Monday, December 19, 2011

አባ እስጢፋኖስና ደቂቁ ተሐድሶኣውያን ናቸው - - - Read PDF

ይህ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ የነበረው አዲስ ጉዳይ ለተባለ የግል መጽሔት ነበረ። ይኩኖ አምላክ የተባሉ ሰው አባ እስጢፋኖስና ደቂቁ የተሐድሶ አራማጆች አልነበሩም፤ የእነርሱ አጀንዳ ሌላ ነው። ተሐድሶ ያልናቸው እኛ ነን፤ ያም ስሕተት ነው፤ ሲሉ ለጻፉት መልስ እንዲሆን ነበር የተጻፈው። ይሁን እንጂ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ሳያወጣው ቀርቷል። ለምን አላወጣውም? በእኔ ግምት ግን የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኞች ሙያቸውን በሃይማኖት የሚቃኙት ይመስለኛል። ጋዜጠኞች ቢሆኑም አንድን ጽሑፍ ሊያወጡ የሚችሉት በያዘው ፍሬ ነገር ሳይሆን ሃይማኖታቸውን ደግፎ እስከ ተጻፈና እስካልተቃወመ ድረስ ነው። ምናልባትም የማኅበረ ቅዱሳን ፊት አውራሪዎች ዳንኤል ክብረት እና ኤፍሬም እሸቴ የመጽሔቱ አምደኞች ስለሆኑም ጋዜጠኞቹ ከእነርሱ ጋር የዐላማ አንድነት ይኖራቸው ይሆናል። ይሁን እንጂ ጽሑፉን ነጋድራስ ጋዜጣ ተቀብሎ አስተናግዶታል። ወደፊት አንዳንድ የግል ጋዜጦችና መጽሔቶች ነጻ ነን እያሉ የሌላው ሐሳብ እንዳይስተናገድ እያደረጉ ያለውን ሐሣብን የማፈን አካሄድ በተመለከተ ጽሑፍ ለማቅረብ እሞክራለሁ።


እውነት ተደብቃ አትቀርም፡፡ እንደ ወንጌሉ ቃልም "የማይገለጥ የተከደነ፣ የማይታወቅ የተሰወረ የለም፡፡" (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 10 ቁጥር 26)፡፡ መነሻው እውነት፣ ከእውነትም የወንጌል እውነት የሆነው የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቹ ደቂቀ እስጢፋኖስ ገድልና የተጋድሎ ታሪክ በሰው ሐሳብ እንዳይነሣ ተደርጎ ከተገደለና ከተቀበረ ብዙ ምእት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአንጻሩ የእነርሱ እውነተኛነት በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና በተከታዮቹ ሐሰተኛ ምስክርነት ሲስተባበል ኖሯል፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ እውነተኛ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ሐሰተኛ፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሃይማኖተኛ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ከሓድያን፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የማርያም ወዳጅ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ የማርያም ጠላት፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ክርስቲያን፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ደግሞ አይሁዳውያን፣ ሰው በላው ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጻድቅ፣ ስለ ክርስቶስ ወንጌል የተገደሉና እንደሚታረዱ በጎች የተቆጠሩት አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ግን ኃጥኣን፤ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሃይማኖትን በካራ ለማስፋፋት ላወጀው ጭፍጨፋ ብርሃን የወረደለት የእግዚአብሔር ወዳጅ፣ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ለማርያም ሥዕልና ለመስቀል አንሰግድም ስላሉ መቅሠፍት የወረደባቸው አፅራረ እግዚአብሔር መሆናቸው ሲተረክ ምእት ዓመታት ዐልፈዋል፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ባስተረጎመውና የራሱንም ድርሰት ባካተተበት ተኣምረ ማርያም ይህን በማስነገር፣ በእርሱ ዘመን እንደተደረሰ በሚነገረው በ"ማኅሌተ ጽጌ" ላይም "ዘሰ ይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር ተኣምረኪ ክርስቲያናዊ ኢክርስቱን ውእቱ አይሁዳዊ ወሠርፀ እስጢፋ ሐሳዊ፤ - አንቺን እወዳለሁ እያለ ክርስቲያናዊ የሆነ ተኣምርሽን የማይወድ እርሱ አይሁዳዊ እንጂ ክርስቲያን አይደለም፤ እንዲያውም የዚያ የእስጢፋ ብቃይ ነው፡፡" በማሰኘትና ሌላም ብዙ ሐሰተኛ ወሬ በማስወራት ራሱን ትክክለኛ አባ እስጢፋኖስንና ተከታዮቹን ሐሰተኞች በማድረግ ታሪካቸውን ቀብሮ ኖሯል፡፡ ይሁን እንጂ ጊዜው ሲደርስ የእነዚህ ቅዱሳን ገድል ከተቀበረበት መውጣት ጀምሯል፤ የብዙዎች መነጋገሪያም ሆኗል፡፡ የሚገርመው የቅዱሳኑ የገድላት መጻሕፍት የኅትመት ብርሃን ያዩት ተመሳሳይ በሆነ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡ ተርጓሚዎቹና አሳታሚዎቹ በሳይሆንተለያየ ቦታና ሁኔታ ያሉ ቢሆንም በአንድ ወቅት ማሳተማቸው በራሱ የእነዚህ ቅዱሳን ገድል ከተቀበረበት የሚወጣበት ጊዜ መድረሱን የሚያበሥር ታላቅ የምሥራች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ በሌሎች ጉዳዮች ለአገራችን ጠቃሚ ሥራ የሠራ ንጉሥ መሆኑ ቢታወቅም፥ በክርስትና ላይ ካደረሰው አሉታዊ ተጽዕኖ አንጻር፥ በክርስትና ታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አያመልጥም፡፡ ከላይ የተጠቀሰው የእርሱ ማንነትም በዚሁ መንፈስ የቀረበ መሆኑን ለአንባቢ መግለጽ ያስፈልጋል፡፡እንዲረዳ ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌ፣ የተተረጎመው የአባ እስጢፋኖስና የተከታዮቹ ገድላት ከተለያዩ ጎኖች አንጻር እየታየና ልዩ ልዩ ትርጉም እየተሰጠው መወያያ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በርካታ ምሁራንም ተራ ገብተው የሐሳብ ፍጭት እያደረጉበት ይገኛሉ፡፡ ማጠንጠኛ የሆነው ነጥብ በንጉሡና በአባ እስጢፋኖስ መካከል የነበረው ውዝግብ በዋናነት ሃይማኖታዊ ነው ወይስ ፖለቲካዊ? የሚል ሆኖ ይታያል፡፡ በሁለቱም አቅጣጫዎች እየተንሸራሸረ ያለው አመለካከት በማስረጃ እየተደገፈ መቅረቡ ደግሞ ውይይቱን እንዲጦፍ አድርጎታል፡፡ በዚህ መካከል ግን በጊዜው የነበረውን የንጉሡንና የመነኩሴውን ግጭት ወደ ራስ ጉዳይ የመሳብና ለራስ አመለካከት ማዳበሪያ አድርጎ የማቅረብ ሁኔታ አልተስተዋለም ማለትም አይቻልም፡፡
በእስጢፋኖሳውያን ዙሪያ በርካታ ርእሰ ጉዳዮች መነሣታቸውና ሰዎቹ አነጋጋሪዎች መሆናቸው በራሱ ታላቅ ነገር ነው፡፡ ከሁሉ አስገራሚ የሆነው ግን ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ክርስቲያን፥ አባ እስጢፋኖስንና ተከታዮቹን ግን መናፍቃንና ፀረ ማርያም ሲሉ የነበሩ አንዳንዶች፥ «አባ እስጢፋኖስ የተሐድሶ አራማጅ አልነበረም» የሚል የዐቋም ለውጥ እያሳዩ መሆናቸው ነው፡፡ ለምሳሌ።- ገብር ሄር የተባለው ብሎግ ላይ ወንድምስሻ አየለ የተባሉ ቀሲስ «የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተ ክርስቲያን ተስፋ» በሚል ርእስ ባወጡት ጽሑፍ ውስጥ፥ ተሐድሶዎች የደቂቀ እስጢፋን ታሪክ ለሐሳባቸው ማስኬጃ ሊጠቀሙባቸው እንደሚፈልጉ ጠቅሰዋል  “ደቂቀ እስጢፋ ያላቸው ሐሳብ ከዛሬዎቹ ፕሮቴስታንታዊዎቹ ተሐድሶዎች ጋር ምንም ተዘምዶ የላቸውም” ሲሉም አክለዋል፡፡

ልብ እንበል! ጸሓፊው እስጢፋኖሳውያንን “ደቂቀ እስጢፋ” (የሰይጣን ልጆች) በሚለው የዘርዐ ያዕቆብ አጠራር ነው የጠሯቸው፡፡ ይህም በአንድ ወገን ለእስጢፋኖሳውያን ያላቸው አመለካከት ፈጽሞ እንዳልተቀየረ ያስረዳል፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ አባቶቻችን እነ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና እነ ዐፄ ልብነ ድንግል የቀበሩት የእነርሱ ታሪክ ለምን ወጣ? የሚል አንድምታ ያለው ይመስላል፡፡ ይህ ጉዳይ ብዙ ሳያነጋገር አይቀርም፡፡ ነገር ግን ይህን የዐቋም ለውጥ ያመጣው ከቶ ምን ይሆን? እንደ አስተያየት ሰጪዎቹ የእስጢፋኖሳውያንን ትክክለኛ ክርስቲያንነት በመገንዘብ ነው? ወይስ አሁን “ተሐድሶ” የሚል ስም የወጣላቸውን ወገኖች ደስ ላለማሰኘትና ከእስጢፋኖስ ዐላማ ለመነጠል? የሚለው ገና ብዙ ያወያያል፡፡

እንደ አመለካከታችን፣ እንደ ርእዮተ ዓለማችን፣ እንደ ሃይማኖታችን፣ ወዘተ. አንድን ታሪካዊ ክሥተት የምናይበት መነጽር የተለያየ ነው፡፡ ከሃይማኖታዊ አቋማቸው አንጻር አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ የተሐድሶ አራማጆች ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ፤  ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኀይሌ ናቸው፡፡ ይሁንና ይህን የማይቀበሉ አንዳንድ ወገኖችም አልጠፉም፡፡ ለምሳሌ፡- ይኩኖ አምላክ የተባሉ ሰው በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የኅዳር 2004 ዓ.ም. ዕትም ላይ ባወጡት ጽሑፍ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው የለውጥ አራማጆች ናቸው መባሉ ስሕተት መሆኑንና “በሌላው ዓለም እድገት ከመመሰጣችንና ያንኑም የሰውነት መስፈርት አድርገን ከማየታችን የተነሣ በሌላው ዓለም ያወቅናቸውን ባለታሪኮች ሊመስሉ የሚችሉትን አባቶች ፈለግን የብድር ንባባችንን ጫንባቸው፤ የሆኑትን ሳይሆን የፈለግነውን መልክ” ሰጠናቸው ሲሉ ጽፈዋል፡፡

ይህ የይኩኖ አምላክ አመለካከት ከምን የመነጨ ነው? በእኔ ግምት ተሐድሶ የሚለውን ነገረ መለኮታዊ ቃል አለመቀበልና የእስጢፋኖሳውያን እንቅስቃሴ በስምም በግብርም ከማርቲን ሉተር ዐይነት እንቅስቃሴ ፈጽሞ የተለየና አንዳች ንክኪ የሌለው መሆኑን ለማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚያ አስታከው ያሉበትን ሃይማኖታዊ ሥርዐት ለውጥ ወይም ተሐድሶ ሊያገኘው የማይገባ እንከን የለሽ አድርጎ መሣልም ይመስላል፡፡ ቀጥሎ የሰፈረውን ሐሳባቸውን እንመልከት፤

“የደቂቀ አስጢፋኖስን ክሥተት እስካሁን የጠቀስንበትና የተጠቀምንበት መንገድ ብዙም ትርፍ አላስገኘም፡፡ እስካሁን ድረስ ደቂቀ እስጢፋኖስ የሚባሉ የለውጥና የተሐድሶ አራማጆች በኢትዮጵያ ተነሥተው ነበር፤ እነ ማርቲን ሉተርንም ቀድመው ነበር የተነሡ፤ ግን ምን ይደረግ አልተሳካም ስንል ኖረናል፤ ለአንድ ኀምሳ ዓመታት፡፡ ይህ አንደኛ ስሕተት፤ ሁለተኛ ጥቅም የሌለው ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ውድቀትን ብቻ የሚዘግብ ነው፡፡ ስሕተትነቱ የእነ አባ እስጢፋኖስን ሐሳብ አዛብቶና ገልብጦ ማቅረቡ ነው፡፡ እነ አባ እስጢፋኖስ መለወጥን ሳይሆን መተከልን፣ መሰረትን አለመልቀቅን ነበር የሰበኩ፡፡ መጽሐፍ 'ካብ የሚያፈርስ እባብ ይነክሰዋል' ስለሚል 'አባቶችህ የሠሩትን ሥርዐት አታፍርስ'፤ የሐዋርያትና የነቢያት (የነቢያትና የሐዋርያት ቢል በቀና ነበር) ሥርዐት ሙሉ ሆኖ ሳለ ውሃ በላዩ የምትጨምርበት ምንድን ነው? ከሙሉው ጽዋ ላይ ውሃ ቢጨምሩበት ይፈሳል ነበር የሚሉ፡፡” ብለዋል፡፡

በቅድሚያ ስለ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቻቸው “ለአንድ ኀምሳ ዓመታት” ተባለ ያሉት፥ ከዚያ በፊት ከአራት ምእት ዓመታት በላይ በሌላ ገጽታ ስንል የኖርነው ነው እንጂ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ ልዩነቱ ለአራት ምእት ዓመታት እነርሱን “መናፍቃን፣ ፀረ ማርያምና ፀረ መስቀል” ሲሉ የነበሩት፥ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ትምህርት ተከታዮች (የእስጢፋኖሳውያን ተቃራኒዎች) መሆናቸው ነው፤ ከኀምሳ ዓመት ወዲህ የእነርሱን ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊነት የተመለከቱ (ደጋፊዎቻቸው) ደግሞ አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ የተሐድሶ አራማጆች ናቸው ይላሉ፡፡ እኒያ ለክፉ ያወጡትን ስም እኒህ ደግሞ ለበጎ ተጠቀሙበት ማለት ነው፡፡ «ተሐድሶ» የሚለውን ስም አንዳንዶች ዛሬም እንኳ አፍራሽ አድርገው ቢወስዱትም፡፡

እነአባ እስጢፋኖስ “የተሐድሶ አራማጆች” የሚል ስም ተሰጣቸው ያሉት ከግማሽ ምእት ዓመት ጀምሮ ነው፤ ይሁን እንጂ ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጊዜ አንሥቶ ከሃይማኖት ማፈንገጣቸውን በሚገልጹ ስሞች፥ ለምሳሌ፡- ፀረ ማርያም፣ ፀረ መስቀል፣ መናፍቃን፣ ወዘተ. እየተባሉ ሲጠሩ እንደ ነበረ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ላይ ቢኖሩ ኖሮ ተረኛው ስም «ተሐድሶ» ይወጣላቸው እንደ ነበረም አያጠራጥርም፡፡

አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ ከሃይማኖት አፈንግጠዋል ያልሁት በጊዜው ከሚታየው ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርትና ሥርዐት እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱሳዊው አስተምህሮና በዚያ ላይ ተመሥርቶ ከተደነገገው ሃይማኖታዊ ሥርዐት እንዳልወጡና በዚያው እንጽና እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ በዘመናቸው እንደ እነርሱ ባሉ መነኮሳትና በቀረውም ሕዝብ ሕይወት የሚስተዋሉትን ክርስቲያናዊ ያልሆኑ ትምህርቶችንና አካሄዶችን ግን ተቃውመዋል፡፡ ይህ ነው የለውጥ ወይም የተሐድሶ አራማጆች የሚያሰኛቸው፡፡

ተሐድሶ ከእግዚአብሔር ለሰዎች የተሰጠውንና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ላይ የተመሠረተውን ሃይማኖት መለወጥ አይደለም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ሐሳብ መሠረት መኖር፣ ከእርሱ ተቃራኒ የሆኑ ሰው ሠራሽ ትምህርቶችንና ልማዶችን በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ማረምና ማስተካከል ነው፡፡ እስጢፋኖሳውያን በደረሱበት መረዳት ለማድረግ የሞከሩት ይህንኑ ነው፡፡ ተሐድሶኣውያን ናቸው ያሰኛቸውም ይኸው እንቅስቃሴያቸው ነው፡፡ መቼም በአገራችን ከእነርሱ በፊት በታሪክ ትልቅ ቦታ የተሰጠው የተሐድሶ እንቅስቃሴ ተደርጓል ማለት ባያስደፍርም፥ አንዳንድ መጠነኛ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ፡- የሥዕል አምልኮን የተቃወሙ ሰዎች የእነ አባ እስጢፋኖስ ተሐድሶኣዊ እንቅስቃሴ በተመሠረተበት በትግራይ ክልል ውስጥ ተነሥተው እንደነበረ ፕሮፌሰር ጌታቸው ጠቅሰዋል፡፡ ይሁን እንጂ በእስጢፋኖሳውያን አማካይነት ከተካሄደው እንቅስቃሴ አንጻር ያን ያህል የታወቀ ነበር ማለት አያስደፍርም፡፡ ነገር ግን ለእስጢፋኖሳውያን እንቅስቃሴ ያበረከተው አስተዋፅኦ ጨርሶ የለም ማለት አይቻልም፡፡

ይኩኖ አምላክ እንዳሉት፥ እስጢፋኖሳውያንን የተሐድሶ አራማጆች ነበሩ የተባለው ከምዕራባውያን ጋር ለመፎካከርና ለአባቶቻችን አለስማቸው ስም ለመስጠት ተፈልጎ አለመሆኑ ከግምት ሊገባ ይገባል፡፡ በርግጥ በዚህ ሐሳብ ላይ መግባባት የሚቻለው «ተሐድሶ» ስለ ተባለው ነገረ መለኮታዊ ቃል በስማ በለው ሳይሆን በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ግንዛቤ መጨበጥ ሲቻል ነው፡፡ ብዙዎች ቃሉን ከማርቲን ሉተር ፕሮቴስታንታዊ እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሥርዐት ለመበረዝና ለመከለስ ወይም ለመለወጥ የተነሣ የአዲስ ሃይማኖት ስመ ተጸውኦ አድርገው እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ አጠቃቀማቸው አሉታዊነት ይንጸባረቅበታል፡፡ ይኩኖ አምላክም እስጢፋኖሳውያንን ከዚህ ነጻ ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉ ይመስላል፡፡

እስጢፋኖሳውያን የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጆች ነበሩ የተባሉት፥ በገድላቸው ተጽፎ እንደ ተገኘው በልዩ ልዩ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው እውነት በማፈንገጥ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ በሆኑ ትምህርቶችና ልምምዶች ሥር የወደቁ መነኮሳትንና ምእመናንን በእግዚአብሔር ቃል ለማቃናትና ለማስተካከል፥ በቃልም በሥራም ካደረጉት የለውጥ እንቅስቃሴ አንጻር ነው፡፡ ይኩኖ አምላክ እንዳሉት «እነ አባ እስጢፋኖስ መለወጥን ሳይሆን መተከልን፣ መሰረትን አለመልቀቅን ነበር የሰበኩ፡፡ መጽሐፍ 'ካብ የሚያፈርስ እባብ ይነክሰዋል' ስለሚል 'አባቶችህ የሠሩትን ሥርዐት አታፍርስ'፤ የሐዋርያትና የነቢያት (የነቢያትና የሐዋርያት ቢል በቀና ነበር) ሥርዐት ሙሉ ሆኖ ሳለ ውሃ በላዩ የምትጨምርበት ምንድን ነው? ከሙሉው ጽዋ ላይ ውሃ ቢጨምሩበት ይፈሳል ነበር የሚሉ፡፡» ይህ በመርሕ ደረጃ ትክክል ነው፡፡ በአባ እስጢፋኖስ ጊዜ በተግባር የሚታየው ግን ከዚህ በተቃራኒ ስለ ነበረ፥ መሠረታችንን አንልቀቅ፤ የለቀቅንም ወደ መሠረታችን እንመለስ ነበር የእነርሱ ተጋድሎ፡፡ በትምህርታቸው መሳጭነት የተበሳጩትና በመንፈሳዊ ኑሯቸው ማራኪነት ውስጣዊ ሰብእናቸው የተከሰሰው መነኮሳት ግን ልዩ ልዩ ስም ሰጥተው አባ እስጢፋኖስን በመጤ ሃይማኖት አቀንቃኝነት እስከ መክሰስ ደርሰው ነበር፡፡

የክሳቸው አንዱና ዋነው ጭብጥ “የሀገራችን ትምህርት ያልሆነ ታስተምራለህ» የሚል ነበር፡፡ አባ እስጢፋኖስም ሲመልስ፥ «የአባቶቻችን ያልሆነውን አመጣ የሚሉት እኔ ከእግዚአብሔር ሕግ በቀር ሌላ ያስተማርሁት ነገር የለም” (ደቂቀ እስጢፋኖስ ገጽ 80) ብሏል፡፡ እንደ ገናም “የዚህች አገር ትምህርት ምንድር ነው? እንዴትስ የሌላ ነው?” በማለት ጥያቄያቸውን በጥያቄ ይመልሳል፡፡ እኔስ “በክርስቶስና በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ከሆነው ሁሉ በቀር ሌላ አላውቅም፡፡” (ዝኒ ከማሁ ገጽ 87) ሲልም የቤተክርስቲያንን አሐቲነት በማወጅ፥ ከሳሾቹ “የእኛ” እና “የእነርሱ” በሚል ያቀነቀኑትን፥ በቤተክርስቲያን ትምህርት ውስጥ የሌለውንና ብዙዎች ዛሬም እንኳ በጭፍን የሚያቀነቅኑትን የልዩነት አመለካከት አፍርሶታል፡፡ ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ የነበረና ያለ፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቁና በክርስትና ስም የሚጠሩ ወገኖች ግን ያላስተዋሉት እውነት ነው፡፡ አባ እስጢፋኖስ በምላሹ፥ ባለማወቅ የተጣለውን ይህን የከበረ እውነት ወደ ስፍራው መልሶታል፡፡ ከዚህ አንጻር አባ እስጢፋኖስ የተሐድሶ አራማጅ አልነበረም ማለት እንዴት ይቻላል?

ከሳሾቹ ስሙን በከንቱ ሲያጠፉ የነበረ ቢሆንም፥ መኳንንቱ ግን የክሱ መነሻ ቅናት መሆኑን በመገንዘብና በትምህርቱ የተገኘውን ጥቅም በመግለጥ ስለ አባ እስጢፋኖስ እውነተኛ ምስክርነት የሰጡበት ጊዜ ነበረ፤ እንዲህ በማለት፥ “አባት ሆይ የቃልህን እውነትነት፥ የትምህርትህንም ሥርዐት ትክክለኛነት፥ በእውነት የእግዚአብሔር መሆኑን የማናውቅ አይደለንም፡፡ አንተ በዚህች በምድራችን ላይ ከሄድክባት ጊዜ ጀምሮ ምሕረት ወርዷል፡፡ የትምህርትህን ስብከት በመስማት ብዙ ስሕተቶች ተወግደዋል፡፡ ይህም እዚህ ብቻ ሳይሆን ዜናህ በተሰማባቸው በሩቆች አገሮች ሁሉ ነው እንጂ፡፡” (ደቂቀ እስጢፋኖስ ገጽ 79-80)፡፡ ልብ እንበል! “የትምህርትህን ስብከት በመስማት ብዙ ስሕተቶች ተወግደዋል፡፡” ነው ያሉት፡፡ ታዲያ ከዚህ የበለጠ የእርሱን የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅነት የሚያስረዳ ምስክርነት ከወደ የት ይገኛል?

በሌሎች ገድላትና ድርሳናት ውስጥ ለፍጡራን የተሰጠውን የአዳኝነት ሥራ ወደ እውነተኛው አዳኝ በመመለስ ረገድም አባ እስጢፋኖስ ተሐድሶን አካሂዷል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ “ፈጣሪ ካልሆነ በቀር ሌላ ሊሠራው የማይችለውን ሕይወትን የመስጠትና የማዳን ሥራውን አሳየ (ገለጠ)” (ገድለ እስጢፋኖስ ዘጉንዳ ጉንዶ ገጽ 101) ሲል መስክሯል፡፡ ይህን እንደ ታሪክ መተረክ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ የእያንዳንዱን ሰው የኀጢአት ዕዳ ለመክፈል እንደ ሞተ በማመን ሊድን የሚችልበትን መንገድ ማሳየት የትምህርቱ ማእከል ነበረ፡፡ “የሕይወትን መንገድ ለሚፈልግ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ተናግሬአለሁ፤  … በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲድኑና እንዲያገለግሉት የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርሁ” (ገድለ አቡነ እስጢፋኖስ ዘጒንዳ ጒንዶ ገጽ 85)፡፡ ዛሬም እንኳ በክርስትና ስም እየተጠራንና የክርስትናን ማእከላዊ ሐሳብ “መዳን የሚገኘው በእግዚአብሔር ጸጋ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ በተከናወነው የቤዛነት ሥራ ነው” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ሸራርፈንና ለውጠን፥ ብዙ የመዳኛ አማራጭ መንገዶችንም ቀይሰን ላለነው ክርስቲያኖች ጭምር የአባ እስጢፋኖስ ተጋድሎ የነበረው፥ ሰዎች ሁሉ እርሱ ያገኘውን ዕረፍተ ነፍስ እንዲያገኙ ነበር፡፡ ታዲያ እርሱ የተሐድሶ አራማጅ ነው ያልተባለ ማን ሊባል ነው?

እዚህ ላይ አንድ መታወቅ ያለበት እውነት ያለ ይመስለኛል፡፡ ይኩኖ አምላክ እስጢፋኖሳውያን የተሐድሶ አራማጆች ላለመሆናቸው ያቀረቡት አንዱ ማስረጃ የማርያምን ስም መጥራታቸውንና በስሟ መማጸናቸውን ነው፡፡ በእኔ ግምት ይህ የተሐድሶን እንቅስቃሴ አንዳንዶች እጅግ አክፍተው ባቀረቡበት መንገድ ከመረዳት የተነሣ የተያዘ አቋም እንጂ፥ እስጢፋኖሳውያንን የተሐድሶ አራማጆች አይደሉም ላለማለት በቂ ምክንያት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡

አባ እስጢፋኖስም ሆነ ከእርሱ በኋላ በምዕራቡ ዓለም ለመጣው ተሐድሶ ፈር ቀዳጅ የሆነው ማርቲን ሉተር የተሐድሶ አራማጆች ናቸው ሲባል፥ በእነርሱ የተነሡት ጉዳዮች በቂዎችና የመጨረሻዎች ነበሩ  ማለት አይደለም፡፡ እነርሱም በያዟቸው አንዳንድ ነገሮች ላይ ጭምር ሌላ ተሐድሶ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እንደ ነበሩ ግልጽ ነው፡፡ ከማርቲን ሉተር በኋላ እንኳ ሌሎች ተሐድሶኣውያን በማርቲን ሉተር ጊዜ ባልጠሩና በርካታ መታደስ፣ መሻሻልና መወገድ በነበረባቸው ነገሮች ላይ ተሐድሶን ዐውጀዋል፡፡ ነገሩ በዚህ መልክ ነው እየቀጠለና እየዳበረ የመጣው፡፡ የእኛው ችግር ግን በእነ አባ እስጢፋኖስ የተለኮሰውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ማቀጣጠል ሲገባና ወደ ተሻለ ተሐድሶ መሸጋገር ስንችል፥ እነርሱንም እንቅስቃሴአቸውንም ያነሧቸውን ታላላቅ ተሐድሶኣዊ ሐሳቦችንም በዐጭሩ ቀጨናቸው፡፡

ምናልባት ዛሬ የእነርሱ የተጋድሎ ታሪክ ከተቀበረበት እየወጣ በመሆኑ፥ ብዙዎች ዐርማቸውን አንሥተው የወጠኑትን ተሐድሶ ከግቡ ለማድረስ የሚችሉበት ጊዜ የመጣ ይመስላል፡፡ ለዚህ እውን መሆን ግን ቢያንስ ተሐድሶ በሚለው ፅንሰ ሐሳብ ላይ ከተራ አሉባልታ ወጥተን ትክክለኛ ግንዛቤ መያዝ ይኖርብናል፡፡ ተሐድሶ አፍራሽ ሳይሆን ገንቢና ጠቃሚ፥ ሃይማኖትን ጨምሮ ሁሉንም የሕይወታችንንና የኑሮአችንን ክፍል የሚዳስስ፥ መንፈሳዊም ተፈጥሮኣዊም የለውጥ ጥሪ ነውና፡፡

መምህር በጸጋው አማረ

13 comments:

 1. ''ተሐድሶ ከእግዚአብሔር ለሰዎች
  የተሰጠውንና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ
  ላይ የተመሠረተውን ሃይማኖት መለወጥ
  አይደለም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ በተገለጠው
  የእግዚአብሔር ሐሳብ መሠረት መኖር፣
  ከእርሱ ተቃራኒ የሆኑ ሰው ሠራሽ
  ትምህርቶችንና ልማዶችን በእግዚአብሔር
  ቃል መሠረት ማረምና ማስተካከል ነው፡፡
  እስጢፋኖሳውያን በደረሱበት መረዳት
  ለማድረግ የሞከሩት ይህንኑ ነው፡፡''
  This your words but a true one.So why do you pull them to your camp by say the opposite.''

  ReplyDelete
 2. Ere enante sewoch, Motewem enkuan be mahebere kidusan litaswoguzuachew neew.

  ReplyDelete
 3. tera were yazele blog

  ReplyDelete
 4. Schools of Tehadeso:

  1) Those who passionately care for the true faith and seek reform to clean the dust thrown against the church over the years.

  2) Hirlings of the Protestant church who are bent on corrupting the EOTC core faith, spreading confusion, stealing innocent sheep and eventually destroying the EOTC.

  3) Confused folks who think the Protestant faith is a true way to life and would like the EOTC changed accordingly.

  4) Weyane tplf who wants to divide the EOTC and make it disunified so that they can stay in power for generations without opposition from the followers of the church. Mind you EOTC was a power broker during the old days and Weyane fears it a lot. Also, Weyane considers the church as the den of neftagna Amhara, who they consider as their sworn enemy.

  ReplyDelete
 5. በርቱ ተበራቱ ቀጥሉበት እውነትን ግለጡ፡፡ ዋሾን አስደንግጡ፣ ለቃሉ ኑሩ፣ እንዲህ ያለ አገልግሎት ጥሩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. let us know the truth. we are behind the gospel of God. Bible! Bible! Bible! the other day when I was reading the book of Nicodemus( I book printed in 1926 which is among the lost books of the bible) I found that even Pilate (pilatose) and other Jesus accuser, praised the lord Jesus. I do not understand why our church bihind knowing the son of God.

  ReplyDelete
 7. አይ ተሃድሶ ዘመድ ለማግኘት የማታደርጉት ጥረት የለም::
  በቅርቡ በፕሮፌሰሩ የተተረጎመው የደቂቀ እስጢፋኖስና የተከታዮቹ ታሪክ ትክክለኛ ከሆነ ከእናንተ በብዙ ይለያሉ:: ከልዩነታችሁ መካከል
  • እነርሱ መነኮሳት የነበሩ በትርህምት የሚኖሩ ነበሩ እናንተ ምንኩስናን ትቃወማላችሁ
  • እነርሱ በመልካም ስራ የሚያምኑ በሃይማኖት ጸንተው በሃይማኖትም ለመኖር የሚታገሉ ነበሩ እናንተ መልካም ስራ ለጽድቅ ዋጋ የለውም የምትሉ ናችሁ
  • እነርሱ አዲስ የመሰላቸውን ነገር /ለማርያም መስገድን/ አንቀበልም ቢሉም ጳጳሱ ባስተማራቸው ጊዜ የተረዱና ለድንግል ማርያም ስግደትን ያቀረቡ ናቸው በአንጻሩ እናንተ እንደማታደርጉ የታወቀ ነው::
  • እነርሱ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን ለመጠበቅ የተጉ ናቸው እናንተ ደግሞ ፈረንጂ የነገራችሁንና ለማድረግ
  • እነርሱ በድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት የሚያምኑ የሚማጸኑ እንደነበር ተጽፏል እናንተ ይህንን እንደ ፌዝ እንደምትቆጥሩት ዌብሳይታችሁ አሳይታናለች
  ሌላም ብዙ መጨመር ይቻላል::

  ReplyDelete
 8. to those «Tewahedo said» & his followers፣
  1, ተአምረ ማርያም ራሱ መጣሁ የሚለው ዘርዓ ያዕቆብ በነገሰ በ7ኛው ዓመት ነው። የእነእስጢፋኖስ ጠብ ሀ/ ለንጉስ ስገዱ የሚለው ትክክል አይደለም።
  ለ/ ለስእል ስገዱ የሚለው ትክክል አይደለም።
  ሐ/ ለመስቀል ስገዱ የሚለው ትክክል አይደለም።
  ነው ሲሉ የነበሩት። ምክንያቱም ከዚያ በፊት እንደዚህ የሚል የአበው አስተምህሮ አልነበረምና ነው። ክርስትና ከዚያ በፊት 1200 ዓመት በሀገሪቱ የኖረ ሆኖ ሳለ ዘርዓያእቆብ በ15ኛው ክ/ዘመን ምንኩስናውን ትቶ ሲነግስ አዲስ ትምህርት ማምጣቱ ክህደቱ ነው።
  2/ ተአምረ ማርያም ከግብጽ መጣሁ ይበል እንጂ ከመጣ በኋላ ብዙ ድሪቶ ተደርቶበታል። ወይ እንደመጣ የያዘውን ይዞ አላረፈ፤ እዚህ ገብቶ እነደብተራ ገለፈቶች ሲጨምሩበት ኖረዋል። ይኸውም፣
  ሀ/ ስለአባ እስጢፋኖስ ከሃዲነትና የግድያ ታሪክ ነገሩ ደብረ ብርሃን ከተፈጸመ በኋላ የተጨመረው እዚሁ ነው።
  ለ/እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ታሪክ ገብቶበታል። «አውገዝነ ወአሰርነ በማእሰር ዘኢይትፈታህ» የሚለው ውግዘት ከግብጽ መጣ በተባለው ተአምር ውስጥ የሀገር ቤቶቹ ሲጨምሩበት እርግማኑ አይሰራባቸውም? ከመጣ በኋላ መጨመር ከሌለበት አሁን ያለው ትክክል አይደለም ማለት ነው። የለም! መጨመር ይቻላል የሚባል ከሆነ ውግዘቱ አይሰራም ማለት ነው። ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እነመምሩ ከቅዳሴ በኋላ ይዘው ብቅ ይሉና አባ ሚካኤል፤አባ ገብርኤል በተባሉ ሊቃነጳጳሳት በውግዘት የጸና ተአምር ብለው በማንበብ እራሳቸውንም ህዝቡንም አውግዘው ወደቤተመቅደስ ይገባሉ። ህዝቡም አሜን፤ አሜን ይላል።
  3/ቅድስት ማርያም ተአምሬ ካልተነበበ ክርስትናችሁ የተሟላ አይደለም አትልም። እርሷ የጌታ እናት ሆና እዚህ ምድር እንዳሉ በእርግማን ያጸኑትን አፍርሰው በፈለጋቸው ጊዜ እንደሚጨምሩት ወይም አፍንጫና ጆሮ ቆርጠው ከነሕይወታቸው ሰው እንደሚቀብሩ ዘርዓ ያዕቆባዊ ኦርቶዶክሶች አይደለችም። ድንግል ማርያም ሁሉን ነገር በልቧ የምትጠብቅ የትእግስትና የትህትና እናት እንጂ ተአምሬ ካልተነበበ ብላ ህዝቡን በጳጳሳት የምታስወግዝ ጨካኝ አይደለችም። «የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም» ብላ ባዶ ለሆኑ ሰዎች የምታሳስብ እንጂ አፍንጫና ጆሮ እንዲቆረጥ፤ ከነህይወታቸው ተቀብረው የሞቱ ሰዎችን የርሷ ተአምር አድርጋ የምታስብ አይደለችም። የተባለው መጽሐፍ እስኪመጣ እስከ15ኛው ክ/ዘመን ድረስ ያሉ ኦርቶዶክሶች በማርያም የተረገሙ ናቸው? ወይም ተአምር ከመጣ በኋላ ያሉ ኦርቶዶክሶች ጥዋት ጥዋት ከውግዘት ለመዳን ስለሰሙ ከማንም የበለጠ የተባረኩ ናቸው? ብላም አታስብም።
  በጥቅሉ ሰዎች ማርያምን ከፍ ከፍ ያደረጉ መስሏቸውና ይህንን በማድረጋቸው ከማንም ቀድመው ገነት የሚገቡ የሚመስላቸው ሰዎች ከውግዘት በፊትና በኋላ የመሰላቸውን ጽፈው የዋሁ ህዝብ ግእዙን ሳያውቅ አሜን አሜን ስለሚል ስር ተክሎ ኖረ እንጂ ማርያም የኔ ተአምር ብላ የሰጠችው ሰውም የለ፣ መጽሐፍም የለ!! ወደድንም ጠላንም እውነቱ ይህ ነው። ዳሩ ግን ለመረዳትና ለማወቅ ስንፍና ቤቱን የሰራባቸው ይህንን አይቀበሉትም። መጽሐፍም እንዲህ ይላቸዋልና። «ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ስንፍናው ከእርሱ አይርቅም» ምሳ27፣22

  ReplyDelete
 9. ገድለ እስጢፋኖስ ያልከው ላይ እንዲህ አንደሚልስ ታውቃለህ?

  "በዛ ላይ አንደ ሌሎቹ ሁሉ የቅዱስ ኤፍሬምን ውዳሴ ማርያም እና የቅዱስ ያሬድን አንቀጸ ብርሃን ይደግሙ ነበረ:: እነዚህ ሁለት ድርሰቶች እመቤታችንን የሚያደንቁና የሚያመሰግኑ:በየአንቀጹ 'ሰአሊነ ቅድስት' (ቅድስት ሆይ: ኃጢያታችንን ይቅር እንዲለን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ዘንድ አማልጅን)የሚል ንባብ ያለባቸው ናቸው::ጳጳሱም ለቅድስት ድንግል ማርያም ብትሰግዱ ስህተት አይሆንባቹም ብለዋቸው አብረው መስገዳቸውን መስክረዋል::" ገጽ 30
  አንተ አሁን ገድለ እስጢፋኖስ ተቀብለህ ታምረ ማርያምን ለማቃለል ትሞክራለህ? ነው ወይስ አጼ ዘርዓ ያዕቆብን ይሰድብልኛል ብለህ ነው? ገድለ እስጢፋኖስም እኮ አስከሬናቸውን ፈወሰ ይላል:: አመንከው?????
  እና እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆነው እስከችግሩ ነው የምንቀበለው:: አንተ ካልተመቸህ ከቤተክርስቲያናችን ውልቅ በልልን:: ስንቱ የቤተክርስቲያናችን ምሁር ቦታ አጥቶ ሎተሪ ያዞራል አንተ ሁለት ደሞዝ ትበላለህ::ከንቱ::

  ReplyDelete
 10. "ለንጉስ ስገዱ የሚለው ትክክል አይደለም።"
  መፅሐፍ ቅዱስ መመሪያዬ ነው ካለ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲህ እንደሚል አባ እስጢፋ አላነበበውም?

  ምዕራፍ 2 ቁጥር 13
  'ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤

  ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።'

  ReplyDelete
 11. 2ኛ ጴጥ 1፡20 ማንም የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃላት እንደፈለገው መተርጎም እንደማይችል ተጽፏል የሐመር መጽሔት አዘጋጆች የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጉም በማጣመም የራሳቸውን ሀሳብ ያንጸባርቃሉ፡፡ ተብሎ ከደረሰን ደብዳቤ \የሚከተለውን አውጥተናል፡፡

  እስከ አሁን በእኔ የኢሜል አድራሻ samuelabay68@yahoo.com በርካታ የሐመርና የስምዐ ጽድቅ፣ የልዩ ልዩ ሕትመቶች፣ ሐመረ ጽቅ በተለይ የተሰራጩ የኑፋቄ ትምህርቶች ደርሰውናል ለጻፋችሁ ሁሉ ወደ ፊትም ለምትጽፉ የላቀ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ ጽሑፎቹን የማናወጣው በተሰጠን አስተያየት መሠረት ኑፋቄው በአግባቡ ለቅዱስ ሲኖዶስ በሚደርስ መንገድ መዘጋጀት ስላለበት ነው፡፡ ግን መጽሔቱና ጋዜጣው አሁንም ከስሕተት የማይጠራ መሆኑን ለመግለጽ የቅርቡ የባለፈው ክረምት ሕትመት ሐመር 19ኛ አመት ቁጥር 3 ሐምሌ 2003 ሕትመት ምን አለ መሰላችሁ

  የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉ ጥቃቅን ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን፡ መኃ 2፡ 15 በሚል ርዕስ "በመ/ር ሰሎሞን መኩሪያ" የተጻው በራሱ ፍላጉትን ስጋና ደሙ በመራ ሲተረጉም፡፡ ከዋናው ትርጉም ትምህርት ፈጽ የማይገናኝ ፍጹም ክህደት የሆነ ትምህርት አስተምሯል፡፡

  ለማነጻጸር እንዲመቻችሁ ዋናውን ትርጉም ከመጽሐፈ ሰሎሞን ትርጓሜ የመኃልይ መጽሐፍ ትርጉም ምዕራፍ 2 ቁጥር 15 ተመልከት፡፡

  የወይን ቦታችንን የሚያጠፉ ንዑሳን ቀበራርትን አጥፉልን፡፡ የሕግ (እግዚአብሔርን የመፍራትና አባቶችን የማክበር፣ መንፈሳዊነት) ማደሪያ ልባችንን የሚያስቱ ነቢያተ ሐሰትን ካህናተ ጣዖትን አጥፉልን፡፡ አንድም ወንጌል ያለ ኦሪት፣ ጥምቀት ያለ ግዝረት አትጠቅምም እያሉ የሕግ ማደሪያ ልባችንን የሚያስቱ ሐሰተኛ ወንድሞችን አጥፉልን፡፡ ነው፡፡

  ከጥቅሱና ከትርጉም እንደምንረዳው ትናናሽ ቀበሮዎች ሐመርና ስምዐ ጽድቅ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በቤተ ክህነት ጥላ ስር ትናናሽ ቤተ ክህነት ለመመስረት የሚጣደፉ በወንጌል ላይ ፖለቲካና ሐሜት ብጥብጥ የሚፈጥሩ፣ በመንፈሳዊነት ላይ ስጋዊ ንግድ የሚነግዱ፣ በአለም አቀፋዋቷ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሰፈር ቡድነኛነትን የሚያካሄዱ ያንን ስራቸውን ወደ ሌላ ለማላከክ፡፡ ባለ አክሲዎን "በመ/ር ሰሎሞን መኩሪያ" በኑፋቄ አዘል ጽሑፍ ወይኑን በጌታ መሰለ እንግዱህ ትልቁ ክህደት መናፍቁ ጸሐፊ በወይን የመሰለውን ጌታችንን መድሐኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብል የማይበላው፣ ነቀዝ የማያበላሸው፣ ማእበል ማይገፋው፣ የማይጠልቅ ጸሐይ እያሉ ሊቃውንት ያስተማሩለትን ያሁኑ አስተማሪ በጽሑፉ ገጽ 4-5 ላይ ወይኑን ክርስቶስን ጥቃቅን ቀበሮዎች 1/ ተሸልከው ይገቡበታል፣(ገጽ 5 ሁለተኛ አንቀጽ) 2/ ወይኑን ያበላሻሉ፣ (ገጽ 5 ሶስተኛ አንቀጽ) 3/ የወይኑን ሥር በመቁረጥ ወየኑን ያደርቁል፡፡ (ገጽ 5 አራተኛ አንቀጽ) እያሉ ያስተምራሉ፡፡ በርግጥ ወደ ውስጥ ሲገባ ብዙ ክህደት አለ
  ስለዚህ፡፡ እነዚህ ሳይማሩ እናስተምር፣ ሳይጠመቁ ኪራይ ሰብሳቢ መዋጮ ሰብሳቢ አስራት ተቀባይ የሆኑ ሰዋች ከከሀዲም ከመናፍቅም በላይ የከፉ ብዙ ነገር ስላለባቸው ምን ብለል እንደምንፈራጃቸው ከአሁኑ እናስብበት፡፡

  ስለዚህ ለማኛውም ሕትመቶቻቸውን ስታነቡ፣ የተኮረጁ፣ የሰዋችን ስም ለማጥፋትና ታዎቂ እንዳይሆኑ ለማድረግ ስራቸውን የተዘረፉ፣ ቃል በቃል የተገለበጡ፣ የተሳሳቱ፣ ትርጉቸው የተጣመመ፣ የቡድን ፕሮፖጋንዳ የተላለፋባቸው፣ የሰው ስም በከንቱ የጠፋባቸው፣ ታሪክ ሆን ተብሎ ተዛባባቸው፣ ከመንፈሳዊ ዓላማ ውጭ የተለየ ትምህርት የሚያስተምሩ፣ ሰዎችን መተቀሚያ ለማድረግ የተጻፉ፣ ፖለቲካ አዘል ጽሑፎች የመሳሳሉት በተመለከተ ደርሶናል፡፡ የትርጉም ስራዎቻቸውን በተመለከተ የተተረጎመው የማን መጽሐፍ እንደሆነ ሃይማኖቱ፣ ዓላማው፣ ሲተረጎም የተወሰደው የስራ ሂደት፣ የድምጽ የምስል ስራዎቻቸውንም በመገምገም ከዚህ ሌላ ካለ ወይም ለዚህ ማጠናከሪያ የሚሆን ሌላም ካለ አሁንም እያሰባሰብን ስለሆነ samuelabay68@yahoo.com ወይም በፈለጋችሁት መንገድ ሊገኘ በሚችል ሁኔታ ጻፉልን፡፡ ትናናሽ ቀበሮዎችን አብረን እናድናለን፡፡

  ReplyDelete
 12. Selam Wondimoch. According to Gedle Estifanos, Zerayakob is very harsh man who did very bad things on them. I don't appreciate their faith and the purpose that the king hate them is since they don't bow for him. Really sad to be king have power. Like the woyannes kill may people.

  Any how this has learnt us something about Zerayacob and them. However I know that they are not like Tehadisos of these days. Rather they are more close to orthodox tewahedo belief than tehadiso.

  Tewahedo

  ReplyDelete
 13. ትናናሽ ቀበሮዎችን አብረን እናድናለን፡፡
  አንተን ትልቁን ለምድ የለበሰ ተኩላ:ቀበሮ ማን ያድንህ ታዲያ? ማህበረ ቅዱሳን?

  ReplyDelete