Friday, December 30, 2011

ተጠንቀቁ - ክፍል ሁለት - - - Read PDF

 
ፈሪሳውያን በጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ሌሎችን መተቸት ይወዳሉ

ፈሪሳውያንም አይተው እነሆ፥ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ማድረግ ያልተፈቀደውን ያደርጋሉ አሉት። (ማቴ 12:2)
ፈሪሳውያን በአይሁድ ሕግ ከሰው መሬት ላይ ተክል ነቅሎ መብላት ክልክል እንደሆነ ያውቁ ነበር። እዚህ ላይ ጌታን የሚጠይቁት ግን ደቀ መዛሙርቱ ለምን እንደዚህ አይነቱን ነገር በሰንበት ያደርጋሉ ብለው ነው። ፈሪሳውያን በጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ሌሎችን መተቸት ይወዳሉ። ማቴዎስ 15:2 ላይ ጌታን "ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና" ብለው ጠየቁት። ሁልጊዜም ሌሎች አማኞችን ተከታትለው ትንሽም እንኳ ቢሆን ጥፋትን ለማግኘት ይሞክራሉ። ሐሰተኛ ወንድሞቻችንም ዛሬ እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው።

   ማንም ሰው ታላቅ መሪ ሆኖ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ በሚያገለግልበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ፈሪሳውያንን ሊያፈራ ይችላል። ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ሰዎች የመሪያቸውን ባህርይ ነው የሚወርሱት። ይሄንንም በዮሐንስ ራዕይ 2 እና 3 ላይ እናያለን። መሪ የሆነ ሰው ግን ከፈሪሳዊነት የራቀ ከሆነ ተከታዩም ከዚህ ባህሪ የራቀ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ክርስቲያኖች እንደዚህ ካሉ የቤተክርስቲያን መሪዎች መራቅ አለባቸው። ጌታን እራሱን መከተል ነው እንጂ እንደነዚህ ያሉትን የሀይማኖት መሪዎች መከተል የለብንም።

ፈሪሳውያን ኑሮአቸው ስርአትና ደንብ ላይ የተመሰረተ ነው

 እነሆም፥ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤ ይከሱትም ዘንድ  በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን? ብለው ጠየቁት። (ማቴ 12:10) ፈሪሳውያን ኑሮአቸው በስርአትና ደንብ ላይ የተመሰረተ ነው እንጂ በኢየሱስ ላይ የተመሰረተ አይደለም። በሕጋቸውም መሰረት የታመመ ሰው ፈውስን በሰንበት ማግኘት የለበትም ብለው ነበር የሚያስቡት። በአሁኑም ጊዜ ብዙ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አጉል የሆኑ ስርዓቶችን በማውጣት አባሎች ላይ ችግር ይፈጥራሉ። ፈሪሳውያን ጌታን እንደዚያ ብለው የጠየቁት ሊከሱት ስለፈለጉ ብቻ ነበር። በአሁኑም ጊዜ ቢሆን አንዳንድ መሪዎች ሰው ሰራሽ ህጎችን ተላልፈዋል ብለው ሰዎችን ለመክሰስ በጥብቅ ይከታተላሉ።

ፈሪሳውያን በቅናትና በጥላቻ የተነሳሱ ናቸው

  ፈሪሳውያን ግን ወጥተው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ተማከሩበት።(ማቴ 12:14) ቀናተኛ የሚቀናበትን ሰው መግደል ደርጃ አያደርስ ይሆናል ነገር ግን ቅናት እና ጥላቻ ሰውን ለመግደል፣ የመጀመሪያ ደረጃ እንደሆኑ መዘንጋት የለበትም ቃኤል የሰራው ስራ የተሳካለት እንደዚህ ነበር፤ ቅናት...ጥላቻ...መግደል፣ ፈሪሳውያን በኢየሱስ ይቀኑ ነበር ምክንያቱም እነሱ ማድርግ የማይችሉትን ነገር እሱ ስላደረገ እና ከእነሱ የበለጠ በጣም ታዋቂ ስለነበር። ጲላጦስ እንኳ ስለ ጌታ ብዙም የማያውቀው ፈሪሳውያን በቅናት ሊሰቅሉት እንደፈለጉ አውቋል። በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። (ማቴ 27:18) ሰው በሰው ሲቀና በአነጋገሩ እና በተግባሩ በግልጽ ይታያል።
አንድ ሰው ከሌላው በስብከት፣ በሀብት በመንፈሳዊ ስጦታዎች ከሌላው ሊበልጥ ይችላል። በእንደዚህ ዓይነት ሰው የሚቀና በዛ ሰው ላይ ትንንሽ ስሕተቶችን ማግኘት በቀላሉ ይችላል ከዛም ለመተቸት ይመቸዋል። የዛን
ሰው አወዳደቅ ማየትም በጣም ይፈልጋል። የፈሪሳውያን ሀይማኖት የቃኤል ሀይማኖት ነው። የሰው ዘር ታሪክ በሁለት ዘርፍ ይከፈላል፣ አንድ መንፈሳዊ (አቤል) እና ሌላው ሀይማኖት (ቃኤል) የቃኤል መጀመሪያ ሀጢአት ቅናት በአቤል ላይ ነበር። እነዚህ ሁለት ዘርፎች በመጨረሻ በእየሩሳሌም ውስጥ (እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን) እና ሀሰተኛዋ ቤተ ክርስቲያን (ባቢሎን) ላይ አበቁ። የሀይማኖትን እና የቅናትን በቃኤል የተሞላውን ዘርፍ ከተከተልን የባቢሎን ወገን እንሆናለን።

ፈሪሳውያን ተጠራጣሪ እና የሰውን ክፉ የሚጠባብቁ ናቸው

  ፈሪሳውያን ግን ሰምተው። ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ። (ማቴ 12:24) ጌታ ሰይጣንን ሲያስለቅቅ  "ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና። እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን?አሉ።" (ማቴ 12:23) ነገር ግን ፈሪሳውያን እነሱ ማድረግ ያልቻሉትን ጌታ አድርጎ ስላዩት ተረበሹ። የጌታንም ክፉ ተመኙ። ሰው ጥሩ ነገር ሰርቶ ሌላውን የሚጠቅም እንኳ ቢሆን ፈሪሳውያን ለዛ ጥሩ ስራ መጥፎ ነገር ያወጡለታል። ልጆቻቸው ግን ከሆኑ ያደረጉት ይኩራሩበታል። ፈሪሳውያን ሰውን በጣም ተጠራጣሪ ስለሆኑ ማንም ሰው ራሱን ዝቅ አድርጎ ጥሩ ስራ ይሰራል ብለው አያምኑም ምክንያቱም እነሱ ራሳቸውን ወዳድ ስለሆኑ። ፈሪሳውያን በንግግራቸው ግድየለሾች ናቸው ፈሪሳውያን ግን ሰምተው ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።(ማቴ 12:24) ፈሪሳውያን በንግግራቸው ደፋሮች ለሰው የማይጠነቀቁ እና በሰው ላይ የሚፈርዱ ናቸው። የእግዚአብሔርን ልጅ "የአጋንንት አለቃ" ብሎ መጥራት ምን ማለት እንደሆን አስቡት። ጌታ ምን ብሎ መለሰ ለዚህ አባባላቸው? "በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም" (ማቴ 12:32) በሰው ላይ ሀጢያት ስንሰራ ሁለት አይነት ሀጢአቶችን ነው የምንፈጽመው፤ አንደኛው በሰው ላይ፤ ሁለተኛው በእግዚአብሔር ላይ ነው። ሰውም እግዚአብሔርም ይቅር ሊሉን ይገባል። ነገር ግን እግዚአብሔር ይቅር ከማለቱ በፊት ንሰሀ መገባት አለበት። ስለዚህ ሰው እንኳ ይቅር ቢለን ንስሀ እስክንገባ ድረስ እና እግዚአብሔርን ይቅርታ እስክንጠይቅ ድረስ በእሱ ፊት ለፍርድ እንቀርባለን። ኢየሱስ ከዚህ ንግግር አስጠንቅቆናል። "ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ" (ማቴ 12:37)

ፈሪሳውያን ሀይማኖትን ሰበብ በማድረግ የቤተሰብ ሀላፊነታቸውን ችላ ይላሉ

"... እናንተስ ስለ ወጋችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ስለ ምን ትተላለፋላችሁ? እግዚአብሔር አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ ... ከእኔ የምትጠቀምበት መባ ነው የሚል ሁሉ፥ አባቱን ወይም እናቱን አያከብርም ትላላችሁ፤ ስለ ወጋችሁም የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ። ....(ማቴ 15:1-9)  ፈሪሳውያን የእግዚአብሔርን ቃል በመሻር ገንዘቡን ለቤተ መቅደስ የሰጠ ሰው የተቸገሩ ቤተሰቦቹን መርዳት የለበትም ብለው ያስተምራሉ። የዛሬው ዘመን ፈሪሳዊነት ደግሞ ለምሳሌ ባል ተነስቶ ሚስቱን "ወደ ቤተ ክርስቲያን ለስብሰባ ልሄድ ስለሆነ የቤቱን ስራ ልረዳሽ አልችልም" የሚል መልእክት ሊሆን ይቸላል። ወይም ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ይዞ  ሚስቱ ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት ለመውሰድ ስትጣደፍ እያየ ዝም ይላታል። እግዚአብሔር የሚነግረው ግን መጽሐፍ ቅዱሱን ዘግቶ ሚስቱን እንዲረዳ ነው። ነገር ግን የፈሪሳዊ ጆሮው የእግዚአብሔርን ድምጽ ሊሰማው አይችልም። ከመንፈሳዊነት አንዱ ስራ በቤት ውስጥ ያለውን ስራ በሀላፊነት መካፈል ነው። ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው። (1 ጢሞ 5:8)

 ለፈሪሳውያን  የሰው ስርኣት የመንፈሳዊነት መለኪያቸው ነው።  

"እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ የምንጦመው፥ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት።"   (ማቲ 9:14) ፈሪሳውያን ሰዎች እንዲጾሙ እና እንዲጸልዩ ያስገድዳሉበሰው ሰራሽ ስርአት መንፈሳዊነት ይገኛል ብለው ያሳስባሉ እነሱም በዚህ ስራቸው ይመካሉ   ኢየሱስ ከፈሪሳውያን የበለጠ ጾሟል ነገር ግን ቅዱስ ለመሆን ሳይሆን የጾመው እሱ ራሱ ቅዱስ ስለሆነ ነውኢየሱስ ግን እንደፈሪሳውያን በመጾሙ አልተኩራራበትም ደግሞም ሌሎችን እንዲጾሙ አላስገደደም ወይም ተጽእኖን አላደረገም። ኢየሱስ ዛሬም ይሁን ወይም በምድር እያለ ይህን አይነት ነገር አላደረገም። ጾም በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ የሚኖረው በፈቃደኝነት ሲሆን ነው አለበለዚያ የሞተ ሥራ ነው የሚሆነው።

   በተለያየ ሀይማኖት ስር ያሉ ሰዎች ጾም ላይ ብዙ ሕጎች አሏቸው። አንዳንዶች እንደውም ቅዱስ ለመሆን በጾም ጊዜ ከትዳር ጓደኛቸው ጋር እንኳ አብረው መተኛትን ያቆማሉ። ነገር ግን ይህ ክርስቲያኖች ቅዱስ የሚሆኑበት
መንገድ አይደለም። "ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው" (ያዕ 3:2) ስለዚህ ሀሳባችንን እና አይኖቻችንን መቆጣጠር አለብን። አንዳንዶች በዚህ ጉዳይ ሲያንጎራጉሩ እንሰማለን፤ ዛሬ ልደታ ነገ ባታ ናት እያሉ ሚስቶቻቸውን የሚጨቁኑ ወንዶች ብዙ ሲሆኑ ሴቶችም የሚካኤል በአል የገብሬል በዓል በማለት ባሎቻቸውን የሚከለክሉ እና የሚፈታተኑ መሆናቸውን ብዙዎች ይናገራሉ። የሰው ሥርዓት እና ትምህርት እግዚአብሔርን በንጹሕ ልብ እንዳናመልክ የሚያደርግ አደገኛ ነገር ነው።  በእርግጥ በክርስቲያን ህይወት ላይ በአበላል በግብረ ሥጋ ግንኙነት የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ስነሥነርዓት ሊኖር ይገባል። ማለት እንደ አሕዛብ በየሜዳውና በሕዝብ እይታ ውስጥ ባሉ ሥፍራዎች፣ እንዲሁም በኃይልና በግድ መሆን የለበትም፣ ጋብቻ ክቡር ነው ምኝታውም ቅዱስ ነውና በተቀደሰው የባልና የሚስት ስፍራ በፍቅር መሆን አለበት።  ነገር ግን ይሄን በማድረጋችን ትልቅ ክብር እንዳለን አድርገን ለሌሎች ሰዎች መንገር የለብንም።

  ፈሪሳውያን በቀላሉ ይናደዳሉ

በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ቀርበው። ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሰምተው እንደ ተሰናከሉ አወቅህን? አሉት። እርሱ ግን መልሶ። የሰማዩ አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል። ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች
ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ አለ። (ማቴ 15:12-14)
ጌታ ፈሪሳውያንን በሚያስተምሩት ትምህርት ባረማቸው ጊዜ ደስተኞች አልነበሩም እንደውም በጣም ቅር ተሰኙ። ከክርስቲያን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቶች አንዱ ቅያሜን ማስወገድ ነው። በስህተታችን ሰው ሲያርመን የምንቀየም ከሆነ እና ቂም የምንይዝ ከሆነ ከሀጢያታችን ይቅር የመባል ተስፋ አይኖረንም።

  ተጠንቀቁ!

                 ከፍቅርተ ኢየሱስ

17 comments:

 1. kale hiwot yasemalen abo! That is 100% true.

  ReplyDelete
 2. Esey - des yelal. We all need to learn from this.

  ReplyDelete
 3. ሰላም ጤና ይስጥልኝ ፍቅርተ ኢየሱስ

  በቅድሚያ ለጥያቄየ ይቅርታ ያድርጉልኝና ሀይማኖትዎ ምንድን ነው?
  ስለመልሱ በቅድሚያ አመሰግናለሁ::
  ከወለተ ማርያም
  December 29, 2011 9:58 PM

  ReplyDelete
 4. ስርአትና ደንብ የማይወድ ማን ነው?

  ReplyDelete
 5. ለወለተ ማርያም ከፍቅርተ ኢየሱስ
  እምነቴ ከማኅበር በላይ በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፩አምላክ ማመንና ለእርሱ ብቻ መገዛት!! እርስዎ(ወለተማርያም)ለሥላሴ ከዚያም ለማኅበሩ ይገዛሉ፣ አይደል?

  ReplyDelete
 6. Haymanote MK NEWO

  ReplyDelete
 7. All Ethiopians EOTC followers, do every thing to eradicate from the earth surface those fundemetalist group of mk that hater of Jesus and our church. Jesus is lord amen.

  ReplyDelete
 8. Haymanotiwa Yenaziretu Geta Iyesus Kiristos new. Amen.

  ReplyDelete
 9. Haymanotiwa ferisawiyan bekinat sekilew yegedelut Yenaziretu Geta Iyesus Kiristos new.Amen. Abba negn.

  ReplyDelete
 10. The ethiopian orthodox church needs this kind of women , the woman know bible because most of our sunday school females know only mezemur and netel matafat fekert yesus is very goog example good job keep it up !

  ReplyDelete
 11. Thank you Fikert, God bless you! for the Anonymous: you asked the writer (fikert's) religion, Why you ask this kind of non-sense question? my kids can easily figure "what religion fikert follow." please open your heart! Answer: FIKERT'S religion is CHRISTIAN.

  TIGIST

  ReplyDelete
 12. Fikrte Eyesue Enamesginalen

  ReplyDelete
 13. 3rd anonymous must be a member of ፈሪሳውያን. What is the importance of the writer's faith to you? You should have said something based on the article.I think the article is good. There are many ፈሪሳውያን in the church today than they were long long time ago. Let God guide them to the directions of wisdom.

  ReplyDelete
 14. Fikertiysus kale hiwot yasemaln. LELOCH SETOCH ENDANICHI BIMARU MELKAM NEOW MK ATRAMASH SETOCH WONDE FELEGA ENGI GETA FELEGA AYHEDUM GETA YASEBACHW. YEMIYADERGUT AYAWOKUMNA.

  ReplyDelete
 15. surprisingly you are the writer at the same time suggestion giver; had it not been,all the information sent to you would have been put without modification.Hence, this blog is reserved to you and your groups only which is always targeted to insult and attack the counterparts which is very foolishness.

  ReplyDelete
 16. Kelay yetafekew, ante sint mk neta sit setoch ateramesehal? Endshabiya materamednew mk set ferisawe netche lebash zim bel. Kelay yalekew kemitetif better to be ur death. With out pre condition join geta then be in the heaven. That smart choice for real person matermas yibekahe.

  ReplyDelete
 17. Ewunatin Mekeble alebin, ewunat Geetaa Iyesus naew

  ReplyDelete