Wednesday, November 30, 2011

የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ፍልስፍና - ክፍል ሁለት - - - Read PDF

ከወልደ አበክረዙን
ባለፈው ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ፖለቲካዊ ዓማውን በሃይማኖት ሽፋን በምን መልኩ ያራምድ እንደነበር እና እንዳለ በመጠኑም ቢሆን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሃይማኖታዊ ዓላማውን /ሃይማኖት ከተባለ/ በፖለቲካ ተጽእኖ ለማሳካት የቀደምት አባቶቹን ስልት እንዴት እንየተጠቀመት እንዳለ ለማየት እንሞክራለን፡፡
በርካታ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሃይማኖታዊ ፍላጎታቸውን በፖለቲካ ጡንቻ ለማሳካት የሞከሩ መሆናቸው ቢታወቅም ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› እንደ ሞዴሉ አድርጎ ከሚወስዳቸው እንደ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና /ድብ-ፀር/ ልጁ በእደማርያም/ አድማስ-ለፀር/ በቅዱሳን ደም የተጨማለቀ የለም፡፡ እነዚህ አባትና ልጅ ነገሥታት  ሥልጣናቸውን  ላለማስነጠቅ ሲሉ አጅግ አረሜናዊ በሆነ ሰይጣናዊ መንገድ የቡዙ ሺሕ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደም አፍስሰዋል፡፡
ደቂቀ እስጢፋኖስ በደማቸው ጽፈው በመሠረትዋቸው ገዳማት ከተዉልን ከሀያ ሁለት በላይ ታላላቅ የብራና መጻሕፍት መረዳት እንደሚቻለውና የታሪክ ምሁራን በምርምር እንዳረጋገጡት እነዚህ ንጹሐን የቤተ ክርስቲያን ሰዎች በግፍ የተጨፈጨፉት ድብ ፀር በሓሳውያን ተከታዮቹ እንዳጻፈው የሃይማኖት ሕጸጽ ስለተገኘባቸው አልነበረም፡፡ የእነሱ ስህተት /ስህተት ከተባለ/ ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተችበትን የክርስቶስ መንገድና በደሙ የታተመውን የመስቀል ልዕልና ትተን ለነገሥታት ክብር፣ ለጊዜያዊ ፍርፋሪና ዓለማዊ ሥልጣን ብለን መንፈሳዊ ክብራችንን አንሸጥም ብለው እስከ መጨረሻው በዓላማቸው መጽናታቸው ነበር፡፡ የአባ እስጢፋኖስ ኮከብ ዘምድረ አግአዚ ደቀ መዛሙርት የሆኑት እነዚህ ቅዱሳን ወንጌልን፣ መጽሐፈ ሲኖዶስ ዘሐዋርያትን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ጠንቅቀው የሚያውቁ ሥርዓተ እንጦንስ ወመቃርስን አጥብቀው የሚከተሉ ነበሩ፡፡
በአጠቃላይ የደቂቀ እስጢፋኖስ መንፈሳዊ ጉዞና አቋም የሐዋርያትና የጻድቃን ሰማዕታት መንገድ የተከተለ ነበር፡፡ አፍንጫቸውና ምላሳቸው በስለት እየተቆረጠ፣  እጅና እግራቸው እንደ ዛፍ ግንድ በፋስና በመጋዝ እየተሰነጠቀ፣  ሴቶቹ ጡታቸው እየተቆረጠ፣ በማህፀናቸው /በብልታቸው/ የእሳት ፍም እየተጨመረ፣ እርቃናቸው ከቤተ መንግሥት በሚወጣ የሽንት ቤት ማፍሰሻ ቱቦ እንዲተኙ እየተደረጉ፣ እንደ በሬ በቀንበር ተጠምደው በጅራፍ ሲገረፉ፣ ላይ ላያቸው እንጨት ከተከመረባቸው በኋላ በእሳት ነበልባል እርጥብ ገላቸው እንደ ጧፍ ሲነድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር የሚያመሰጥር፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንል ማርያም የብርሃን እናትነትን፣ የንጽሕና መሠረትነትን፣ የመስቀል የማቸነፍ ኃያልነትን የሚያወሱ መንፈሳዊ መዝሙራትን እየዘመሩ መሥዋዕትነታቸውን በደስታ ይፈጽሙ ነበር እንጂ ለቅጽበትም ከዓላማቸው ፍንክች ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡
ይህ ብቻ አይደለም ልክ እንደ ሐዋርያትና ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ በነገሥታትና ገዥዎች ስቃይና መከራ ሲደርስባቸው እግዚአብሔር በእነሱ አድሮ ተአምራትን ያሳይ ነበር፡፡ ለምሳሌ ያህል ሞተው ከተቀበሩ በኋ አጥንታቸው /መቃብራቸው/ ሙታን ያስነሳና፣ ህሙማንን ይፈውስ ነበር ፡፡ ከዚህም በላይ በእሳት መሃል ሲጣሉ ከመካከላቸው እንደ ሠለስቱ ደቂቅ በእሳቱ ወላፈን ሳይቃጠሉ አመዱ መካከል ቁጭ ብለው ይገኙ ነበር፡፡ በንጉሥ አድማስ ለፀር ዘመን እንደታየውም ወደ አናብስት ማደሪያ የተጣሉ ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እንደ ነቢዩ ዳንኤል ከአናብስቱ ጋር እየተሻሹ ሲጫወቱ ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ተአምርም የአድማስ ለፀር ናቡከደነጾራዊነት በተግባር ታይቷል፡፡
ከዚህም በላይ ድብ ፀርና ልጁ አድማስ ለፀር በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ተደጋጋሚ አረመኔያዊ ቅጣቶች በፈጸሙባቸው ወቅት እግዚአብሔር በነገሥታቱ፣ በአዝማቾቻቸው፣ በወታደሮቻቸው ላይ ያልታሰበ ቀሳፊ በሽታ በመላክ በተደጋጋሚ ፈጅቶአቸዋል፡፡ እነርሱን ለማዳን ሠራዊት ባዘመቱባቸው ጊዜያትም ኃይለኛ ወጀብና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በመጣል ቀጥቶአቸዋል፡፡ ድብ ፀር ዘርዓ ያዕቆብ ራሱ በመጨረሻ እኩለ ቀን ላይ ምሳውን እየበላ እያለ ድንገት ቀሳፊ መልአክ መጥቶ ስለቀሰፈው ለኑዛዜ ሳይበቃና በልቶ ሳይጠገብ ሞቶ ቀረ፡፡ ቀደም ሲል ሀገረ ደሟ/ኢባ/ ደብረ ብርሃን የተባለችው እነ ድብ ፀር እንዳሉዋት ደቂቀ እስጢፋኖስ በሠሩት ኃጢአት ሳይሆን  በድብ ፀርና ተከታዮቹ በብርሃን አምሳያ በወረደ የእግዚአብሔር የቁጣ ምልክት ምክንያት ነበር፡፡
ደቂቀ እስጢፋኖስ በእምነታቸው፣ በሥርዓታቸው ንጹሆችና ቅዱሳን መሆናቸው በእውነተኞቹ ነገሥታት ጭምር የተመሰከረላቸው ነበሩ፡፡ ለምሳሌ ያህል በዐፄ ይስሐቅና ዐፄ ናዖድ ከከሳሾቻቸው ጋር በአደባባይ አቁመው የአገሪቱ ታላላቅ ሊቃውንት ባሉበት ትክክለኛ መሆናቸው ተመልስክሮላቸው፣ በእነዚህ ነገሥታት ወቅት በነፃነትና በሰላም ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም ዛሬም ድረስ ደቂቀ እስጢፋኖስ ፀረ ማርያም ነበሩ ብለው የሚያምኑና ለማሳመን የሚሞክሩ የድብ ፀር ደቀመዛሙርት ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› ደቂቀ እስጢፋኖስን ብቻ ሳይሆን ዐፄ ይስሐቅንና ዐፄ ናዖድንም ጨምረው ማውገዝ ነበረባቸው፡፡
ይሁንና ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ‹‹ለማርያም ሥዕልና ለመስቀል አንሰግድም›› ብለዋል በሚል ሽፋን ደቂቀ እስጢፋኖስን የጨፈጨፈበትና ያስጨፈጨፈበት ምስጢር ምን እንደነበር ብዙኀኑ ባያውቅም ስውሮቹ የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› አመራር ግን አብጠርጥረው ያውቁታል፡፡ ቀደም ሲል ለመጠቆም እንደተሞከረው ደቂቀ እስጢፋኖስ በነገረ መኮትና በመጻሕፍት ትምህርት የመጠቀ እውቀት የጨበጡ ስለነበር ድብ ፀርና በቤተ መንግሥቱ ያስቀመጣቸው ለሆዳቸው ያደሩ ቅምጥል ‹‹መነኮሳት›› ተከራክረው መርታተ አልቻሉም ነበር፡፡ በመሆኑም ንጉሡና ተከታዮቹ መቸነፋቸውን ለመሸፈን ሲሉ ማርያም ታይታናለች፣ ለንጉሡ ተገልጻለች ወዘተ በሚል ፈጠራ የራሳቸውን ተረትና ልብወለድ ተአምራት የያዙ መጻሐፍትን በመጻፍ ማሠራጨት ጀመሩ፡፡ ማሠራጨት ብቻ ሳይሆን እነርሱ የጻፍዋቸውን መጻሕፈት በማስቀመጥ በአንጻሩ ቤተ ክርስቲያንዋ ለዘመናት ስትገለገልባቸው የቆየችውን ነባር ቅዱሳት መጻሕፈትን ከየገዳማቱ እያስወጡ ያጠፉዋቸው ጀመር፡፡
ደቂቀ እስጢፋኖስ ይህንን ከቤተ ክርስቲያንዋ ቀኖና ውጭ የሆነ አሠራር አንቀበልም፣ ድብ ፀር የጻፋቸውና ያጻፋቸው መጻሕፈትም ወደ ገዳሞቻችን አናስገባም በማለት በአቋማቸው ጸኑ፡፡ ድብፀር ይህንን አጋጣሚ በሽፋንነት በመጠቀም ማለትም ‹‹አልታዘዝም አሉ›› በማለት እነርሱን ከማሰርና ከመግደል አልፎ በእመቤታችን ቅድስት ድንገል ማርያም ስም ያነጽዋቸውን ገዳማት በእሳት አቃጠለ፡፡
እዚህ ላይ ‹‹ለመሆኑ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ /ድብፀር/ ለምን በደቂቀ እስጢፋኖስ ላይ ያን የመሰለ አሰቃቂ እርምጃ ለመውሰድ ቻለ;››  የሚለው ጥያቄ መመለስ ያለበት ይመስልኛል፡፡ በመሠረቱ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን በተለይ መሥራቾቹን በአካል ጭምር ያውቃቸዋል፡፡ ታሪኩ በአጭሩ እንዲህ ነው፡፡ በቀድሞ ሥርዓት አንድ ሰው ሲነግሥ ወንድሞቹ እንዳይቀናቀኑት በወኅኒ ዐምባ እንዲቀመጡ  ነበር የሚደረገው፡፡ ይሁንና አንዳንድ ጊዜ ነገሥታቱ ለሥልጣናቸው ከሰጉ በወኅኒ ዐምባ እያሉ ጭምር በስውር የሚያስገድሉበት ሁኔታ ነበር፡፡
ይህንን የፈራችው የዘርዓ ያዕቆብ እናት /ትውልዷ ተግራይ በአክሱም ሰሜን አቅጣጫ ባለው መደባይ በሚባል ቦታ ነው/ ልጇን በምስጢር ወደ አኵሱም ትልከዋለች፡፡ ይህም ያደረገችበት ምከንያት አንድም ሥርዓተ ቤተክርስቲያንና ሥርዓተ ቤተመንግሥት ከሊቃውንት እየተማረ እንዲያድግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ከወንድሞቹና ከሸዋ መኳንንት ጥቃት ርቆ እንዲቀመጥ በማሰብ ነው፡፡ ዘርዓ ያዕቆብ አኵሱም እንደገባ ተራ ሰው መስሎ ሁለት ዓመት በደወል ደዋይነት ሦስት ዓመታት በድቁና ሲያገለግል ከቆየ በኋላ እዛ መኖሩ ስለታወቀ ወደ ደብረ ዓባይ ገዳም ሄደ፡፡ ከደብረ ዓባይ ትንሽ ቆይቶ ወደ ዋልድባ ገዳም በመግባት መንኵሶ ተቀመጠ፡፡
በወቅቱ ከእርሱ በላይ አራት ወንድሞች ስለነበሩት እነግሣለሁ የሚል ምኞት የነበረው አይመስልም፡፡ ይሁንና ወንድሞቹ ከፊሎቹ በነገሡ በየስድስት ወራት ግማሾቹ በአራት ና በስምንት ወራት ዕድሜ ሞተው ስላለቁ እናቱ ቀደም ብላ በዘረጋችው ስውር መስመር የተወሰኑ መኳንንት በመላክ አስመጣችው፡፡ ዘርዓ ያዕቆብ ወደ ሸዋ ሲመጣ ከነቆቡ /መነኩሴ አንደሆነ/ ነበር፡፡ ይሁንና የሸዋ መኳንንት ከተማከሩ በኋላ ቆቡን ለእናትህ ስጥ ብለው ለእርሱ ዘውድ ጫኑለትና አነገሡት፡፡ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንደነገሠ ደቂቀ እስጢፋኖስን ተቀብሎአቸው ነበር፡፡ ምክንያቱም ትምህርታቸው ስህተት እንደሌለበት ያውቅ ስልነበር ነው፡፡ ወደ ቤተ መንግሥት ሊያቀርባቸውም ፈልጎ ነበር፤ እነርሱ ግን ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡
ይባስ ብለውም የምንኵስና ሥርዓትና ዓላማ በመተው ከእግዚአብሔር ይልቅ ገዥዎችን ማገልግል የጀመሩትን የገዳማት አበምኔቶችን፣ መነኮሳትን በመንቀፍ ማስትማር ጀመሩ፡፡ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብንም ‹‹ለዓለማዊ ሥልጣን ሲል ሥርዓተ እንጦስንና መቃርስን ያፈረሰ›› እያሉ ይከሱት ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ‹‹ከአብሮ አደግህ ጋር አትሰደድ›› እንደተባለው እነዚህ ማንነቴን የሚያውቁ ሰዎች ከዋሉ ካደሩ ሥልጣኔን ያስወስዱብኛል በሚል ቂም ያዘባቸው፡፡
እንደዚህም ሆኖ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የትግራይ መኳንንትና አድርባይ መነኮሳትን ካልያዘ ደቂቀ እስጢፋኖስን እንደማያቸንፍ ያውቅ ነበር፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ የወሰደው እርምጃ ሠራዊቱን አስከትሎ ወደ አክሱም መገስገስ ነበር፡፡ እንደደረሰ የዐፄ ገብረ መስቀልን ዐዋጅ አድሻለሁ በማለት ለማርያም ጽዮንና ለካህናቶቿ ሰፊ ርስተ ጉልት ሰጠ፡፡ ከመሃል ሀገር አስከ ጐንደር ያሉት አድባራትና ገዳማት ለአክሱም ጽዮን እንዲገብሩ አዘዘ፡፡ በማከታተልም ለደብረ ዳሞና ተምቤን ውስጥ ለነበሩት ጥንታዊያን ገዳማት ተመሳሳይ ገጸ በረከት ርስተ ጉልት ሰጠ፡፡
ከዚህ ጐን ለጐን የትግራይ መኳንንትን ሹመት በሹመት ወርቅ በወርቅ አደረጋቸው፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረገ አሁን የቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በተሠራበት /አክሱም ዩኒቨርስቲ ያለበት አካባቢ/ ቦታ ጊዜያዊ ቤተ መንግሥትና ሥዕል ቤት ሠርቶ ለአምስት ዓመታት ያህል ቆየ፡፡ በመጨረሻም በወቅቱ የደብረ ዳሞ ገዳም አበምኔት የነበረውን የግል አማካሪው አድርጎ በመሾም ይዞት ወደ ሸዋ ተመለሰ፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ ይህንን አበምኔት ‹‹የሰይጣን ከበሮ›› እያሉ ነበር የሚጠሩት፡፡
ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በደቂቀ አስጠፋኖስ ላይ ሌላም ስጋት ነበረበት፡፡ ደቂቀ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በግብፃውያን ጳጳሳት መመራት የለባትም የሚል አቋም ነበራቸው፡፡ እንደነሱ አባባል ጳጳስ ቢያስፈልግም እንኳን የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጳጳስ ከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ ሶሪያዊ ስለሆነ ጳጳስ መምጣት ያለበት ከሶርያ ነው ባዮች ነበሩ፡፡ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በበኩሉ ደቂቀ እስጢፋኖስ ከነበራቸው ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ጋር ተዳምሮ ድንገት ከሶሪያ ጳጳስ ቢያመጡ አልያም ከመካከላቸው ጳጳስ አድርገው ቢያሾሙ በአኵሱም የራሳቸው ንጉሥ በማንገሥ ሥርወ መንግሥቱን ከሸዋ ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋት አደረበት፡፡ በመጨረሻም ጉዳዩን ከቄስ ዐጤዎቹ ጋር ከተመካከረ በኋላ ‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስ በተገኙበት እንዲታደኑ፣ ታስረው ንጉሡ ዘንድ እንዲቀርቡ፣ ካልሆነም እንዲገደሉ፣ እነርሱን ተቀብሎ ያስትናገደ ሀብት ነብረቱ እንዲወሰድና ለፈርድ እንዲቀርብ›› የሚል ዐዋጅ አስነገረ፡፡ /ቄስ ዐጤ፡- የንጉሥ ነፍስ አባት፣ ዘውድ አጣኝ፣ ማእድ ባራኪ ማለት ነው/፡፡
ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ምን ያህል ሥልጣን አፍቃሪ እንደነበር የሚያመለክተው ሌላው ተጨባጭ ማስረጃ ከበርካታ ሚስቶቹ መካከል አንዷ የነበረችው ጽዮን ሞገሳን ‹‹እኔ በመንግሥቴ እያለሁ ልጅሽን ለማንገሥ አሲረሻል›› በሚል /ልጅሽን የሚለው የገዛ ልጁን ነው/ በአደባባይ በጅራፍ ተገርፋ እንድትሞት ማድረጉ ነው፡፡ ያም ተባለ ይህ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ደቂቀ እስጢፋኖስ ድብ ፀር ለሥልጣኑና ፖለቲካዊ ጥቅሙ ሲል በፈጠረው ሤራ ፀረ ማርያም የሚል ስም ተሰጥቷቸው ቆይቷል፡፡
ይሁንና መጽሐፍ ‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› አንዳለው ለዘመናት ተቀብሮ የቆየው እውነተኛ የደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ይፋ መውጣት ጀምሯል፡፡ በዚህ በኩል ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ አሜሪካ ሚኒሶታ ሆነው ደቂቀ እስጢፋስ ‹‹በሕግ አምላክ›› በሚል ርእስ ከደቂቀ እስጢፋኖስ ታሪክ በከፊል ወደ አማርኛ ተርጉመው በማቅረብ የመጀመሪያው ናቸው፡፡ በመቀጠልም ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር በ2000 ዓ.ም  ባሳተሙት ‹‹ምንኵስና በኢትዮጵያ ዛሬና ትላንትና›› በሚል መጽሐፋቸው ስለ ደቂቀ እስጢፋኖስ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ በዚሁ ዓመት በግርማ ኤልያስ የተጻፈና ከገዳማቱ ከራሳቸው የተገኘ መረጃ ተመሥርቶ ‹‹ደቂቀ እስጢፋኖስና የደብረ ብርሃን ሸንጎ›› ክፍል በሚል ርእስ ዘርዘር ያለ መረጃ የያዘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕዝብ እጅ በብዛት ባይገባም በ1996 ዓ.ም የአስራ መቲራ ቅድስት ማርያም ገዳም ገድለ አቡነ እስጢፋኖስን ለንባብ አብቅቶ ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ ነበር ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› የሚይዙት የሚጨብጡት የጠፋቸው፡፡ በመጀመሪያ ፕሮፌሰር ጌታቸው ያሳተሙት መጽሐፍ ሀገር ውስጥ ገብቶ ሰው እጅ እንዳይገባ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ በኋላም ቢሆን የግርማ ኤልያስና የካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር መጻሕፍትን በማጥላላት በአንባብያን እጅ እንዳይግቡ ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቅጠል አልነበረም፡፡ ይህ ሁሉ ሞክረው አልሳካ ሲላቸው ‹‹ደቂቀ አስጢፋኖስን በመደገፍ የቤተክርስቲያኒቱንና የዘርዓ ያዕቆብን ታሪክ በማዛባትና በዓላትን በመቃወም›› ስለጻፉ እንዲወገዙ በማለት ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ መምህር ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም፣ ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር፣ ግርማ ኤልያስ፣ ፍስሐጽዮን ዘብሔረ እንዳቤትና አባ ገብረ መድህን ገ/ጊዮርጊስ በቅዱስ ሲኖዶስ ክስ መሥርቶባቸዋል፡፡     
‹‹የደንቆሮ እውቀቱ ድፍረቱ›› እንዲል የሀገሬ ሰው የማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› አመራር በሕይወት ያሉትን ብቻ ሳይሆን ለሀገራቸውና ለቤተክረስቲያናቸው ታላላቅ ሥራዎችን ሠርተው በክብር ያለፉትን እንደ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ አለቃ ተክለጽዮን፣ አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ፣ ዐቃቤ ሰዓት ከብቴ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባክዳኝ የመሳሰሉትን ዕውቅ ሊቃውንትን ‹‹አንተ›› እያሉ በመዘርጠጥ እንዲወገዙላቸው ጠይቀዋል፡፡ አንዲወገዙ ስማቸው ከተጠቀሱት መካከልም የማንም እምነት ተከታይ ያልሆኑ ፖለቲከኞች ይገኙባቸዋል፡፡ እንደ ማኅበረ ‹‹ቅዱሳን›› አቅድ እነዚህ ሊቃውንት ቢወገዙ በነገታው እንደ አባታቸው ዘርዓ ያዕቆብ አጥንታቸው ከመቃብር ወጥቶ ይቃጠል ማለታቸው የማይቀር ነው፡፡ 
ይህም የሚያሳየው የማኅበሩ አመራር ምን ያህል ፖለቲካዊ መሠረት አነዳላቸው ብቻ ሳይሆን መጽሐፍ    ‹‹ልባቸው ደነደነ ሰባም›› /መዝ. 11870/ አንዳለው ውስጣቸው በድንቁርና ትዕቢት የተወጠረ አርሶ ፈረሶችና መሰሪዎች መሆናቸውን ነው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አባልና ተከታይ የሆነ ሁሉ እንዚህ ‹‹አሜን ብለው ሃሌ›› የሚሉ፣ ሳይበጡ ማገም የሚሞክሩ የኅዳር ዝናሞችን በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካ ዓላማቸውን ላማሳካት የሚሞክሩ ‹‹ነጫጭ እባቦች›› መሆናቸውን አውቆ በተገኘው መድረክ ሁሉ ሊያጋልጣቸው ይገባል፡፡ እኛም በተከታታይ የማኅበረ ቅዱሳንን ማንነት የሚያሳይ ዘገባችንን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡ በመጨረሻም ዝርዝር ሰነዶች በማካተት በመጽሐፍ መልክ አሳትመን ለምእምናን እንዲዳረስ እናደርጋለን፡ የዚህን ተከታይ በቅርቡ ተጠባበቁ፡፡
‹‹በድንግል ማርያም የማያምንና የማይወዳት ሊወድቅ የተቃረበ ግንብና የፈረሰ ሕንፃ ይመስላል ››
ቅዱስ እስጢፋኖስ

26 comments:

 1. በድንግል ማርያም የማያምን???
  what? when aba estifa say this its correct????
  ውሸታም የእፉኝት ልጆች::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምነው በድንግል ማሪያም አማላጅነት አያምኑም እንዴ? ጌታችን የመጀመሪያ ተአምራቱን በቃና ሲያደርግ ወይን ማለቁን አውቆ ነው እንዴ? ወይስ ሰርገኞቹ ነግረውት? አረ እየተስተዋለ ወገን እኔ ሃጢያተኛው እንኳን እናቴ የምትጠይቀኝን ለማድረግ ለምን? እንዴት የሚሉ ጣያቄዎችን አልጠይቅም። ወይኑ እኮ አለቀ ስትለው ለርሷ እኮ አይደለም ለሦስተኛ ክፍል ነው እርሱም ባዷቸውን የቀረቡለትን ጋኖች ውሃ ሙሉባቸው አለ ወይንም አደረጋቸው ለዚያውም ጣፋጭ መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ እንደኛ አይደለም እንኳን እናቱ ድንግልዬ ጠይቃውና እኛ ጠይቀነውም የሚሞላን የሞላው አምላክ ነው። አላምንም ካሉ መብቶ ነው አብርሃም አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነው። ይሄ ሳይንስ አይደለም ካልኩሌሽን የሚፈልግ በቀላሉ እመን የፈለግከውን ታገኛለህ ነው። አላምን ካልንም የኛ ድንግል ማሪያምን አማላጅነት የምናምን ሚሊዮኖች ስላለን አይለመኑም። በቸር ይግጠመን።

   Delete
  2. አዋቂ ከሆኑ እርሶም ጽፈው ያሳዩና።

   Delete
 2. 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
  ምዕራፍ 2 ቁጥር 13

  ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
  ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።

  አየህ እስጢፋ የተሳሳተውን::

  ReplyDelete
 3. HOOO ABASELAMAWOCH SELAM LE ENANETE YIHUN BE EWENET EGEZIABHER BECHERENETU AGELEGELOTACHEHUN YEBAREK AMEN

  BETAM ASFELAGI YEHONE TARIKENA MEREJA NEW YIGEREMAL ENDHI YALE METFO TARIKEM ALE LEKA EGZIABHER MELKAM NEW YETEDEBEKE YETEKEDENE MINEM NEGER YELEM BE EGZIABHER ZENDE ::: MAHEBERE KIDUSAN MINALBET BE HAYEMANOT SHEFAN BIKERBACHEW BEAHUN SEAT TAWEKOBACHEWAL BEKENETU MELFAT ANY WAY BALENEBET BOTA HULU BEKACHU LENEL YASEFELEGAL MIKENYATUM BETEKERESTEYANN TEGEN ADERGO POLETIKA MAKAHEDE LE NETSHUE MEEMEN TERU AYEDELEM WENDEMOCH SEBAKEYANEN HONE MEZEMERAN :: ABATOCHACHENENEM MASADED YIBEKA LINEL YASEFELEGALL WENGEL BESEFAT YEDARES YIHE NEW ASEFELAGI NEGER HUALACHENEM METEGAT YASEFELGENAL BERTU ABASELAMAWOCH BETAM YEMEYASEMESEGIN SERA NEW MAWEK YALEBENEN NEGER HULU WEDHWALA SATELU TSAFULEN EGZIABHER KEFETENA YETEBAKACHEW AMEN
  AYKERM KE KE CANDA

  ReplyDelete
 4. ገብረ ሚካኤልDecember 1, 2011 at 5:31 AM

  you shmeful guys I read Kahsay G/Egziabher's book for the first time getting in the library of Mahibere kidusan wana maekel. ሄዶ ማየት ይቻላል
  Additionally where do you get the list of these all writers? Was it your assumption? But it is not the truth.
  In my standing the history of Dekike Estifanos needs carefull study.History of ZeraYaekob(Dib Tser) too.
  But I am not on the side of you. Because I am Child of Tewahedo but you are servants of Western Poletics(Protestantism - በማንነት ማፈር).
  እባካችሁ ቤተ ክርስቲያናችንን ለቀቅ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ማህበረ ቅዱሳን እናንተን ለማውወቅ ጊዜም አያስፈልግ። አነበቡ ባነበቡት ላይ አስተያየት ሰጡ ጡሩ ነው ከዚያ በኋላ ታፔላውን ምን አመጣው? ለርሶ ስላተስማማ ጸሃፊው ፕሮተስታንት ይሁን አድቬንቲስት በምን አወቁ? ትሮቴስታንቶች እኮ በድንግል ማሪያም የማያምኑ ሲሆኑ ጸሃፊው ግን ያምንባታል። ጥያቄው ግን ለምን ያልሆነ ስም ለመስጠት እንሞክራለን ለዚያውም ለማናውቀው ሰው። እግዚአብሄር በምህረቱ ይጎብኘን። በቸር ይግጠመን።

   Delete
 5. why don't u post the comment yet.

  ReplyDelete
 6. continue working with God. It is time to save God's Church from the danger of false teachings. MK is working against God not against the idea of Church Tehadiso. Tehadiso is God's agenda. They can't stop it.

  ReplyDelete
 7. የደንቆሮ እውቀቱ ድፍረቱ
  This describe the writer very well.

  ReplyDelete
 8. እንዲህ ነው እውነቷን ቁጭ እንግዲህ አንባቢ አሁን ከቃለ እግዚአብሔር አንጻር ይመዝናል!ማነው ክርስቲያን የገደለው ወይስ የተገደለው?አይ አጼው ምነካቸው እባክህ?ለሚስታቸው እንኳን አይራሩም ወይ ነዶ አለ የሀገሬ ሰው?ግራ ያገባል ሰው ትውልድ ሀገር ድረስ ሄዶ መጨፍጨፍ ምን ይሉታል?ለመሆኑ እኒህን አጼ ነው እንዴ በስማቸው ታቦት ተቀርጾ ደብረብርሃን ሥላሴ አለ የሚባለው??????????????ብቻ እንዳይሆንንና የደብረብርሃንን ህዝብ ለሰልፍ እንዳትቀሰቀሰው!!!ይህች ጽሑፍ እንደምንም ብላ ደብረብርሃን መግባት ለሕዝቡ በነጻ ወይም በርካሽ መዳረስ አለባት!!ኧረ ቤተክርስቲያናችን ትጽዳበት ለምንድን ነው ለረባ ላልረባውም ታቦት ይቀረጽ እየተባለ ሥቃይ የምናየው??እንደው እግረመንገዴን ብዬ ነው እንጂ ይህ የ ደቂቀ ታሪክ አቀራረባችሁ ልብ ወለድ እንጂ እውነት አይመስልም!ሥእሉን አይደለም እንዴ የሳላችሁት እኔ እራሴ እዚያ ያለሁ ነው የመሰለኝ ገዳማቸው እኮ ደርሼ እንድመጣ አደረጋችሁኝ በምናብ ማለቴ ነው እኔ እንኳ ያለሁት ከባህር ማዶ ነው!በርቱ ዙሪያውን ጥሩ አድርጋችሁ እየቆፈራችሁ ነው የማንን ዙሪያ እንዳትሉኝ?? የ MK ነዋ!በደንብ ቆፍሩ ወይ ንስሐ ይግቡ ወይ በእልካቸው ይቀጥሉ እኔ መቼም የምጓጓው እነርሱ ንስሐ ገብተው እንዲመለሱ ነው መቼም እናንተ አትናደዱም አይደል???እስቲ ደግሞ ቀጣዩን ለማንበብ ያብቃን!
  ኒቆዲሞስ

  ReplyDelete
 9. Thank you for your information. I think God is visiting the people of Ethiopia. Let us give our heart to the truth that is Bible!

  ReplyDelete
 10. aye ante tehafi kehzib atgenagnm ende bewushet yetemola tihuf endew kezerezerkachew tehafiwech wust mahberekidusan abal yehonum alu malete elet elet kemehaberu gar bemehon sirawun yemidegfu wye tamir ebakachihu aba selamawech kemetafachihu befit asbu enantema yemariyam telat mehonachihun zare aweku mikneyatum beemebetachin ametawi beal ken yihn tera metafachihu yeprotestant dikala mehonachihun aweku

  ReplyDelete
 11. benegerachin lay "dhiba" malet be oromigna gif malet new.yegif meret weyim akaldema malet new. deqiqe estifanos yetechefechefubet bota malet new

  ReplyDelete
 12. አንደኛ የሚገረምህ በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ጊዜ የሸዋ መንግስት የሚባል የለም
  ሁለተኛ ጌታቸው ኃይሌ የተባለ ሠፈርተኛ ራሱ በመጀመሪያ ደቂቀ እስጢፋኖስን መናፍቅ ካለ በኋላ እንደማያዋጣው ሲያውቅ ደግሞ የሸዋ መንግስት ታሪክ አለ ብሎ ውሸት ለመትከል ደጋፊ ሆነ ኢትዮጵያን ትግሬ አማራ ሸዋ እያለ የሚከፋፍል ነው ሊጠቀስ አይችልም
  ሦስተኛ የአጼ አርዓ ያዕቆብ ንግስና የታሰበብ ነው ያልከው ትክክል አይደለም በድንገት የተፈጠረ ነው
  አራተኛ ለአጼ ዘርኣ ያእቆብ ታቦተ ተቀረጸ ያልከው ትክክል አይደለም ይህ ከሆነ ቤተ ክርስቲያነኗ ከፍተኛ ችግር ላይ ትወድቃለች ሰውየው በመጠኑ አስተዋጽ ሊኖረው ይችላል እንጅ ምንኩስናውን የተወ፣ ብዙ ሚስት ያገባ፣ ብዙ ሰው በሃይማኖት ስም የገደለ፣ በመጨረሻ በአእምሮ በሽታ የታመመ፣ ነው፡፡ የሚገርመው የራሱን ሚስትና ልጅ ሁሉ ገድሏል ከእምነት ሥርዓት ውጭ፣ እንደዚህ ከሆነ ለአጼ ሃይለ ስላሴም ለልጅ ኢያሱም ታቦት ሊቀረጽ ነው ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
  ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።

  አየህ እስጢፋ የተሳሳተውን::

  እንዴት ነው እባክህ መጽሐፍን የምትረዳው ቅዱስ ጴጥሮስ ለገዥዎቻችሁ ተገዙ አለ እንጅ ገዥዎቻችሁን አምልኩ አለ እንዴ፣ ልክ ጌታ የቄሳርን ለቄሳር እንዳለው ለቅሳር የሚገባውን ግብር ክፈሉ ለመንግስታችሁ ታማን ሁኑ አለ እንጅ በጻድቃን በሰማዕታት ልክ አክብሩኝ ስገዱልኝ፣ እንደ እግዚአብሔር አምልኩኝ የሚልን ንጉሥ አክብሩ ያለ ሐዋርያ የለም፡፡ ስማ አጼ ሀይለ ስላሴም የተቀሰፉት እራቸውን የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ አድርገው አምልኩኝ ስላሉ ነው፡፡ ዘርዓ ያዕቆብም ተገዙልኝ ሳይሆን ስገዱልኝ ነው ያለው፡፡ ታሪክ ተረዳ ቅዱሳት መጻፍትን በደንብ አንብብ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ አጼ ሃይለስላሴን ታውቃቸው ይሆን። እቃ እቃ አብራችሁ የተጫወታችሁ ይመስላሉ። አጼ ኃይለ ሥላሴ ለኢትዮፕጵያ ቤተክርስትያን ባለለታ መሆናቸውን ያውቁ ይሆን። ሃገራችን ቀደም ባሉት ጊዜያቶች ጳጳሳትን የምታሾመው ግብጽ አሌክሳንደሪያ ከሚገኘው መንበረ ማርቆስ ተብሎ ከተሰየመ የማርቆስ ቤተክርስቲያን ነበር። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ግን አጼ ኃይለ ሥላሴ ጳጳሱ ህዝቤ በጦርነት ላይ በነበረ ጊዜ ጥለው ወደ ግብጽ ስለ ሄዱ መንበር ማርቆስ ይፍቀደልንና የራሳችንን ጳጳስ እንድንሾም ይፈቀደልን ባሉት መሰረት እኮ ነው ተፈቅዶላቸው ዛሬ በመንበረ ማርቆስ መሰየሙ ቀርቶ መንበረ ተክለሃይማኖት ትብሎ የራሳችንን ጳጳስ መሾም የቻልነው። ዛሬ ላይ ሆነን ሃይለ ሥላሴ የመእተ ዓመቱ ታዋቂ ዲፕሎማትን መናቅ ክርስቲያናዊ ይሆን? አምልኩኝ ያሉበትን ጊዜና ዘመን እርሶ ጸሃፊው በሚገባ ያውቁ ይሆናል እኔ ግን ቤተክርስትያን ሳሚ እና ገንቢ መሆናቸውን ስላየሁ እመሰክራለሁ። ቸር ያሰማን።

   Delete
 14. አባ እስጢፋኖስ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ነው፡፡ ስማ ለማንኛውም ለመረጃ ያህል አባ እስጢፋኖስ የመሠረቷት ገዳም ስሟ ደብረ ገሪዛን ቅድስት እመ ኩሉ ማርያም ነው፡፡ በሰውነቱም ውስጥ ዙሪያው በጳኩሚስ ሕግ በመስቀል የታሠረ ነው፡፡ የፕሮቴስታንት ተላላኪ የወንጌል መምህራንን ከቤተ ክርስያን ለማባረር ገንዘብ የተከፈላቸው ማህበረ ቅዱሰን ብቻ ናቸው ደቂቀ እስጢፋኖስን ጸረ ማርያም እያሉ የሚያባርሩት

  ReplyDelete
 15. YE matitekimu yewodekachihu wushetamoch,ayihud getan sisekilut be ewunet neber endea enante wushetamoch enante teftachihu sewun litatefu yetenesachihu wushoch libona yisitachihu

  ReplyDelete
 16. አዝናለሁ ለሁሉም ነገር ግን ጊዜ አለ ይህ ነገር ከእውነት የራቀ ውሸት ነው ብዙ አትድከሙ ማህበረ ቅዱሳን ማለት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የተቻለውን ያህል ጥረት እያደረገ ነው እንጂ እናንተ እንደምትሉት የውሸት ዜና እያቀረበ አይደለም እነሱ የሚያደርጉትን ነገር በሙሉ በመረጃ ነው ደግሞ እስኪ አስቡት እኛ ማን ነንና ስለሰው ማንነት እናወራለን ማህበረ ቅዱሳን እኮ ከትንሹ ነገር ብንነሳ ስንት የተዘጉ አብያተ ቤተክርስቲያንን ፣ ማስቀደሻ ያጡትን ፣ ስንት በችግር ምክንያት በመከራ በህይወት መካከል ያሉትን ህጻናትንና አረጋውያንን ነፍስ እግዚአብሔር በታች ሆነው ታዱ ስንቱን ወጣት በየትምህርት ቤቱና በየ ስራ ቦታቸው ቃለወንጌል እንዲማሩ አደረጉ ይህንንስ ከግምት ውስጥ አስገብታችሁታል አሁን እንዳሉት አገልጋዮች ነን ባዮች ግን መንፈሳዊ አገልጋይ ያልሆኑ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለጥቅም፣ ለገንዘብ መጠቀሚያ ያደረጉ ህዝበ ክርስቲያንን በወንጌል አንጾ እንደመያዝ ይልቅ የራሳቸውን የተመቻቸ ነገር የሚፈልጉ በገቢ ያነሱ አብያተ ክርስቲያንን የማያገለግሉ ስንት አሉ ለምን እነሱን አታርሙም ድሮም እኮ ሰይጣን የሚፈልገው የራሱ የሆነውን አይደለም የራሱ ያልሆነውን እንጂ እባካችሁ እምነታችንን ሰድበን ለሰዳቢ አንስጣት እናስተውል እግዚአብሔር ከእኛ ይልቅ እሱን ያውቃል ዝም ያለበት ምክንያትም ደግሞ አለው እናም እባካችሁ ለህዝበ ክርስቲያኑ መልካም የሆነ ነገር አስተምሩ እንጂ የተሳሳተ የውሸት ነገር አትዝሩ ለሁሉም የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ መድኃኔአለም እሱ ልብ ይስጣችሁ !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለተደረገው ነገር ሁሉ ክብር የሚገባው መድኃኔዓለም የተመሰገነ ይሁን እንጂ ማህበረ ቅዱሳንን ስናመሰግን የምንኖርበት ጊዜ አይደለም። ይደንግል ማሪያም ልጅ ለሁላችንም ልብ ይስጠንና አለርሱ ፈቃድ የሚከናወን አንዳች ነገር እንደሌለ አውቀን እርሱን ብቻ ለማመስገን ያብቃን። በቸር ይግጠመን።

   Delete
 17. mat-12

  35 መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።

  36 እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤

  37 ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።

  ReplyDelete
 18. ይገርማል ያለማፈርህ በጣም አስገረመኝ
  እስቲ አንተው የጻፍከውን ወደ ኋላ ሄድ ብለህ ተመልከተው
  ደግሞ አታፍርም በድንግል ማርያም ያላመነ??? ስሟን ለመጥራት እንኳን አልፈቅድልህም ምክንያቱም አንተ እርጉም ነህ. የተረገምክ ነህ. የእመቤታችንን ስም ሁለተኛ እንዳትጠራ እንደ አንተ አይነት አሜኬላ አያውቃትም አንት የሰይጣን ፈረስ.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወዳጄ የድንግል ማሪያምን ሥም ለመጥራት እኮ ጸሃፊው ከርሶ ፈቃድ ማውጣት የለበትም። በአንድ አፍ ሁለት ምላስ አይሁኑ ጊታው። ለምን ይቆጣሉ የድንግል ማሪያምን ስም ለመጥራት ፈቃድ ሰጪ አካል አ በትኝሹ አይራገምም። የድንግሊቱ ልጅ ያስተማረን ትዕግስትን አይደለም እንዴ "ቢመቱት ቢገርፉት ቢያላግጡበት፣ ምንም አላገኙም ከርሱ ዘንድ ስህተት።" የተባለለት አምላካችን እንደዚያም ሆኖ "አባት ሆይ የሚያረጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" አይደለም እንዴ ያለው አስተማሪያችን መካሪያችን የድንግል ልጅ እየሱስ ክርስቶስ። ታዲያ እርሶ ከየት መጥተው ነው የእርግማን መአት የሚያወርዱት። እኔ የማነበው መጽሃፍ ቅዱስ የሚረግሟችሁን መርቁ ስለሚል እግዚአብሄር አምላክ ይባርክዎት። ስህተት እንኳን ሲመለከቱ ለማስተካከል ካልሆነ በቀር የመራገምን መንፈስ ከርሶ ያርቅሎት። በቸር ይግጠመን።

   Delete
 19. ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም በፓለቲካው አለም የሚታየዉ የሸዋ ልጆችና የትግራይ ልጆች የበላይ የመሆን ሽኩቻ የሚታይበት ሰይጣናዊ አላማ ያዘለ በማህበረ ቅዱሳን ላይ በአንዳንድ ስለሀይማኖት ግድ በሌላቸዉ ዘረኛ የትግራይ ተወላጆች የሚደረግ ጥቃት መሆኑ ገሀድ የወጣ ሀቅ ነዉ

  ReplyDelete
 20. ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም በፓለቲካው አለም የሚታየዉ የሸዋ ልጆችና የትግራይ ልጆች የበላይ የመሆን ሽኩቻ የሚታይበት ሰይጣናዊ አላማ ያዘለ በማህበረ ቅዱሳን ላይ በአንዳንድ ስለሀይማኖት ግድ በሌላቸዉ ዘረኛ የትግራይ ተወላጆች የሚደረግ ጥቃት መሆኑ ገሀድ የወጣ ሀቅ ነዉ

  ReplyDelete