Sunday, December 11, 2011

ወደ አባቶቻችን እምነት እንመለስ - - - Read PDF

በክርስትና ታሪክ እምነታችንን መሠረት አድርገን አባቶቻችን ብለን የምንጠቸራው ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያሉትን ነው፤ አብርሃም በሥጋ የአይሁድ አባት ሲሆን ለኛ ለክርስቲያኖች ግን የእምነት አባታችን ነው። ይህም በክርስቶስ በኩል ባገኘነው እምነት ማለት ነው። መጸሐፍ ቅዱስ አብርሃም የእምነት አባታችን መሆኑን እዲህ ሲል ያስተምረናል።
  «እምነቱ ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት እንላለንና።  እንዴት ተቆጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ። ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው» ሮሜ 49-12

  አብርሃም «የምድር ነገዶች በዘርህ ይባረካሉ የሚለውን» የተስፋ ቃል ሰምቶ አመነ፣ አምኖም እግዚአብሔርን ታዘዘ፣ ሀገሩን እና ወገኑን ትቶ እግዚአብሔር ወደሚያሳየው ቦታ በእምነት ሄደ። እንግዲህ የአብርሃም ዋና ተስፋ የምድር ነገዶች በዘርህ ይባረካሉ የሚለው ነው። ይህ ዘር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ሐዋርያው እንዲህ ሲል መስክሯል፦ "ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር። ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን። ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።» ገላ 316   ከአብርሃም ጀምሮ ይስሐቅና ያዕቆብ ሌሎችም እስከ ክርስቶስ የነበሩ ነቢያት ሁሉ ተስፋቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። ስለ እርሱ መከራ ተቀብለዋል፤ ሞተዋል፣ ሰብከዋል ሆኖም ክርስቶስን በዓይነ መንፈስ ተመለከቱት እንጂ በዓይነ ሥጋ አላዩትም ነበር። ሐዋርያው ይህን ሲመሰከር እንዲህ ይላል"እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ» ዕብ 1113  ልብ የምንለው ቃል እነዚህ በዕብራውያን ምራፍ 11 ላይ የተዘረዘሩት አባቶች ሁሉ አምነው መሞታቸውን ነው ያመኑትም ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። ዘመናቸው ሩቅ ቢሆንም በመንፈስ አይተውታል። ስለዚህ አምነው የሞቱት ሁሉ የእምነት አባቶቻችን ናቸው።

  የብሉይ ኪዳን አባቶች አምነውት የሞቱለት፣ ከሩቅ የተሳለሙት፣ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚያው ዘራቸው ከሆነችው ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ መጣ ወይም ሥጋን ለብሶ ተገለጠ፤ እርሱም ቅድመ ዓለም የነበረ፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፤ እውነተኛ አምላክ ነው። ሐዋርያው ሲመሰክር «እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤ አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን» ብሏል ሮሜ 94-5   አብርሃምና ልጆቹ ተስፋ ያደረጉት እምነታቸው ተፈጸመ፣ ሕግና ነቢያት የተናገሩትም ይህን እውነት ነው፤ እርሱም ሕግና ነቢያትን ልፈጽም መጣሁ አለ። ሰው ሆኖ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ አባቶቻቸው ነቢያት የተናገሩለትና ያመኑት እርሱ መሆኑን ተስፋውን ሊፈጽም መምጣቱን ለሐዋርያት ገለጠላቸው። ባቶቻቸው ተስፋ ያደረጉትን እነርሱ በማየታቸው ብፁዓን መሆናቸውን አስረገጠላቸው «የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም» ተባለላቸው ማቴ 1316-17

 እንግዲህ እኛ ኦርቶዶክሳውያን የአባቶቻችን እምነት የምንለው ይህን አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ ያመኑትን፤ ነቢያት በመንፈስ ከሩቅ አይተው የተሳለሙትን፤ አባቶቻችን ሐዋርያት በአይናቸው ያዩትን፣ በጆሯቸው የሰሙትን፣ በእጃቸው የዳሰሱትን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው። ከዚህ ውጭ ሌላ ሃይማኖት የለንም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአባቶቻችን ሐዋርያት ይህን አንድ ሃይማኖት ነው የሰጠው፤ ጌታ ከተናገራቸው የእምነታችን ቃላት ከሆኑት ጥቂቶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንጠቅስ «እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» ዮሐ 146 ወደ አብ መሄጃ መንገዱ አንድ ብቻ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንድ ሃይማኖት የሚባለው ይኸው ነው። መንገድ ሃይማኖት ነው ሃይማኖትም መንገድ ነው።
  «ኢየሱስም ደግሞ አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም። በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል» የሐ 107-9  ወደ እግዚአሔር መንግሥት ለመግባት አንድ በር ብቻ አለ፣ በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል እንዳለ ለመዳን የሚፈልግ ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ይጠበቅበታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ይህን ንጹሕ ኪዳን ካስተማራቸው በኋላ በደሙ አትሞታል።  «ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፤ እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ። ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው» ይላል ማቴ 2626

  እንግዲህ አንድ ሃይማኖት የምንለው ጌታ እንደዚህ ለሐዋርያቱ ያስተማረውን ነው። ሐዋርያት አባቶቻችን ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ እንዲያስተምሩ በተላኩበት መሠረት ሰው መዳን የሚችለው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን አስተምረዋል «መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለም» ብለውዋል የሐዋ 412 ሐዋራያት የተሰጣቸው አንድ ሃይማኖት ስለሆነ ሌላ ስም መላክ ወይም ነቢይ ለመዳናችን እንደማይሆን አስቀድመው አስተምረዋል፣ እኛም ይህን እምነታቸውን እናምናለን።  ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ሐዋርያት የተሰጠው ሃይማኖት እንድ ሃይማኖት ነው። ከሐዋርያት በኋላ ለተነሱ አባቶችም ሌላ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባ ኪዳን አልተሰጠም። ሌላ ኪዳን ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ አንድ ሃይማኖት የሚለው ቀርቶ ሁለት ወይም ሦስት ሃይማኖት ይኖር ነበር። ሐዋርያው ይሁዳ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ በማለት ይመክራል«ወዳጆች ሆይ፥ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ» ይሁዳ 13ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠው ሃይማኖት «በክርስቶስ በኩል ወደ አብ» የሚለው የአባቶቻችን ሐዋርያት እምነት ነው።  ጳውሎስ እንዲህ ይላል፦
«በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን። ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም» 2ቆሮ 34-5

 ኢትዮጵያውያን አባቶቻችንስ እምነታቸው እንዴት ነበር? እምነታቸው የአብርሃም የነቢያት የሐዋርያት ነበርን ወይስ አላዋቂዎች እንደሚያወሩት ይሆን?  አይደለም! አንዳድ ጭፍን የፕሮቴስንታት አስተማሪዎች ኦርቶዶክስ ምንም እውነት የሌላት በባዶ ተረት የምትመራ ናት ሲሉ አላዋቂነታቸውን አሳውቀውናል። ይህን ያሉበት ምክንያት ዛሬ ሕዝቡ እየተለማመደ ያለውን ሰርጎ ገብ ሐሰተኛ አስተማሪዎችና የፖለቲካ ኃይሎች የጫኑባትን ሀሰተኛ ኪዳን ስለሚመለከቱ ነው ብየ አምናለሁ። ስለዚህ ይቅር ብያቸዋለሁ። ነገር ግን እውነቱን እንዲያውቁ፣ ጥንታውያን ኦርቶዳክሳውያንና ዛሬ አንገታቸውን ደፍተው በቤታቸው የተቀመጡ አባቶችም ሃይማኖታቸው የሐዋርያት አንድ ሃይማኖት መሆኑን ከጻፏቸው ድርሳኖቻቸቸው ጥቂት ማሳየት እፈልጋለሁ።

 ለምሳሌ ከሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምረው ከነበሩት ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ብጀምር ቅዱስ ያሬድ እንደ አንድ ማስረጃ ይሆንልኛል። ቅዱስ ያሬድ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰከረውን ምሥክርነት ከዝማሬው እንመለከት፦ «በዲበ ዕፀ መስቀል ጸርሐ ወልድ ኀበ አቡሁ እንዘ ይብል መሐር ተግባረከ ወኢታማስን ልሕኲተከ ወኢትስድድ ዘፈጠርከ ዘፈጠረት የማንከ ለእመ አዳም አበሰ ወአለወ ትእዛዝከ አባ መሐሪ ርኢ እደውየ ወእገርየ እለ ቀነውኒ አይሁድ አማጽያን ለእመ ለእመ አዳም አቢሶ በልዓ እምፍሬ ዕፅ አባ መሐሪ ነጽር ዘንተ መስቀለ ዘሰቀሉኒ ቦቱ ከመ ዕቡስ ሥጋየ ወደምየ ንጹሐ አዓርግ  ቍርባነ እስከ አግእዞ ለአዳም እምግብርናት ወአገብዖ ካዕበ ውስተ ገነት ምስሌየ ለዝሉፉ ወለኩሎሙ ደቂቁ እሠሪ ሎሙ»

ትርጉም «ወልድ በዕፀ መስቀል ላይ ሳለ ወደ አባቱ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ ፍጥረትህን ይቅር በል፣ ሸክላህንም አታፍርስ፣ ቀኝህ የፈጠረችውን ፍጥረትህን አታጥፋ። አዳም ትዛዝህን እምቢ ብሎ ባይታዘዝህና የዛፉን ፍሬ በልቶ ቢበድልህም መሐሪው አባት ሆይ፣ ስለ እርሱ አይሁድ የቸነከሩኝን እጆቼን እና እግሮቼን ተመልከት፣ ይቅር ባዩ አባት ሆይ፣ እኔን እንደበደለኛ የሰቀሉበትን ይህን መስቀል ተመልከት፣ አዳምንና ልጆቹን ሁሉ ለዘላለሙ ከባርነት ነጻ አወጣቸው ዘንድ፣ ሀጢአታቸውንም አስተሠርይላቸው ዘንድ፤ ዳግመኛም ወደ ገነት አስገባው ዘንድ  ሥጋየን እና ደሜን ቁርባን አድርጌ አሳርጋለሁ»  ዝማሬ ዘሐሙስ ገጽ 87
 በዚህ በቅዱስ ያሬድ ድርሰት፣ ጌታ ስለ ኃጢተኞች የተነቸነከሩ እጆቹን፣ የፈሰሰው ደሙን የተቆረሰው ሥጋውን ለአብ እንደሚይሳያላቸው፤ አዳምና ልጆቹን ከባርነት ነጻ ለማውጣት የሞት ዋጋ መክፈሉን እየዘረዘረ በርሱ በኩል ወደ አብ የሚመጡትን ጠበቃ እንደሚሆንላቸው የሚናገር ነው። የቅዱስ ያሬድ ሃይማኖት ከሐዋርያት እምነት አንድ መሆኑን ለመረዳት ከቅዱስ ያሬድ ድርሰት ጋር የሚመሳሰለውን የሐዋርያት ትምሕርት ደግሞ እንምልከት

«ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ» ዕብ 924

 ቅዱስ ያሬድ ወልድን እጆቼን እግሮቼን ተመልከት ብሎ ስለኃጢአኞች ጨኸ ብሎ የመሠከረው በቅዱስ ጳውሎስ «በእግዚአብሔር ፊት ስለኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ ሰማይ ገባ» ከሚለው ጋር አንድ ነው። ዛሬም ወልድ በአብ ቀኝ ሆኖ ሲታይ በርሱ በኩል እኛም ያመንበት እንደምንታይ የሚናገር ነው፤ ነገር ግን አሁንም በየጊዜው ልመና ያቀርባል ማለት እንዳለሆነ ግልጥ ነው። ይታያል ማለት እና ይለምናል ማለት አንድ አይደለም።

ሐዋርያው ዮሐንስ «ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ»ይላል 1ዮሐ 21-2 ጌታ ጠበቃ የሚሆነን ቅዱስ ያሬድ እንድተናገረው በፈሰሰው ደሙ በተወጋው ጎኑ በተቸነከሩት እጆቹና በአጠቃላይ በመከራውና በሞቱ ነው። ሞቱ ስለኛ ይከራከራል ማለት እንጂ ዛሬም በአብና በወልድ መካከል ክርክር አለ ማለት አይደለም።

 የመጽሐፈ ሰዓታት ደራሲም «ፍኖት ለኀበ አቡሁ አንቀጽ ዘመንገለ ወላዲሁ» ወደ አባቱ የሚወስድ መንገድ፣ ወደ ወለደውም የሚያስገባ በር በማለት አንዱን ሃይማኖት መስክሯል። የቅዳሴ ሐዋርያት ደራሲ ደግም «ወናሁ ደመ መሲሕከ ይኬልህ ሕየንቴየ»  የልጅህ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ እኔ ይጮኻል ብሏል። እንግዲህ ጥንታዊውና አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠው ሃይማኖት ከዚህ በላይ እንዳየነው ነው «በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሔር» ማለት ነው።

 አሁን እየተሰበከ ያለውና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መስሎ ለዛሬው መከራችን ምክንያት የሆነብን ግን ከዘርዓ ያዕቆብ በኋላ በፖለቲካ የበላይነት የተጨመረብን ሌላ ሃይማኖት እንጂ ሐዋርያዊውና ኦርቶዶክሳዊው አንዱ የአብቶች ሃይማኖት አይደለም። የአባቶቻችን ኪዳን እርሱም በክርስቶስ ደም የተመሠረተው ሃይማኖት ሲሆን፤ ሌላ ኪዳን ተሰጥቷል ብለው የሚሰብኩ ሰዎች በመቶዎች የሚቆጥሩ ኪዳኖች አሏቸው። ይህም አንድ ሃይማኖት የሚለውን የአባቶች እምነት ያፈርሰዋል።

ለምሳሌ «ዝክርህን የዘከረ፣ ደብረ ሊባኖስ የተቀበረ በስምህ የተማጸነ እስከ ሰባት ትውልድ ድረስ ኃጢአቱ ይሰራያል ስምሽን የጠራ፣ ቤተ ክርስቲያንሽን የተሳለመ ባማላጅነትሽ የተማመነ፣ በስምሽ ስሙን የሰየመ፣ ወዘተ ይድናል » የሚለው ኪዳን ሌላ ሃይማኖት ነው። በወልድ ያመነ ይድናል የሚለውን አንድ ሃይማኖት የሚቃወም ክህደት ነው። ለዚህ ይህ የኦርቶዶክስ እምነት ሳይሆን የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት አዲስ ሃይማኖት ነው።

 አንባቢ ሆይ የኦርቶዶክስን ጥንታዊ ሃይማኖትና በዘርዓ ያዕቆብ የተፈጠረውን የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ሃይማኖት ለይታችሁ እንድታውቁልን እንወዳለን። አንዳድ አላዋቂ የሆናችሁ ፕሮቴስታንቶችም ኦርቶዶክስን ሳትረዱ ከመተቸት እንድትታቀቡ ጥሪ እናቀርባለን። ትንሽ እውነት የተገለጠላችሁ ኦርቶዶክሶችም ሁሉንም ስሕተት አድርጋችሁ ከማየት እንድትቆጠቡ ስንል እናሳስባለን። የአባቶቻችንን እመነት ከድርሳኖቻቸው ተመልከቱ፣ የሐሰተኞች ትምህርት ቀብሮት ስለኖረ እንጂ ንጽሕና ያለው እውነት ነው። ዛሬ ይህን ኦርቶዶክሳዊ እውነት እየቆፈርን ከተቀበረበት በማውጣት ላይ ስለሆንን የጠራውን ብቻ እንድትይዙ እንመክራለን። በሐስተኞች የተሸፈነው የአባቶች እምነት በሕይወት አለ አልሞተም። ዛሬም አንገት ደፍተው የሚኖሩ በርካታ አስተማሪዎችም አሉት፣ የሰሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት ሃይማኖትና የእውነተኛው ኦርቶዶክስ እምነት ተለይቶ የሚታወቅበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፣ እንዲህ ተደባልቆ መኖር አብቅቷል። እውነቱ ይወጣል፣ የእግዚአብሔር ክብር ይገለጣል፣ የኢትዮጵያ ትንሣኤም በቅርቡ ይመጣል አሜን!
 ሁላችንም አንድ ጊዜ ለቅዱሳን ፈጽሞ ወደ ተሰጠው ሃይማኖት እንመለስ!
ተስፋ ነኝ

37 comments:

 1. Thank you so much! Tesfa. One thing we should understand is that our church should loudly and proudly start saying "JESUS IS LORD." Let say some from the bible: When Jesus appeared to Thomas and showed him the wounds in his hands, feet and side, Thomas exclaimed "My Lord and my God!" (Jn 20:28). This profession "Jesus is Lord" was very common among the early Christians. St. Paul also constantly referring to Jesus as the "Lord", or he addresses his converts "in the Lord". Finally, In 1 Corinthians (12:3) he says, "No one can say 'Jesus is Lord' unless he is under the influence of the Holy Spirit." Paul claims that he is not preaching himself but "Christ Jesus as the Lord" (2 Cor 4:5). The Acts of the Apostles speaks a number of times about the first Christians being "baptized in the Lord".

  If you want to know about me "I am a true Christian came from the family worshiping God." Please let us give our self to the Lord Jesus; we are in the 11th hours.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yhn ke irdata sinde gar nechoch yemegebushn titesh wede iwnetu temelesh! Zm blesh bematawkiw guday wst gebtesh atalakuchi! Mejemeriya iski rasishin temelkech libe bis!

   Delete
 2. mesthafe seatat teret new sitlu alneber? Zare endet ewunetegna hone? Ebakachihu ke ahun befit yestafachihutnim eyasebachihu.

  ReplyDelete
 3. አንተ መናፈቅ ለራሰሀ

  ReplyDelete
 4. ከላይ ፎቶአቸውን የለጠፍካቸው አባቶች "ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገ እመረዋለሁ "የሚለዉን አስተምረዉን አስተላልፈዉለናል እኛም ተዋህዶዎች እየፈጸምነው እንገኛለን።አሁን ያሉት ፎቶአቸውን የለጠክባቸው አቡነ መልከ ጸዲቅም የሚያስተምሩን ይህንን ነው።ለቅዱሳን የተሰጠውን ቃል ኪዳን እንድናምን።አንተ ከየትኛው ነህ?እጅግ ግራ አጋቢ ሆንክ እኮ።ወይ ፎቶአቸውን አንሳ፤አለበለዚያ እነርሱ በሚያስተምሩንና ጠብቀው ያስተላለፉትን ትምህርት ተቀበል እመን።

  ReplyDelete
 5. አባ ሰላማዎችም የእኛን አስተያየት ማጥፋት ፈለጋችሁ:: እውነቱን ለምን እንደብቃለን እናንተ የሚደግፍ ብቻ አታውጡ:: ምነው የእኔን አስተያየት በልታችሁ አስቀራችሁት?

  ReplyDelete
 6. ሰላም ወገኖች የዚህ ዌብ ሳይት አዘጋጆች የኦርቶዶክስ እምነት የሚሉት የክርስቶስን አማላጅነት (ክብር ይግባውና እርሱ እንደማይለምን ነግሮናል) እና ቅዱሳንን ማቃለል ብቻ ነው? ክርስትና እኮ ብዙ የሚባልለት ሃይማኖት ነው:: የእግዚአብሔር ቃልም ብዙ ነው ለሰውም የሚያስፈልገው ብዙ መልካም ቃላት አሉ:: ምነው እናንተ ለጥርጥር የሚዳርግ ነገር ላይ ብቻ አተኮራችሁ::
  የዚህ ዌብሳይት ጽሁፍ እንደተመለከትሁት በሚከተሉት ርእሶች ዙሪያ ያጠነጥናል
   ማህበረ ቅዱሳንን በማስጠላትና በማጥላላት:: እንደ እኔ እንደ እኔ ማህበረ ቅዱሳን የሚነቀፍበት ነገር ቢኖርም እንኳን እናንተ እንደምትሉት ግን አይደለም
   ዘርአያቆብን መስደብና የቤተ ክርስቲያንን የቅዱሳንን አማላጅነት ትምህርት እርሱ እንዳመጣው አድርጎ መናገር:: እኔ ስለዘርአያቆብ ብዙ ጥናት ባላካሄድም አንድ ልትረዱት የሚገባ ነገር ግን ሌሎች ኦሬንታል ኦርቶዶክሶችን የምስራቅ ኦርቶዶክሶችን እና ካቶሊኮችን ስለቅዱሳን ምልጃ ማን አስተማራቸው?ዘርአይ ያቆብ እንዳልሆነ ግን ታውቁታላችሁ:: ለቅዱሳን ክብር መስጠትን እና ቅዱሳን ስእላትንስ መጠቀም ገና በ2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በግበበ ምድር ውስጥ በካታኮምብ ዋሻ እንደተጀመረ ለምን ማወቅ አልቻላችሁም? መጽሐፍስ የሚለውን ለመስማትና ለማገናዘብ ምነው ህሌናችሁን አዘገያችሁ?
   በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚታመነውን አብዛኛውን ትምህርት ማጥላላት:: በእርግጥ ይህንን የሚያደርጉ ሰዎች ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ናቸው ባንልም:: አንዳንድ ስህተቶች ካሉ ለሲኖዶስ ማቅረቡ የሚበረታታ ቢሆንም ይህ ዌብ ሳይት ግን ጭልጥ ያለ የፕሮቴስታንት ትምህርትን የኦርቶዶክስ እምነት ነው ብሎ ያቀርባል::
   የዚህ ዌብ ሳይት አዘጋጆች ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል ያሰቡ ይመስላል:: ምንም እንኳን አንዳንድ ችግር እንዳለባቸው ቢታወቅም ደጀ ሰላም የሚያብጠለጥላቸው አቡነ ፋኑኤልና እነ በጋሻው የዚህን ዌብሳይት እምነት የሚጋሩ አይመስለኝም:: ሆኖም ግን ይህ ዌብሳይት ለእነርሱና ለፓትሪያርኩ ደጋፊ ሆኖ ሲቀርብ ይታያል:: የእነርሱ ደጋፊ ከሆነና እነርሱም በዚህ ዌብ ሳይት የሚወጣውን የሚቀበሉ ከሆነ ችግር አለ ማለት ነው:: ሆኖም ግን ይህ ዌብሳት ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል ካለው ጽኑ አቋም የተነሳ ደጋፊ መስሎ ይታያል እንጂ እምነቱን ሰዎቹ የሚጋሩለት አይመስለኝም::

  ምክር የዚህ ዌብሳይት ተመልካቹ ብዙ ይሆን ይሆናል ተከታይ ግን እንደማይኖረው ልታውቁ ይገባል:: ኦርቶዶክሳዊያን የምናምነውን የምናውቅ ነን:: አንድ እውነት ተናግሮ አራት ውሸት የሚናገረውን የአባ ሰላማን ዌብ ሳይት ሁልጊዜ ባያትም ተከታዩኧ ግን ልሆን አልችልም::
  ወደ አባቶቻችን እምነት እንመለስ:: አወን እንመለስ ሁሉንም ይዘን እንመለስ

  መልካም ጊዜ :: ዘእግዚእነ

  ReplyDelete
 7. “አሁን እየተሰበከ ያለውና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መስሎ ለዛሬው መከራችን ምክንያት የሆነብን ግን ከዘርዓ ያዕቆብ በኋላ በፖለቲካ የበላይነት የተጨመረብን ሌላ ሃይማኖት” ብለሃል
  በየብሎጉ የምታጥላላው የ ነቢዩ ኤልያስ፣ የ ቅዱስ ጳውሎስ ፣የአባ እንጦንስ፣ የአባ ጳኩሚስ ፣የአባ አረጋዊና የሌሎች ንጹሃን አባቶች እና እናቶች የምንኩስና ሕይወትስ የተጀመረው በ ዘርዐ ያዕቆብ ነው ???
  ወይስ ምዕራባውያን ስለሚያንቋሽሹት ? ወይስ መነኮሳት ላልሆናችሁ ጵጵስና ተሰጥቶ ቤተክርስቲያንን በመምራት ጠላቶች የምትሉዋቸውን ገብታችሁ መበቀል ስላልቻላችሁ(አስባረሩን እያላችሁ ሁልጊዜ ስለምትከሱዋቸው ነው)???
  ወይስ ወደልቦናህ በመመለስ ላይ ነህ ?
  ስለ ለቅዱሳን የሚሰጥ ቃል ኪዳን እስከ ሰባት ትውልድ ብቻ ሳይሆን እስከ ሺሕ ትውልድና ዘርንም በሙሉ እንደሚያስባርክ ልብ ያላልከው እንደሆነ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ተፅፎ ይገኛል፡፡
  ስለ ቅዱሳን ማመንም ትዕቢት ልቦናችሁን እያደነቆረው ለመስማት ዝግጁዎች አይደላችሁም እንጂ ከክርስቶስ ማመን ጋር የማይገናኝ መሆኑ ሳይነገራችሁ ቀርቶ አይደለም፡፡
  አስቲ ቀጥሎ ያለውን እምነት እይና ጽሑፍህን መዝንበት፡፡
  ዘጸ 14፤31 እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ።
  አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር አስተዋይ ልቦናን ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
 8. To G/Micheal: I think you are out of the line. I don't have doubt that you have never read bible.

  "ስለ ለቅዱሳን የሚሰጥ ቃል ኪዳን እስከ ሰባት ትውልድ ብቻ ሳይሆን እስከ ሺሕ ትውልድና ዘርንም በሙሉ እንደሚያስባርክ ልብ ያላልከው እንደሆነ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ተፅፎ ይገኛል፡፡"

  let us get the reference from the bible and believe on kudusan , instead of the son of God (lord Jesus). I am telling again men you don't have a place in heaven if you take the Lord Jesus your only way to God.

  Tigist

  ReplyDelete
 9. እውነተኛ የክርስትና መልእክተኛ የሆነ እስቲ መጀመሪያ በውጭ ያሉትን ይመልስ። ገድሉን ተረት ተረት ፀሎቱን ባእድ አምልኮ ብሎ ባዶ ማስቀረት ንቦችን በጭስ የሚያባርር ማር ቆራጭን ይመስላል። እስካሁን የውስጡን ቦርቧሪ እንጂ የውጭውን ጠሪ አላየንም። ይህ ብቻ ክፉውን ከደጉ እውነተኛውን ከሀሰተኛው ለመለየት በቂ ነው። በውጭ ያሉት ግን ብዙ ናቸው። ልዩ ልዩ አይነት እምነት ያላቸው የሌላቸውም ናቸው።

  ReplyDelete
 10. እኔ ግርም የሚለኝ በጨለማ ውስጥ ተቀምጦ እዳከረ ሳለ ቲኒሽ እንኳ አለማሰቡ ነው። ለሱ በቃ እምነቱን አውቋል።
  በናትህ እስኪ please read about the biography of other foreigners (may be you may believe them because they are outsiders) who spent their time dedicatedly to find God. I think you had some theology in MS or above from somewhere, so do more research and save your self first, I think Father Lazarous from Australia, he did I guess 4 MSs in theology, history, literature and philosophy. He did all this to find a clue about the true God, but finally get lost. The reason was all his research was just plain as usual read and write without any prayer, respect and devotion with the love of God. Fortunately God showed him the true path after 40 years lost. So please first pray for what you are doing. I scare for your final destination too. By the way I am professional in hard science stream but not theologist like you but learned everything from my true fathers starting way back from my child hood. Though I am living far away my church, the love of my church burns me like fire. I bleed too much when I see all your abusing comments.
  Your comment about Zeyakob, you wrote all this staff may be drinking coffee, ... or what ever, but he wrote all those things after weeks of 'Subae' with the help of the holy spirit.

  ReplyDelete
 11. To Tigist
  Have you read
  ዘጸ 14፤31 እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ።
  Does it mean they have replaced The GOD by Mussie? Please think again and again.
  Why you quote ስለ ለቅዱሳን የሚሰጥ ቃል ኪዳን እስከ ሰባት ትውልድ ብቻ ሳይሆን እስከ ሺሕ ትውልድና ዘርንም በሙሉ እንደሚያስባርክ ልብ ያላልከው እንደሆነ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ተፅፎ ይገኛል፡፡ for the above case. Are confused or you need to confuse readers. May GOD forgive you.
  If you need reference for the concept you quoted read the ff.
  ዘጸ 20፤6 ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።
  ዘፍ 22፡18 የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ ቃሌን ሰምተሃልና።
  ዘ ጸ 3፤16 ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ። እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ። መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፥ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ
  ሉቃ 1፤54-55 ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፥ ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም ምሕረቱ ትዝ እያለው እስራኤልን ብላቴናውን ረድቶአል።
  አሁንም በዘመናችን እስራኤል ዘነፍስ የሆንን አኛን ለቅዱሳኑ ስለ ገባላቸው ቃልኪዳን ድንቅ ሥራውን ሲያደርግልን ይኖራል፡፡ ጠላት ግን ዘወትር ምክንተ ጥፋቶችን ያሰማራል ግን ይሸነፋል፡፡
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ
  እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ

  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ

  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ
  በእንተ ቅዱሳን መሐረነ ክርስቶስ

  ስንል እንኖራለን ፡፡

  May The Almighty God open Your eyes! አሜን

  ReplyDelete
 12. ቅዱስ ያሬድንማ ካነሳህ ስለእመቤታችን ክብርና ምልጃ በሰፊው ተናግሮ የለምወይ?
  ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል ይእቲ ተዐቢ አምኪሩቤል ወትፈደፍድ እምሱራፌል።
  ድንግል ማርያም የደናግል መመኪያቸው ናት እርስዋ ከኪሩቤል ትበልጣለች ከሱራፌልም ከፍ ከፍ ክትላለች።
  ሰአሊ ለነ ማርያም አምነ ወእሙ ለእግዚእነ ወልድኪ ይምሐረነ ወመዋርስቲሁ ይረስየነ።
  ማርያም እናታችን የጌታችንም እናት ልጅሽ ይምረን ዘንድ ባለምዋሎቹም ያደርገን ዘንድ ለምኝል። እያለ የዘመረው ስለድንግል ማርያም ክብርና አማላጅነት ነው።
  ቅዱስ ኤፍሬምንስ እንዴት ታየው ይሆን?

  ReplyDelete
 13. Thank you for your response G/Micheal, what you are telling me that the road to God is through "Kidusan." But you did not give me any reference from the new testament.

  But I have one for your "St. Paul for Rome people clearly said that the road to the Almighty of God is only through the Lord Jesus Christ." My kids even know that. I do not understand why we Ethiopian need always short cut, short cut to be wealthy, short cut to get any of our demand, and short cut to remove our sin through "Kidusan" it is very shame. we call our Ethiopia is a christian island, it is absolutely false, it is can not happen unless a person like you change and receive the lord Jesus your Savior.

  finally , I am telling you that my eyes are opened, the remain one is yours. Read the bible! not teret teret men.

  Tigist

  ReplyDelete
 14. tigist God Himself tells us to use prophets to go to Him.Zefetret 20:7

  ReplyDelete
 15. @Tigist yanchi aynet dekama sew silemisemachew new aba selamawoch mitsfut enji yetewahdon lijoch miyateratir tenkara neger adelem eyetsafu yalew. orthodox tibetbet enji sewu seol biwerd entorotos bigeba gid yelachewum.min meserete emnet rasu endeminageru giltse adelem.ya demo minfikinam (keflo mamen)adelem.matfat bicha new alamachew.lanchi mels mestet yichalal gin lemeredat filagotum yalesh atmesyim .demo gobez yehonsh endaymeslish alwakinetsh bicha ketenegeresh yibekal.

  ReplyDelete
 16. To Anonymous: I can not understand most of the comment,but I read one sentence it said that "lanchi mels mestet yichalal gin lemeredat filagotum yalesh atmesyim .demo gobez yehonsh endaymeslish alwakinetsh bicha ketenegeresh yibekal."

  let me ask you dear anonymous! what is wrong with my comment? let me give you some hint how I got the son of God: in your daily prayer ask the Almighty of God to show the road to him. if your daily prayer is through Kudsan ask them to show you the road to Jesus. finally, I am proudly telling you that my house and me worship God, I doubt you believe in God. Next time let us your comment in legibly and sensibly, the son of God and the mother of the most high Jesus give you the wisdom to know the son of God that is Jesus of the Nazareth.
  Tigist

  ReplyDelete
 17. ትዕግስት መናፍቅ ነች። ለምን? ተጠራጣሪ ነችና። እምነት ለሷ "ተረት ተረት" ነው። ።

  ReplyDelete
 18. To Anonymous: If loving the son of God and take him as a savior consider as a protestant, yes! I am a protestant. let me tell you men, you are stupid and nonsense! religious will not take you to heaven, only the your relation to God. Again you are insecure! I can teach you what orthodox means but I do not have time for a person like you full of your life reading tert tert (yeweshet gedele), for your information, I accept gedele only written by Jesus dispels, for example all Miraculous St Mary had done with her infant son Jesus and a lot other at Egypt and Israel, however it is not written in the holly bible, I also ask her help during my prayer. let me add some but I the child of the most high God will not accept all tert tert written by Debeter (yehant abatoch), I support the movement of Tehadeso, I hope they will bring change in Ethiopian Orthodox Church. JESUS IS LORD!
  Tigist

  ReplyDelete
 19. ትዕግስት ትናገራለች በትእቢት። የትእቢት አባቷ ግን ሰይጣን ነው።

  ReplyDelete
 20. እኛስ በተግባር አይተናል……እንዘን አይነ ልቦናቸው ማየት ለተሳነው…….
  “እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን ፡ የተጎዱ ቤተክርስቲያናትን ሲያስጠግን ፣ ገዳማትን ሲረዳ ፣ የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ሲያስከፍት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ተማሪወችን በብዙ ነገር ሲያግዝ ፣ በገጠር ላሉ ምእመናን ወንጌልን በነፃ ሲያስተምር ፣ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ሲያዘጋጅ ፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪወችን ከመናፍቃን ይጠብቅ ዘንድ ሰብስቦ ሲያስተምር ፣ በግእዝ ብቻ ተፅፈው የነበሩ ቅዱሳን መፃህፍትን ወደ ተለያዩ ቋንቋወች በመተርጎም ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ፣ መንፈሳዊ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን በየጊዜው ለአንባቢያን ሲያደርስ ፣ ስርአተ ቤተክርስቲያን ይከበር ሲል ፣ ስርአቱን የጠበቀ መዝሙራትን ሲያወጣ ፣ ቤተክርስቲያንን ለመውረር የሚተጉ መናፍቃንን የከፋ ግብራቸውን በማስረጃ እያጋለጠ ቤተክርስቲያንን ከተኩላወች ሲጠብቅ ፣ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን - - - ይህን ሁሉ ስለመስራቱ በተለይም መናፍቃን እንዳሻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እንዳይቦርቁ ዘብ ሆኖ በንቃት ተዋህዶን በመጠበቁ መናፍቃንና መሰሎቻቸው ይህን ማህበር ለማጥቃት ቢነሱ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን መናፍቃንንም አናጣቸውም፡፡”

  ReplyDelete
 21. "you are stupid and nonsense!" you said.How dare you teach about Jesus to orthodox. anyways I am not worried for your insulting us. you can confess and get merry from GOD.but I doubt if you are humble enough to ask His forgiveness of our Lord through st.peter(the priest).as you said being religious only may not take us to heaven but it is a way.Don't forget there are religions like protestant that lead us to hell.

  ReplyDelete
 22. yes, if you don't know Jesus , you are stupid and nonsense. Don't proud by saying that "Ethiopia is a christian country." it is far from the truth, Unless you guys are accept our lord Jesus Christ in your faith, you are counting like a Muslim or mehafekan. tegest said correct about you guys, Thank you TG.

  ReplyDelete
 23. @Tigist and her friends:- It is you Guys proud of saying "I know Jesus" while you don't know in practice. who teaches you to insult while you are preaching Gospel? for you, loving Jesus is saying "Jesus is Lord" many times.we know and believe Jesus is LORD but you deny his power. I feel His love,His Power and His mercy on me when our father call him Our Lord,The GOD,The Holy Savior Jesus Christ. b/c they are not cheaters like you guys.100% His name is preached in EOTC church with humble heart and full of respect.please don't talk as if you know Jesus but we are far from the truth.who are you? I thought devil spirit is using people like you to call His name senselessly and make others disappointed with.unless you or your back supporters have hidden agenda ,willn't start preach Jesus for EOTC christians? Don't worry we have learned enough when, how and where to call Him,Praise to be for His name Our Lord,The GOD,The Holy Savior Jesus Christ(please as I wrote His name patiently read it patiently and slowly feeling He is Lord,GOD,and Holy Savior... respect and love starts here).

  Ayne libonachinin yabralin.
  zetewahdo.

  ReplyDelete
 24. Are you sure me and my friends denied his power? In your assumption devil spirit playing or has a role in christian life, like me. Thanks God you accept you too close to say that "JESUS IS LORD." you just around that , do not afraid of saying that JESUS IS THE LORD OF LORD. AMEN!

  I AM THE DAUGHTER OF THE MOST HIGH GOD ( JESUS) , I will not stop call Jesus is Lord, until I die.

  ReplyDelete
 25. Tigist said..."I can teach you what orthodox means" it is because
  "የደንቆሮ መንፈስ ምንኛ ታደለ
  ብልጥነት አላጣም ሞኝ እየመሰለ
  ምኑንም ሳያውቀው እንደው በደፈና
  ሁሉንም ያወቀ ይመሰለዋልና።"
  ከከበደ ሚካኤል ግጥሞች

  ReplyDelete
 26. mat-07
  21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

  ReplyDelete
 27. Not every one that saith unto me, Lord, Lord, shall enter into the kingdom of heaven; but he that doeth the will of my Father which is in heaven.Mat 7:21
  @Tigst take care not to be among those...
  I am not blaming for your saying 'Jesus is Lord' what I am trying to advise you is:-
  Atasmesyi, lelawunm christosn atakewum,alberalhim,wengel algebahim ,teret teret new mitakew eyalsh atitabeyi, tihtinana fikir yinurish.

  it is not to late to return to your mind and listen what GOD is talking to you using US.

  Bemhretu Ayleyen.
  Bechristos wedmish.

  ReplyDelete
 28. I am tigist, you guys are living with devils. Bad spirit controlled your life. Again you don't like the name of Jesus to be called by christian, by the name of Jesus the devil spirit order you to be out of these guys. JESUS IS LORD!!!!!!!!!!!!!!-----
  TIGIST

  ReplyDelete
 29. "Not every one that saith unto me, Lord, Lord, shall enter into the kingdom of heaven; but he that doeth the will of my Father which is in heaven.Mat 7:21" so you advice her to stop calling Jesus? I doubt you are Islam, or betenkua yemyamen family new yasadegeh. (you raised by a family do not believe by God)I agree with her" Jesus Christ is lord."

  ReplyDelete
 30. @Tigist and her friends
  Is there any book which you call "teret teret" which denies or doesn't mention Jesus is lord?
  I beg you to tell me at lest one.

  1co-12
  ምዕራፍ 12


  3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።
  ..............
  14 አካል ብዙ ብልቶች እንጂ አንድ ብልት አይደለምና።

  ..........
  23 ከአካልም ብልቶች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፥ በምናፍርባቸውም ብልቶቻችን ክብር ይጨመርላቸዋል፤
  .............
  26 አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።

  27 እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።

  28 እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን፥ ሦስተኛም አስተማሪዎችን፥ ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን፥ ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ፥ እርዳታንም፥ አገዛዝንም፥ የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጎአል።

  ReplyDelete
 31. To Anonymous: do you want to know , okay today I will give you " Gedele Tekelhaimanot" Read chapter 48 and 54 paragraph 22 and 23. I do not want to say any thing , because the website is free for any reader.if other religious follower read it they will laugh on us. please! please let go back to our original doctrine. I am not protestant, I can be a protestant I found Jesus in our holly church orthodox. finally, I am telling you , I respect and love Abuna tekelehimanot, but the book written about him is far from the truth. please read the reference.

  leholachenem Geta lebona yesten!

  ReplyDelete
 32. mat-10

  40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

  41 ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።

  42 ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።

  joh-14

  12 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፥
  ..........
  20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።

  do you think a book like this "teret teret"?
  that is why you are መናፍቅ(ተጠራጣሪ)

  ReplyDelete
 33. ።ፍርድ።

  mat-25
  31 የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤
  32 አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥
  33 በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።
  34 ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
  35 ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
  36 ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
  37 ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
  38 እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
  39 ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
  40 ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

  ReplyDelete
 34. ከላይ ፎቶአቸውን የለጠፍካቸው አባቶች "ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገ እመረዋለሁ "የሚለዉን አስተምረዉን አስተላልፈዉለናል እኛም ተዋህዶዎች እየፈጸምነው እንገኛለን።አሁን ያሉት ፎቶአቸውን የለጠክባቸው አቡነ መልከ ጸዲቅም የሚያስተምሩን ይህንን ነው።ለቅዱሳን የተሰጠውን ቃል ኪዳን እንድናምን።አንተ ከየትኛው ነህ?እጅግ ግራ አጋቢ ሆንክ እኮ።ወይ ፎቶአቸውን አንሳ፤አለበለዚያ እነርሱ በሚያስተምሩንና ጠብቀው ያስተላለፉትን ትምህርት eko newe,

  ere sewene mawenabede tsedeke aydelm, wenegel bemawenabede aydel yemisebekewe...

  gin dese yemilewe gebre aberochahehu mane endehonu eyasayachehune yemeselegnale...

  ReplyDelete
 35. Ante tekula! Awkenibachihuwa! Geez yetenagerk meslehmerzihn litzera! Merzu lerasih yhun! Mamenina makber leyteh yematawk lehod yetefeterk hula! And ken EGZIABBHIER rasu yiferdbachihuwal! Inante yemenafkan telalakina temetsiwach hula! Haymanotachihu hodachihu slehone haymanotn tewu kenante gar ayhedm!!!

  ReplyDelete