Tuesday, December 6, 2011

ማህበረ ቅዱሳን በሰሜን አሜሪካ የናሽቢል ቴነሲ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንን ለሁለት ሊከፍለው ነው ተባለ - - - Read PDF

ማስተካከያ፦ ውድ አንባብያን፤ ማህበረ ቅዱሳን የናሽቪልን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል ከመንፊስ የላከው ሰው መርጌታ ሳይሆን አቶ አክሊሉ ብለው አስተካክለው እንዲያነቡ እንጠይቃለን። ግለሰቡ በአሁኑ ሰዓት ወደ ኦርገን ተዛውሮ በቄስ አንዱአለም ቤተ ክርስቲያን ያንኑ ስራውን እየሰራ መሆኑን ደርሰንበታል።

በቴነሲ እስቴት ናሽቢል ከተማ የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን  ከተመሠረተ 12 ዓመት እንደሆነው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመሰረቱትም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የስደተኛው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ መሆናቸው ታውቋል። ስደተኛው ሲኖዶስ ተጨማሪ ጳጳሳትን ሾሞ መንቀሳቀስ እስከ ጀመረ ድረስ በውጭ አገር በስደት የሚገኙ ጳጳሳት ይመሩት እንደነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን የጳጳሳትን መሾም በመቃወም ከሁለቱም ሲኖዶሶች ራሱን አግልሎ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል። ይሁን እንጂ ከሁለቱም ሲኖዶሶች ቤተ ክርስቲያኑን ለመጎብኘት የሚመጡ ጳጳሳትን ሲያስተናግድ ቆይቷል። 
  ለምሳሌ ከስደተኛው ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጸዴቅ፣ በቅርቡ ወደ ጌታ የሄዱት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጎበኙት ሲሆን፤ ከሀገር ቤት ሲኖዶስ አባቶች ደግሞ ብፁዕ አቡነ ገብሬል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጎበኙት መሆኑ ታውቋል። ራሱን ገለልተኛ አድርጎ ሁሉንም አባቶች እቀበላለሁ ነገር ግን ለቡራኬ ካልሆነ በቀር አስተዳደራዊ ነገሮችን በቦርድ በሚመራው የምመናን ተወካይ ሲመራ ይቆያል የሚል አቋም ያለው ቤተ ክርስቲያን ነው።
  ማህበረ ቅዱሳን ወደዚያ ቤተ ክርስቲያን ከገባ ጊዜ ጀምሮ ግን የስደተኛው ሲኖዶስ አባቶች ቤተ ክርስቲያኑን እንዳይጎበኙት በመደረጋቸው ሰባኪዎችም እንዳይጋበዙ ተከልክለው ነበር ተብሏል። የሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ተቃዋሚዎች ደግሞ በተራቸው የውጮቹ ከተከለከሉ የሀገር ቤቶቹም እንዳይመጡብን የሚል የውስጥ ትግል ሲካሂዱና፣ አደባባይ ያልወጣ ነገር ግን ውስጥ ውስጡን የሚካሄድ ልዩነት እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
 ማህበረ ቅዱሳን መንፊስ ከሚባል ከተማ ልዩ የማህበሩን ተልዕኮ ይዞ ወደ ናሽቢል በመጣው መርጌታ አክሊሉ አማካኝነት በሥውር የአባላት ምልመላና የገንዘብ ስብሰባ ሲያካሂድ ቆይቷል። ማህበሩ በወር አንድ ቀን እሑድ፣ በሳምንት አንድ ቀን ማክሰኞ ማታ ማታ የቤት ውስጥ የጸሎት ፕሮግራም ሲያደርግ መቆየቱ ታውቋል። በዚያ የጾሎት ፕሮግራም ላይ ያቡነ ተክለ ሃይማኖትን ስእል በትልቅ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ሻማ በመልኮስ ስግደትና አምልኮ ይቀርቡለታል ተብሏል።
   ከቴነሲ የማህበረ ቅዱሳን ንኡስ ማዕከል የአባላት መዋጮ በየዓመቱ 7000 ዶላር በላይ ለሀገር ቤቱ ዋና ማዕከል ይላካል በተለያዩ አጋጣሚዎች በሎተሪ፣ በመጽሔት፣ ለገዳማት፣ ለፈረሱ አብያተ ክርስቲያናት እየተባለ ከመላው ምመናን ሲሰሰበሰብ የነበረው ገንዘብ ግን አሁን ሊከፈት ለታቀደው ቤተ ክርስውቲያን በምሥጢር ተይዞ  እንደቆየ የሚገምቱም አሉ። የማህበሩ የረጅም ጊዜ አባል እንደነበር የገለጠልን ወንድም እንደተናገረው የናሽቢልን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈል እቅድ ከተያዘ ቆይቷል፣ እቅዱና ፕላኑ የሚተላለፈውም አትላንታ ከሚገኘው የማህበረ ቅዱሳን ንዑስ ማዕከል እንደነበር ነው። በሌላ በኩል ብፁዕ አቡነ አብርሃም የናሽቢልን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደ አገር ቤቱ ሲኖዶስ ለማስገባት ከፍተኛ ጫና ያደርጉ ነበር።
 በቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ የሆነ አንድ ቄስ በማህበረ ቅዱሳን አካሄድ ያልተደሰተ መሆኑንን ማህበረ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤቱን ተጠቅሞ ቤተ ክርስቲያኑንን ሊከፍለው እንደሚችል ደጋግሞ ለቦርዱ ያቀርብ እንደነበር፣ ነገር ግን የሚሰማው እንዳልነበረ ታውቋል። የማህበረ ቅዱሳን ዋና ተንኮል ካህናት እንዳይስማሙ ማድረግ ሲሆን በናሽቢል መድኃኔ ዓለም ሁለቱን ካህናት የማህበሩ ወዳጅ እና ጠላት አድርጎ በመመደብ አንዱን ቄስ በማሞገስ ሌላውን ቄስ በማግለል በመካከላቸው መግባባት እንዳይኖር ሲያደርግ መቆየቱን፤ እንዲሁም አስቀድሞ የባነነው ቄስ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲካሄድበት እንደኖረና ዛሬም የጥቃቱ ሰለባ ሆኖ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

  ይህ በእንዲህ እንዳለ ቤተ ክርስቲያኑ ለረጀም ጊዜ በሰበሰበው ገንዘብ አዲስ ቤተ ክርስቲያን ገዝቶ ለማስመረቅ በሚዘጋጅበት ወቅት ማህበረ ቅዱሳን ሁለት እድሎች እንደተከፈቱለት ተገነዘበ፣ 1 ቤተ ክርስቲያኑን ወደ ሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ለማስገባት ጥያቄ ማንሳት እና እድሉን መጠቀም፣ 2 ይህ ሳይሆን ቢቀር አስቀድሞ የተዘጋጀበትን ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ጥሩ አጋጣሚና ምክንያት ማግኘቱን ተገነዘበ፣ ይህ ወቅት ማህበረ ቅዱሳን የቢዝነስ ምንጭ የሚሆነውን የንግድ ማዕከል ለማቋቋም መልካም አጋጣሚ ሆኖለታል። ማህበሩ ወደ ሀገር ቤት ሲኖዶስ እንግባ የሚለው ስለቤተ ክርስቲያን አንድነት አስቦ ሳይሆን የውጩን ሲኖዶስ ለመቃወም ሲሆን የሀገር ቤቱን ሲኖዶስ እደግፋለሁ የሚለው ደግሞ ያገር ቤት ጥቅሙን ለማስጠበቅ ብቻ ነው የሚሉ አሉ። ለዚህ ማስረጃው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ላይ ውስጥ ለውስጥ የሚካሄድውን አድማ መጥቀስ ይችላል ይላሉ።  

   የናሽቢል ምመናን አዲስ ቤተ ክርስቲያን ገዝተው በሚያስመርቁበት ጊዜ ማህበሩ አቡነ አብርሃም ካልባረኩት ሞቼ እገኛለሁ አለ። ውስጡን ለቄስ እንደተባለው የአቡነ አብርሃም የረጅም ጊዜ እቅድ በዚህ ጊዜ ይፋ ወጣ፤ የማህበሩ ዘማሪዎች ዝማሬያቸውን አቆሙ፣ ከዚያም ጥያቄያችን ካልተመለሰ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አንመጣም አሉ፣ ቦርዱም መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ በማለት ማህበረ ቅዱሳንን መለማመጡን አቆመ። በድንገት ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩትን አቡነ ፋኑኤልን ጋብዞ ቤተ ክርስትያኑን በድምቀት አስመረቀ። ከዚህ ጊዜ ጅምሮ ቤተ ክርስቲያኑ ሰላም እንዳገኘ ይነገራል። ዝማሬውም መላው ምመናን እየተሳተፉበት ደመቅ ያለ አምልኮ እየተድረገ ነው ተብሏል። ማህበረ ቅዱሳን ግን በሽማግሌዎች እንዲመለሱ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
  ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በዝግጅት ላይ የሚገኙት አቡነ አብርሃም የናሽቢልን ቤተ ክርስቲያን ሳይከፍሉ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይገቡ ይዝቱ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል። እርሳቸው ተከልክለው በላያቸው ላይ አቡነ ፋኑኤል የተጋበዙበትን ሁኔታ ላለመበቀል ያሚያደርጉት እንቅሥቃሴ ነው የሚሉም አሉ። የሆነው ሆኖ ማህበረ ቅዱሳን የራሱን አዲስ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት ዝግጅቱን አጠናቋል፣ በናሽቢል ሌላ የገንዘብ ምንጭ ተከፈተለት ማለት ነው።    
  ብፁዕ አቡነ አብርሃም ገለልተኛ የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናትን በረት እያሉ የሚጠሯቸው ሲሆን የናሽቢል ምመናንም ከዚህ ቃላቸው ተነስተው እንዴት በረት ሊባርኩ ይመጣሉ ሲሉ ተቃውሟቸውን እንዳሰሙ ታውቋል። በፁዕ አቡነ ፋኑኤል ግን በገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነት እንዳላቸው ይህም አብያተ ክርስቲያናቱን ወደ አንድነት ለማምጣት መልካም እድል መሆኑን ነገር ግን የማህበረ ቅዱሳን ጣልቃ ገብነት ካልቆመ እንኳንስ ወደ አንድነት መምጣት አሁን ከሚታየው መከፋፈል በባሰ ሁኔታ የመበታተን አደጋ እንደተደቀነባቸው በርካታ ምመናን ይናገራሉ።
    ማህበሩ በማንኛውም ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ በመምሰል አባላቱን ሲመለምል ከቆየ በኋላ የሚፈለገው ቁጥር ሲሞላ የራሱን ቤተ ክርስቲያን እንደሚመሠርት እየታወቀ የመጣ አሠራሩ ነው ተብሏል። አሁንም ይህን ተልዕኮ ለሟሟላት አድፍጠው የተቀመጡ አባላቱ ውስጥ ለውስጥ እየሰሩ ነው ይባላል። የዲሲ ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት ወደፊት የዚህ አሰራር ሰለባ እንደሚሆኑ ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል። በስደተኛው ሲኖዶስ ግን አባላቱ ወደዚያ እንዲገቡ ተልዕኮ ቢሰጣቸውም ተደጋግሞ የሚጠራው የኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በኦርጋን የሚቀርበው መዝሙር ትግሥታቸውን ስለሚጨርሰው በዚያ መቆየት እንዳማይችሉ ተረጋግጧል። ማህበረ ቅዱሳንን ለማባረር የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ደጋግሞ መጥራትና በፒያኖ መዘመር ፍቱን መድኃኒት መሆኑንን ከአሜሪካ የመጡ ሰው አጫውተውናል። የማህበረ ቅዱሳን አባላት ጌታ ኢየሱስ፤ አዳኝ፣ ሕይወት፣ መዳን በሌላ በማንም የለም፣ የሚሉ ቃላትን በትግስት ማዳመጥ ወይም እንዲህ በሚነገርበት ቦታ ብዙ መቆየት እንደማይችሉ እኛም የምናውቀው ጉዳይ ነው።

 መልካሙን ገድል ተጋደል
በዲያቆን ክብሩ

39 comments:

 1. ማህበረ ቅዱሳንን ለማባረር የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ደጋግሞ መጥራትና በፒያኖ መዘመር ፍቱን መድኃኒት መሆኑንን ከአሜሪካ የመጡ ሰው አጫውተውናል። የማህበረ ቅዱሳን አባላት ጌታ ኢየሱስ፤ አዳኝ፣ ሕይወት፣ መዳን በሌላ በማንም የለም፣ የሚሉ ቃላትን በትግስት ማዳመጥ ወይም እንዲህ በሚነገርበት ቦታ ብዙ መቆየት እንደማይችሉ እኛም የምናውቀው ጉዳይ ነው።
  ይህ ነገር ሊበረታታ ይገባል። ኢየሱስ ጌታ ነው እያሉ በአርጋኖን ማባረር ነው። ይህም አለ ለካ!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. “የቸገረው እርጉዝ ያገባል፣ ሲቸግረው ገደል ይገባል” ሆኖበት ነው። አዶ ከበሬ ማስጨፈርም ምሱ መሆኑን አንድ ጎረቤቱ የሆነ ቃልቻ ጠቁሞ ናሽቭል በቄሱ ላይ ሲያጓራባቸው ሰንብቷል፡፡ የናሸቪል በጎች ከበረት አንወጣም በማለታቸውና ይሄውም እንደ የአባሉ መሪ ድክመት ተቆጥሮ ገቢው ማነሱን ምክንያት በማድረግ ለናሽቭል አባሉ የሚከፍለውን እቀንሳለሁ እያለ እያስፈራራ ስለሆነ የንዘብ ማእቀቡን መቀጠል፡; ሌላው ደግሞ እባቡ መስቀልና የሙሴን ብትር አይወድም ሰለተባለ ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ መስቀልና በትሩን ይዞ ማሳደድ የመሳሰሉት ሰሞኑን ከተገኙት መፍትሔዎች ጥቂቶቹ ናቸው።

   Delete
  2. ወንድም ዓለም ሲቸግረው አይደለም "ስትወልድ" ነው ተረቱ። ጌታ ይባርክህ።

   Delete
 2. MK Getachin Amlakachin Medhanitachin Eyesus Kirstos bilo asamiro yiterawal, lesim ateraru kibir misgana yigbaw amen. Endenantena Endegibir abatachihu amalaj Ayilim.
  Mikniyatum MK Amlakena Amalaj Leyito temiruowal yastemiral.
  Libona Yistachihu

  ReplyDelete
 3. ያባ ሰላማ ተከታዮች ሆይ በርቱ እናተ በላይ ሆናችሁ እራስ ራሱን ቀጥቅጡ
  እባቡ ማኅበር ደግሞ እግር እግራችሁን ሊነድፋችሁ እየተስለከለከ ነውና እወቁበት፤

  ReplyDelete
 4. According to Meregeta from Atlanta, GA , Abazelebanose, who pretened himself with out spritual ethics he owen house, foodmart store and taxi cpnc number. The point is how and where is the source of the money came from? Meregeta in the very top secret he will be inform you very soon the corruption of zelebanose and his collagues onbehalf of the church.

  ReplyDelete
 5. Do u know that guy whose his name is zelibanos?
  we know him well when he was serving at Holy Trinity cathedral in Addis. in the locked room he takes many time mostly through out the day with the black girl which her house was at kebena.
  now we are hearing of about him that he became business man. kkkkkkkkkkkk zelibanos.... the church monks are mocking on the followers........

  ReplyDelete
 6. Mereget aba that he reported the corruption zelebamose he had sent to you his contact through your email.

  ReplyDelete
 7. ይህን የጻፍክ እና አንተን መሰሎች

  Anonymous
  MK Getachin Amlakachin Medhanitachin Eyesus Kirstos bilo asamiro yiterawal, lesim ateraru kibir misgana yigbaw amen. Endenantena Endegibir abatachihu amalaj Ayilim.
  Mikniyatum MK Amlakena Amalaj Leyito temiruowal yastemiral.
  Libona Yistachihu
  --------------------------
  ወንጌልህን ገልጠህ ጌታ ያስተማረውን በጥሞና አጥና

  የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14

  6. ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
  7. እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል አለው።
  8. ፊልጶስ። ጌታ ሆይ፥ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው።
  9. ኢየሱስም አለው። አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?
  10. እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል።
  11. እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።
  12. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥
  13. እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።
  14. ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
  15.-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤


  ዛሬ አምላክ አማላጅ አይሆንም ያልክ
  አምላክ ከሰማይ ወርዶ በሥጋ ተወልዶ እንደሰው በየጥቂቱ አድጎ
  በበረሃ በገዳም ጾሞ ያባቱን መንግስት ሰብኮ ወንጌል አስተምሮ
  በመስቀል ላይ ራሱን ላባቱ መስዋት አቅርቦ የሰውን ዘር አዳነ ከአባቱ ጋር አስታረቀ

  ታዲያ አንተ ማን ነህ ይህን የማትቀበል የምትክድ
  የቀናውን የኦርቶዶክስ ትምህርት ሳያውቁ ይሄ የፕሮቴስታንት ትምህርት ነው
  እያሉ ራሳቸውንና ሌሎችን የሚያሳስቱ ወዮላቸው

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ አዋቂ ለመሆኑ 12 ቁጥር ላይ ያልከው አማላጅነትን ለመግለጽ ነው? ቁጥር 13 በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ሲል አማላጅነትን ማመልከቱ ነው እንዴ የኛ ጨዋ? ቁጥር 14 ላይም ደገምከው ማናቸውንም በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋልሁ። ማለትም በየሱስ ስም ወጣ ብለህ ጋኔኑን ብታዘው ይወጣል ማለቱ እኮ ነው ታዲያ ይህን ማለቱ እኮ አማላጅ ነኝ ሳይሆን ራሴ አድራጊ ነኝ ማለቱን ነው የሚያሳየን። የመሃበረ ቀዱሳንን ስም እያጠፋህ ነው። ሰንበት ት/ቤት ተማሪ ነህ መሰለኝ? ገና ትንሽ ስለ እግዚአብሄር ቃል ታወቀና ለትችት መቸኮል ክርስትና አይደለምና ወንድሜ?እህቴ እንጠንቀቅ። ምን አይነት ትምህርት እያስተማርክ/ሽ ነው፣ "አምላክ ከሰማይ ወርዶ......ያባቱን መንግሥት ሰብኮ..." አረ አባትና ልጁን አትለያያቸው። ሰንበት ት/ቤት የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን አንድነትና ሶስትነትን አላስተማሩህም/ሽም እንዴ አይ ማህበረ ቅዱሳን ለካስ እንዲህ "ጨዋዎች" ናችሁ። የሚሰሩትን አያውቁምና... ያለው እኮ ለእንደናንተ አይነት ምስኪን ነው በጎ እየመሰላቸው ልክ ሥላሴዎች ከሰው ነጥለው ለናንተ ብቻ ምሥጢራቸውን የገለጹላችሁ እየመሰላችሁ ከግብር ገብታችሁ ለምትፈተፍቱት። አረ እየተስተዋል አሁንስ ይበቃችሁአል። ደግሞ ልክ አዋቂ ይመሰል "ወንጌልን ገልጠህ ጌታ ያስተማርውን በጥሞና አጥና።" ለመሆኑ እርሶ ወንጌልን ገልጠው አይተውት ያውቃሉ? መጀመሪያ ራስን መጠየቅ ትልቅ አዋቂነት ነው። ወንጌልን ገልጦ ጌታ ያስተማረውን በጥሞና ያጠና ሰው እኮ፣ የበታችነትን ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ ይማራል፤ እርሱ ጌታ ሆኖ እያለ ዝቅ ብሎ የሃዋሪያትን እግር ያጠበው እኮ ለኔና ለርሶ የበታችነትን ሊያስተምር እንጂ አያውቁም ብለን በገመትናቸው ሕዝበ ክርስቲያኖች ላይ አዋቂ መስለን ለመታየት አይደለም (ፈሪሳውያንን ያሳታውሱ) ያለ ኃጢያቱ ያለ ጥፋቱ የተተፋበትን እናስታውስ እስኪ የተወጋ ጎኑን እንመልከት የፈሰሰ ደሙን የቆሰለ ስጋውን ያ ሁሉ ሲሆን የነበረውን ትዕግስቱን (የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው)አይደል እንዴ ያለው መድሃኒታችን። እርሶስ ይህን አይደል እንዴ ሰንበት ት/ቤት ውስጥ የተማሩት ለምን ማህበረ ቅዱሳንን ያሰድባሉ። ስለክርስትና ህይወት ያላወቀ ቢኖር ቃሉን ለማሳውቅ እንጣር እርስ በእርሳችን አንባላ እባካችሁ እኔ ስለ ቃሉ ባውቅ ቃሉ ህይወት እንደሆነ ህይወት ባለው መንገድ ካልገለጽኩት መሰናከያ ነው የምሆነው ታዲያ ጊታ የምንለው ኢየሱስ መድህናችን ትዕግስትን ካስተማረን፣ የበታችነትን ካስተማረን፣ ይቀር ባይነትን ካስተማረን፣ ክሁሉም በላይ ፍቅርን ለዚያውም እስከሞት የሚያደርስን ፍቅር ካስተማረን (የምናመልከው አምላክ ሞትን ድል ያደረገ ብቸኝ አምላክ ነው) ለምን ትንሽ የርሱን ቃል አወቅን ብለን እንታበያለን። አዋቂነት ብዙ ተጠያቂነት አለበት በጌታችን መንግስት እና እንጠንቀቅ። እግዚአብሔር አምላክም ይህቺን የበቀለች ትንሽ ትዕቢት እንዲቆርጥልን በንስሃ እንንበርከክ ምህረቱ የበዛ አምላካችንም ሳናውቅ በስህተት እያወቅንም በድፍረት ከሰራነው ኃጢያት ሁሉ በጊታችንና በመድኃኒታችን ደም ይጠበን። በቸር ይግጠመን። አሜን።

   Delete
 8. Abune Abraha is at his las days of ministry in the USA and I think he is copying what Peter said on DebreTabor 2000yrs a go. AHADE LEBIRHANU,AHADE LEMESFIN....

  He is disgrace and shameless bishop.
  Who knows he might have give Tabots to each MK MEMBERS.

  ReplyDelete
 9. What is hapenning in Nashbille is not surprising. Mahibere Kedusan in association with Abune Abraham have been relentless in their efforts to divide Ethiopian Orthodox followers all over the United States. We have never heard of Mahibere Kedusan or their patriarch (Abune Abraham) being involved in reconcillation talks with the synod in North America for example. Church leaders and those who are claiming that they know EOTC's teaching and traditions should preach reconcillation, unity, peace, love and marriage not division, hatred and divorce.

  Hope the Almighty save us from these divisiveness and lead us to see the light and love of our savior Jesus Christ.

  ReplyDelete
 10. How much Abreha sell price of Tabot? Does he pay sell tax? If the answer is no will be notify FBI then they lock him jail before he leave.

  ReplyDelete
 11. Patriarc Abune Abrham?

  ReplyDelete
 12. ከሁሉ በፊት ዲያቆን ክብሩን ለመረጃው እናመሰግናለን፡፡ በሰጠሀው መረጃ የማህበሩ የንግድና የሥራጋዊ አለማዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ የራሱ በቤተ ክህነት ስም የተደራጀ የንግድና የፖለቲካ ተቋም ምስረታ በውጭ ሀገር ደግሞ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ማቋቋም ስም የገንዘብ ስብሰባና ክፍፍል ጠባብነት አመጽ መሆኑን በመጠኑ ተረድተናል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎች ካሏችሁ እባካችሁ አካፍሉን

  ReplyDelete
 13. እኔ እኮ የማይገባኝ ሰው ስላበደ ብቻ አብረን ተከትለን ማበድ አለብን እንዴ???? ወይስ እውነቱ ሳያውቁና ሳያጣሩ በሚዘበራርቁት ደካማ ግለሰቦች ተነድተን መጉዝ አለብን ...ፈጽሞ ሊገባኝ አይችልም። ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበሷ ነገር ሆነኮ ነገሩ... መጀመሪያ ስለጸፊው ስገርመኝ የሌሎቻችን ጻሐፊውን ማደነቅና ማሞገስ ምን የሚሉት ወኝተኝነት ነው። በግላጩ ብርሃን ሰው ይዋሻል እንዴ...በናሽቪል አከባቢ ከ10k ኢትዮጵያን የሚኖሩበት ከተማ ነች በትንሹ ስለዚህ እራሱን ዲ/ን ክብሩ ብሎ የሰየመው ግለሰብ ...ምንም ከሩቅ የመጣ ሳይሆን ለዚሁ ድብቅ አላማ ተዘጋጅቶ የተቀመጠ እና ፈርሃ እግዚአብሔር የሌለው ሰው መሆኑ ከጽሁፉ በግልጽ ማንበብ ይቻላል። ጽሑፉ በአጠቃላይ አንድም እውነት የሌለውና ሆን ተብሎ እዝቡን ለማወናበድ የተደረገ እንደሆነ ሁሉም እንዲረዳው መልካም ነው። የቤተክርስቲያን ስርዓት ይጠበቅ ብሎ የተነሱ ንጸሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የጠዩቁት ጥያቄ በተገቢው መልኩ አስተዳዳር ቦርድም ሆነ ካህናት ማስተናገድ ስላልፈለጉ የቤተክርስቲያኗ ባለውለታ የነበሩት ንጽህ የቤተክርስቲያን ልጆች ቤተክርስቲያኑን ለቀው ወጥተዋል። ይህ ደግሞ ከማንም ማህበራት ጋር ግንኙነት የሌለውና ስለቤተክርስቲያን ፍቅር ብቻ ተብሎ የተወሰደ አስደሳች ውሳኔ ነው። ምናልባትም ለሌሎች ከተሞች ታላቅ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ እንደሆኑ ይሰማኛል። በሰላማዊና በትህትና ጠየቁ ምላሽ አጡ የራሳቸውን ውሳኔ ወሰዱ። ስለቤተክርስቲያን ተሰደዱ...ስለዚህ ዲ/ን ክብሩ ባይ ነኝ የምትልና መሳዮችን እውነቱ የምናውቅ ብዙዎች ስላላን እባክህ አትዘበራርቅ...እንዳስፈላጊነቱ መረጃዎቹን መልቀቅና ማስለቀቅ ስለሚቻል ብዙም አትድከም።
  የተከበራቹ አንባቢዎች፡ የምናነበው ሁሉ እውነት ነው በማለት የተሳሰተ አመለካከትና ውሳኔ ከመስጠታችን በፊት መስቀለኛ ነገሮችን ቼክ በማድረግ ፍርዱን እንስጥ...
  ለዛሬው ይብቃኝ
  ቸር ወሬ ያሰማን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ ብዙ እውነቱን የሚያውቁ ሰዎችም አሉ። በድብቅ አንሰበሰብም ነበር ልትለን ነው። ቤተክርስትያኑን ለማፍረስ ለቤተክርስትያን የአባልነት መዋጮ አቁመው በድብቅ ለራሳቸው ማህበር ገንዘብ አያዋጡም ነበር ነው የምትለን። የጠየቁትን ጥያቄ አስተደዳር ቦርዱና ካህናቱ አልተቀበሉትም የምትለን አስተዳደር ቦርዱ ስንት ጊዜ ሽማግሌ ላከ? የተሞከርውን ሙከራ ያከሸፉት ልጆቹ ለሽማግሌ ቃል የማይገዙ ሽማግሌ የማያከብሩ በምሆናቸው የተደረገውን ጥረት ሁሉ ለምን አታወራም አንተስ እውነተኛ ክሆንክ? የኔ ነገር ልጆቹ አልኩ የሰንበት ት/ቤት ተማሪ ነን ባዮቹ እኮ ክ35 ዓመት በላይ ያላቸው ናቸው ተተኪ እንኳን ለመትካት ጥረት ያላደረጉ። በቦርድ አናሳብ በካህን አናሳብ አንዳችም አለርሱ ፈቃድ የማይከናወነው መድሃኔዓለም በእለተ ቀኑ ነው ጠርጎ ያወጣቸው ጣዖት ሊሆን ስለፈለጉ እውነቱ ይህ ነው።

   Delete
  2. አንድ ጥያቄ አለኝ ስደት ተሰደዱ የሚለው ስደት ማላት ምን ማለት ነው? ወደየትስ ተሰደዱ? ለቤተክርስቲያን ባለውለታዎችስ ምን ይሸለሙ? ንጽሁ የቤተክርስቲያን ለጆች ያልካቸውን (ጨዋዎች ብላቸው።

   Delete
  3. አሁን በእግዚአብሔር ስም ነው የምንነጋገረው (ለነገሩ እግዚአብሔርን ብትፈራ እንደዚህ በውሸት ዐይኔን ግንባር ያድርገው አትልም ነበር) እና ውሸት ተባለ ልትል ከሆነ ለመድከውና እውነት የተናገርክ መስሎህ ይሆናል። መላ ቅጡን ነው ያጣችሁት። አንዴ በሲኖዶስ፣ ሳይሳካ ደግሞ በካህን፣ ሌላ ጊዜ በቦርድ ወይም በጎሳ ታመካኙ ነበር። ሰሞኑን ደግሞ በካህኑ የዘመታችሁትን ሰምተናል። እኛም አልሸጥ ያለን ዕቃ በቅናሽ አወጡት ብለን ስቀን ዝም ብለናል። ቅዱስ መንፈስ ቢርቃችሁ ነው እንጂ እሄን ሁሉ ዓመት አድፍጣችሁ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ ትደፍሩ ነበር እንዴ! ጥቂቶቻችሁ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆናቸውን እንኳን እያወቅን ለመንናችሁ። እናንተ ግን እምቢ አላችሁ። ይባስ ብላችሁም ተሳደባችሁ። አብዛኞቹ ግን ጥሩ ያደረጉ መስሏቸው ነው፡; እንኳን በኦርቶዶክስ እምነታችን ቀርቶ በኢትዮጵያ ባሕላችን ሽማግሌ ክቡር ነው፤ እናንተ ግን ናቃችሁና ተሳደባችሁ። የደብረ ቀራኒዮ መድኃኒዓለም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴኒሲ ናሺቭል ግን ከበረ ፣ ልጆቹን ሰበሰበ እልልልልል ደስ ብሎናልና እናመስግነው፡; የናሺቭል መድኃኒዓለም ምዕምናንን የሚመራው እግዚአብሔር ብቻ ነው። የመጣውን ጉሳንጉስ እና የዲያብሎስን ተንኮል እያጋለጠና እያስወገደ ምዕምናኑ ላይ ፍቅርና በረከቱን እያበዛ በቅጥሩ ሰብስቧል፤ እናም ምስጋና ለድንግል ልጅ ለመድኃኒዓለም ይድረሰው። አሁንም እራሳችሁን መርምሩና (አንተም የሥጋ ጥቅምህን በእግዚአብሔር ፍቅር ለውጠህ) የሚነገራችሁን ውስጠ ገበና ተመልክታችሁ በመንቃት “አውቀን በድፍረት ሳናውቅ በስህተት የሠራነውን ሀጢአት እግዚአብሔር ይቅር ይበለን።” ብላችሁ ብትመለሱ የመድኃኒዓለም በሩ ክፍት ነው። ሌሎቻችሁ ግን ሳታውቁና ሳትጸልዩበት በመስማት ብቻ እና ለቆማችሁለት ዓላማ ብላችሁ በምትጽፉት ጽሑፍ የመድኃኒዓለምን የተባረከ ምዕምን ለመናድ መሞከር ከሃይለኛው ነፋስ (እፊቱ ያገኘውን ሁሉ ገለባብጦ እንዳልነበረ ከሚያደርገው) ቶርኔዶ ፊት ለፊት ቆሞ ከሚያሾፍ ነፍስ የለሽ ግዑዝ ጋር አለመተናነስ ነው። ፈተናውን በሚገባ ያለፈ ቅዱስ ሕዝብን፣ ግን እኛ መቅደሱ በምንለው እናንተ ደግሞ በረት፣ መጋዘን ባላችሁት ቤቱ ሰብስቦናል። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!

   Delete
 14. Yes this is exactly what happen in Nashville....good point

  ReplyDelete
 15. Thank you Diakon Kibru, this is what happen in Nashville...a group of some people organized themselves and tried to divide the Nashville church. They have been begged by mediators to come back and save the church from dividing but they refused and working on opening a new church. This is so sad....

  ReplyDelete
 16. በግሩፕ የተደራጁት አባላት በሽማግሌዎች እንዲመለሱ ቢጠየቁም ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል አላማቸው ህዝቡን እና ቤተክርሰትያንን መከፋፈል ስለሆነ ያሳዝናል

  ReplyDelete
 17. ዲያቆን ክብሩ ችግሩን ለማሳየት ሞክሯል “ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው ይላል” እነማን እንደሆናችሁ እኮ እናውቃለን በቡድን ተደራጅታችሁ ቤተክርስትያኑን ስትረብሹ ቆያችሁ እና ወደዛም አንሄድም ብላችሁ በየቤቱ አሉባልታ ስታስወሩ ቆያችሁ: ብዙዎችንም አሳስታችሁ ወደ ቡድናችሁ አስገባችሁ:: ህዝቡም መለያየት አይጠቅምም በአንድላይ ሆነን ችግሩን እንፍታ በማለት በቤተክርስትያኑ ስም ሽማግሌ አቌቁሞ ቢለምናችሁ እምብኝ አላችሁ። ይቅር የማይል ሰው ከሰይጣን እንጅ ከሌላ ስላልሆነ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ። ብታውቁ እማ ኑሮ ሁሉም እኮ የራሳችን ቤተክርስትያን ነው። የሚገርመው ደግሞ አንድም ክእናንተ ውስጥ ዲቁናም ሆነ ቅስና ወይም ጠለቅ ያለ የሃይማኖት እውቀት ያለው የለም ሁላችሁም ጀማሪ ሰንበት ተማሪዎች ናችሁ ለዛም ነው ከውስጥ በአቶ ሳሙኤል ቶማስ በሚነገራችሁ አሉባልታ እና ወሬ ተመርታችሁ ቤተክርስትያንን ያሳዘናችሁ የተባላችሁትን ለማስፈጸም ብቻ የእናት ጡት ነካሾች ሆናችሁ ያሳደገቻችሁን ቤተክርስትያን አጋጣሚውን ተጠቅማችሁ ለማፈራረስ ተነሳችሁ ምክንያቱ ቤተክርስትያን በመለያየት ፈተና እየታመሰች ትገኛለችና። የሚገርመው ደግሞ አንድ ሰው ጥቂት የሚመስሉትን ሰወች አደራጅቶ እንደ ቀላል ነገር ቤተክርስትያንን ያክል የከበረ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ መክፈት መቻሉ። ለምን ሌላ የገንዘብ ማግኛዘዴ አትፈልጉም? ቤተክርስትያን ምን በደለች በእናንተ የግል ፍላጎት የምትረበሽ። እሱ ይቅር ይበላችሁ ባለማወቅ ነውና።

  ReplyDelete
 18. ጅብ በማያቁበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል አይደል የሚሉት አባቶቻችን...ከላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ በጣም አሳዘኑኝና አንድ ነገር ልል ወደድኩ...ለመሆኑ የተጠቀሙበትን የመየጸሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለምንና እንዴት ቦታ መጠቀም እንዳለባቸው እንካ የወቁ አልመሰሉኝ። ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው የሚለው እኮ መጻሓፉ በቅድስናው ስፍራና ፤ ቃሉ በሚነገርበት ቦታ ፤ ወንጌሉ በሚሰበክበት ቦታ እንጂ እንደ አንተ አይነቱ ዳካማ አስተሳሰብ ያለው ግለሰብ የፈለገውን የሚፈነጭበት ቦታ ላይ አይደለም። ቢገባህ ኖሮ ወጣቶቹ የጠየቁትን አስቀድመህ በጠይቅህ ነበር ዳሩ ግን ካንተና ከመሰሎችህ ይህ የማይጠበቅ ስለሆነ ብዙም አትቸገር...ግን አንድ ቀን አይነ ሕሊናህ ተገልጦ ለስጋ ፍላጎትህ ሳይሆን በቃሉ መኖር ስትጀምር ምን አልኩ ብለህ ወደ ኃላ ማሰብ እንደምትጀምር ተስፋ አደርጋለሁ። መቼም የጵላጦስ እድል እንዲገጥም አልመኝልህም። በሚሰጥህ እድል ግን እንድትጠቀም የሁል ጊዜዬ ጸሎቴ ነው። የሚገርምህ ግን ለቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ካንተ የተሸለ ሰው እንዳለ ማሰብ ቢትጀምር ይሻለሃል። መለያየትን ግን በወጣቶች ሳይሆን የሌሎች ወገን ምርጫ መሆኑ አሁን ጠፍቶህ ነው? ወይስ ይም እስትራቴጃዊ ማወናበጃ መንገድ ነው? መለያየት ይብቃ አንድ እንሁን፣ የቤተክረስቲያን ህልውና ይጠበቅ ይህን ያህል ጠላትንትን የስነሳል ? ጊዜው ስለሆነ አላዝንብህመ። ብዙም አይግረምህ ለቤተክርስቲያን ስርሃት ይከበር ለማለት ዲቁናም ቅስናም አያስፈልግም የምን ወደኀላ ማለት ነው፤ እንግዲህ እነሱስ ባለቸው እውቀት ስለቤተክረስቲያን ይህን ያህል አድርጉአል አንተስ ምን አድርገሃል? ወይስ ሆዳቸው አምላካቸው ከሆኑ ወገን በመሆንህ ስለቤተክረስቲያን ትዝ ብሎህም አያውቅም። ልክ ነህ እኔም ብዙም አልጠብቅብህም ምክንያቱም የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ አይደል የሚባለው.... ምንም ሁላቹውም ጀማሪ ሰንበት ተማሪዎች ለማለት ብተሞክርም ...ለመሆኑ እንማን ናቸው ጀማሪ ሰንበት ተማሪ? ለክርስቲና ደገሞ ጀማሪ ገለመሌ አይባልም እንዳተ አውቆ ከማጥፋት ግን ያመኑበትህን ማስተላለፍ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነውና ምንም ጀማሪ ቢሆኑም ለአንተ እነሱ ግን ሐዋሪያዊ ተልሆኮያቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡; ምናልባት አቶ ሳሙኤል አንተ እንደምትለዉ አሉባልታ ሳይሆን ቃሉንና የሚጠበቅበትንንስ ተወጥቶ እንደሆነስ በምን ታውቃለህ? ስለአቶ ሳሙኤል ብዙም የምታውቅ ነገር ያለ ስላልመሰለኝ አንተን በማስረዳት ጊዜዬን መጨረስ ስለማልፈልግ ትቼዋለሁ። ስለሱ ባለፉት በርካታ አመታት ማዋቅ ካልቻልክ መቼም ቢነግሩህ ስለማይገባህና ማዋቅ ስለማትፈልግ ዘላላም ስትሰድበው ትኖራለህ እንጂ ስለሱ ብዙ የሚያውቁ ስላሉ ብዙም አትቸገር ባጭሩ ልጁ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ፤ ያመነበትን ከመናገር ወደ ኃላ የማይል፤ ንጽህና ቅን የሆነ ልብ ለቤተክርስቲያን ያለው፤ ስለቤተክርስቲያን እውነተኛ አንድነትና መዋቅር ፍላጎትና ያለው እንደሆን ልገልጸልህ እወደላሁ። ነገር ግን አንተ እንደምታስበው ሳይሆን ወጣቶቹ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩና አስተዋይና ብልህ ናቸው እንጂ በአንድ ግለሰብ የሚነዱ እንዳልሄዱ አጥብአቄ ልነግርህ እወዳለሁ። ቤተክርሰቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆኑን ካወቅህ ለምን ሌሎቹን ችግሮች አምነህ መቀበል አልቻልክም? ይልቁኑ እኛ ቤተክርስቲያንን እየበደል ሳይሆን ከአንተና ከመሰሎች የቤተክርስቲያን ጠላቶች እናድናት እያል ነው ያልለነው። ምነው ገቢ ይቀንስብኛል ብለህ ሰጋህ እንዴ ለምን ሌላ የገቢ ማግኛ ዜዴ አትፈልጉም ነው ያልሁ? አምለከ ቅዱሳን ይቅር ይበለልህ...እኛስ ለገቢ ማግኛ ሳይሆን ትክክለኛውና በመዋቅር ስር ያለ ቤተክርስቲያን ይኑረን ነው ጥያቄው።;

  ReplyDelete
  Replies
  1. በሰንበት ት/ቤት ተማሪነት ሲያታልሉን የነበሩት አዛውንቶች እንበላቸው እንጂ ተገንጥለው ቤተክርስቲያን ከፈቱ። አበቃ እኮ። እነርሱም ያምልኩ እኛም እናምልክ. እግዚአብሄር የሚሰራውን እንመልከት። ስለቤተክርስቲያን ስራት የሚቃወም ግን በሰዓቱ መጥቶ ሥነስራአቱን በሙሉ የተከታተለ እንጂ ቁርባን ካለቀ ብኋላ ለመዘመር ልብሱን እየሮጠ ያጠለቀና መቅደስ ፊት ለፊት ቆሞ የዘመረ ሁሉ ስላላየው ሥራዓት የተጓደለ ይሁን ሙሉ ይሁን እንዴት አውቆ ነው ተጓደለ የሚለው? እስኪ ከዘማሪዎቹ እንጥቀስ ቤተክርስቲያን ከካህኑ ጋር አብሮ የሚከፍት? አብዛኛዎቹ ዘማሪዎች እናውቃቸዋለን ሎውስ ቫንደርቢልት ወይም ኦፕሪላንድ ለስጋቸው ተሰልፈው ነው የሚገኙት እኮ። አረ እየተስተዋለ። ስለዚህ መወቃቀሱ ይብቃ ሰላም ለማምጣት ተሞከረ አልተቻለም ስለዚህ አታካራው ይቅርና የፍቅር አምላክ የሆነውን ክርስቶስ ብቻ እናስብ እንጂ። ብዙ ስለኛ ብቻ ስናወራ የመስቀሉ ላይ ፍቅርን እንዳንረሳ እፈራለሁ። ሰላሙን ይስጠን፡፤

   Delete
 19. Ewnet new betekristyanwa tikkekeklegna bemawakir sir endehon yenashville tenessee tewahdo legoch hasabina megnote new.ewneten mekade ayechalem .Egzehabere yerdan minem enkan bemehidanelem betekiristian sir binohnem yemedianelem betekiristian betekiklegnaw endaimera deacn kibret ena meselechu tiret biadergum medehanalem yeredanal. December 20,2011 9:45 PM

  ReplyDelete
 20. yihe hulu wuta wured minim aysfeligim. kelelaw egna kidusoch nen hatiat yelebinim lelaw hatiategna new bilew wetwal yerasachewinim betekrstian keftewal ageru demo america new. mikniyat eyefeteru ande siratu lik aydelem ande qesu aystemrum ande demo bordu tesasitwal eyalu lelawn siwenejilu yerasachewn tselot metseleya gizena mamesgegna gize siabakinu yihew 12 amet honachew. yemitenakosut demo abroachew yalewn hizb new. lemin wede islamochu ena pentewochu hedew endemaymelswachew new gira yegebagn. yedrochu mahber kidusanoch ya neber sirachew alu. enezih ke amlak gar yemiatalu cultoch nachew. milasachewm ende ibab yerezeme new. kidusnetachew minulay endehone eko new gira yemigebaw. betekrstiyan simetu fitachewn kemetemtem belay. Wustachew kifu new. Egziabher yiqir yibelachew

  ReplyDelete
 21. Mabre kidusan eyalne anwengelachew eyesus simeta man tikiklegna endehone yetawakal.Ene yemabre kidusan abal aydelehum neger gen. mabrekidusan origional tewahdo new. abalenet biasfelege wede mabrekidusn new yemehedew.Because in my opinion mabrekidusanen yemekaw ewnetegna yetewahdo lige new lemalet echegeralew. Any way kirstina badmegnet aywonem.lewnetegnawa tewahdo enkuan egna our children they gone pay secrify.But we are not going any were from medehanelem church, we gone do any thing what we want in here. Thanks

  ReplyDelete
 22. To the anonymous above, there is nothing wrong with this church unless you are of other denomination and want to preach hate among Orthodox Christians in Medhanialem church. This Church is here to stay with its dedicated belief. The talk about sacrifice at this moment is hot air. You just need to pray for your soul my friend. I repeat pray for your soul. Something is disturbing you and it is not the church. You are just one of those who think about themselves as "highly Christian than Christians" and who want to structure the oldest belief in the world. Won't happen. Nashville Medhanialem highly respect all fathers. They all are welcome. It doesn't intimidate one from the other. If you want to create havoc in this God's house again, let me tell you this, he has a way of protecting his. If you live in Nashville, I am sure you saw how the membership doubled after "kidusochu" left. I am sure you also saw how christians in the church relieved from unnecessary debates and hatred speeches inside the church. My advice to those who still think they can change and restructure by remaining in the church to create another chaos, think twice. Remember that God Almighty sees through you. He protects what is his. Stay away or repent. This advice is from one of the sinners. May God Almighty cleanse our sins and the Mother of Jesus, our blessed Mother Mary, watch over our daily efforts and deeds. Amen.

  ReplyDelete
 23. I didnt said we are kidusan than the others. probably you create this word.jesus teaches me erasun zike madreg new.you said nothing wrong in medehanalem Church. I know nothing wrong from Medhanelem,that what i learn from the Bible.Though,he knows our mistake, we can leave this to him. He knows about everybodys heart,we all pray to get clean heart. This is christianity it is not eder.we gone pray for our Medhanelem Church.I hope he gone do something miracle for his house,I believe him.
  December 22,2011 8:49 pm

  ReplyDelete
 24. The new Church is opened whether you like or not. The Nashville Orthodox Church members are going to be separare into two. I have a different opinion than you,it is not havoc.It is an idea. I dont think you understand why you are coming in Church. Probably you are coming to gossip. My friend , my advice is for you to talk like a Christian, and also change your character as a Christian.And also talk for your self , you are not representative of all Nashville Medhanalem Church members. The first step to Christianity is to stop insult. You probably went to Church for many years yet you dont have Christanity character. Let the Vergine Mary help yoou to change your character. December 23,2011 at 8.51 pm

  ReplyDelete
  Replies
  1. "THE FIRST STEP TO CHRISTIANITY IS TO STOP INSULT." GOOD YOU ARE ONE OF THOSE PERFECT CHRISTIAN IN NASHVILLE. LET'S SEE WHAT YOUR WORDS ARE "I DON'T THINK YOU UNDERSTAND WHY YOU ARE COMING TO CHURCH, PROBABLY YOU ARE COMING TO GOSSIP" INSULT #1 "YOU PROBABLY WENT TO CHURCH FOR MANY YEARS YET YOU DON'T HAVE CHRISTIAN CHARACTER" INSULT #2 ከዚህ በኋላ በማውቀው ቋንቋ ልጻፍ፦ ሰውን መሳደብ የክርስትያን መለያው አይደለም ይሉንና ከላይ ጽሁፋቸውን የጠሉትን ሰው እራስዎ ሲዘልፉ ይገኛሉ "ጅራፍ" እንደሚባለው። ለርሶና ለመሰልዋ "INSULT" ማድረግ ይፈቀዳል እንዴ? "YOU ARE COMING TO CHURCH TO GOSSIP" ማለት ቤተክርስቲያን የሚመጡት ለሃሜት ነው ማለት አይደለም እንዴ ታዲያ ይሄ ሰውን አለ ስሙ ስም መስጠት አይደለም እንዴ? እንዴት አወቁ ቢባሉስ? እርሶ የበቁ ክርስቲያን ስለሆኑ ልባና ኩላሊትን ስለሚመረምሩ እንደልብዎ ለህዝበ ክርስቲያኑ ታፔላ ይለጥፋሉ ሌላውን ግን መስመር ስትለፍ ክርስትና አይደለም ይሉናል። መልካም የማይሰማ የለም። ቀጥለውም ጸሃፊውን ብዙ ጊዜ ቤተክርስቲያን ተመላልሰዋል እስካሁን ግን የክርስትናን ባህሪይ አልተላበሱም ብለው የማያውቁትን ሰው ማንጓጠጥ ክርስትና ወይስ ማህበረ ቅደስና? አረ እየተስተዋለ አይ ኪዳነ ምህረት። በስሟማ አትነግዱ። ድንግሊቱ እኮ ከነ ስሟ መሃሪ ሌላውን አታድርግ ያለችውን እንደርሶ በእጥፉ የምታደርግ አይደለችም። እባክዎ በአይኖ ያለውን ግንድ ሳያወጡ የሌላውን ጉድፍ አይመልከቱ። በቸር ይግጠመን።

   Delete
 25. abeeet! abeeet! bitwedum batwedum betekrstianun lehulet linkefelew new teblo ewnet sineger lemejemeria gize semahu ezih bet. egziabher yibarkot. yehenen eko new yeminlew. betekrstian litkeflu new yemtetaglut new eko yalnew. Min atefan? ideaw keyet meta? man shuk alachihu? Werew enante kegemetachihut belay sigenbachihu gize gera gebachihu. ande endeigna hunu ande christian aydelachihum. Feredebin eko? yenante drama eko lewere yimechal. atfredubin mechem egziabher agalto yasayew neger kaltewera min liwera new? demos weregnaw man honena? egnas yeminaweraw ezaw bebetekristianachin wust new. Zim maletma diro qere. haymanotachin and nat. metebeq alebin. amlakim yiredanal.

  ReplyDelete
 26. For the above anonyms, explains about our back ground, and the place of where we are. We are at a very back pleace run,run.We live one of the richest Country in the World,so we have different kinds of media.These are internet,Tv ,radio, and news papers.It is not the time of believe in suuk,shuk., Though,friend my advice is for you,to liston one of the preach of Daniel Kibret.so i cant give you the title of the preach, but one of the preach, will give you a good answer.Thanks
  December 31, 2011 at 7:45 Am

  ReplyDelete
 27. በኦርጋን መዘመር ተገቢ ነዉ?ችግሩ ያስተዳደር ወይስ የሃይማኖት?
  ተረጋግቶ ላነበበዉ ቀላል ነዉ ::

  ReplyDelete
 28. let me tell you something. Both parts do not tell the truth. I don't know who is who anymore. We are all fullish and selfish. We don't know who is right and who is wrong. the way i see it both parties are making it business. IF they were really working for God they will just pray instade of insulting each other. I am sick of both parties. I am just going to pray for me and for everyone. May God help us find our senses. I don't think any one care for the church. every one cares about thier pride . it looks like it is a game now. who is going to win??? whoes members are going to be increasing??? bunch of selfish people. I hope the mekseft is NOT going to come on all of us because of some selfish people who only cares about their income for thier church. I don't think God is being worshiped in those churchs. Please MOVE ON!!!!

  ReplyDelete
 29. PRAY PRAY PRAY PRAY PRAY PRAY.
  FOR THE TRUTH FOR MERCY , FOR LOVE, FOR UNITY. PLEASE PRAY. FOR HONEST MEMBERS, BORD MEMBERS, PRISTS, DICONS, MEMBERS, SISTERS, BROTHERS.OUR SISTERS AND BROTHERS ARE DYING OF HUNGER, WAR , SICKNESS. WE HAVE ALL WE NEED IN USA. WE LEFT OUR COUNTRY TO BE BETTER PEOPLE AND WE ARE FIGHTING. SHAME ON US. WHY DON'T WE PRAY ????
  PLEASE FORGET AND PRAY. THE TRUTH WILL BE OUT. ALL OF YOU PRAY. BUT MAKE SURE YOU KNOW WHAT YOU ARE ASKING FOR. MAY GOD BLESS ALL OF US.

  ReplyDelete
 30. The sad part is nobody pray for the unity of the church, they dis agree because of different ideas and go on their own way. Christinity is love, unity...if this is the truth what are we doing? Let's wake up christians. Our enemy satan is working day and night to make us fight oneanother under the name of the church. We distroy our church history in group but when we die our soul is alone and the truth will come out.

  ReplyDelete
 31. የዛሬ ሃያ ሥድስት ዓመት አካባቢ አንድ የስምንት ዓምት ህፃን ልጅ በወቅቱ አርባዎች ውስጥ በሆነ ብሩክ በሚባል ሰው መጫወቻው ተይዞበት እንዲለቅለት በዙ ጊዜ እቤቱ ተመላልሶ ያጣዋል። ሌላ ሰው እንዳይሰጠው ደግሞ ብሩክ ያስቀመጠው በግራ እጁ ስለ ሆነ ማንም ዕቃውን አግኝቶ ሊሰጠው አልቻለም። ብሩክም እኔ እራሴ መክሬው ዘክሬው እሰጠዋለሁ በማለቱ፣ የልጁ ወሳጆች ደግሞ የልጃቸውን ዕቃ መመለስ በተመለከተ መሪር ለቅሶ በብሩክ ሥውር መልካምነት ጆሮ ዳባ ብለው ገና ትቀምሳታለህ ዓይነት አባሱበት፡; በዚያው ሰሞን የጌታችን ጥምቀት ስለነበረ የልጁ ወላጆች ግቢ ውስጥ ቅርጫ ታርዶ ለመከፋፈል ከታደመው ሰው መሀል የልጆች አባት ትልቁ ብሩክም ነበርና ከህፃኑ ጋር ፊት ለፊት ይተያዩ ጀመር። ታዲያ “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ሆነና ልጁ በአጋጠመው ተጠቅሞ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፤ እንዲህ ሲል፥ አንቱ የሚለውን አንተ ብሎ “የብሩክ ስም ይቀየር” አለ። ሁሉም ጸጥ እንዳሉ ሥጋውን እኩል በማከፋፈል ያሉት በሬ አራጅ ሰው ብቻ ቢላቸውን እየሳሉ “ማን ልትለው ፈለክ ደግሞ” ብለው በመቀጠል “ልጅ ነገሮች በግልጽ ይታዩታል” አሉና ለልጁ “በል አዲሱን የብሩክ ስም ንገረን ዳቦም አያስፈልግ ጥሩ ጊዜ ነው።” ብለው ደስ የሚል እና ቅርጫ አራጅ የሚለውን ደግሞ አዲስ ስም እንዲሰይምላቸው የፈለጉ ይመስል ድምፅ እንዳይረብሸው ቢላ መሳሉን ቆም አደረጉለት፡; ህፃኑም “ለሰው ልጅ ስም መውጣት ያለበት አድጎ ተግባሩ በሚሠራው ሥራ እየታየ መሆን ነበረበት።” ብሎ በመቀጠል “ለምሳሌ እኔ እንዳልኩት ቢሆን ኖሮ የጋሼ ብሩክ ስም ጋሼ እርኩስ ይሆን ነበር።” ሲል ግማሹን አስቆ ሌላውን ደግሞ አስደንግጦ ከሁዋላው ነብር እንደተከተለው ፍየል ተፈተለከ። ስለዚህም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ እየዋለ ሲገለጽ ትክክለኛ ስሙን ማግኘት ይገባዋል። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት መሆኑ ናሺቭል ካለው ቅርንጫፍ አባል ተረድተናል። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; ጊዜውም የዐብይ ጾም ወቅት ሰለሆነ እኛም በጸሎት ተግተን እናግዛለን፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete