Saturday, November 26, 2011

ዕንቁ መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ወይስ ነጻ መጽሔት? - - - Read PDF

ማኅበረ ቅዱሳን ሁለት ገጽታ ያለው ማኅበር መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ ከፊት ለፊት የሚታየው ሃይማኖታዊ ሽፋኑ ሲሆን፣ ያ ሲገፈፍ የሚቀረው ደግሞ የተደበቀውና ፖለቲካዊ ማንነቱ ነው፡፡ በሁለቱም አቅጣጫ ሲንቀሳቀስ ሚዲያዎችን ለአላማው ማሳኪያነት እንደየማንነቱ ይገለገልባቸዋል፡፡ ከፊት ለፊት ለሚታየው ሃይማኖታዊ ካባው ሐመርና ስምአ ጽድቅን ሲጠቀምባቸው፣ በማኅበሩ ስም በከፈተው ድረ ገጽም ተመሳሳይ ነገር ያቀርባል፡፡ ለድብቅ አላማው ማራመጃነት ደግሞ በርካታ ብሎጎችን፣ ለምሳሌ፡- ደጀሰላም፣ ገብር ሄር፣ አንዳድርግን፣ አሐቲ ተዋሕዶን፣ ይጠቀማል፡፡ በግለሰቦች ስም የተመዘገቡ የግል ጋዜጦችና መጽሔቶችንም ሁሉ ይጠቀማል፡፡ በተለይም ዕንቁ መጽሔት በግልጽ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ መጽሔቱ እንደ ነጻ መጽሔት አንድን ጉዳይ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ማቅረብ ሲገባው ብዙ ጊዜ ለማኅበረ ቅዱሳን ጥብቅና ቆሞና ሲብስም እርሱን ተክቶ ነው የሚናገረው፡፡ በነጻ ግን አይደለም፤ የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ተከፋይ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ መጽሔቱ የማኅበሩን ጉዳይ በጋዜጠኛ ደንብ ሳይሆን እንደማኅበሩ ልሳን ሆኖ የያዘውም ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ያው በበላበት መጮኹ ነው፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያኗን እንዳሻው ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ቆርጦ ከተነሣ ወዲህ "ተሀድሶ መናፍቃን" የሚለውን የቸከ ነጠላ ዜማውን ተቀብለው እንዲያጫፍሩት ራሱም የፈጠራቸውን ጨምሮ በቤተ ክርስቲያን ልጆች ላይ ያወጀውን ጦርነት እንዲያራግቡለት ከወራት በፊት ያቀናጃቸውና የእርሱን አላማ እንዲራምዱለት የሚከፍላቸው የነጻው ፕሬስ ውጤቶች የሆኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች አሉ፡፡ የተረጋገጠም እውነት ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል ዕንቁ መጽሔት አንዱና ዋናው ተዋናይ ነው፡፡

መጽሔቱ በኪነ ጥበብና በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ነው ቢባልም፣ ይህ ሽፋን ነው፡፡ ዋናውና ድብቁ የመጽሔቱ አጀንዳ ማኅበረ ቅዱሳን ወደፊት እንዲያገኝ ለሚፈለገው ፖለቲካዊ ድል ከአሁኑ ጀምሮ በሃይማኖት ሽፋን ኀያልነቱንና የበላይነቱን ማሳየት ነው፡፡ መጽሔቱን የሚያነቡት በአብዛኛው የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሳይሆኑ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደ መሆናቸው በእነርሱ ዘንድ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን እያደረገ ያለው "ተጋድሎ" እንዲታወቅና ብዙ ደጋፊ እንዲያገኝ ማስቻል ነው የመጽሔቱ ትግል፡፡ ይህ በባዶ ሜዳ የተወራ ሐሰተኛ ወሬ ሳይሆን መጽሔቱ በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ከሚያስነብባቸው ዘገባዎቹ በግልጽ የምንረዳው ሐቅ ነው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን በግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ውስጥ እጁ አለ የሚባለው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ ለዚህ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ለአንድ ሰሞን ታይተው የሚጠፉ ፕሬሶችን ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፡፡ አሁንም መዝለቃቸው የሚያጠራጥርና ማኅበረ ቅዱሳን የሚሰጣቸውን ተልእኮ ፈጽመው ከፕሬሱ መንደር የሚታጡ የፕሬስ ውጤቶችም እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ ቤተ ክህነት አካባቢ አንድ ጉዳይ ካላቸው ለዚያ አላማ ተጀምረው ያ ጉዳዩ ሲያበቃ የሚዘጉ ጋዜጦችና መጽሔቶች እንደነበሩና እንዳሉም ይታወቃል፡፡ የሩቁን ትተን በቅርቡ የጥቅምቱ ሲኖዶስ ሊጀመር ጥቂት ሳምንት ሲቀረው ቁጥር 1 ብሎ የተጀመረውን ቆንጆ መጽሔትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህ መጽሔት በቁጥር 1 እትሙ ዋና ዜና አድርጎ ያቀረበው "በፓትርያርኩ ሐውልት ዙሪያ የተወሰነው ውሳኔ የት ገባ?" የሚል ወሬ ነው ይዞ የወጣው፡፡ ይህም በአባ ሳሙኤል የሚቀነቀንና ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈልገውን አጀንዳ ለማስፈጸም መንጠላጠያ ያደረገው አጀንዳ ነበረ፡፡ ይኸው ቆንጆ መጽሔት በቀጣዩ እትም ደግሞ በሲኖዶስ ስብሰባ "ዘጠኝ ግለሰቦች ይወገዛሉ፣ ይታገዳሉ" ሲል በፊት ገጹ አስነበበ፡፡ እንዲህ የሚል አጀንዳ በየትኛው የሲኖዶስ ስብሰባ ተነሣ? ያው ማኅበረ ቅዱሳን በሌለው ውክልና፣ በሌለው አቅም እና በሌለው መብት ይወገዙልኝ ብሎ አቀረበው የተባለውን የክስ ሰነድ ይዞም አይደል? እንዲህ ያለው። "ዘጠኝ ግለሰቦች ሊወገዙ ነው" ብሎ መዘገብ ማኅበረ ቅዱሳን መሆን እንጂ ከአንድ በመረጃ ላይ ተመስርቶ ይሰራል ተብሎ ከሚታሰብ መጽሔት ፈጽሞ አይጠበቅም፡፡ ታዲያ ዘጠኙ ሰዎች የታለ የተወገዙት? ለምንስ ይህን ዝርዝር የሌለውን ርእስ ለማሻሻጫ በሽፋኑ ላይ ብቻ ጻፈ? ወደውስጥ ሲገባ ስለዘጠኙ ግለሰቦች ያለው አንዳች ነገር የለም፡፡ ከዚህ ሁሉ ጀርባ ግን ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡

ዕንቁ መጽሔትም ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንዳለና የእርሱ ልሳን መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ስሙ የሌላ ቢመስልም፣ ሥራው ግን የማኅበረ ቅዱሳን ልሳንነት ነው፡፡ አዘጋጆቹ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ንክኪ አላቸው፡፡ ከዚህም ሌላ የማኅበሩ ሰዎች በመጽሔቱ ላይ አምደኞች ናቸው፡፡ ዳንኤል ክብረት በአምደኛነት ስሙ ባይመዘገብም ቋሚ አምደኛ ነው፡፡ የስምአ ጽድቅ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር  ታደሰ ወርቁም በስም የተመዘገበ የዕንቁ መጽሔት አምደኛ ነው፡፡ በዚህ እትሙም በስምአ ጽድቅ ጋዜጣ ላይ ደፍሮ የማይጽፈውን አይነት ጽሑፍ ጽፎ አስነብቦናል፡፡ ያን ጽሑፍም ሌላው የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን የሆነውና ማኅበረ ቅዱሳን በየብሎጉ፣ በየጋዜጣውና በየመጽሔቱ ያወጣቸውን ተራ ወሬዎች አንድ አድርጎ እያወጣ የማለያየት ሥራ በመሥራት የሚታወቀው "አንድአድርገን" የተባለው ብሎግም አውጥቶታል።  ልብ በሉ! ዕንቁ መጽሔት አባ ሰላማ ብሎግን ከሜዳ ተነሥቶ ለመንቀፍ ዋቢ ያደረገው ደጀሰላምን ነው። አንድ አድርገንና ሌሎቹም ከዕንቁ ይወስዳሉ። እንዲህ እየተመጋገቡ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የማኅበረ ቅዱሳንን አጀንዳ ለማስፈጸም ደፋ ቀና የሚሉት። 

ዕንቁ መጽሔት የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ነው የተባለው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ እስካሁን በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ያወጣቸውን ዘገባዎች ያነበበ ሰው እንደሚያስተውለው፣ የዕንቁ ዘገባዎች ደጀ ሰላም የሚያወጣቸው ዘገባዎች ሌላ ገጽታ ነው። እዚህ ላይ ግን ዕንቁ መጽሔት "ተሐድሶ መናፍቃን" ተብለው በማኅበረ ቅዱሳን እየተሰደቡ ያሉትን ወገኖች በተመለከተ ያወጣውን ዘገባ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ እስኪ የሩቁን ትተን ሰሞኑን በሲኖዶሱ ስብሰባ ዙሪያ ያወጣውን ዘገባ እንመልከት፡፡ ለዚህ ዘገባው ዋና ምንጮች የማኅበረ ቅዱሳን የሆኑት ድረ ገጾች ደጀ ሰላም፣ ገብር ሄር፣ አንድ አድርገን ናቸው፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ሁሉም ተመጋጋቢዎች ናቸውና።

ዕንቁ መጽሔት በሲኖዶሱ ዙሪያ ያወጣው ዘገባ ማኅበረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱሳን የሚሸት ነው፡፡ በኅዳር 2004 እትሙ ላይ ዕንቁ ፍጹም ወገንተኛ ሆኖና ማኅበረ ቅዱሳንን ወክሎ፣ ማኅበሩን እያወደሰና ሌሎችን እየኮነነ ጽፏል፡፡ ነጻ መጽሔት ነኝ እያለ እንዲህ መጻፉ ከጋዜጠኛነት አኳያ አያስኬድም፡፡ ወይ ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ነኝ ቢል እንደሐመርና ስምአጽድቅ እንቆጥረው ነበር፡፡ ርግጥ በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ ከሚያወጣቸው ዘገባዎች አንጻር የነበረንን ጥርጣሬ አጉልቶ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን መሆኑን አረጋግጦልናል፡፡ የማኅበሩ ድረ ገጾች ሲያራግቡት የሰነበቱትን መሠረተ ቢስ ወሬ እውነት አስመስሎ ነው "የሲኖዶሱ ውሳኔዎች" በሚል ርእስ ሐተታ ያቀረበው፡፡ "እነበጋሻው ታገዱ"፣ "መዝሙር በኦርጋን መዘመር ተፈቅዷልን?" በሲኖዶስ የተኮነኑት ጳጳስ ሹመት ማግኘት (ስለ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነው) የሚሉ ነጥቦችን በ"ሃይላይት" መልክ አቅርቧል፡፡ እነዚህ ሁሉ በተጠቀሱት ድረ ገጾች ላይ ሲራገቡ የነበሩ የማኅበረ ቅዱሳን ወሬዎችና አሉባልታዎች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ ያልተወሰኑ፣ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን ተወስነልን እያለ የሚያስወራቸው ወሬዎቹ ሁሉ "የሲኖዶስ ውሳኔ" ተብለው በዕንቁ መጽሔት ላይ ተጠቅሰዋል፡፡ ለምሳሌ "ማደራጃ መምሪያውም ራሱን የቻለ ሀገረ ስብከት የሌለው ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብለት" የሚል ይገኝበታል፡፡ ይህ የማኅበረ ቅዱሳን የልብ ምኞት እንጂ የሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም፡፡ ሲኖዶሱ በአባ ሠረቀ ምትክ ሌላ መነኩሴ አስቀምጧል፡፡ ማኅበሩም ከሰሞኑ አቀባበል አደረኩላቸው ሲልም በየብሎጎቹ አስነብቦናል። ለምን ይሆን አቀባበል ማድረግ ያስፈለገው? አዲሱን ተሿሚ ወደ ራሱ አላማ በማስገባት የሚለውን እንዲፈጽሙለት ለማግባባት? ወይስ ያለውን ኀይል በማሳየት ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን ተሰልፈው ካልሰሩና በተቃራኒው ከተጓዙ በአባ ሠረቀ የደረሰው በእርስዎም ይደርሳል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ? ጊዜ ይፍታው። ማኅበረ ቅዱሳን ለምን እንዲህ አደረገ? ቢባል ማደራጃ መምሪያው ሀገረ ስብከት በሌለውና ራሱን በቻለ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ሲኖዶስ ወሰነ ብሎ ዕንቁን በፈቃደኛነት ለማሳሳትና ወደፊት "ያልተተገበረ የሲኖዶስ ውሳኔ" ብሎ በግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አቧራ ለማስነሳት እንደሆነ እንገምታለን፡፡

ከሁሉም የሚገርመው ዕንቁ መጽሔት "አባ ሰላማ" ድረ ገጽ ላይ ያቀረበው መሠረተ ቢስና በጥላቻ የተሞላ ትችት ነው፡፡ ዕንቁ መጽሔት ነጻ መጽሔት ቢሆን ኖሮ ያለአንዳች ማስረጃ ማኅበረ ቅዱሳንን ደግፎ አባ ሰላማን ባልተቃወመ፣ አባ ሰላማን ዘልፎ ማኅበረ ቅዱሳንን ባላሞገሰ ነበር፡፡ እስኪ አንባቢ ፍርድ ይስጥ "አባ ሰላማ ድረ ገጽ ፍፁም ፀረ ቤተ ክርስቲያን የሆነ አቋም በማንጸባረቅ ማኅበረ ቅዱሳንን በመተቸት " በማለት የሰነዘረው ከአንድ ገለልተኛ ነው ከሚባል መጽሔት ፈጽሞ ይጠበቃልን? እንዲህ ለማለት ዕንቁ መጽሔት ማነው? ከመቼ ጀምሮ ነው በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ እገሌ ልክ ነው፤ እገሌ ደግሞ የተሳሳተ ነው? ለማለት የቃጣው። እንዲህ ለማለት ብቃቱስ፣ ሞራሉስ፣ መብቱስ አለው ወይ? መቼም መጽሔቱ እንዲህ አይነቱን ድፍረት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ከዋለ ጀምሮ የተማረው ነው ከማለት በቀር ምንም ማለት አይቻልም። ባይሆን እንኳ በዘገባው ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ ብሏል ቢለን ኖሮ እንደ ማኅበረ ቅዱሳን ንግግር እንወስድለት ነበር። እርሱ ግን በራሱ ነው አውጋዥ ናዛዥ የሆነው። ለነገሩ ዕንቁ መጽሔት ምን ያድርግ? በበላት መጮህ ስላለበት ነው የማኅበረ ቅዱሳን አፍ ሆኖ አባ ሰላማን የወረፈው፡፡

መጽሔቱ "የድረ ገጾች መካሰስ" በሚል ንኡስ ርእስ ባሰፈረው ጽሑፍም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ድረ ገጽን በማብጠልጠልና የአባ ሠረቀ ድረገጽ በማለት "ብሎጎች (ጡመራዎች) ለወንጌል ወይስ ለወንጀል?" በሚል ርእስ ያወጣውን ጽሑፍ የተቸ ሲሆን፣ ደጀ ሰላም ከእነአባ ሰላማ ጋር ለምን ተደበለ? ሲልም አማሯል፡፡ አባ ሰላማ ብሎግ በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ ያወጣውን ዘገባ እውነተኛነቱንና ሐሰተኛነቱን መፈተሽ ሲገባ፣ እንዲሁ ፀረ ቤተ ክርስቲያን በሚል መፈረጅ ተገቢ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የማኅበረ ቅዱሳን ተራ ስድብና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደ እውነተኛ ምስክር፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረተው የአባ ሰላማ ድረ ገጽ ሐተታ ግን እንደ ስድብ የተቆጠረው ከቶ ለምን ይሆን? ደጀ ሰላም ለማኅበረ ቅዱሳን አልመች ያሉትን አባቶች ስም አለአግባብ እያጠፋ መሆኑ እየታወቀ፣ ስም አጥፊነቱ እውነተኛ ምስክር ይባልልኝስ እንዴት ይላል፡፡

ደጀ ሰላም "የተሳሳተ ያልነው ከመስመር የወጣውን የአባ ሰረቀን ቡድን፣ ቀኖና ጣሰ ያልነው ደግሞ አባ ፋኑኤልን ነው" በማለት እነዚህን አባቶች ብቻ የተሳሳቱ ሲል እንደፈረጃቸው አምኗል። ነገር ግን እንዲህ ለማለትስ እርሱ ማነው? ቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳስቷል ያላለችውን እርሱ በግብታዊነት ተሳስተዋል ማለትስ ከየት የመጣ ነው? ይሁን እንጂ እርሱም ሆነ ወንድሞቹ እነ ገብር ሄር፣ እነአንድ አድርገን ከላይ የተጠቀሱትን አባቶች ብቻ ሳይሆን፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ሐሳብ በተጻራሪ የቆሙትን ሁሉ ስማቸውን ሲያጠፉና ሲወርፉአቸው ነው የኖሩት። አሁንም በዚሁ ስራቸው እንደቀጠሉ ነው። ፓትርያርኩን ባለማቁዋረጥ እየወረፉአቸው ይገኛሉ። አባ ሠረቀን አባ "ሰረቀ" በማለት ተራ ስድብ ውስጥ ሁሉ ገብተዋል። ንቡረእድ ኤልያስን "ኑረዲን" ኤልያስ በማለትም ፖለቲካ መሰል ቧልት ይቧልታሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በሲኖዶስ ስብሰባ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሰነዘሩትን የሰላ ትችት ተከትለው "አድርባይ"፣ "የፓትርያርክ ጳውሎስ ተለጣፊ"፣ "የሚፈልጉትን ያላገኙ"፣ ወዘተ. እያሉ ሲነቅፉአቸው ነበር፡፡ ዕንቁ ግን ይህን የማኅበረ ቅዱሳን ኢሃይማኖታዊ ስራ ከማወደስ በቀር አልተቸም፡፡ እንዲያውም እንደጽድቅ ነው የቆጠረው፡፡ ለእነዚህ አባቶች ያልሆነ ስም ሰጥቶ መፈረጅና መሳደብስ በየትኛው መስፈርት ነው መንፈሳዊ ሊባል የሚችለው? ይህ ከመንፈሳዊው ይልቅ ለፖለቲካው ዓለም የቀረበ አሰራር ነው፡፡

የማኅበረ ቅዱሳኑ ዕንቁ ደጀሰላምን አሞግሶ አባ ሰላማ ብሎግን ቢተቸውም፣ ነጋድራስ ጋዜጣና ማራኪ መጽሔት ደግሞ የአባ ሰላማን በመረጃ ላይ የተመሠረተ ዜና ለንባብ አብቅተዋል። ዕንቁ መጽሔትን ቅር ቢያሰኘውም፡፡ ነጋድራስ ጋዜጣ አባ ሰላማ ብሎግን ጠቅሶ ዜና ሲሠራ ማራኪ መጽሔት ደግሞ "በሁለት ስልት የቀረቡት የማኅበረ ቅዱሳን የክስ መዝገቦች ይፋ ሆኑ" የሚለውን የአባ ሰላማ ዜና ከነአስተያየቶቹ በኅዳር 2004 ዓ.ም. ዕትሙ አውጥቶታል።

እነዚህ የፕሬስ ውጤቶች ሚዛናዊ ዜናዎችን ስላቀረቡ ሊበረታቱ ይገባል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን መሣሪያ አለመሆናቸውና በመረጃ ላይ ለተመሠረተ ዜና ትኩረት መስጠታቸው ይበል ያሰኛል፡፡ ይሁን እንጂ ማኅበረ ቅዱሳን ደግፈዉት ስላልጻፉና ከአባ ሰላማ ብሎግን በምንጭነት ጠቅሰው  ስለጻፉ በ"ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን" ልሳንነት እንዳይፈርጇቸው ያሰጋል፡፡

ይቆየን!

15 comments:

 1. Abaselam selam le enanete yihun betam tekami neger new eysawekachehun yalachut ayee mahebrekidusan hule besew Gereba endezorachehu andim ken yegna sera new belachehu alafinet atewesdum neger gin beyewhe meemen jerba poletikan tetekemalachehu ewentegna kersetyan kehonachehu manenetachehun geletsu ahunema yetegna sew yelem edeme leaba selama blog gudachehun eyawekin new be Germen endhi ayenet sera seteseru neber gin manem zim alalachehum yewahe yehonuten tikit meemenan yezachehu gedel gebachehu ahunem begelets yematenkesakesu kehone yetm atederesum abaselama ahunem beretu yensu were ayalikim ye erkus menfes hasab bewesetachew moletoal weladiteamelak tasebachew enante beretu

  ReplyDelete
 2. ማኅበረ ቅዱሳንን እናዉቃለን እንደግፋለን ደጋፊዎቹንም ይታወቃሉ ግራ የገባን የናንተ ጉዳይ ነዉ እነ ማን ናችሁ???
  ዓላማችሁ ምንድነዉ ብሎገችሁን ዓላማ ማለቴ ኣይደለም እሱን የሳታችሁት ስለ ሆነ በቅርቡ እንደምታሻሽሉት እንጠብቃለን።

  ReplyDelete
 3. god bless "ene begashaw"

  ReplyDelete
 4. nice nice and nice. besal sehuf new bertu

  ReplyDelete
 5. SELAM ABASELAMA EGZIABHER YETEBEKACHEHUU ENKU METSEHET EKO YE MK METSEHET NEW YEHE EKO YE TAWEKE NEW ENESU YEMIHEDUT WEST LEWEST NEWW KELAY ASTEYAYET YESTUT BELEWETAL BEBESTEJERBA NEW SERACHEW ENE BALEHUBET BE CANDAA SIBETEBETUN KALHUBET YALUT AGELEGAYOCH BEMETENAKER ASEWEGEDENACHEW ENANETE METENEKER ALEBACHEHUU BETEKERESTEYAN EWENETEGNA BEHONECH MENGED MEMERAT ALEBAT BE NECH LIBES TESHEFENO MEHED AYASEFELEGIM KEDEMO BEAMERICA YALU ABATOCHEN SEYASADEDU KOYU LEPOLETICA ENDIMECHACHEW SAYESAKALACHEW SIKER DEGEMO AHUN ABUNE PAWLOSN MESEDB JEMERU ERE LEMEHONU ENESU MANACHEW ?? KE WETADERENET; BE 40&50 EDEMEYACHEW DIYAKON KES EYEHONU AWAKI ENESU LIKAWENETU ALAWAKI HONEW BENEZHI WOROBELAWOCH YIWOREFALU GIZI YESTEN HULUN ENAYALEN BE ENTESELEMARIYAM BELEW TEMERW LEZHI YADERESUNIN ABATOCH MASADED SAWOLENET NEW ABASELAMWOCH EGZIABHER YEBAREKACHEHU KE C.A.N

  ReplyDelete
 6. ነጋ ድራስ እና ማራኪ የተሀድሶ ናቸው ማለት ነው?
  ማቅ= እንቁ
  ተሀድሶ= ነጋ ድራስ ማራኪ የሙሉ ወንጀል ልሳኖች

  ReplyDelete
 7. Wefefewoch! Your ideas are very confused. You tie enqu with MK b/c it print what other website post by the same saying we should blame the one who posts your menfeqena. However, you are saying that's not correct to blame negadras and maraki. Are you kidding me? Is your brain function or dead?

  ReplyDelete
 8. እነሱ በከፉ ስሕተቶች የተሞሉ መናፍቃን ሰው መናፍቅ ይላሉ

  አንድ ሐመር ለምሳሌ ያህል

  ቀደም ሲል በተጠቀሰው ሐመር የተባለው 7ኛ ዓመት ቁጥር 3 1991 ዓ/ም የማህበረ ቅዱሳን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሕትመት ውስጥ አንድ ነገር እጠቅሳለሁ ብየ ነበር አጋጣሚው ስለገረመኝ ነው ይህን ያልኩት በዚህ መጽሔት ውስጥ ስለ ማነፈፍቃን የጻፉትን ማስተካከያ እንዲህ ሲሉ ይሰጣሉ፡፡ ቀደም ሲል በሐመር 7ኛ ዓመት ቁጥር 2 1991 ዓ/ም ባስተማሩት የተሳሳተ ትምህርት ማስተካከያው እንዲህ ይላል፡፡ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ በሚለው አምድ ውስጥ ገጽ 31 6ኛ አንቀጽ // ነገር ግን አንድም ብሎ ከአተረጓጓም ህግ ውጭ ትርጉም የተረጎመ ብዙ ሐተታ አትቶ በቂ አስረጂ ያመጣ የተደበቀውን ያወጣ እንደሆነ መናፍቅ ይባላል/// ብለው ጽፈዋል አረምን ብለው መንፈቅ ሕዝቡን ካባሉና ስንቱን ሰው መናፍቅ ከደረጉ በኋላ ለእነሱ መናፍቅ ማለት እስከዚህ በጣም ቀላል ስለሆነ ሲያርሙት በጎደለ አእምሯቸው/// አንድም ብሎ ከአተረጓጓም ህጉ ውጭ ትርጉም የተረጎመ መናፍቅ ይባላል፡፡ ብለዋል፡፡ ለነጋዴው ለዘራፊው ለአሉባልተኛው ቡድን መናፍቅ ማለት የትርጉም ሕግ ያዛባ ነው፡፡ ስንት የትርጎም ህግ እንዳለ በትርጉም ህግና በትርጉም መካከል ያለውን ልዩነት የማያውቁ ያልተማሩ አስተማሪዎች ከሃይመኖት አንጸር ለእነሱ ማፍቅ ማለት ይህ ነው፡፡ በተግባር ያየነው ደግሞ ለእነሱ ማነፍቅ ማለት የእንሱ ቡድን አባል አለመሆን፣ መዎጮ አለማዋጣት፣ የእነሱም .... አለመደገፍ ነው፡፡ ልብ ይስጣቸው፡፡ ቀደም ሲል በተጠቀሰው ሐመር የተባለው 7ኛ ዓመት ቁጥር 3 1991 ዓ/ም የማህበረ ቅዱሳን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሕትመት ውስጥ አንድ ነገር እጠቅሳለሁ ብየ ነበር አጋጣሚው ስለገረመኝ ነው ይህን ያልኩት በዚህ መጽሔት ውስጥ ስለ ማነፈፍቃን የጻፉትን ማስተካከያ እንዲህ ሲሉ ይሰጣሉ፡፡ ቀደም ሲል በሐመር 7ኛ ዓመት ቁጥር 2 1991 ዓ/ም ባስተማሩት የተሳሳተ ትምህርት ማስተካከያው እንዲህ ይላል፡፡ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ በሚለው አምድ ውስጥ ገጽ 31 6ኛ አንቀጽ // ነገር ግን አንድም ብሎ ከአተረጓጓም ህግ ውጭ ትርጉም የተረጎመ ብዙ ሐተታ አትቶ በቂ አስረጂ ያመጣ የተደበቀውን ያወጣ እንደሆነ መናፍቅ ይባላል/// ብለው ጽፈዋል አረምን ብለው መንፈቅ ሕዝቡን ካባሉና ስንቱን ሰው መናፍቅ ከደረጉ በኋላ ለእነሱ መናፍቅ ማለት እስከዚህ በጣም ቀላል ስለሆነ ሲያርሙት በጎደለ አእምሯቸው/// አንድም ብሎ ከአተረጓጓም ህጉ ውጭ ትርጉም የተረጎመ መናፍቅ ይባላል፡፡ ብለዋል፡፡ ለነጋዴው ለዘራፊው ለአሉባልተኛው ቡድን መናፍቅ ማለት የትርጉም ሕግ ያዛባ ነው፡፡ ስንት የትርጎም ህግ እንዳለ በትርጉም ህግና በትርጉም መካከል ያለውን ልዩነት የማያውቁ ያልተማሩ አስተማሪዎች ከሃይመኖት አንጸር ለእነሱ ማፍቅ ማለት ይህ ነው፡፡ በተግባር ያየነው ደግሞ ለእነሱ ማነፍቅ ማለት የእንሱ ቡድን አባል አለመሆን፣ መዎጮ አለማዋጣት፣ የእነሱም .... አለመደገፍ ነው፡፡ ልብ ይስጣቸው፡፡


  የአባይነህ ካሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በጨረፍታ ሲዳሰስ

  አባይነህ ካሴ የተባለ የቀድሞ የቡድኑ አመራር ከሊቃውንት ገልብጦ በጻፈው ጽሑፍ ሲገለብጥ ተሳስቶ ይሁን ወይም በራሴ አብራራለሁ ሲል // የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ብሎ ባሳተመውና ብዙ በነገደበት መጽሐፍ የሚከተሉትን ጽፏል
  • ገጽ 124 // 2.4.2// ከየት እንዳመጣው አይታወቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግነት ይጠቀማል ብሎ ተናግሯል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ቅዱሳን የጻፉትን መጽሐፍ አጋናኝ ብሎ መሳደብ ምን ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አጋናኝ ካለ ገድላትንና ድርሳናትን፣ ተአምራትን ምን ሊላቸው ነው፡፡ ምሳሌው ደግሞ በገጽ 125 ከጩኸታቸው የተነሳ ምድር ተናወጠች የሚለው ተጋነነ አቀራረብ ነው እንጅ ምድር አልተናወጣችም ይለናል፡፡
  • በገጽ 217 ደግሞ ይባሰ ምን ይላል መሰላችሁ /// ነፍስ አትጾምም /// የሚጾም ስጋ ነው ዳዊት ነፍሴን በጾም አደከምኳት ሲል ስለ ስጋው ነውእንጅ ነፍስ አትጾምም ብሎ የክፋት ትርጎም ያስተምራል
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዳለ ገልብጦ ከጻፈው ምእራፍ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ትውፊት ሳይረዳና ምንጩን የማን እንደሆነ ሳይጠይቅ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው ብሉ አስከፊ ስህተትን ምናልባትም ከእነሱ ቡድን ውጭ መዋጮ የማይከፍል ወይም አብሮ የማይነግድ ነው ቢሳሳተው ኖሮ እስከ አሁን ተሐድሶ መናፍቅ ተብሎ ነበር፡፡
  ገና ይቀጥላል ይህ እንደው ገለጥ ገለጥ ተድርጎ በማየት የተገኘ ስህተት ነው፡፡ ሊቀውንት ቁጭ ብለው ቢመረምሩትማ ምን ያህል ስህተት ይገኝ ይሆን በእኛ አቅም እንኳ ይህን ያህል ከተገኘ፡፡
  ጎበዝ አሁን እንግዲህ // ዲን አባይነህ ካሴን // ምን እንበለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያጋናል፣ ነፍስ አትጦምም፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆን ነው ብሏል፡፡ እኛ እንደእነሱ ባለጌአይደለንም ሲኖዶስ ይፈረድበት፡፡
  አንድ አጭር መልእክት ትናንት የደረሰኝ አባይነህ ካሴ የተባለ የቀድሞ የቡድኑ አመራር ከሊቃውንት ገልብጦ በጻፈው ጽሑፍ ሲገለብጥ ተሳስቶ ይሁን ወይም በራሴ አብራራለሁ ሲል // የመጽፍ ቅዱስ ጥናት ብሎ ባሳተመውና ብዙ በነገደበት መጽሐፍ የሚከተሉትን ጽፏል
  • ገጽ 124 // 2.4.2// ከየት እንዳመጣው አይታወቅም መጽሐፍ ቅዱስ ግነት ይጠቀማል ብሎ ተናግሯል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ቅዱሳን የጻፉትን መጽሐፍ አጋናኝ ብሎ መሳደብ ምን ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን አጋናኝ ካለ ገድላትንና ድርሳናትን፣ ተአምራትን ምን ሊላቸው ነው፡፡ ምሳሌው ደግሞ በገጽ 125 ከጩኸታቸው የተነሳ ምድር ተናወጠች የሚለው ተጋነነ አቀራረብ ነው እንጅ ምድር አልተናወጣችም ይለናል፡፡
  • በገጽ 217 ደግሞ ይባሰ ምን ይላል መሰላችሁ /// ነፍስ አትጾምም /// የሚጾም ስጋ ነው ዳዊት ነፍሴን በጾም አደከምኳት ሲል ስለ ስጋው ነውእንጅ ነፍስ አትጾምም ብሎ የክፋት ትርጎም ያስተምራል
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዳለ ገልብጦ ከጻፈው ምእራፍ ላይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዋና ትውፊት ሳይረዳና ምንጩን የማን እንደሆነ ሳይጠይቅ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆኑ ፊሊጶስ ነው ብሉ አስከፊ ስህተትን ምናልባትም ከእነሱ ቡድን ውጭ መዋጮ የማይከፍል ወይም አብሮ የማይነግድ ነው ቢሳሳተው ኖሮ እስከ አሁን ተሐድሶ መናፍቅ ተብሎ ነበር፡፡
  ገና ይቀጥላል ይህ እንደው ገለጥ ገለጥ ተድርጎ በማየት የተገኘ ስህተት ነው፡፡ ሊቀውንት ቁጭ ብለው ቢመረምሩትማ ምን ያህል ስህተት ይገኝ ይሆን በእኛ አቅም እንኳ ይህን ያህል ከተገኘ፡፡
  ጎበዝ አሁን እንግዲህ // ዲን አባይነህ ካሴን // ምን እንበለው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያጋናል፣ ነፍስ አትጦምም፣ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባን ያጠመቀው ዲያቆን ነው ብሏል፡፡ እኛ እንደእነሱ ባለጌአይደለንም ሲኖዶስ ይፈረድበት፡፡

  ReplyDelete
 9. ሌባ ፖሊስን አይወድም ምክንያቱም እንዳይሰረቅ እድል ስለማይሰጠው፤ እንዲሁም ተሀድስዎች ማህበረ ቅዱሳንን አይውዱም ምክንያቱም ሰይጣናዊ ስራ ሲሰሩ ዝም እይላቸውምና፡፡

  ReplyDelete
 10. Mk false preacher stop yelling!!! You are zero qualification to say any thing about the church, but your longterm plan is clear to control poltics. The master leading of all nasty things that happened to our ancient church have created by Mk.

  ReplyDelete
 11. ሁለታችሁም እውነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንጻር ጻፉ እኛ እንደቀድሞ ሞኞች አይደለንም መጽሐፍ ቅዱስን አንብበን እየመረመርን እንደ ቤርያ ሰዎች ማለት እንችላለን እኮ!ግብረ ሐዋርያት 17:10-11 ሁል ጊዜ ደንቆሮ አታድርጉን ብዙ ነገር የምታስተምሩበትን ድኅረ ገጽ አታባክኑት ለሕዝባችንማህበረ ቅዱሳንም እውነት አለ ካሉን ይንገሩን የመንደር ወሬ በሃይማኖታችን ስምና በክርስትና ስም ይቁም!እንኳን እንቁ መጽሔት ሌላውንም ይጠቀሙበት የቻሉትን ሁሉ ይጠቀሙበት ከታሪክ የማይማር ሁሉ ዋጋውን ያገኛልና የሚያወናብዱን ሁሉ ራቁታቸውን የሚቀሩበት ጊዜ ቅርብ ነው!እግዚአብሔር ሕዝቡን አይተውም እንደዚህ እንደተሰቃየን ቅድስት ቤ/ክርስቲያናችንም የወንበዴዎች ዋሻ ሆና አትቀርም!ጅራፍ በቅርብ ጊዜ ይነሳል::እንኳን እኛ የምድሪቱ ክርስትና እንኳን እንደወርቅ ይጠራል!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 12. abaselawoche men yahele lmahbrqedusane seme etefiwoch yeseme lapisoche endhonachehu ytehedeso selbawoche enedehonachehu seltaweqebacheu sera batefetu teru newe mechem bihon ewenet selemiyashenefe ynanet qeraqenebo tsehufe syasasebem

  ReplyDelete
 13. lmenesetewe esetyaye aprove ymetadergutu enanet enmanachu yminkachu sihone letetewut ymiteqmacheu sihon lettelut newe blu enanetese yhene meche ezurachu tayalachu

  ReplyDelete
 14. Mahibre Kidusan is against protestant reformation while your objective is to establish Ethiopian Reformed Protestant Church. All members of EOTC including Deacon Begashew and his associates are against you. Because your preaching against the Dogama of EOTC.

  Gebre Maraiam

  ReplyDelete
 15. የማቅ ደጋፊ ወይም አባል፣ ለቤተ ክርስቲያን የምታስብ ከሆነ እስኪ የአባይነህን ስህተት አርም የተዋሕዶ ልጆች ገና የእናንተን ዝርፊያና መናፍቅነት ያጋልጣሉ አባይነህ በራሱ ጽሑፍ መረጃ
  1. መጽሐፍ ቅዱስ ያጋናል
  2. ነፍስ አትጾምም
  3. ኢትዮጵያዊውን ያጠመቀው ዲያቆኑ ነው ብሏል ምን ትላለህ

  ገና ሌላም ኑፋቄዎቻችሁ ይመጣሉ ምን ትሆናለህ

  ReplyDelete