Thursday, December 22, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲወገዙ ጥያቄ ሊያቀርብባቸው የሚገቡ ቀደምት "ተሐድሶ መናፍቃን" - - - Read PDF

ውድ አባ ሰላማዎች “ማራኪ” የተባለ መጽሔት ኅዳር ወር እትም ላይ አባ ሰላማ ብሎግን ጠቅሶ ማኅበረ ቅዱሳን በሁለት የክስ መዝገቦች ላይ ውግዘት እንዲተላለፍባቸው ጥያቄ ያቀረበባቸውን ግለሰቦች ዝርዝርና በዚያ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን አስነብቦናል፡፡ በእኔ እይታ ችግሩን ከምንጩ ማድረቅ ካልተቻለ ማኅበረ ቅዱሳን የወጠነው የ«ተሐድሶ መናፍቃን» ዘመቻ ግቡን ይመታል ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ ማኅበረ  ቅዱሳን ምንጩን በማድረቅ ላይ ትኩረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ማኅበሩ ስማቸውን የጠቀሳቸው ሰዎች ሁሉ ለእርሱ «ተሐድሶ መናፍቃን» ከሆኑ የእነርሱ «ኑፋቄ» የተገኘበትን ምንጭ መፈለጉና ማድረቁ ነው መፍትሔ የሚሆነው፤ በእነርሱ ላይ ብቻ መረባረቡ ግን ጠላት ማብዛት ነው እንጂ ዘመቻውን በድል ለመቋጨት ብዙም አይረዳም፡፡ ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ከፈለገ የረሳቸውንና በፍረጃው ውስጥ ሊካተቱ የሚገባቸውን ዋናዎቹን የ«ተሐድሶ መናፍቃን» ምንጮች ስም ዝርዝርና «ኑፋቄዎቻቸውን» ይፋ ማድረግ አለበት፡፡ የሚከተሉት ቢካተቱበት መልካም ነው፡፡
1.      በማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ መሠረት አንዱ ኑፋቄ «ቅዱሳት» ለተባሉት ሥዕላት ተማፅኖ እና የአክብሮት ስግደት ማቅረብን መቃወም ነው፡፡ ይህን «ኑፋቄ» በማራመድ የመጀመሪያው ተጠያቂ እግዚአብሔር ራሱ ነው፡፡ በዐሥሩ ትእዛዛት ውስጥ የተቀረጹ ምስሎችን ለአንተ አታድርግ ሲል ያስተማረውና ይህን ተላልፈው የተገኙትን ሲጸየፋቸው የነበረውና በኀጢአተኛነት የፈረጃቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህን ትምህርት ከእርሱ ተቀብሎ ሲያስፋፋው የነበረው ሙሴም በዚህ «ኑፋቄ» ውስጥ እጁ አለበት፡፡ ሌሎች በርካታ ነቢያትና ሐዋርያትም ይህን ትምህርት በማስፋፋት ይታወቃሉ፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር፣ ሙሴ፣ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉ በ«ተሐድሶ መናፍቅነት» መከሰስ አለባቸው፡፡
2.     ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚለውን «ኑፋቄ» በመጀመሪያ የዘራው ነቢዩ ኢሳይያስ ነው፡፡ "ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።" ሲልም ነው የተናገረው (ትንቢተ ኢሳይያስ 53፥12)፡፡ ይህን «ኑፋቄ» ከእርሱ ተቀብሎ ያስተጋባውና ያስፋፋው፣ ለደቀ መዛሙርቱም ያስተላለፈው ራሱ ኢየሱስ ነው፡፡ እንዲህ ማለቱ ከቶ አይረሳም «ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።» (የሉቃስ ወንጌል 22፥31-32)፡፡ የእርሱ «ኑፋቄ» መች በዚህ ብቻ ሊያበቃ፣ «እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።» (የዮሐንስ ወንጌል 14፥13-14) በማለት ተከታዮቹ ሁሉ በእርሱ ስም እንዲለምኑ ያስተማረውም እርሱ ነው፡፡ እኔ አደርገዋለሁ ብቻም ሳይሆን በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አብ ያደርገዋል ሲል በኢየሱስ ስም እንድንለምን የአብ ፈቃድ መሆኑንም አስረግጦ አስተምሯል (የዮሐንስ ወንጌል 16፥23)፡፡ ተከታዮቹ ካልሆኑት ከማኅበረ ቅዱሳን አባላት በቀርም ሁሉም በዚህ «የተሳሳተ» ትምህርት ተወስዷል፡፡ ታዲያ ያስተማረውን ዋናውን እርሱን ትቶ ከእርሱ የተማሩትንና እንዳላቸው እያደረጉ ያሉትን ክርስቲያኖች ማዋከቡ ምን ዋጋ አለው? ሌላም ልጨምር፤ «እሺ አማላጅስ በሉት ነገር ግን ማንን ነው የሚለምነው? እርሱ ራሱ እግዚአብሔር አይደለም ወይ?» ለሚለው የማኅበረ ቅዱሳን መከራከሪያ አስቀድሞ ምላሽ በመስጠት የክርክሩን በር «እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤» በማለት በቅድሚያ በቃል ትምህርቱ፣ በኋላም ተሰቅሎ ሳለ በተግባር «አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው» (የሉቃስ ወንጌል 23፥34) ብሎ በመለመን የዘጋው ራሱ ኢየሱስ አይደለምን? (የዮሐንስ ወንጌል 14፥15-16)፡፡ ስለዚህ ለምን እንዲህ እንዳደረገ እንዲጠየቅ በክሱ መዝገብ ውስጥ ስሙ ሊሰፍር ይገባል፡፡
በሌሎች በኩል ወደ አብ እንዳንቀርብ አድርጎ፣ «እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።» (የዮሐንስ ወንጌል 14፥6) ሲል ያከላከለው ማን ሆነና ነው እርሱ የሚታለፈው፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስስ ቢሆን ይህንኑ ሰምቶም አይደል «አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤» ሲል የደመደመው (1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5) እርሱስ ከመከሰስ እንዴት ይድናል? ከተነሣ አይቀር በእዚህ ነጥብ ሥር የተናገራቸውን ሌሎቹን የእርሱን «ኑፋቄዎች» ልጥቀስ፤
·        «እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።» (ሮሜ 8፥34)፡፡

·        «እርሱም በሥጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።» (ዕብራውያን 5፥7-10)፡፡

·        «እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።» (ዕብራውያን 7፥23-25)፡፡ ታዲያ ይህን «የተሐድሶ ትምህርት» ያስፋፋው ሐዋርያው ጳውሎስ ሆኖ ሳለ እርሱ በቸልታ መታለፉ አግባብነት አለውን? ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ሆይ! የሐዋርያው ጳውሎስን ስም በተከሳሾች መዝገብ ውስጥ ማስገባትህን አትርሳ፡፡


 ኢየሱስን አማላጅ ማለቱ ሳያንስ አብንም መንፈስ ቅዱስንም አማላጆች አድርጎ መጻፉም ሌላው ጳውሎስን በ«ተሐድሶነት» የሚያስፈርጀው «ኑፋቄ» ነው፡፡

·        «ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤» (2ኛ ቆሮንቶስ 5፥18-19)

·        « እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤» (ሮሜ 8፥26)
በማኅበረ ቅዱሳን እምነት መሠረት እንደ ጳውሎስ ሁሉ ሐዋርያው ዮሐንስም «መናፍቅ» የሚያሰኘውን «ተሐድሶአዊ» ትምህርት አስተምሯል፤ እንዲህ በማለት፥ «ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።» (1ኛ ዮሐንስ 2፥1-2)፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ዮሐንስም ከቀደምት «ተሐድሶዎች» አንዱ መሆኑ እንዳይረሳ፡፡

3.     የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ስግደት የሚገባው ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለእመቤታችን፣ ለቅዱሳን፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታት፣ ለመላእክትም የአክብሮት ስግደት ሊሰገድ ይገባል የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ቀደምት «ተሐድሶ መናፍቃን» ይህን የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት የሚያፋልስ «ኑፋቄ» ሲያራምዱ መኖራቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በዋናነት ሰይጣን፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በፈተነው ጊዜ ለእርሱ እንዲሰግድለት ጠይቆት ነበረ፤ ኢየሱስም «ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።» (የማቴዎስ ወንጌል 4፥10)፡፡ በእውነቱ ይህ ከማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ያፈነገጠ «ምንፍቅና» ስለሆነ እንዲህ ያለው ሰው «ተሐድሶ» ተብሎ ሊፈረጅ ይገባል፡፡
ኢየሱስ እንዳስተማራቸው የሚኖሩት ቅዱሳንም የዚህ ትምህርት ሰለባ በመሆናቸው ጉዳያቸው ሊጣራና ተገቢው እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ ቆርኔሌዎስ ለጴጥሮስ «የአክብሮት» ስግደት ቢሰግድለት «ጴጥሮስ ግን። ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።» (የሐዋርያት ስራ 10፥26)፡፡ እንዲህ ማድረጉ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት አይገባም ማለቱም አይደል፡፡ እርሱ እንዲያውም ትምህርቱን በቃል መቃወም ብቻም ሳይሆን በተግባርም ነው የተቃወመው፡፡ ስለዚህ ጥፋቱ ከበድ ያለ ነው፡፡ ይህም የማኅበረ ቅዱሳንን ትምህርት መቃወም ስለሆነ ጴጥሮስም ከተጠያቂነት ማምለጥ የለበትም፡፡
አንድ ስሙ ያልተጠቀሰው መልአክስ ቢሆን ዮሐንስ ከአንዴም ሁለት ጊዜ «የአክብሮት ስግደት» ቢሰግድለት፣ «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤» ብሎ አልከለከለውምን? (የዮሐንስ ራእይ 19፥10፤ 22፥8-9)፡፡ ታዲያ ይህስ መልአክ እንዴት ዝም ይባላል? እርሱም «ተሐድሶ» ስለሆነ ከሌሎቹ ጋር መከሰስ አለበት፡፡
4.     ስለታቦትስ ቢሆን በአዲስ ኪዳን ታቦት የለም ተሽሯል የሚለውን «ኑፋቄ» በመጀመሪያ ያሰራጨው ሐዋርያው ጳውሎስ አይደለምን? ማኅበረ ቅዱሳን የማቴዎስ ወንጌል 5፥17ን በመጥቀስ ጌታ ህግንና ነቢያትን ለመሻር እንዳልመጣ እያስረዳ፣ ጳውሎስ ግን በ2ቆሮንቶስ ምዕራፍ 3 ላይ፣ እንዲሁም በዕብራውያን መልእክት ውስጥ ታቦትን ጨምሮ ብሉይ ኪዳን (ኦሪት) ከነጓዙ በአዲስ ኪዳን (በወንጌል) መተካቱን ያስተማረው እርሱው አይደለምን? ማስረጃ ካስፈለገ እነሆ!
·        «ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።» (ዕብራውያን 7፥18-19)
·        እንዲሁም «አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል። ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። … አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።» (ዕብራውያን 8፥6-7፡13)፡፡


ስለዚህ ጳውሎስና ከማኅበረ ቅዱሳን አስተምህሮ ጋር በብዙ ሁኔታ እየተጋጨ ያለው የዕብራውያን መልእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ እንዲሆን የድጋፍ ፊርማ መሰባሰብ አለበት፡፡


በዚህ ጽሑፍ የተነሡት ጥቂቶቹ የቀደምት «ተሐድሶ መናፍቃን» «ኑፋቄዎች» ናቸው፡፡ ጊዜና ቦታ አይበቃም እንጂ እነርሱም ሆኑ ከሐዋርያት በኋላ የተነሡት የእነ አትናቴዎስ፣ የእነ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ የእነ ቄርሎስ፣ የእነጎርጎርዮስ ወዘተርፈ አስተምህሮ ሁሉ ቢፈተሽ፣ ከማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት ጋር የሚጋጩ ኑፋቄዎች ይገኙባቸዋልና በቀጣዩ የሲኖዶስ ስብሰባ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው  በጥያቄ መልክ ሊቀርቡ ይገባል፤ ከአሁኑም የተቀናጀ ሥራ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ዋናዎቹ «የኑፋቄና የተሐድሶ» ትምህርት አራማጆች ክስ ካልተመሰረተባቸውና ካልተወገዙ በቀር የአሁኖቹን ብቻ ማሳደዱ የትም አያደርስም፡፡ ስለዚህ ጎበዝ ቤተ ክርስቲያናችንን ከአሁኖቹ ሳይሆን ከቀደምት «ተሐድሶ መናፍቃን» ለማጽዳት ተነሡ፡፡ እነርሱን ካላወገዛችሁ እነዚህኞቹን ለማውገዝ አቅም ታጣላችሁ፡፡

ከጸጋ ታደለ

53 comments:

 1. It's very tricky one!!!
  I think, you brought up an argument topic that challenging idea of MK, but it can be stretched over and over. Please don’t make jock and sarcasm on our Lord and his witnesses and servants. It’s shame on you!

  ReplyDelete
 2. ዋው\\\\\ ዋው\\\\\ በጣም በጣም ግሩም ድንቅ ፅሑፍ ነው። ምን አይነት ልበ ብርሃን የሆንክ ክርስቲያን ነህ።
  ጌታችን ይባርክህ፡ እንዳንተ ያሉትን ክርስቲያኖች ደግሞ ደግሞ ያብዛልን። ዋው\\\ ዋው\\ዋው\\\
  መጀመሪያ ሳነበው ግን በጣም እየሳቅሁ ነበር የማነበውና ቤተሰቦቼ ምን ሆነሽ ነው እስከሚሉኝ ድረስ
  እና ያው ገባችሁ አይደል በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ ክፉ አይንካችሁ።

  እንኩአን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ።
  በክርስቶስ እህታችሁ ሜላት ነኝ። እኔም በኢየሱስ ወንጌል ስለማምን ማቅ በክሱ ውስጥ ያስገባኝ። ኪ--ኪ---ኪ---

  ReplyDelete
 3. ዋው\\\\\ ዋው\\\\\ በጣም በጣም ግሩም ድንቅ ፅሑፍ ነው። ምን አይነት ልበ ብርሃን የሆንክ ክርስቲያን ነህ።
  ጌታችን ይባርክህ፡ እንዳንተ ያሉትን ክርስቲያኖች ደግሞ ደግሞ ያብዛልን። ዋው\\\ ዋው\\ዋው\\\
  መጀመሪያ ሳነበው ግን በጣም እየሳቅሁ ነበር የማነበውና ቤተሰቦቼ ምን ሆነሽ ነው እስከሚሉኝ ድረስ
  እና ያው ገባችሁ አይደል በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ ክፉ አይንካችሁ።

  እንኩአን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እላለሁ።
  በክርስቶስ እህታችሁ ሜላት ነኝ። እኔም በኢየሱስ ወንጌል ስለማምን ማቅ በክሱ ውስጥ ያስገባኝ። ኪ--ኪ---ኪ---

  ReplyDelete
 4. Are you telling us your teachings indirectly? We know all these were your teachings before and your goals are destroying our church's teachings and the true biblical heritages by your heretic teachings. We know Isayiyas, St paolos, all other saints well before; more than this we know our Lord Jesus Christ as as The Son of God and True savior not as intercessor as you say. You better learn the truth and think for your souls and for the souls of your followers before the days pass and nights come.

  ReplyDelete
 5. እግዚአብሔር ይባርክህ! እውነትም «ጸጋ ታደለ»! አሁንም ጨምሮ ያድልህ። «ለጥፋት የተዘጋጀት ከተማ፣ ብትመከር አትሰማ» ነውና የቱንም ያህል የሚታይ ቢሆን እውነትን ለመቀበል የሚችሉ አይደሉም። ምክንያቱም «ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ»2ኛ ቆሮ4፣4 የሚለው ቃል ስለደረሰባቸው የሚሰማ ልቡና፣የሚያስተውል ኅሊና የላቸውም። ሁል ጊዜ የሞኝ ለቅሶአቸውን«ተሃድሶ፣ ተሃድሶ ወይኔ ተሃድሶ» እያሉ ጩኸትና ጭንቀት ማሰማት ነው ችሎታቸው። እስኪ እንደቀደሙት የአበው ሥርዓት ጉባዔ ይጠራና ሊቃነጳጳሳት፣ መነኮሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት፣ ምእመናንና ምእመናት በተገኙበት አዳራሽ የማኅበረ ቅዱሳን የጥብቅና ቡድንና ተሃድሶ የሚባሉ ሰዎች ቡድን ቅዱሳት መጻሕፍትን ብቻ መሰረት አድርጎ ክርክር ያድርጉ። ምሁራኑና ሊቃውንቱ ዳኝነት ይስጡ። ጉባኤውም ይፍረድ። ከዚያ በኋላ መናፍቅ ሆኖ የሚረታ ማን እንደሆነ ይታይ። ማቅ እውነት በኛ ዘንድ አለች የሚሉ ከሆነና ስለሃይማኖታቸው ተሃድሶ የሚባሉትን መርታት የሚችል እውቀት ካላቸው ይህንን ያድርጉ!! በጅምላ እገሌን እንጠረጥራለን፣ እገሌም ነገረ ስራው ይመስላል፣ እንትናም ተሀድሶ ነው ይወገዝ ብሎ በዘመቻና ጫና በመፍጠር የራስን ምኞት ለማሳካት ከመሞከር ይልቅ እስኪ ፍትህ ዘቀደምት አበውን ያሳዩ!! ያኔ የተረታው ተወግዞ ይለያል። ይህን ለማድረግ የሚችል ክርስትና መቼ ኖሯቸው ነው? መናፍቅ ራሳቸው ስለሆኑና ከተረት ያለፈ እውቀት ስለሌላቸው ለድብደባ፣ ለግድያ፣ ለወከባ፣ ለጅምላ ውግዘት ከመሯሯጥ ያለፈ ቅንጣት እምነት የላቸውም። ነጋዴ ድሮስ ልቡ ያለችው ስትወድቅ ቅጭል ከምትለው ሳንቲም ላይ እንጂ መግስተ ሰማይ ከሚያስገባው ክርስትና ላይ አይደለም። ማቅ ነጋዴው ሆይ « ኢየሱስም፦ ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው።
  ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ» ማቴ19፣21-22 የተባለው ላንተ ነው። ጭንቀትህ ዝናህ እንዳይቀንስ፣ ሀብትህ እንዳይጎድል እንጂ ሀዘንህ ቤተክርስቲያን አይደለችም!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 6. great! This is the real solution.

  ReplyDelete
 7. አባ ሰላማ ደግሞ ብላችሁ በቅዱሳን መጫወት ጀመራችሁ?ጸጋ ማፈሪያ ነህ ባንተ በት ማስቀየስህ ነው በቃላት ጨዋታ።ይህ የአጸ ተውድሮስ ጸሐፊ እንደጀመሩት ዓይነት የሚመስል መጽሐፈ ጨዋት ነው የጻፍከው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ¨wedaje yehe yemayastewul sega yetebale sewu sera temeleketehe bemenekatehe dese belognal menafekane kerebewunalena enetenekeke

   Delete
 8. mahibere kotetam bel engidih merejahin sebisibina kebefitu mezigeb gar kelakilina asiwegiz

  ReplyDelete
 9. ወዳጀ በጣም ደክመሀል ይህን የመሰለ ትምህርት ለነጋዴዎችና ለፖለቲከኞች አይገባቸውም መጀመሪያ የእነሱን ዓላመ ተረዳ እነሱ እኮ የሃይማኖት አላማ የላቸውም የሃይማኖት አላማ ቢኖራቸው፡፡

   በየቤተ ክርስቲያኑ በሚገባቸው ቋንቋ ዘወትር የሚባለውን በሰሙ፣

   በአንድ ልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በርሱ ያለ ክብር ጸጋ ከርሱ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር …

   አቤቱ ስለ ሰምህ ስትል ማረን

   በበላነው ቅዱስ ሥጋ በጠጣነው ክቡር ደም ይማረን እተባለ የሚባለው በበቃቸው፡፡ ሥጋወ ደሙ ማለት እኮ ክርስቶስ ነው፡፡ በናትህ ለደንቆሮዎችና ለክፉዎች ኣላማቸው ከፖለቲካ ውጭ ምንም ያልሆነ ዘረኞች ጠባቦች ባትጨነቅ፣

  ቤተ ክርስቲያን እኮ ሲኦል ደጆች አይችሏትም ነው የተባለች ማህበረ ቅዱሳን የሲኦል ደጆች ናቸው አትጠራጠር ዝም ቢባሉ ማንነታቸው ያልታወቀ አይምሰልህ፡፡ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥ ሆነው የሚያምሱ ቀበሮዎች ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በቱርኩ ግራኝ፣ በጅሱሳውያን፣ በመናፍቃን ከደረሰባት ጥፋት እና የምእመናና የሊቃውንት ስደት የበለጠ እያሳደዱን ነው፡፡ ዋናው ስደቱ እንዴት ይቁም ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ! ስለ ማህበረ ቅዱሳን (የደህንነት ድርጅት) እሩቡን ያህል ገና አልተገለጸልህም። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ ይፋ ሲሆን በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; አንተም ከወንድሞችህ ጋራ ሆነህ በጸሎት ተግተህ አግዛቸው፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

   Delete
  2. ወንድም እግዚአብሄር በፍቅሩ ያስብህ አልፈርድብህም ሴጣን የተመረጡትን እንጂ ሌላማ ምንን ያሳድዳል ከእግዚአብሄር ለራቁትማ ሰላም ሰጠቷቸዋል ወደ እነሱም አይቀርብ ማህበረ ቅዱሳኖች የክርስቶስ ጽጌረዳዎች ናቸው እሾህ የበዛባቸው

   Delete
  3. ወንድም እግዚአብሄር በፍቅሩ ያስብህ አልፈርድብህም ሴጣን የተመረጡትን እንጂ ሌላማ ምንን ያሳድዳል ከእግዚአብሄር ለራቁትማ ሰላም ሰጠቷቸዋል ወደ እነሱም አይቀርብ ማህበረ ቅዱሳኖች የክርስቶስ ጽጌረዳዎች ናቸው እሾህ የበዛባቸው

   Delete
  4. ወንድም እግዚአብሄር በፍቅሩ ያስብህ አልፈርድብህም ሴጣን የተመረጡትን እንጂ ሌላማ ምንን ያሳድዳል ከእግዚአብሄር ለራቁትማ ሰላም ሰጠቷቸዋል ወደ እነሱም አይቀርብ ማህበረ ቅዱሳኖች የክርስቶስ ጽጌረዳዎች ናቸው እሾህ የበዛባቸው

   Delete
 10. ወዳጀ በጣም ደክመሀል ይህን የመሰለ ትምህርት ለነጋዴዎችና ለፖለቲከኞች አይገባቸውም መጀመሪያ የእነሱን ዓላመ ተረዳ እነሱ እኮ የሃይማኖት አላማ የላቸውም የሃይማኖት አላማ ቢኖራቸው፡፡

   በየቤተ ክርስቲያኑ በሚገባቸው ቋንቋ ዘወትር የሚባለውን በሰሙ፣

   በአንድ ልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በርሱ ያለ ክብር ጸጋ ከርሱ ጋር ከመንፈስ ቅዱስ ጋር …

   አቤቱ ስለ ሰምህ ስትል ማረን

   በበላነው ቅዱስ ሥጋ በጠጣነው ክቡር ደም ይማረን እተባለ የሚባለው በበቃቸው፡፡ ሥጋወ ደሙ ማለት እኮ ክርስቶስ ነው፡፡ በናትህ ለደንቆሮዎችና ለክፉዎች ኣላማቸው ከፖለቲካ ውጭ ምንም ያልሆነ ዘረኞች ጠባቦች ባትጨነቅ፣

  ቤተ ክርስቲያን እኮ ሲኦል ደጆች አይችሏትም ነው የተባለች ማህበረ ቅዱሳን የሲኦል ደጆች ናቸው አትጠራጠር ዝም ቢባሉ ማንነታቸው ያልታወቀ አይምሰልህ፡፡ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥ ሆነው የሚያምሱ ቀበሮዎች ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በቱርኩ ግራኝ፣ በጅሱሳውያን፣ በመናፍቃን ከደረሰባት ጥፋት እና የምእመናና የሊቃውንት ስደት የበለጠ እያሳደዱን ነው፡፡ ዋናው ስደቱ እንዴት ይቁም ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድሜ! ስለ ማህበረ ቅዱሳን (የደህንነት ድርጅት) እሩቡን ያህል ገና አልተገለጸልህም። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ ይፋ ሲሆን በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; አንተም ከወንድሞችህ ጋራ ሆነህ በጸሎት ተግተህ አግዛቸው፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

   Delete
 11. Oh my God this is a very good job that mk has no answer and confused. ABA SELAMA KEEP IT UP !

  ReplyDelete
 12. hi guys
  why yu\ou didn't post my comment?

  I think it have been hearted u

  ReplyDelete
 13. God bless you Tsega.

  ReplyDelete
 14. ቆርኔሌዎስ ለጴጥሮስ «የአክብሮት» ስግደት ቢሰግድለት «ጴጥሮስ ግን። ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ ብሎ አስነሣው።» (የሐዋርያት ስራ 10፥26)፡፡ እንዲህ ማድረጉ ለቅዱሳን የአክብሮት ስግደት አይገባም ማለቱም አይደል፡፡ እርሱ እንዲያውም ትምህርቱን በቃል መቃወም ብቻም ሳይሆን በተግባርም ነው የተቃወመው፡፡ ስለዚህ ጥፋቱ ከበድ ያለ ነው፡፡ ይህም የማኅበረ ቅዱሳንን ትምህርት መቃወም ስለሆነ ጴጥሮስም ከተጠያቂነት ማምለጥ የለበትም፡፡
  አንድ ስሙ ያልተጠቀሰው መልአክስ ቢሆን ዮሐንስ ከአንዴም ሁለት ጊዜ «የአክብሮት ስግደት» ቢሰግድለት፣ «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤» ብሎ አልከለከለውምን? (የዮሐንስ ራእይ 19፥10፤ 22፥8-9)፡፡ ታዲያ ይህስ መልአክ እንዴት ዝም ይባላል? እርሱም «ተሐድሶ» ስለሆነ ከሌሎቹ ጋር መከሰስ አለበት፡፡

  የማቅ ደቀ መዛሙርት ለጳጳሱ ሲሰግዱ ተመልከቱ

  http://www.dejeselam.org/2011/12/blog-post_21.html#more

  ማንም ከመካከላቸው ጳጳሱንም ጨምሮ "ስግደት ለኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሰው አይገባም"
  ብሎ ያለ ያስተማረ የለም ያሳዝናል::

  ReplyDelete
 15. Gud bel Gondar ... Zendro :)

  Merry Christmas to true orthodox, MK and all

  ReplyDelete
 16. "ሰይጣን ላመሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል" ይቺ ተረት ድሮም የነበረች ናት። ጥቅስ መጥቀስማ ሰይጣንም ይጠቅሳል። ክፉና ደጉን መለየት እንዴት አቃታችሁ? ዮሀንስ ሊሰግድ ተደፋ ትህትናን አስተማረን። መልአኩም ባርያ ነኝ አለ ትህትናን አስተማረን። እስቲ እንደ መልአኩ ራሳችንን ዝቅ እናድርግ። እንደ ዮሀንስም ቅዱሳንን እናክብር። "አንጋጠው ቢተፉ ተመልሶ ባፉ"ይቺ ተረት ድሮም የነበረች ናት። ትዕቢት ክፉ ነው። ትህትና ደግ ነው። ቢጠቀስም ባይጠቀስም። ክፉውን ደግ ነው ብሎ ጥቅስ በመጥቀስ ለማሳመን መሞከር ይቺ የሰይጣን ዘዴ ነች። "ሰይጣን ያረቀቀውን መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን..." ይሉ ነበር አባ ሰላማ ሲያሳርጉ።

  ReplyDelete
 17. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ
  አዳም ከገነት ከተባረረ በኋላ
  ተመልሶ እንዳይገባ ወደ ገነት የሚወስደው መንገድ በኪሩቤል ይጠበቅ ነበር
  ፍጹም ሞትን እንደሚሞት በመጀመሪያው ትእዛዝ በተገለጸው መሠረት ሞት ነግሶበታል

  ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞቱ
  የገነት መንገድ እንደገና ተከፈተ ፤ የመጀመሪያው ወደ ገነት ተጓዥ የነበረውም በቀኙ የተሰቀለው ወንበዴ ነው ፡፡ የኢየሱስ መንገድነት በእምነት የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል
  በሰው ልጅ ላይ ነግሦ የነበረው ዘለዓለማዊ ሞት ፣ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጐ በመነሳት በኩር ሆኖ ሽሮታል /ሕይወትነቱን ገልጿል/


  ከአማላጅነት ጋር በተያያዘ የሚነሳው አለመረዳት የሚያመራው የትምህርት ተፋልሶ በመፍጠር ይሆናል
  1. በስላሴ አንድነትና ሶስትነት ትምህርት ላይ / በስላሴ ላይ መበላለጥን ፣ መከፋፈልን ይፈጥራል/
  2. ቃል /እግዚአብሔር ወልድ/ ሥጋ ሆነ የሚለውን የተዋህዶ ጽንሰ ሃሳብ ይጥሳል

  ማማለድ የሚለው ቃል ሌላ አዲስ ትርጉም እስካልተገኘለት ድረስ ፈጣሪአችን ነው ለምንለው ለእግዚአብሔር በፍጹም የማይስማማ ፣ የማይመጥን ተግባር ነው ፡፡
  ኢየሱስ እግዚአብሔር ሰው የሆነ አምላክ ሲሆን የሰው ባህርያትን እንደሰውነቱ አንጸባርቋል ፣ እንደ አምላክነቱ ደግሞ የመለኮትን ሥራዎች ፈጽሟል ፡፡ ተከታዮቹንም ለማስተማር በቃሉ አስረድቷል ፣ በተግባርም ምሳሌ እየሆነ አሳይቷል ፡፡ ይህን ማለት ግን ሥጋና መለኮት እየተነጣጠሉ የየራሳቸውን ፈቃድ ፈጽመዋል የሚል የአርዮሳውያን ቋንቋ ወይም ፍልስፍና ለማንጸባረቅ አይደለም ፡፡ ነገር ግን በተዋሃዱት ሁለቱ ባህርያቱ የተከወኑትን አማላጅነቱን በደረት በቀጥታ ለሚተረጉሙት እንዲረዱ መንገድ ለመጠቆም ያህል ነው ፡፡

  የኢየሱስ አማላጅነት የተፈጸመው በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ከአዳም የወረስነውን የሞት ፍርድ ስለሞተልን ነው /ዘለዓለማዊ ዕርቅም ወልድ አስገኘልን በማለት እናመልከዋለን/ ፡፡ ኢየሱስ አማለደን የምንለው አዳም በትእዛዝ ተላላፊነቱ ምክንያት ከተፈረደበት ዘለዓለማዊ የሞት ፍርድ ነው ፡፡ የተደመሰሰው ነፍሳት ሁሉ በግዞት በሲዖል ይጠበቁ የሚለውን ፍጹም ሞት ነው ፡፡ በየእለቱ በማወቅና ባለማወቅ የምንፈጽመውን ግብረ ኃጢአት በንስሐ ፣ በጾምና በጸሎት መወጣት ያለብን እኛው ያመንን ሰዎች ሆኖ በቅዱሳን አማላጅነት ይሆናል ፡፡

  ዮሐ 16 ፡ 23
  በዚያ ቀን / ከትንሣዔ በፊት በስቅለት/ ከእኔ አንዳች አትለምኑም ፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል ፡፡ እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም

  ዮሐ 16 ፡ 27
  በዚያ ቀን /ከትንሣዔ በኋላ/ በስሜ ትለምናላችሁ ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም /አማላጅነቱ እስከዚሀ ዕለት ብቻ እንደነበረ የሚያስረዳ ነው/

  ሉቃ 22 ፡ 31 – 32
  እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።

  በተረፈ ስለ አማላጅነት በሁለተኛው ቆሮንቶስ የተገለጸውን እየጐረድን ባናነብና ባንሳሳትበት ጥሩ ነው ፡፡
  2 ቆሮ 5 ፡ 18 – 19 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር ፡፡ ያስተርቅ ነበርና ነበር የሚሉት ቃላት በሰዋስው የሚየመለክተው ያለፈን ጊዜ ነው ፡፡ ይህንኑ ሲደመድመው

  2 ቆሮ 5 ፡ 19 – 2ዐ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ፡፡

  በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ሲል የጥንት ክብሩን መልሶ ተቀዳጀ ማለት ስለሆነ ፣ አሁን የኢየሱስ ክርስቶስ
  መደበኛ ሥራ በዙፋኑ ሆኖ ለመዳኘት በዝግጅት ላይ እንደሆነ ነው እንጅ እያማለደ አይደለም ፡፡

  ካህን የሚለውን ቃልም በጥሬው አለመተርጐምም ምናልባት ግንዛቤአችንን ያስተካክልልናል ፡፡ ካህን የሚለው ቃል የመስዋዕቱን ደም ይዘው ለሚረጩት አገልጋዮች የተሰጠ ስም ስለነበረ ፣ ኢየሱስ የራሱን ደም ራሱ ይዞ በመስዋዕትነት ሲቀርብ የሚያከናውነው ሌላ ተግባር ስላልሆነ ባይመጥነውም ካህን የሚለው ቃል ለአምላካችንም ተሰጠው ፡፡ ይህ ካህንነት ደግሞ እንደ ሌሎቹ ቀደምት ካህናት በዕድሜ የተወሰነ ፣ ሞት የሚያሸንፈውና ዘመን የሚሽረው ስላልሆነ ዘለዓለማዊ ተባለ ፡፡

  ስለ ታቦት መሻር የሚገልጽ መጽሐፍ ቅዱስ ከራዕየ ዮሐንስ /ከምጽዓት በኋላ/ በስተቀር አንድም ኃይለ ቃል የለውም ፡፡ ይልቁንም ሐዋርያው ታቦትን የሚያከብር እንደነበር ከጣዖት ጋር ስላላቸው ልዩነት በማነጻጸር በትምህርቱ ጠቅሶታል ፡፡ ይህ እኛ እንደገባን የምንጠመዝዘው ገለጻ በህግ ፈጻሚነት ስለሚገኘው ጽድቅና በእምነት ስለሚገኘው ጽድቅ ለማወዳደር ነው እንጅ አንዳንዶች እንደማረዱት ታቦትን በመንቀፍና በማንቋሸስ አይደለም ፡፡

  ከመኝታችን ስንነሳ ጀምሮ በየደቂቃው በማወቅም ባለማወቅም ከህግ በታች የምንውልበት ምክንያት እጅግ ብዙና ሰፊ ስለሆነ ፡ በህግ ፈጻሚነት መጽደቅ አዳጋች ነው ፡፡ ሰው በተፈጥሮ ከነሙሉ አእምሮው እያለ ብቻ አይደለም ፣ኃጢአትን የማፈጽመው ተኝቶም በህልሙና በቅዠቱ ይተገብረዋል ፡፡ ይህን ነው ፍጹም መሆን አዳጋች እንደሆነ የመሰከረና ፣ እንድንድንበት የተሰጠን ኢየሱስን ማመን ነው ብሎ ያስተማረው ፡፡

  የብርሃን አምላክ ዓላማውን እንድንረዳ ብረሃኑን ይስጠን

  ReplyDelete
 18. አንድ ስሙ ያልተጠቀሰው መልአክስ ቢሆን ዮሐንስ ከአንዴም ሁለት ጊዜ «የአክብሮት ስግደት» ቢሰግድለት፣ «እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤» ብሎ አልከለከለውምን? (የዮሐንስ ራእይ 19፥10፤ 22፥8-9)፡፡ሚገርም እኮ ነዉ በመጀመሪያ ቃል ነበር ቃልም እግዚአብሔር ነበር ብሎ የክርስቶስን አምላክነት የመሰከረ ሐዋርያ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ለመልአኩ መስገዱ ለምን አልዋጥልህ አለ?እውነትም "ጸጋ" ሀዋርያው ያላወቀዉን (ለመልአክ መሰገድ አለመሰገዱን) ላንተ የተገለጸልህ_እውነትህን ነው "ጸግሽ" የተሃድሶን እንቅስቃሴ ከስሩ ለማድረቅ አንተና አንተን መሰሎቹ የምትጋልቡትን(የሚጋልባችሁን)ፈረሰ (ሰይጣን)እስከ መጨረሻዉ መዋጋት ነው::እግዚአብሔር ማስተዋሉን ትህትናውን ሰጥቶህ የወንጌል ትርጉምን ይግለጽልህ::ከነጌሌ

  ReplyDelete
 19. እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
  እኔ በአባቴ እንዳለሁ እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።
  ከእግዚአብሔር ለሆኑቱ መስገድ መታደል ነው። የሱ ለሆኑቱ የሰገዱ ለባለቤቱማ እንዴት አብልጠው አይሰግዱ? እነኚህን ምእመናን ነው እንግዲህ "ፀጋ" ልትመክር የሞከርከው? እነሱስ ወደ እግዚአብሔር መንበር እና በፊቱ ወዳሉት ቅዱሳን ሰገዱ አንተ ወዴት በኩል ልትሰግድ ነው? "ፀጋ" ሆይ በእግዚአብሔር መንበር ፊት ካሉት ቅዱሳን በፀጋ ትበልጣለህን? ካነጋገርህ ግን የምትበልጥ አይመስለኝም።
  "ፀጋ" የት ነው ያለኸው? "ማንም የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።"

  ReplyDelete
 20. ሰይፈ ገብርኤልDecember 25, 2011 at 8:47 PM

  ውድ አባ ሰላማዎች ያወጣችሁትን ጽሁፍ እንዳነበብኩ የደመነፍስ ያዘጋጀሁትን ጽሁፍ አታወጡት ይሆናል በማለት ወዲያውኑ ያለአንዳች እርማት ሰድጄው ስለነበር ይህን በመጠኑ አስተካክዬ ያብራራሁትን ዳግም ልኬአለሁ በሚያመቻችሁ ዓምድ ብታቀርቡትና ወንድሞች የሚለዩበትን ብናውቅ ክርስትናውን ለመማማር መጽሐፍ ቅዱስንም ለማንበብና በመንፈስ ሆኖ ለመመርመር በጣም ይጠቅማል የሚል አመለካከት ስለአለኝ እንድንማማርበት በማለት ደግም ሰድጄዋለሁ ፡፡

  አቶ ጸጋ ታደለ የጻፉትን ደጋግሜ ለማንበብና ለመረዳት ብዙ ደክሜአለሁ ፡፡ ጽሁፍዎትን ለማገጣጠም የተጠቀሙበት መጽሐፍ የለበጣ ጨዋታን እንደሚያወግዝ እንዴት እንዳልተገነዘቡ አልገባኝም ፡፡ በተለይም ስለ አምላክ ስም መከበርና ፣ በሥርዓትም መገልገል እንደሚገባን በብዙ ተጠቅሷል ፣ ስለ ስሙም ጥቅም እጅግ ብዙ ተብሏል ፡፡ እንደ ባለጌ እየዘረጠጡ ያለአግባብና ያለሥርዓት እንዳገኙ በመጠቃቀስ አጐደፉት ፡፡ ተቀበልንም አልተቀበልን የአምላክ ስሙ በራሱ ክቡር ነው ፡፡

  አይሁዳውያን የአምላክን ስም ቢቻላቸው በቀጥታ ላለመጥራትና ሙሉ ስሙን ላለመጻፍ ብዙ ይሞክራሉ ፡፡ በጸሎት መጽሃፋቸውም ስሙን በሚያገኙበት ወቅት እንኳን አንድም ስሙን ሳያነቡ ለማለፍ ፣ አልፎ አልፎ የግድ ስሙን መጥራት ካለባቸው ደግሞ ስሙን ከመጥራታቸው በፊት ከመቀመጫቸው ተነስተው በአክብሮት ቆመው ነው ስሙን የሚያነሱት ፤ በአጻጻፋቸው ላይ ቢሆንም እንዲሁ ጥንቃቄ ያደርጋሉ ፡፡ ስሙን የግድ መጻፍ ካለባቸው ከስሙ የተወሰኑ ፊደሎችን በማጉደል ይጠቀማሉ እንጅ እንደተገኘ ስሙን በየቦታው አይደነቅሩትም ፡፡ ከነዚህ ጥንቃቄዎች የተነሳም በጊዜ ብዛት የአምላክን ስም በትክክለኛ ለመጻፍና ለመጥራት በችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተዘግቧል ፡፡

  አይሁዳውያን አናባቢ ፊደል ስለማይጠቀሙ ፣ ያህዌህ / YHWH ወይም የኸወኸ / የሚለውን ስም ዛሬ በእርግጠኝነት የሚነበብና የሚጻፈው እንዲህ ነው ብሎ የሚያስረዳ አንድም ሊቅ እንደሌላቸው የአይሁድ እምነት መጽሐፍ ተመራማሪዎች ጽፈውታል ፡፡ ከዚሁ ስም ማክበር ጋር ለመጥቀስ የምፈልገው በመጽሐፍ የሚገኙትን የአምላክ ስሞች በቆሸሸ ጣታቸው ላለመጠንቆል ፣ ለማንበብያ የሚጠቀሙበት “ያድ” የተባለ ጣት መሰል ቁስ ሠርተው በየምኩራቦቻቸው ከመጽሃፋቸው ጐን ማስቀመጣቸው ነው ፡፡ እኛም ብንሆን ምንም እንኳን እንደእነሱ ባንሰቅለውም ስሙን መጠቀም ያለብን በአክብሮት ለጸሎትና ለውዳሴ ብቻ መሆን እንዳለበት ማወቅ ያስፈልገናል ፡፡ እንደ ቆሎ ጓደኛ እሱን ክሰሱት እሷንም እንዲህ በሏት እያሉ ማውሳቱ ፣ ነገርን ለማሳመር ካልሆነ በስተቀር ሌላ የሚያስተምረን መልካም የክርስቲያን ባህርይ አላየሁበትም ፡፡ የአምላካችሁን ስም አታርክሱ ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ ዘሌ 19 ፡ 12

  1. ስለ ሥዕላት አክብሮትና ስግደት
  ስዕልና ቅርጽን እንዲቀረጽና ለአምልኮ መገልገያነት እንዲውል በታቦት መልክ ያስጀመረው አምላካችን ነው ፡፡ በወቅቱ የነበሩ ፈሪሃ እግዚአብሔር አማኞች ታቦትንና ጽላትን ከሰሩና ካጠናቀቁ በኋላ እንዳይዳፈሩት ፣ በበቁ ሰዎች መያዝ እንዳለበት ትእዛዝ በመስጠት ያከበረውም አምላካችነ ነው ፡፡ ይህም ማለት ለፈጣሪና ለቅዱሳን ስዕልና ለቅርጻ ቅርጽ የሚሰጠው የፈጣሪነት አምልኮ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መገለጫነቱ የአክብሮት ብቻ ነው ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ ፣ አትስገድላቸውም ያለው ፈጣሪ ታቦትን እንድናከብር ሰጥቶናል ፡፡ ስለ ስዕልና ቅርጻ ቅርጽ የሚናገሩ ኃይለ ቃሎች ዘጸ 25 ፡ 18 ፣ 37 ፡ 7 ፣ 21 ፡ 1 ፤ ህዝ 4 ፡ 1 – 3 ፤ 1 ነገ 6 ፡ 21 – 29 ፤ ገላ 3 ፡ 1

  ወደዚህኛው ዘመን ስንሸጋገር የምናገኘው ታሪክ ደግሞ በአራተኛሙ መቶ ዓ.ም. ገደማ በግሪኮችና በሩስያውያን በስዕል መጠቀምን የደገፉበት ምክንያት መሃይም ክርስቲያኖችን ለማስተማርና አህዛብን ለመመለስ ቀላል የመገናኛ ስልት በመሆኑና የክርስትና ሃይማኖትን ለማስፋፋት ቀና መንገድ ስለሆነ ነበር ፤ በወቅቱም የዚህ ሥርዓት መስፋፋት የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከሮማ ካቶሊክ እንድታፈነግጥ ያደረገ ከሌሎች ልዩነቶች ተጨማሪ ምክንያት ነበር ፡፡ በወቅቱ በሥዕላቱ የሚገለጹት ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ያሳለፋቸውንና የፈጸማቸውን ታሪኮች ፣ የቅድስትና ድንግል ማርያም የአምላክ እናትነትን እንዲሁም የቅዱሳን ተግባራትን የሚያንጸባርቁና የሚያስታውሱ ናቸው ፡፡ እነዚህ ሥዕላት አእምሮአችንን በመንፈስ ለመሰብሰብና /meditation/ ጸሎታችንን ወደ ብቸኛው ፈጣሪ ለማቅረብ እንድናተኩር ይረዱናል እንጅ አምልኮ ስግደት እየተፈጸመባቸው አይደለም ፡፡

  2. እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ሲል የሚያመለክተው ሁለት ክስተቶችን ነው ፤
  ሀ. አዳም ከገነት ከተባረረ በኋላ የተተገበሩትን ሁኔታዎች ፡-
  አዳም ተመልሶ እንዳይገባ ወደ ገነት የሚወስደው መንገድ በኪሩቤል ይጠበቅ ነበር
  የተሰጠውን ትእዛዝ ስለተላለፈ ፍጹም ሞትን ይሞት ፣ ሞትም በሰው ሁሉ ላይ ነግሶ ነበር

  ለ. ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞቱ የተገኘውን ለውጥ ፡-
  - ወደ ገነት መግቢያው መንገድ እንደ አዲስ ተከፈተ ፤ የመጀመሪያ ወደ ገነት ተጓዥ የነበረውም በቀኙ የተሰቀለው ወንበዴ ነበር ፡፡ የኢየሱስ መንገድነት በእምነት የሚገኝ መሆኑ በትምህርቱ ተገልጿል
  - በሰው ልጅ ላይ ነግሦ የነበረውን ዘለዓለማዊ ሞት ፣ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጐ በበኩርነት በመነሳት ሽሮታል /ሕይወት ነኝ ማለቱም ይህን በተግባር የሚገልጸውን ለመጠቆም ነው/

  ReplyDelete
 21. Mecheresachehu tefat nehonu askedemo yeteteqeselachehu bemhonu ansheberem manenetachehun erasachew geletacehu.Mechem beohne betekrstyanachen atetadesem enante talfalacheu enje

  ReplyDelete
 22. YOU are not working with reality b/c why you approve our comment.

  ReplyDelete
 23. Ur idea and u wrote on the wall shows no knowledge about Jesus Christ and bible .

  ReplyDelete
 24. aye aba selama mahiberekidusanen lemekawem belachehu be geta mekeled jemerachu??

  ReplyDelete
 25. ነገርን ትተን የእግዚአብሔርን ቃል ብቻ ብንነጋገር፡ በመታመስ ላይ ስላለችው ቤተ ክርስቲያናችንና ስለአባቶቻችንም ብንጸልይ አይሻልም?
  ኑና ለሁሉም ዘመን ለሁሉም ሰው የተጻፈውን ታላቁን መጽሐፍ እናጥና። ፍቅርን ብቻ እንዝራ
  http://dat27.blogspot.com/

  ReplyDelete
 26. mahibere kidusin mekawom lela ye menafikan astemiro masitegabat lela new yilikunum abba selamawoch bitasibubet melikam new yih timihirt ye tehadiso woyim yelela menafikan tekuwamoch timihirt new tesga tadele botah lelela new timirtihin astesasebihin yizeh ke tewahido bet zewor bel

  ReplyDelete
 27. አይ አናንተ አሁን አሁን በግልጽ ማን እንደሆናችሁ እያሳወቃቸሁን ነው በቃ ሰው እንደዚህ በግልጽ ሲናገር ደስ ይላል ከዚህም በሁዋላ በግልጽ እንደ አርዮስ ጌታ ሰው ነው በሉን (ምን በሉን አላችሁ) ቅዱሳን፣ መላእክት ምናምን የሚባል የለም በማለት ክርስትና አይሉት ፍልስፍና አካሂዱ ድሮም እናንተ አላማችሁ እግዝአብሄርን ማምለክ ሳይሆን ቀስ በቀስ ሰው ሁሉ ፈጣሪን ክዶ ሃይማኖት የለሽ እንዲሆን ማድረግ ነው፡ የሚገባው ይገባዋል የሄንን ጠንካራ ምነት የሌለውን አሳስቱ ሌላው እንኩዋን ይረዳችሁዋል፡
  እንግዲህ ምን ትሉ ክርስቶስ አምላክ አይደለም ካላችሁን ሌላ ከናንተ ምን እንጠብቅ በቃ እንደዚህ በግልጽ በቃ ፈጣሪያችሁ ሰው ነው ብላችሁን ማንነታችሁን ማሳወቃችሁን ግን ማንነታችሁን እንድንረዳ ስላደረገን ሳናመሰግናችሁ አናልፍም ግን አላማችሁ ምንድን ነው፡
  ደግሞ ስወር አካዳችሁ ሁንም አለ
  ክርስቶስ አምላክ ነው
  ቅዱሳን ያማልዳሉ
  ለመላእክት እና ለቅዱሳን ስግድት ይገባል የሚለው አስተምህሮ የማህበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱ እምንተ ነው ይህንን ደግሞ እንደናንተ ዘመን አመጣሾቹ ናቸው እንጂ የጥንት ክርስቲያኖች ለምሳሌ ካቶሊኮች፣ ግሪክ ኦርቶዶክስ፣ የሩሲያ ቤተክርስቲያን ሌሎቹም ቀደምት ሆኑት ሁሉ የሚቀበሉት ነው፡፡ ምናለ እናንተ የመከፋፈል ሴራ ለማድረግ ይህንን ትለልቁን ነገር የማህበረ ቅዱሳን ብቻ አደረጋችሁት ይሄ አካሄድ ለመከፋፈል ነው በዚህ ማንንም አታታልሉም እና ተዉት እባካችሁ
  እኛ አባቶቻችን እንዳስተማሩን ክርስቶስ በተዋህዶ የከበረ አምላክ ነው፣ ቅዱሳንም ያማልዳሉ መላእክትም ያማልዳሉ ስግድትም (ያክብሮት) ይገባቸዋል ጌታ ደግሞ ማላጅ ሳሆን ፈራጅ ነው፡፡
  ተማሩ ሰው አታደናብሩ እህ እህ

  ReplyDelete
 28. አቡነ አብርሃም እጅ ሰጡ

  ይህ ዘገባ የተላከልን ከአሜሪካ ሲሆን፣ ዘጋቢው ያቀነባበሩትን ሳንጨምር፣ ሳንቀንስ እንዳለ አቅርበነዋል፡፡ "ማኅበረ ቅዱሳን" በdeje selam ትዊተር ገጹ፣ በገብርኄር፣ በአንድ አድርገን እና በሌሎቹም ብሎጎቹ በ"ዕንባ ታጠብን" ካለበት የአቡነ አብርሃም ሽኝት ዘገባዎች ጋር ያስተያዩት፡፡
  "በቀልን ለተጠማ አባት እጄን አልሰጥም" ሲሉ የነበሩት አቡነ አብርሃም የጠየቁት የፖለቲካ ጥገኝነት ስላልተሳካላቸው እጃቸውን ለመስጠት ተገደዋል፡፡ ቀድሞውንም ቢሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አሜሪካን የላካቸው እንዲያስተምሩ ቤ/ክ እንዲሰሩ ህዝቡን እንዲያጽናኑ እንጂ የአሜሪካን የመኖርያ ፈቃድ አውጥተው እንዲኖሩ አልነበረም፡፡ እናም የቅዱስ ሲኖዶስን ስብሰባ ሲቀሩ ፓትርያሪኩ ግሪን ካርድ አላሰጡኘምና እጄን አልሰጥም በማለት ፎክረው ነበር የዛሬን አያድርገውና፡፡


  ከሰሞኑ የማቅ ልሳናት የሆኑት ብሎጎች የአቡነ አብርሃምን መመለስ አስነብበውናል፡፡ ጥቂት የማቅ አባላትም ሲላቀሱ በቪድዮ አሳይተውናል ምን ያድርጉ እንደፈለጉ የሚነዱዋቸው የነሱን ሀሳብ የሚያራምድላቸው ሰው ማጣት ለማቅ ትልቅ ክስረት መሆኑንም ስለተገነዘቡ ነው፡፡ መመለሳቸው መልካም ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን የተላኩበትንና ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣቸውን አደራ ወደ ጎን በመተው የማቅ ተላላኪ መሆናቸውና ባይሳካም ለፖለቲካ ጥገኝነት ሲዳክሩ ቆይተው መመለሳቸው ነው፡፡


  ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አሜሪካን ሲልካቸው ቤተክርስቲያን እንዲሰሩ ህዝቡን እንዲያስተምሩ እንዲያጽናኑ ነበር እሳቸው ግን አሜሪካንን ከረገጡበት ጊዜ ጀምሮ የሰሩት ስራ ቢኖር የሚያስተዳድራቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ በመተው በሀገረ ስብከት ስም ማህበርዋን ማጠናከር ማደራጀት ስራቸው አደረጉ፡፡ በእርግጥ አቡነ አብርሃም ለመጠቀሚያነት ማህበሩን ቢጠጉም ማህበሩ ግን ወቅታዊ መለመኛ ጉዳይ ማስፈጸሚያ በክብር የተሰጣቸውን አስኬማ የማህበሩ የማስታወቂያ መለጠፍያ አደረጉት፡፡ ሠይጣን በህድረት በእባብ እንደሰራ ማህበረ ቅዱሳንም በአቡነ አብርሃም መስቀልና አስኬማ የዘረኝነትን የድል ዜማ የገንዘብ መውደድ ጠኔውን የቡድናዊነት ባንዲራውን ሰቀለበት፡፡ እናም አቡነ አብርሃም ከማቅ ውጪ ለምኔ አሉ፡፡


  በዚህ ቢያበቁ መልካም፡፤ ከሀገሩ ተሰዶ በባዕድ አገር እየተሰባሰበ የሚያስቀድስበትን ቅዱስ ስጋውና ደሙን የሚቀበልበትን በተለምዶ /ገለልተኛ/ ተብለው የሚጠሩትን የኢ.ኦ.ተ.አቢያተ ክርስቲያናት አቡነ አብርሃም የጣኦት ቤት ህዝቡንም ጣኦት አምላኪ ካህናቱንም ለሆዳቸው ያደሩ በማለት በማግለላቸው ከሀገር ከወገን ተለይቶ የአፅናኝ ያለህ የሚለው የዲሲና አካባቢው ምዕመን በቁጣ በገነ፡፡ ሆድ ለባሰው እንዲሉ …….. አቡነ አብርሃም ማለቱን ትቶ "ሼህ ኢብራሂም" የሚል ቅጽል ሰጥተዋቸው በቆሙበት ላይቆም በሄዱበት ላያልፍ መስቀላቸውን ላይሳለም ቃል ገባ፡፡ አቡነ አብርሃም ህዝቡን አጽናኑ ተብለው ቢባሉ አሳዘኑት፤ ባርኩት አስተምሩት ቢባሉ ጣኦት አምላኪ ብለው ሰደቡት፡፡ የማይጠበቅባቸውን ፈጸሙ ዘረኝነታቸውንና ቡድናዊነታቸውን በአደባባይ ገለጡ፡፡


  በዚህ ብቻ አላበቁም ማህበረ ቅዱሳን ለሚያልመው የፖለቲካ ማራመጃ አባላትን መመልመያ የጽንፈኞች ዋሻ በመንበረ ጵጵስና ሽፋን በቨርጂንያ በተክለ ሃማኖት ስም የከፈተው ቤ/ክ ትልቁ ማሳያ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በዲሲና አከባቢው የሚኖሩ ነባር አቢያተ ክርስትያናትና ምዕመናን ግልጽ ምስክሮች ናቸው፡፡ ማቅ በሀዋሳ በዲላና በተለዩ ቦታዎች ከየአቢያተ ክርስትያናቱ በስነምግባር ችግር የተባረሩ ወጣቶችን እንዲሁም የቤተክርስቲያንን ንብረት በመዝረፍ በየፍ/ቤቱ እየተከሰሱ ያሉትን ግለሰቦች በማሰባሰብ አይዙዋችሁ እኔ አለሁ፤ በማለት ለሁከትና ብጥብጥ እንደሚያሰለጥናቸው ሁሉ፣ የአቡነ አብርሃምን ከፋፋይ ትምህርት የሰሙ ከየሰንበት ት/ቤቶች በስነ ምግባር ችግር የተባረሩ ወጣቶችን በመስበብ ለሚያቅደው የተንኮል ዕቅድ እያዘጋጃቸው መሆኑን በዲሲና አከባቢው የሚገኙ ምዕመናን የሚያውቁት እውነት ነው፡፡


  እነዚህ ስብስቦች በነበሩባቸው ቤተ ክርስትያናት የስነምግባር ችግር ያለባቸው ጠበኞች ስም አጥፊዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ደግሞ ለማቅ ውድ መሳርያ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በነዚህ ህጻናት መካከል ያለ እድሜዋ የምትዳክረው የአባቶችንና የአገልጋዮችን ስም በማጥፋት ዶክተሬትዋን የጨበጠችው እድሜዋን እንኩዋን በውል የማታውቀው ፋንቱ ወልዴ ናት፡፡ እኛ ግን በየመድረኩ የምታደርገውን ዝላይ አቁሚና እንደ ዕድሜሽ ንሰሀ ገብተሽ ቁረቢ እንላለን፡፡ እናም ዛሬ አቡነ አብርሃም ትላንት እጅ አልሰጥም ቢሉም የጀመሩት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ እጅ ሊሰጡ ተገደዋል፡፡ የማህበሩ ብሎጎች እንደዘገቡትም ወደ ሀገር ቤት ገብተዋል፡፡ አቡነ አብርሃም እዛም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ይቀጥሉ ይሆን? ወደ ፊት የምናየው ይሆናል …..  እግዚአብሄር ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ይጠብቅልን!!

  ReplyDelete
 29. ማቆች ማቅ እስኪለብሱ ድረስ በዚሁ ቀጥሉ

  ReplyDelete
 30. Are you telling us your teachings indirectly? We know all these were your teachings before and your goals are destroying our church's teachings and the true biblical heritages by your heretic teachings. We know Isayiyas, St paolos, all other saints well before; more than this we know our Lord Jesus Christ as as The Son of God and True savior not as intercessor as you say. You better learn the truth and think for your souls and for the souls of your followers before the days pass and nights come.

  ReplyDelete
 31. the fact that protestant is driven by money we do not take any consideration for what ever they write and come with.because the more they are funded the more they will write false messages, which otherwise, no food to eat.however,despite your daily false deeds,mk keep doing its work ahead more than ever been with the help of God.

  ReplyDelete
 32. Tebate and aba zelebanose sexual life released for public the victom speak out those monk still behind the bar please make some thing because the only choice to learn bible about Jesus is this web. God bless you GA

  ReplyDelete
 33. Egziabiher Yibarikih Seyife Gebreil Tsega Tadle Yemilut Menafik Lestafew Melsun Ygegne Yimesilegnal Tiyake Le Tsega Tadele Eyasu Ye segedew Lemann New???????

  ReplyDelete
 34. ሠይፈ ገብርኤልDecember 28, 2011 at 1:38 PM

  የቄሳርን ለቄሳር ስለሚል የሃይማኖትን ትምህርት ከምድራዊ አስተዳደርና ፖለቲካ ጋር እየደባለቃችሁ የምታደናብሩን ካላችሁ ወገናችሁን ለዩልን ፡፡ እኔ አስተያየቴን ማካፈል የፈለግሁት አቶ ጸጋ ታደለ ለሰጡት መሠረታዊ የሃይማኖት መልዕክት ከኦርቶዶክስ እምነቴ ጋር ስላልተጣጣመ ፣ መጽሐፍ ቅዱሱም ግንዛቤ ላይ ሰፊ ልዩነት ስለፈጠረ እንማማርበት እንደሁ በማለት ነው ፤ ከዚህ ውጭ ግን የማንኛውም ቡድን ተከታይ አይደለሁም ፡፡ ብዙ ነፍሳት የሚድኑበትን ሥራ መሥራት ሰንችል በማይጠቅመው ላይ በማተኮር ጊዜ እናጠፋለን ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስትና እምነት ጉዞ ውስጥ ልዩነትና ቅራኔ ሲኖር እንዴት እንደሚፈታ ስላስተማረ አለመግባባቱ ካለ መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ አካሄድ ብንጓዝና በሲኖዶስ ብንመራ መልካም ነው ፡፡ ካባ ለብሳችሁ ሲመች በቅስና ሳይሆን በጀሌነት ለመኖር የምትፍጨረጨሩና ከሁለት ወገን ገበጣ መጫወት የምትመኙ ካላችሁ እግዚአብሔር አይወደውምና ፣ ከየአቅጣጫው /ከላይ ባለዘውዶች ከታችም መዥገሮች ከጐንም ጠላቶች/ በየአይነቱ እየተቆፈሯት ያለች ቤተ ክርስቲያን ናትና ሃይማኖታችንን የባሰውኑ አታዳክሙ ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር የሆነውንም የዋህ ምእመን በየቦታው አትከፋፍሉት ፡፡ የዚህ ዘመን ትውልድ የአህያዋን እኔ ከሞትኩ ተረት ይመስል እኔ ከሌለሁበት ወይም ካልተጠቀምኩበት በማለት የሚቅበጠበጥ ይመስላልና ለሁላችንም ቸሩ አምላክ ልቦናችንን ወደራሱ መንገድ ይመልስልን ፡፡

  ከዚህ በተረፈ ከዚህ ቀደም አስተካክዬ ከላክሁት መልስ ውስጥ ተጐርዶ የቀረውና ልንማማርበት ይችል ይሆናል የምለውን አስተያየት ከዚህ አስከትዬዋለሁ ፡፡


  3. በአማላጅነት ዙሪያ የሚነሳው ማደናገሪያ የሚያመራው መሠረታዊ ወደ ሆኑ የሃይማኖት ትምህርት ተፋልሶ ነው
  ሀ- በስላሴ አንድነትና ሶስትነት ትምህርት ላይ መከፋፈልንና መበላለጥን ፣ ብዙሃ አምላኮችንም ይፈጥራል
  ለ- ቃል /እግዚአብሔር ወልድ/ ሥጋ ሆነ የሚለውንም የተዋህዶ ቀዳሚ እምነት መሠረት ያፈርሳል

  ማማለድ የሚለው ቃል መዝገበ ቃላት ከሚሰጠው ውጭ ሌላ አዲስ ትርጉም እስካልተገኘለት ድረስ ፈጣሪአችን ነው ለምንለው አምላክ በፍጹም የማይስማማና የማይመጥን ተግባር ነው ፡፡
  ኢየሱስ እግዚአብሔር ሰው የሆነ አምላክ ሲሆን የሰው ባህርያትን /መራብ ፣ መጠማት ፣ መድከም ፣ መፍራት ፣ ማልቀስ / እንደሰውነቱ አንጸባርቋል ፣ እንደ አምላክነቱ ደግሞ የመለኮትን ሥራዎች /ህሙማንንና ድውያንን ፈውሷል ፣ ዕውራንን አብርቷል ፣ ሙታንን አስነስቷል …./ ፈጽሟል ፡፡ ተከታዮቹንም ለማስተማር ደግሞ በቃሉ አስረድቷል ፣ በተግባርም ምሳሌ እየሆነ ማድረግ የሚገባቸውን አሳይቷል ፡፡ ይህን ስንል ግን መለኮትና ሥጋ እየተነጣጠሉ የየራሳቸውን ፈቃድ ፈጽመዋል የሚል የአርዮሳውያን ቋንቋ ደግመን ለመናገር ወይም ፍልስፍናቸውን ለማንጸባረቅ አይደለም ፡፡ ነገር ግን በመዋሃድ አንድ የሆኑት ሁለቱ ባህርያቱ የከወኑትን አማላጅነት በደረት በቀጥታ ለሚተረጉሙት እንዲረዱ መንገድ ለመጠቆም ያህል እንጅ ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስም የእነዚህን ሁለት ባህርያት ሥራ ላልገባቸው ለማስረዳት በተለያየ ቦታና ሰዓት በተለያየ መንገድ አንዴ የሥጋን ሌላ ጊዜ ደግሞ የመለኮትን ባህርይ በመግለጽ ተጠቅሞባቸዋል ፡፡

  መጽሃፍ እንደሚያስረዳን የኢየሱስ አማላጅነት የተፈጸመው በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ፣ እንደብራና ተወጥሮ በሞተልን ዕለት ነው ፡፡ አዳም በትእዛዝ ተላላፊነቱ ምክንያት የተፈረደበትን ተወራራሽ ዘለዓለማዊ የሞት ፍርድ ለመሻር በእኛ ምትክ በተሰዋልን ሰዓት /ዕብ 9 ፡ 26/ ፣ በአዳም ዝርያና በአምላክ መሃከል የነበረውን የጸብ ግድግዳ በመስበሩ አማለደን እንላለን ፤ ስለዚህም ተግባሩ ዘለዓለማዊውን ዕርቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወልድ አስገኘልን በማለት እናመልከዋለን ፡፡ ይህን በመፈጸሙም በሲዖል በግዞት ይጠበቁ የነበሩት ነፍሳት ሁሉ ከነበሩበት በኢየሱስ ክርስቶስ የደም ካሳ ነጻ ወጥተዋል ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን በየዕለቱ አውቀን በድፍረት ፣ ሳናውቅ በስህተት የምንፈጽማቸውን ግብረ ኃጢአት በሙሉ የምንሽረው በእምነት ፣ በመልካም ተግባር ፣ በንስሐ ፣ በጾምና በጸሎት ራሳችንን በማጠንከርና በቅዱሳን አማላጅነት ነው ፡፡
  ዮሐ 16 ፡ 23
  በዚያ ቀን / ከትንሣዔ በፊት በስቅለት ለማለት/ ከእኔ አንዳች አትለምኑም ፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል ፡፡ እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም ፤ ወረድ ብሎ ደግሞ
  ዮሐ 16 ፡ 27 ላይ
  በዚያ ቀን /ከትንሣዔው በኋላ ለማለት/ በስሜ ትለምናላችሁ ፤ እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም /እነዚህ ሁለቱ የተጠቀሱት ኃይለ ቃሎች የአማላጅነቱ ሥራ መደምደሚያ ድንበር ወይም ዕለት መች እንደነበረ የሚያስረዱን ናቸው/
  ሉቃ 22 ፡ 31 – 32
  እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና፤ አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ። ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ። እዚህም ላይ ዙፋኑን ከተረከበ በኋላ የቀደመ ሥራውን መሥራት ሲጀምር እራሱ እንደሚፈጽመው ማለቱ ነው ፡፡

  ከዚህ በተረፈ ስለ አማላጅነት በሁለተኛው ቆሮንቶስ የተገለጸውን እንዲያመቸን እየጐራረድን ባናነብና ባንሳሳትና ባናሳስትበት መልካም ነው ፡፡
  - 2 ቆሮ 5 ፡ 18 – 19 ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር ፡፡ ያስተርቅ ነበርና ነበር የሚሉት ቃላት በሰዋስው የሚየመለክተው ያለፈን ጊዜ ተግባር ነው ፤ መፈጸሙን ለመግለጽ ነው ፡፡ ይህንኑ የነበር ታሪክ ለመደምደም በሚቀጥለው ኃይለ ቃል እንዲህ ብሏል
  - 2 ቆሮ 5 ፡ 19 – 2ዐ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን ፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ፡፡ ይህም ማለቱ አማላጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያትና የበቁ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ይገልጻል ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 35. ሠይፈ ገብርኤልDecember 28, 2011 at 1:40 PM

  መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ካረገ በኋላ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ ሲልም የጥንት ክብሩን መልሶ ተቀዳጀ ማለቱ ስለሆነ ፣ አሁን የኢየሱስ ክርስቶስ መደበኛ ሥራ እንደ አዳም ዘርነቱ ወዙ ጠብ እስከሚል በግንባሩ ተደፍቶ መጸለይና ማማለድ ሳይሆን በዙፋኑ ሆኖ ለመዳኘት በዝግጅት ላይ ነው ፡፡

  ካህን የሚለውን ቃልም በጥሬው አለመተርጐም ምናልባት ግንዛቤአችንን ያስተካክልልናል ፡፡ ካህን የሚለው ቃል የመስዋዕቱን ደም ይዘው ለሚረጩት አገልጋዮች የተሰጠ ስም ስለነበረ ፣ ኢየሱስ የራሱን ደም ራሱ ይዞ በመስዋዕትነት ሲቀርብ የሚያከናውነው ሌላ ተግባር ስላልሆነ ባይመጥነውም ሊቀ ካህን የሚለው ቃል ለአምላካችንም ተሰጠው ፡፡ ይህ ካህንነት ደግሞ እንደ ሌሎቹ ቀደምት ካህናት በዕድሜ የተወሰነ ፣ ሞት የሚያሸንፈውና ዘመን የሚሽረው ስላልሆነ ዘለዓለማዊ ተባለለት ፡፡

  በአጠቃላይ ከላይ የገለጽኳቸውን ለመሰብሰብ ኢየሱስ አማለደ የሚባልበትን ዘመንና ስለካህንነቱ የተነገረለትን ለማየት እንዲያስችለንን ለዕብራውያን ከተጻፈው መልዕክት በምዕራ. 5 ፡ 7 – 1ዐ የተገለጠውን እንመልከት
  ** 7 እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤
  ** 9-10 ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጸዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ ፣ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።

  ሐዋርያው ያስተማረውን በአጭር ቃል ለመግለጽ፡-
  1. ኢየሱስ ከእንባ ጋር ጸሎቱንና ምልጃውን ያቀረበው ወይም የፈጸመው በስጋው ወራት /በአካል በመሃከላችን እያለ/ እንጅ አሁን በአምላክነት በአባቱ ቀኝ ወደ ዙፋኑ ከተመለሰ በኋላ አይደለም
  2. ይህ በስጋ ወራት የተፈጸመው ጉዳይ / በመስቀል ላይ መስዋዕት ከሆነና ደሙን ካፈሰሰ በኋላ/ እንደ መልከ ጸዴቅ ሊቀ ካህናት ተባለልን ፡፡

  መጥፎ ምሳሌ ቢሆንም አንድ ወታደር የሚታወቀው በመጨረሻ በደረሰበት ሹመቱ እንጅ ሥራ በጀመረበትና በተቀጠረበት የተራ ወታደርነት ማዕረግ አይደለም ፤ ወደ ክርስትና ትምህርትም ስንመልሰው ኢየሱስ ይህን የእኛን ሥጋ በመልበስ በእኛ ባህርይ እየተራበ ፣ እይተጠማ ፣ እየደከመ ለተወሰነ ዘመን ኑሯል ፤ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን የማዳን ተልዕኮ ከፈጸመ በኋላ ግን ወደ ዙፋኑ ተመልሶ በአባቱ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ አሁን እሱን ማወቅና መቀበል ያለብን በዚህ ክብሩ ነው እንጅ ለምሳሌነት በየተራራው እየተደፋ የልቅሶ ጸሎት በሚያደርስበት ዘመኑ በነበረው ደካማ ሥጋው አይደለም ፤ እኒያን ወቅቶች ማብቃታቸውን ሲያውጅ ተፈጸመ በማለት በመስቀል ላይ ነፍሱን ሰጥቷል ፡፡

  4. ስለ ታቦት ክብርና አገልግሎት መሻር በግልጽ የተነገረ ወይም የተጻፈ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ኃይለ ቃል የለም ፡፡ እንዲያውም በራዕየ ዮሐንስ እንደተጠቀሰው ከሆነ በሰማይም ባለው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ታቦት ስለአለ ከታቦት ጋር ቅራኔ ያላችሁ ምናልባት በተዘዋዋሪ እምነት የመሄድ ዕድሉ ከገጠማችሁ እዛም ይጠብቃችኋልና ተዘጋጁ /ራዕ 11 ፡ 19/ ፡፡ ወደፊት ግን አዲሲቱ ሰማይና ምድር ከተገኘችና ሁሉም ነገር አዲስ ከተደረገ በኋላ ፣ ሞት ፣ ኃዘን ፣ ሥቃይና ጩኸት ሁሉ ለመጨረሻ ጊዜ ከሰዎች ዘንድ ከተወገዱና ሁሉንም በሥርዓቱ በማስተካከል ከፈጸመ በኋላ ፣ ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ስለሚሆን ታቦት የማይኖርበትና የማያስፈልግበት ጊዜ / ራዕ 21 ፡ 1 ፣ 4 – 6 ፣ 22 / ይመጣል ፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ሌሎች ይኸኛው የቅድስና አሻራ ስለሌላቸው ቀርቷል ተሠርዟል ቢሉም እኛ ስላለን ፣ መቅረትና መሠረዙ በየትኛውም የመጽሐፍ ክፍል የተገለጸ ስላልሆነ በሥርዓቱ እንገለገልበታለን ፡፡ ለሚያምኑበትም ብዙ ተአምራትንና ገድላትን መፈጸሙ አገልግሎቱ እንዳልተቋረጠ እራሱ እየመሰከረ ይገኛል ፡፡

  ከዚህ በተረፈ ግን ሐዋርያው ጳውሎስ ታቦትን የሚያከብር እንደነበር የምንረዳው ከጣዖት ጋር ስላለው ልዩነት በማነጻጸር ታቦት ክብር እንዳለው በትምህርቱ መጥቀሱ ነው /2 ቆሮ 6 ፡ 16/ ፡፡ ይህ እኛ እንደገባን የምንጠመዝዘው ገለጻ በህግ ፈጻሚነት ስለሚገኘው ጽድቅና በእምነት በኩል የሚገኘውን ጽድቅ ልዩነት ለማወዳደር የተናገረውን በመመርኰዝ ነው እንጅ አንዳንዶች እንደተረዱት ታቦትን በመንቀፍና በማንቋሸስ አይደለም ፡፡
  --ዕብ 9 ፡ 5 ስለ ታቦት ዝርዝር ሁኔታ ካስረዳ በኋላ “ስለ እነዚህም ፣ ስለ እያንዳንዳቸው ልንናገር አሁን አንችልም “ ይላል ፡፡ ይህም ማለት እሥራኤላውያን ታቦታቸው ጠፍቶባቸው ስለነበረ ስለዛ ነገር ማስላት አለመቻላቸውን ሲያስረዳ የገለጸው ነው ፡፡ ሐዋርያው በነበረበት ዘመን የታቦት ሥርዓቱና ክብሩ ሁሉ በእሥራኤላውን ዘንድ ተዘንግቶና ተረስቶ ነበረ ፡፡
  --ዕብ 9 ፡ 1ዐ የሚፈጸሙት ሥርዓቶች “የሚያመልከውን በሕሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም” ሲልም ሰው በሰራው ኃጢአት ሕሊናው ከተጐዳ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለማገገም እንደማይችል ሲያስረዳ እንጅ እግዚአብሔር የመዳኛ መንገድ አድርጐ የደነገገውን ሥርዓት አያድንም ለማለት አይደለም ፡፡ ሰው በተፈጥሮው ባህርዩ ስህተት ሲሰራ ሕሊናው ስለሚፈርድበት ያንን የሕሊና ቁስልና ጠባሳ መጠገን አይችልም ፤ ዘወትር ከመጸጸትም እንደማይድን መግለጹ ነው ፡፡
  ይቀጥላል

  ReplyDelete
 36. ሠይፈ ገብርኤልDecember 28, 2011 at 1:44 PM

  ከመኝታችን ስንነሳ ጀምሮ በየደቂቃው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከህግ በታች የምንውልበት ምክንያት እጅግ ብዙና ሰፊ ስለሆነ ፡ ሙሉ በሙሉ በህግ ፈጻሚነት ብቻ መጽደቅ አስቸጋሪ እንደሆነ ያስተምራል ፤ ያላመነዘረው ይሠርቃል ፣ ያልሠረቀው ደግሞ ይዋሻል ፣ ያልዋሸው ቢሆን ያመነዝራልና ፡፡ በጠቅላላው ሰው ኃጢአትን የሚፈጽመው በሙሉ አእምሮው እየተንቀሳቀሰ ሳለ ብቻ ሳይሆን ፣ ተኝቶም በህልሙና በቅዠቱ ጭምር ነው ፡፡ ይህን ሁኔታ ሐዋርያው በሥርዓቱ ስለተገገነዘበ ፣ እንድንድንበት የተሰጠን መንገድ ኢየሱስን ማመን ብቻ እንደሆነ አስተማረን ፡፡ ህግ ፈጻሚነት መልካም ቢሆንም ሰው ዘወትር ከስህተት ስለማያመልጥ በዚኸኛው መንገድ የመዳን ዕድላችን ደካማ መሆኑን ገለጸ ፡፡

  5. ለመላእክትና ቅዱሳን ስግደትን በተመለከተ ፡-
  የክርስቲያንነትን መድረሻው ድንበር ከመረመርነውና ከተረዳነውና በመንፈስ ሆነን ከቃኘነው ፣ በተቻለን ሁሉ በጾሙ ፣ በጸሎቱና በምግባሩ ሁሉ የኢየሱስን ምሳሌነት መከተል” ነው ፡፡
  አምላክ ሆኖ ሳለ የፈጠረውን የአዳምን ሥጋ በመዋሃድ ሰውን መሆን ማለት ራሱን ከምንም በላይ እጅግ ዝቅ ማድረጉንና ማዋረዱን የሚያሳየን ነው ፡፡ በእኛ የስግብግብነት ባህርይ እንኳንስ ከሰማያዊው ዙፋን ከመንደርም የሥልጣን ወንበር ተነስቶ ራሱን ዞር ለማድረግ የሚፈቅድ ሰው የለም ፡፡ የክርስትና እምነታችን በጐለበተ መጠን ግን ራሳችንን ማዋረድና ዝቅ ማድረግ መልመድ እንደሚገባንና ምንም የማንረባ መሆናችንን መረዳት ፣ በራሳችን ምንም ዋጋ እንደሌለን መገንዘብ እንዳለብን ሲያስተምሩን የአክብሮት ስግደት የቀረበላቸውን የተቃወሙ ግለሰቦችና መላዕክት እንዳሉ በመጽሐፍ ቅዱሱ በተለያየ ሥፍራ ተጠቀሶልናል
  1. እኛ በባዶ ሜዳ እንዳንኮፈስ ፣ በራሳችንም እጅግ እንዳንታበይ ፣ በሆነውና ባልሆነው ፣ በሚገባውና በማይገባው ሁሉ ከሌሎች በላይ ራሳችንን ከፍ እንዳናደርግ ለማስተማር ያስተላለፉልን መልዕክት ነው ፡፡ ሌሎች እንኳን በራሳቸው ስሜት ተገፋፍተው ከፍ ቢያደርጉን የማይገባን መሆኑን መግለጽ እንዳለብን እንድንማርበት እንደምሳሌ መሆናቸው ነው
  2. ይቀርብላቸው የነበረው የስግደት ደረጃና ክብደት ደግሞ እጅግ ከፍተኛና የአምልኮ ያህል ሰለነበረ ያንን ለማስተካከልና ለማረም ሲሉ ራሳቸው የሚገኙበትን ደረጃ ኧረ እኔም እንዳንተው ሰው ነኝ…. እንዳንተው ለፈጣሪ የምሰግድ ነኝ ….. በማለትና በማስረዳት የቀረበላቸውን የስግደት መጠንን ተቃውመዋል
  3. ትህትናን ለማስተማር ነው ፤ የድንግል ማርያም ከቅዱስ ገብርኤል ጋር በነበረው ውይይትን ላይ- የአምላክ እናት ለመሆን የታጨች ትልቅ ሹመት እንዳገኙች ሲነገራት ለመልአኩ እነሆኝ የጌታ ባሪያ ፣ የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቷልና ብላለች /ሉቃ 1 ፡ 38 ፣ 48/ ፣ ኢየሱስም ቸር መምህር በተባለ ጊዜ ከአንዱ እግዚአብሔር በስተቀር ቸር የሚባል አለመኖሩን የገለጸው /ማር 1ዐ ፡ 17/ ቸር አምላክነት ሥልጣኑ ስላልሆነ ሳይሆን ፣ ይህንኑ የትህትናን መንገድ ሲያስተምረን ነው ፡፡

  ከዚህ በተረፈ ግን ቅዱሳኑንና መላዕክቱን ፣ እሱ እኛን ከምንም ነገር የፈጠረን አምላክ ሲያከበራቸው ፣ ከጭቃ አሻንጉሊት የማንሻል ግለ ሰዎች ስለምን ምክንያት አናከብራቸውም ፡፡ ዕብ 6 ፡ 1ዐ “ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ ፣ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችሁትን ሥራ ፣ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓመፀኛ አይደለምና” ይላል ፡፡ ለቅዱሳን ማገልገልና ቅዱሳንን ማክበር ከክርስትና የምግባር መገለጫ በጣም አነስተኛው ነው ፡፡ እንደ ክርስቲያንነታችን መጠን ማክበር የሚገባን በመንፈሳዊ ተጋድሎአቸው የታወቁትንና የበቁትን ብቻ ሳይሆን ፣ በአጠገባችን የሚገኘውን ከእኛ ታናሽና ደካማ የሆነውንም ወንድም ሁሉ ብናከብር ራሱን የቻለ የአርአያነትና የቅድስና እምነታችን የግብር መገለጫ ስለሆነ መለማመዱ አይከፋም ፡፡

  የብርሃን አምላክ ዓላማውን እንድንረዳ ለሁላችን የዕውቀት ብረሃኑን ይስጠን
  መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተያየቶችን እጠብቃለሁ
  ሰይፈ ገብርኤል

  ReplyDelete
 37. http://konjotube.com/ethiopian-orthodox-mezmur-amalagenet-part-6-of-1Esti Yihih Temeliket Ato Tesaga Tadele Libona Keseteh Temeles Kalhonem Botahin Felig Ye Tewehedo Timihirt Kedusanen Yakebiral Amalajinetachewu Yikebelal Aleke Tefesteme

  ReplyDelete
  Replies
  1. seyitan eyob enditefalet lemen geta hawariyaten seyitan ende sindae liyabetrachew lemene yilal bibel lemhonu hayilu ena kibiru yetegefefe siytan letifat endi yelemene kekibirachew yetenesa midir yemitaberalachew kidusan melakt sele sew lij dihinet ayileminum yihon?lemehonu seyitan midir lay yalewn egizabehr fit kerbo riport kaderege kiduasn melakit wede semay yizew yemihedut negr yelem malet yichalal?

   Delete
 38. yacob ye yosaf lijochn sibark ke lijinetae jemiro yetebekegn melak enezin lijoch yibark biloal tesasito yihon?

  ReplyDelete
 39. የዛሬ ሃያ ሥድስት ዓመት አካባቢ አንድ የስምንት ዓምት ህፃን ልጅ በወቅቱ አርባዎች ውስጥ በሆነ ብሩክ በሚባል ሰው መጫወቻው ተይዞበት እንዲለቅለት በዙ ጊዜ እቤቱ ተመላልሶ ያጣዋል። ሌላ ሰው እንዳይሰጠው ደግሞ ብሩክ ያስቀመጠው በግራ እጁ ስለ ሆነ ማንም ዕቃውን አግኝቶ ሊሰጠው አልቻለም። ብሩክም እኔ እራሴ መክሬው ዘክሬው እሰጠዋለሁ በማለቱ፣ የልጁ ወሳጆች ደግሞ የልጃቸውን ዕቃ መመለስ በተመለከተ መሪር ለቅሶ በብሩክ ሥውር መልካምነት ጆሮ ዳባ ብለው ገና ትቀምሳታለህ ዓይነት አባሱበት፡; በዚያው ሰሞን የጌታችን ጥምቀት ስለነበረ የልጁ ወላጆች ግቢ ውስጥ ቅርጫ ታርዶ ለመከፋፈል ከታደመው ሰው መሀል የልጆች አባት ትልቁ ብሩክም ነበርና ከህፃኑ ጋር ፊት ለፊት ይተያዩ ጀመር። ታዲያ “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም” ሆነና ልጁ በአጋጠመው ተጠቅሞ ድምፅ ማሰማት ጀመረ፤ እንዲህ ሲል፥ አንቱ የሚለውን አንተ ብሎ “የብሩክ ስም ይቀየር” አለ። ሁሉም ጸጥ እንዳሉ ሥጋውን እኩል በማከፋፈል ያሉት በሬ አራጅ ሰው ብቻ ቢላቸውን እየሳሉ “ማን ልትለው ፈለክ ደግሞ” ብለው በመቀጠል “ልጅ ነገሮች በግልጽ ይታዩታል” አሉና ለልጁ “በል አዲሱን የብሩክ ስም ንገረን ዳቦም አያስፈልግ ጥሩ ጊዜ ነው።” ብለው ደስ የሚል እና ቅርጫ አራጅ የሚለውን ደግሞ አዲስ ስም እንዲሰይምላቸው የፈለጉ ይመስል ድምፅ እንዳይረብሸው ቢላ መሳሉን ቆም አደረጉለት፡; ህፃኑም “ለሰው ልጅ ስም መውጣት ያለበት አድጎ ተግባሩ በሚሠራው ሥራ እየታየ መሆን ነበረበት።” ብሎ በመቀጠል “ለምሳሌ እኔ እንዳልኩት ቢሆን ኖሮ የጋሼ ብሩክ ስም ጋሼ እርኩስ ይሆን ነበር።” ሲል ግማሹን አስቆ ሌላውን ደግሞ አስደንግጦ ከሁዋላው ነብር እንደተከተለው ፍየል ተፈተለከ። ስለዚህም የማህበረ ቅዱሳን ሥራ እየዋለ ሲገለጽ ትክክለኛ ስሙን ማግኘት ይገባዋል። ማህበረ ቅዱሳን ማለት ፍቅርን የማይወድ የፍቅር ቂመኛ፣ ጳጳስን ከጳጳስ፣ ቤተክርስቲያንን ከቤተክርስቲያን፣ ቄስን ከቄስ፣ ምዕምናን ከምዕምናን፣ ወጣቱን ከወጣት፣ቤተሰብን ከዘመድ፣ ሚስትን ከባል፣ ልጆችን ከወላጅ እና ሕዝብን ከሀገር እያጋጨ የሚሳለቅ የበግ ለምድ ለባሽ የተዋጣለት እርኩስ የደህንነት ድርጅት ነው። ብጹዐን ጳጳሳት በፍጹም እንዲታረቁ እንደማይፈልግ ከአባሎቹ ፉከራ ታውቋል። የእባቡ (የማህበረ ቅዱሳን ድርጅት) ጂራቱ ተቆርጧል፤ ጭንቅላቱ ነው አራት ኪሎ እና ስድስት ኪሎ የመሸገው። ለእርሱም የሚመለከተው ክፍል ጸሎቱን በሱባዔ ጀምሮለታል እናም በቅርቡ በራሱ አንደበት ማንነቱን ይፋ ሲያደርግ ተብትቦ የያዛቸውን በጎች ይለቃቸዋል። በጎቹም ሞቶ እንደተነሳ ያህል ለዓምላካቸው ይቅርታን በንሰሀ ይጠይቃሉ፤ እባቡንም ጭንቅላቱን ይቀጠቅጣሉ፤ ያን ጊዜ አባቶች በፍቅር ተሸንፈው ይታረቃሉ፤ በጎቹም (የአደራ ልጆቻቸውም) በለመለመው መስክ ምግቡና መጠጡን እንደልባቸው ያገኛሉ፡; ጊዜውም የዐብይ ጾም ወቅት ሰለሆነ እኛም በጸሎት ተግተን እናግዛለን፡; ወሥብኃት ለእግዚአብሔር።

  ReplyDelete
 40. ለማህበረ ቅዱሳን አሁንም እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጣቸው!

  ReplyDelete
 41. ወንድም እግዚአብሄር በፍቅሩ ያስብህ አልፈርድብህም ሴጣን የተመረጡትን እንጂ ሌላማ ማንን ያሳድዳል ከእግዚአብሄር ለራቁትማ ሰላም ሰጠቷቸዋል ወደ እነሱም አይቀርብ ማህበረ ቅዱሳኖች የክርስቶስ ጽጌረዳዎች ናቸው እሾህ የበዛባቸው

  ReplyDelete
 42. I have a comment on your opinion about Our Lord and Savior Jeses Christ. First start to pray according to the teaching of the bible which says, when you prey "O our Lord in the heaven..." instead of talking meaningless words. Then read bible from beginning to the end. Why you select few verses only and try to give meanings to your earthly belief. You should prey God to reveal you what trinity is and why Jesus Christ came and when He finished his mediation humanbeings with Him, and His Father. Dont't be foolish He will come to judge, not to mediate. Read the following few of verses among many to know that Jesus christ is GOd. How one Being the Judge appeal? To whom will he appeal? Read the bible. Always denouce Satan in your prayers, and worship God by kneeling down to him and search the trus. Hop He will lead to the right way.Other wise Satan is leading you the wrong way becuse you never include your denial in your prayers.Why don't you read the following verses who explicity speaks about the Godship of Our Lord, Savior and God Jesus Christ.
  ዘፍ 1፤ 1-በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
  ዮሐ 1፤ 1-3-በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ።ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።
  ዮሐ 1፤ 14ቃልም ሥጋ ሆነ ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።
  1ኛ ዮሐ 5, 20-የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ( Jesus Christ is God )
  1ኛ ጢሞ 6,15-16-ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን ጠብቅ ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። ( He is the Lord of Lords, The King of kings)
  ይሁ 1, 25-ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። ( It Says "He is the Only God and Savior"
  Do you belive the Father (Ab) is crucified to be Our Savior, No.
  Even Christianity Baptism is in the name The Father, Son and Holy Sprit. (One God). They are same in GodShip,and three in person. All of them Jesus,they are one in will, creation, and Godship. No one among Them is Superior, and no one is inferior. Jesus Chrust came and teach us how to live spritually by his practical acts doing things like humanbeing except doing sins. He a humanbeing and a God (ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ)
  የማቴ 28፤19-20-እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
  May God Open your spritual Eye to understand WHO GOD IS.Amen.

  ReplyDelete
 43. Please start know before writing and speaking religious things to save your Soul as the bible says
  የማቴዎስ ወንጌል 12
  31 ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።

  ReplyDelete
 44. ተሃድሶንም ማህበረ ቅዱሳንም እግዚአብሔር ይገስጻቸው:: አሜን::

  ReplyDelete