Friday, December 9, 2011

ነጋዴው ዘመድኩን አዘግቼዋለሁ ያለው ፋይል ዳግም እንዲከፈት ትእዛዝ ተሰጠ፤ ነጋዴው ዘመድኩን እንደተሰወረ ሲሆን፤ ዋሱ ልዑል ሰገድ እየተፈለገ ቢሆንም ስልኩን እንደተዘጋ ነው። - - - Read PDF

መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ በመጽሔት እና በመጽሐፍ ላይ ስሜን አጉድፈዋል በማለት ክስ የመሰረተባቸውና በአቡነ ፊልጶስ ጣልቃ ገብነት እንዲዘጋ ተደርጎ የነበረው የዘመድኩን እና የደስታ የክስ መዝገብ ዳግም እንዲከፈት ትእዛዝ መተላለፉን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ ትእዛዙ ዳግም ሊተላለፍ የቻለው ብፁእ አቡነ ፊልጶስ የተባለውን ደብዳቤ እኔ አልጻፍኩም ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ክሱን የመሠረተው መጋቤ ሐዲስ በጋሻው «ብፁዕ አባታችን እነ ዘመድኩን ስሜን አጉድፈው እያለ እንዴት ጉዳዩ የሃይማኖት ነው ብለው ክሱ እንዲቋረጥ ያስደርጋሉ?» ሲል ዋና ስራ አስኪያጁን አባ ፊልጶስን የጠየቃቸው ሲሆን፣ እርሳቸውም ምለውና ተገዝተው እኔ አልጻፍኩም ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ ከዚያ በጋሻው ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር በማምራት ክሱ እንዲቋረጥ ላዘዙት ባለሥልጣን ጉዳዩን በማስረዳትና ማጭበርበር እንደተፈጸመ በመግለጽ ጉዳዩ እንዲጣራ ያደርጋል፡፡ ባለሥልጣኑም ወደ አባ ፊልጶስ ደውለው «ደብዳቤውን የጻፉት እርስዎ አይደሉምን?» ሲሉ በጠየቋቸው ጊዜ ለበጋሻው የመለሱትን ደግመው ይመልሳሉ፡፡ ይህን ተከትሎ ባለሥልጣኑ አዝነው ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በማምራት አቡኑን እንዳነገሯቸው ምንጮቻችን ገልጸው፣ ደብዳቤውን በማሳየትና ከመዝግብ ቤትም ፋይሉ እንዲወጣ ተደርጎ ዳግም ሲጠየቁ መደናገጥና መርበትበት እንደተስተዋለባቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው አባ ፊልጶስ በሕግ ሊጠየቁ የሚገባ ቢሆንም ለቤተክርስቲያኒቱ ክብር ሲባል እርሳቸውን በማለፍ የተቋረጠው ክስ ዳግም እንዲከፈት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡

በስም ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱት ዘመድኩንና ደስታ በ4/4/2004 ዓ.ም ቦሌ ምድብ ችሎት እንዲቀርቡ ዳግም መጥሪያ የወጣባቸው ሲሆን፣ ደስታ ቀርቦ መጥሪያውን ወስዷል፡፡ ዘመድኩን ግን ተሰውሮ ነው የሚገኘው፡፡ መጥሪያውን እንዲወስድ ስልክ ቢደወልለትም «አልተመቸኝም ኑ እና ስጡኝ» እያለ በሱቆቹም ሆነ በመኖሪያ ቤቱ ሊገኝ አልቻለም፡፡ በመሆኑም በፖሊስ ተይዞ እንዲቀርብ አስገዳጅ መጥሪያ ወጥቶበታል፡፡ ዋስ ሆኖ ያስፈታው ልዑል ሰገድ እንዲቀርብ ለማድረግ ስልክ ቢደወልለትም እርሱም ስልኩን መዝጋቱንና እስካሁን ያለበት አለመታወቁን ለመረዳት ተችሏል፡፡

የበጋሻውን ስም በመጽሐፍ ያጎደፈው ደስታ ግን መጥሪያውን ከወሰደ በኋላ ጉዳዩ በይቅርታ እንዲያልቅ አማላጅ መላኩን ምንጮቻችን አለክለው ገልጸዋል፡፡ ከእርሱ ቀደም ብሎ ሳህሉ የተባለው ሰው በተመሳሳይ መጽሐፍ ጽፎ የበጋሻውን ስም በማጉደፉ ከዘመድኩንና ከደስታ ጋር ተከሶ የነበረ ቢሆንም በይቅርታ ጉዳዩን መጨረስ ችሏል፡፡ ደስታ ግን ከይቅርታ ይልቅ በአቡነ ፊልጶስ በኩል ተጀምሮ የነበረውን ጥረት ተስፋ አድርጎ የቆየ ሲሆን፣ ተስፋ ያደረገው የተፈጸመለትም መስሎት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የተዘጋው ፋይል ዳግም እንዲከፈት ሲደረግ የረፈደ ይቅርታውን ማቅረቡን ከምንጮቻችን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዘመድኩን ግን ከዚህ ቀደም በማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ በደጀሰላም ላይ «ከእርሱ ጋር ከምታረቅ ሲኦል ብገባ ይሻለኛል» ማለቱ የሚታወስ ሲሆን፣ አሁንም ይቅርታ ይጠይቃል ተብሎ እንደማይታሰብ አንዳንዶች አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው፡፡ «ከእርሱ ጋር ከምታረቅ ሲኦል ብገባ ይሻለኛል» ማለቱም ሲሣለቅ  ነው የሚሉት ወገኖች፣ ንስሐ ካልገባና የሞተለትን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ማሳደድ ትቶ በአዳኝነቱ ካላመነ በዚህ አካሄዱ ሲኦል እንጂ ገነት እንደማይገባ ስለሚታወቅ የቦታ ለውጥ አላደርግም ብሎ ነው እንዲያ ያለው ሲሉ ይናገራሉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በማኅበረ ቅዱሳን ተደርሶ በዘመድኩን በተተወነው አርማጌዶን ቁጥር 2 ቪሲዲ ምክንያት በዘመድኩን ላይ ክስ የተመሰረተበት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ጉዳዩ ታህሳስ 3/2004 ዓ.ም  እንደሚታይ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው ዘመድኩን ገንዘብ እስካስገኘ ድረስ የትኛውንም ወንጀል ለመፈጸም ወደኋላ እንደማይል ነው፡፡ ምክንያቱም ተቋርጦ እንዲቀጥል የተደረገው ክስ በሂደት ላይ እያለ ነው «አርማጌዶንን ተውኜ ብዙ ብር አፍሳለሁ» ሲል እጁን በሌላ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ከቶ የተገኘውና እርሱም ቪሲዲውም በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ ከዚያም ጠፍቶ ከሰነበተ በኋላ አንደኛው የክስ መዝገብ ይዘጋል በተባለበት ቀን ህዳር 6/2004 ዓ.ም በቦሌ ምድብ ችሎት ተገኝቶ ሳለ፣ በፖሊስ ተይዞ ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ተወስዶ ቀኑን ሙሉ ታስሮ ከዋለ በኋላ በልኡል ሰገድ ዋስነት የተፈታው፡፡ ከዚህ ልምድ በመነሳት ምናልባትም ታህሳስ 3 ቀን በፈቃደኝነት ሳይቀርብ እንደተሸሸገ ሊሰነብት ይችል ይሆናል የሚል ግምት የተወሰደ ቢሆንም ሁሉንም ቀኑ  ደርሶ የምናየው ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስም ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመባቸው መጻሕፍት የታተሙት ማህበረ ቅዱሳን «ስለተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ» ግንዛቤ በማስጨበጥ ስም ባጋበሰውና የሰባክያን ጥምረት በሚል ሽፋን ባደራጀው ስብስብ በኩል መሆኑን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ገቢው ባካፋ ወጪው ግን በመንኪያ እንደ ሆነባቸው እነዚሁ ምንጮች አክለው ይናገራሉ፡፡

16 comments:

 1. አላዋቂ፣ ጠባቦች፣ የእፉኝት ልጆች ናችሁ። እግዚአብሔር ይቅር ይበላችሁ።

  ReplyDelete
 2. EGEZEOO... YEZEMEDEKUEN MECHERESHA MENALE BALEWALEKEBET KEMETEBETEBET LEJOCHEHEN BETASADEG

  ReplyDelete
 3. yemntebekwe nebere witetun bekerbu yasemanema

  ReplyDelete
 4. wow! you idiocy amused me. Aba Diablos!

  ReplyDelete
 5. ke mejemeriya iske meceresha yetesafew andim neger masreja yelewum. yihenen yemilew le andu weyim lelelaw lemagez felige sayihon sanebew yetsafacihut hulu yeMENDER WERE yimesilal. lemanignawum kelay yalew sew indaleh ATO ABEBE KEBEDE yihenen Blog bileh kefteh mekerahin kemitay lemin lela neger lemesirat atimokirim??? iwun TEHADISO tikikilegna haimanot nat? kehonecis yihe hulu sim matifat ye sewun hiwot ye ignan ye ORTHODOX TEWAHIDO haimanot makoshesh. be haset sim matifat lemin asfelege??? tigermaleh yemidenkew FB sitijemir ande Politica, ande Zefen asmeraci, kezam Quwanquwa astemari honeh neber. ayeh yetewataleh tinish commentoci yesebesebkew be Sim matifatu sirah lay new. yeteregeme sew yezerawun yacidal. Astawus 1Qen lezih sirah wagahin tagegnibetaleh. bebekule. EGZIABIHER YIKIRTAWUN YADILEN.

  ReplyDelete
 6. we need this news. tell us more. he is the son of devilmk

  ReplyDelete
 7. Ewunetu mech tedebiko yikeral!!!
  yihew endezih yigeltsewal!!!
  yeEwunet amilak yifareden!!!!!

  ReplyDelete
 8. this is completely far from truth. it is false full talk. we know everything.

  ReplyDelete
 9. የሚገርመው ብሎም የሚያሳዝነው ነው

  "ደብዳቤውን በማሳየትና ከመዝግብ ቤትም ፋይሉ እንዲወጣ ተደርጎ ዳግም ሲጠየቁ መደናገጥና መርበትበት እንደተስተዋለባቸው ከምንጮቻችን መረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ድርጊታቸው አባ ፊልጶስ በሕግ ሊጠየቁ የሚገባ ቢሆንም ለቤተክርስቲያኒቱ ክብር ሲባል እርሳቸውን በማለፍ የተቋረጠው ክስ ዳግም እንዲከፈት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡"


  የቤተክርስቲያን ክብርና ልዕልና የሚዋረደው እንዲህ ያለ ቀጣፊ ሀሰተኛ
  ጽፎ የፈረመውን ደብዳቤ የሚክድ ቤተክርስቲያንን እንዲመራ ስልጣን ሲሰጠው ነው
  አሁን ይህ ጳጳስ በሀሰት አትመስክሩ ብሎ ሌሎችን በምን አንደበቱ ሊያስተምር
  ነው
  ምነው የቀደሙ አባቶቻችን መንገድ የተከተለ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያደረበት ጌታ መንፈስ ቅዱስ ቢያስነሳልን

  ReplyDelete
 10. lemen yesewen sem bemetsehaf matfat asfelege? yemitsefut wois yemiastemerut atu ende? yasazenal

  ReplyDelete
 11. ሁሉም በየደረጃው በድሎአል!

  ቤተ ክርስትያን የሃይማኖት እጸጽን በመድረኳ ላይ ሲሰበኩ ግን ዝም ማለት ግን አትችልም! የሰባኪው ብስለት ችግር ነው እያለችና እያልን ብዙ ታግሰን ነው! ፈጣጣ ሌባ ያሳደግነው፡፡

  የሐሰት ክስ (ስም ማጥፋት) ወንጀል ነው እያላቹ ጻሐፊው ጣቱን በሌላ ላይ ቀስሮ ሲከስ ይታያል፡፡ መጀመሪያ ቤተ ክርስትያንንና አማኙን "ኢየሱስ" አትልም/አትሉም ብሎ ስማችንን ከሚያጠፉ... ምን እንበላቸው? የተጀመረ ወንጀል አይደለም ወይ? ይቅርታ ሳይጠይቁ ይቅርታ ጠይቁን ማለት / ማስገድድ ምን ለማለት ነው?
  በሕግ ከለላነት ቤተ ክርስትያን ላይ ወንጀል እየሠሩ ለመኖር ማሰብ ከእንግዲህ ሞኝነት ነው፡፡ ንስሃ ግን ከቤተ ክርስትያን ለመቆየት አማራጭ የሌለው ነገር ነው!

  ReplyDelete
 12. Enquan des alachihu?????????????????????????????

  ReplyDelete
 13. አቤት ተረት ተረት
  ተረት ተረት የመሰረት አንድ በጋሻው ነበረ:: የጌታን ስም ስለጠራ ዘመድኩን አሳደደው::
  ተረቴን መልሱ አፌን....

  ReplyDelete
 14. Egzabir beneger hulu tibeb ena mastewal ystachw Ersun (jesus)bemawek ewnett jesus new

  ReplyDelete
 15. • የተማረው መምህር ዘመድኩን የሰው ታሪክ ያውቃል ምናልባት እሱ አንተ ዶክትሬት ከያዝክበት ተቋም አልተመረቀም ይሆን እንዴ፤፤
  • ከየትኛውም ትምህርት ቤት ሰርተፊኬት ሆነ የሰባኪነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠው ሰው ነው ስትል ሆንክ እንዴ ሲኦሲ የምትሰጥ በተንኮል መቀስ የተጎዳ ሲዲ ይሆን እንዴ ብቃት የሚረጋገጠው፡፡
  • አርማጌዶንማ መቀስ ሳይሆን መትረቢያ ያረፈበት ያንተ ሸር ነው፡፡
  • የወንጌል ቃል እንደ ፈለጉት ሲባል ተሰምቶ አየታወቅም አንተ ፊቺ ልሁንላችሁ በተለይ የዲቆን በጋሻው በእኔ ካልሆነ ሰው አገባውም በፍጹም የእሱን ሳይሆ እኔልፍታላችሁ የእኔን ሲዲ ስትሰሙት በግልጽ ይሆንችኋል ነው የምትለው ትንሽ በእግዚያብሄር ቃል ስትፈላስፍና ያልሆነ ፍቺ ስትሰጥ ሲዲ ግዙና አዳምጡ ላንተ እኮ ንግድ ነው ደረከው ትሁትና ፈሪሀ እግዚብሄርን ይኑርህ ህይወት ሳሆን መናፍቅነት ይሄ ነው፡፡
  ዘመድኩን የስም ላፒስ መናፍቅ ውሸት የማያልቅበት ባደባባይ ቤተክርስቲያንዋ ስትሰደብ መልስ ያልሰጠ አሁን በውሸት ሰውን እያሳሰተ መናፍቅነቱ እንዳነቃ ጣቱን በሌሎቹ ላይ ይቀስራል አትስሙት ዘመድኩን መናፍቅ ነው፡፡

  ReplyDelete
 16. egziabeher ewnwtun yaweta

  ReplyDelete