እለእስክንድሮስ በጣችሁ ነው እሱን የምትነቅፉት።ያንን ሁሉ ሕዝብ በጥበበ እግዚአብሐር ከባዕድ አምልኮ አዉጥቶ ክርስቲያን ማድረግ የፈጣሪ ፈቃድ ነበር።የለመዱትን በዓል እምቢ ቢላቸው እነሱም እንግዳስ አንጠመቅም እምቢ ቢሉትስ ኖሮ፤ስለዚህ ልክ እንደ ቅዱስ ጳዎሎስ በጥበብ መልሶ በዓሉን በቅዱስ ሚካእል ስም አረገላቸው ዙሀልን ረሱት።ብዙ ቅዱሳን በተ ጣኦቱን ወደ በተ ክርስቲያን መለወጣቸው ሀጢያት ሊሆን ነው በእናንተ ትርጉም።ለላው ከላይ የደረዳራችኋቸው አባቶቻችን ድርሳነ ሚካእልን ሲሰሙ ሲያቡ ያደጉ ለመሆናቸው ጥርጣረ አይኖርም።ለዚህ ክብራቸው ያበቃቻቸው በተ ክርስቲያን ዉስጥ ሲነበብ ሲጸለይበት የኖረውን መጽሐፍ እናንተ ተነስታችሁ ይጥፋ ብትሉ አይሆንም እናንተ ትጠፋላችሁ እንጂ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. TAWOT AMLAKI ZEWER MALET YALEBET WEDE EGZIABHER ENJI WEDE MICHAEL AYDELEM COZ MICHAEL BY HIM SELF ALLWAYS TURN HIS FACE TO ALMIGHTY GOD.

   Delete
 26. jos-05
  13፤ እንዲህም ሆነ፤ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፥ እነሆም፥ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ። ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን? አለው።

  14፤ እርሱም። አይደለሁም፤ እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና። ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።

  15፤ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን። አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።


  rev-18.
  1.ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

  ReplyDelete
 27. Tadia " Aydelehum" Kale begid "HUN" Naw? But your quotes are perfrct and educational. We need to give due respect to angels and other saints. But not in place of God. I would like to stress, " due respect" which does not in any way imply worship or things of that nature. Human opinion or good will or personal attachment to beings is not any basis for our faith. If we read and understand "Tselote Haimanote", that would solve most of the unnecessary issues going on for generations.

  ReplyDelete
 28. Very wonderful point. Aba selamawoch Melkamun sera sertachuwhalena Medhanialem chemero yegeletelachehu. Lelochahechum kesehetet bememeles ewenetun temaru. Geta yelkedesewenena yarekesewen enante atekedesu.

  ReplyDelete
 29. rev-12

  "7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥

  8 ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።
  .......

  13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።"

  የቆሰለ አውሬ ይቅበዘበዛል።

  ReplyDelete
 30. እናንተ ሰይጣንኖች ቅዱስ ሚካኤል የስራችሁን የስጣችሁ:: በፈጠራችሁ አምላክ ይህንን ሰይጣናዊ ስራችሁን ይዛችሁ ከቅድስት ቤትክርስቲያናችን እንድትወጡ በቅዱስ ሚካኤል ስም እለምናችሁዋለሁ::

  ReplyDelete
 31. ለ“ዲያቆን” ሉሌ እና አባ ሰላማ በሎግ

  መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ

  አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር አስቀድሞ ምልክታችሁንና አመላችሁን ባይነግረን ኖሮ ምን ያህል እንደምንረበሽ ሳስበው እግዚአብሔር አምላክንና የእርሱን ደቀ መዘሙርት ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡ ለመሆኑ ጌታችን መጽሐፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ በማለት ፈሪሳውያንን የወቀሰው ለምንድነው ብንል ልክ እንደናንተ ስለነበሩ፤ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና ምድራዊ ልደቱን/ፈጹም አምላ ፍጹም ሰው መሆኑን/ ባለመረዳት የቆጥ የባጡን ይቀባጥሩ ስለነበር ይህን የምትስቱት የመጽሐፍትን አገባ ስለማትረዱ አዋቂዎች ነን የምትሉ ግን ደንቆሮዎች፤ የእግዚአብሔርን ጥበብና የማዳን ሥራውን ያላመናችሁ እንደስጋ እንጂ እነደ መንፈስ የማታስቡ ናችሁ ሲል፡፡ ይህ ቃል ስንመለከት ስታችኋል ሳይሆን ያለው ትስታላችሁ ነው የሚለው ፊደል ለቆጠረ ሰው ይህን ማስረዳት በጣም ቀላል ነው ይህ ለወደፊ የሚደረገውንም የሚያመላክት ነው፡፡ ለመሆኑ እናንተ እኛ ዲቆናት ነን ስትሉ፤ የእኛ ቤተክርስቲን የጥንቱ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ስትሉ ትንሽ እንከዋ አታፍሩም ለነገረሩ መጽሐፍስ “ለዘንዶው የስድብ አፍ ተሰጠው” አደል የሚል፤ እኛ የምንረዳው እናተ እንደምትሉት ካህናት የአምልኮ ዝሙት እየፈፀሙ ሳይሆን(ይህን ቃል በመድገሜ እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ አሁንም ደግሜ እላሁ መልአኩ በአማላጂነቱ ይጠብቀኝ፤ ይርዳኝ) እግዚአብሔር እያከበሩ ነው ይህን ደግሞ እናንተ በነገራችሁን የስድብ አፋ ሳይሆን በሕይዎታችን እንረዳዋለን፡፡ ታዲያ ይህ ነገር ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ አይደል እንዴ፡፡ ለመሆኑ እናንተ የየትኛው መጽሐፍ አዋቂ ሆናችሁና ነው ለመጽሐፍት ትችት ሰጭ ያረጋችሁ ለመሆኑ ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጂነት(በአጠቃላይም ስለቅዱሳን ተራዳኢነት) መጽሐፍ ቅዱስ አልተናገረም አስኪ የሚከተሉትን ልብ ብላችሁ ተመልከቷቸው፡-

  - «የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደመጣ ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤» መሳ ፲፫
  - «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ፤» ኢያ ፭፥፲፫-፲፭።
  - «ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤» ። መዝ ፩፻፪፥፳፩።
  - ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ዳን ፲፪፥፩
  - «ዳንኤል ሆይ! አትፍራ፥ ልብህ ያስተውል ዘንድ፥ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ከአደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን (ኀዘን፥ ጾም፥ ጸሎት ከጀመርክበት ዕለት) ጀምሮ ቃልህ (ጸሎትህ፥ ምልጃህ) ተሰምቷል፥ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ። የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን በፊቴ ነበር። እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፥ እኔም ከፋርስ ንጉሥ ጋር በዚያ ተውሁት።» ዳን ፲፥፲፫
  - ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም። ዳን ፲፥፳፩
  - በእስራኤልም ሠራዊት ፊት ይሄድ (ይመራቸው፥ ይጠብቃቸው) የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ (ከፈርዖንና ከሠራዊቱ በክንፈ ረድኤቱ ጋረዳቸው)፤ የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፥ በግብፃውያን ሰፈርና በእስራኤል ሰፈር መካከልም ገባ፥ በዚያም ጭጋግና ጨለማ ነበረ፤ ሌሊቱም አለፈ፥ ሌሊቱንም ሁሉ እርስ በርሳቸው አልተቃረቡም። ሲነጋም እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደተናገረ በበትረ ሙሴ ላይ ኃይለ እግዚአብሔር ተገልጦ ባሕረ ኤርትራ ለሁለት ተከፈለ፥ ውኃው ግራና ቀኝ እንደ ግድግዳ ቆሞ፥ እስራኤል በደረቅ ተሻገሩ፥ ግብፃውያን ሰጥመው ቀሩ። ዘጸ ፲፬፥፩-፴፩።
  - “መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉም? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?” (ዕብ.፩÷0፬)
  - “በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ መተላለፍና አለመታዘዝ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ..” (ዕብ.፪÷፪)
  - “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ” (ኢያ ፭÷0፫) ይለናል፡፡
  - “በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም”(ዳን.0÷፳፩)ብሎአል፡፡
  ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር “እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው”አለ፡፡ (የሐዋ.፩÷፴፭)
  - “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ” (ማቴ.0፰÷0)
  - እግዚአብሐርም ሙሰን "እይ እነ ለፈርኦን አምላክ ዘጸ ፯÷፩:
  - "...በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በመጣ ጊዘ እናንተም(12 ሐዋርያትን) 12 ዙፋን ተቀምጣችሁ...ትፈርዳላችሁ። ማቴ፲፱÷፳፰
  በመጨረሻ፡- «የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳን ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር በተከራከረ ጊዜ የስድብን ቃል ሊናገር አልደፈረም፥ እግዚአብሔር ይገሥጽህ አለው እንጂ። እነዚህ ግን የማያውቁትን በመሳደብ ይበድላሉ፤» ብሏል። ይሁ ፩፥፱። ሐዋርያው በመልዕክቱ እንደጻፈልን እናንተም ታገሱ እንጂ አትሳደቡ፤ በአጠቃላይ ይህነገራችሁ ወደየት እያመራ እንደሆነ ጥሩ አመላካችና እኛም ተንክረን እንድንሰራ የሚረዳን እንጂ ከሃይማኖታችን የሚያናውጸን ስላልሆነ ከንቱ አትድከሙ እና ከመጽሐፍቱ ባሻጋር አሁንም ደግሜ እላሁ በሕዎታችን አጣጥመን እናውቀዋለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ANTEDEGMO YETGNAW TEGUAMI NEH EGZIABHER YALTSAFEWUN(ጸሎትህ፥ ምልጃህ)(ኀዘን፥ ጾም፥ ጸሎት ከጀመርክበት ዕለት)EYALK TICHEMRALEH?

   Delete
 32. ወገኖቼ ምን ዓይነት ሰይጣን ነው ያደረባችሁ እግዚአብሔር ያከበረውን ማክበር እግዚአብሔር የወደደውን መውደድ ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን ክብር ማሳነስ ነውን እግዚአብሔር አብርሃምን ያለው የሚያከብሩህን አከብራለሁ የሚረግሙህን ደግሞ እረግማለሁ አይደል እንዴ ያለው ቅድስት ቤተክርስትያናችን ለቅዱሳኑ በምትሰጠው ክብር ለእግዚአብሔር በምታቀርበው አምላካዊ ምስጋና እስከዛሬ እርሷንም ልጆቿንም ጠብቆ አቆየን እንጂ ምን አደረገን ቅዱሳኑን መላአክቱን የናቁትና ያቃለሉት አውሮፓውያን ዛሬ ምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት እግዚያብሔር የለም አሉ እንጂ ምን አተረፉ ካህናቶቻቻውና ፓፓሳቶቻቸው ሳይቀር ወንድ ለወንድ እንዲጋቡ ሆኑ እንጂ ምን አተረፉ እስኪ አስረዱን

  ReplyDelete
 33. የሚገርም ነው የአንዳንድ ሰዎች ድርቅናና እያወቁ መካድ፡፡ በእውነቱ ይሄ በዚህ የጡመራ መድረክ የተጻፈው መልዕክት የተባረከ ሐሳብ ያለበትና እውነቱ የተገለጠበት ነው፡፡ እግዚአብሔር ጸሐፊውን ያሳድግልን የዕውቀቱን ብርሃንም ያብራለት፡፡ ዛሬ ባለችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወገኖቻችንን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነው ትምህርት ልቦናቸውን የወሰደውና አዕምሮአቸውን የበረዘው ጥንት በነበሩ የሀሰት ደራሲዎች የተዘጋጀው፤ የሰውንም አዕምሮ እየበረዘ ለሲዖል እያዘጋጀ ያለው እንደ “መልካ ሚካኤል” ባሉና መሰል የተረት መጽሐፍት የተጻፈ የኑፋቄ ትምህርት ነው፡፡ ፈጣሪ አንድ ቀን ይፈርዳል፡፡ እባካችሁ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼና እህቶቼ ከዚህ የተረት ድርሰት ፈጥናችሁ አምልጡ፡፡ ዘላለማዊ እውነት ወደ ሆነውና ወደ ማይሻረው ደግሞም በምንም ሊተካ ወደ ማይችለው ወደ እግዚአብሔር ቃል ተመለሱ፡፡ ለድነታችሁ የሚጠቅመው የመዳንን መንገድም የሚያሳያችሁ ቅዱስ ቃሉ ብቻ ነው፡፡ ይህም የመዳን መንገድ ብቸኛ አዳኛችን በሆነው በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጧል፡፡ ወደዚህ እውነት ሁላችሁም ተጋባዛችኃል፡፡

  ReplyDelete
 34. From the Biblical perspective and the teachings of real Tewado, none or our HAWARAYAT wrote about the comparison of the holy ANGLES AND ALMIGHTY LORD, instead st. Paul wrote in Hebrew that Angles to worship God,to obey him, to serve him, none of them deserve over magnified respect and a comparison with God. Remember their previous Boss Satinael was cast out because he wanted to share God's honor. We shouldn't even dare to argue about it. If you ask st. Michael about it, he will not agree with you. He himself and his followers are busy worshiping God nonstop. I don't think he has a time to receive worship like praise from you.
  MASTEWAL YESTACHU

  ReplyDelete
 35. የኢኦተቤ ቅዱሳንን አክብራ አክብሩ ትላለች እንጂ ተጠራጣሪዎች እንደሚከሱአት አይደለችም። ቤተክርስቲያኗን በሩቅ እንዲሸሹአት ወይም በውስጧ ያሉትን ለመበረዝ እያደረግአችሁ ያላችሁት ተግባር ራሳችሁን ከማጋለጥ አላለፈም። አሁን እየተጋለጣችሁ ነው። ወደፊት ደግሞ ትቀሰፋላችሁ። እስቲ የት ቦታ ነው ፍጡርን አምልኩ ያለችው? አሳሳች የዲያብሎስ መልእክተኞች። ቃላቶችን በማጋጨት መንፈሳዊ ተግባርን የሚጋጩ ማስመሰል የዲያብሎስ ምክር ነው። መንፈሳዊ ተግባር ቅን ለሆነ ሰው የተሰወረ ኦይደለም።

  ReplyDelete
 36. Daniel said,'It is only michael who helps me"(dan10,13)what does it mean for this man?The government of GOD is not as we think.we people and angles can do what GOD can if we're perfect except creation.GOD or Jesus crist is by his own power,ours is by gift.In the bible we read "mikael fought satan and his folowers"If we have to believe Your nonesense words of protestants(just prtesting is the name holly sprit has given you)why God fights him self.If the thrown satan has the power divert people from their true creater,why not true angles bring us to the kingdom of GOD?

  ReplyDelete
  Replies
  1. FIRST OF ALL TRY TO READ WHO SAID (DANIEL 10:13)THE SPEAKER IS SAINT GEBREAL NOT DANIEL.SO..........SO PLZ PRAY BEFORE READING BIBLE.LEMEKERAKER SAYHON HIWOT ENDIHONLIH BIBLE MANBEB ALEBIH.

   Delete
 37. edegemewalehu
  ሉለ እስቲ መጻሕፍት ምን እንደሚሉ አንብ።ደስ ያለህን ብቻ ሳይሆን የሚቀጥሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብ ባትቀበላቸዉም።
  ነብዩ ኢልያስ እልሳን ወደ እነ ለምን ያለውና የሱን መንፈስ እጥፍ ለምኖ ማግኘቱን አላነበብክምን?2ነገ2:9-11 እኛም ቅዱሳንን ቀጥታ ወደ እነሱም እንለምናለን፤ከነብያቱ ተምረናልና።
  ዘፍ2:7፡እግዚአብሐር አዳምና ሚስቱን"...በምድር የሚንቀሳቀሰዉን ሁሉ ግዟቸው"አላቸው።ፍጥረት የተፈጠረ ለእኛ ነው።ድንግልማ፤ቅዱስ ሚካእልም ምን ይጠየቃል ገዥዎቻንን ናቸው
  ዘጸ7:1-እግዚአብሐርም ሙሰን "እይ እነ ለፈርኦን አምላክ አድርጊሀለ።እልቅስ ቅ/ሚካእል አምላክ ሆኖ ተሽሞብህ እንደሆነ በምን ታዉቃለህ?እንደ ፈርኦን ትቢተኛ በሆነ ሰው ላይ አሁንም እግዚአብሐር ወደጆቹን ከመሾም ማንም አይከለክለዉም።
  ኢያሱ5፡13-15፡ኢያሱ የሙሰ ምትክ ለእግዚአብሐር የሰራዊት አለቃ ሰገደ።መል አኩም ጫምህንም አዉልቅ መስገድህ ብቻ በቂ አይደለም ነው ያለው።
  ዮሐ14:12 እውነት እውነት እላችኋለሁ በእነ ያመነ እነ የማደርገዉን ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ።
  ማተ10፡40"እናንተን የሚቀበል እነን ይቀበላል...
  ማተ16:19፤...የመግስተ ሰማያትን መክፈቻ እሰጣሃለሁ...
  ማተ17:20 የሰናፍጭ ያህል እምነት ቢኖራችሁ...የሚሳናችሁ ነገር የለም።
  ማተ19:28"...በዳግም ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በመጣ ጊዘ እናንተም(12 ሐዋርያትን) 12 ዙፋን ተቀምጣችሁ...ትፈርዳላችሁ።

  ReplyDelete
 38. 'deyaqone' lule manini eyageleglik enidhon yisemahale? Brigiti yegeta ageligay wyisi qalatin kshino maqirbi silchaliki hunetawoch silfqdulihi bicha Yetgnawu hawariya newu rasun dbiqo simhenim
  silmiteratrwu nwu abune selama bytignaw tarikachw
  yanten asitmehiro yemidgifu honew new klay yaluts abatoch xinigidihe ke achiberibarent ytenesa kante min enmare lwnigel kqomike xbaselaman twewuna klay yasiqmtikachewun xbatoch siel tewewuna kasiflge fotohin yizeh wuta yane yeewunt ageligay mhonikin geltsih esikmot diresi letamnikibt Yemitnori moti enkwa bimta sitsheshi jerbahin sayihon ginbarihin sthe litimoti yigbal yihi gini tra achibribare wenigel yemiyasitmire sayihon memari yemigbahi nehi biye aminalhu

  ReplyDelete
  Replies
  1. AGELGAY MALETKO YE'EGZIABHERN KAL YEMIYASTEMIR ENJI YEMAYHON TERET TERET MESBEK AYDELEM.YEY LULE U R Z RIGHT MAN FROM GOD.BLESS U MORE.TERET YALTERETE BEKA BENANTE BET AGELGAY AYDELEM?KA...KA....KA....."EGNAS KE'EGZIABHER GAR TAREKU BLEN SILE KIRISTOS ENSEBKALEN"YILAL BIBLE.MASTEWAL YISTEN.

   Delete
 39. ወደ መላእክት ጸሎት ያቀረበ የእግዚአብሔር ሰው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም አይገኝም። min malet new? metshaf kidusun alayewutim eko melkam neger new!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 40. Besmeab yegna diakon wedase mariamune ena lelochen enkuan beagbabu yetemerek atemeselegnem enezih yemelke metsehafoche endante balu sewoche sayhone egzoabher tebebune begeletelachew sewoche yetetsafu selehonu yanten yemayreba were alsemame metfo YETEHADESO MENAFEKE BLOG NEWWWWWW!!!!!!

  ReplyDelete
 41. GREAT POINTS MENTIONED HERE.Please back to the truth of bible.Only jusus is savior,no one another.God bless you lule.

  ReplyDelete