Monday, November 21, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በመንፈሳውያን ኮሌጆቻችን ውስጥ ምን እየሠራ ነው? - - - Read PDF

ማኅበረ ቅዱሳን የጥቃቱ ዋና ኢላማ ካደረጋቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋማት መካከል መንፈሳውያን ኮሌጆች ይገኙበታል፡፡ "ከእኔ በቀር ሌላው ሁሉ የተሳሳተ ነው፤ ስለዚህ ቤተ ክርስቲያኗን ለቆ ይውጣልኝ" እያለ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን፣ መንፈሳውያን ኮሌጆችን በጥርጣሬና በክፉ አይን ነው የሚያያቸው፡፡ በተለይም የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የቅድስት ሥላሴን መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በመቀሌ የሚገኘው የከሣቴ ብርሃን አባ ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለማኅበረ ቅዱሳን "የመናፍቃን መፈልፈያዎች" ናቸው፡፡ ማኅበሩ እንዲህ ለማለት አቅምም፣ ስልጣንም ሆነ መብት የሌለው ቢሆንም፣ እርሱ ግን ማንንም ሳያፍርና ሳይፈራ ሁሉ ስሕተተኛ ነው፤ እኔ ብቻ ነኝ ልክ በሚለው የተሳሳተ አቋሙ ጸንቶ ቤተ ክርስቲያናችንን እያመሰ ይገኛል፡፡

መንፈሳውያን ኮሌጆቻችን ለእርሱ የማይመቹና ተረታ ተረቶቹን የሚያጣጥሉበት የዕውቀት ስፍራዎች ስለሆኑ ይፈራቸዋል፡፡ ብዙዎችም ካለማወቅ ወደማወቅ የሚሸጋገሩባቸው፣ ከተረታ ተረት ወደ ወንጌል እውነት ዘወር የሚሉባቸው፣ አዳኛቸውንና የነፍሳቸውን ዕረፍት ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያውቁባቸው ተቋማት ናቸው፡፡ በዚህ ምክንያት ተቋማቱ ማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ የራስ ምታት ሆነውበት ቆይተዋል፡፡ እንዴት እንደሚያጠቃቸውም ስልቶችን ነድፎ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በተቻለው መጠንና ባገኘው መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከተማሪዎች እስከ መምህራን የጠረጠራቸውን እንዲባረሩና ወደ ሌላ ቦታ እንዲቀየሩ ሲያስደርግም ቆይቷል፡፡ ይሁን እንጂ የወንጌል እውነት ምን ጊዜም አሸናፊ በመሆኑ ማኅበሩ አንዳንድ ሰዎችን በማስባረርና በማሳደድ የልቡን ሊያደርስ አልቻለም፡፡ እርሱ ባስባረራቸው ምትክ ብዙዎች በወንጌል እውነት ሕይወታቸው ተለውጦ ይገኛል፡፡

ማኅበሩ በመንፈሳውያን ኮሌጆች ዙሪያ የከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ የኮሌጆቹ ማኅበረሰቦች በቸልታ አላዩትም፡፡ ተባብረው በአንድነት ድምፃቸውን እስከ ማሰማት የደረሱበት አጋጣሚም ጥቂት አይደለም፡፡ ከዚህ ቀደም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ የከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በይፋ እና በጽሑፍ የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ አሁንም ቢሆን ይኸው ተቃውሞ እንደ ቀጠለ ነው፡፡

ከውጪ ሆኖ መወንጀል ብዙ እንደማያዋጣው የተረዳው ማኅበረ ቅዱሳን የተቃውሞውን አቅጣጫ ለውጧል፡፡ ወደ ኮሌጆች ለመማር የገቡትን ደቀ መዛሙርት ለማጥመድና ለመወንጀል ሲል የራሱን አባላት በየኮሌጆቹ እንደሰገሰገ ይታወቃል፡፡ ከውጪ መሰግሰግ ብቻም ሳይሆን አንዳንድ የገንዘብ ችግር ያለባቸውን ደቀ መዛሙርት በገንዘብ በመደለል ለእርሱ እንዲሰልሉ እያደረገ ነው፡፡ ማኅበሩ እየከፈለላቸው በየኮሌጆቹ የሚማሩት አባላቱና ምልምሎቹ ዋና አላማቸው መማር ሳይሆን በክፍል ውስጥ ትምህርት ሲሰጥ ለየት ያለ ጥያቄ የሚያነሡትንና አመለካከታቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ተረት ጋር አልገጥም ያለውን ሰው ማንነት ለማኅበረ ቅዱሳን የስለላ ክፍል በማሳወቅ በዚያ ሰው ላይ ክትትል እንዲደረግ መጠቆምና ከኮሌጁ ብሎም ከቤተ ክርስቲያን የሚባረርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው፡፡ ብዙዎቹም የመቅጃ መሳሪያ ይዘው እንደሚገቡ ይታወቃል፡፡ እስከዚያው እነዚህ ተማሪ መስለው ወደ ኮሌጆቻችን የገቡት የማኅበረ ቅዱሳን የመረጃ ክፍል አባላት ጥያቄዎች ሲነሡና ለማኅበረ ቅዱሳን አመለካከት የማይስማሙ ሆነው ሲገኙ፣ "ይህ የመናፍቃን ጥያቄ ነው ለምን እዚህ ይነሣል? … ይህ የፕሮቴስታንት ትምህርት ነው ለምን እዚህ ይነገራል?" ወዘተ እያሉ ጠያቂውንም ሆነ መምህሩን በማሸማቀቅ ሥራ ተጠምደው እንደሚገኙ በየጊዜው የሚስተዋል እውነት ነው፡፡
ከዚህ አልፎ ተርፎም በየኮሌጁ የሚማሩና ማኅበረ ቅዱሳን ያደራጃቸው ደብዳቢዎች አሉ፡፡ እነዚህ ክፍሎች በማኅበረ ቅዱሳን ተሐድሶ መናፍቅ ተብሎ የተፈረጀውን ሰው መውጫ መግቢያውን ካጠኑ በኋላ፣ አሳቻ ሰዓትና ቦታ ጠብቀው የሚደበድቡ ናቸው፡፡ በዚህ መንገድ ብዙዎች እየተደበደቡ መሆናውን ከዚህ ቀደም አስነብበናል፡፡  

ለመሆኑ የኦርቶዶክስ ትምህርት ገምጋሚና ይህ ልክ ነው ይህ ደግሞ ስሕተት ነው ለማለት ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኮሌጆች የገቡት ሊማሩና ሊያውቁ፣ ቤተ ክርስቲያናቸውንም ወደ ተሻለ ነገር ሊያደርሱ ነው እንጂ ተጭነው ይዘው የገቡትን ይዘው እንዲወጡ አይደለም፡፡ ደግሞስ ሃይማኖት በዱላ ነው ወይ የሚስፋፋው? ለዚህ ነው እኮ ብዙ ጊዜ የማኅበረ ቅዱሳን አጀንዳ ሃይማኖት ሳይሆን ፖለቲካ ነው የምንለው፡፡

ስለዚህ በማኅበሩ ሰላዮች መሸማቀቅ ሳይሆን እናንተ ማናችሁ? ብሎ ማሳፈር ይገባል፡፡ በየኮሌጆቹ እየተነሣ ያለው ማኅበረ ቅዱሳንን በክፉ ስራው የመቃወም እንቅስቃሴም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ለዚህም መተባበርና የማኅበረ ቅዱሳንን እኩይ ተግባር መግለጥ ወቅቱ የሚጠይቀው ትልቅ የቤት ስራ ነው፡፡ በመደባደብ ተግባር የተሰማሩትንም ለሚመለከታቸው የሕግ አካላት እያቀረቡ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ ይገባል፡፡

20 comments:

 1. The Colleges need to make sure that the academic rights and security of students and teachers must be protected like any other academic institution. The police should issure restraining orders to MK suspects and must be chased out of the premises of these sacred institutions. May Elshady, our Lord fight and overthrow this agent of the prince of darkness.

  ReplyDelete
 2. America's former president Ronald Regen once called Libiya's former dictator Gadafi " mad dog of the middle east" Gadafi ያላቅሙ ሁሉንም ይተናኮል ይለካክፍ ነበር ስለዚህ ያበደ ውሻ ብሎታል። የኛው አገር ያበደ ውሻ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን ነው። የማይለክፈው ነገር የማይገባበት ነገር የለውም። አቅሙን፤ ቦታውን ግን አያውቅም ስለዚህ የሚገባበት ነገር በሙሉ የብጥብጥ መንደር እየሆነ መጥቶአል። አሁን ደግሞ ያሉንን፣ ተስፋ የተጣለባቸውን ትምህርት ቤቶች መተናኮል ጀመረ። ያበደ ውሻ።

  ReplyDelete
 3. kealem slehonachihu yesidib af alachihu kemeknat mesirat mk sleseranew bealem behulum bota yalew enam ene mk balhonm sirachew des slmilegn ewedachewalehu betam betam kenategna slehonachihu enante dejeselamawech manm yetwahdo lijoch aysemachihum atlfu bemtiku yilk yemiyant tihuf bitawetu melkam new

  ReplyDelete
 4. andit enkua besim yetetekese masreja yelelew tsihuf. Mk alalawus alachihu aydel. Ay Mk EGZIABHER yibarkachihu.

  ReplyDelete
 5. kehonew 1% alsafachehum. mk eko awere new. hulun asdo lebla bay new. yihen awere fitlefit mekuwakuwam yasefelegal.

  ReplyDelete
 6. 100 % true new. yihe ye aganenete menfese yaderebet mahebere betebeten eko

  ReplyDelete
 7. ወንጌል ያለመከራ አይሰበክም፡፡ ለክርስቶስ ወንጌል መስፋፋት ምክንያት አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ምክንያቱም በአዳምና ሄዋን ምክንያት አንድ ጊዜ ወደዓለም የገባው የርኩሰትና የጥፋት በደል የደም ዋጋና ሞት ነው ያስከፈለው፡፡ ለምሳሌ አዳምና ሄዋን በለስን በልተን ሁሉን እናውቃለን ብለው እራሳቸውንና ሁሉንም ጨለማ እንዳስገቡትና የእግዚአብሔርን ልጅ ደም እንዳስከፈሉት ሁሉ፣ ይህም ማኅበር የጥፋት በለስን ሁልጊዜ ስለሚበላ የክርስቶስን ተከታዮች እየተከታተለ ደም ማፍሰስ አለበት፡፡እኛ መዳናችን ያወቅነው ክርስቶስ ተከሶ በአደባባይ ሲቆምና ደሙን ሲያፈስ ነው፡፡ አሁንም በተረፈ አይሁድ ማኅበረ ቅዱሳን እጅ የወንድሞቻችን ደም በእግዚአብሔር ልጅ ስም መፍሰስ አለበት፡፡ ይህ የወንጌል አርማችን ነው!!!! የጌታ ልጆች ደስ ይበላችሁ፡፡ ውሸት ከሌለ እውነት ሊታወቅ አይችልምና፡፡

  ReplyDelete
 8. what do the protestant menafkans work in our spiritual colleges? MK should be there ( every college) to clean these wolfs who are sponsored by dabilos -led menafkan organization (muluwongel, kale hiwot, mekaneyesus, meseretekirstos....etc). mark my word you do not post it.

  ReplyDelete
 9. "ብዙዎቹ ካለማወቅ ወደማወቅ ከተረታ ተረት ወደወንጌል ብርሃን"ጽሁፋችሁን ግን ታስተውሉታላችሁ?? አይ ማህበረ ቅዱሳን!ኑፋቄያችሁን እንዳትበትኑ ራስ ምታት ሆናችሁ አይደል?? እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን ይባርክ!!!! ለናንተም ልብ ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 10. Yeaganenet abat eko new Mk. Yesew mist yemedefer ZEMAWE Balege!!!!

  ReplyDelete
 11. ማኅበረ ቅዱሳን በኮሌጆቻችን ምን እያደረገ ነው? ደግሞ ኮሌጆቹ የናንተ ሆኑ እንደ? እኛ ተሃድሶዎች እያላችሁ ከጻፋችሁን በኋላ የኛ ቤተ ክርስቲያን ትላላችሁ እንዴ? እኔ እኮ እኛ ተሃድሶዎች ስትሉ በእውነት መናገር የተማራችሁ መስሎኝ ነበር ነገር ግን እውነትን የማይወድ እናንተን በእናታችሁ ላይ ያሰለፈ ጠላት ማንነታችሁን ማጋለጣችሁ መዘዙ ምን እንደሆነ ስለሚያውቅ የቀደመውን ማመሳሰል አጥብቃችሁ ቀጥሉ ኦርቶዶክስ ነን በሉ በስሟ እየተጠራችሁ እኔ የምፈልገውን ያክል ነፍስ ልቀማ አላችሁ አይደል? ያሳዝናል ሰው ሳያውቀው በጠላቱ እጅ ሁኖ ወገኖቹን ሲያጠቃ አሁንም እውነቱን ይግለጥላችሁ:: ባይሆን እንኳ የሆናችሁትን ነን እንድትሉ ይርዳችሁ:: ማኅበረ ቅዱሳን ግን በኮሌጆቻችን ማለትም በኛ በኦርቶዶክሳውያን ኮሌጆች ይማራሉ ያጠናሉ ጠላት እንዳይገባ ይጠብቃሉ:: ወደፊት ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅሙ የተዋኅዶ እምነትን አመሳጥረው የሚያስተምሩትን ነፍሳት ኮሌጆቹ እንዲያበዙ ይረዳሉ:: ኧረ ስንቱ ማ/ቅ ገና ብዙ ይሰራሉ::

  ReplyDelete
 12. For the above comment, guy you are living in the dark. What are you talking about do you want us to learn, and based our life with tert tert or based on the blood of the son of God Jesus? who is protestant, in short any one who based his or her life on tert tert in stead of the holly bible.

  ReplyDelete
 13. ዲያብሎስ ማለት ትክክለኛ ትርጉሙ ከሳሽ ማለት ነው።
  ማቅ ማለት ጽልመት ማለት ነው።
  በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ውስጥ፣ ወንጌል ሰባኪዎችን፣ ሓዋርያትን ኣርድእትን፣ ራሱ ክብር ለሱ ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሳይቀርL ተከሰሱ ሲባሉ ነው ያነበብነው እንጂ ከሰሱ የሚል ጽሁፍም ትምህርትም በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽሞ ኣይገኝም፣ ማቅና መሰሎቻቸው ያስገቡት ትምህርትና ጽሁፍ ካልሆነ በቀር።
  ምክንያቱም ከሳሽ ዲያቦልስና ልጆቹ (ማኅበረ- ቅዱሳን (ማኅበረ ሰይጣን፣ ዲያብሎስ) ብቻ ናቸው።
  በማኅበረ ሰይጣን፣ ያልተሰደበ፣ ያልተከሰሰ፣ ያልተደበደበ፣ ወይም የማይሰደብ፣ የማይከሰስ የማይደበደብ እውነትኛ ኣገልጋይና ክርስቲያን በኢትዮጵያ ምድር ካለ፣
  ክርስትናውን የጣለ የዲያብሎስ ምርኮኛ ሰው መሆን ኣለበት፣ በተረፈ ለክብሩ ፈተናን የተቀበሉ ቅዱሳን እንደ እነመጋቤ ሓዲስ በጋሻውና መሰሎቻቸው፣ ለጌታ ክብር ብለው ስደት እስከ ሞት ተቀብለዋል።

  ReplyDelete
 14. ቤተ ክርስቲያን መልስ አላት
  READ IN PDF
  በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለያዩ ዘመናት አያሌ መናፍቃን ተነስተው ነበረ:: ከአርዮስ ጀምሮ ብዙ መናፍቃን በክህደታቸው ምክንያት ሊቃውንቱ ከቤተ ክርስቲያን አውግዘው ለይተዋቸዋል:: አውግዞ መለየትም ብቻ ሳይሆን መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥቶባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ለመናፍቃን መልስ የሚሰጡ ሊቃውንትን አፍርታለች:: ቤተ ክርስቲያን ምልዑ ናት የሚባለው ለዚህም ነው::

  አሁን በእኛ ዘመን ተረፈ አርዮሳውያን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ሳይረዱ፤ ነገር ግን ግዕዝ ስለተናገሩ ብቻ ሁሉንም ነገር እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ተነስተዋል:: ለምሳሌ “አባ ሰላማ” የተባለው ብሎግ ማየት በቂ ምስክር ነው:: ይህ ብሎግ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረው ነገረ እግዚአብሔርን ይቃወማል:: የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት አይቀበልም፤ ነገር ግን የተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነ እያስመሰለ ሲያጭበረብር ይታያል:: የቅዱሳን ገድል እና የቅዱሳን መላእክት ድርሳን የሚተቸው የዘመናችን ተረፈ አርዮሳዊው ለ“አባ ሰላማ” ብሎግ መልስ የሚሆን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተመርጉዘው መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው እንደ ሊቃውንቱ አባቶቻቸው ጦምረዋል:: ይህንን በመጫን ያንብቡ CLICK HERE TO READ
  መልካም ንባብ::

  ReplyDelete
 15. you all guys who are employed to insult Mahibere Kidusan what is your salary??? Let me tell you one great truth, you can talk a lot since GOD gives freedom for anyone but be sure and remind that you cannot achieve the greatest place that is heaven unless u turn ur mind with 180 degree !!! So we have a great difference!

  ReplyDelete
 16. I don't have words to say about our church. look the guy wrote in Amahric, he is telling us that "holly books," all these tert tert books are holly books reading the bible and based our spiritual life on it counting like protestant. let me tell any one oppose this web site are grew up by the family who worship sitan or tenquye.
  Good job Aba Selam! Go head and praising God!
  Jesus is Lord!

  ReplyDelete
 17. MK use to come to my church. They occupy the church like they own the church. They don't contribute a single penny to the church. But they want to sell their magazines to our parishioners in a Holloway even though they were told reputedly not to. They have no respect for the priests who been serving the church for years. They visit some of the younger members homes and tell them the priests are not following the right bible. After so many incidents and trying to distribute political articles in the church we told them to get out. Since they left our church, we have been at peace.MK are in my opinion cancer to our society. If any one of you have to deal with MK, God help you. They have no problem lying. Get them out of your churches. God Bless You.

  ReplyDelete
 18. አሁን በግልጽ ነገራችሁን ለካ መንፈሳዊ ኮሌጆችም በእናንተ ቁጥጥር ናቸው፡፡ በጣም ይገርማል ---

  ReplyDelete
 19. ይህ ጽሑፋችሁ በእውነቱ ከእውነት የራቀ ነው ለመሆኑ ኮሌጆቻችንን ታውቁአቸዋላችሁን? እኛ ተሀድሶ በኮሌጆቻችን ውስጥ ምን እየሰራ እንዳለ በደንብ እናውቃለን በዚህ ጽሑፋችሁም ማንነታችሁን አረጋግጣችሁልናልና በጣም እናመሰግናችሁአለን ልቡናውንም ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 20. በጣም ደስ የሚል ዜና ነው ያስነበባችሁን። ሆድ ያባውን ____ ለማንኛውም ማመናችሁ እና ራሳችሑን መግለጻችሑ ጥሩ ነው፡፡ ለናንተ ግን የበግ ለምድ ለብሶ መምጣቱ ይሻላችሑ ነበር፡፡ አምላከ ቅዱሳን ልቦና ይስጣችሑ፡፡ አሜን

  ReplyDelete