Thursday, November 3, 2011

አንዳንድ ጳጳሳት የሚያወግዙ ሳይሆኑ የሚወገዙ መሆናቸው ተገለጠ - - - Read PDF

የቤተ ክርስቲያን ደጅ ረግጠው፣ ቀድሰውም ሆነ ሰብከው የማያውቁት፣ በአሁኑ የሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በአይናቸው ያለውን ግንድ ሳይመለከቱ በሰው አይን ያለውን ጉድፍ ላውጣ እያሉ ከሌሎች ግብር አበሮቻቸው ጋር ሲኖዶሱን ሲያውኩ የሰነበቱት አባ ሳሙኤል፣ የሚወገዙበት በርካታ ኑፋቄና የሥነ ምግባር ችግሮች ያሉባቸው መሆኑን ስለ እርሳቸው በቅርብ የሚያውቁ አንዳንዶች እየተናገሩና ማስረጃዎችንም ይፋ እያደረጉ ነው፡፡ በቅርበት የሚያውቋቸው የዋልድባ መነኮሳት አባ ሳሙኤል ዘጠኝ መለኮት የሚለውን ኑፋቄ የሚከተሉና የዚህ ትምህርት አቀንቃኝ መሆናቸውን በስፋት እየተናገሩ ሲሆን፣ ይህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም "ይነጋል" በተባለው መጽሐፍ ላይም የተጻፈ መሆኑ ይታወሳል፤ አባ ሳሙኤልን የጠየቃቸው አካል ስለ መኖሩ፣ እርሳቸውም የቀረበባቸውን ኑፋቄ ስለ ማስተባበላቸው የታወቀ ነገር ግን የለም፡፡ ይህ ጉዳይ በዋናው የሃይማኖት ትምህርት በምስጢረ ሥላሴ ላይ የቀረበ ኑፋቄ በመሆኑ፣ ማስረጃዎች ቀርበውና ጳጳሱ ተጠይቀው ውሳኔ ሊያገኙ ይገባል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ የሃይማኖታችንን መሠረት ንደው እያለ፣ አባ ሠረቀን ሃይማኖታዊ ኑፋቄ ባልሆነ እውነተኛ ትምህርት መክሰሳቸው ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

አባ ሳሙኤል ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከተነሡ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያን ደጅ ረግጠው አያውቁም፡፡  በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ግን ሌሎችን በማሳደምና ሤራ በመሸረብ ሥራ ተጠምደው ባለማስታጎል ዋና ተዋናይ ነው የሚሆኑት፡፡ ነገር ከመሥራት በቀር ሌላ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሙያ ስለ ሌላቸው፣ ቅዳሴ እንኳ በኢንተርኔት ካልተቀደሰ እያሉ በመንፈስ ሊከናወን የሚገባውን አምልኮተ እግዚአብሔር በኢንተርኔት ይከናወን ሲሉ አላዋቂነታቸውን መሸፈኛ የሚሆን ከንቱ ሐሳብ አቅርበው እንደ ነበር ይታወሳል፡፡

አባ ሚካኤልንና ወ/ሮ መሠረት ታደሰን በስውር ያጋቡት አባ ሳሙኤል፣ የአባ ሚካኤልን ሞት ተከትሎ ለወ/ሮ መሠረት ፍርድ ቤት የወሰነላቸውን የወራሽነት መብት ከምንም ባለመቁጠርና ከሕግ በላይ ለመሆን በማሰብ የሚደርሳቸውን ሀብት እንዳይወርሱ በማከላከል ላይ መሆናቸውን ወ/ሮ መሠረት ይናገራሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ብቻ የሚከናወነውን ምስጢረ ቁርባንን በቤታቸው በማዘጋጀትና እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት ተጾሞ ሊወሰድ የሚገባውን ቅዱስ ቁርባንን ከእራት በኋላ በመስጠት ሥርአተ ቤተ ክርስቲያንን ጥሰዋል፡፡ አባ ሳሙኤል በመኖሪያ ቤታቸው ባዘጋጁትና ማንም ቄስ ካዘጋጀው ጳጳስ ያዘጋጀው ይበልጣል በሚል ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ ቁርባን በቤታቸው አዘጋጅተው የተድበለበለ ነገር አጎረሱኝ የሚሉት የአባ ሚካኤል ባለቤት ከእራት በኋላ ቁርባን እንዴት ይቻላል ብለው ላቀረቡላቸው ጥያቄ አባ ሳሙኤል ሲመልሱ፣ “ጌታ እኮ ራት ከበሉ በኋላ ነው ለሐዋርያት ቁርባንን የሰጣቸው፣ ጳጳሳትም ራት ከበሉ በኋላ መቁረብ ይችላሉ” እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡ “ታዲያ እኔ መቼ ጳጳስ ነኝ” ብለው ሌላ ጥያቄ ሲያነሡም፣ “ጳጳስ አግብተሽ አይደለም እንዴ! ትችያለሽ” አሉኝ ይላሉ፡፡ “አሁን ታዲያ መሽቷል፤ የትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው የምቆርበው” ሲሏቸውም፣ “ማንም ቄስ ካጨማለቀው ጳጳስ ያዘጋጀው ይሻላል” በማለት መመለሳቸውን ወይዘሮዋ ይናገራሉ፡፡

ብፁዕ አቡነ ሚካኤልም “ይኸው እኔን አላመንሽኝም እንጂ ጳጳስ እንደሚያገባ የተማሩ ጳጳሳት ሁሉ ያውቁታል፡፡ ብፁዕነታቸው አቡነ ሳሙኤልም ባለትዳር ጳጳስ ናቸው” አሉኝ፣ ሲሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ በጻፉት ደብዳቤ ውስጥ ተናግረዋል፡፡ ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ድረስ ከአባ ሚካኤል ጋር በትዳር መኖራቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ መሠረት፣ "በነሐሴ 2000 ዓ.ም. ላይ ፀነስኩ፤ የ3 ወር እርጉዝ ሳለሁኝ ባለቤቴ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ክብሬ እንዳይነካና ስሜ እንዳይጠፋ በሚል ፅንሱን እንዳስወርድ አዘዙኝና 4 ኪሎ በሚገኘው በርጌስ በተባለ ክሊኒክ ጥቅምት 6 የውርጃ መርፌ ከተወጋሁ በኋላ ጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ.ም. ውርጃው ተፈጸመ፡፡" ይላሉ፡፡ የሐኪም ማስረጃም እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ወ/ሮ መሠረት ጉዳዩን በቀን 2/2/2004 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ እና በግልባጭም ለተለያዩ የመንግሥት አካላት ያመለከቱ ቢሆንም በጊዜው የተሰበሰቡትና ከዚህ ነገር ነጻ ያልሆኑት አንዳንድ ጳጳሳት ሐሰት ነው በሚል ጉዳዩ ለውይይት እንዳይቀርብና ታፍኖ እንዲቀር እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል፡፡ እንደዚህ ያሉትና በሚያስወግዝ ኑፋቄና የስነምግባር ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ሌሎችን የማውገዝ ብቃቱም ሆነ ሞራሉም እንደሌላቸው የሚታወቅ ቢሆንም፣ ከስርአት ወጪ እናወግዛለን ቢሉ፣ ውግዘታቸው "ወፈ ገዝት" ከመሆን እንደማይዘል፣ ፍጹም ተቀባይነት እንደማይኖረውና መብታቸው የሚነካ ሰዎችም ጉዳዩን ወደ ሕግ እንደሚወስዱት እየተነገረ ነው፡፡

ይህ በቤተ ክርስቲያን ስርአት ውስጥ የሌለና አባ ሳሙኤልና መሰሎቻቸው በስውር እያከናወኑት ያለው የጳጳሳት ጋብቻና የቤት ውስጥ ቁርባን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠውና ቤተ ክርስቲያን የወንበዴዎች ዋሻ ከመሆኗ በፊት ሲኖዶሱ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ እንዲህ ያለ ኑፋቄና ምግባረ ብልሹነት ውስጥ ተዘፍቀው ያሉ አንዳንድ ጳጳሳት፣ ይህን አንገብጋቢ የቤተ ክርስቲያን ችግር ወደ ጎን በመተውና አቅጣጫ ለማስለወጥ በመሞከር፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተላላኪ ሆነው ተሐድሶ የተባሉ ወገኖችን ካላወገዝን ወደ ሀገረ ስብከታችን አንመለስም እያሉ ያሉት፣ ብርሃንን ስለሚጠሉና ክፉ ሥራቸው በወንጌል ብርሃን እንዳይገለጥ ስለሚፈልጉ እንደ ሆነ ግልጽ ነው፡፡ "ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደ ሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል" (ዮሐ. 3፡20-21) እንዲል ቅዱስ ወንጌል፡፡


የወ/ሮ መሠረት ታደሰና የአባ ሚካኤል ልጅ የዮሐንስ የወራሽነት ማስረጃ እና ወ/ሮ መሠረት ለቅዱስ ሲኖዶስ የጻፉት ደብዳቤ ደርሶናል፡፡ የቀጣዮቹንም ጳጳሳት መረጃዎች በቀጣይ እንለቃለን፡፡
ይቀጥላል፡፡

32 comments:

 1. GUD BEL GONDER YILEHAL YEHEN NEW.

  ReplyDelete
 2. Tadiya manew menafeke rat abeleto bemesete yimiyakorebe papase wes ma? mk do u have the answer. maferiyawoche.

  ReplyDelete
 3. Capital shame for Abune Samuael and his friends. Till today ,I didn’t believe your blog but now I confess. Regarding to this topic I was seriously following to one comment giver, the so-called ‘Zewde zearat killo’ who was fearfully trying to share some secrets in different topics. I didn't beileve him but now since it is affirmed by your evidence he seems true.


  Zewde ze-arat kilo said...
  Aba selama?
  I have enough concret documents including eye witnesses concerning the evil faces of MK (its leaders), and some carnal bishops. However, still I am waiting untill my patience is ended up for the fact that thinking to the betterment of the church.
  eg. if you want to get additional evidence about Abune Samuael's 'gemena', I lead you to approach the house servant of Abune Michael; she was in Addis Ababa and so as to keep the secrecy for their evil life ,the bishop took her to shire. There, the big drama was also continued.
  If you understand me, my focus is not on the departed bishop as he is already left us but on Abune Samueal whose full darkened history (evidence) is available to the house servant.
  October 29, 2011 9:28 PM

  zewde ze-arat kilo said...
  ምንኩስናን አጥብቆ ከሚቃወሙ አንዱ እኔ ነኝ ግን ራሱ “ግሎባላይዜሽን” በሒደት እያስቀረው ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ጊዜ ባይጠፋበት መልካም ነው እላለሁ።
  መረጃ አግንተናል ስላላችሁት ጉዳይ ደግሞ ከኔ ጀምሮ በየቤቱ ያለው ቢቆጠር ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለዓለም በሙሉ አሳዛኝ ታሪክ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ስለዚህ “እንደራበህ አይበላም እንደተናደድክም አይነገርም” እንደተባለው ሁሉ መቸኮሉ ብዙሐንን ይዞ ሊሄድ ስለሚችል መታገሱ ይመረጣል። እኔም’ኮ ስለ ማሕበረ ቅዱሳንና ስለ አንዳንድ ጳጳሳት ገመናችውን የሚገልጹ ሕጋዊ መረጃዎች አሉኝ ነገርግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ብዬ ስለማምን እስካሁን ድረሰ ለመልቀቅ በፈራ ተባ እኖራለሁ።
  November 1, 2011 4:07 AM

  zewde ze-arat kilo said...
  አባ ሰላማ?
  በአባ ሳሙኤል ተንኮል ጠንሳሽነት ይህ ጉደኛ የሰይጣን ማሕበር የያዝኩት የገመና ዶክሜንት በጭብጥ ስለሚያውቅ ወደአደባባይ ያወጣዋል ብሎ በመፍራት እኔ ከሚሰራበት መስራቤት ተመሻጥሮ ለግማሽ ዓመት ሰርተህ እንድትመጣ በማለት ኢንተርኔት ወደሌለበት ሲዳማ ገጠር እንደመደቡኝ ትናንት ደብዳቤ ደርሶኛል። እና ማሕበሩ የትም ብሔድ መፋናፈኛ አሳጠዋለሁ’ንጂ የውድመት ዓላማ ይዞ አይቀጥልም። እናንተም የጀመራችሁት ፕሮጀክት ቤተ ክርስቲያናችን የተሸከመችው አደገኛ ቆሌ በሒደት ከሥሩ ለመንቀል ስለሆነ ምንም ቢደርስባችሁም ሳትሰለቹ ከግብ እንድትደርሱ አስተያየት ሲሰጥ እኔም ዘወትር ከጎናችሁ ሆኜ የተቻለኝን ያህል ለማድረግ በእግርም ቢሆን ተጉዤ አልፎ አልፎ ለብሎጋችሁ ሪፖርት ማድረጌ አይቀርም።
  የመጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ በርቱ።
  November 2, 2011 8:52 PM

  ReplyDelete
 4. ኣባ ሰላማዎች እንግዲህ ምን ይደረግ ቸግሮአችሁ ኣይደል ይህ ሁሉ የዚያ ንጹሕ መነኩሴ የአባ ሠረቀ ግፍ እና የማህበረ ርኩሳን እኩይ ተግባር ያመጣው ጣጣ ነው። እንደምንም ብለን ቤተ ክርስቲያንን ከመነኮሳት አስተዳደርና ከማህብረ ርኩሳን ማውጣት አለብን።እናንተም በርቱ ጠንክሩ።

  ReplyDelete
 5. OMG! what is going on?

  ReplyDelete
 6. It is shame. We know that MQ protect and work with such individuals. They support MQ to hidden their shame, but it is time to uncover their unfathful doings.

  ReplyDelete
 7. ሳሙኤል ምነው? እግዚአብሔር ምስክር በሆነበት ጋብቻ የሰራኸውን ትክዳለህ? ጋብቻ እኮ ክቡር እንጂ ርኩስ አይደለም። ደግሞም አንተ እንዳልከው ጳጳስም እንዲያገባ ተፈቅዷል፤ ታዲያ መሠረት ለ11 ዓመታት ስታስኮመኩም ኖረህ ዛሬ ትሸመጥጣለህ? እግዚአብሔር ይፍረድብህ?

  ReplyDelete
 8. አባ ሰላማ የዚያ ንጹሕ መነኩሴ የአባ ሠረቀ ብሎግ ነው እንዴ? ሃ….ሃ……ሃ……ሃ….ሃ…..

  ReplyDelete
 9. In the Name of the Father, and of the the Son and the Holy Spirit. Amen

  Canon V of the Canons of the Twelve Apostles (Apostolic Canons):Let not a bishop, presbyter, or deacon, put away his wife under pretence of religion; but if he put her away, let him be excommunicated; and if he persists, let him be deposed.


  “Serve the Lord with fear, and rejoice in Him with trembling.” Ps. 2:11
  “bearing with one another and, if one has a complaint against another, forgiving each other; as the Lord has forgiven you, so you also must forgive.” col.3:13

  People who grow up with low self-esteem, self- arrogance often find it difficult to apologize, to ask forgiveness and to let it go . To them, an apology or asking forgiveness seems to be a sign of weakness. In reality, apologizing enhances one's self-esteem.

  People respect the man or woman who is willing to take responsibility for their own failures. Receiving the respect and admiration of others thus enhances how we feel about ourselves.

  On the other hand, those who try to hide or excuse wrongful behavior will almost always lose the respect and affirmation of others.
  A sincere apology is always a sign of maturity, understanding of the Gospel but not a sign of weakness. Admitting we have a problem is the first step of healing our self and others. So, Apology opens the door to forgiveness. And forgiveness means that we can now continue to grow in our relationship with God and the people we apologized. It's never too late to learn to apologize.. I feel like there is a family crisis among the bishops. Let us stop the pain and forgive each other. Let us keep the holiness of the sacraments.
  God accepts fallen man, however, for he was ransomed not “with silver or gold, but with the precious blood of Christ” (peter 1:18-19)

  O God, be merciful to me, a sinner.
  I remain,
  abba

  ReplyDelete
 10. እነገብርኤል፤ ኤልያስ፤ ሳሙኤል፤ ሳዊሮስ። አብርሃም፤ ዲዮስቆሮስ፤ እስጢፋኖስ፤ ጳውሎስ፤ ወዘተ ወዘተ ሁሉም ቆንጆ እየመረጡ ድራሹን የሚያጠፉ ኮርማዎች መሆናቸው የታወቀ ነው። አባ ወይም አቡነ ያላልኳቸው
  በማቴ23፥9
  አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ የሚል ሕያው ቃል ስላለ ነው። እነዚህ በጥቁር ቀሚስ ጥቁር ገበናቸውን የከለሉ አጭበርባሪዎች በግል መኖሪያ ቤታቸው ቅምጥ እንዳላቸው፤ ግማሾቹም የልጆች አባቶች መሆናቸው ይታወቃል። አንድ ጊዜ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው መነኩሴ ከአንድ ሴት ጋር ሲንጎዳጎድ ተንኮለኞች የደብረ----ዲያቆናት አድፍጠው እጅ ከፍንጅ ይይዙታል። ተከሶ ከጳጳሳት ዘንድ ይቀርብና ምን የተባለ ይመስላችኋል፤« አንተም አበዛኸው፤ ይህንን ያህል እጅ ከፍንጅ እስክትያዝ አለመጠንቀቅህ» አሉትና እርፍ። ምን ማለታቸው መሰላችሁ፤ ይህ ጅል ሕዝብ ምንም ስለማይገባው ላለመታወቅ በተቻለህ ከመሞከር በቀር ነገሩንስ ካገኘህ በለው! ማለታቸው ነው።
  አሁን የሚያስፈልገው ነገር የመንግስት ድጋፍ ነው። ሕዝብን የሚያታልሉና የሚበጠብጡ ቀሚስ ለባሾች ቦታ ቦታቸውን እንዲይዙ ማድረግ! ወይ ሚስቶቻቸውን አለበለዚያም ቢጸድቁም ባይጸድቁም የራሳቸው ጉዳይ ወደመነኮሱበት ገዳም እንዲሄዱ ያድርግልን።የሱር ታክስ፤ የስራ ግብር የማይከፍሉ ሽፍቶችን ወደሕግ ማዕቀፍ ማስገባት አለበት። ምእመናንም እነዚህ እንኳን የሰውን የራሳቸውም ኃጢአት የገማ ሰዎችን «ይፍቱኝ» እያለ ጊዜውን አያባክን። ማንም መፍታት አይችልም። ይፍቱን ሳይሆን ኃጢአትን የሚደመስሰው ንስሐ ብቻ ነው። ከዚያም ባሻገር እግዚአብሔር ባልከበረበትና ቅዱስ መቅደሱ በተበላሸበት መንፈስ ቅዱስ ስለማይኖር ዋጋ አገኝበታለሁ፤ ብለህ ገንዘብህን ለሌቦችና ለዱርዬዎች አትበትን። ይልቁንም ብራብ አብልታችሁናል፤ ብታረዝ አልብሳችሁኛል፤ ብታመም ጠይቃችሁኛል፤ የአባቴ ቡሩካን ኑ በቀኜ ቁሙ የሚላችሁ ገንዘባችሁን ለሌቦች ጳጳሳትን መነኮሳት ስለሰጣችሁ ሳይሆን ምንም ለሌለው ደሃ፤ በየጎዳናው ረግጣችሁ የምታልፉት ድሃና ለማኝ፤ ወላጅና ጣሪ የሌላቸውን አረጋውያን መርዳት ስትችሉ ብቻ ነው የአባቴ ቡሩካን የምትባሉት። እኔ ሌቦች በእግዚአብሔር ስም ባሰሩት በዚያ የብር ምስጥ በሆነ ሳጥን ውስጥ ጨምሬ አላውቅም። ነፍሰገዳዮችና ቀማኞችም እግዚአብሔርን ያውቁታል፤ ስሙን ስለጠሩ ቅዱሳን ናቸው አይደለም። እንደዚሁ ሁሉ ገንዘባችሁን ለቸገረው እንጂ ህንጻ ለውሽሞቻቸው ለሚሰሩት አትስጡ።
  የመነኮሳት፤ የጳጳሳት እንዲሁም ይህንን የሽርሙጥና ግብራቸውን እያወቀ ለርሱ እስከተመቹት ድረስ ሰይጣን ነኝ ቢሉም የማይናገራቸው የምግባር ወንድማቸው ማኅበረ ቅዱሳን ዘመን እያበቃ ነው። ሰው ሁሉ እየሰማ፤ እያነበበ፤ እየተጠራጠረና ይህም አለእንዴ ለካ እያለ ነው ያለው። አሁን በየጎዳናውና በየስፍራው ለነዚህ ቀሚስ ለባሾች ንቀትና ጥላቻ እያደገ በተግባርም እየተገለጸ ነው። ወደፊት ደግሞ ይጥፉልን የሚባልበት የተቃውሞ ጊዜ ቅርብ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ነጠላ ውስጥ መሸፋፈኑ አብቅቷል፤ ገመናው ተገልጧል። ቤተክርስቲያናችን ሐዋርያዊ መሰረት ያላት፤ ምስጢረ ሥላሴንና ምስጢረ ሥጋዌን አምልታና አስፍታ የምታስተምር፤ ጥንታዊት እንደሆነች መቀጠል የምትችለው ቆሻሻዎችና ጉድፎች ከመቅደሷ ወመውጣት ሲችሉ ብቻ ነው። ነገሮች እየተለወጡ ናቸው፤ ያልተለወጠው የኃጢአት መሪዎች ግብር ብቻ ነው። የሰላማ ከሳቴ ብርሃን ወንጌል ዳግም ይነግሳል! እግዚአብሔርን የሚፈሩ ቅዱሳን ዳግም ይፈጠራሉ! እግዚአብሔርን የሚታዘዝ ትውልድ ይመጣል!!! ይህንን ለቤቱ የማያንቀላፋ አምላክ እውን ያደርገዋል! አቤቱ ይህንን ትንሣዔ አሳየን፤ አሜን።

  ReplyDelete
 11. Shame! Shame!Shame! lord Jesus! please clean our church. Either any one can tell us the root cause of all the problems in our church other than mine. my finding is our church is not bible based and does not accept the holly ghost. our church is responsible for all the damage happened on the country famine and drought. we have luck of God faith. The most highly God will clean all those messes. This is the start let us talk and discuss, Aba paoulos should take a big measure before he is going to God to be with him, He can only be with him , if and only if clean the church messes.

  ReplyDelete
 12. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!
  ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቸ : ዛሬ አንድ ቀጥተኛ ጥያቄ ልጠይቃችሁ እና እስኪ መልሱልኝ:: እስካሁን በዌብሳይቶቻችን የሚጻፈውንና የሚነገረውን እየሰማሁ ነው:: ታዲያ አንድ ጥያቄ ግን አለኝ ያልተመለሰ:: የምችለውን ያክል ጥረት አደረግሁ እንደሚወራው እኔም ለመሆን ግን ትክክለኛ መረጃ ልቤ ፈለገ:: ጥያቄየ በእነ በጋሻውና በግብረአበሮቹ ላይ ነው::
  እኔ እንደተረዳሁት:
  1. በጋሻው ስድብ ይችላል:: የፈለገውን ነገር በድፍረት ይናገራል:: የቤተ ክርስቲያን አባቶች ዓይነት ያነጋገር ለዛ ይጎድለዋል:: ግን መናፍቅ ያስባለው ነገር ምንድ ነው? መናፍቅ ለማለት እኮ ኑፋቄ ሲናገር መስማት አለብን:: ስላሴ አትበሉ ያለውን ስብከት አድምጨዋለሁ:: በእርግጥ ይህን ተመልክቶ በጋሻው መናፍቅ ነው ያለ ሰው ንስሃ ይግባ:: ሰውን በበደሉ መክሰው ተገቢ ነው ያለበደሉ መናገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ከተጠያቂነት አያስመልጥም:: በብሉይ ኪዳን ኢየሱስ እንዲህ አደረገ እንደማንለው ሁሉ በሃዲስ ኪዳን ጌታ በስጋው ወራት ያደረገውንም ስላሴ እንዲህ አደረጉ ማለት ለአረዳድ የሚያመች አይደለም:: እዚህ ላይ እንደተረዳነው መጠን እንጂ ልጁ ኑፋቄ ነው ያስተላለፈው የሚል ሰው ቢያስብበት እላለሁ:: አሁንም ግን ኑፋቄውን ማድመጥ እፈልጋለሁ:: በትክክል ለማመን እንዲያስችለኝ::
  2. አባ ፋኑኤልንም እንዲሁ እንደተመለከትኋቸው ሰውየው ሃይለኝነት ይታይባቸዋል:: ከሌላኛው ወገን ተቃውሞ ስለደረሰባቸው ከነበጋሻው ጋር ወግነዋል:: ታዲያ መናፍቁ ጳጳስ ለማለት ያስበቃን ነገር ምን ይሆን? ምን ብለው ኑፋቄ አስተማሩ እስኪ ስሞት ጥቀሱልኝ::
  3. የምንወዳቸው ዘማሪያን አሸናፊ ምርትነሽ ትዝታውና ቅድስትስ ኑፋቄቸው ምን ላይ ይኆን እባካችሁ እስኪ ተናገሩና እንስማ:: ኑፋቄቸውን ሳናውቅ መናፍቅ ማለት ይከብዳል:: ማናት ዘማሪት ዘርፌ ወደ አሜሪካ ስላቀናች ድምጽዋ ቢጠፋም: እርስዋስ ለምን ቀረች ወይስ እርስዋ የለችበትም::

  እንደ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ሲደርስ ማየት አልፈልግም:: ኑፋቄ ያለበት ሰው ቤተ ክርስቲያንን ሲቆጣጠር ማየት አሳፋሪና አስጠይ ነገር ነው:: ሆኖም ግን ቤተ ክርስቲያንን ለመጥቀም ብለን ሰዎችን አንጉዳ:: በጋሻው ሃይለኛ ንግግሩ እንጂ ኑፋቄው አልታይ ያለኝ እውነት ፈላጊው ኦርቶዶክሳዊ የተዋህዶ ልጅ ነኝ::

  ReplyDelete
 13. አቡነ ፋኑኤል በሰላም ይምጡልንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያኖች ሁሉ አንድነት ይኖረናል።
  አባ ሰረቀም ወደዚህ ቢመጡልን በጣም ደስ ይለናል። በጣም ከተወሰኑ የቤተክርስቲያን ጠላቶችና ከማህበረ ቅዱሳን
  ነን ባዮች በቀር። ምክንያቱም የማህበሩን ማንነት ጠንቅቀው ስላውቁባቸው በጣም ይጠሉአቸዋል። የተለያየ የሀሰት
  ስምም በመስጠት ከምዕመናኑ ጋር እንዳይግባቡ ለማድረግ በጣም ይጥራሉ፡ ነገር ግን የእያንዳንዳችንን የስውር ደባና
  ጥላቻ የተሞላውን ልባችንን ስለሚያውቅ እግዚአብሔር እውነተኞችን እየተመለከተ ነገሮችን በማስተካከል ላይ ነውና
  በአምላካችን እንታመናለን። - ያመንነውን አውቀናል የቆምንበትን አለት፤ ፅኑ ነው መሠረቱ የታመነ ነው ከጥንቱ።

  ሰለስቱ ደቂቅን ከነደደ እሳት ያወጣ አምላካችን ዛሬም ሁሌም ከኛ ጋር ነው። ሰለሰቱ ደቂቃን እንዳሉት ደግሞ አምላካችን የራሱ ሰዓት አለውና ከዚህ ከነደደ እሳት ባያወጣን እንኩአን ንጉሱ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም እንዳሉት ሁሉ
  እኛም የምንፈልገው ጥራት እንጂ ብዛት አይደለም። የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው እንዳለ አምላካችን ፡ እንደዚሁ ከምርጦቹ እንድንሆን ሰለምንፈልግ የማህበረ ቅዱሳን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጥሪ ተቃዋሚዎችን ቢያበዛምእኛ ግን እንዳልኩት ጥራት እንጂ ብዛት እንፈልግም። እውነትና ንጋት እያደር የገለጣል።

  በተለያየ መንገድ ማህበሩ ንፁሃን የሆኑትን ነገር ግን የማህበሩን ድብቅ አላማና ሐሰቱን ለሚገልጡበት ሁሉ በተቻለው
  መጠን ተሃድሶ እያለ የታውቁትን የቤተክርስቲያናችንን ሊቃውንቶች፣ ሰባኪዎችና ዘማሪያንን ለምዕመናን ለማስጠላት
  ያለ የሌለውን ኃይል እያስተባበረ የሙት ሙቱን ቢጣጣርም በጣም ብዙ ምዕመናን ግን አሁን እውነቱን እየተረዱ
  ሰለመጡ ይህ ማህበር ፀረ ክርስትና መሆኑ ታውቁአል።

  አባ ሠረቀ፣ እጅግ በጣም እንወድዎታለን፣ እንከበርዎታለን እግዚአበሔርም እንደዚሁ፤ ሰለዚህ እይዞዎት የእግዚአብሔር ልጅ የሆንን ሁሉ ከጎንዎት ነን፣ ከሰይጣን ኃይል የእግዚአብሔር ኃይል ይበልጣል።

  አምላካችን በቅዱሳን መላዕክቱ ይጠብቃችሁ ። አሜን።

  ReplyDelete
 14. ማ/ቅ የምትቀባጥሩትን የጳጳሳት ጉዳይ እናንተ እንደምትሉት የሚደግፍ አይመስለኝም:: የግለሰቦችን ኃጥያት የሚመረምር እግዚአብሔር ነው:: ሁሉም የራሱ ይኖረዋልና:: ነገር ግን ሰዎቹ አለባቸው የምትሉትን ኃጥያት ለሚመለከተው ማቅረብ ነው እንጅ የማ/ቅ ስም ከነሱ ኃጥያት ጋ ለማቀባባት የምትሞክሩት ምን ያህል እንደምትጠሏቸው ግልጥ ያለ መረጃ ነው:: ጥላቻችሁ ደግሞ ስለኃጥያት ሳይሆን በጸረ ማርያምነታችሁ ስላሰደዷችሁ እንደሆነ ከሌሎቹ ጽሁፎቻችሁ መረዳት ይቻላል:: ጸረ ማርያሞች አታወናብዱ!

  ReplyDelete
 15. አይ እጅጋየሁ; ኤልዛቤል አንቺም አባ ጳውሎስ ሲጭሩ ልትከሺ ነው ማለት ነው? በኃላ እነ አቡነ ሳሙኤል አንቺንም አንዳይከለክሉሽ ጋብቻሽን በማዘጋጃ ቤት አድርጊው:: መቸም አንቺ ልትወልጂም ሆነ ልታስወርጂ አርጠሻልና ፎርጅድ ብታሰሪም የሚያምንሽ የለም:: ለፎርጅድ አንቺ: ሰረቀ እና ይህ የምንፍቅና ጣቢያችሁ አትቻሉም:: መጀመሪያ የራስሽን ጉድ ሽፍኝ:: ማፈሪያ::

  ReplyDelete
 16. @Anonymous
  November 4, 2011 12:29 PM

  ስላሴ እንዲህ አደረጉ ማለት ለአረዳድ የሚያመች አይደለም


  ስላሴ የሚለው ብቻ ነው የተሰማህ ማለት ነው? እግዚአብሔር አትበሉ ያለውስ::
  እግዚአብሔርም በሐዲስ ኪዳን የለም ማለት ነው? በነገራችን ላይ የስላሴም ምስጢር የተገለጠው በሐዲስ ኪዳን ነው:: አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ:: አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? እግዚአብሔር ነው:: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው:: ሰውየው ያለው ስላሴ አትበሉ እግዚአብሔር አትበሉ ኢየሱስ በሉ ነው::
  ካልሰማህ ድጋሚ ስማው:: ያለው ትክክል ነው ልዩነት አላቸው አንድ ነኝ ከሱ ጋር ካልክ ሌላ ነገር ነው:: አላለም ማለት ግን ጆሮህን እንድትመረምር ያስመክርሃል:: አባ ፋኑኤል እሱን መደገፋቸው ያስጠይቃቸዋል::

  ReplyDelete
 17. here we go again. it is coming back to them.

  "Who are you to judge the life I live? I know I'm not perfect and I don't live to be, but before you start pointing fingers make sure your hands are clean."

  Bob Marley

  ReplyDelete
 18. ብፁዕ አቡነ ሚካኤልም “ይኸው እኔን አላመንሽኝም እንጂ ጳጳስ እንደሚያገባ የተማሩ ጳጳሳት ሁሉ ያውቁታል፡፡ ብፁዕነታቸው አቡነ ሳሙኤልም ባለትዳር ጳጳስ ናቸው” how is this related to our church? who is doing this work? may be they know all about the Coptic Orthodox Synaxarian records. hmmmmm

  "The Coptic Orthodox Synaxarian records one of
  the early Patriarchs of the Church of Alexandria as being a married man. The record states he had lived a celibate life since the beginning of marriage and it is not known whether this is a later redaction to cover the obvious conflict that would ensue otherwise. In any case, the fact of his enthronement again confirms that the tradition of the Church at that time did not consider marriage to be a bar to even hold the highest office of the Orthodox Church."

  Wow!

  ReplyDelete
 19. Just for FYI

  I found this from the liberay.. is this lead them to get merried? NOTE, this was happen to protect the church from accusation and shortege of celibate..(monk Priest)

  "The Byzantine Church
  In 1990, an article from The Orthodox Observer, a Greek Orthodox Archdiocese of North and South America publication, states, At the 1992 meeting of the clergy-laity conference of the Greek Orthodox Archdiocese of North and South America (Archbishop Iacovos), held in New Orleans, a formal resolution was sent to the Ecumenical Patriarchate in Constantinople 'to consider returning to the practice of ordaining married priests as bishops as was done in the early church.' ... Earlier in December 1991, the Greek Archdiocese stated that it was the original practice of the Church for a married Episcopate. Please also note that Archbishop Iakovos promoted the return of married bishops to worldwide Orthodoxy and agreed that individual jurisdictions could retain the Apostolic tradition of the Early Church."

  ReplyDelete
 20. «የአይጥ ምስክር ድንቢጥ» አንዲሉ ማቅ(የሀዘን ልብስ) የኃጢአተኞች ጳጳሳት ደጋፊ አይደለም ሲል ለመከራከር የሞከርከው ሰው፤ አንድ ነገር ልንገርህ ማቅ የሚደግፉትን ጳጳሳት ምንም ይሁኑ ምንም አለኝታዎቼ ሲላቸው አሰራርህ ትክክል አይደለም የሚሉትን ደግሞ ተሃድሶ ይላቸዋል። ለምሳሌ ሳሙኤል ባለትዳር ነው፤ አብርሃም፤ ዲዮስቆሮስ የለየላቸው ናቸው፤ እስጢፋኖስ ባለጎጆ ነው። እነዚህን ግን ትንፍሽ ሳይል ፋኑኤል ላይ ይዘምታል፤ ምክንያቱ ልጄ ወዳጄ አንተ ማኅበር ስላላለው ብቻ ነው። ነገ በሆነ ሽምግልና ይሁን የጫወታ መንገድ ቢስማሙ በእውነት እኒህን የመሰሉ አባት እያለ ሲያቆላምጥ ይገኛል። ማኅበሩ ራሱ አገባሻለሁ፤ ከድቼሻለሁ፤ ትቼሻለሁ በተባሉ መበለታትና የመበለታት ቀማሾች የተሞላ ነው። ማቅ የቤተክርስቲያን ጥቁር የሀዘን ልብስ ነው እንደስሙ። እምነት ሳይሆን ባህል የሚያመልክ የብልጦችና የጅሎች ስብስብ ነው። ብልጦቹ ገንዘብ የሚገኝበት መሆኑን አሳምረው ያውቃሉ፤ እየሰሩ ያሉት ትክክል አለመሆኑም ቢያውቁም በጥቃቅንና አነስተኛ ከመደራጀት ይህ ሃይማኖትን ከለላ ያደረገ ግብርና ታክስ የሌለው ተቋም ይሻላቸዋልና አመራራቸውን በጥበብ ይመሩታል። ጅሎቹ ሴቶችና ወጣት ወንዶች ገንዘባቸውን እየገፈገፉ፤ነጠላቸውን መስቀለኛ አጣፍተው ከበሮ ሲደልቁና ማቅ ቅዱሱ እያሉ ዋናዋን ቤተክርስቲያን ለማቅ የማትመች ደካማና የተሃድሶ መፈልፈያ ሲሏት ይውላሉ። እንግዲህ ማቅ ማለት ይህን ነው። ልጆቿ አልቀው የተረፋት ጥቁር የሀዘን ልብስ፤ማቅ!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 21. 'ኣባ ሰላማዎች እንግዲህ ምን ይደረግ ቸግሮአችሁ ኣይደል ይህ ሁሉ የዚያ ንጹሕ መነኩሴ የአባ ሠረቀ ግፍ እና የማህበረ ርኩሳን እኩይ ተግባር ያመጣው ጣጣ ነው። እንደምንም ብለን ቤተ ክርስቲያንን ከመነኮሳት አስተዳደርና ከማህብረ ርኩሳን ማውጣት አለብን።እናንተም በርቱ ጠንክሩ። '

  satna'el hulem be KIDDISTITU TEWAHEDO LAY YIFOKIRAL; DIABILOS TEWAGA , KESTUN ARAGEFE, BETEKIRISTIANIN GIN AL-WEGGATIM; AYWEGATIMIM!!!
  Ye tallaku zendo ye sidib andebet ke minim gizze belay aba selaman andebet adirgo ye sidibun dof biyawerdim yetewahedo lijoch ayinnawetuminna seytan ijjigun yibbesachal. yihem tegbar le Tewahedo lijoch ye KIRISTOOS memcha gize dewol mehonu aytefachewum.

  ReplyDelete
 22. አቡነ ፋኑኤል በሰላም ይምጡልን አባ ሠረቀ፣ እጅግ በጣም እንወድዎታለን፣ እንከበርዎታለን አባ ሰረቀም ወደዚህ ቢመጡልን በጣም ደስ ይለናል ምክንያቱም እኛ ተሃድሶዎች መድረሻ አጣን ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ

  ReplyDelete
 23. Aba selama why 're u write Aba Mikael and Aba Samueal weanes only why Aba Abrham ,Aba Melketsedeq Aba matewos and so on if u have the right mid do the others evil work too.what I read about Aba mikael case after he pass away u konw many arcbishos pass away were acuses in civile court 4 ep Aba meketsede and some aother please be honest whetnjdage someone thank u y

  ReplyDelete
 24. ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ?...እንግዲህ ምን ቀረ? ዲያብሎስ ወንጌል ሰባኪ ነኝ አለ። ኦ አምላክ ምን ዘመን ላይ ደረስን?

  ReplyDelete
 25. Aba Selama,
  What is wrong with you? The holy synod has already finished the meeting. But we did not have fresh new from your side.Could you say some thing about it.

  ReplyDelete
 26. What is wrong with this web bloge I have not heird anything truth since it started please try to teach us something helps us to do good things dont fillfull us by this kind very wofule not tressted news...try be good...

  ReplyDelete
 27. ማ/ቅን ከጨሰ አቧራ ጋ የምታያይዙት እናንተ እንጅ ሌላ አይደለም:: አቡነ ፋኑኤልን መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣቸው የሐዋሳ ከተማ ሕዝብ እንጅ ማ/ቅ አይደለም:: ነገር ግን እናንተን መሳዮች ሐዋሳ ላይ ለተፈጠረው ችግር ማ/ቅ በሌለበት እውነታው ሕዝቡ ማለትም የቅዱስ ገብርኤልን ምእመናን የተመለከተ ሆኖ ሳለ ችግሩን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያላከካችሁት በሕዝብ ዘንድ ለማስጠላት በታቀደ ሁኔታ የምትሰሩት እንደሆነ እኮ ዓለም ያወቀው ኃ ቅ ሆኗል:: ሐዋሳ የተፈጠረውን ችግር አቡነ ፋኑኤል እንደተሰጣቸው ኃላፊነት መፍታት ይጠበቅባቸው ነበር ይህን ደግሞ ከአቅም ማጣት ይሁን ወይንም በግደለሽነት መፍታት አልቻሉም:: ፍትህን ከሳቸው ጽ/ቤት ያጣውን ሕዝብ ከሳቸው በላይ ውሳኔ ይሰጣል ወደአሉትም አካል ሄደው ፍትህን በድጋሜ ያጡት ተበዳዮች( አባቱ ዳኛ ልጁቀማኛ ) አይነት ነገር ገጥሟቸው ሳለ ያለፍላጎታቸው በደላቸውን ወደ ዓለማዊ ፍርድ ቤት ወስደው አስፈርደዋል:: ታዲያ ይህንን ምን ልትሉት ነው:: ዳኞቹ ማ/ቅ ናቸው ነው ልትሉን ነው::ማ/ቅ እንደ ተቋም የሚያደርጋቸውን የተሃድሶ እንቅስቃሴዎች የተመለከቱ ያለመረጃ እስካሁን ማንንም ከሶ አያውቅም ሳናውቅ ተቀድተናል የሚሉ ካልሆነ በስተቀር በይሆናል ማንንም ከሶ አያውቅም:: ነገር የተሃድሶ እንቅስቃሴ በየአቅጣጫው ተቃዉሞ ሲበረታበት የተቃውሞን ምንጭ ማ/ቅ ነው ማለት ግን እብደት ነው:: የተዋህዶ ልጆች ተታለው የሄዱት ሳያዉቁ በክህደት መንገድ ሳያዉቁት እየነጎዱ ነው ይህንን ያስተዋለ ማንም ምእመን ወንድሞቹ እና እህቶቹ የሄዱትን የጥፋት አካሄድ እያየ አይቃወመንም ብሎ መገመት ነው የናንተ ጠላት:: ግመል ሰርቆ አጎንብሶ አይነት መሆኑ ነው ግመል መስረቃችሁን ሳይሆን ግመልን ያክል ነገር የሚጎትተውን ሌባ ከርቀት ያየውን ቀውላላ ሁሉ ሌባው እሱ ነው ይሄ ቀውላላ የተናገረብኝ ብሎ ለስርቆቱ መከላከያን እንደሚያቀርበው ሌባ አይነት መሆኑ ነው:: ተሃድሶዎች ለናንተ ጠላታችሁ ማ/ቅ ሳይሆን ክህደትን ባህሪያችሁ ያደረገው ድንግልን እንደጠላት እንድታዩ ያደረጋችሁ፣ ክፉ ሰይጣን ነው:: ይህን ደግሞ ለማወቅ ጾምና ጸሎት በብዙው ያስፈልገዋል እናንተ ደግሞ መራብን እንደወንጀል ስለምትቆጥሩት ለመድሃኒታችሁ የራቃችሁ ሆናችሁ ይልቅስ ይህንን ሞክሩትና ከክህደት ያውጣችሁ::
  ተጠምቀ መድህን

  ReplyDelete
 28. የፍርድ ቤት ደብዳቤው ፎርጀሪ ትንሽ ጥራት ያንሰዋል በተለይ የመዝገብ ቁጥሩና ማህተሙ፡፡ ቂቂቂቂቂቂ

  ReplyDelete
 29. tanks to the rise of tehadiso, i have fallen in love of MK. the reason is while I was in search of evidences from both sides ( MK & TEHADISO) , MK published outputs ( siema tsdik and hummer)documents have attracted me and i got them fond of the church, i judged every thing, and finally came in to conclusion that MK is the real keaper of the church and , now, due to this fact i become the customer of hummer and sema tsdik , and every thing written on that is perfect , thanks to the rise of tehadiso. before that time, i was cool , didn't have interest on church

  ReplyDelete
 30. አባ ሰላማ ብሎግ?,,,,"የግለሰብን ስም በመጥፎ የሚያነሱ ሥነ ጽሑፍም ሆነ አስተያየት ብሎጓ ፈጽሞ አትቀበልም?..." where is that blog?. oh!! our fathers, our saints, our holy books insulted.oh!! God please shut this mouth.

  ReplyDelete
 31. የአባ ሰረቀው እና የበጋሻው ብሎግ

  ReplyDelete
 32. Aba Estsifanosin lekeki adrgu yesira sew yelmat abat nachew astedaderim yichilalu magbat yale- yenebere- yetefekede-yeteregagetse new Abune Fanueil -Abune Esitsifanos- Abune Kerilos-Abune gorgoryos- Abune Elyas -Abune Lukas-Abune Yosef melkam abatochi nache Abune Abirham-Abune tsimotewos-Abune pawlos- Abune diyoskoros-baletdarochi nachew- ye Abune Abirhamin mist simina Addrasha kefelegachihu tseyikug semonun asawkalehu beteley Aba Gebre Tinsae ( Abune-----melkam tidar tilk lig alachew ayer tsina kidane mihiret atsegeb yalachewn bet mayet yichalal

  ReplyDelete