Friday, December 2, 2011

ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ መጥሪያ ወጣባቸው - - - Read PDF

በብፁዕ አቡነ ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ መሠረት ታደሰ ላይ «ስሜን አጥፍታለች» የሚል ክስ የመሠረቱትና ክስ መስርተው ሲያበቁ በቀጠሮው ዕለት በ18/3/2004 ዓ.ም ያልተገኙት አባ ሳሙኤል በፖሊስ ተይዘው በ28/3/2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ መጥሪያ የወጣባቸው መሆኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተናገሩ፡፡
ወ/ሮ መሠረት በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ላይ ክስ መመስረታቸውን ተከትሎ አባ ሳሙኤል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሰው ልከው ሊቀጳጳስ ስለሆንሁ ወዳለሁበት መጥታችሁ ቃሌን ተቀበሉ ሲሉ በመልእክተኛ ክስ ለመመስረት ሞክረው ነበር፡፡ ፖሊስም ለተላከው ሰው ማንም ከህግ በላይ ሊሆን ስለማይችል እዚሁ ድረስ መጥተው መክሰስ ይችላሉ የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡ አባ ሳሙኤልም ሳይወዱ በግድ ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ክስ ይመሰርታሉ፡፡ ፖሊስም ተከሳሿ እንዲቀርቡ አድርጎ ጉዳዩ ወደፍርድ ቤት ያመራል፡፡ ይሁን እንጂ በቀነ ቀጠሮው አባ ሳሙኤል ፍርድ ቤት ሳይገኙ ይቀራሉ፡፡ ወ/ሮ መሠረት ግን በብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ዋስ ተለቀዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ አባ ሳሙኤል በፖሊስ ተይዘው ለ28/3/2004 ዓ.ም እንዲቀርቡ ያዘዘው፡፡
ከዚህ በፊት አባ ሰላማ ብሎግ ላይ ወ/ሮ መሰረት በፍርድ ቤት የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ህጋዊ ወራሽ መሆናቸው የተረጋገጠ መሆኑን መዘገቡ ይታወሳል፡፡ አባ ሳሙኤል በወ/ሮ መሰረት ላይ ክስ የመሰረቱት ያንን ዘገባ ተከትሎ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸው፣ በቀጠሮው ቀን ያልተገኙትም የመሰረቱት ክስ እንደማያዋጣቸው ስላወቁ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡
ጳጳሳት ሲሞቱ ሀብታቸውና ንብረታቸው የቤተክርስቲያን ይሆናል የሚለውን የቆየ ድንጋጌ በማሻሻል ለዘመዶቻቸው እንዲያወርሱ በሲኖዶስ ከተወሰነ ከጥቂት አመታት ወዲህ የጳጳሳት ሕጋዊ ወራሾች ነን የሚሉ ሰዎች፣ በተለይም ሚስት እና ልጅ ነን የሚሉ ወራሾች መነሣታቸው ጉዳዩን አነጋጋሪ እያደረገው ሲሆን፣ ይህን ለመሸፋፈን በሚደረገው ጥረትም ወደአላስፈላጊ ንትርክ መገባቱና የሰዎች ሰብኣዊ መብት እየተጣሰ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ቤተክርስቲያኗ መፍትሔ ካላበጀችለት ጉዳዩ በዚህ እንደማያበቃ ብዙዎች አስተያየታቸውን በመስጠት ላይ ናቸው፡፡   

26 comments:

 1. Hi Aba Selama:
  This is tasteless,unethical and irresponsible. "...."BEDEKEMEW ATIFREDU"

  ReplyDelete
 2. ምንኩስና የተጀመረው በምንኩስና አራማጅ አብያተክርስቲያናት ዘንድ እንጦንስን ይጠቅሳሉ። ይሁን እንጂ ምንኩስና ከዚያ ቀደም ብሎ በ6ኛው ክ/ዘመን ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በቡድሃ ሃይማኖት መስራቹ በጉተማ በኩል በህንድ ሀገር እንደሆነ ታሪክ ያረጋግጣል። ስለሆነም በ4ኛው ክ/ዘመን ድኅረ ልደተ ክርስቶስ ወደግብጽ ሀገር ያስገባው በአባቱ ሞት መሪር ሃዘን የተሰማውና የሃብት ውርስ ሙግትን ንቆ የኮበለለው አባ እንጦንስ ነው። እንደዚያ እንደዚያ እያለ የጥንቱ የቡድሃ ስርዓት ክርስቲያናዊ መልክና ህግ ይዞ በየሀገሩ ብቅ አለ።
  በመሰረቱ በአዲስ ኪዳን ለክርስቶስ ወንጌል ሲሉ ሁሉን የተዉ፣ የወንጌል አገልግሎትን የሕይወታቸው አንድ አካል አድርገው ለመኖር የወሰኑ ብዙ ቅዱሳን ነበሩ፣አሉም። ሰው ጋብቻን መተው የሚችለው በጋብቻ ኃጢአት እንዳለ ስላመነ ሳይሆን ያለጋብቻ(ትዳር) ለመኖር አዳማዊ ተፈጥሮውን ማሸነፍ የሚችል መሆን ይገባዋል። እንደዚያም ስጋውን ማሸነፍ የሚችል ሆኖ ስራው ጫካ መግባት ወይም ሴትን መሸሽ ሳይሆን እስከዓለም ዳርቻ የክርስቶስን ወንጌል መስበክ ነው።(እንደጳውሎስ) ያለበለዚያ አዳማዊ/ሔዋናዊ ባህርይውን ለመግደል ምግብ በመከልከል ስጋውን በመጨቆንና ሴቱ ወንዱን ላለማየት፣ወንዱ ሴቱን ላለማየት ፊቱን እየሸፈነና እየተሸሸገ መኖሩ የመንፈስ ቅዱስ አሰራር አይደለም። መጽሐፍ የሚለው«ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ»1ኛ 7፣9 የሚለውን አንፈልግም ብለው ሲያበቁ ከምንኩስና እስከጵጵስና ድረስ ያ እንደዝንጅብል ከተቀበረበት ጭናቸው የዝሙት ስር እየወጣባቸው በሽፍንፍኑ ባለትዳር መሆናቸው ይታወቃል። ከላይ በጽሁፍ የተገለጸው የእነ አባ ሚካኤል ችግርም ይኼው ነው። አባ ሚካኤል(የቀድሞው አባ ተክለሚካኤል ዓባይ)በአዲስ አበቤው ዲያቆንና ደብተራ (አባ ግሪክ፣ አባ ከሊፋ) ተብለው የሚጠሩት ሰው ቤተክርስቲያን አለኝ የምትለውን ለጵጵስና ከሴት የመራቅ ግዴታ እንደማያሟሉ አስቀድሞ ሲነገር ነበር። ወንድማቸው አባ ሳሙኤል(የቀድሞው አባ ተከስተ ብርሃን) ቅድስት ማርያም አካባቢ ጸሐፊ ሳለ ብዙ ይታወቅ ነበር። ይህንንም አቡነ መርሐ ክርስቶስ አባ ቃለጽድቅ(አባ አብርሃም) እና አባ ተከስተ(አባ ሳሙኤል) ጵጵስና ከምንሰጣቸው ብንድራቸው ይሻላል ብለው የተናገሩት ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ እንደነበር ይታወቃል።
  አሁን ማለት የምንፈልገው ጋብቻ ከምንም በላይ ክቡር ነው። አዳምም ብቻውን ሊኖር እንደማይገባ እግዚአብሔር አውቆ ሴትን ሰጠው። ያለሴት ለመኖር ወሳኙ ነገር ቆብና ቀሚስ ሳይሆን ለዚያ የሚያበቃ ጸጋና ስጦታ ሲሆን እሱም ቢሆን የክርስቶስን ወንጌል ወደኋላ የሚያስቀረው ጓዝ ሳይኖረው እንዲሰብክ እንጂ ጫካ ገብቶ ዝንጀሮ እንዲሆን አይደለም።
  በጥቅሉ ማግባት የፈለጉና እሳቱን መሸከም ያቃታቸው ጳጳሳትና መነኮሳት በህግና በግልጽ አግብተው አገልግሎታቸውን ከስርቆት ውጪ በነጻነት እንዲሰሩ እድል ሊሰጣቸው ይገባል። ጋብቻ ክቡር ነው። ጳጳስም ሆነ መነኩሴ ሲሞት በእዚያ በባለትዳሩ በአብርሃም እጅ እንዲያርፍ( እግዚኦ እእርፍ ለነፍሰ ገብርከ/አመትከ እገሌ ውስተ ህጽነ አብርሃም» ይባላል እንጂ ውስተ ህጽነ እንጦንስ አይደለም።
  ማ ግ ባ ት፣ ለ ፈ ለ ገ ይፈቀድ!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለማግባት ልቦናውን አድምጦ ካልሆነ ባለቤቱ ለሌብነት ከመጋለጥ ማግብቱ ይመረጣል ነገር ግን ባለቤቱ ልቡን ያድምጥ ከአምላኩ ይማከር

   Delete
 3. ስም አጥፊ እንጂ መልእክት የሚያስተላልፍ አይደለም ይህ ገጽ ሥራችሁ ክፉ ነው ዛሬ መኖራችሁን መናገራችሁን ስም ማጥፋታችሁን አባቶቻችን ያስቀመሩትን ሥርዓት እየነቀፋችሁ ቤተ ክርስቲያኒቷ የክብር መጎናጸፊያዋን እየቀደዳችሁ ነው ያላችሁት በእግዚአብሔርም ሆነ በሰው ዘንድ የተረገማችሁ ነው የሆናችሁት ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ ንስሐ ግቡ ቤተ ክርስቲያን ሰዎች ከሆናችሁ ጳጳስ ሚስት አለው? ህሊናችሁ አንዴት እያሰበ ነው እናተ የአባቶችን ስም በማጥፋታችሁ ታሪክ የሰራችሁ መስሏችሁ ሊሆን ይችላል እግዚአብሔር ግን ፍርዱን ይሰጣል ሲሆን ኃጢአት እንኳን ቢኖር መሸፈን ነው እንጂ እንዲህ አይነት አጸያፊ ቃል አይወጣም የማታውቁ ስለሆናችሁ ለማወቅ ጣሩ እራሳችሁን መርምሩ

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር የቀደሰውን ነገር ባናረክሰው መልካም ነው!ጋብቻ ቅዱስ ነው መኝታውም ንጽሁሕ ነው::ታዲያ ሰዎች ከአቅማቸው በላይ ቀንበር ተሸክመው ለምን ይሰቃያሉ::በተሰሳሰተ መልኩም ይሁን በመታለል ከመለኮሱ በኋላ ልክ እንደተገደዱ ነገር ለምን በሹልክታ ነገሮችን ያደርጋሉ?የተዘራው በሥጋ ከሆነ መበስበስ ይታጨዳልና የዚህን ውጤት ነው ያየነው እንጂ ሌላ አይደለም!ታዲያ ብልህ ከዚህ ይማራል ሰነፍ ደግሞ ይድረስብኝና ጉድ አያለሁ ይላል!
  ግን እኔ ያልገባኝ አንድ ጊዜ ከመለኮሱ በኋላ በቃኝ ምንኩስና ብለው ወደ ጋብቻ አለም አይገባም ወይ?ካልተቻለ ለምን?ኧረ ለወደፊቱና ለቀሩት በቁም ላሉት ይታሰብ እንጂ እያንዳንዱ አባት ሲሞት ነገሩ ይወጣል እያልን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም::አባሰላማዎች ግን ይህን አይነት ነገር ባታስተናግዱ መልካም ነው አንድ መነኩሴ ወይም ጳጳስ አገባ ወለደ እያላችሁ ወርቃማ የወንጌል ጊዜያችሁን ባታባክኑ ምን ይመስላችኋል?
  ኒቆዲሞስ ነኝ

  ReplyDelete
 5. ይህን አስተያየት የጻፍክ Anonymous
  "ስም አጥፊ እንጂ መልእክት የሚያስተላልፍ አይደለም ይህ ገጽ ሥራችሁ ክፉ ነው ዛሬ መኖራችሁን መናገራችሁን ስም ማጥፋታችሁን አባቶቻችን ያስቀመሩትን ሥርዓት እየነቀፋችሁ ቤተ ክርስቲያኒቷ የክብር መጎናጸፊያዋን እየቀደዳችሁ ነው ያላችሁት ............................."

  መልሰህ ራስህን አንብብ

  ስም ማጥፋት ማለት አንድ ሰው የላደረገውን አደረገ ብሎ መናገር መጻፍ ማለት ነው

  እነዚህ ጰጳጳሳት መነኮሳት ነን ብለው በሃሰት ራሳቸውን አቅርበው የቤተ ክርስቲያናንን ከፍተኛ የአገልግሎት
  ሃላፊነት ተቀበሉ

  በሰውና በእግዚያብሔር ፊት ዋሹ ሌሎችን አታመንዝሩ ከሕግ ውጭ የግብረ ሥጋ አትፈጽሙ እያሉ

  አመንዝራዎች

  ሃሰተኞች የተገኙ

  እነሱ ናቸው የበደሉ በማጭበርበር የተቀበሉትን ሥልጣን መመለስ ከዛም ንስሀም መግባት ያለባችው
  ጵጵስናውን የፈለጉት በክብር በቅምጥል ያለ ድካም ስራ በደሀው ክርስትያን ላብና ገንዘብ ለመኖር እንጂ ለወንጌል ተልእኮ ሃዋርያትን ለመከተል የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርት ለመስበክ አይደለም

  አስያየት ሰጭ “በእግዚአብሔርም ሆነ በሰው ዘንድ የተረገማችሁ ነው የሆናችሁት ”
  ስትል የእግዚአብሔርና የክርስያኖች አፈቀልላጤ ፈራጅ ማን አረገህ

  አይምሮህን አንጻ ወንጌልህን በጥሞዕና አጥና

  ReplyDelete
 6. What about others that hide with an illegal fundementalist organization of mk? The majority of mk false priest ,who have had none formal education of our church made sexual harrasement. They have multi sexual partner with muslim women. I will write more detail sexual behavior of mk priest with supported by specfic evidence.

  ReplyDelete
 7. የጉድ ቀን አይመሽም!!!


  የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሊቃነ ጳጳሳት እንደ ማኅበራቸው ውሸትን የመረጡ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ያዘጋጀው ቀን አለው፡፡ ሌሎችም በተራቸው እንዲህ በጠራራ ፀሐይ ይጋለጣሉ፡፡ አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ፤ አሜን!!!. . . .

  ReplyDelete
 8. Mk paid about $10,000 dollar pocket money for aba zelebanose to invite aba abrham to attack abune fanuel.That is shame on aba zelebanose that he sold himself for money similar to yehuda. Location Atlanta, Ga

  ReplyDelete
 9. ማነህ አባ ዘሊባኖስን የምትተች ደግሞ:: ትገርማለህ አባ ዘሊባኖስ አንተ እነደምታስበው በገንዘብ የሚታሙ አይደሉም እኔ አትላንታ አልኖርም ነገር ግን አውቃቸዋለሁ:: በጣም ተሳስተሃል:: ማ/ቅም ቢሆን ያን አያደርግም በእርግጠኝነት እነግርሃለሁ:: ችግሩ አባ ፋኑኤል አመጣጣቸው ልክ ካለመሆኑ የመጣ ችግር ነው የሚሆነው:: እሳቸው ወደዚህ አገር ሲመደቡ እንደ ደንቡ ከሆነ ከተቀየሩት አባት ተገናኝተው ስለ ሃገረ ስብከቱ ስራ ተነጋግረው የተጀመረውን ያለቀውን እና የመሳሰለውን የሃገረ ስብከቱን ስራ ተረድተው ስራ መጀመር ሲገባቸው ያ ሳያስፈልጋቸው የግላቸው ከሆነው ቤተ ክርስቲያን ገብተው እንደመደበቅ ነው ያሉት:: ታዲያ የሃገረ ስብከቱን መረጃ ሳይለዋወጡ እነማን በቅዱስ ሲኖዶስ ስር እንደሆኑስ ሊያውቁ ይችላሉ ነው ወይንስ ከአሁን በፊግ በእናትቤተ ክርስቲያን ስር ያሉትን በትነው እንደአዲስ ሊያቋቁሙ ነው ይህንን እንዲረዳቸው ነው ቀሲስ ሰሎሞንን ያመጡትን? ብቻ በሬ ውሻ ወለደ አይነት የመንደር ወሬ ነው::

  ReplyDelete
 10. Dear abaselama,

  Bertu, We know ther is no any lies, all what you wrote is 100 persent TRUE. at list we really get one web site who tells the truth.

  Thankyou and God bless you.

  ReplyDelete
 11. One of his senior priest (meregeta) in
  formed to the source zelebanose in Atlanta church had recieved money from mk to make change the decission by campaign of some official in addis to stay abraham in usa. Corruption is immoral, unethical and illegal in the law of the church on the contorary it seems like prevelant from all official in the church.

  ReplyDelete
 12. You wrote 100% true I knew zelebanose, he is too far from real world just in simple language called pretender.

  ReplyDelete
 13. See how your Megabe Hadis is copying:

  http://andadirgen.blogspot.com/

  ReplyDelete
 14. Megabe Hadis Begadshaow is the most powerful and really ethical preacher in EOTC in 2011.

  ReplyDelete
 15. «አንድ አድርገን»ብሎግ እናንተ በበጋሻው ላይ ላቀረባችሁት ፋላሲ የተሰጠውን ሎጂካዊ መልስ ለመመልከት
  http://dejebirhan.blogspot.com በመግባት ስለግብራችሁ እፈሩ!!!

  ReplyDelete
 16. pleas look papas can mareid only one womon 1Timoty 1:1-15 ::

  ReplyDelete
 17. Is their any pricher like Megaby Haddis Begashew,Aseged,Berhyhun,tiztaw, and more. But MK are very jelous, because they have so many followers. They are gifted by God!!!!. Zemedkun is a dog of Mk. I know Zemedkun very well, he is in love with money, If devel comes and pay him maney I will assure he is ready to sell his wife for the devel.

  ReplyDelete
 18. ለካ የሀሰተኞች ሀሳብ ብቻ ነው የሚቀርብበት ቤተክርስቲያንን አድሳለሁ ብለህ ዘመንህ ያልፍና ገሀነም ትጣላለህ፡፡ተጠንቀቁ እግዚአብሄር አይዘበትበትም፡፡የናንተን ሀሳብ ሌሎች ላይ አትጫኑ ፍርዱ ይከብድባችኋል፡፡Why do you approve somebody's comment

  ReplyDelete
 19. egzeabehere zamen ametetwal hulum yaserawen yameyagagebat

  ReplyDelete
 20. oh my God this is one of the nonsenseless blog i have ever seen.

  ReplyDelete
 21. betekiristiyan Yitadesal Bileh Atitebik Irass ketadesk tadess kalebeleziya fird isktagegn ketil inkirdadinetik iskiley diress ( tibit mefetsemiya BEGMESILEH TEKULA SINDE MESLEH INKIRDAD)

  ReplyDelete
 22. ALUBALTAHIN AKUM BENATH.ANTE KALTESHOMIH KALZEREFEH
  KIRISTIANOCH MESEDEB ALEBACHEW?MK.EN MANIM YAWKEWAL.YE MKEN
  YAHIL YKIRINA MENEM SIRA YALSERACHIHU LEWEREI TIBERETALACHU
  YENANTE EWUKET KEAFENCHACHU SELEMAYALIF.

  ReplyDelete
 23. የባህር አሸዋ

  ራዕየ ዮሃንስ ምዕራፍ 12 መነጋገሪያ መሆን ከጀመረ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል፡፡ በጣም የገረመኝ ነገር “…መጽሃፍ ቅዱስ ትርጓሜ አያስፈልገውም… እንደ ንባቡ ብቻ በጥሬው መፈታት አለበት…” ሲሉ የነበሩ ፕሮቴስታንቶች ጭምር የትርጓሜ ሊቃውንት ሆነው “… ጸሀይን ተጎናጽፋ.. ተብሎ የተነገረላት እስራኤል ናት …..” ማለታቸው ነው፡፡ ነገሩ “…. መች መጣሽ ሙሽራ መች በላሽ ሽንብራ…” የተባለው ቢጤ ነው፡፡ “..መጽሃፍ ቅዱስ መተርጎም የለበትም…” የሚለው ጽኑ መከራከሪያችው ከመቸው ጠፋና ለመተረጎም በቁ? ነው ወይስ ኦርቶዶክሶች ያቺን ሴት በማርያም ስለሚመስሏት “…ደስ አይበላቸው!!” ብለው ይሆን? መቼም ከሰይጣን ይበልጥ ኦርቶዶክስን እንደ ሚጠሉ ይታወቃል፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስሟ አለመጠቀሱ የሚያበሳጫት እንግሊዝ ዘፍጥረት 2፡13 ላይ “..ኢትዮጵያ..” የሚለውን “..ኩሽ..” ብላ በኪንግ ጀምስ ቨርሽኗ ላይ እንዳሳተመችው መሆኑ ነው፡፡

  ለማንኛውም ለመተርጎም ከበቃችሁና ከጀመራችሁ ምነው እስከ መጨረሻያልገፋችሁበት? የምን ቆነጻጽሎ መተው ነው? ራዕይ 12 ላይኮ የተፃፈው ጨረቃን ከእግሮቿ በታች ስላደረገች ሴት ብቻ አይደለም፡፡ ያሳድዳት የነበረው ዘንዶም አብሮ አለ፡፡ እንግዲህ በናንተ አባባል ሴቲቱ እስራኤል ከሆነች ዘንዶውስ ማ ሊሆን ነው፡፡ አደራችሁን “አሜሪካ” ብላችሁ ረሃብ የሚፈጀን አንሶ በኒኩለር ቦምብ እንዳታስጨርሱን!!
  አውነተኛው ዘንዶ ሰይጣን ዲያብሎስ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም እዚያው ቦታ ላይ (ራጭ12፡9) “ ዓለሙን ሁሉ የሚያሥተው ዲያብሎስ ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ….” ተብሎ በግልጥ ተቀምጧል፡፡

  አውሬው ሴቲቱን ሊያሰጥም ፈልጎ ብዙ ውሃ ከአፉ ተፍቷል (ራዕ12፡15)፡፡ ያ ከዘንዶ አፍ የወጣ ውሃ የሃሰት (የኑፋቄ) ትምህርት ነው፡፡
  ቁጥር 16 ላይ ደግሞ “…ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት አፍዋን ከፍታ ዘንዶውን የተፋውን ወንዝ ዋጠች…” ይላል፡፡ በምድር የተመሰሉት ደግሞ በተለያየ ጊዜ ተነስተው ዓለምን የኑፋቄ ትምህርትን በእውነተኛው ወንጌል ያጠፉ ሊቃውንት የሃይማኖት አርበኞች ናቸው፡፡
  ቁትር 17 ላይ “.. ዘንዶውም ሴቲቱን ና ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ…” ካለ በኋላ ቁጥር 18 ላይ
  “…. በባህርም አሸዋ ላይ ቆመ..” ይላል፡፡

  ባህር ብዙ ይዘት ያለው የውሃ ክፍል መሆኑ ይታወቃል፡፡ ውሃ ደግሞ በእግዚአብሄር ቃል (መጽኃፍ ቅዱስ) ይመሰላል፡፡ የዮሓንስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ላይ “….እኔ ከምሰጠው ውሓ የሚጠጣ ለዘለዓለም አይጠማም..” የሚል ቃል ተፅፏል፡፡

  አሸዋ ደግሞ በስም ብቻ የእግዚአብሄር ነን የሚሉ መናፍቃን ምሳሌ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለአብርሃም ”… ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ…” ብሎታል፡፡ እግዚአብሄር በአሸዋ የመሰላቸው እስራኤል ደግሞ በስም ብቻ “የአብርሃም ነገዶች ነን …የእግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ነን …” ማለት የማይሰለቻቸው ነገር ግን ለክፉ ስራቸው ዳር ድንበር የሌለው ሰዎች ናቸው፡፡

  አሸዋ ና ውሃ እድሜ ልክ አብረው ይኖራሉ፡፡ ተዋህደው ግን አያውቁም፡፡ ውሃው ካላይ አሸዋው ከታች!!!
  የዘመናችን መናፍቃንም እንዲሁ “…እኛ ወንጌልን ብቻ እንከተላለን… ወንጌልን ከነመረቁ ጠጥተነዋል.. ከኛ ወዲያ ወንጌል ላሳር ..” ይላሉ፡፡ ጥቅስም ያጣቅሳሉ፡፡ ተዋህደው ግን አያውቁም፡፡

  ስለዚህ “…ከሰማይ ስፍራ የታጣለት ዘንዶ በባህር ውስጥ እየኖረ ከባህር ጋር በማይዋሃደው አሸዋ ላይ ቆመ..” ማለት “….ሰይጣን መፅሃፍ ቅዱስን በያዙ ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱስ ካልተዋሃዳችው መናፍቃን ልብላይ ቆመ…” ማለት ነው፡፡
  የባህር አሸዋ ከመሆን ይሰውረን!!!!

  ReplyDelete