Wednesday, December 7, 2011

ምስጋናና ዝማሬ መቅረብ ያለበት ለማን ነው? - - - Read PDF

እግዚአብሔር ሕዝብ የተፈጠረው የእግዚአብሔርን ምስጋና እንዲናገር ነው (ኢሳ. 43፥20-21)፡፡ በክርስትና ትምህርት መሠረት ምስጋናና ዝማሬ የሚገባው አምላክ ብቻ ሲሆን፥ የሚቀርበውም ለእርሱው ብቻ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምስጋናና ዝማሬ አቅርቡ የተባልነው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው (መዝ. 47፥695፥2፤ 135፥3፤ 147፥1፡7፤ ኤፌ. 5፥19፤ ቈላ. 3፥16)፡፡ ይህን እውነት ያልተረዱ አንዳንድ ሰዎች ግን የእግዚአብሔርን ምስጋናና ዝማሬ ለፍጡራን ሲሰጡ ይታያል፡፡ ለእግዚአብሔር ብቻ የተገባውን ምስጋናና ዝማሬ ለፍጡራን ማጋራትከጥንት ያልነበረና በኋላ ላይ የመጣ አምልኮ ባዕድ ነው፡፡

ከሐዋርያት አንሥቶ ቀደምት አባቶች በትምህርታቸውና በጸሎታቸው መጨረሻ ላይክብርንና ምስጋናን የሰጡት ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ከየድርሳኖቻቸው እናነባለን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ምስጋናንና ክብርን ለፍጡራን ማጋራት የተጀመረውበተለይ ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን አንሥቶ እንደ ሆነ ይነገራል፡፡ ለፈጣሪ ብቻ የተገባውን ምስጋናና ስግደትድንግል ማርያምና ዕፀ መስቀል እንዲጋሩ ያደረገውም እርሱ መሆኑን ካሁን ቀደም ተመልክተናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባስተማረው በ"አባታችን ሆይ" ጸሎት ላይ "እመቤታችን ሆይ" የሚለውን ያከለውም እርሱ ነው ይባላል (አባ መልከ ጼዴቅ 1963፣ 50)፡፡ በቅዳሴ ማርያም አንድምታ  (1988፣ 223) ላይ "በኀበ ኲሉ መካን ርስት አንቲ፤ - በቦታው ሁሉ ዘንድ አንቺ ርስት ነሽ" ለሚለው ንባብ በተሰጠው አንድምታዊ ትርጒም ላይእመቤታችን ከምስጋና /ለፈጣሪ ከሚቀርበው/ ሲሶውን እንደምትጋራ ተጽፏል፡፡
በቤተ ክርስቲያን በሚገኙ በአብዛኛዎቹ የጸሎት መጻሕፍት ውስጥ ምስጋናዝማሬና ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ የቀረበ አይደለም፤ ቅዱሳን ሰዎችና መላእክትም ተጋሪ ሆነዋል እንጂ፡፡ ለምሳሌ፡-

«ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ዐረፍተ ጽርሑ ዘነድ ወጸፍጸፈ ቤቱ በረድ ኅቡር ህላዌሁ ዘኢይትበዐድ ሎቱ ለባሕቲቱ ይደሉ ሰጊድ፡፡

«የአዳራሹ ግድግዳ የእሳት የቤቱም ንጣፍ የበረድ የሚሆን እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው፡፡ የማይለይ አኗኗሩ አንድ ነው፤ ለእርሱ ለብቻው ሊሰግዱለት ይገባል» (ሰዓታት ዘሌሊት ወዘነግህ  1989፣ 25)

በማለት እግዚአብሔርን ያመሰግንና ስግደትም የሚገባው ለእርሱ ብቻ እንደ ሆነ ይገልጻል፡፡ ይህ እውነት ነው፡፡ ነገር ግን ዐለፍ ይልና ይህን ማለቱን ዘንግቶ፥ «ንዑ ንስግድ ለባሕቲታ ለማርያም ድንግል ስመ መንታ ለአግብርታ  ወለአእማታ  ትኩነነ ወልታ ፡፡ - ስመ መንታ  ለሆነች ለድንግል ማርያም ለእርስዋ ብቻ ኑ እንስገድ፤ ለወንዶችና ለሴቶች ባሮቿ ጋሻ መከታ  ትሁነን» በማለት ለማርያም ብቻ እንድንሰግድ ይጋብዘናል (ዝኒ ከማሁ፣ 172)፡፡ እዚህ ላይ በተለይ በመጀመሪያው ምስጋና ላይ ስለ ስግደት የተነገረው፥ በሁለተኛው ምስጋና ላይ እንደ ፈረሰ ልብ ይሏል፡፡ ይህን የመሰለ ብዙ የተምታታና የተቀየጠ አምልኮ በመጽሐፉ ውስጥ በስፋት ይስተዋላል፡፡

ይህን ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊት በመከተል ይመስላል፥ ዛሬ በተለይ በዐማርኛ ቋንቋ ተዘጋጅተው የሚወጡ አንዳንድ መዝሙሮች፥ እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ቅዱሳንን የሚያመሰግኑና የሚማፀኑ ጭምር ሆነው       እናገኛቸዋለን፡፡ እንደዚህ ያለ ይዘት ባላቸው መዝሙሮች ውስጥ የሚተላለፈው መልእክት፥ ቅዱሳንን እንደ ክብራቸው መጠን አገልግሎታቸውንና ለእግዚአብሔር ያሳዩትን ፍቅር የሚገልጽ ሳይሆን፥ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስተካክላቸው ሆኖ ይታያል፡፡  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ደንብና ሥርዐት የወጡ የሚባሉ መዝሙራት፥ በአንድ ወገን መጽሐፍ ቅዱሳዊና እግዚአብሔር ብቻውን የሚመሰገንባቸው ናቸው፡፡  በአንድ ራስ ሁለት ምላስ እንዲሉ፥ እዚያው ካሴት፣ ወይም ሲዲ፣ ወይም ቪሲዲ ላይ ደግሞ፥ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አዳኝና አምላክ ያለ የሚያስመስል መልእክት ያላቸው ዝማሬዎችን መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ፡- ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል ባሳተመው ቊጥር 3 ካሴት ላይ «መርከቤ» የተሰኘው መዝሙር ጥቂት ስንኞች እንዲህ ይላሉ፥

«ማዕበል ወጀብ ቢበዛ
አንተ ነህ የሕይወቴ ቤዛ
በሞት መካከል ብሄድም
እንግዲህ አልታወክም»

እዚያው ካሴት ላይ ደግሞ ሌላው «ባለጸጋ» የተሰኘው መዝሙር አራት ስንኞች እንዲህ ይላሉ፥

«ባለጸጋ እመቤት ባለጸጋ እናት
አፍሰናል ከደጅሽ ብዙ በረከት
ወጀቡን ቀዝፈናል ብለን ማርያም
እንዘምራለን እስከ ዘላለም»

የመጀመሪያው መዝሙር ስንኞች፥ የበዛውን ማዕበልና ወጀብ መሻገር የሚቻለው በእግዚአብሔር እንደ ሆነ ሲናገሩ፥ የሁለተኛው መዝሙር ስንኞች ደግሞ እግዚአብሔርን ከዚህ ስፍራው አንሥተው፥ በድንግል ማርያም የተኩበት ሁኔታ  በግልጽ ይታያል፡፡ /ይህን ለማነጻጸር በተለይ የተሠመረባቸውን ስንኞች ያመሳክሯል/፡፡ ይህ ታዲያ ሁለት አማልክት ያሉን አያስመስልብንም? እንዲህ ያለው እርስ በርሱ የሚጋጭየመጀመሪያው በሁለተኛው የሚፈርስበትና የሚተካበት ውጥንቅጥ ዝማሬ ለዘማሪዎቹ  ኅሊና ባይቈረቊርም፥ አስተዋይ ለሆነው ሰሚ ምእመን ግን ግራ የሚያጋባና ፈጽሞ የማይዋጥ ነው፡፡

የአንዳንድ «አዝማሪ-መዘምራን» ዝማሬዎችም ፍጹም ክሕደትንና አምልኮ ባዕድን የሚያስፋፉ ናቸው፡፡ አዝማሪ፥ ሰዎች በተሰበሰቡበት ስፍራ ሲጫወት ዐላማው ሰዎችን አሞጋግሶ ገንዘብ መሸለም ነው፡፡ ስለ ሆነም አንዱን ባሞገሰባቸው ስንኞች፥ ስም ብቻ እየለወጠ ሌላውን ያሞግሳል፡፡ «አዝማሪ-መዘምራን» የተባሉ ዘማሪዎችም ለእግዚአብሔር ብቻ የተነገረውንና ለእርሱ ብቻ የተገባውን ምስጋናለፍጡራን በመስጠትና ለክብራቸው ባልተገባ አምልኮኣዊ ዝማሬ በመወደስ አምልኮ ባዕድን ማስፋፋታቸው እየተለመደ መጥቷል፡፡ ርግጥ ይህ ዐዲስ አይደለም፤ መሪጌታውና ደባትሩ ክፍል በመጽሐፈ ዚቅ፣ ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ደግሞ በመጽሐፈ ሰዓታትና በመሳሰለው በእግዚአብሔር ምስጋና ፍጡራንን የሚያመሰግኑ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ስለዚህ አንዳንድ «አዝማሪ-መዘምራን» ይህን ተመክሮ የወሰዱት ከእነዚህ ወገኖች ሳይሆን አይቀርም፡፡

እዚህ ላይ የዲያቆን እንግዳ ወርቅ በቀለ ቊጥር 9 ቪሲዲ መዝሙርን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚህ ቪሲዲ ላይ የእግዚአብሔር ቃል ስለ እግዚአብሔር የተናገረውን በቀጥታ ለድንግል ማርያም በመስጠት፥ በአክብሮት ስም አምልኮተ ማርያም እየተንጸባረቀ እንደ ሆነ ከመዝሙሮቹ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በመዝሙረ ዳዊት 40፥1 ላይ «ቈይቼ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት» እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ» የሚለውንና እግዚአብሔርን ደጅ ስለ መጥናት የተነገረውን ቃል እናነባለን፡፡ /ደግሞም ደጅ ጥኑ የተባልነው እግዚአብሔርን ብቻ ነው (መዝ. 27፥14፤ 37፥9፡34)/፡፡ በተጨማሪም፥ «ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምንን እመልሳለሁ?» (መዝ. 116፥12) በማለት የእግዚአብሔርን ውለታ ለመመለስ የማይቻል ስለ መሆኑ የዘመረውን እናገኛለን፡፡ በቪሲዲው ላይ ግን እነዚህ የዳዊት ዝማሬዎች ስም በመተካት ለድንግል ማርያም እንደ ተሰጡ የሚከተሉት ከሁለት መዝሙሮች ላይ የተወሰዱት ስንኞች ያሳያሉ፡፡

«ደጅ ጠናሁ ቈይቼ ኪዳነ ምሕረትን
ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሐዘኔን»

        እና

«ስላደረገችልኝ ለእናቴ
ምን እከፍላ ለሁ ለእመቤቴ»

በነዚህ ስንኞች የእግዚአብሔር ቃላት እንደ ተለወጡ ልብ ይሏል፡፡

ደግሞም ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ እስረኛ መሆኑን በየመልእክቶቹ የገለጸውን (ኤፌ. 3፥1፤ 4፥1፤ 2ጢሞ. 1፥8፡17፤ 2፥9፤ ፊልሞና 9) እና «ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቊትነት፥ ወይስ ፍርሀት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?» (ሮሜ 8፥35) በማለት ለክርስቶስ ስላለው ጥልቅ ፍቅር የመሰከረውን እውነት

«በእስራቴ አላፍርም እኔ የማርያም ነኝ
ሮማዊ አይደለሁ ፍጹም ክርስቲያን ነኝ
እመቤቴ ፍቅር የሚለየኝ ማነው?
መከራ ነው ችግር ወይስ እስራት ነው?»

ብሎአል፡፡ ርግጥ ይህ ሰው ዝማሬውን ከዋናው ምንጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ ቢቀዳ ኖሮ እንዲህ ባላለም ነበር፡፡ ነገር ግን የቀዳው ፍጹም ከደፈረሰው ምንጭ ከመጽሐፈ ሰዓታት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ይህንኑ /ሁለተኛውን/ የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፈ ሰዓታት ለውጦ እንዲህ ብሏልና፤ «ሃይማኖተ ፊልጶስ አንቲ ማርያም ከመ ጳውሎስ ይዜኑ፤ ሕማምኑ? መጥባሕትኑ? ጻዕርኑ? አኅድጎ ፍቅርኪ ዘይክለነ መኑ? - ማርያም ሆይ፥ ጳውሎስ እንደሚናገረው የፊልጶስ ሃይማኖት አንቺ ነሽ፤ ፍቅርሽን የሚያስተወን ማን ነው? ሕማም ነውን? ሰይፍ ነውን? ጭንቀት ነውን?» (መጽሐፈ ሰዓታት 1989፣ 234)፡፡ ታዲያ ድንግል ማርያምን በዚህ መንገድ ማመስገን አምልኮት እንጂ አክብሮት እንዴት ይሆናል? ይህ «ነፍሴ ጌታን  ታከብረዋለች» (ሉቃ. 146) ብላ በትሕትና የተናገረችውን የድንግል ማርምን መልካም ስም እንደ ማጥፋት ይቈጠራል፡፡ ይህን አምልኮኣዊ ውዳሴ እርሷ እንደማትቀበለውም ጥርጥር የለውም፡፡              

በመጽሐፍ ቅዱስ ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀርምስጋናና ዝማሬ እንዲቀርብ የታዘዘበት ሁኔታ ፈጽሞ የለም፡፡ የእግዚአብሔር ሰዎችም ከእርሱ በቀር ማንንም አላመሰገኑም፤ ለማንም አልዘመሩም፡፡ አምላክ በሰዎች ዐድሮ ስላደረገው ሁሉ ምስጋናውን ጠቅልሎ ሊወስድ ይገባዋል፡፡ እርሱ ሲሠራ በመሣሪያነት ያገለገሉት ሰዎችየእርሱን ክብር ለራሳቸው የሚወስዱበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ይህን ደግሞ ከማንም በላይ ዛሬ ባለማወቅ  ካልዘመርንላችሁ፥ ካላመለክናችሁ  የምንላቸው ቅዱሳን ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡

በዘመነ መሳፍንት እስራኤልን ለመታደግ እግዚአብሔር ያስነሣቸው ነቢዪቱ ዲቦራና ባርቅበጠላቶቻቸው ላይ ድልን ከተቀዳጁ በኋላ፥ ክብሩንና ምስጋናውን ለራሳቸው አልወሰዱም፤ ለእስራኤል ልጆችም አሳልፈው አልሰጡም፡፡ ነገር ግን እንዲህ ሲሉ ተቀኙ፤ «በእስራኤል ውስጥ መሪዎች ስለ መሩ፥ ሕዝቡም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ስለ ሰጡ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ» (መሳ. 5፥1-2)፡፡ በዚህ ቅኔ የተመሰገነው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ መሪዎቹ እና/ወይም ነፍሳቸውን በፈቃዳቸው ሰጡ የተባሉት ሕዝቡ እንዲሠሩ የታዘዙትን ስላደረጉ እግዚአብሔርን ቅኔ የሚጋሩበት ምክንያት የለም፡፡ እነርሱም ቢሆኑ ለእኛም የጸጋ ወይም የአክብሮት ተቀኙልን አላሉም፡፡

ከብዙው በጥቂቱ ስለ ምስጋናና ዝማሬ መጽሐፍ ቅዱሳዊው ትምህርትና ተመክሮ ይህን ይመስላል፡፡ ከዚህ ውጪ በእግዚአብሔር ምስጋናና ዝማሬ እግዚአብሔርን ብቻ ማምለክ ትተን ሌሎችንም ካከበርንበት ፈጣሪያችንን እናስቀናዋለን (ዘፀ. 20፥6፤ 34፥14፤ ዘዳ. 4፥23-24፤ 6፥15-16፤ 1ቆሮ. 10፥21-22)፡፡ «ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ» (ዘፀ. 20፥3) ያለውን የመጀመሪያውን ትእዛዝም እንጥሳለን፡፡ ስለዚህ ምስጋናችንና ዝማሬያችን መስተካከልና ለእግዚአብሔር ብቻ መቅረብ አለበት፡፡


(የለውጥ ያለህ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 206 ላይ የተወሰደ)

13 comments:

 1. heb-13
  ምዕራፍ 13
  7 የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።

  8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።

  9 ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ፤ ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና።
  ................
  17 ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ።

  ReplyDelete
 2. luk-01
  ምዕራፍ 1
  "28 መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።
  ................

  41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥

  42 በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

  43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?

  44 እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።

  45 ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።

  46 ማርያምም እንዲህ አለች።

  47 ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፥ መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤

  48 የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤"
  ............


  ብፅዕት ማርያም፤ ጸጋ የሞላብሽ ማርያም፤ የተባረክሽ ማርያም፤ የልዑል ኃይል የጸለለሽ ማርያም፤ ድንግል ወእም ማርያም፤ የጌታዬ እናት ማርያም፤
  ...............
  አ ማርያም በእንተዝ ናከብረኪ ወናአብየኪ አስመ ወለድኪ ለነ መብልአ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን።

  ReplyDelete
 3. ከላይ የተጻፉት አስተያየቶች ሁሉ የሚነግሩን ምስጋና ለድንግል ማርያም እንድናቀርብ ነው።አንተ ፍጡር ናትና ምስጋና ለድንግል ማርያም አይገባም የምትለው አንተ ከቅዱስ ገብርእል ከቅድስት ኢልሳበጥ ትበልጣለህ?እመበታችን አትመስገን የሚል ዲያብሎስና ልጆቹ ናቸው።አንተ ጸሐፊ ከየትኛው ነህ?ከቅዱስ ገብርኢል ወይስ ከዲያብሎስ?መዝሙር 32:1 ለቅኖች ምስጋና ይገባል ይልብሃል ቅዱስ መጽሐፍ።ቅዱሳን ሁሉ መስቀሉም ቅን ነገር ያደረጉ፤የሚያደርጉ ስለሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል።ከዚህ የምነረዳው ለቅዱሳን ምስጋና ይገባል ብሎ የጀመረ አንተ በሀሰት እንደምትለው ንጉሡ ዘርዓ ያዕቆብ ሳይሆን ቅዱሱ የእግዚአብሐር መንፈስ በነ ቅዱስ ዳዊት፡ በቅዱስ ገብርኢል፤በቅዱስት ኢልሳበጥ ያደረ መስክሯልና የአንተን ምስክርነት አንቀበልም፤አያሻንም።ዘጸአት7፤1 እግዚአብሐርም አለ፦እይ አንተን ለፈርኦን አምላክ አድርገሃለሁ።ምስጋና ብቻ ሳይሆን አምላካችን ለወዳጆቹ የጸጋ አምላክነት ሰቷል፤ይሰጣልም።ለሙሰ የጸጋ አምላክነት የሰጠ ለእነቱ፤ለሐዋርያትም ሰቷቸዋል።2ጰጥሮስ1፤4

  ReplyDelete
 4. እርዳታ የሰጠህን ሁሉ፤ያለፈ ያገደመዉን ሁሉ፤ አመስገናለሁ thank you ስትል የምትውል ሆነህ ሳለህ ለቅዱሳን ምስጋና አይገባም ስትል ትንሽ አታፍርም?አይሰቀጥጥህምን?

  ReplyDelete
 5. extremist Jews, extremist Muslim, extremist Buddhist, extremist orthodoxy ወዘተ የሚባሉት ግራና ቀኝ የማያዩ፣ የማይመረምሩ፣ ዓይን ያወጣ ውሸት ቢሆንም ሲሰሙ ከቆዩበት ሌላ እውነት እንኳን ቢሆን ለመስማት የሚፈልግ ጆሮ የሌላቸው፣ ከእነሱ በቀር ማንም ቢሆን እንደማይጸድቅ የወሰኑ፣ የነሱ አምላክ የነሱን ብቻ ትክክለኛ ሃይማኖት ብሎ እንደተቀበለላቸው አምነው የተቀመጡ፣ ሌላውን ለማሳመን የማይችሉ፣ ግፋ ቢል መሳደብ፣መደባደብ ብሎም መግደል የእምነታቸውን ህግጋት የሚተገበሩ፣ ስለሚያምኑት ነገር ከደረቅ አክራሪነት ባሻገር የጠለቀ እውቀት የሌላቸው፣ ብዙው አስተምህሮአቸው በተረት፣ በባህል፣ በልምድ፣ በትውፊትና በፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሰረተና ሃይማኖታቸውን የሚያመልኩት አምላክ መጠበቅ እንደማይችል ያህል ቆጥረው ለራሳቸው እስከደም ጠብታ ለመጠበቅ ቃል የገቡ ናቸው። ይህ ዓይነቱ አክራሪነት በየትኛውም የዓለም ሃይማኖት ዘንድ አለ። እዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን ለመቃወም ወይም ለመተቸት ወይም የሚያሳስት ነገር ካለው በማስረጃ የተደገፈ መልስ መስጠት የጨዋ ወግና ደንብ ሆኖ ሳለ ብዙዎች ከላይ የዘረዘርናቸው የሃይማኖት አክራሪዎች የሚሰጡት አስተያየት ስድብ፣ ሽሙጥ፣ ዘለፋ፣ ፈር የለቀቀ ትችትና ነቀፋ፣ መልክ ያለው ምላሽና ማስረጃን ባለማቅረብ «ማሞ ሌላ ፎቶው ሌላ»እንዲሉ የተሰጠባቸውን ሂስ ለመከላከል ወይም ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን እዚህም እዚያ የሚዘል አስተያየት ሲያቀርቡ እናያቸዋለን። እነዚህ አንብበው፣ ጠይቀው፣ ተምረውና ተመራምረው ወደሚያምኑት ሃይማኖት የደረሱ ሳይሆን በዘር የወረሱትና ከዚያም ስለሃይማኖት ምንም እውቀት ያልነበረውን አእምሮአቸውን በውርስ የትምህርት መድረክ ልክ እንደቴፕ ካሴት ከተሞላ በኋላ ያንኑ መልሶ መልሶ የሚዘፍን፣ ሌላ ነገር ለመያዝ የሞላና «delete» ለማድረግ የማይቻል ሃሳብ የተሸከሙ ናቸው። ስለዚህም አክራሪ እስላም፣ አክራሪ ኦርቶዶክስ፣ አክራሪ ይሁዲ...ወዘተ ተብለው ይጠራሉ። ሁሉም አክራሪዎች ለሃይማኖታቸው ቀናተኞች ከመሆን ባለፈ እውቀት የላቸውም። ይህንን ቃል ጳውሎስ በአይሁዳውያን ለሃይማኖታቸው ከመቅናት ባለፈ እውቀት እንዳልነበራቸው ተናግሯል።«በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና»ሮሜ 10፣2 ዛሬም የሚታየው ይኸው ነው።

  ReplyDelete
 6. ወንድም ብርሃን አንተ እንደምትለም ሀይማኖትን በመላላት ሳይሆን አክርሮ መያዝ ያስፈልጋል።አክርርን ይዘንም እናንተን አልቻልናችሁም እንኳን አላልተን።ስለዚህ ቢቻል ሁሉም አክራሪ ኦርቶዶክስ(ያክረረ) መሆን አለበት።የላላ ነገር ሁሉ ነገ ይጣላል።አላልተህ ይዘህው እኮ ነው አንዲ ኦርቶዶክስ ለላ ጊዚ ደግሞ ቆንጢ የሚሆኑት።እስከ ሞት ድረስ የጸና ይድናል ማለት እኮ እስከ መጨረሻው እምነቱን አክርሮ ጠብቆ፤አክራሪ ክርስቲያን ሆኖ የኖረ ይድናል ማለቱ ነው እንጂ አንዳንዲ እያፈገፈጉና እየካዱ እምነትን አላልቶ ይዞ መኖር ማለት ነው።ሃይማኖትን አክርሮ መያዝ፤አማኙም አክራሪ መሆን አለበት።

  ReplyDelete
 7. እኛ ተሀድሶዎች ለጊዜው ምስጋና የምንሰጠው ላባ ጳውሎስ: ለሰረቀ: ላባ ፋኑኤል እና ለበግ አሻው ብቻ:: ሌሎቻችሁ ተራ ጠብቁ::

  ReplyDelete
 8. ገብረሚካኤልDecember 9, 2011 at 11:23 PM

  I am sending it for the second time you can read it if u don't want to post.
  ራዕ 17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
  18 በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።

  አሸዋዎች ሆይ
  የምን መመሳሰል ነው እንዲህ ራሳችሁን ገልጣችሁ ተዋጉ፡፡ ስማችሁንና የብፁዓን አባቶቻችን ምስሎችንም በምታምኑበትና በሚገልጻችሁ ዘንዶ ወይም በ ፓስተሮቹ ቀይሩት፡፡
  የተዋሕዶ ልጆች ግን እንደምታዩት ከተኩላዎች ሴራ ስለ ቅዱሳኑ ሲል ጠብቆቱን ሲያበዛልን ይኖራል፡፡
  አኛም

  መዝ 68፥35
  እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል እግዚአብሔርም ይመስገን።


  እያልን እንዘምራለን
  እናንተንም
  “ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር አውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ
  ጠዐሙ ከመ ታዕምሩ ከመ ሔር እግዚአብሔር” መዝ 33(34)፡7-8
  እያልን የምዕራባውያን አምልኮአችሁን ትታችሁን ወደ ልቦናችሁ እንድትመለሱ አንመክራችኋለን፡፡
  አምላከ ቅዱሳን ለብዎዉን ይስጣችሁ

  ReplyDelete
 9. በ ቅድስት ማሪያም ስም ሆኖ አምልኮውን የሚቀበላችሁ ዲያቢሎስ ነውና ንቁ። ቅድስት ማርያምን በመንግስተ ሰማያት አግኝተን ብጽዕት እንላታለን። ዛሬ ግን አምላኳን እያመሰገነች በገነት ነውና ያለችው በስሟ ዲያቢሎስን አታምልኩ።

  ReplyDelete
 10. "በስሟ ዲያቢሎስን አታምልኩ" ዲያቢሎስ ነው የነገረህ?

  ReplyDelete
 11. "ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤" ትውልድ ሁሉ!!!!!

  ReplyDelete
 12. mat-10
  24 ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም።

  25 ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው
  ...............
  40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

  41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

  ReplyDelete
 13. በስመኣብ ወወልስ ወመንፈስ ቅዱስ ኣንድ ኣምላክ ኣሜን
  በመጀመርያ ኣንተ/ኣንቱ ማን ነህ/ኖት? ብሎ መጠየቅ ይሻላል ይህ ማለቴ ደሞ ማንመትህ ለራስህ ብታሳውቃት ቆንጆ ነገር ነው፥ በንስ ትውክልት ሆነህ ነው ኣምትናገረው፥ ቆሞ ያለው አሚመስለው ሁሉ አንዳይወድቅ ይተንቀቅ ይላል ቅዱሱ መጽሃፍ፥ ስለዚ ኣምተም ማንነትህ ኣራስሁን ንምአሳወቅ ኣራስህን ብትመረምር ይበልጣል፥ስለ ቅዱሳን ከመናገር ይበልት እና፥ኣሁንም ላሳስብህ አምፈልገው ነገር ቢኖር የቀናው ምንገዱን መድሃኒ ኣለም ክርስቶስ አንድያሳይህ በጸሎት በርታ፥
  የቅዱሳን ኣና የእመቤቴ ጸሎት ኣንተ ጋ ይሁ። ለሊድያ ኣስተዋይ ሊብ የሰተ ገታ ላንተም ኣስተዋይ ልቦና ይስጥህ፡

  ReplyDelete