Sunday, December 30, 2012

ፍካሬ መጻሕፍት

(በጮራ ድረ ገጽ ላይ የቀረበ፦ http://www.chorra.net/)

                             “ወትቀውም ንግሥት በየማንከ
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአፅምኢ እዝነኪ”
“በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ” (መዝ. 44/45፥9-10)

ይህን የመዝሙረ ዳዊት ጥቅስ በሚያነብብ በአብዛኛው ሰው አእምሮ ውስጥ በቶሎ የምትከሠተው ድንግል ማርያም ናት። ይህ የሆነው ጥቅሱ ስለ እርሷ የተነገረ ስለ ሆነ ግን አይደለም። ስለ እርሷ የተነገረ ነው ተብሎ ስለ ተወሰደ፥ በተደጋጋሚ ከእርሷ ጋር ተያይዞ ስለ ተነገረ፥ በየወሩ በ21 ለበዓለ ማርያም የሚዜም ምስባክ ስለ ሆነ ነው ስለ እርሷ የተነገረ ያህል እየተሰማን የመጣው። ቅድስት ድንግል ማርያምን ንግሥተ ሰማይ ወምድር ብለው የሚያምኑ ክፍሎች፥ ሐሳባቸውን በዚህ ጥቅስ ለማስደገፍ ይሞክራሉ። እርሷን በንጉሥ እግዚአብሔር ቀኝ እንደ ተቀመጠች ንግሥትም ይቈጥሯታል።

ቃሉ ስለ ማን እንደ ተነገረ ከመጽሐፉ ተነሥተን እንመልክት። ጥቅሱ ለሚገኝበት ለዚህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የዐማርኛው የ1953ቱ ዕትም መጽሐፍ ቅዱስ “ለመዘምራን አለቃ፤ በመለከቶች፤ የቆሬ ልጆች ትምህርት፤ የፍቅር መዝሙር” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለራሷ ባሳተመችው የ2 ሺሁ ዕትም መጽሐፍ ቅዱስም “ለመዘምራን አለቃ በመለከቶች የቆሬ ልጆች ትምህርት የፍቅር መዝሙር” በማለት ይህንኑ ርእስ ነው ያስቀመጠው።

Saturday, December 29, 2012

በውጭ የሚገኙ ገለልተኛ እንዲሁም በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት በውጭው ሲኖዶስ ስር ለመጠቃለል ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

የእርቁ ተስፋ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ እየተሟጠጠ ነው። የሰላም እና አንድነት ጉባኤ አባላት የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴና ዲያቆን አንዱአለም የእርቁን ጉዳይ ለመወያየትና ለመጭው የጥር ስብሰባ የማግባባት ስራ ለመስራት በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ ሄደው እንደነበር ይታወቃል። ሆኖም ግን እነዚህ ግለሰቦች የሄዱበትን ጉዳይ በአግባቡ ሊፈጽሙ አልቻሉም። ወደ ቤተ ክህነት መግባት አልቻሉም። ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ማን እንደቆረጠው ባልታወቀ ቲኬት በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገው ዛሬ አሜሪካ ገብተዋል። በትዕዛዝ ከአገር እንዲወጡ እንደተደረጉም በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል። ዲያቆን አንዱአለምም እዚያው አዲስ አበባ ባልታወቁ ሰዎች ተወስዶ ወዴት እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም። ይህ ሁኔታ መንግስት ጣልቃ አልገባም ብሎ የሰጠውን መግለጫ ከፍተኛ ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል ወይንም በተግባር ሊታይ አልቻለም ማለት ነው። ይህ ደግሞ እጅግ አሳፋሪ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በውጭው ዓለም የሚገኙ በርካታ የገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት በውጭው ሲኖዶስ ለመጠቃለል እየተነጋገሩ ነው። በሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር በሚመሩ አብያተ ክርስቲያናት ያሉ  በርካታ ምዕመናንን ጨምሮ በስደት ወዳለው ሲኖዶስ ለመጠቃለል ጥያቄ እያነሱ ነው። በውጭው ሲኖዶስ የተገኙ ምንጮች እንደሚጠቁሙት  በውጭ በገልልተኛነት ያሉ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ወደውጭው ሲኖዶስ ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡና ውይይት እያካሄዱ ነው። በነዚሁ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙ ካህናትና የቦርድ (ሰበካ ጉባኤ) አባላት የአባሎቻቸውን ድምጽ በመስማት በጉዳዩ ውይይት እያደረጉ ነው። በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር የነበሩ የተወሰኑ አብያተ ክርስቲያናትም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭው ሲኖዶስ የመቀላቀል ጥያቄ እያንሸራሸሩ ነው። ይህ የሚያመለክተው የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው ምዕመን ትዕግስቱ እያለቀበት መሆኑን ነው።

ተጠያቂው ማን ነው?

በመንግስትም ሆነ በቤተ ክርስቲያን መልካም አስተዳደር እንዲኖር ከተፈለገ ግልጽ የሆነ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባዋል። ተጠያቂነት ካለ በነዚህ ተቋማት ስር የሚተዳደረው ህዝብ ወይንም ምዕመን ትክክለኛ እርምጃ/ግንዛቤ ሊወስድ ይችላል።  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመላው ዓለም እያነጋገረ ያለው የወቅቱ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ነገሮችን በተዓምሩ ካላስተካከለ አሁን እያየናቸው ያሉ ብዙ ምልክቶች የሚጠቁሙት የአብዛኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ምኞት የነበረው እርቅ እና አንድነት ህልም ብቻ ሆኖ የቀረ ይመስላል። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ 6ኛ ፓትርያርክ የመሾሙን እንቅስቃሴ በፍጥነት እያራመደ ነው። ብዙ የደከመው የሰላም እና አንድነት ኮሚቴ በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ጀርባ እየተሰጠው ይገኛል። ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረ ገጽ እንደዘገበው በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የተላኩ ሁለት የኮሚቴው አባላት ቤተ ክህነት እንዳይገቡ መከልከል ብቻ ሳይሆን እንደኛው በመንግስት ታፍሰው ወደ መጡበት አሜሪካ በግድ እንዲመለሱ ተደርገዋል። ይህ ሁሉ የሚጠቁመው በሰላም እና አንድነት ላይ በር እየተዘጋበት መሆኑን ነው።

በርግጥ እግዚአብሔር በአውሎና በወጀብ መካከል መንገድ አለው። አምላካችን እግዚአብሔር ነውና ተስፋ አንቆርጥም፤ አሁንም እርቅና ሰላም ሊመጣ ይችላል። ተግተን ከጸለይን እና እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ በአንድነት ለዘመናት የኖረችውን ይህችን ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ይታደጋታል። አሁን የተጀመረው እና እየተዳከመ ያለው የእርቅ እና አንድነት ጉዞ ባይሳካ ግን ተጠያቂው ማን ነው? የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ነው?  በስደት ያለው ሲኖዶስ ነው? መንግስት ነው?  ማን ነው?  በርግጥ ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነውና ህዝቡ እነዚህን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ ብዙም ጊዜ የሚፈጅ አይሆንም። በአሁኑ ሰዓት ግን ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም።  መንግስት በመገናኛ ብዙሃን እኔ አያገባኝም ብሏል። የአዲስ አበባው ሲኖዶስም መንግስት ተጽዕኖ እያሳደረብኝ ነው አላለም።  መንግስት አዲስ አበባ ባሉ አባቶች ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው ብለው የዘገቡም የመገናኛ ብዙሃን አሉ።  ምን አይነት ተጽዕኖ? ማስፈራሪያ?  ምን አይነት ማስፈራሪያ?  የሞት ቅጣት? እስራት?   የመንግስትም ተጽዕኖ ካለበት ከአባቶች መካከል እውነቱን ለመናገር አንድ ደፋር መንፈሳዊ ይገኝ ይሆን? 

እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች የመረጃ ኃይልና ጊዜ ይፈታቸዋል። ሆኖም ግን እስካሁን ያስተዋልናቸው ነገሮች ተጠያቂነቱን አዲስ አበባ ባሉ አቦቶች ላይ እንድናስቀምጥ ያስገድዱናል። በእርቁ ዙሪያ አባቶቹ ተከፋፍለዋል። ግን ታዲያ ለምን እርቅ የማይፈልጉት ጠንክረው ተገኙ? ብዙዎች ስለሆኑ? መንግስት ከጎናቸው ስላለ?  ሁሉም የመገናኛ ብዙሃን ተጠያቂነትን ለህዝቡ ግልጽ ለማድረግ ሊሰሩ ይገባል።

ከአባሰላማ አንባቢ

Thursday, December 27, 2012

አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእሳት ያወጣው ማነው? ገብርኤል ወይስ ሚካኤል? ወይስ እግዚአብሔር?

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” መዝ. 33፡7፡፡ ይህ ጥቅስ የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ከእግዚአብሔር ተልኮ በዙሪያቸው ሆኖ ከመከራ እንደሚያድናቸው ያስተምራል፡፡ የመላእክት አንዱ ተግባር መዳንን ይወርሱ ዘንድ ያላቸውን ሰዎች መጠበቅ መሆኑ ተጽፏል፡፡ “ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?” ዕብ. 1፡14፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ስለሚል እግዚአብሔር ገብርኤልን ልኮ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ከእሳቱ ሊያድን እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ነገር ግን በሶስቱ ወጣቶች ታሪክ ውስጥ እንደምናነበው ወጣቶቹን ለጣኦት አንሰግድም በማለታቸው ከተጣሉበት እሳት ውስጥ ያዳናቸው ገብርኤል መሆኑ አልተጻፈም። ያዳናቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ ገብርኤልንም ልኮ እንኳን ቢሆን አዳነ የሚባለው እግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ በግድ ገብርኤል ነው ያዳናችሁ ብንላቸውም አናንያ አዛርያ ሚሳኤል ግን “የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።” ነው የሚለው፡፡ ዳን. 3፡18-19፡፡ ይህም የሚያስተምረን መልአኩንም ልኮ ሆነ ሳይልክ የሚያድን እግዚአብሔር መሆኑን ነው፡፡

አቡነ መርቆሬዎስን የመመለስ አለመመለሱ ምርጫ በአገር ቤቱ ሲኖዶስ እጅ ላይ ወድቋል

ረቡዕ ታኅሣሥ 17/2005 ለንባቢ የበቃው “ሰንደቅ” የተባለው የግል ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ “መንግስት አቡነ መርቆሬዎስ ቢመለሱ እንደማይቃወም አስታወቀ” በሚል ርእስ ዜና አውጥቷል፡፡ አቡነ መርቆሬዎስን የመመለስ አለመመለሱ ምርጫ በአገር ቤቱ ሲኖዶስ እጅ ላይ ወድቋል፡፡
ከአቶ ስብሀት ነጋ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስም አቶ ስብሀት የእምነቱ አመራር ቢሆን የአማኙን መንፈሳዊ ህይወት ሊያረካ አልቻለም፡፡ … የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አመራር ለሃይማኖቱም ሆነ ለአጠቃላይ ስርአቱ አደጋ ወደመሆን ተቃርቧል” ማለታቸውንና “የአሜሪካው ሲኖዶስ የእስልምና አክራሪ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ እንደሚደግፍ ይወራል፡፡” የሚል አስያየት መሰንዘራቸውን አስነብቧል፡፡ ሁለቱን ጉዳዮች ለአንባብያን ቀጥሎ አቅርበናል፡፡

Wednesday, December 26, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴን ከሓላፊነት አነሣ

ሐራ ተዋህዶ እንደዘገበው። ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ላይ በመጫን ከሐራ ብሎግ ማንበብ ይችላሉ።

(በሲኖዶሶች እርቀ ሰላም ዙሪያ የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች መከፋፈል ይታይባቸዋል)

እርቅ ከእግዚአብሔር ጋር

·        ከአምስተኛ ወደ አራተኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚለው አቋም ክርስቲያናዊ አቋም አይደለም። ስለ ክርስቶስ መመለስ ይቻላል።
 ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን ካላደረገ ከወንድሙ ጋር ሰላም አይኖረውም። ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፤ እግዚአብሔርን ትተን ሰላምን ስንፈልግ ከንቱ ድካም እንጂ ሌላ ትርፍ አናገኝም። ነቢዩ ኢሳይያስ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል። ክፉዎች እግዚአብሔርን አይፈሩም ሰላምን በጉልበታቸው፤ ወይም በገንዘባቸው ለማምጣት ይሞክራሉ። ሌሎች ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ ስለሰላም ይፈራረማሉ። ነገር ግን ክፉዎች ስለሆኑ እራሳቸው የመሠረቱትን ሰላም እራሳቸው ያፈርሱታል። ለዚህ ነው ነቢዩ ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ያለው።57፥21።
    ሰው ከአምላኩ ከተጣላ በኋላ እግዚአብሔር የሰውን ልብ ጎብኝቶ ነበር። የሰው ልብ እግዚአብሔር እንዳየው ይህን ይመስላል «እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደበዛ የልቡ ሐሳብ ምኞቱም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ» ይላል ዘፍ 6፥5። ነቢዩ ኤርምያስም የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነው ማንስ ያውቀዋል? ብሏል። ጠቢቡ ሰሎሞን «የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ» ይላል መክ 9፥5። ይህ የሰው የልብ ክፋት ሊወገድ የሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር ሲታረቅ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ክፋትን ከሰው ያስወግድ ዘንድ አንድያ ልጁን ልኳል። ክፋት ለሚባለው የልብ በሽታ መድኃኒቱ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቃሉ «ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ እያንዳዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ሰደደ» ይላል የሐዋ 3፥26።

Monday, December 24, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ግራ ማጋባትና የእርቁ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

አቡነ ህዝቅኤል  «በውጪ የሚገኙ አባቶቻችን እዚህ መጥተው የመምረጥም ሆነ የመመረጥ እድል ይኖራቸዋል» አሉ። ምን ማለት ነው?
የሰሞኑ የማኅበረ ቅዱሳን «እርቁ ይቅደም» የሚለው ጩኸት ብዙዎችን ግራ እያጋባ ነው፡፡  እስካሁን የእርቁን ሂደት ከልቡ ሳይደግፍና ተገቢውን ጥረት ሳያደርግ ቆይቶአል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ ቀደምም እንዳልነው በውጭ አገር በሚገኘው ሲኖዶስ ውስጥ ያሉትን ብዙዎቹን አባቶችና መምህራን ተሐድሶ ናቸው ብሎ ስለፈረጃቸው ነው፡፡ እንደታሰበው እርቁ ቢሳካና በውጭ ያሉ አባቶች በአገር ቤት ካሉ አባቶች ጋር በአንድ ሲኖዶስ ስር ከቆሙ ጳጳሳቱ ሀገረ ስብከት ይኖራቸዋል፡፡ መምህራኑም በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ስፍራ ይሰጣቸዋል ብለን እናስባለን፡፡ ይህ ግን ለማህበረ ቅዱሳን ትልቅ ራስ ምታት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ተሐድሶ ብሎ የፈረጃቸውና በየልሳኖቹ ስማቸውን ያጠፋቸው አባቶችና መምህራን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ስፍራ ካገኙና አገልግሎታቸውን ከቀጠሉ ከማህበሩ ጋር ግጭት መፈጠሩ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ምናልባትም እንደ ግንቦቱ ያለ ውግዘት እንዲተላለፍ ሌላ የክስ ፋይል ከፍቶ ውግዘት የሚጠይቅባቸው አባቶችና መምህራን ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ ከዚህ ሁኔታ አንጻር ማቅ እርቁን አይደግፍም፡፡ ስለእርቁ ከልቡ ያልተንቀሳቀሰው ለዚህ ነው፡፡

Sunday, December 23, 2012

የትንቢት መፈጸሚያ ወይስ መጠቀሚያ?

በቅርቡ የይሁዳ ወንጌል መገኘቱን ሰምተው ይሆን? የመልዕከቱን ሐሰተኝነት እንዲያውም ከቅዱሳት መጻፍት ተራ ሊታሰብ የሚችል ቁምነገር እንደሌለው በመመልከት ከቀኖና መጻሕፍት ውጭ ሆነው ከተወገዱት መሓል እንዲሆን በቅዱሳን አባቶች የተወሰነበት የይሁዳ ወንጌል አርቀው ቢቀብሩትም ቀን ጠብቆ ለመገኘት በመብቃቱ የብዙዎችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል። የመጽሐፉን ብዙ ዘመን ማስቆጠርና ቀዳሚ ከነበሩት ወንጌላት ተርታ እንደነበረ በማየት ሃሳቡ ምንም ከቀኖና መጻሀፍት መልዕክት ጋር የሚጋጭ ቢሆንም የሚንከባከቡትና የሚያሽሞነሙኑት ኣላጣም። በዚህ ረገድ በጥንታዊ ጽሁፎች ላይ ምርምር በማድረግ ረገድ ስም የወጣላቸው አንጋፋ ምሁራን ሳይንቲስቶች ሳይቀሩ ይህንን ወንጌል እሹሩሩ ሲሉት ይስተዋላሉ፡፡ ይሁዳን አንደ ጀግና ደግሞም የአምላኩን ሃሳብ በሚገባ አንደፈጸመ ብሎም የተጣለበትን ጌታውን አሳልፎ የመስጠት ተልዕኮውን በሚገባ እንደተወጣ ሃቀኛ አገልጋይ አድርጎ የሚያወሳው ይህ የሐሰት ወንጌል፤ ብዙዎችን “ነገሩ እውነት ይሆንን” ብለው እንዲጠይቁ ምክንያት እየፈጠረላቸው ነው። በጥቅማ ጥቅም ተደልሎ ጌታውን አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ መሆኑ ቀርቶ የሚያወድሰውና እንደ ጀግና የሚቆጥረው ወንጌል በስሙ     ተጽፎ መገኘቱ እውን የይሁዳን ሀጢአት ያቀልለት ይሆን?

Saturday, December 22, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርክ ምርጫ ህጉ እንዲጸድቅ ሲገፋ ከርሞ እንደሚፈልገው ሳይሆን በመቅረቱ አገር ይያዝልኝ እያለ ነው

የማህበረ ቅዱሳንና የአባ ሳሙኤል ፍቅር አደጋ ላይ ወድቋል
የራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ላይ ታች ሲል፣ የነበረውና የምርጫ ህጉ የእርሱን ምራጮች እንዲያስቀምጥልት በሚያስችለው አኳኋን ከጀርባ ሆኖ በቀረጻው ዋና ተዋናይ የነበረውና 5 ገጽ አስተያየት ለጳጳሳት ሲበትን የሰነበተው ማህበረ ቅዱሳን፣ የምርጫ ህጉ እርሱ ባሰበው መንገድ ስላልሄደለትና ብዙ ማሻሻያዎች በመደረጋቸው ምክንያት እቅዱ ሁሉ መክሸፉን ተከትሎ ከልቡ የማይፈልገውን «እርቅ» አጀንዳው አድርጎ እየተንቀሳቀሰና ህዝቡንም ለጦርነት ተነስ እያለ በመቀስቀስ ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡ ይህ የታወቀው  በደጀሰላም እና አንድ አድርገን ድረገጾቹ ላይ በተከታታይ ባወጣቸው ዘገባዎቹ ላይ ነው፡፡ እነዚህ ድረገጾች የምርጫ ህጉ ሲረቀቅና ውይይትም እየተደረገበት ሳለ ስለ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ሲጽፉና ሲያበረታቱ እንዳልነበር አሁን ያን ሁሉ ወደጎን ብለው በመጀመሪያ እርቅ ይውረድ አሊያ አመፅ እናስነሳለን እያሉ ህዝቡን እየቀሰቀሱ ነው፡፡ ድረገጾቹ  ካስተላለፉት ቅስቀሳ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

Friday, December 21, 2012

ቤተ ክርስቲያኒቱ የወንበዴዎች ዋሻ፣ ንስሐ የማይገቡ ሌቦች መሸሺያ ሆናለች!!

Read in PDF  (ምንጭ፦ ደጀ ብርሃን http://dejebirhan.blogspot.com)
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሰይጣን እንደ ስንዴ  ሊያበጥራት እግዚአብሔርን የለመነ ይመስላል። ልክ የክርስቶስን ደቀ መዛሙርት በጭንቅ ይፈትናቸው ዘንድ እንደለመነው ማለት ነው።

 “ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ” ሉቃ 22  እንዳለው።

ከዚህ ፈተና ቤተ ክርስቲያኒቱ ትወጣ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጸልይ ኤልያሳዊ ማንነት  ያለው አንድም ሰው ጠፍቷል። ገዳማቱን የዐመጻ ሰዎች ሞልተውበታል። ዋልድባን በመሳሰሉ ትላልቅ ገዳማት ሳይቀር ቀጣፊዎች እርስ በእርስ በመነቃቀፍና  የሀሰት ስም በመለጣጠፍ፣ ስለሃይማኖት ልዩነት በማውራትና በማስወራት የሰይጣንን አገልግሎት በተገቢው እየፈጸሙ መገኘታቸው  በጸሎታቸው እንኳን ለዓለሙ ሊተርፉ የራሳቸውን ይዞታ ከስኳር ልማት ለማስጠበቅ የማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ የተቃውሞ ሰልፍ አስፈልጓቸዋል። አብዛኛዎቹ ገዳማትም የመርበብተ ሰሎሞን፣ የመድፍነ ጸር፣ የዐቃቤ ርእስና የገድላ ገድል መፈልፈያዎች ከመሆን አልፈው የሀገሪቱን ችግር ማቃለል የሚችል የጸሎት መልስ የሚገኝባቸው ናቸው ብሎ መጠበቁ ከቀረ ዓመታት አልፈዋል። ደብረ ሊባኖስን ያየ ዓለም እንዴት ሰነበትሽ? ማለቱ እንደማይቀር  ጥርጥር የለንም።  ያላየም ሄዶ በማየት እውነታውን ሊያረጋግጥ ይችላል።

Wednesday, December 19, 2012

አባ ሳሙኤል ቀጣዩ ፓትርያርክ እኔ ነኝ በማለት እያወሩና እያስወሩ ነው

ቀጣዩ ፓትርያርክ ማን ይሆናል? የሚለው ጥያቄ በመላምትና በግምት ደረጃ አቡነ እከሌ ናቸው አይደለም አቡነ እከሌ ናቸው እየተባለ መወራት ከጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ መካከል ሁሉም የየራሱን ፓትርያርክ ለማስቀመጥ እየተንቀሳቀሰ መሆኑም ይወራል፡፡ የቤተክርስቲያኗን አስተዳደር የመቆጣጠር ህልም ያለውና ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ ሰፊ እድል እንዳገኘ ቆጥሮ እንዳሻው እየሆነ ያለው ማህበረ ቅዱሳንም ይፋ ባያወጣም የራሱን ጳጳስ አቡነ እከሌ ካልሆኑ አቡነ እከሌ በሚል በአማራጭ ደረጃ ማስቀመጡም እንደዚሁ ከሚናፈሱት ወሬዎች መካከል ይገኛል፡፡ ማህበሩ ካጫቸው ጳጳሳት መካከል አባ ሳሙኤል አንዱ መሆናቸው አቡነ ጳውሎስ በሕይወት እያሉ በስፋት ሲወራ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ ማህበሩም ይሁን አባ ሳሙኤል ራሳቸውን ተተኪው ፓትርያርክ አድርገው የመመልከት ነገር ነበራቸው፡፡ የማህበረ ቅዱሳን እጅ ያለባቸው የግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ይህን በስፋት ሲያራግቡ ነበር፡፡ በአቡነ ጳውሎስ ጊዜ እንኳን የአቡነ ጳውሎስን ፎቶ ከአባ ሳሙኤል ፎቶ ጋር በማውጣት ሁለቱን ተገዳዳሪዎች አድርጎ የማቅረብ ነገር ነበር፡፡ ከዚህም ሲያልፍ አባ ሳሙኤልን «ብፁዕ» ከሚለው የሹመት ስም አልፎ ፓትርያርኩ በሚጠሩበት «ቅዱስ» የሚለውን ማእረግ ሰተው የጻፉ ጋዜጦችና መጽሔቶች ነበሩ፡፡

Monday, December 17, 2012

በክርስቶስ ላይ አታመንዝሩ

 እዚህ ስዕል ላይ በተጻፈው ጽሑፍ ኦርቶዶክሳውያን ይስማማሉ ብዬ አላምንም፡፡ ይህን ጽሁፍም በስእሉ ላይ የጻፉ ሰዎች ኦርቶዶክሳውያን ናቸው ማለት ይከብዳል፡፡ በጽሑፉ የሚስማሙ ካሉ ግን አመንዝራዎች ናቸው፡፡ በክርስቶስ ላይ ያመነዘሩ ስለሆኑም ክርስቲያንም ተብለው ሊጠሩ አይገባም፡፡ ስእሉ ከፌስ ቡክ ላይ የወረደ ነው፡፡
ማመንዘር ሚስትን/ባልን ትቶ የሌላውን ሚስት/ባል መመኘትና ዝሙት መፈጸም ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ይህን ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ የሚፈጸመውን መንፈሳዊ ምንዝርና እዳስሳለሁ፡፡ በቅድሚያ ቃሉ ምን ይላል?

Saturday, December 15, 2012

4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ያለፈቃዳቸውና ሳይታመሙ ከስልጣን እንዲወርዱ እንደተደረጉ የሚጠቁሙ ሰነዶች

ደብዳቤዎቹ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ያለፈቃዳቸው፣ የጤና ችግርም ሳይኖርባቸው ከመንበራቸው እንዲወርዱ መደረጋቸውን ያሳያሉ። በተለይ ቅዱስነታቸው የጻፉት ደብዳቤ ይህንን ግልጽ ያደርገዋል። በወቅቱ የነበረውን የመንግስት ተጽዕኖም በጊዜው ከነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ታምራት ላይኔ የተጻፈው በጀትን የማገድ ደብዳቤ ግልጽ ያደርገዋል።


  • በሰነዶች ላይ ኢሳት ያቀረበውን ሰፋ ያለ ዘገባም ያዳምጡThursday, December 13, 2012

በጥቂት ግለሰቦች አምባገነንነት ቤተ ክህነት ከኢየሩሳሌም ድርጅትና ከሌሎች አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ መግባቱ ተሰማ

ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኗ ከቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሚ እንዳትሆንና እርሱ ተጠቃሚ የሚሆንበትን  ስራ እየሰራ ነው
ቤተ ክህነቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ፓትርያርክ ተክቶ ቤተክርስቲያኗን የሚመራውን አባት ለማስቀመጥ ከፊት ትልቅ የቤት ስራ ተደቅኖበት ባለበትና በጳጳሳት መካከል ውዝግቡ ባየለበት በዚህ ወቅት፣ የቤተክርስቲያኗን ገንዘብና ሀብት በማባከን ሥራ የተጠመዱ አንዳንድ ጥቅመኞች የግል ቢዝነሳቸውን በቤተክርስቲያኗ ሀብትና ንብረት ላይ እየሰሩ ሀብት ለማጋበስ እየተሯሯጡ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ከገዳማት መምሪያ የተነሳውና የውጪ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ ሆኖ ቢመደብም የመምሪያው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ አልቀበልም ብለውት ተንሳፎ የሚገኘው ሰለሞን ቶልቻ ሲሆን ቤተክህነት ከኢየሩሳሌም ድርጅትና ከሌሎችም አስጎብኚ ድርጅቶች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ እንዲገባ ምክንያቱ ሰለሞን ተቀባይነት ባላገኘውና በሌለው ስልጣን የውጭ ግንኙነት መምሪያ ስራ አስኪያጅ ነኝ በሚል ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጠው መግለጫ ነው ተብሏል፡፡

Wednesday, December 12, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ስውር ብሎጎች በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈቱ

Read in PDF (ግሩም ተግሳጽ፦ ጊዜ ወስደው ሙሉውን እንዲያነቡ እንጋብዛለን)
ብፁዕ አባታችን ከማህበረ ቅዱሳን ስለወንጌል በደረሰብዎ ተቃውሞ እንኳን ደስ አለዎ እንላለን
«ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ። ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።» ማቴዎስ 5፥11-12

ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ። 1ጴጥሮስ 4፥14

«በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቶአችኋልና፤ ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም፤ በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት፥ ያው መጋደል ደርሶባችኋልና።» ፊልጵስዩስ 1፥28-30

አንዳንድ ጳጳሳት ስማቸው እየተነሳ ያለው ለጵጵስና በማይገባና በሚያሳፍር ተግባር ላይ ተገኝተው ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚደርስባቸው ነቀፌታ በእግዚአብሔር ዘንድ ወደውርደት የሚመራ እንጂ ወደክብር የሚያመጣ እንዳልሆነ ቃሉ ምስክር ነው፡፡ ብጹዕ አቡነ ማርቆስ ግን ስማቸው በማህበረ ቅዱሳን ብሎጎች እየጠፋ ያለው በወንጌል ምክንያት ነው፡፡ ይህም በወንጌል አይን ሲታይ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ለብፁእነታቸውም ታላቅ ክብር ነው፡፡

Tuesday, December 11, 2012

አባ ሳሙኤልና መሰሎቻቸው እንዲሁም ማህበረ ቅዱሳን «በልካቸው ያሰፉት» የፓትርያርክ ምርጫ ህገ ደንብ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው፤ ጳጳሳት እርስበርስ እንዳይከፋፈሉ አስግቷል

Read in PDF

በዘንድሮው የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እስከ ህዳር 30 የፓትርያርክ ምርጫ ህገ ደንብ ረቂቁ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ በተወሰነው መሰረት ሲኖዶሱ በረቂቅ ህገ ደንቡ ላይ እየተወያየ ይገኛል፡፡  በውይይቱ ላይ በውጪ ሀገር የሚገኙ የሲኖዶሱ አባላት ጳጳሳትን «መምጣት አያስፈልጋችሁም፤ ያለውን ነገር እናሳውቃችኋለን» በሚል እንዳይገኙ በአባ ህዝቅኤል የተነገራቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህም የሆነው በነአባ ሳሙኤል ልክ የተሰፋው ህገ ደንብ ሊገጥመው የሚችለውን ተቃውሞ ለመቀነስ ታስቦ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡ ይሁን እንጂ አገር ውስጥ ባሉት ጳጳሳትም ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ቀድሞ አቡነ ጳውሎስን ለመጣል አንድ የሆኑ የመሰሉት ጳጳሳት ጭምር በአቋም ተለያይተው ታይተዋል ተብሏል፡፡

15 አንቀጾች ባሉት 9 ገጽ ህገ ደንብ ላይ በአንቀጽ 5 የሰፈሩት አንዳንድ ነጥቦች ለአለመግባባቱ መንስኤ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ አንቀጽ 5 እንዲህ ይላል፦
«ለፓትርያርክነት የሚመረጡ ዕጩዎች መመዘኛ
ለፓትርያርክነት የሚቀርብ እጩ ተወዳዳሪ የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለበት፡፡
1.     ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ

በዳላስ ቴክሳስ ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላምና አንድነት ጉባኤ የጋራ መግለጫ

Read in PDF

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የጉባኤው ዋና አጀንዳ፦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ቅድስት አገራቸው ኢትዮጵያ ስለሚመለሱበት ጉዳይ

በመግለጫው መሰረት ቅዱስነታቸው ወደ አገራቸው ይመለሱ በሚለው ከሁለቱም ወገን በመጡ ልዑካን ዘንድ ተቀባይነት አገኝቷል።  ቅዱስነታቸው እንዴት ወይም በምን ሁኔታ ይመለሱ በሚለው ነጥብ ላይ ግን ስምምነት አልነበረም።

የኢትዮጵያ ልኡካን አቋም፦ ቅዱስነታቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶላቸው፣ ክብራቸውና ደረጃቸው ተጠብቆ በመረጡት ቦታ ይኑሩ የሚል ነው።

የሰሜን አሜሪካ ልኡካን አቋም፦ ቅዱስነታቸው ከነሙሉ ሥልጣናቸው ወደ መንበራቸው ሊመለሱ ይገባል የሚል ነው።

በነዚህ ሁለት የተለያዩ አቋሞች ላይ ስምምነት ስላልተደረሰ አራተኛ ጉባኤ በሚመጣው ጥር 16-18 2005 / (January 24-26,2013) በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ እንዲካሄድ ወስነዋል።  እስከ  አራተኛው  ጉባኤ ድረስ  ልኡካኑ የየራሳቸውን ሲኖዶስ አባላት (ምልዓተ ጉባኤ)  ሲያግባቡና ሲያሳምኑ ይቆያሉ። 

የሁላችንም ጉጉት የአንድነቱ ድርድር ጫፍ ላይ እንዲደርስ ነበር፤ ሆኖም ግን የአራተኛውም ጉባኤም ቅርብ ስለሆነ በትዕግስት እንጠብቃለን። የቤተ ክርስቲያን አንድነት የመላው ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄ መሆኑን ተረድተው አባቶች አንድነትን ያመጣሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
 

Monday, December 10, 2012

በአቡነ ሚካኤል ልጅ የውርስ ጉዳይ የተደረገውን ክርክር ሲኖዶሱ የከፍተኛ ፍርድ ቤትን የመጨረሻ የውሳኔ ቀን ሳይጠብቅ በአቋራጭ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰደው

Read in PDF

ታላላቅ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን መመልከትና ውሳኔዎችን ማሳለፍ የሚጠበቅበትና በአሁኑ ወቅት ጥቂቶች የሚያሽከረክሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ከደረጃው እጅግ ዝቅ ብሎ እንደሌሎቹ ጳጳሳት ሊሸፈን ያልቻለ የአንድን ጳጳስ ገመና ለመደበቅ ሲል ሃይማኖታዊ ያልሆነና ከግለሰብ መብት ጋር የተያያዘ ጉዳይን የሃይማኖት ጉዳይ አስመስሎ ሥልጣኑን አለአግባብ በመጠቀም የግለሰብ መብትን በመጋፋት ስራው መቀጠሉ ተሰማ፡፡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልጅነትን ማረጋገጥ ሰብአዊ መብት እንጂ የሀይማኖት ጉዳይ አይደለም በማለት የአቡነ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዲወጣ እና የዲኤን ኤ ምርመራ እንዲደረግ ይህ የማይደረግ ከሆነ ደግሞ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈጻሚ ይሁን ብሎ የወሰነው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዳይሆን ሲል ሲኖዶስ ባቋራጭ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሌላ አቤቱታ አቀርቧል፡፡ አቤቱታው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳቀረበው አይነት «ጉዳዩ የሀይማኖት ጉዳይ ነውና ፍርድ ቤት ሊመለከተው አይገባም» የሚል ነው፡፡

Sunday, December 9, 2012

የአንድነት ጉዟችንን ጀምረን ከግማሽ በላይ ተጉዘናል - ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ

ዛሬ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከሁለቱም ሲኖዶሶች የመጡ አባቶች በአንድነት  ተገኝተው የቅዳሴ ስነ ስርዓት አካሂደዋል። ቅዳሴውን በዋናነት የቀደሱት በስደት ያለው ሲኖዶስ አባል የሆኑት ብጹዕ አቡነ ኤልያስ ሲሆኑ በቅዱስ ቁርባን ሰዓት ላይ ደግሞ በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ያሉት ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ ትምህርት አስተምረዋል።  ከዚያም በስደት ያለው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ትምህርትና ቃለ ምዕዳን ሰጥተዋል። ዘማሪ ትዝታው ሊነጋ ሲል ይጨልማል የሚለውን መዝሙር በምዕመናን  ግብዣ የዘመረ ሲሆን ከራሱ ደግሞ የፈራ ይመለስ ከልዓድ ተራራ የሚለውን መዝሙር ዘምሯል። የእርቁን ውጤት በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው የዳላስ ህዝብ ከምን ጊዜውም በበለጠ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኑን አጨናንቆ ነበር።

የዕለቱ ፕሮግራም የተመራው በዲያቆን አንዱዓለም ሲሆን ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ ( በማታው ጉባኤ)  የመላው ዳላስ ምዕመናን በሚገኙበት የእርቅ ድርድሩ ውጤት በመግለጫ መልክ በዳላስ ሚካኤል ይቀርባል።

የብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ የትምህርት ርዕስ «አባት ሆይ እኔ እና አንተ አንድ እንደሆንን እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምንሃለው» የሚለው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸሎት ነበር። በዚህ ርዕስ ስለ አንድነት ሰፋ ያለና ህዝቡን ያስደሰተ ትምህርት ሰጥተዋል። የብጹዕነታቸው ትምህርት የሚከተሉት የሰላምና የአንድነት ሃሳቦች ነበሩት፦

Saturday, December 8, 2012

ላለመታረቅ የተያዘ የእርቅ ስብሰባ

በሁለት ሲኖዶሶች አየተመራች ያለችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ወደአንድነት ለማምጣት የዕርቁ ስብሰባ በዳላስ ተካሂዷል፡፡ ከአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ በሁለቱም በኩል የወጡት መግለጫዎች የሚያሳዩት የእርቁ ሂደት አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን እያሳዩ ነው፡፡ ለእርቁ መሳካት አንደኛው ወገን ለቤተክርስቲያን አንድነት ሲል የግድ መሸነፍ እንዳለበት ይታመናል፡፡ ለመሸነፍ ፈቃደኛ የሆነ ወገን ግን አለ ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ በዚህ ረገድ በአገር ቤት ያለው ሲኖዶስ ከፍተኛ ሀላፊነት ያለበት ይመስለናል፡፡ በውጪ ያለው ሲኖዶስም የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት፡፡

Thursday, December 6, 2012

ከፕሬዚዳንት ግርማ ደብዳቤ ምን እንማራለን?

በትላንትናው ዕለት (Dec 5,2012) እንደዘገብንላችሁ ፕሬዝዳንት ግርማ ተስፋ ሰጭ የሆነና የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የማይፈልጉ ግለሰቦችን ወይንም ቡድኖችን ምክንያት የሚያሳጣ ደብዳቤ ጽፈው ነበር። በአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ እንደተደመጠው ፕሬዝዳንት ግርማ አዲስ አበባ ካለው ቤተ ክህነት በደረሰባቸው ተቃውሞ የጻፉት ደብዳቤ ችግር እንደፈጠረ በማብራራት እንዲስተባበልላቸው አሳስበዋል። ከፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ እንዲሁም በ VOAከሰጡት ማስተካከያ ማብራርያ ልናስብባቸው የሚገቡና የምንማራቸው 2 ነገሮች፦

1ኛ) በዳላስ የሚካሄደው ድርድር ውጤት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ ቢሆን መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ፦
ፕሬዝዳንት ግርማ የጻፉት ደብዳቤ መንፈሱ መንግስት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ የገባ ስለሚያስመስለው ተቃውሞ የደረሰበት ይመስላል። ፕሬዝዳንቱም ከቤተ ክህነት የመጣውን ወቀሳ ስላመኑበት በቅንነት የጻፉትን ደብዳቤ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ይህ ማለት ግን የኢትዮጵያ መንግስት አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ አይፈቅድም የሚል አንድምታ አይሰጥም። የሲኖዶሶቹ ውሳኔ የአቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ ከሆነ በስደት ያሉትን የሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ አቡነ መልከጼዴቅን ጨምሮ የሲኖዶስ አባላትና ካህናት ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ወይንም መንበርነቱ አዲስ አበባ ከሚሆነው የአንድነት ሲኖዶስ ጋር ያለ ተጽዕኖ እንዲሰሩ መንግስት ሊፈቅድ ይገባል። በዚህም ውስጥ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ችግር ይሆናል ብለን አናምንም የፕሬዚዳንቱም ደብዳቤ የሚጠቁመውም ይህንኑ ነው። 

2ኛ) አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ የአቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስ ብዙም እንደማይደግፍ፦ 
 በፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤ ከቤተ ክህነት የደረሰው ፈጣንና ጠንካራ ተቃውሞ  የሚያመለክተው ቤተ ክህነት የመንግስትን ጣልቃ ገብነት አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን የአቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስን ያለመፈለግም ጨምሮ ይመስላል። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ባለፈው የግንቦቱ ስብሰባ እንደወሰነው 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም ቅድመ ሁኔታዎችን ማስተካከል እንደሚጀምር ለህዝብ ይፋ አድርጎ ነበር።  እንደሚታወቀው ይህ ለኦርቶዶክሳዊው ምዕመን እንቆቅልሽ ነው። ቤተ ክርስቲያናችን ለ 20ዓመታት በ ሁለት ሲኖዶስ ስተመራ የቆየችው እኮ የቀድሞው ፓትርያርክ በህይወት እያሉ ለምን ሌላ ፓትርያርክ ተሾመ በሚል የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ነበር። እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አንደኛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድነት ለመመለስ ግልጽና ትክክል የሆነው እርምጃ (most logical approach) በይህወት ያሉትን ፓትርያርክ ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን መሪ ማድረግ ነው። ይሄ ለምን ድርድር እንደሚያስፈልገውና ከባድ እንደሆነ ለህዝብ ግልጽ አይደለም።

የዚህች ቤተ ክርስቲያን አንድ መሆን ለቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለሀገራችንም ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚኖረው መንግስትም ሆነ ማንኛውም ወገን የራስን ጥቅም፣ ስልጣን  ወይንም ሌላ ነገር ወደ ጎን አድርጎ የአንድነቱን ሂደት መደገፍ ይኖርበታል።

Wednesday, December 5, 2012

አስደናቂ ሰበር ዜና፦ የኢትዮጵያ መንግስት የቤተ ክርስቲያናችንን የእርቅ ሂደት እንደሚደግፍ በደብዳቤ አረጋገጠ

በቀጥታ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በተላከ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት የቅዱስነታችውን ወደ መንበራቸው መመለስ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ አስታወቀ።  ደብዳቤው እንደሚገልጸው ቤተ ክርስቲያንን ወደ አድነት ለማምጣት የአገር ውስጥ ሽማግሌዎችን ሃሳብ ተቀብሎ ይህንን እንደወሰነ ይናገራል። ይህ መልካም ዜና አሁን በዳላስ እየተካሄደ ያለውን የእርቅ ውይይት መሰረታዊ በሆነ መልኩ ይቀይረዋል ተብሎ ይገመታል። 

ሙሉውን ደብዳቤ  ከዚህ በታች ማንበብ ይችላሉ (ደብዳቤው ላይ ቢጫኑ ለማንበብ ይቀልዎታል)

እግዚአብሔር ሀገራችንንም ቤተ ክርስቲያናችንንም ይጠብቅልን።  ለመሪዎቻችንም አስተዋይ ልቦና ስለሰጠልን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።  ለቤተ ክርስቲያን መሪዎቻችንም እንዲሁ ያድርግልን።


በሁለቱ ሲኖዶሶች ዛሬ በአሜሪካ ዳላስ ከተማ የተጀመረው የእርቅ ሂደት- አበረታች ምልክቶች እየታዩ ነው

የዳላስ ህዝብ ለድርድሩ ለመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከፍተኛ አቀባበል አደረገ። በዳላስ የሚገኙ የ 6ቱም ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት ካህናት እና ምዕመናን በአቀባበሉ ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከሁለቱ ሲኖዶሶች የመጡ አባቶች በጋራ ሆነው ጸሎት አድርገዋል። የጸሎቱና የቡራኬው ስነ ስርዓት የተመራው በስደተኛው ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና አንጋፋው ሊቅ ብጹዕ አቡነ መልከጼዴቅ ነበር።
የእርቅ ውይይቱ ከዳላስ ሚካኤል ፈቀቅ ብሎ በሚገኝ ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን የዳላስ ምዕመናንም ገንዘብ ከማዋጣት ጀምሮ ከፍተኛ ድጋፍ እየሰጡ ይገኛሉ። የዕርቁን ሂደት በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በታላቅ ጉጉት እየተከታተሉት ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ መንግስትም የእርቁን ሂደት እንደሚደግፍና ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስም ወደ ሃገራቸው ገብተው መንበራቸውን እንዲረከቡ ፍላጎት እንዳለው ከአንዳንድ የመንግስት ምንጮች እየተገለጹ ነው። ዝርዝሩን እየተከታተልን  ከተጨባጭ መረጃዎች ጋር እናቀርባለን።
ለድርድሩ የመጡ አባቶች አንድ በሚያደርጋቸው ነገሮች ላይ ትኩረት በመስጠት ታሪክ እንዲሰሩና አንድ ሆና ለዘመናት የቆየችውን ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን እንዲመልሱላት የመላው ኢትዮጵያዊ ምኞት ነው። እግዚአብሔር በአባቶችና በመሪዎች ልቦና ውስጥ የአንድነትና የፍቅር ዘር በመዝራት መልካም ውጤት ያሰማን እንላለን።  

Tuesday, December 4, 2012

ይድረስ ለጾመኛው ዳንኤል ክብረት

«ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።» (ማቴ. 6፥16-18)

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ዳንኤል ክብረት በድረገጹ ላይ “ወርቅ የማይገዛው አገልግሎት” በሚል ርእስ Monday, November 26, 2012 በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የጻፈው ትችት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈ አየር መንገድ መሆኑ ለማንኛችንም ግልጽ ነው። ከፍተኛ ዝናን ማትረፍ የቻለውም በሚሰጠው አገልግሎት ነው እንጂ በሌላ አይደለም። እንዲህ ሲባል አየር መንገዱ ፍጹም ነው አንዳችም እንከን የለበትም ለማለት ፈልጌ አይደለም። ፍጹም ሊሆን አይችልምና፡፡ ከችግሮቹ ይልቅ ስኬቶቹ ስለበለጡ ግን አየር መንገዱ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ፣ ዝነኛ፣ አትራፊ፣ ስኬታማና ተሸላሚ ሆኖ ቀጥሏል። የዚህ ጽሑፍ ዋና ትኩረት በቀጥታ አየር መንገዱ አይደለም። ዳንኤል ክብረት በአየር መንገዱ ላይ ያቀረበውና “ጾመኛ ነኝ እወቁልኝ” አይነት በእኔ እምነት በግብዝነት የተሞላ አስተያየቱ ነው።

Saturday, December 1, 2012

ያመነች ብፅእት ናት

«ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅእት ናት» ሉቃ 1፥45
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማኝ ከሚባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ ታላቋ ናት። የድንግል ማርያም ታላቅነት እጅግ ከምናስበው በላይ ነው። አካላዊ እና መለኮታዊ ቃልን በማህጸኗ ተሸክማ ወልዳለች፤ ከጽንሰቱ ጀምራ በልደቱ፣ በእድገቱ፣ በአገልግሎቱ፣ከዚያም በሞቱ፤ ሞቶ ካረገ በኋላም እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ ጌታን ያገለገለች ታላቅ እናት ናት። መጽሐፍ «ሌላውም በመልካም መሬት ወደቀ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ» ማቴ 13፥8 ይላል። ይህ ቃል በጌታ መንግሥት የሥራ ልዩነት እንዳለ እና ክብሩም በዚያው ልክ ክፍ እና ዝቅ የሚል መሆኑን የሚያስረዳ ነው። ከዋክብት ጸሐይና ጨረቃ በክብር እንደሚለያዩ ቅዱስ ጳውሎስ ጽፏል 1ቆሮ 15፥40-41። በዚህ መሠረት የድንግል ማርያም ፍሬ ቢታሰብ ከመቶ በላይ ነው ምክንያቱም እግዚአብሔርን እንደ ድንግል ማርያም ያመነ እና ያገለገለ የለም ማለት ይቻላል።
 እኛ ጌታን በማገልገላችን ደስተኞች ነን፤ ዋጋም እንቀበላለን። ዛሬ ብንጎዳም በሰማይ ክብሩ ይቆየናል ብለን እናምናለን። ይህን ስናስብ ትልቅ ደስታ ይሰማናል። ሐዋርያው ጳውሎስ «ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን ያሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ» ብሏል። ሮሜ 8፥18። እንግዲህ ለኛም ገና የሚገለጥ ክብር አለ። በዚህ ትንሽ እና እንከን የበዛበት አገልግሎታችን ይህን ያህል ክብር ከጠበቅን የድንግል ማርያም ክብርማ ምን ያህል ይሆን?

Friday, November 30, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ ደጀሰላም የወሬ እጥረት ያጋጠመው ይመስላል

ክፍተቱ የተፈጠረው ከቤተክህነት ወሬዎችን የሚለቃቅመውና የሚያቀብለው ማንያዘዋል ግብጽ ስለሚገኝ ነው

ማኅበረ ቅዱሳን የእኔ አይደለም እያለ የሚያስተባብለውና የእርሱ መሆኑ ግን የሚታወቀው «ደጀሰላም» የወሬ እጥረት ያጋጠመው መሆኑ እየታየ ነው፡፡ ራሱም ኅዳር 18/2005 ፖስት ባደረገው ጽሑፍ  «በየአካባቢያቸው ያለውን የቤተ ክርስቲያንን ሁኔታ በመከታተልሪፖርትየሚልኩልን ፈቃደኛ ደጀ ሰላማውያንአለንእንዲሉን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን» ብሏል፡፡ የወሬ እጥረቱ የተፈጠረው እንደእርጎ እንትን በየቦታው ጥልቅ የሚለውና የደጀሰላም ዋና ወሬ አቀባይ የሆነው ማንያዘዋል ለግብጹ ፓትርያርክ ባኣለ ሲመት ከጳጳሳት ጋር ተለጣፊ ሆኖ በማኅበሩ ወጪ ወደግብጽ ስለሄደና እስካሁን ድረስ በአገር ውስጥ ስለሌለ ነው ተብሏል፡፡ ማንያዘዋል ለአንድ ወር ቆይታ በማኅበሩ 32 ሺ ብር ወጪ ተደርጎለት የሄደ መሆኑ ቢታወቅም እርሱ ግን የከፈለልኝ የቲዎሎጂ ማኅበሩ በማለት ያስወራ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡  ማኅበሩ በገጠር አብያተ ክርስቲያናትናት በገዳማት ስም ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር የሚሰበስበውን ገንዘብ እንዲህ ባለመንገድ እንደሚያባክን ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

Thursday, November 29, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ «ብላክ ማርኬት» እንዳለው ተሰማ

ድብቅ አላማ ይዞ በሃይማኖት ሽፋን የሚንቀሳቀሰው ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ቢሮ በድብቅ መክፈቱን ምንጮቻችን ገለጹ፡፡ እንደ ምንጮቻችን ከሆነ ማኅበሩ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የሚጠቀምበት ቢሮ በስም «የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር» እየተባለ የሚጠራውና የቲዎሎጂ ምሩቃን በአባልነት የሌሉበትና ማንያዘዋልን ጨምሮ ጥቂት የማቅ «የቲዎሎጂ ምሩቃን» አባላት የሚገናኙበት ቢሮ ነው ብለዋል፡፡ ቢሮው ቀድሞ ከነበረበት ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ቢሮ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገውም የውጭ ምንዛሬውን ጨምሮ ሌሎች ድብቅ ስራዎችን ለመስራትና ለመጠቀም አስቦ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡ ቢሮው የማቅ ሌላው ቢሮ ነው እያሉም ነው፡፡ ማኅበሩ የዶላር ዩሮና ፓውንድ ምንዛሬዎችን የሚያካሂደው በድብቅ ሲሆን ከውጪ አገር ዶላር ይዘው የሚመጡና ዶላር የተላከላቸው የማኅበሩ አባላትና አንዳንድ ጳጳሳትም ዶላር ዩሮና ፓውንድ በዚሁ ቢሮ እንዲመነዝሩ እንደሚደረግ የደረሰን መረጃ ያመለከታል፡፡ መንግስት የዶላር እጥረት አጋጥሞኛል በሚልበት በዚህ ወቅት ማቅ እንዲህ እያደረገ መሆኑ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል፡፡

Monday, November 26, 2012

«አለው ነገር» የተሰኘ አዲስ ኦርቶዶክሳዊ የዝማሬ ሲዲ በዘማርያን ትዝታው፣ ምርትነሽና ዘርፌ

‘ማልደራደርበት‘ ማልቀብረው እውነት
አንገት ‘ማያስደፋኝ የማላፍርበት
ኢየሱስ የሚለው ስም እስትንፋሴ ነው
እውነቱ ይሄው ነው


አንዱን መዝሙር ለቅምሻ ጋብዘናል- ሌላውን ገዝተው ያዳምጡ

እነዚህ ስንኞች የተወሰዱት ከአንድ የግጥም መድበል ውስጥ እንዳይመስላችሁ፤ ዲ/ን ትዝታው ሳሙኤል ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በጋራ ከሳተሙትና «አለው ነገር» የሚል ርእስ ከተሰጠው የዝማሬ ሲዲ ላይ የተወሰደ ነው፡፡ እውነት ነው ኢየሱስ የሚለው ስም ለእውነተኛ ክርስቲያን እስትንፋስ ነው፡፡ አንገት የማያስደፋና የማያሳፍር የማይቀበርና ለድርድር የማይቀርብ ስም ነው፡፡ እውነትም ኢየሱስ በሚለው ስም ላይ ድርድር የለም!!!

Sunday, November 25, 2012

መዳንም በሌላ በማንም የለም

  • ዛሬ በኢየሱስ ስም መስበክ መናፍቅ አሰኝቶ ያስወግዛል
  • ገድለ ተክለ ሃይማኖት የተክለ ሃይማኖትን ስም የጠራ ይድናል ይላል
 «መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የተሰጠን ከሰማይ በታች ሌላ የለም» የሐዋ 12፥4
ይህን ቃል የተናገረው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። የተናገረውም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ነው። ይህን ቃል ለመናገር ያበቃው ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበር። ሰውዬው ለመሥራት ለመሮጥ፣ ለመቅደም፣ ለመታገል የማይችል ምስኪን ሰው ሆኖ በወላጆቹ ላይ ወድቆ የሚኖር ሰው ነበር። ጥዋትና ማታ በቤተ መቅደስ በር ላይ እያመጡ ይጥሉታል፣ ከሕዝብ ምጽዋት እየለመነ የዕለት እንጀራውን ያገኛል። ከዚህ ሕይወት የሚያወጣው ሌላ እድል አያገኝም፣ ተስፋው በሙሉ በሰው ስጦታ ላይ የተመሠረተ ነው። አንድ ቀን በትክክል ቆሜ እራመዳለሁ ብሎ አስቦ አያውቅም፣ የሚያስበው በቀን ምን ያህል ምጽዋት እንደሚያገኝና ኑሮውን እንደሚገፋ ብቻ ነው። በዚህ ሁኔታ ከ40 ዓመት በላይ አሳልፏል።

Wednesday, November 21, 2012

ወደ ፍ/ቤት ሽማግሌ ይላካል አይላክም በሚል «አባ» ሳሙኤልና ጠበቆቻቸው ሳይስማሙ ቀሩ

የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ከወሰነ ወዲህ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገቡትና ነገሩን በሽማግሌ ለመጨረስ እየተንቀሳቀሱ ያሉት «አባ» ሳሙኤል ወደ ፍ/ቤት ይሄዱልኛል ያሏቸውን ሽማግሌዎች ያዘጋጁ ቢሆንም በጠበቆቻቸው በኩል ግን ሀሳቡ ተቀባይነት ሳያገኝና ሽማግሌም ሳይላክ መቅረቱ ተነግሯል፡፡ በጠበቆቹ በኩል የቀረበው ሐሳብ ተገቢነት ያለውና ህጋዊውን መንገድ የተከተለ  ሲሆን፣ «አባ» ሳሙኤልን «እርስዎ ጳጳስ ሆነው የሽምግልና ሕግን እንዴት አያውቁም? ሽምግልና እኮ እየተካሰሱ ባሉት ሁለት ወገኖች መካከል የሚከናወን የእርቅ ሂደት እንጂ ከፍርድ ቤት ጋር አይደለም፡፡ በፍ/ቤት ሕግ እንዲህ አይነት ሽምግልና ተሰምቶም ታይቶም አያውቅም» ብለዋቸዋል ተብሏል፡፡ አክለውም «ሽማግሌ መላክ ካለብንም መላክ የምንችለው የአባ ሚካኤል ልጅ ነኝ ወደሚለው ወደ ዮሐንስ ነው፡፡» ብለዋል፡፡

Monday, November 19, 2012

የግንቦት 15ቱ ውግዘት መነሻ፣ ሂደት፣ ፍጻሜና ቀጣዩ ሲገመገም

ክፍል 7
read in PDF

በልዩ ልዩ ወቅታዊ ጉዳየች ምክንያት ገታ አድርገነው የነበረውን የግንቦት 15ቱን «ውግዘት» የተመለከተ ዘገባችንን ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ከሳቴ ብርሃን በተሰኘው ማህበር ላይ የቀረበው ሌላው «ኑፋቄ» የሚከተለው ነው።


«5ኛ. ‘በአባቶቻችን አፈርን’ በተሰኘው መጽሐፋቸው፦
«ሀ. እንደ ፈጣሪ ያለ ክብርና ምስጋና የሚገባቸው ፍጡራንና የእጅ ስራዎች ያሏት ቤተክርስቲያን ባዕድ አምላኪ ወይም ባለብዙ አማልክት ካልተባለች ምን ልትባል ትችላለች» በማለት ቤተክርስቲያናችንን በመንቀፍ ጽፈዋል፡፡ 2003 ዓ.ም. እትም ገጽ 39»

አሁን ይህ ጠንከር ያለ አስተያየት እንጂ ኑፋቄ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኑፋቄ እኮ በሃይማኖት ትምህርት ላይ ጥርጥር ሲፈጠር የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግን ራስን ለመመልከትና ለማስተካከል የሚረዳ ጠቃሚ ምክር ተደርጎ ነው መወሰድ ያለበት፡፡ የኑፋቄ መመዘኛ ሚዛኑን የጣለ ወይም የጠፋበት የመሰለው የግንቦቱ ሲኖዶስ ውግዘት ያሳለፈባቸው አብዛኞቹ ነጥቦች ከኑፋቄ ቁጥር የሚገቡና የሚያስወግዙ አልነበሩም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲያውም ቤተክርስቲያኗ ተቀብላ ራሷን ልታርምባቸው የሚገቡ ጠቃሚ አስተያየቶችና ምክሮች ናቸው፡፡

Saturday, November 17, 2012

ይድረስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት - አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል

 ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል በቅዱስ ሲኖዶስ የትምህርት ማሰልጠኛ መምሪያ ሃላፊ በቤተ ክርስቲያን አንድነት ዙሪያ ላይ ያተኮረ ደብዳቤ ለብፁዓን አባቶች ጽፈዋል።

አባ ሰረቀ የጻፉትን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

Thursday, November 15, 2012

ሰበር ዜና: የአባ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ እንዳይወጣ ለማድረግ «አባ» ሳሙኤል ወደፍርድ ቤት ሽማግሌ ሊልኩ መሆናቸው ተሰማ

ሰኞ ዕለት ባወጣነው ዘገባ እንደ ገለጽነው የልደታ ምድብ ችሎት ባለፈው አርብ[1] የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድበት ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ እውነት የምትገለጥበት ጊዜ መቅረቡ ያሳሰባቸውና የሚይዙ የሚጨብጡትን አጥተው የሰነበቱት «አባ» ሳሙኤል በዓለም ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ አሰፋሪ ሁኔታ ሲኖዶስ ወስኖ በደብዳቤ የጠየቀውንና ከፍርድ ቤት በኩል ምላሽ ያጣበትን ጉዳይ በሽምግልና ለመጨረስ በማሰብ ዛሬ ኅዳር 6/2005 ዓ.ም ለፍርድ ቤት ሽማግሌ ለመላክ መወሰናቸውንና ለዚሁ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡

Monday, November 12, 2012

የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ እንዲመረመር ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላለፈ

ሲኖዶስ «የአባ ሚካኤል ጉዳይ የሓይማኖት ጉዳይ ነውና ፋይሉ ይዘጋ» ሲል ያቀረበው መቃወሚያ ውድቅ ተደርጓል
ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት የልደታ ምድብ ባስዋለው ችሎት የብፁዕ አቡነ ሚካኤል አስከሬን ተቆፍሮ ውጥቶ የዲኤንኤ ምርመራ እንዲካሄድና ውጤቱ ለህዳር 25/2005 እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ የሟቹ ብፁእ አቡነ ሚካኤል ልጅ የዮሀንስ ሚካኤል የወራሽነት ጉዳይ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ በስር ፍርድ ቤት ዮሐንስ ያቀረበው ማስረጃ የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ካቀረበው መከላከያ ይልቅ አሳማኝ ሆኖ በመገኘቱ ውሳኔ ያገኘና ልጅነቱ የተረጋገጠ መሆኑን ከዚህ ቀደም ዘግበን የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ ተይዞ ክርክሩ ቀጥሎ የነበረ ሲሆን የተለየ ማስረጃ ማቅረብ ያልቻለውና ጉዳዩን አፍኖ ማስቀረት የፈለገው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን ፋይሉን ለማዘጋትና ክሱን እንዲቋረጥ ለማድረግ ያልቆፈረው ድንጋይ አልነበረም ተብሏል፡፡ ለዚህም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ህልፈት በኋላ አለሁ አለሁ ማለታቸውን በእጥፍ የጨመሩትና ሁሉንም ነገር እኔ ካላማሰልኩ የሚሉት «አባ» ሳሙኤል በግል ከመንቀሳቀስ አንስቶ የሲኖዶሱን አባላት አስተባብረው ጉዳዩ የሃይማኖት ነውና ፍ/ቤት ሊመለከተው አይገባም የሚል ደብዳቤ እስከማጻፍ የደረሰ ሴራ ሲጎነጉን ከርመዋል። በልደታ ምድብ ችሎት ጉዳዩን የተመለከተው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በ29/2/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የአባ ሚካኤል አስከሬን ወጥቶ የዲ.ኤን.ኤ ምርመራ እንዲደረግና ውጤቱ ለህዳር 25 እንዲቀርብ ውሳኔ ማስተላለፉ ታውቋል፡፡

Sunday, November 11, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሲኖዶሱን አልሰበስብም ብለው አሰናበቱ

ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውም ታውቋል
አክሱሞች አጣሪውን ቡድን አልተቀበሉም አባ ሰላማም ይልቀቁልን ብለዋል

በአቃቤ መንበር ብፁእ አቡነ ናትናኤልና በG8 የጳጳሳት ቡድን መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ተካሮ ትናንትና አርብ ብፁእ አቡነ ናትናኤል በአቋማቸው ጸንተው በቃኝ ከዚህ በኋላ አልሰበስባችሁም ብለው ከወጡ በኋላ ከሰዓት በኋላ ሳይመለሱ ቀርተዋል። ጳጳሳቱም ተሰብስበው ቢጠብቋቸው ሳይመጡ በመቅረታቸው ስብሰባውን ሳያካሂዱ ተበትነዋል። በቀጣይ የሚሆነው ባይታወቅም በአሁኑ ጊዜ ወደሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸው ተዘግቧል። በአቃቤ መንበርነት ከተሾሙ ወዲህ ወደ ሀገረ ስብከታቸው ሲሄዱም የመጀመሪያቸው ነው ተብሏል።

Friday, November 9, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን “ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ” የተባለ የንግድ ተቋም መመሥረቱ ተሰማ

በቤተክርስቲያን ስም ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ፖለቲካዊ አላማውን ለማሳካት ላለፉት 20 ዓመታት  ሲንቀሳቀስ የቆየው ማኅበረ ቅዱሳን አሁን ካለው በበለጠ ኢኮኖሚያዊ ክንዱን ለማፈርጠምና በገንዘብ ሀይል ያሻውን ለማድረግ በማሰብ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ሆኖ ልዩ ልዩ የንግድ ተቋሞችን ከፍቶ ቀረጥ ሳይከፍል ከሌሎች ቀረጥ ከፋይ ነጋዴዎች ጋር እየተወዳደረ የቆየ ሲሆን፣ የንግድ ሜዳውን ይበልጥ ለማስፋት «ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ» መመስረቱ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው ማኅበሩ ለኅዳር 1/2005 በቸርችል ሆቴል ባዘጋጀው መርሀግብር ላይ አክስዮን የሚገዙ ሰዎች እንዲገኙለት በበተነው የግብዣ ደብዳቤ ላይ ነው።

Thursday, November 8, 2012

አቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቋሚ ሲኖዶስን አልመራም ብለው ከስበሰባ መውጣታቸው ተነገረ

Read in PDF
ሮብ እለት በ28/2/2005 በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በተደረገው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ስብሰባውን በጸሎት እንዲያስጀምሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ «የእኔን አቃቤ መንበርነት መች ተቀበላችሁና ነው በጸሎት የማስጀምረው? ህጉ የሚለው የሚሾምን ሰው ሥራ አስኪያጁ ያቀርባል ፓትርያርኩ ይሾማል ነው። አሁን ግን የምትሾሙ የምትሽሩ እናንተ ሆናችኋል። ታዲያ እኔ የእናንተ አሻንጉሊት ነኝ? ስልጣኔ ምን እንደሆነ በዛሬው እለት እንድታሳውቁኝ እፈልጋለሁ። እስከዚያው ግን ስብሰባውን አልመራም» ብለው ከስብሰባው መውጣታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል። አባ ሳሙኤል «እኛ ላይ እኮ በድረገጽ እየተጻፈብንና ስማችን እየጠፋ ነው» በማለት ሊያግባቧቸው ቢሞክሩም ብፁእነታቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የቋሚ ሲኖዶስን ስልጣን በጎን ቀምቶ ፈላጭ ቆራጭ እኔ ነኝ የሚለው የእነ «አባ» ሳሙኤል ቡድን አላንቀሳቅስ ካላቸውና ስልጣናቸው የሚፈቅድላቸውን ስራ እንዳይሰሩ ካደረጋቸው ወዲህ በአቃቤ መንበሩና በዚህ ቡድን መካከል ውጥረቱ እያየለ መጥቷል። የዛሬውም አቃቤ መንበሩ ከስብሰባው መውጣት ውጥረቱ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ነው ይላሉ ታዛቢዎች።

Monday, November 5, 2012

ዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን የG8 አባላት የሆኑት ሦስቱ የጉድ ሙዳዮች አላሠራ ስላሏቸው የሕግ ያለህ እያሉ መሆናቸው ተሰማ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የሾሟቸው ነገር ግን ተመልሰው ጠላት የሆኗቸውና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በማበር ልዩ ልዩ ሤራዎችን በመጠንሰስና በማሳደም እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ሲያሳዝኗቸው የኖሩት የጉድ ሙዳዮች አባ ሳሙኤል፣ አባ አብርሃም እንዲሁም አባ ሉቃስ፣ ከዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጋር መጋጨታቸው ተሰማ። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዜና ዕረፍት ተከትሎ “እንዳሻን እናደርጋቸዋለን” በሚል የመረጧቸውንና ከሾሟቸው በኋላ» ግን ቋሚ ሲኖዶስ እያለ ዐቃቤ መንበሩን እንረዳለን በሚል ተመሳጥረው የተሰየሙትና 8 አባላት የሚገኙበትና «G8» እየተባሉ የሚጠሩት የጳጳሳት ቡድን፣ እንደፈለጉት ያልሆኑላቸውን አቡነ ናትናኤልን አላሰራ ብለው ሲያስቸግሯቸው እንደቆዩ የገለጹት ምንጮቻችን አሁን ነገሩ ጦዞ ወደአልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመራ ተሰግቷል ይላሉ።

Sunday, November 4, 2012

የቤተ ክርስቲያን አንድነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል

በአገር ቤትም በአሜሪካም በስደት ያሉት ሲኖዶሶች ስብሰባቸውን አድርገው የአቋም መግለጫዎችን አውጥተዋል። ከቤተክርስቲያን አንድነት ጋር ተያይዞ የወጡት መግለጫዎች ሲፈተሹ ግን ቀሪው የቤት ስራ የቤተ ክርስቲያንንን አንድነት ለማምጣት ቀላል እንዳልሆነ መገመት አያስቸግርም። የአዲስ አበባው ሲኖዶስ በአንድ በኩል የዕርቅና የሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ፈቃዱ መሆኑን ቢገልጽም የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበራቸው መመለስን አልተቀበለም። ለስድስተኛ ፓትርያርክ ምርጫም በዝግጅት ላይ ነው።

ለዚህ እየቀረበ ያለው አንዱና  ዋናው ምክንያት አቡነ ጳውሎስን 5ኛ ፓትርያርክ ብለን እንደገና ወደ 4ኛ ፓትርያርክ አንመለስም የሚል ነው። ይሁን እንጂ ፓትርያርክ ሳይሆኑ ወደ አገር ቤት ገብተው በፈለጉት ስፍራ ተከብረው መቀመጥ እንደሚችሉ ሲኖዶሱ ወስኗል። ከዚህ ቀደም ለዕርቁ ሂደት ትልቁ እንቅፋት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩ አንዳንድ ጳጳሳት ከእርሳቸው ህልፈት በኋላ በያዙት አቋም እንቅፋት እየሆኑ ያሉት እነርሱም መሆናቸውን እያንጸባረቁ ነው።

Saturday, November 3, 2012

በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው ሲኖዶስ 34ኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

 በስደት የሚገኘውና በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው 34ኛው የሲኖዶስ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ ተጠናቀቀ።  በጉባኤውም ማጠናቀቂያ ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ያወጣ ሲሆን መግለጫው የሲኖዶሱ ጉባኤ ያተኮረባቸውን አበይት የውይይት ነጥቦች ያንጸባርቃል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ቀልብ ያልሳበው የአዲስ አበባው የጥቅምት ሲኖዶስ ስበሰባ ተጠናቀቀ

እንደ ወትሮው የመገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ያልሳበውና በአብዛኛው ሲኖዶስ ለተባለው የቤተክርስቲያን የበላይ አካል በማይመጥኑና ተራ አጀንዳዎች ሲወያይ የሰነበተው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ ስበሰባ ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 21/2005 ዓ/ም ተጠናቋል። በማኅበረ ቅዱሳን እዝ ስር በመሆን ቅዱስ ፓትርያርኩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመጣል አንድ ሆነው የነበሩት ጳጳሳት ከቅዱስነታቸው ዕረፍት በኋላ ያለ መሪ ፓትርያርክ በዐቃቤ መንበር አንድነታቸውን ጠብቀው መቀጠል እንዳልቻሉ በታየበት በዚህ ስብሰባ ላይ ፓትርያርክ ጳውሎስ የሲኖዶስ ስበሰባ ለሚያገኘው ትኩረት ዋና እንደነበሩ መታዘብ ተችሏል። ሲኖዶሱ በዋናና ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትና ጥንካሬ የሚረዱ፣ ቤተክርስቲያንም በአገራችን ተገቢ ሚናዋን እንድትጫወት የሚያደርጉ አጀንዳዎችን ከመቅረጽና ከመወያየት፣ ጠቃሚ ውሳኔዎችንም ከማሳለፍ ይልቅ በአብዛኛው ተራ በሆኑና ሲኖዶስ ላይ ሳይደርሱ መፈታት ባለባቸው ጥቃቅን አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ አብዛኛውን ጊዜውን ማቃጠሉ፣ የሲኖዶሱ አባላት የሚገኙበትን ደረጃ ያሳየ ክስተት ሆኖ አልፏል።

Friday, November 2, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ውስጡ እየተቃወሰ መሆኑን የሚያሳዩ ምልከቶች እየታዩ ነው

ቤተ ክርስቲያንን ለመቆጣጠርና በራሱ መንገድ ለመምራት እየተንቀሳቀሰ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን ውስጡ በልዩ ልዩ ችግሮች እየታመሰ መሆኑን ምንጮቻችን እየተናገሩ ነው። የማኅበሩ ሁነኛ የሚባሉ አገልጋዮችም በልዩ ልዩ ችግሮች መጠላለፋቸው እየተሰማና እየታየም ነው። ከእነዚህም መካከል፦ ደሴ ቀለብ፣  ኅሩይ ስሜ፣ ኅሩይ ባየ፣ አባይነህ ካሴ፣ ያሉበት ሁኔታ ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው ይላሉ።

እንደምንጮቻችን ከሆነ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል መምህር፣ የማቅ የግእዝ አስተማሪና የሐመር መጽሔት ቋሚ አምደኛ የሆነው ደሴ ቀለብ በአሁኑ ሰዓት የአእምሮ ሕመምተኛ ሆኖ፣ ሥራውን ሳይሠራ ደሞዝ እየተከፈለው እንደሚገኝ ምንጮቻችን ጠቅሰው፣ የዲፓርትመንቱ ኃላፊ የሆነው ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ስለ ግለሰቡ ችግር በተዳጋጋሚ ለማቅ ያሳወቀ ሲሆን፣ ደሴ ሳይሰራ ደሞዝ መከፈሉ ከታወቀ በእርሱ ላይ ችግር እንደሚያስከትልበት እየተናገረ ነው። ደሴ ቀለብ በአሁኑ ወቅት ከስድስት ኪሎ በላይ እንደማይወጣና ከ4 ኪሎ በታች  እንደማይወርድ የታወቀ ሲሆን፣ በማኅበሩ ህንጻ አካባቢ ሲዞር ይውላል ነው የተባለው። ምናልባትም ማኅበሩ በሚታማበት የድግምት አሰራሩ አንዳች ነገር አዙሮበት ይሆናል የሚል ግምት አሳድሯል። ይህን ሰው እግዚአብሔር እንዲፈውሰው ምኞታችን ነው።

Thursday, November 1, 2012

Tuesday, October 30, 2012

የጥቅምት ሲኖዶስ ስብሰባ በአዲስ አበባና በ አሜሪካ እየተካሄደ ነው

ከ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፍትም በኋላ ቤተ ክርስቲያናችን ሁለት የተለያየ የሲኖዶስ ስብሰባ እያካሄደች ነው። በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲወያይ የነበረው የአዲስ አበባው ስብሰባ እየተገባደደ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ ኮሎምበስ ኦሃዮ የሚካሄደው በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሚመራው ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ስብሰባውን ይጀምራል።  በአሜሪካ ስለሚካሄደው ስብሰባ ፍሬ ፍሬ የሆኑ ነገሮችን የምንዘግብ ሲሆን ስለ አዲስ አበባው ስብሰባ ዐውደ ምህረትን ይመልከቱ፦ http://awdemihret.wordpress.com/

በሁለቱም ወገን ያሉ ብፁዓን አባቶች የሚመሩት ህዝብ ፍላጎት አንድነት መሆኑን ተገንዝበው የህዝቡን ምኞትና የልብ ትርታ እንደሚያዳምጡለት ተስፋ እናደርጋለን።


Thursday, October 25, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን «ወደ ግብጽ እንመለስ» የሚል ዘፈን ዛሬም ቀጥሏል

ማኅበሩ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ የሚያጎድፍ ጽሑፍ አወጣ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ 121ኛ ፓትርያርክ ናቸው አለ   
ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን በድንቅና በተአምራት ከግብጽ ምድር ነጻ ካወጣቸው በኋላ በእርሱ ይታመኑ ወይም አይታመኑ እንደሆነ ሊፈትናቸው በምድረ በዳ በኩል ነበር የወሰዳቸው። በምድረ በዳ በገጠማቸው ፈተና ግን በእግር የተለዩአትን ከልባቸው ግን ያላወጧትን ግብጽን እየጠሩ፣ «ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እዚያው ብንሞት ይሻለን ነበር?...» ይሉ እንደነበር ተጽፏል። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1700 ዓመታት ያህል አለአግባብና በግብጾች ሴራ በግብጽ ቤተ ክርስቲያን ስር በመንፈሳዊ ባርነት ስትማቅቅ ኖራለች። ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗ ራሷን እንድትችል ጥረት ሲደረግ እንደቆየ የቤተክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል። የብዙ ዘመናት ጥረቱ ተሳክቶም በ1951 ዓ.ም ቤተክርስቲያኗ ራሷን ችላ የራሷን ፓትርያርክ ሾማለች። ከዚያ በኋላም ኢትዮጵያዊ የሆኑ 5 ፓትርያርኮችን አሳልፋለች። እንዲህ በመሆኑ ምን የሚጎዳው ወይም የሚጠቀመው ነገር እንዳለ ባይታወቅም፣ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን ሕያው ታሪክ በመፋቅ የሌለ ታሪክ በሐመር መጽሔት ላይ አውጥቷል።