Friday, December 16, 2011

ተጠንቀቁ - - - Read PDF

ማህበረ ቅዱሳን እነማን እንደሆኑ ብዙ ሰዎች ለይተው ማወቅ እንደማይችሉ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስን ጠንቅቀን ብናነብ ግን ማህበረ ቅዱሳንን ለይተን እንድናውቃቸው ያደርገናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዳለ የማህበረ ቅዱሳንን ትምክህት፣ ውጫዊ ሥራት፣ የአምልኮ መልክ የሚመስለውን ሁሉ በቃሉ እንገመግማለን። በዚህ ጽሑፍ እኛንም የሚገሥጽ እንድንጠነቀቅ እና እራሳችንን ከፈሪሳዊነት ጠባይ እንድንጠብቅ የሚመክር መልእክት እናገኛለን። የማህበረ ቅዱሳንም አባላት ሆኑ ተሃድሶዎች፣ ወይም በክርስትና ሃይማኖት እንኖራለን የሚሉ ሁሉ እራሳቸውን ይመረምሩ ዘንድ ይህ መልእክት ያሳሳባል። በተለይም ማህበረ ቅዱሳን የሚባሉ የፈሪሳውያን ቡድን ለማወቅ እና ከነርሱ ትምህርት ለመጠንቀቅ ይረዳናል ብለን ስለአመንን እንዲህ አቅርበነዋል።

በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ከሶስት አይነት እርሾዎች እንዲጠበቁ ደቀ መዛሙርቱን ሲያስጠነቅቅ እናያለን::
1. ከሄሮድስ እርሾ (ማርቆስ 8፥15)
2. ከሰዱቃውያን እርሾ (ማቴዎስ 16፥6)
3. ከፈሪሳውያን እርሾ (ማቴዎስ 16፥6)
እነዚህ ሶስት አይነት ክርስቲያኖችን ይመስላሉ/ይወክላሉ።
የንጉስ ሄሮድስ እርሾ አለማዊነት ነበር። ማርቆስ 6፥20 ላይ ሄሮድስ የመጥምቁ ዮሐንስን ትምህርት ማዳመጥ ይወድ እንደነበር እናነባለን። ንገር ግን ከሁለት ቁጥር በኋላ ደግሞ ሰሎሜ ስትደንስ ማየት እንዳስደሰተው እናያለን። ሰሎሜ በምትደንስበት ጊዜ የለበሰችው ልብስ ምናልባት ሰውነቷን በደንብ የሚያሳይና እንቅስቃሴዋም የወንድን አይን የሚስብ ሊሆን ይችላል።
በአሁኑ ጊዜ እንደዚህ አይነት ክርስቲያኖች አሉ። እሁድ ጠዋት የሚደነቅ ስብከት ሰምተውና ተደስተውበት ከሰአት በኋላ ደግሞ መጥፎ የሆነ ፊልም ያያሉ። ሄሮድስ የዮሐንስ መጥምቁን ስብከት ማዳመጥ የወደደበት ምክንያት የዮሐንስ ስብከት እንደፈሪሳውያን የሚያሰለች ሳይሆን ነገር ግን በጣም የሚደነቅና እንደ እሳት የተቀጣጠለ ነበር። ጥሩ ስብከትን ማዳመጥ አንድን ሰው መንፈሳዊ ሊያደርገው አይችልም። ብዙ ጊዜ አለማዊ ክርስቲያኖች አይመጻደቁም። አለም የምትሰጠውን ደስታ ሁሉ ይደሰቱበታል ደስታቸውንም ደግሞ አይደብቁም።

   የሰዱቃውያን እርሾ የስሕተት ትምህርት ነበር። እምነታቸው ነጻ/ሰፊ ወይንም ማንንም የማይቃወም (liberal) የሚል አስተሳሰብ ላይ የተመርኮዘ ነበር። በመላእክት, በተአምር፣ በሙታን ትንሳኤና በመንፈስ አያምኑም ነበር። በአሁኑም ጊዜ እንደዚህ ያሉ ከመንፈሳዊው አለምጋ የማይገናኙ ክርስቲያኖች አሉ። እግዚአብሔር ባሁኑ ጊዜ ምንም አይነት ተአምራትን ያደርጋል ብለው የማያምኑና መንፈስ ቅዱስ ለክርስቲያኖች የሚሰጠውን መለኮታዊ ስጦታ የማይቀበሉ ናቸው።

  የፈሪሳውያን እርሾ ግን ሲጀመርም በመመጻደቅ ነው። በሀይማኖት ትምህርታቸው አክራሪ የሆኑና ጽድቃቸው በውጪያዊ ሕይወታቸው ላይ ብቻ የሚታይ ነበር። ኢየሱስ እንኳ እነዚህን ሁለት ነገሮች አረጋግጦላቸዋል (ማቴዎስ 23፥2፣ 25)። አስራት ይሰጣሉ ይጸልያሉ ይጾማሉ ውጭያዊ የሆነውን የሕግ ስርአት ሁሉ ይጠብቃሉ በሀይማኖት ስራዎችም ላይ ይሳተፋሉ። ባሁኑ ጊዜም ልክ እንደዚህ ያሉ ክርስቲያኖች አሉ። የሚጾሙ የሚጸልዩ ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ አስራት የሚሰጡ ነገር ግን ልክ እንደፈሪሳውያን የሆኑ፣ ኮናኞች ክፉዎች ግብዞች የሰውን ሕይወት የሚሰልሉ የሃይማኖት ፖሊስ ሆነው የሚያስሩ አሉ ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ቡድን ይህን ይመስላል። አንዳንድ ክርስቲያኖች የሶስቱም አይነት እርሾ በውስጣቸው ይኖራል።

  ከላይ የተጠቀሱትን በመመልከት ኢየሱስ የነበረው ትልቅ ግጭት ከሄሮድሳውያን ወይም ከሰዱቃውያን ጋር እንዳልሆነ ማሰብ ይቻላል። ነገር ግን ግጭቱ ከነርሱ ጋር አልነበረም። ኢየሱስ የነበረው ችግር ሥርዓትና ወግን ከሚሰብኩ ከአክራሪ ፈሪሳውያን ጋር ነበር። እንደነሱም ዓይነት ሰዎች ነበሩ ኢየሱስን ለመስቀል ቆርጠው የተነሡት። በአሁኑ ዘመን በቤተክርቲያን ውስጥ ሰዱቃውያንና ሄሮድሳውያን የፈሪሳውያንን ያህል አደገኞች አይደሉም። ሄሮድሳዊ ምናልባት ሲኦል ይገባ ይሆናል ነገር ግን ሌላን ሰው ወደ ሲኦል አይመራም ምክንያቱም አለማዊነቱ ስለሚታወቅ በርሱ ትምህርት ማንም ሊሳሳት አይችልም። በሰዱቃውያንም ትምህርት ማንም መንፈሳዊ ናቸው ብሎ የሚሳሳት አይኖርም ምክንያቱም በተአምራትም ሆነ በሙታን ትንሳኤ አያምኑም ነበር።

   ከሁሉም አደገኛ የሆኑት ባሁኑ ጊዜ በቤተክርስቲያን ውስጥም ሆነ በኢየሱስ ጊዜ ፈሪሳውያን ነበሩ። የሃይማኖት ትምህርትን በደንብ ያወቁ እና የሰው ሥራትን የሚሰብኩ ቅድስናቸው ግን በሕግ ስራ ስርአቶችን በመጠበቅ ላይ የተመረኮዘ ነበር። ጽድቃቸውም የመንፈስ ቅዱስ ደስታና ሰላም የሌለው ነው (ሮሜ 14፥17)። እንደዚህ ያሉ ክርስቲያኖች በጣም አደገኞች ናቸው ምክንያቱም ክርስቲያኖችን ወደ ስህተት ትምህርትና አክራሪነት ሊመሩ ይችላሉ።

  ስለዚህ የፈሪሳውያንን ባሕርያት ማወቅና ማስተዋል በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስለሄሮድሳውያንና ስለሰዱቃውያን ብዙ የተጻፈ ነገር የለም። ስለፈሪሳውያን ግን ወንጌል ውስጥ በሰፊው ተጽፏል ስለዚህ እግዚአብሔር ዛሬ ስለፈሪሳውያን ባሕርይና ተግባር እንድናጠና ሳይፈልግ አይቀርም።

  ማንም አማኝ አክራሪ የሃይማኖት ትምህርት ያለውና የሰው ወግን የሚፈልግ ከሆነ ፈሪሳዊ ለመሆን ትልቅ አደጋ ላይ ነው። ይሄም የሚሆነው ሳይታሰብ ነው። ወንድሞቻችን የማህበረ ቅዱሳን አባላትም በዚህ ችግር ሳይጠመዱ እንዳልቀሩ እንገምታለን።

  አብዛኛዎቻችን የማህበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎቻችን በዚህ ክፍል ውስጥ ስላለን፣ ይሄንን አመለካከት በጥሞና እንመልከተው።
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ከብዙው ጥቂት የሆኑት የፈሪሳውያን ባሕርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ናቸው። ከተዘረዘሩት ባሕርያት ሌላውን ሳንጨምር አንዱን ብቻ እንኳ የምንመስል ከሆነ እኛም ፈሪሳዊ ነን። የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ በማህበሩ አባላት ላይ ጎልተው የሚታዩ ቢሆንም በኛም ላይ አይታጡም። የራሳችንን ሕይወት ብንመረምር ሌሎችም ባህርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተጠቀሱ እናገኛለን።
  
    የፈሪሳውያን መንፈስ የኢየሱስን መንፈስ በጣም የሚቃረን ነበር። ስለዚህ ነው በጣም ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን። ኢየሱስ ቅንጣት ያህል መጥፎ መንፈስ በውስጣችን እንዲኖር እንደማይፍፈልግ ሁሉ እኛም ቅንጣት ያህል እንኳ የፈሪሳዊ መንፈስ በውስጣችን ኢንዲኖረን መፍቀድ ወይም መፈለግ የለብንም።

    የእግዚአብሔር አንዱና ዋነኛው በረከት መንፈስ ቅዱስ በላያችን ላይ የሚያበራልን ብርሃን ነው። በሕይወታችን ውስጥ ክርስቲያናዊ ባልሆኑት ቦታዎች ላይ ብርሃን የማይበራልን ከሆነ በእግዚአብሔር እየተባረክን አይደለም ማለት ነው። ጤናና ሀብት የእግዚአብሔር የበረከት ምልክቶች አይደሉም ምክንያቱም ብዙ የማያምኑ ሰዎች ሁለቱም አላቸው እንዲያውም ከብዙ አማኞች የበለጠ አላቸው።
እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ያሉትን ክርስቲያናዊ ያልሆኑትን ባሕሪያችንን ሲያሳየን, ከነዚያ ባሕርያት እንድንነጻ ሲፈልግ ነው (2 ቆሮንቶስ 7፥1) ይህን በማድረግም የሱን ባሕርይ ተካፋዮች እንሆናለን። ስለዚህ የግል ሕይወታችን የቤተሰባችንና የቤተክርስቲያናችን ሕይወትም ብርሃን የሞላበት ይሆናል። ከዛም ከሰው ስርአት ነፃ ወጥተን እንደመላእክት በሰማያዊ እንመራለን። ፈሪሳዊነታችንን በውስጣችን ካላየነው በምድር ላይ እንደታሰርን እንኖራለን።
እግዚአብሔር ቃሉን የሰጠን በውስጣችን ብርሃን እንዲኖረንና ፈሪሳዊነትንም በሌሎች ላይ አይተን እንዳንታለል ነው። ፈሪሳዊነትን በውስጣችን ስናየውና ስናነፃው ብቻ ነው እግዚአብሔርን ማገልገል የምንችለውና ከሱም ጋር ኅብረት ሊኖረን የሚችለው።


  የፈሪሳውያን ጠባያት
ፈሪሳውያን ከእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ይሞገሳሉ/ያጌጣሉ
“በልባችሁም አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና። ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል። (ማቴ 3፥9)
ፈሪሳዊ እርሱ ራሱ የእግዚአብሔር ሰው መሆኑን ስለሚጠራጠር ወይም መንፈስ ቅዱስ ለሕሊናው ስለማይመሰክርለት ሌላ "የእግዚአብሔር ሰው" ተብሎ ከተመሰከረለት ክርስቲያን ጋር ግንኙነት ይፈጥራል። ይህን የሚያደርግበትም ምክንያት በታዛዋሪ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት አለኝ ብሎ ለመናገር ነው። ዛሬም ብዙ ስጋዊ የሆኑ ክርስቲያኖች ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን አባል የሆኑ አሉ። እነዚህ ክርስቲያኖች "የእግዚአብሔር ሰው" ተብሎ በሚነገርለት ሰው የሚመራ ቤተክርስቲያን ውስጥ አባል በመሆናቸው የሚሞገሱ/የሚያጌጡ/የሚኮሩ አሉ። ምንም እንኳ እነርሱ ቅድስና ባይኖራቸውም በዚህ ዝና ይኖራሉ። ፈሪሳውያን ከክርስቲያኖች ጋር ስለተደባለቁ እራሳቸው ቅዱሳን እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ። የኛዎቹ የማህበረ ቅዱሳን ተካታዮች ግን ከዚህ የባሰ አስተሳሰብ አላቸው። በምድር ላይ ካሉ ቅዱሳን ጋር ኅብረት ማድረግ የሚከብዳቸው፣ ከማህበሩ አባላት ውጭ ሰላም መፍጠር የማይሆንላቸው ናቸው። እንዲያውም በምድር ላይ ያሉ ቅዱሳንን በማሳደድ በታሪክ ብቻ ከተማሯቸውና በእርግጠኝነት ከማያውቋቸው ያረፉ ቅዱሳን ጋር በመገናኘት ቅድስናን የሚያገኙ ይመስላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡና በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ ወዮላችሁ“ ሲል ይገሥጻል ማቴ 23፥29-30።

  አንድ ሰው የጥሩ ቤተ ክርስቲያን አባል መሆኑ ሲኦል ከመግባት አያድነውም። ንሰሐ ያልተገባለት ኃጢአትና በሌላ ሰው ላይ የተያዘ ቂም ካለ ከዚህ ኃጢአት ምንም አይነት ስራ ሊያደነው አይችልም። የጥሩ ቤተ ክርስቲያን አባሎች ስለሆንን ብቻ እግዚአብሔር ሐሜትንና ክፉ ንግግራችንን ዝም ብሎ ያልፋል ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። በመጨረሻው የፍርድ ቀንም ትልቅ ያልጠበቅነው ነገር ያጋጥመናል። ምናልባት ድኅነትን አንድ ቀን አግኝተን ይሆናል ግን ዛሬ ደሞ ጠፍተን ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ከጥሩ ክርስቲያኖችና ካረፉ ቅዱሳን ጋር ባለን ግንኙነት መመካት አይገባንም።ፈሪሳውያን ባላቸው ውጪያዊ ጻድቅነት [የአምልኮ መልክ]ይሞገሳሉ/ያጌጣሉ
“እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም“ (ማቴ 5፥20)
ኢየሱስ እዚህ ላይ ምን ማለቱ ነው? ከፈሪሳውያን የበለጠ መጾም, መጸለይና አስራት መስጠት አለብን? ኢየሱስ የሚናገረው ብዛትን ሳይሆን ጥራትን ነበር። የእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለመግባት የጽድቃችን ጥራት ከፈሪሳውያን መብለጥ እንዳለበት ነው የሚነግረን። ይሄም ምን ማለት እንደሆነ በዚሁ ምዕራፍ ውስጥ ያብራራዋል። የፈሪሳውያን ጽድቅ ውጫዊ ብቻ ነበር። ለሕጉ ባላቸው ውጭያዊ ታዛዥነት ይመካሉ/ይሞገሳሉ/ያጌጣሉ። አለባበሳቸው የአምልኮ ሥራታቸው ያስመካቸዋል። ነገር ግን ኢየሱስ የነገረን እግዚአብሔር የሚፈልገው ውጪያዊ ከሆነው ነፍሰ ገዳይነት ነጻ መሆንንና ዝሙትን ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ ንዴትንና ውስጣዊ አመንዝራነትን/ፍላጎትን እንድናስወግድ ነው። ኢየሱስ ቁጡነትና ውስጣዊ የወሲብ ፍላጎት ከባድ ኃጢአት እንደሆኑና ወደ ሲኦልም እንደሚመሩ ነው የነገረን (ማቴ 5:22, 29, 30)። ብዙ ክርስቲያኖች እነዚህን ውስጣዊ ኃጢአቶች ችላ ይሉዋቸዋል ምክንያቱም ፈሪሳውያን ናቸው። በውጫዊ ምስክረነታቸው አምረው በሰው ፊት ይቀርባሉ/ይታያሉ/ይሞገሳሉ። "... ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል..." (1 ሳሙኤል 16፥7)። ሌላ ሰው ስለኛ ጻድቅነት የሚናገረው በእግዚአብሔር ፊት ምንም ዋጋ የለውም። እርሱ የሚያየው ሀሳባችንን፣ የሚያነሳሳንን ምክንያትና አቋማችንን ነው። ልባችን ንጹሕ ሳይሆን በዝናችን ብቻ ማጌጥ/መሞግስ/መደሰት የለብንም።
 
 
ፈሪሳውያን ከኃጢያተኛ ሰዎች ጋር አይቀላቀሉም
“ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው“ (ማቴ 9፥ 11)
ፈሪሳውያን የሚቀላቀሉም ከራሳቸው ሰዎች "ቅዱሳን ጋር" ብቻ ነው። ኢየሱስን እንኳ ከኃጢያተኞች ጋር በመደባለቁ ተችተውታል። የእኛ ሐሰተኛ ወንድሞችም የማህበሩ ልጅ ካልሆነ ትክክለኛ ያልሆነ ሰው ስለሚመስላቸው ያገሉታል። ቅድስናችን አማኝ ካልሆኑ ዘመዶቻችን ጋር መደባለቅን የሚከለክለን ነውን? አይደለም። መንፈሳዊ ኅብረት ማድረግ የምንችለው በእርግጥ ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር ብቻ ነው። ነገር ግን ከሁሉም ጋር ጓደኛ መሆን እንችላለን። ኢየሱስ "የኃጢያተኞች ጓድኛ" በመባል ይታወቅ ነበር። እንደ ኢየሱስ መሆን ከፈለግን ከኃጢያተኞች ጋር ጓደኛ መሆን አለብን። አለባለዚያ ክርስቶስን ልናሳየው አንችልም። ፈሪሳዊ፣ አማኝ ያልሆነን ሰው ዘመዱን ሠርጉ ላይ ቢገኝ አይወድም። ምክንያቱም ቢገኝ የሚረክስ ወይም ሃይማኖቱን የለወጠ ይመስለዋል። ኢየሱስ ግን ባላመነው ሰው ሠርግ በደስታ ይካፈል ነበር። ከኃጢአተኞች ጋር መገናኘቱ ቅድስናውን አላረከሰውም ምክንያቱም የእርሱ ቅድስና ውስጣዊ የሆነ ነገር ነው። እርግጥ ብዙውን ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ያሳልፍ ነበር ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜውን ከኃጢያተኞች ጋር በመነጋገር ያሳልፍ ነበር:: ከኃጢአተኞች ጋር ካልተነጋገርን እንዴት ወደ እግዚአብሔር ልናመጣቸው እንችላለን? እያንዳንዳችን ምን ያህል ሰዎችን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን እንዳመጣን እራሳችንን መጠየቅ ይገባናል። በእኛ ወንድሞች ፈሪሳውያን ምክንያት ስንት ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያናችን መጣ? ስንቶች ቤተ ክርስቲያናችንን እየለቀቁ ወጡ? ይህን ለታዛቢ እተዋለሁ።

ፈሪሳውያን ወደ መታዘዝ የማያደርስ እውቀት አላቸው
"ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ" ማቴ 23፥2-3)
በመጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት ምእራፎች ሁሉ ማቴዎስ 23 ላይ ኢየሱስ ስለፈሪሳውያን ባሕሪያት በበለጠ ይናገራል። ማቴዎስ 23 ከ 1ኛ ቆሮንቶስ ም 1 የተለየ ወይም የሚቃረን ምእራፍ ነው። በሕግ መመራት ማለት በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በመለኮታዊ ፍቅር ከመመራት ተቃራኒ ነው። ስለዚህ ከፈሪሳዊ እና ከሕጋዊ ምሪት ውስጥ ወጥተን ወደ መለኮታዊ ፍቅር ወደሞላበት ሕይወት ውስጥ ለመግባት ከፈለግን ማቴዎስ 23ን በጥሞና ማጥናት አለብን።

   ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል ማለት: ከመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ኮሌጅ ተምረዋል የዶክትሬት ዲግሪያቸውን አግኝተዋል ብዙ ትክክለኛ የሆነ እውቀት አላቸው። ኢየሱስ እንኳ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸው ፈሪሳውያን የሚያስተምሩትን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው። እንደዚህ ከሆነ የፈሪሳውያን ትምህርት ትክክል ነው ማለት ነው። ነገር ግን ለሚያስተምሩት እውነት አይታዘዙለትም። እውቀት ጠቃሚ እንደመሆኑም መጠን አደገኛ ሊሆንም ይችላል። እውቀትና መታዘዝ አንድ ላይ ሲሆን ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ያመጣል። እውቀት ኑሮን ግን መታዘዝ ከሌለን መንፈሳዊ ሞትን ያመጣል። እውቀት እያለን ግን መታዘዝ ከሌለን ምንም እውቀት ባይኖረን ይሻላል። የእኛ ሐሰተኞ ወንድሞች ግን ባዋልድ መጻሕፍት ላይ የተመሠረተ እውቀት ብቻ ስላላቸው ትምህርታቸውም በኢየሱስ ዘመን ከነበሩ ፈሪሳውያን ትምህርት የተለየ ነው። በዚህ ሐሰተኛ እውቀታቸው በፈጠሩት ሕግ ሥራት ከፈጣሪ በላይ ዋስትና እንዳለው ቢያምኑም ሲታዘዙለት ግን አናይም።

 ፈሪሳውያን የሚያስተምሩትን አይለማመዱትም ወይም በተግባር ላይ አያውሉትም
ፈሪሳውያን የሚሉትን ነገር አያደርጉትም (ማቴዎስ 23:3) ይህ ጥቅስ ከሐዋርያት ሥራ 1:1 ላይ ካለው ስለ ኢየሱስ ከሚናገረው ጥቅስ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው። ምክንያቱም የሐዋርያት ሥራ 1:1 ላይ የሚነግረን ኢየሱስ መጀመሪያ ያስተማረውን ነገር ሁሉ ራሱ እንዳደረገው ነው። ፈሪሳውያን ግን የሚያውቁትን ያስተምራሉ እንጂ ራሳቸው አይለማመዱትም። ኢየሱስ ግን ያስተማረው መጀመሪያ ራሱ የፈጸማቸውን ነገሮች ብቻ ነው። እነዚህ ሁለቱ ተቃራኒ መንፈሶች ናቸው። የፈሪሳውያን መንፈስ ያላቸው የባቢሎንን ቤተክርስቲያን ይመሰርታሉ፣ የክርስቶስ መንፈስ ያላቸው ደግሞ ሙሸራይቷን የኢየሩሳሌምን ቤተክርስቲያን ይመሰረታሉ።
ኢየሱስ ያላደረገውን አንዳንችም ነገር አላስተማረም። የተራራውን ስብከት (ማቴ 5, 6, 7)ን እንኳ ለመስበክ ሰላሳ አመት ነው የተዘጋጀበት። ስብከቱ ከራሱ ሕይወትና ሀሳብ የመነጨ ነው።
ሰዎች ከሰው የሰሙትን ስብከት ደግመው ለሌላ ሰው ሲሰብኩት የሚያስተላልፉት መልክት ሕይወት የማይታይበት እውቀት ብቻ ነው የሚሆነው። እንደ ኢየሱስ ያለ ስብከት መስበክ ከተፈለገ መጀመሪያ በምናስተላልፈው ቃል መሰረት መኖር አለብን ከዛ የተለማመደነውን መስበክ።
(18)
ፈሪሳውያን ከባድ ጫናን በሌሎች ላይ ያደርጋሉ
"ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም"(ማቴ 23፥4)
ፈሪሳውያን ሥርአቶች በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ አለባቸው እያሉ ለሌላው በመስበክና በማዘዝ መንፈሳዊ መስለው ይቀርባሉ። የሚሰብኩትን ነገር ግን እራሳቸው አይፈጽሙትም። ለምሳሌ ሕዝቡን ከገቢው አስር እጅ ያላነሰ አስራት እንዲሰጥ ያሳስባሉ እነሱ ግን አያደርጉትም። በዚህ ዓይነት ስብከት ምክንያት ከቤተክርስቲያን የሚቀረው ሕዝብ ትንሽ አይደለም። ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ትምህርት ሲያስተምር ሕዝቡን ነፃ አወጣ። ፈሪሳውያን ግን ያንኑ መጽሐፍ በመጠቀም ሕዝቡን በሰንሰለት አሰሩት።

ፈሪሳውያን ከሰው ክብርን ለማግኘት ይጥራሉ
"ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ" (ማቴ 23:5)
ኢየሱስ ማቴዎስ 6፥1 ላይ ፈሪሳውያን በየመንገዱ ላይ ቆመው በከፍታ ድምጽ እንደሚጸልዩ አስተምሯል።


ፈሪሳውያን ቅድስና በአለባበስ እንደሆነ አርድርገው ያስባሉ
"ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ"(ማቴ 23፥5) የፈረሳውያን ሌላው ባሕርይ በአለባበሳቸው ስርአት ቅድስና እንደሚያገኙ ያስባሉ። እግዚአብሔር እስራኤሎችን በልብሳቸው ላይ የሚንጠለጠል ዘርፍ እንዲያንደርጉ ነገራቸው ይህን ያለበትም ምክንያት ዘርፉን ባዩት ቁጥር ቃል ኪዳኑን እንዲያስታውሱት ነው። "ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው። እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው።(ዘኍልቁ 15፥38)) ፈሪሳውያን ግን የራሳቸውን የልብስ ዘርፍ ከሌላው ሕዝብ ረዘም ያደርጉትና ቅድስናቸውን ለማሳየት ይጥራሉ። ፈሪሳውያን ሌሎች ሰዎች ላይ የሚያስነቅፍ ነገርን ለማግኘት ሲሉ ሌሎች የሚለብሱትን ልብስ የሚያደርጉትን ጫማ የሚያደርጉትን ጌጣ ጌጥ በጥንቃቄ ይመለከታሉ። መንፈስ ቅዱስ ሴቶችን ወግ ባለው ሁኔታ እንዲለብሱ ያስተምራል (1 ጢሞ 2፥9, 1 ጴጥሮስ 3:3):: ነገር ግን ቅድስና በአለባበስ ሳይሆን የሚገኘው በውስጣዊ ማንነት ነው። የእኛ ሐሰተኛ ወንድሞችም ስለአለባበስ የሚሰብኩትን እና የሚከራከሩበትን ሁኔታ በመመልከት ማንነታቸውን አውቀን ከትምህርታቸው መጠንቀቅ አለብን፣ ነጭ ልብስ መልበስ ከኃጢአት ነጻ መሆናችንን አያመለክትም፣ ነጭ ልብስ በበጉ ደም የታጠበው የቅዱሳን የውስጥ ልብስ ነው እንጅ በውጭ ጋቢ ወይም ቀሚስአይደለም።
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል“ ማቴ 23፥25-27። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ“ማቴ 23፥14።

ፈሪሳውያን ማዕረግና ስልጣን ይወዳሉ
በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ“ (ማቴዎስ 23:6-8) እያንዳዳችን አገልጋይ ነን የምንል ሁሉ ልናስብበት ይገባል።
ፈሪሳውያን ሌሎችን ያበላሻሉ
"እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ" (ማቴ 23:13)
እግዚአብሔርን የሚወዱ፣ ኃጢአትን አሸንፎ የመኖር ኃይለኛ ፍላጎት ያላቸው አማኝ ወጣቶች በፈሪሳውያን አማካኝነት በእምነታቸው ይሰናከላሉ። ይህም የሚሆነው: ፈሪሳውያን መሪዎቻቸው በኢየሱስ ስም እየሰበኩና ገንዘብ እየሰበሰቡ ልክ እንደፊልም ተዋናዮች ተዝናንተው ሲኖሩ በሚያዩበት ጊዜ ነው። እነዚህ እንደ ክርስቶስ ሆነው ለመኖር ፍላጎት የነበራቸው ወጣቶች ሳያስቡት እንደመሪዎቻቸው መኖር ይጀምራሉ። ስለዚህ መሪዎቻቸው ኢየሱስን ለመከተልና የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ እንቅፋት ይሆኑባቸዋል።
እኛም የመንግሥተ ሰማያትን በር በሰዎች ላይ እንዳንዘጋ፣ ከስሕተት አስተምሕሮ፣ በውግና በልማድ ከመኖር፣ ያሮጊቶችን ተረት ከሚመስል ትምህርት ከማስተማር፣ መጠንቀቅ አለብን።
"ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጭዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን እራስህን አስለምድ" 1ጢሞ 4፥7።
 
 
ተጠንቀቁ
from fikirte iyesus

32 comments:

 1. I WAS SUPPORTING YOU BEFORE BUT YOU DON'T HAVE WORDS THAT DOESN'T TOUCH MK. I TOOK TIME TO SEE MK IF THEY ARE AS YOU SAID. THOUGH I OBSERVED SOME PROBLEMS THEY ARE NOT AS ARROGANT AS YOU ARE READ WHAT YOU WROTE, IT HAS NO RELATION WITH MK. HWY YOU FEAR MK? WHY YOU ALWAYS KID PEOPLE?

  ReplyDelete
 2. This is the point kale hiwot yasemalen.

  ReplyDelete
 3. Egziabiher yibarikish. Tiru timihirt kesimyaleh.

  ReplyDelete
 4. what you wrote is pre- text as you learned from your father devil. as you are enemy of church mk remains always your enemy

  ReplyDelete
 5. Fikirte Eyesus, what a wonder-full article. God Blesse you many many years. This is exactlly what mk. is, are, doing. God please open thair eyes.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mahibre Kidusans Work day and nght to keep the Orthodox Tewahido church from people who think they can change the Dogma, kenona,when they dont want to change them selves they accuse others and the church claiming its in need of a change, ክርስትና የምቾትና የመደላደል ኑሮ አይደለም... and this people are the ones that own this pages.... "ዘመዶቼ በክርስትና ህይወት ተነቀፈን ብላቹ እናንተ እራሳቹ መልሳቹ ማህበረ ቅዱሳንን ትወቅሳላቹ፣ እስቲ በየትኛው መንገድ ይሆን እናንተ ከእነ እርሱ የተሻላችሁት "መፅሀፍ የሚወቅስህን መልሰህ ውቀሰው ብሎ አይልም" ሆኖም ግን የተከሰሳችሁበትንም ቢሆን መስማትን ለሚሰማ ሁሉም አድምጧል ፣ "ሚስጥረ ሥላሴን፣ ሚስጥረ ስጋዌን፣ ሚስጥረ ጥምቀትን፣ ሚስጥረ ቁርባንን፣ ሚስጥረ ትንሣኤ ሙታንን ሁሉ ሽራቹ ሁላችንም በክርስቶስ አንድ ነን ማለት በጣም ከባድ ነው፣ እንዲያውም ክስ ሁላ ትንሽ ነው ፣ በዚያ ላይ ሙሉ ሆና በሐዋሪያት ጉባኤ የተመሰረተችን አንዲት ቤተ ከርስቲያን፣ ወልደ እ/ር በደሙ ያፀናትን ቤተክርስቲያን ስርአቷን እነወለውጥ እናድስ ማለት ደግሞ ሌላው ሁለተኛው ከባድ እና ክስም የሚያንሰው ነገር ነው ፣ ሆኖም ግን ሁሉም እንደ ስራው ይከፈለዋል "ለለአሀዱ በከመ ግብሩ" … ተከሰስኩ ብሎ መልሶ የሚከስ፣ ተወነጀልኩ ብሎ መልሶ የሚወነጅል ሰው "ይኼ ሌባ ሲያዝ የሚጮኸው ጩኸት ነው።" እኔ ከእርሱ እሻላለው እኔ ከማህበረ ቅዱሳኖች ይለቅ አማኝ ነኝ ሲል ደግሞ ትንሽ ያሳፍራል … "ወነአምን በአሀቲ ቅድስት ቤተክርሰቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋሪያት" ጸሎተ ሐይማኖት… ማስተዋል፣ ያድለን ለእናንተም ያድላችሁ ከመመለስ ጋር ምክንያቱም የአባ ሰላማ አጥንት እራሷ መጥታ እንዳትወጋችሁ፣ እስከ አሁን በስማቸው ነገዳችሁበት፣ በጣም ያሳዝናል።

   Delete
 6. I am recomand you to read and practice God word. We have not enemy except deveil that you have mentioned. If your plan to attack human that created by God, your life will be in deep darkeness.

  ReplyDelete
 7. ፈሪሳውያን ፈሪሳውያን ናቸው። ማህበረ ቅዱሳንም ማህበረ ቅዱሳን ናቸው። ጥቁሩን ጥቁር እንደ ማለት ነው።

  ReplyDelete
 8. Thank you, my sister. you made it, your message is really touching all of us. I used to attain MK meeting long time ago, in short they are arrogant and killed the church, they are responsible for all the lost of our brothers and sisters from the mother church. Their tert tert preaching too funny, even this generation kids will not listen it. By the way how is protestant or menafek? there is no doubt that this organization (MK)is Menafeke, because they brought us false preaching to our church. who are our father? I believe our fathers are Saint Paul,peter, and other God dispels, I don't understand that if this org (MK) respect our fathers, why not teach us a Bible instead of tert tert. Finally, who I am? God please open my eyes.

  Tigist

  ReplyDelete
 9. Amazing, yet nebereku? Abaselamawoch eyebasebachihu neew. Good job!!

  I will read Math 23 and compare. I am sure I will also see myself. How about Silela (MK) ?

  God bless Fikrete Eyesus.

  ReplyDelete
 10. Ferisawinet == MK == Tsere Iyesus == Taliban

  Need further research!

  ReplyDelete
 11. Hi guys,
  I am really sad for you because you do not have any idea what you are talking about. Instead of accusing MK, please come to your mind and follow them and doing some thing good to our mother church.
  May God be guide you to the right path.

  ReplyDelete
 12. እኛስ በተግባር አይተናል……እንዘን አይነ ልቦናቸው ማየት ለተሳነው…….
  “እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን ፡ የተጎዱ ቤተክርስቲያናትን ሲያስጠግን ፣ ገዳማትን ሲረዳ ፣ የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ሲያስከፍት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ተማሪወችን በብዙ ነገር ሲያግዝ ፣ በገጠር ላሉ ምእመናን ወንጌልን በነፃ ሲያስተምር ፣ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ሲያዘጋጅ ፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪወችን ከመናፍቃን ይጠብቅ ዘንድ ሰብስቦ ሲያስተምር ፣ በግእዝ ብቻ ተፅፈው የነበሩ ቅዱሳን መፃህፍትን ወደ ተለያዩ ቋንቋወች በመተርጎም ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ፣ መንፈሳዊ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን በየጊዜው ለአንባቢያን ሲያደርስ ፣ ስርአተ ቤተክርስቲያን ይከበር ሲል ፣ ስርአቱን የጠበቀ መዝሙራትን ሲያወጣ ፣ ቤተክርስቲያንን ለመውረር የሚተጉ መናፍቃንን የከፋ ግብራቸውን በማስረጃ እያጋለጠ ቤተክርስቲያንን ከተኩላወች ሲጠብቅ ፣ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን - - - ይህን ሁሉ ስለመስራቱ በተለይም መናፍቃን እንዳሻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እንዳይቦርቁ ዘብ ሆኖ በንቃት ተዋህዶን በመጠበቁ መናፍቃንና መሰሎቻቸው ይህን ማህበር ለማጥቃት ቢነሱ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን መናፍቃንንም አናጣቸውም፡፡”

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፈሪሳዉያንም ይህንን ሁሉ ያደርጉታል፤የሚገርመው ግን አየሱስ ክርሰቶስ በስራቸው አንድም አላስደሰተውም ምክንያቱም በቅድስና ስለመኖርና በክርስቶስ ስለሚገኘው መዳን ግድ የላቸውምና፡፡በክርስቶስ የሚገኘውን ደህንነት ችላ ብለን ልክ እንደ ፈሪሳዊያን ስለ ሐይማኖት ብንጨነቅ፣ ብንጠበብ በክርስቶስ ዘንድ ዕርስት የለንም፡፡
   እግዚአብሄር ይባርካችሁ!!!

   Delete
  2. ፈሪሳዉያንም ይህንን ሁሉ ያደርጉታል፤የሚገርመው ግን ኢየሱስ ክርሰቶስ አንድም ይህ ስራቸው አላስደሰተውም ምክንያቱም በቅድስና ስለመኖርና በክርስቶስ ስለሚገኘው መዳን ግድ የላቸውምና፡፡በክርስቶስ የሚገኘውን ደህንነት ችላ ብለን ልክ እንደ ፈሪሳዊያን ስለ ሐይማኖት ብንጨነቅ፣ ብንጠበብ በክርስቶስ ዘንድ ዕርስት የለንም፡፡
   እግዚአብሄር ይባርካችሁ!!!

   Delete
 13. "ለሥራ ያልታደለ አዕምሮ ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውም"።ማህበረቅዱሳን ማን እንደሆኑ ሥራቸው እንጂ የጥላቻ መንፈስ በተሞላ አስተሳሰብ አይደለም።የሚያሳዝነው በቅዱሱ አባት ስም ይህንን ጦማር መክፈታችሁ እጅግ ያሳዝናል።

  ReplyDelete
 14. Poor. you have only one rythem...MK...MK...MK ..... Please try to song other, so that people will give you their ears to listen. MK is know well by all with all its weakness and strength. And millions support it regardless of its weakness because it shows them with deeds it is from the side of the church. However, you are showing us just talk..talk...and talk. Please take time to turn off your PC and think about what you can do in practice. Then people will start to say 'Bravo Aba Selam...you are better than MK!!!'.
  Tazabiw

  ReplyDelete
 15. it is amizing truth is alwyas win the open mouth will be close

  ReplyDelete
 16. Mk= Antichrist, because they don't want Jesus to be praised in our church.

  ReplyDelete
 17. kenante naw enji metebek...Tekuloch! lenegeru Mawenabed ke gibr abatchu ke diabilos yeweresachut naw

  ReplyDelete
 18. Mahbere Kidusan - zendro gudachihu fela :)

  Ke Eyesus gar - ke wongel ga gibeb ayawatam

  ReplyDelete
 19. እኛስ በተግባር አይተናል……እንዘን አይነ ልቦናቸው ማየት ለተሳነው…….
  “እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን ፡ የተጎዱ ቤተክርስቲያናትን ሲያስጠግን ፣ ገዳማትን ሲረዳ ፣ የተዘጉ ቤተክርስቲያናትን ሲያስከፍት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶችንና ተማሪወችን በብዙ ነገር ሲያግዝ ፣ በገጠር ላሉ ምእመናን ወንጌልን በነፃ ሲያስተምር ፣ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የውይይት መድረኮችን ሲያዘጋጅ ፣ የዩንቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪወችን ከመናፍቃን ይጠብቅ ዘንድ ሰብስቦ ሲያስተምር ፣ በግእዝ ብቻ ተፅፈው የነበሩ ቅዱሳን መፃህፍትን ወደ ተለያዩ ቋንቋወች በመተርጎም ለህብረተሰቡ ሲያቀርብ ፣ መንፈሳዊ መፅሄቶችንና ጋዜጦችን በየጊዜው ለአንባቢያን ሲያደርስ ፣ ስርአተ ቤተክርስቲያን ይከበር ሲል ፣ ስርአቱን የጠበቀ መዝሙራትን ሲያወጣ ፣ ቤተክርስቲያንን ለመውረር የሚተጉ መናፍቃንን የከፋ ግብራቸውን በማስረጃ እያጋለጠ ቤተክርስቲያንን ከተኩላወች ሲጠብቅ ፣ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን - - - ይህን ሁሉ ስለመስራቱ በተለይም መናፍቃን እንዳሻቸው በቤተክርስቲያን ላይ እንዳይቦርቁ ዘብ ሆኖ በንቃት ተዋህዶን በመጠበቁ መናፍቃንና መሰሎቻቸው ይህን ማህበር ለማጥቃት ቢነሱ የሚደንቅ አይደለም፡፡ እኛስ ማህበረ ቅዱሳንን እናውቀዋለን መናፍቃንንም አናጣቸውም፡፡”

  ReplyDelete
  Replies
  1. ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም ነው የሚሉት ምን ነገር ትደጋግማለህ አንድ ጊዜ ክላይ ጻፍክ እውነት ከሆን እኮ በቂ ነው። እውነት የናንተ የማህበረ ሰይጣኖች ጊታ እየሱስ ብቻ ነው። የተደረገው ነገር ሁሉ በማህበረ ቅዱሳን የተደረገ ለምን ታስመስሉታላችሁ? አረ አንዳንድ ጊዜ ይህን ለማድረግ የረዳን አምላካችን ይመስገን በሉ። ማህበረ ቅዱሳንና ኦርቶዶክስ እመነታችን እኮ ዕድሜያቸው ሲወዳደር የትየለሌ ነው። "ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ" እንደሚባለው ትላንት ተገኝታችሁ አባቶችን ምናለበት ባታውኩ ለምትሰሩት ሥራ ደግሞ በጉልበታችሁ ሳይሆን በእግዚአብሄር ፈቃድ ስለሆነ ሰራን የምትሉት ቀርቶ ወጥታችሁ መግባት የቻላችሁትም በእርሱ ፈቃድ ነውና ወደፊትም እግዚአብሄር ከፈቀደ ብዙ እንሰራለን የማለት ልምድ ይኑራችሁ። አዋኪነታችሁ፣ ፍሪሳዊነታችሁ እየተበላ ስለመጣ ሌላ ነገር ቀይሩ እስኪ። ለመሂኑ ከአባላችሁ ከበጋሻው ምን አናከሳችሁ? ጥቅም ወይስ...መልስ ስጡበት አባላችሁ ነበር ከነበረስ ሰሞኑን ምን አባላችሁ ነቄ አለ እንዴ?

   Delete
  2. ፈሪሳዉያንም ይህንን ሁሉ ያደርጉታል፤የሚገርመው ግን ኢየሱስ ክርሰቶስ አንድም ይህ ስራቸው አላስደሰተውም ምክንያቱም በቅድስና ስለመኖርና በክርስቶስ ስለሚገኘው መዳን ግድ የላቸውምና፡፡በክርስቶስ የሚገኘውን ደህንነት ችላ ብለን ልክ እንደ ፈሪሳዊያን ስለ ሐይማኖት ብንጨነቅ፣ ብንጠበብ በክርስቶስ ዘንድ ዕርስት የለንም፡፡
   እግዚአብሄር ይባርካችሁ!!!

   Delete
 20. wow aba selama Mhaber kidsuan lasera lachu aydel that why you guys talk all the time about mk long live for mk brovo mk

  ReplyDelete
 21. To Anonymous: you slogan "long live for mk brovo mk" remembered me Derge "long live for ESEPA."

  ReplyDelete
 22. For me you explained the characteristics of Ferisawiyan but not the characteristics of Mk.Endezia kehone,Fikire Eyesusim yaderegew Ferisawinet new.Wengelun Matamem Yichalal egna wedeminfeligew direction.That is why you tried to relate to Mk.
  Mk with its weakiness(as far as the association of humanbeings)is doing for the sake of our church.The main objective of Mk is to preach the Holy Gospel to all humanbeings through out the world but you tried to denay what MK is doing.In short,You are against of ETOC preachings that is why you are always singing about MK. Thank you for your deeds because you are helping the people ,who don't know about Mk,approach and know mk.That is what I do.To the contrary,I know "Abaselama"as opponent of our church.By the way are you listening the radio of Mk,Dimtse tewahido Radio Program,which is listened through out the World with the link of WWW.dtradio.org That is a wonderful deeds for Mk.I appreciate for your post of my comments on your blog.May God give us heartful love for the people.Amlake kidusan Libona lehulachin Yadilen.
  Teshome from USA.

  ReplyDelete
 23. To Teshome: wow you are in the land of freedom, good for you! Teshe bertu, you are funny ; you are telling us the main objective of Mk (mahaber sitan) is to preach the holly Gospel, their objective is dissolution of the church.

  ReplyDelete
 24. 2ኛ ጴጥ 1፡20 ማንም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃላት እንደፈለገው መተርጎም እንደማይችል ተጽፏል የሐመር መጽሔት አዘጋጆች የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በማጣመም የራሳቸውን ሀሳብ ያንጸባርቃሉ፡፡ ተብሎ ከደረሰን ደብዳቤ \የሚከተለውን አውጥተናል፡፡

  እስከ አሁን በእኔ የኢሜል አድራሻ samuelabay68@yahoo.com በርካታ የሐመርና የስምዐ ጽድቅ፣ የልዩ ልዩ ሕትመቶች፣ ሐመረ ጽቅ በተለይ የተሰራጩ የኑፋቄ ትምህርቶች ደርሰውናል ለጻፋችሁ ሁሉ ወደ ፊትም ለምትጽፉ የላቀ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ ጽሑፎቹን የማናወጣው በተሰጠን አስተያየት መሠረት ኑፋቄው በአግባቡ ለቅዱስ ሲኖዶስ በሚደርስ መንገድ መዘጋጀት ስላለበት ነው፡፡ ግን መጽሔቱና ጋዜጣው አሁንም ከስሕተት የማይጠራ መሆኑን ለመግለጽ የቅርቡ የባለፈው ክረምት ሕትመት ሐመር 19ኛ አመት ቁጥር 3 ሐምሌ 2003 ሕትመት ምን አለ መሰላችሁ

  የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉ ጥቃቅን ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን፡ መኃ 2፡ 15 በሚል ርዕስ "በመ/ር ሰሎሞን መኩሪያ" የተጻው በራሱ ፍላጉትን ስጋና ደሙ በመራ ሲተረጉም፡፡ ከዋናው ትርጉም ትምህርት ፈጽ የማይገናኝ ፍጹም ክህደት የሆነ ትምህርት አስተምሯል፡፡

  ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ዋናውን ትርጉም ከመጽሐፈ ሰሎሞን ትርጓሜ የመኃልይ መጽሐፍ ትርጉም ምዕራፍ 2 ቁጥር 15 ተመልከት፡፡

  የወይን ቦታችንን የሚያጠፉ ንዑሳን ቀበራርትን አጥፉልን፡፡ የሕግ (እግዚአብሔርን የመፍራትና አባቶችን የማክበር፣ መንፈሳዊነት) ማደሪያ ልባችንን የሚያስቱ ነቢያተ ሐሰትን ካህናተ ጣዖትን አጥፉልን፡፡ አንድም ወንጌል ያለ ኦሪት፣ ጥምቀት ያለ ግዝረት አትጠቅምም እያሉ የሕግ ማደሪያ ልባችንን የሚያስቱ ሐሰተኛ ወንድሞችን አጥፉልን፡፡ ነው፡፡

  ከጥቅሱና ከትርጉም እንደምንረዳው ትናናሽ ቀበሮዎች ሐመርና ስምዐ ጽድቅ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በቤተ ክህነት ጥላ ስር ትናናሽ ቤተ ክህነት ለመመስረት የሚጣደፉ በወንጌል ላይ ፖለቲካና ሐሜት ብጥብጥ የሚፈጥሩ፣ በመንፈሳዊነት ላይ ስጋዊ ንግድ የሚነግዱ፣ በአለም አቀፋዋቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሰፈር ቡድነኛነትን የሚያካሄዱ ያንን ስራቸውን ወደ ሌላ ለማላከክ፡፡ ባለ አክሲዎን "በመ/ር ሰሎሞን መኩሪያ" በኑፋቄ አዘል ጽሑፍ ወይኑን በጌታ መሰለ እንግዱህ ትልቁ ክህደት መናፍቁ ጸሐፊ በወይን የመሰለውን ጌታችንን መድሐኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብል የማይበላው፣ ነቀዝ የማያበላሸው፣ ማእበል ማይገፋው፣ የማይጠልቅ ጸሐይ እያሉ ሊቃውንት ያስተማሩለትን ያሁኑ አስተማሪ በጽሑፉ ገጽ 4-5 ላይ ወይኑን ክርስቶስን ጥቃቅን ቀበሮዎች 1/ ተሸልከው ይገቡበታል፣(ገጽ 5 ሁለተኛ አንቀጽ) 2/ ወይኑን ያበላሻሉ፣ (ገጽ 5 ሶስተኛ አንቀጽ) 3/ የወይኑን ሥር በመቁረጥ ወየኑን ያደርቁል፡፡ (ገጽ 5 አራተኛ አንቀጽ) እያሉ ያስተምራሉ፡፡ በርግጥ ወደ ውስጥ ሲገባ ብዙ ክህደት አለ
  ስለዚህ፡፡ እነዚህ ሳይማሩ እናስተምር፣ ሳይጠመቁ ኪራይ ሰብሳቢ መዋጮ ሰብሳቢ አስራት ተቀባይ የሆኑ ሰዋች ከከሀዲም ከመናፍቅም በላይ የከፉ ብዙ ነገር ስላለባቸው ምን ብለል እንደምንፈራጃቸው ከአሁኑ እናስብበት፡፡

  ስለዚህ ለማኛውም ሕትመቶቻቸውን ስታነቡ፣ የተኮረጁ፣ የሰዋችን ስም ለማጥፋትና ታዎቂ እንዳይሆኑ ለማድረግ ስራቸውን የተዘረፉ፣ ቃል በቃል የተገለበጡ፣ የተሳሳቱ፣ ትርጉቸው የተጣመመ፣ የቡድን ፕሮፖጋንዳ የተላለፋባቸው፣ የሰው ስም በከንቱ የጠፋባቸው፣ ታሪክ ሆን ተብሎ ተዛባባቸው፣ ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የተለየ ትምህርት የሚያስተምሩ፣ ሰዎችን መተቀሚያ ለማድረግ የተጻፉ፣ ፖለቲካ አዘል ጽሑፎች የመሳሳሉት በተመለከተ ደርሶናል፡፡ የትርጉም ስራዎቻቸውን በተመለከተ የተተረጎመው የማን መጽሐፍ እንደሆነ ሃይማኖቱ፣ ዓላማው፣ ሲተረጎም የተወሰደው የስራ ሂደት፣ የድምጽ የምስል ስራዎቻቸውንም በመገምገም ከዚህ ሌላ ካለ ወይም ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆን ሌላም ካለ አሁንም እያሰባሰብን ስለሆነ samuelabay68@yahoo.com ወይም በፈለጋችሁት መንገድ ሊገኘ በሚችል ሁኔታ ጻፉልን፡፡ ትናናሽ ቀበሮዎችን አብረን እናድናለን፡፡

  ReplyDelete
 25. ቡድነኛ ወንዘኛ ልቡ የጠበበ
  ዘራፊ ቀማኛ ሥጋው የደለበ
  ሲሰድብ አይሰማው
  ሲያማ ስቅቅ አይለው
  ሲማታ ልክ የለው
  ሲነክስ አይጠርሰው
  ወገን እንደቀጨ ሀገር እንዳደማ
  ቢመክሩት አይረጥብ ቢነግሩት አይሰማ
  ሰው የሚያገልበትን የቡድን መርዝ ይዞ
  የስድብ ምላሱን አስረዝሞ መዞ

  አንገት ደፊ . . . ሀገር አጥፊ. . . እንዳሉት

  ቅልስልስ እያለ መንፈሳዊ መስሎ
  ዝክር እንኳ አያወጣም የአምላክን ልጅ ገድሎ
  ነጠላ አሸርጦ አልባሰት ይዘርፋል
  እያሸበሸበ ሊቃውንት ይዘልፋል
  ማህበር ብሎ ጦስ ማን ያጠፋልናል
  በኮትና ሱሬ ከረባት ሰክቶ
  ማቅ ነኝ እኔ ይላል ሰው ማቅ ቀምቶ
  አታላይ ደም አፍሰሽ ነጋዴ ዘረኛ
  የአስመሳዮች ቡድን የትውልድ ቀበኛ

  ደጀ ሰላሞችና አካላዊ ማንነታቸው ማቅ ማንነታቸውን የሚነግሯቸውን ሰዋች ከፌስ ቡካቸው ደልተዋል፡፡ ስለዚህ ሌላ መንገድ እናፈላልግ፣ አስገራሚ ሰዎች ናቸው ምን ያህል ማንነታቸውን እንደሚጠሉት መገንዘብ ችለናል፡፡ በተጨማሪም ስለ እነሱ ያለን አመለካከት ትክክለኛ መሆኑን ተረድተናል፡፡

  ሳሙኤል አባይ

  ReplyDelete
 26. Sirachihu minden new? mamat, yemiseran sew metechet, yemasenakeya dingay mehon......weys betekirstiyanen metadeg? MK silesera endih tegemegem enantens bemin engemigemachu kemaweratina kefu hasab kemamenchet yezelel min yemitay giber alchihu? Alamchihu miderawi kehonem bengid ena bemiyaterf negr bitisemaru yishalchihual Egzihabeher mulu tena setuachihu silemin lemagnchina, leboch ena kemagnoch tihonalachihu?

  ReplyDelete